Top Banner
78ኛ ዓመት ቁጥር 102 መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር የሴቶችን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሙስናን እንታገል ሙስና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጐዳ ወንጀል ቢሆንም የጉዳቱ መጠን ግን በሴቶች ላይ አመዝኖ እንደሚታይ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። በዓለማችን ከሚገኙ ድሆች ውስጥ ሴቶች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙና የዚህም አንዱ መንስዔ ፍትሐዊ ያልሆነ የፆታ ግንኙነትና ሙስና መሆኑን ጥናቶቹ ይጠቁ ማሉ። ሙስና በተንሰራፋበት ህብረተሰብ ውስጥ የሴቶች የተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ሚና በእጅጉ ይገደባል። በሴቶች ላይ ይደርስ የነበረውን ጭቆና ለማስወገድ የተደረገውን ሁለንተናዊ የትግል እንቅስቃሴና ውጤት ለመዘከርና ሴቶች ከነበረባቸው ጭቆና ተላቀው በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ መስኮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን / ማርች8 ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ108ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ43ኛ ጊዜ የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚል መሪ ቃል ተከብሯል። የሴቶችን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሙስናን ለመታገል በሴቶች እና በመንግሥት በኩል በሚደረገው እንቅስቃሴ ብቻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም። በመሆኑም መላው ህብረተሰብ ሴቶች ከልማትና ዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል ሙስናን ለመዋጋት በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረክት ይገባል። ስልክ፡-01155291 00/011 552 77 74/81 ወይም ነፃ የስልክ መስመር 988 ፋክስ፡- 011-553 69 91 ኢሜይል፡- feacinve @ethionet.et ፖ.ሣ.ቁ፡ 34798/99 የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሞገስ ፀጋዬ በመዲናችን የሚገኙ ወጣቶች ናቸው፤ አፍላ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ሳይመርጡ የቤት ውስጥ ተረፈ ምርቶችን (ቆሻሻ) ከያለበት ይሰበስባሉ። በተለይ የውሃ መያዣ ፕላስቲኮችን ከየቱቦ፣ ወንዞች፣ መንገዶች... ከወዳደቁበት ቦታ አጠረቃቅመው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ ፋብሪካዎች በማቅረብ ሁልጊዜ በሥራ እንደተጠመዱ ናቸው። የመድከምና የመሰልቸት ስሜት አይታይባቸውም። ወጣቶቹ ለራሳቸው ከፈጠሩት የገቢ ማስገኛ ሥራ ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫና ዕድሜ ጠገብ ለሆነችው መዲናችን ውብና ፅዱ አካባቢን ለመፍጠር ይተጋሉ። በዚሁ ሥራ ከተሰማሩትና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱት መካከል ወጣት አስራት በላይ አንዱ ነው። በመጀመሪያ ለአካባቢ ፅዳት መንግሥት እንዳደራጃቸውና ቀስ በቀስ ደግሞ የውሃ መያዣ እና ሌሎች ፕላስቲኮች በመሰብሰብና ለተረካቢ ድርጅቶች በማቅረብ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ይናገራል። የውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ከተለያዩ ቦታዎች ሰብስበው ለድርጅቶች ማቅረብ ከጀመሩ አምስት ወራትን አስቆጥረዋል። ሥራውን ሲጀምሩም በ60 ሺ ብር ካፒታል እንደነበርም ይገልጻል። በአሁኑ ወቅት ልፋታቸው ፍሬ አፍርቶ ካፒታላቸው ከ400 ሺ ብር በላይ መድረሱንም ይናገራል። መንግሥትም የወጣቶችን የሥራ ፈጠራ ለማበረታታት አንድ የሥራን ክቡርነትን በተግባር የሥራን...ወደ 4ኛው ገጽ ዞሯል የህዳሴ ግድቡን በአዲስ የመነቃቃት መንፈስ መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ ሞገስ ፀጋዬ አዲስ አበባ፡- ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በአዲስ የመነቃቃት መንፈስ ድጋፉን በማጠናከር ለውጤት ማብቃት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። የከተማው አንዳንድ ነዋሪዎች በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት የኢትዮጵያውያን የአንድነት መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው እስኪጠናቀቅ መቀጠል አለበት። የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ አቶ መለሰ ጌታቸው እንዳሉት ታላቁ ህዳሴ ግድብ ከህዝቡ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለው ነው፤ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሀብትም ፈሶበታል፤ በመሆኑም ህዝቡ ተጠናቆ ውጤቱን ማየት ይፈልጋል። እስከፍጻሜ የህዳሴ...ወደ 4ኛው ገጽ ዞሯል በኢኮኖሚው ዘርፍ ጥንካሬም ድክመትም ተስተናግዷል ጽጌረዳ ጫንያለው አዲስ አበባ፡- አዲሱ የለውጥ አመራር በአንድ ዓመት ጉዞው በኢኮኖሚው ዙሪያ በርካታ መፍትሔ ሰጪ ሥራዎችን መሥራቱ እና ከዚሁ ጥንካሬው ጋር ተያይዞም ችግሮችን ያስተናገደ እንደነበር የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገለጹ። የማክሮ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ባለሙያው ዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት አዲሱ የለውጥ አመራር በአንድ ዓመት ጉዞው በኢኮኖሚው ዙሪያ በርካታ መፍትሔ ሰጪ ሥራዎችን ሠርቷል። በተለይም የውጭ ምንዛሬ ችግርን ለመፍታት የተሠራው ሥራ በምንዛሬ እጥረት ሊያርፍ የሚችለውን ጫና በብዙ መልኩ ያቃለለና እፎይታን ያስገኘ እንደነበር አስታውሰዋል ። የአገሪቱ የውጭ ብድር ጫናን ለመቀነስ የአዲስአበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ብድር በ10 ዓመት መከፈል እንዳለበት ስምምነት ቢኖርም ይሄንን የዕዳ ክፍያ ወደ 30 ዓመት እንዲራዘም መደረጉም አንዱ የጥንካሬ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። የፋይናንስ ተቋማትን አሁን ባሉበት ቁመና ይዞ መቀጠል ማክሮ ኢኮኖሚውን በእጅጉ እንደሚጎዳው የሚናገሩት ዶክተር ኢዮብ፤ ፖሊሲን በሚመለከት ብቻ የሚሠራ የፋይናንስ ተቋማት ያስፈልጋሉ። ይሁንና በአገር ውስጥ ከሰው ሀብት ጀምሮ ምንም የተሟላ ነገር የላቸውም። ስለሆነም መንግሥት ይህንን ሊያስተካክል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኤክስፖርት ሴክተሩንና በቱሪዝም ላይ መሥራቱን ማጠናከር እንዲሁም የተረጋጋ ኢኮኖሚ መፍጠር ላይ ማተኮር እንደሚገባም መክረዋል። እንደ ዶክተር ኢዮብ ገለጻ፣ለውጡ ላይ የመጣው የኢኮኖሚ ችግር ቀድሞ የተጠራቀመ ነው። በዓመት ውስጥ ደግሞ ወደነበሩበት መመለስ እጅግ ያዳግታል። ለአብነት የውጭ ምንዛሬ ችግር፤ የሥራ አጥ ቁጥር መጨመር፤ የንግድ ሚዛን ጉድለት በስፋት እየጨመሩ የመጡ መሆናቸውን አንስተው ይህም በአንድ ዓመት የተፈጠረ ችግር ብቻ አይደለም። ሆኖም አሁንም የለውጡ ችግሮች ከመሆን የሚያስቀራቸው አይኖርም ብለዋል። «የግል ዘርፉን በማጠናከር ዙሪያ የፖሊሲ ሮድ ማፕ አለመኖሩ እንደ ችግር የሚነሳ ነው» የሚሉት ዶክተር ኢዮብ፤ ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማስተካከል በፍጥነት አለመኬዱ፤ ቁልፍ የሆኑ በኢኮኖሚው...ወደ 4ኛው ገጽ ዞሯል ከመስከረም 1 እስከ መስከረም 30 ምን ምን ክስተቶችን አሳለፍን። * በዚህ ወር ውስጥ የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸው አንዱ ነው። በአገር ውስጥ ገብተው ሠላማዊ ትግል እንዲያደርጉና ለአገራቸው የዲሞክራሲ መጎልበት እንዲሰሩ ተደርጓል። * ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውጭ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ጋር የተወያዩትም በዚሁ የመስከረም ወር ነው። * የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ የተከናወነውም በመስከረም ሲሆን፤ በዚህ ጉባኤ መክፈቻ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በንግግራቸው የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። «አሁን ተግተን በመሥራትና ነቅተን በመገስገስ አዲስ ታሪክ መሥራት የምንጀምርበት ታሪካዊ የዘመን አካፋይ አንጓ ላይ እንገኛለን። መልካም ምኞት ሳይሆን ንቁ ተሳትፎ፣ ጥረት ብቻ ሳይሆን ፍጥነት፣ ፍጥነት ብቻም ሳይሆን ብልሃት፣ ብልሃት ብቻም ሳይሆን አብሮ መሥራትና መደመር ያስፈልገናል» ብለው ነበር። « የተረከብናትን ኢትዮጵያ ያለመውደድ መብታችን ነው። የምናስረክባትን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ አስውበን መቅረጽ ግን ግዴታችን መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም» * ይህ ወር የኦህዴድ ጉባኤ በአዲሱ ሊቀመንበር የተመራበትና ትልልቅ ውሳኔዎችን ያሳለፈበት ነበር፤ በተመሳሳይ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ብአዴን፤ ደኢህዴንም ጉባኤያቸውን አካሂደዋል። ትልልቅ የፓርቲ ውሳኔዎችን አሳልፈውም የስም ቅየራ አድርገዋል። የግንባሩ ማጠቃለያ መርሀ ግብሩን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ንግግሮችን ያደረጉ ሲሆን፤ ለአብነት - «ኢትዮጵያን እና ድንቅ ሕዝቦቿን ደግሜ ማገልገል እንድችል እድል ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ» - በመንግሥት በኩል የሠላም ተቋም እንደ አዲስ ማደራጀት እና በጠንካራ አመራሮች ትኩረት ሰጥተን እንሥራለን፤ የአገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን እና የሃይማኖት አባቶች በነፃ የተሰጠንን ሠላም ለመጠበቅ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ከመጋቢት እስከ መጋቢት ትውስታ መስከረም 2011 ፎቶ፡- በገባቦ ገብሬ ፕላስቲኩ ተሰብስቦ ጥቅም ላይ መዋሉ ከሥራ ዕድል በተጨማሪ የአካባቢ ብክለትን ይቀንስ፤
9

78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

Oct 30, 2019

Download

Documents

dariahiddleston
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

78ኛ ዓመት ቁጥር 102 መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም ያንዱ ዋጋ 5.75 ብር

የሴቶችን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሙስናን እንታገል

ሙስና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጐዳ ወንጀል ቢሆንም የጉዳቱ መጠን ግን በሴቶች ላይ አመዝኖ እንደሚታይ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። በዓለማችን ከሚገኙ ድሆች ውስጥ ሴቶች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙና የዚህም አንዱ መንስዔ ፍትሐዊ ያልሆነ የፆታ ግንኙነትና ሙስና መሆኑን ጥናቶቹ ይጠቁ ማሉ። ሙስና በተንሰራፋበት ህብረተሰብ ውስጥ የሴቶች የተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ሚና በእጅጉ ይገደባል።

በሴቶች ላይ ይደርስ የነበረውን ጭቆና ለማስወገድ የተደረገውን ሁለንተናዊ የትግል እንቅስቃሴና ውጤት ለመዘከርና ሴቶች ከነበረባቸው ጭቆና ተላቀው በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ መስኮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን / ማርች8 ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ108ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ43ኛ ጊዜ የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

የሴቶችን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሙስናን ለመታገል በሴቶች እና በመንግሥት በኩል በሚደረገው እንቅስቃሴ ብቻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም። በመሆኑም መላው ህብረተሰብ ሴቶች ከልማትና ዴሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል ሙስናን ለመዋጋት በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረክት ይገባል።

ስልክ፡-01155291 00/011 552 77 74/81 ወይም ነፃ የስልክ መስመር 988ፋክስ፡- 011-553 69 91 ኢሜይል፡- feacinve @ethionet.et ፖ.ሣ.ቁ፡ 34798/99

የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

ሞገስ ፀጋዬ

በመዲናችን የሚገኙ ወጣቶች ናቸው፤ አፍላ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ሳይመርጡ የቤት ውስጥ ተረፈ ምርቶችን (ቆሻሻ) ከያለበት ይሰበስባሉ። በተለይ የውሃ መያዣ ፕላስቲኮችን ከየቱቦ፣ ወንዞች፣ መንገዶች... ከወዳደቁበት ቦታ አጠረቃቅመው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ ፋብሪካዎች በማቅረብ ሁልጊዜ በሥራ እንደተጠመዱ ናቸው። የመድከምና የመሰልቸት ስሜት አይታይባቸውም። ወጣቶቹ ለራሳቸው ከፈጠሩት የገቢ ማስገኛ ሥራ ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫና ዕድሜ ጠገብ ለሆነችው መዲናችን ውብና ፅዱ አካባቢን ለመፍጠር ይተጋሉ።

በዚሁ ሥራ ከተሰማሩትና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱት መካከል ወጣት አስራት በላይ አንዱ ነው። በመጀመሪያ ለአካባቢ ፅዳት መንግሥት እንዳደራጃቸውና ቀስ በቀስ ደግሞ የውሃ መያዣ እና ሌሎች ፕላስቲኮች በመሰብሰብና ለተረካቢ ድርጅቶች በማቅረብ ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ይናገራል።

የውሃ መያዣ ፕላስቲኮች ከተለያዩ ቦታዎች ሰብስበው ለድርጅቶች ማቅረብ ከጀመሩ አምስት ወራትን አስቆጥረዋል። ሥራውን ሲጀምሩም በ60 ሺ ብር ካፒታል እንደነበርም ይገልጻል። በአሁኑ ወቅት ልፋታቸው ፍሬ አፍርቶ ካፒታላቸው ከ400 ሺ ብር በላይ መድረሱንም ይናገራል። መንግሥትም የወጣቶችን የሥራ ፈጠራ ለማበረታታት አንድ

የሥራን ክቡርነትን በተግባር

የሥራን...ወደ 4ኛው ገጽ ዞሯል

የህዳሴ ግድቡን በአዲስ የመነቃቃት መንፈስ መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ

ሞገስ ፀጋዬ

አዲስ አበባ፡- ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በአዲስ የመነቃቃት መንፈስ ድጋፉን በማጠናከር ለውጤት ማብቃት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ።

የከተማው አንዳንድ ነዋሪዎች በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት የኢትዮጵያውያን የአንድነት መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው እስኪጠናቀቅ መቀጠል አለበት።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ አቶ መለሰ ጌታቸው እንዳሉት ታላቁ ህዳሴ ግድብ ከህዝቡ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለው ነው፤ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሀብትም ፈሶበታል፤ በመሆኑም ህዝቡ ተጠናቆ ውጤቱን ማየት ይፈልጋል። እስከፍጻሜ

የህዳሴ...ወደ 4ኛው ገጽ ዞሯል

በኢኮኖሚው ዘርፍ ጥንካሬም ድክመትም ተስተናግዷልጽጌረዳ ጫንያለው

አዲስ አበባ፡- አዲሱ የለውጥ አመራር በአንድ ዓመት ጉዞው በኢኮኖሚው ዙሪያ በርካታ መፍትሔ ሰጪ ሥራዎችን መሥራቱ እና ከዚሁ ጥንካሬው ጋር ተያይዞም ችግሮችን ያስተናገደ እንደነበር የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገለጹ።

የማክሮ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ባለሙያው ዶክተር ኢዮብ ተስፋዬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት አዲሱ የለውጥ አመራር በአንድ ዓመት ጉዞው በኢኮኖሚው ዙሪያ በርካታ መፍትሔ ሰጪ ሥራዎችን ሠርቷል። በተለይም

የውጭ ምንዛሬ ችግርን ለመፍታት የተሠራው ሥራ በምንዛሬ እጥረት ሊያርፍ የሚችለውን ጫና በብዙ መልኩ ያቃለለና እፎይታን ያስገኘ እንደነበር አስታውሰዋል ።

የአገሪቱ የውጭ ብድር ጫናን ለመቀነስ የአዲስአበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ብድር በ10 ዓመት መከፈል እንዳለበት ስምምነት ቢኖርም ይሄንን የዕዳ ክፍያ ወደ 30 ዓመት እንዲራዘም መደረጉም አንዱ የጥንካሬ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የፋይናንስ ተቋማትን አሁን ባሉበት ቁመና ይዞ መቀጠል ማክሮ ኢኮኖሚውን በእጅጉ

እንደሚጎዳው የሚናገሩት ዶክተር ኢዮብ፤ ፖሊሲን በሚመለከት ብቻ የሚሠራ የፋይናንስ ተቋማት ያስፈልጋሉ። ይሁንና በአገር ውስጥ ከሰው ሀብት ጀምሮ ምንም የተሟላ ነገር የላቸውም። ስለሆነም መንግሥት ይህንን ሊያስተካክል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኤክስፖርት ሴክተሩንና በቱሪዝም ላይ መሥራቱን ማጠናከር እንዲሁም የተረጋጋ ኢኮኖሚ መፍጠር ላይ ማተኮር እንደሚገባም መክረዋል።

እንደ ዶክተር ኢዮብ ገለጻ፣ለውጡ ላይ የመጣው የኢኮኖሚ ችግር ቀድሞ የተጠራቀመ ነው። በዓመት ውስጥ ደግሞ ወደነበሩበት መመለስ

እጅግ ያዳግታል። ለአብነት የውጭ ምንዛሬ ችግር፤ የሥራ አጥ ቁጥር መጨመር፤ የንግድ ሚዛን ጉድለት በስፋት እየጨመሩ የመጡ መሆናቸውን አንስተው ይህም በአንድ ዓመት የተፈጠረ ችግር ብቻ አይደለም። ሆኖም አሁንም የለውጡ ችግሮች ከመሆን የሚያስቀራቸው አይኖርም ብለዋል።

«የግል ዘርፉን በማጠናከር ዙሪያ የፖሊሲ ሮድ ማፕ አለመኖሩ እንደ ችግር የሚነሳ ነው» የሚሉት ዶክተር ኢዮብ፤ ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማስተካከል በፍጥነት አለመኬዱ፤ ቁልፍ የሆኑ

በኢኮኖሚው...ወደ 4ኛው ገጽ ዞሯል

ከመስከረም 1 እስከ መስከረም 30 ምን ምን ክስተቶችን አሳለፍን።

* በዚህ ወር ውስጥ የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸው አንዱ ነው። በአገር ውስጥ ገብተው ሠላማዊ ትግል እንዲያደርጉና ለአገራቸው የዲሞክራሲ መጎልበት እንዲሰሩ ተደርጓል።

* ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከውጭ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ጋር የተወያዩትም በዚሁ የመስከረም ወር ነው።

* የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ የተከናወነውም በመስከረም ሲሆን፤ በዚህ ጉባኤ መክፈቻ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በንግግራቸው የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። «አሁን ተግተን በመሥራትና ነቅተን በመገስገስ አዲስ ታሪክ መሥራት የምንጀምርበት ታሪካዊ የዘመን አካፋይ አንጓ ላይ እንገኛለን። መልካም ምኞት ሳይሆን ንቁ ተሳትፎ፣ ጥረት ብቻ ሳይሆን ፍጥነት፣ ፍጥነት ብቻም ሳይሆን ብልሃት፣ ብልሃት ብቻም ሳይሆን አብሮ መሥራትና መደመር ያስፈልገናል» ብለው ነበር። « የተረከብናትን ኢትዮጵያ ያለመውደድ መብታችን ነው። የምናስረክባትን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ አስውበን መቅረጽ ግን ግዴታችን መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም»

* ይህ ወር የኦህዴድ ጉባኤ በአዲሱ ሊቀመንበር የተመራበትና ትልልቅ ውሳኔዎችን ያሳለፈበት ነበር፤ በተመሳሳይ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ብአዴን፤ ደኢህዴንም ጉባኤያቸውን አካሂደዋል። ትልልቅ የፓርቲ ውሳኔዎችን አሳልፈውም የስም ቅየራ አድርገዋል።

የግንባሩ ማጠቃለያ መርሀ ግብሩን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ንግግሮችን ያደረጉ ሲሆን፤ ለአብነት

- «ኢትዮጵያን እና ድንቅ ሕዝቦቿን ደግሜ ማገልገል እንድችል እድል ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ»

- በመንግሥት በኩል የሠላም ተቋም እንደ አዲስ ማደራጀት እና በጠንካራ አመራሮች ትኩረት ሰጥተን እንሥራለን፤ የአገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ ወጣቶች፣ ምሁራን እና የሃይማኖት አባቶች በነፃ የተሰጠንን ሠላም ለመጠበቅ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ከመጋቢት እስከ መጋቢት

ትውስታ መስከረም 2011

ፎቶ

፡- በ

ገባቦ

ገብሬ

ፕላስቲኩ ተሰብስቦ ጥቅም ላይ መዋሉ ከሥራ ዕድል በተጨማሪ የአካባቢ ብክለትን ይቀንስ፤

Page 2: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 2

የሞሪንጋ ዛፍ በኢትዮጵያ በተለምዶ ሽፈራው በሚል መጠሪያ ይታወቃል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ13 በላይ ዝርያዎች ያሉትና በሁለገብ ጠቀሜታቸው ከሚታወቁት ዛፎች መካከል አንዱ ነው። በo]ለም ላይ ካሉት የሞሪንጋ ዛፍ ዝርያዎች ውስጥ ሰባት የሚሆኑት በምሥራቅ አፍሪካ በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በጅቡቲ እና በሶማሊያ አካባቢዎች ይገኛሉ።

ሽፈራው ከሚለው ስያሜ ባሻገር የጎመን ዛፍ ወይም የአፍሪካ ሞሪንጋ ተብሎም ይጠራል። ዛፉ በኢትዮጵያ በአብዛኛው በዝቅተኛው የስምጥ ሸለቆ ሃይቅ፣ በደረቃማ እና ከፊል ደረቃማ በሆኑት የአየር ንብረት ክልሎች በጌዲዎ፣ ሲዳማ፣ ኮንሶ፣ ኦሞ (ወላይታ)፤ ምዕራብ ጋሞጎፋ በመሳሰሉት ይገኛል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወሎ፣ ሸዋ፤ ሐረርጌና ሲዳማ አካባቢዎች የግብርና ልማትን ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ጋር በማቀናጀት ለሠርቶ ማሳያነት እየተተከለ ነው። ሞሪንጋ በምድር ወገብ ፈጣን ዕድገት አለው። ይህ ዛፍ ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ

የሽፈራው ዛፍ /ሞሪንጋ/ ምንነትና ጠቀሜታው

ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች

ልጆች እንዴት ናችሁ? ትምህርት ጥሩ ነው? መቼም በሚገባ እየተከታተላችሁ እንደሆነ እገም ታለሁ። ምክንያቱም

የተማረ ወድቆ አይወድቅም ሲባል ትሰማላችሁ አይደል? ይህ ያለምክንያት አልተነገረም። የተማረ ሰው ሁልጊዜም ቢሆን ተፈላጊ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው። የተማረ ሥራ መቀጠር ይችላል፣ በራሱ ሥራ ፈጣሪ ይሆናል። በአገር ውስጥም በውጭም ተንቀሳቅሶ መሥራት ይችላል። ምክንያቱም ብዙ ነገሮችን ያውቃልና ነው። እናንተም ይህንን አስባችሁ በሚገባ ትምህርታችሁን መከታተል አለባችሁ። የተማረ ሰው ለሀገሩ የተለያዩ ነገሮችም ያደርጋል፣ ቅን ሐሳቢም ይሆናል። ስለሀገሩ ይቆረቆራል። ልጆች እናንተም ከአሁኑ ጀምሮ ሀገራችሁን ለመርዳት ጥረት እያደረጋችሁ አይደል? አዎ! በሀገራችን በኢትዮጵያውያን ለሚገነባው ታላቁ ህዳሴ ግድብ ገንዘብ በማዋጣት ድጋፍ እያደረጋችሁ ነው። ይሄ በጣም ደስ ይላል። እስከ ግንባታው ፍፃሜ ድረስም ድጋፍ እንደምታደርጉ እተማመናለሁ። እኔ ደግሞ ስለ ህዳሴ ግድብ አንዳንድ ነገሮችን ላስነብባችሁ።

ልጆች ህዳሴ ግድቡ ከተጀመረ ስንት ዓመት የሆነው ይመስላችኋል? ስምንት ዓመት ካላችሁ ልክ ብላችኋል። ዛሬም የምናነሳው የፊታችን ማክሰኞ ከተመሰረተ ስምንተኛ ዓመቱን ያስቆጥራልና እናንተም በአቅማችሁ ማድረግ ያለባችሁን እንድታደርጉ ለመንገር ጭምር ነው። መቼም ልጆች በየትምህርት ቤታችሁ ለህዳሴ ግድባችን የተለያዩ መዋጮዎችን ስታደርጉ ነበር አይደል? እንደውም ብዙዎቻችሁ በቤተሰባችሁ አማካኝነት ቦንድም እንደገዛችሁ እገምታለሁ።

አሁንም ይህንኑ ድጋፋችሁን ማጠንከር አለባችሁ እሺ! ከዚህ ጋር ተያይዞ ልጆች ለህዳሴ ግድቡ ምን እያደረጉ እንደሆነ የተወሰኑ ልጆችን አነጋግሬያለሁ። እናንተም የእነርሱን አርአያነት ተከትላችሁ የቻላችሁትን እንደምታደርጉ በመገመት እነርሱ የነገሩኝን ላጋራችሁ።

መጀመሪያ ያነጋገርኳት ልጅ የአብስራ አባተ ትባላለች። የምትማረው ቱሉዲምቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን፤ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ናት። ብሔራዊ ተፈታኝ እንደመሆኗ መጠን ትምህርቷን በአግባቡ እያጠናች መሆኗን ነግራኛለች። እንደውም የሰባተኛ ክፍል ትምህርቷን በሚገባ እያነበበችና ሰባ አምስት በመቶ ላይ እንደደረሰችም አጫውታኛለች። ሌሎችም ጓደኞቿ ይህንን እንዲያደርጉ ትመክራለች። ምክንያቱም ጊዜው ቶሎ እየሄደ በመሆኑ ቀድመው መዘጋጀት ካልቻሉ ውጤታማ አይሆኑም ትላለች።

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያም የተለያዩ ሀሳቦችን አንስታ አጫውታኛለች። «ህዳሴ ግድቡ ለአገር ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ መብራት ለማያገኙ የአገራችን ገጠራማ ቦታዎች እጅግ አስፈላጊ ነው። እኛም የመብራት መቆራረጥ የማይገጥመን ህዳሴ ግድቡ ሲሠራ ነው። በተለይ ግን እኛ ብዙ ጊዜ መብራት ሳይጠፋብን በየቀኑ ስንማር በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩት እስካሁን ያለ መብራት መቆየታቸው በጣም

ያሳዝናል። ስለዚህ ይህ የህዳሴ ግድብ ካለቀ በኋላ ማንም በመብራት እንዳይቸገር ይሆናልና ለዚህም እኛ በገንዘብ መደገፍ አለብን ብላለች። ምንም እንኳን ልጆች ብንሆንም ከቤተሰቦቻችን በመጠየቅና ለተለያየ ነገር ከሚሰጠን ላይ ቀንሰን በማጠራቀም የመብራት ብርሃን ያላገኙ የአገራችንን ክፍሎች ለመታደግ ድጋፋችን መጠናከር ይኖርበታል» ስትል ነግራኛለች።

የአብስራ ከዚህ በፊት በትምህርት ቤት አዋጡ በሚባለው ሁሉ እንደምትሳተፍና በቤተሰብ ደረጃም ቦንድ በስሟ ተገዝቶላት እንደነበር አጫውታኛለች። በቀጣይም ቢሆን ትምህርት ቤቱ እንኳን ይህንን ማድረግ ባይችል ከጓደኞቿ ጋር በመመካከር ድጋፏን ለማድረግ እንዳቀደችም ነው የነገረችኝ። ልጆች ዛሬ ላይ ይህንን አይነት የበጎ ተግባር ሥራ መለማመድ ከቻሉ በቀጣይም በጎ ነገር ከማድረግ የሚገድባቸው አይኖርም ብላለችም።

የአብስራ የህዳሴ ግድቡ መሠራት በተለይ ለእኛ ተተኪ ትውልዶች ትልቅ የወደፊት እድል ማመቻቻ ነው ትላለች። ምክንያቷ ደግሞ እኛ ትምህርታችንን ስንጨርስ በመብራት ኃይል የሚሠሩ ነገሮችን ሁሉ ያለምንም ችግር እንድንተገብር እንሆናለን የሚለው ነው። ስለዚህም የዓለም አገራት ሁሉን ነገር በኤሌክትሪክ ኃይል መሥራትና በአጭር ጊዜ መለወጥ የቻሉት ሁሉ ነገር

ልጆች ስለ ህዳሴ ግድቡጽጌረዳ ጫንያለው

ስላላቸው ሳይሆን ያላቸውን በአግባቡ መጠቀም ስለቻሉ እንደሆነም አንስታለች። በዚህም ዛሬ ላይ ያለንን ሀብት እንደ አባይ አይነት ወንዞችን ተጠቅመን ለኃይል ማመንጫነት ማዋል ይገባናልም ባይ ናት። የልጆች ድርሻም መሆኑ ያለበት ይህ ነው። ትልልቆችን ጠባቂ መሆን እንደሌለባቸውም አጠንክራ ትናገራለች።

ሌላዋ ያነጋገርኳት ልጅ በእምነት አባተ ስትሆን፤ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነች። በትምህርቷ ጎበዝና ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን እንደምትወጣም ነግራኛለች። መማርና በትምህርት ጎበዝ መሆን አማራጭን ያሰፋል ብላ ታምናለች። ምክንያቷ ደግሞ የሚፈልጉትን ነገር ያለማንም ጣልቃ ገብነት በእውቀት ብቻ ማግኘት እንደሚቻል በመገንዘቧ ነው።

በእምነት ዶክተር መሆን ትፈልጋለች። ይህንን ሙያ የመረጠችው ደግሞ በጎዳና ያሉ ህፃናት በጣም ስለሚያሳዝኗት ነው። እነርሱን ሰብስባ ከገቡበት ችግር ማውጣትና መንከባከብ ትፈልጋለች። በተለይም የጤና ችግራቸው እንዲፈታላቸው ልዩ ፍላጎት አላት። ስለዚህም በሚገባ ውጤቷን አስጠብቃ ለዚህ ለመብቃት ጠንክራ እንደምትሠራም ነው የምትናገረው።

ስለ ህዳሴውም እንዲህ ብላኛለች « ህዳሴ ግድቡ የሚሠራው በኢትዮጵያውያን ልጆች ነው። ስለዚህ እኛ ልጆች ደግሞ

ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን እናንሳ። ቅጠሉ፡- በውስጡ የተለያዩ ንጥረ

ነገሮችን የያዘ በመሆኑ በምግብ ይዘትነቱ አትክልትን መተካት ይችላል። ለአብነትም በምግብ ንጥረ ነገር ይዘታቸው ከሚታወቁት ከካሮት (ቫይታሚን ኤ)፣ ከአተር (ፕሮቲን)፣ ከብርቱካን (ቫይታሚን ሲ)፣ ከወተት (ካልሸም) እና ከቆስጣ (ብረት) ንጥረ ነገሮች ይዘት እንደሚበልጥ ጥናቶች ያሳያሉ።

ሞሪንጋ ዛፍ በበጋ ወራት ቅጠሉን በመጠኑ የሚያረገፍ ነገር ግን ቅርንጫፉ ከተቆረጠ (ከተገረዘ) ቅጠሉን ከማርገፍ የሚቆጠብና ብዙ ቅጠል የሚያቆጠቁጥ ነው። ደረቃማና ከፊል ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች የሚበቅልና የሚያድግ በመሆኑ የአካባቢ ስነ- ምህዳርን ለመጠበቅና ለምግብነት አገልግሎት ስለሚውል የምግብ ዋስትናን ያረጋግጣል። ሞሪንጋ ከምግብነት አገልግሎት ባሻገር ለሻይ መጠቀምም ይቻላል። ይህ ደግሞ አዲስ የተቆረጠ ቅጠልን ወይም ደርቆ የተፈጨውን ቅጠል ሊሆን ይችላል።

ፍሬው፡- ዘር አቃፊ (ፖድ ወይም ቆባ)

በለጋነቱ እንደፎሶሊያ ተቀቅሎ መመገብ የሚቻል ሲሆን፤ ከደረቀ በኋላ ከዘሩ 40 በመቶ የምግብ ዘይት ይሰጣልም። ተረፈ ምርቱ ደግሞ መኖ ወይም ለውሃ ማጣሪያ ያገለግላል። ፍሬውን በቀጥታ መመገብ ደግሞ ፀረ-ትላትል፣ የጉበት ችግርን፣ የመገጣጠሚያ ቁርጥማትን ማከም እንደሚ ችል ይነገራል።

ከከረሜላችን እንኳን ቀንሰንም ቢሆን ድጋፍ ማድረግ አለብን። ብዙ ጊዜ ቤተሰቦቻችን መዝናኛና ሌሎች ነገሮች ሲያደርጉልን ቆጠብ አድርገን ለህዳሴው ይህንን እናድርግ ማለት ብንችል የታቀደው ላይ መድረስ እንችላለን።»

«ትልልቆች ብቻ የሚችሉ ትን ማድረግ አለባቸው ማለት አይገባም» የምትለው በእምነት፤ ህዳሴ ግድቡ የእኛ የተረካቢ ትውልዶች ነውና እጃችን አለበት ለማለት ትንሽም ቢሆን መደገፍ እንደሚጠበቅባ ቸው ትገልፃለች። ሌላሰው ባደረ ገው መጠቀም የለብንም የሚል እምነትም አላት። በትን ሹም ቢሆን አሻራችን ካረፈበት የእኛነት ስሜት ይፈጥርብናልና ይህንን ማድረግ አለብንም ብላለች።

በእምነት እናቷ በምትሰጣት ገንዘብ በእየዓመቱ ለህዳሴው ግድብ ታዋጣለች። ዘን ድሮ ብቻ ትምህርት ቤታ ቸው አምጡ ባለማለቱ አልከ ፈለችም። በዚህ ደግሞ መቆጨቷን ትናገራለች። ትምህርት ቤቱ ሁል ጊዜ የተማሪዎች ድጋፉ እንዲቀ ጥል ማበረታታት አለበት። በክፍል ውስጥ ብቻ ብዙ ይሰበሰ ባል። ስለዚህ ቢያንስ ትልቅ ነገር ባይሆንም ለህሌና ግን አዋጥቻለሁ የሚለውን ይፈጥራልና ትምህርትቤቱ ሊያስብበት እንደሚገባም ገል ፃልኛለች።

በእምነት እናቷ በስሟ ቦንድ በተደጋጋሚ ገዝታላት

እንደነበርም ነግራኛለች። በቀጣይም ቢሆን ከሚሰጣት ላይ በማጠራቀም እናቷ ቦንድ በስሟ እንድትገዛላት እንደምታደርግና ልጆችም ይህንን ቢያደርጉ ጥሩ እንደሆነ ትመክራለች።

ልጆች የበእምነትም ሆነ የአብስራ ሀሳብ ደስ የሚል ነው አይደል፤ ወደዳችሁት? መልካም ሁለቱም ለህዳሴው ግድብ ያላቸው ምልከታ በጣም ጥሩ ነው። እናንተም ልክ እንደነርሱ ለሰዎች በጎ እንደምታደርጉ አስባለሁ። እኔ ሁሉ ነገር ከሞላልኝ ይበቃል ማለት ጥሩ ሀሳብ አይደለም። ልክ እንደአብስራ ሁሉ የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኙ አካባቢዎችና ትምህርት ቤቶች የመብራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መመኘት አለባችሁ። ምኞታችሁ እውን እንዲሆን ደግሞ እንደ አብስራና በእምነት የተቻላችሁን ለህዳሴው ግድብ ማበርከት አለባችሁ።

ሌላው ልጆች ትምህርት ቤታችሁ ከዚህ በፊት ያደርገው እንደነበረው ሁሉ እንዲያበረታታችሁና ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ መምህራኖቻ ችሁን መጎትጎት አለባችሁ። በእምነት እንዳለችው የእናንተ ነውና ይህንን ማድረግ ያለባችሁም ራሳችሁ መሆናችሁን ማሳመን ይጠበቅባችኋል። በሉ ለዛሬ በዚህ እናብቃ። በቀጣይ ሌላ ጉዳይ ይዘንላችሁ እስክንቀርብ መልካም ሰንበት ተመኘሁ።

ልጆች እንዴት ናችሁ? በዚህኛው አምድ ላይ ታዋቂ ፈላስፋዎችን፣ ጀግና የአገር መሪዎች፣ ሳይንቲስቶችን እና ለዓለም ሥልጣኔ የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡ ሰዎችን እናስተዋውቃችኋለን። እስቲ ልጆች የዓለም ሥልጣኔ እዚህ እንዲደርስ ትልቅ ድርሻ አላቸው የምትሏቸውና ከዚህ ቀደም እናንተ ከምታውቋቸው ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን አስታውሱ። የአገራቸውን ሉአላዊነት ያላስደፈሩ እና መልካም ስብእና ያላቸው መሪዎችንስ ታውቃላችሁ? መልካም! ልጆች ሁሉም ሰው ለዓለም መሰልጠንና ዘመናዊ መሆን እኩል ድርሻ ባይኖረውም ትንሽም ቢሆን የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል። ስለዚህ ለዓለም ስልጣኔ የሁሉም አስተዋጽኦ አለበት ማለት ነው። ለዛሬ ታዋቂና ለአገራቸው ክብር ትልቅ ተጋድሎን ያደረጉትን የአፄ ኃይለሥላሴን ባለቤት እቴጌ መነን አስፋውን እናስተዋውቃችኋለሁ። መቼም ብዙዎቻችሁ ስለእርሳቸው በሚገባ ታውቃላችሁ። ለዘነጋችሁ ወይም ደግሞ ጭራሽ የማታውቁ ካላችሁ በጥቂቱ እናስታውሳችሁ።

• እቴጌ መነን አስፋው የቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ባለቤት ነበሩ። ግርማዊ እቴጌ መነን መጋቢት 25 ቀን 1883 ዓ.ም በወሎ ጠቅላይ ግዛት በአምባሰል አውራጃ ልዩ ስሙ ዕጓ ከተባለው ቀበሌ ከጃንጥራር አስፋውና ከወ/ሮ ስህን ሚካኤል ተወለዱ።

• እቴጌ መነን በልጅነት ዘመናቸው በወላጆቻቸው ቤት መምህር ተቀጥሮላቸው አማርኛ ማንበብና መፃፍ ጠንቅቀው አወቁ። በተጓዳኝ ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ ባልትና ሙያዎችን ተምረው በማጠናቀቃቸው የቤት ራስ ለመባል በቅተዋል።

• እቴጌ መነን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ያፈሯቸው ልጆች ስድስት ሲሆኑ፤ ልዕልት ተናኘወርቅ፣ ልዑል አልጋወራሽ አስፋወሠን፣ ልዕልት ዘነበወርቅ፣ ልዕልት ፀሐይ፣ ልዑል መኮንንና ልዑል ሣህለ ሥላሴ ናቸው።

• እቴጌ መነን ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋር በተጋቡ በሃያ ዓመታቸው ማለትም 1923 ዓ.ም የእቴጌነት ዘውድ ጫኑ። በእድሜ ዘመናቸው በግል ገንዘባቸው በኢትዮጵያና በእየሩሳሌም በርካታ ቤተክርስቲያናትን አሳንፀዋል። በጎ አድራጎት ድርጅቶችንም አቋቁመዋል።

• የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን እንደሚወር ይፋ በሆነበት ጊዜ እቴጌ መነን መስከረም 1 ቀን 1928 ዓ.ም የዘመን መለወጫ ዕለት ለዓለም ሴቶች ሁሉ የትግል ጥሪ አድርገው ነበር። በንግግራቸውም «በዓለም ያላችሁ ሴቶች ሁሉ በዓለም ላይ እውነተኛ ፍርድና ሠላም እንዲነግስ የመንግሥት ስዎች ሁሉ በሚሠሩት ሥራ በእግዚአብሔር መንፈስ እንዲመሩ በምናደርገው ፀሎት ተባባሪዎች እንድትሆኑ እንለምናለን» የሚል ነው።

• እቴጌ መነን በ1928 ዓ.ም ባለቤታቸው ጦር ሜዳ ሄደው ከጠላት ጋራ ሲዋጉ በከተማው ያሉ ወይዛዝርትን እየሰበሰቡ ለቁስለኞች እና ለሠራዊቱ የሚሆን ስንቅ፣ ትጥቅና የህክምና ቁሳቁስ እያዘጋጁ ይልኩ ነበር። የከተማውም ፀጥታ እንዲጠበቅ ከከተማው የጥበቃ ኃላፊዎች ጋር በመመካከር በትጋትና በብርታት ሲሰሩ ቆይተዋል።

• እቴጌ መነን በፖለቲካዊ አስተሳሰብ የተነሣ የእናታቸው የወ/ሮ ስህን ወገኖች በተለይም አያታቸው ንጉሥ ሚካኤልና አጉታቸው ልጅ ኢያሱ ከባለቤታቸው ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጋር በፈጠሩት ፖለቲካዊ ቅራኔ ሰበብ በተካሄደው የሰገሌ ጦርነት ከግራ ከቀኝ ተሰልፈው የተዋጉ ወገኖቻቸው ያለቁባቸው ቢሆንም በየጊዜው ሁለቱንም ወገኖች እያስማሙ በአንድነት እንዲኖሩ አስችለዋል።

• እቴጌ መነን አስፋው የአፄ ፋሲል ተወላጅ ናቸው። ከአፄ ፋሲል ጀምሮ የዘር ኃረጋቸው ሲመዘዝ አያታቸው ንጉሥ ሚካኤል ስምንተኛ ትውልድ እንደሆኑ ይነገራል። እናታቸው ወ/ሮ ስህን ዘጠነኛ እራሣቸው እቴጌ መነን ደግሞ አስረኛ ትውልድ ናቸው። በአፄ ፋሲል በኩል እቴጌ መነንና ቀዳማዊ

ኃይለሥላሴ ዝምድና አላቸው። ዝምድናቸው ግን ጋብቻ የማይከለክል ሲሆን፤ አሥራ ሁለተኛ ትውልዳቸው ላይ የሚገጥም መሆኑን የታሪክ መጽሐፍት ያረጋግጣሉ።

• እቴጌ መነን አስፋው የካቲት 9 ቀን 1954 ዓ.ም ተቀበሩ። ምንጭ፣ ከተለያዩ ድረ ገፆች

እቴጌ መነን

ተማሪ የአብሥራ አባተ

ዛፉ፡- ሞሪንጋ መዓዛማ አበባ ሰጪ ከሚባሉት ውስጥ ስለሚመደብ ለንብ ማነብ፣ ለአጥር፣ ለመድኃኒትነት፣ ለማዳበሪያነት ጥቅም ላይ ይውላል። ከአበቦቹ የተገኘ ጭማቂ ጡት ለምታጠባ ሴት የወተት ጥራትና ፍሰት መጠን እንደሚያሻሽል ይነገራል።

ተማሪ በእምነት አባተ

Page 3: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም 3

ይህ አምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው።በዓምዱ ላይ ሚወጡ ጽሁፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።

ርዕሰ አንቀፅ

አዲስ ዘመን

አጀንዳ

በ1933 ዓመተ ምህረት ተቋቋመ በየዕለቱ እየታተመ የሚወጣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም

አድራሻ:- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 001 የፖ.ሣ.ቁ፡- 30145

ዋና አዘጋጅ - ፍቃዱ ሞላ ኢ ሜይል - [email protected] አድራሻ - የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ - 13 የቤት ቁጥር - B402 H11 ስልክ ቁጥር - 011-126-42-40 የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ስልክ - 011-126-42-22 የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍ የኢሜይል አድራሻ [email protected] ስልክ - 011- 156-98-73 ፋክስ - 011- 156-98-62 የማስታወቂያ መቀበያ ክፍል ስልክ - 011- 156-98-65 የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያ ስልክ - 011-1-26-43-39 ማከፋፈያ ስልክ - 011- 157-02-70

የዕለቱ ምክትል ዋና አዘጋጅ፡- አልማዝ አያሌው ስልክ ቁጥር- 011-126-42-10 አዘጋጆች፡- ጽጌረዳ ጫንያለው አብረሃም ተወልደ ዳግም ከበደ ሊዲያ ተስፋዬ ተገኝ ብሩ ሞገስ ፀጋዬ

website www. press.et email. [email protected]

Facebook Ethiopian Press Agency የዝግጅት ክፍል ፋክስ- 251-011-1-56-98-62

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ሲሆን ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያውያን እውቀት፣ ጉልበትና ገንዘብ ሠርቶ ማጠናቀቅ ህልም እንጂ እውን የሚሆን የማይመስላቸው ብዙዎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን የጦር ጀግንነት ብቻ ሳይሆን በልማትም ጀግንነታችንን ለዓለም እናሳያለን በሚል ቆራጥነት ወደ ሥራው ገብተዋል።

ለፕሮጀክቱ እውን መሆንም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አሻራውን አሳርፏል። ሴት ወንድ፣ ህፃን አዛውንት፣ ሀብታም ደሀ፣ ተማሪ ሠራተኛ ሳይል ሁሉም እኩል ተነቃንቋል። በሞራል፣ በፍቅርና በአገራዊ አንድነት ሰሜት «እንገነባዋለን» በሚል ራሱ ለራሱ ቃል ገብቶና ተግባብቶ፣ አጨብጭቦ በአድናቆት ጭምር የተቀበለው ፕሮጀክት መሆኑን ደጋግሞ አረጋግጧል። በገባው ቃል መሰረትም ቃሉን ሳያጥፍ ድጋፍ ሲያደርግ፣ ቦንድ ሲገዛ አለኝታነቱን አስመስክሯል። ከዚሁ ጎን ለጎንም የአካባቢው ርቀት ሳይገድበው፣ የአየር ንብረቱ ሳይፈትነው ከትንሽ እስከ ትልቅ ረጅሙን ኪሎ ሜትር አቋርጦ ጎብኝቶታል። 284ሺ ሰዎች ቦታው ላይ ደርሰው በሥፍራው ለሚገኙት ሠራተኞችና ባለሙያዎች ሞራል ሰጥተው ተመልሰዋል። ይሄ ህዝቡ ለራሱ የገባውን ቃል በተግባር ሲፈፅመው እንደነበር አንዱ ማሳያ ነው።

መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም መሰረቱ ተጥሎ ወደ ሥራ የተገባው ይሄ ፕሮጀክት ስምንት ዓመቱን ሊደፍን የቀሩት ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው። በአምስት ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ቢታሰብም በተለያየ ምክንያት ሥራው ዘግይቷል። ለመዘግየቱ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በዋነኛነት ግን የብረታ ብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን የያዘው ሥራ በገባው የስምምነት ውል መሰረት ባለመሥራቱ እና የተሠራውም ከጥራት ጋር ተያይዞ ችግር ያለበት በመሆኑ ነው። ይሄንንም ችግር መንግሥት በመረዳት ችግሮቹን በመለየት በአሁኑ ወቅት ልምዱ፣ እውቀቱና ችሎታው ባላቸው የውጭ አገር ኩባንያዎች ጭምር ሥራው እንዲሠራ አድርጓል። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል በሥራው ላይ ያለው የጣሊያኑን ሳሊኒ፣ የቻይና እና የፈረንሳይ ኩባንያዎችን ጨምሮ ሌሎችም በሥራው ላይ ተሠማርተዋል።

ይሄ ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ምክንያት ተስፋ ወደመቁረጥ ለገባው ህዝብ ተስፋን የሚያለመልም እና ዳግም በሞራል የሚያነሳሳ ነው። አሁንም ግን «የሠራነው እኛው ነን» ብሎ በኩራት ለመናገር፣ አንገትን ቀና አድርጎ ለዓለም ለማሳየት አሁንም ከእያንዳንዳችን ገና ብዙ ሥራ፣ ብዙ ድጋፎች ከፊት ለፊታችን ይጠብቃል።

ፕሮጀክቱ ዛሬ 66 ነጥብ 26 በመቶ ላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤት አረጋግጧል። ቀረው ሥራ ደግሞ በአራት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል። በ2012 ዓ.ም. ደግሞ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዩኒቶች 750 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ተብሎ ግብ ተቀምጧል ።

የፈረንሳይና የቻይና ኩባንያዎች ከቅድመ ኃይል ማመንጫ ጋር በተያያዘ፣ ጎን ለጎን ሥራውን የሚሠሩ ሲሆን፣ በእቅዱ መሰረትም ሁለት ጀነሬተር ተርባይኖች ግድቡ ሳይጠናቀቅ ኃይል ለማመንጨት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። የፈረንሳዩ ኩባንያ የተርባይኑን ሥራ ጀምሯል። የቻይና ኩባንያ ደግሞ የብረታ ብረት ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። ይሄን የሚያሳየው መጠናቀቁን በጉጉት ለሚጠብቀው ዜጋ ተስፋ ሰጪ ነገሮች መኖራቸውን ነው። ሥራው በታቀደው መሠረት በጥራት እንዲጠናቀቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ይገኛል።

ስለዚህ የታሰበውን ያህል ስኬታማ መሆን የሚቻለውና አሁንም ከእያንዳንዳች ሊደረግ የሚገባው ድጋፍ ተጠናክሮ ከቀጠለ ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቦንድ በመግዛትም ሆነ በተለያየ መንገድ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት።

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያዊነታችን ጥንካሬ መገለጫ ጭምር በመሆኑ፣ ኢትዮጵያዊ ጀግንነታችንን እና አንድነታችንን ዳግም ማስመስከር ያለብን ድህነትን ሊዋጋ የሚችለውን ፕሮጀክት አጠናቀን በድህነት ላይ መዝመት ስንችል ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ «እኛው እንደጀመርን እኛው እንጨርሰዋለን» ብለን የገባነውን ቃል ዳግም ልናድስ ይገባል።

ሕዝቡ ቃሉን ዳግም ያድስ፤ ለቃሉም ይገዛ !

በኃይሉ አበራ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ጋንዲ መታሰቢያ መካከለኛ ሆስፒታል በኤች.አይ.ቪ ኤድስ እና ተያያዥ የህክምና ተግባራት ዙሪያ በተቋሙ የበሽታ መከላከልና የጤና ማጎልበት ዋና የሥራ ሂደት መሪ አቶ ብርሃኑ ውበቱ ጋር ቆይታ አድርገናል። የሥራ ሂደት መሪው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን የመከላከልና መቆጣጠር ሥራ እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር ተያያዥ የህክምና አገልግሎት በሆስፒታሉ የሚሰጥበትን መንገድ አብራርተውልናል።

እንደ አቶ ብርሃኑ ገለፃ በጋንዲ ሆስፒታል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል እንደ ትልቅ አጀንዳ ይዞ ያለው አንዱ የቅድመ መከላከል ሥራ ነው። የሆስፒታሉ ፖሊሲ በሽታ መከላከልና የህክምና አገልግሎት አቀናጅቶ መሥራት ነው። በተለይም መከላከል የሚቻለውን በሽታ በቅድሚያ መከላከል ዋነኛው ዓላማችን እና የግባችን አካል አድርገን እንሰራለን ይላሉ።

በዚህም ህብረተሰቡ እራሱን ከቫይረሱ እንዲጠብቅና በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ በመጀመሪያ በተለያየ መንገድ የጤና እና የግንዛቤ ትምህርት ወይም የመከላከያ ዘዴዎችን የማስገንዘብ ሥራዎች ይሠራሉ፤ የፀረ ኤች.አይ.ቪ የጤና አገልግ ሎቶችም በተቋሙ ይሰጣሉ። ቫይረሱን መከላከል በሚቻልበት መንገዶች ላይ የግንዛቤ መስጠት ስራዎች በስፋት ይሰ ራሉ። እንዲሁም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ነፃ የምርመራ አገልግሎት መስጠት ሌላው በሽ ታውን የመከላከል ሥራ አካል ነው። የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በአንድ ግለሰብ ደም ውስጥ መኖሩ በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላም የፀረ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ህክምና አገልግሎት በሆስፒታሉ ይሰጣል።

በጋንዲ ሆስፒታል በዋናነት የእናቶ ችና ሕፃናት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ኤች.አይ.ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይ ተላለፍ ለማድረግ የቀድመ መከላከል ሥራዎች ይሠራሉ። በመሆኑም ቫይረሱ

ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ፣ በተለይም መጪው ትውልድ ከኤች.አይ.ቪ ነፃ የሆነ ዜጋ እንዲሆን ማድረግ አንዱ የሆስፒ ታሉ ዓላማና ግብ በመሆኑ በትኩረት እንደሚሠሩም ኃላፊው ገልጸዋል። ከ2005 እስከ 2011 ጥር ወር ባለው ዓመት በነበሩት ጊዚያት ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለእያንዳንዳቸው ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በተደረገ ክትትል አንድ መቶ ሃያ በላይ ህፃናት ከኤች.አይ.ቪ ነፃ መሆን ችለዋል። በሆስፒታሉ ከአምስት ዓመት በታች ላሉ ህፃናት የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት እና ህክምና በሆስፒ ታሉ እስካሁን አልተጀመረም። ሆኖም ከዘውዲቱ መታሳቢያ ሆስፒታል እና ሌሎች ሆስፒታሎች ጋር በመሆን እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ከቫይረሱ ጋር ተያያዥ ችግሮችን በተመለከተ መጀመሪያ አንድ ሰው ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ መሆኑ በምርመራ ከታወቀ ለተለያዩ በሽታዎችም ሊጋለጥ እንደሚችል ግንዛቤ ሊኖር ያስፈልጋል። ይህም ሲባል ኤች.አይ.ቪ በደሙ የሚገኝ ሰው በሽታ የመከላከል አቅሙ ዝቅተኛ ስለሚሆን የተለያዩ ተላላፊ የሆኑም ሆነ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በታማሚው ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ። እነዚህም በኤች.አይ.ቪ ምክንያት የሚከሰቱ ተጓዳኝ በሽታዎች የሚባሉት ሲሆኑ በሆስፒታሉ ውስጥ ይህንንም በፀረ ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ፕሮግራም ወስጥ በማካተት አገልግሎቱ በነፃ እየተሰጠ ይገኛል። ይህም አገልግሎት የሚሰጥበት የተለያዩ ፕሮግራሞች ያሉ ሲሆን በየወሩ፣ በየሦስት ወሩ እና በየስድስት ወሩ ባሉት የሆስፒታሉ ፕሮግራሞች ጋር በማቀናጀት የህክምና እና የአጠቃላይ ምርመራ አገልግሎት ይደረጋል፤ አጋጣሚ በሽታ ካለም አስፈላጊ የሆነ ህክምና አብሮ ይሰጣል።

ከዚህም ውጭ በደማቸው ኤች.አይ.ቪ የተገኘባቸው ወገኖች እንደገና ህመም በሚያጋጥምበት ሰዓት የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ በሚመጡበት

መድኃኒቶችና ሌሎች የህክምና ወጪዎች አገልግሎት በነፃወቅት የላብራቶሪ ምርመራም ሆነ ሌሎች ምርመራዎችን እንዲሁም ሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ መድኃኒቶችና ሌሎች የህክምና ወጪዎችን ጭምር በነፃ አገልግሎት ይሰጣል። አቶ ብርሃኑ የዚህን ተግባር አስፈላጊነት ሲገልፁ ይህ አገልግሎት እንደቀላል የሚታይ ሳይሆን ሰዎች መኖር እንደሚቻል ግንዛቤ ስላገኙ እና በተግባርም የህክምና አገልግሎት ስላዩ በሆስፒታሉ ለመገልገል ወይንም እራሳቸውን ለመግለጽ ወደ ሆስፒታሉ እንዲመጡ መንገድ ስለሚከፍት ትኩረት የሚሰጠው ስራ ነው፤ ብለዋል።

አጠቃላይ በተለያየ የህክምና አገልግሎት ለሚመጡ ሰዎች ዋናው አጀንዳ ሆኖ ከምንሰጠው አንዱ ስለ ኤች.አይ.ቪ ያላቸውን የግንዛቤ አድማስ ማሳደግ ነው። ይህንንም ለማድረግ የግድ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው የግንዛቤ ሁኔታ ማሳደግ፣ ማስተማር፣ ማህበረሰቡ በጉዳዩ ላይ በግልጽ መነጋገር እንዲችል የመቀስቀስ ስራዎችን በሰፊው እንሰራለን። እንዲሁም ወደ ኅብረተሰቡ በመዝለቅ፣ ከጤና ጣቢያዎች ጋር በመቀናጀት፣ በሆስፒታሉ ስር ካሉ ሕዝባዊ ድርጅቶች ጋር ስለ ኤች.አይ.ቪ የተለያዩ ትምህርቶች ይሰጣሉ ብለዋል። ከነዚህም ድርጅቶች ለአብነት ከኢትዮጵያ መንገዶችና ትራንስፖርት ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት በየተወሰኑ ወራት በመሄድ የግንዛቤ ትምህርቶችን እና የኤች.አይ.ቪ ምርመራ አገልግሎት በመስጠት አብረው እየሠሩ መሆናቸውን አብራርተዋል። ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆንም፣ ድጋፍ ሲጠይቁ በማስተማር እና ነፃ የኤች.አይ.ቪ የምርመራ አገልግሎት በመስጠት በቅንጅት እንሠራለን ብለዋል።

የበሽታ መከላከልና የጤና ማጎልበት ዋና የስራ ሂደት መሪው፤ ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ ያለውን ተደራሽነት ለማሳደግ በተለይም ኤችአይ.ቪን እና ሌሎችን ቀላል በሽታዎችንም ለመከላከል የብዙኃን መገናኛ

ትልቁ መሣሪያ ነው፤ ሲሉ ገልፀዋል። በተቋሙ ብዙኃን መገናኛን በመጠቀም የተሄደበት በቂ ባይሆንም አልፎ አልፎ መገናኛ ብዙኃንን በመጋበዝ፣ በደብዳቤ በመፃፃፍ እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን እንዲቀርፁ በማድረግ የሚተላለፉትን የጤና ትምህርቶችና እየተካሄዱ ያሉ እንቅስቃሴዎች በማስተላለፍ ከብዙኃን መገናኛ ጋር አብረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል። በ2011 በሃገራችን ደረጃ የተከበረውን የዓለም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን በሆስፒታሉ በተከበረበት ወቅት፣ ከአዲስ አበባ ብዙኃን መገናኛ ጋር በመሆን መከበሩን አስታውሰው ከብዙኃን መገናኛ ጋር አብሮ መሥራት የሚያስችሉ ብዙ ስራዎች ይኖራሉ ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ብርሐኑ ሲያብራሩ፤ በተቋሙ የኤድስ ሕክምና በሁለት መንገድ የሚሰጥ ሲሆን አንደኛው ማንኛውም ሰው ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ፀረ ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት

ማግኘት አለበት። ኤች.አይ.ቪ እና ኤድስ ልዩነት አላቸው፤ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ነው፤ ኤድስ ደግሞ በሽታ ነው። ኤድስን ማከም ደግሞ የግድ ነው። ይህም የጤና ጥበቃ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የተሻለ ፖሊሲ ነው። ምክንያቱም ሰው ታሞ አልጋ እስኪይዝ መጠበቅ የለበትም፤ አንድ ሰው የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ለመጀመር ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ መሆኑ ብቻ በቂ ነው። ስለዚህ ፀረ ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ጀመረ ማለት ኤድስ የሚባለው በሽታ እንዳይከሰት፣ ታማሚ እንዳይሆን፣ ጤናማ እና አምራች ዜጋ እንዲሆን ስለሚረዳ እንደዚህ አይነት ሰዎችን ቶሎ እናስጀምራለን። ከዚህም ጋር በተያያዘ የቲቢ በሽታን ለመከላከል ምርመራ ይደረጋል የሌሎች የአባለዘር በሽታም ስክሪን በማድረግ እንመረምራለን፤ ተጓዳኝ ችግሮችንም አብረን እናክማለን ብለዋል።

በህክምና ሂደቱ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን አስመልክተውም፤ እነዚህን ሥራዎች በምንሠራበት ጊዜ ውጤታማነቱ ላይ የተለያዩ እንቅፋቶች ወይም ተግዳሮቶች አሉ። የጤና ሥራም የአንድ አካል ሥራ ብቻ ባለመሆኑ እና ዘርፈ ብዙ ምላሽ የሚጠይቅ ሥራ ስለሆነ የጤና ሴክተሩም እንደጤና አገልግሎት ሰጪነቱ ተቀዳሚ ዓላማው ቢሆንም ኅብረተሰቡም ደግሞ አብሮ መሥራት እና መተባበር አለበት። በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የምርመራና የህክምና ተጠቃሚ ግለሰቦች ደግሞ መድኃኒት መጠቀምም ሆነ ሕክምና መውሰድ ሕጋዊ መብታቸው መሆኑ ግልጽ ነው፤ ብለዋል። አክለውም፤ አንድ ሰው ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ ከሆነና የፀረ ኤች.አይ.ቪ ህክምናውን ወዲያውኑ

ካልጀመረ ቫይረሱ በሰውነቱ ውስጥ ተራብቶ በሽታ የመከላከያ አቅሙን ሊያዳክመው ይችላል። በእንዲህ አይነት ሁኔታዎች የግንዛቤ ችግር እና ጎጂ ባህላዊ እምነት ጋር በማያያዝ ከህክምና የሚርቁ በመኖራቸው ምክንያት ህክምናውን በወቅቱ ባለመጀመር ታመው የሚመጡባቸው ሁኔታዎች አሉ። ይህም እንደ ተግዳሮት እያጋጠመ ያለ አንዱ እንቅፋት ነው።

ሌላው ደግሞ ይላሉ አቶ ብርሐኑ፣ መድኃኒቱንም ከጀመሩ በኋላ አልፎ አልፎ ሰዓት የማዛባት አልፎ አልፎ ደግሞ መድኃኒቱን የማቋረጥ ችግሮች ያጋጥማሉ። በዚህም ወቅት በትክክል ሰዓት ጠብቆ መድኃኒት ባለመውሰድ ቫይረሱ መድኃኒቱን የመላመድ ባህሪ በማምጣት የመድኃኒቱን የመፈወስ አቅም በመቀነስ ውጤታማነቱን በማስቀረት ትልቅ ተግዳሮት እየሆነ ይገኛል። ስለዚህም መድኃኒቱን በትክክል መውሰድ፣ የቫይረሱን ምንነት ተረድቶ ጤናማ የመኖር ዘዴን በመላመድ መኖር እንደሚቻል ማሰብ መቻል ተገቢ ነው። ይህ በሚሆንበት ጊዜ አንድ ሰው ምንም ዓይነት በሽታ ሳይኖርበት ጤናማ ሆኖ መኖር ይችላል፤ በማለት ያስረዳሉ። አያይዘውም፤ አልፎ አልፎ እንደ ትልቅ ተግዳሮት የሆነውም አንድ ሰው በቫይረሱ ከተያዘ በኋላ አምኖ የህክምና አገልግሎት መውሰድ በህክምና ተቋማት ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር የምክር አገልግሎት ማግኘት፤ እንዴት ሕይወትን መምራት እንደሚቻል አስፈላጊ የሆነውን ዝግጅት ማድረግ ተገቢ ነው። ከእምነት ጋር በተያያዘም መድኃኒቱን ማቋረጥ ሳያስፈልግ ዕምነትንም ማራመድ እየተቻለ የሚፈጠሩ ተግዳሮቶች መኖራቸውንም ገልጸዋል።

…ከ2005 እስከ 2011 ጥር ወር ባለው ዓመት በነበሩት ጊዜያት ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለእያንዳንዳቸው ለአንድ

ዓመት ከስድስት ወር በተደረገ ክትትል ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ህፃናት

ከኤች.አይ.ቪ ነፃ መሆን ችለዋል…

Page 4: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

አዲስ አበባ፡- የታላቁ ህዳሴ ግድብን ወቅታዊ አቋም የሚቃኝ ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ተደረገ፡፡ ግምገማው የተካሄደው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትናንት በድረገጹ እንዳስነበበው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አሁን ያለበትን ደረጃ በተመለከተም የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንዳቀረቡት የሲቪል ምሕንድስና ሥራው ሰማንያ ሦስት በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራው ሃያ አምስት በመቶ፣ የብረታ ብረት ሥራው አሥራ ሦስት በመቶ በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ክንዋኔ ስልሳ ስድስት በመቶ መሆኑን ገልጸዋል። በፕሮጀክቱ መዘግየት የተነሳም ባጋጠመው የዋጋ ንረት መጀመሪያ ከታቀደው በላይ ከተመደበለት በጀት እስከ አሁን ዘጠና ስምንት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር ፈጅቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በማጠቃለያው ላይ እንደተ ናገሩት፤ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ግድ ቡን ማጠናቀቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

በዕለቱም የታላቁ ህዳሴ ግድብን ወቅታዊ አቋም የሚቃኝ ግምገማ በተለያዩ ኮሚቴዎች የቀረበ ሲሆን ግምገማውም፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ደረጃ፤ የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር፤ የአባይ ተፋሰስ ትብብር ማዕቀፍና የግድቡ ሙሌት ደረጃን ያጠቃለለ ነው።

4 መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን

የሀገር ውስጥ ዜናኪነጥበብዜና

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

በአከበሩት ሥራ...

የህዳሴ ግድቡን...

በኢኮኖሚው ዘርፍ...

ኪሎ ፕላስቲክ የውሃ መያዣዎችን በአራት ብር ሲያስረክቡ በኪሎ ሁለት ብር ድጎማ ያደር ግላቸዋል። በአጠቃላይ ከአንድ ኪሎ ስድስት ብር ያገኛሉ።

የሥራው ባህሪ ምንም እንኳን ከባድ ቢሆንም የአካባቢን ንፅሕናን ከመጠበቅና የሥራ ዕድልን ከመፍጠር አንፃር ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑ ጠንክረው እየሠሩ መሆናቸውን የሚያነሳው ወጣት አስራት፤ ገቢያችን ባደገ ቁጥር የአካባቢ ብክለትንም እንቀንሳለን የሚል ትልቅ ራዕይ እንዳላቸውና ይህንንም ለማሳካት ጠንክረው እንደሚሠሩ ያስረዳል። ለዚህ ውጤት ለመብቃት እንዲችሉ መንግሥት ያለባቸውን የቦታ ችግር እንዲፈታላቸው ይጠይቃል።

የኮባ ኢምፓክት የኅብረት ሥራ ማኅበራት

የፕሮዳክሽን ሱፐርቫይዘር አቶ ዘመን ያሲን እንዳሉት ድርጅቱ በቀን ከ15 ሺ ኪሎ ግራም በላይ ፕላስቲክ የመረከብ አቅም አለው። ለሥራውም ከሰው ኃይል በተጨማሪ 11 ማሽን ገዝቶ ወደ ሥራ ተሰማርተናል፡፡ ነገር ግን «ባለን አቅም ልክ ግብአት አላገኘንም፤ በአሁኑ ወቅት ከ8 እስከ 10 ሺ ኪሎ ግራም ብቻ ነው እያገኘን ያለነው፡፡ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፤ በዚህም ምክንያት ከሦስት ወር ጀምሮ ሥራውን በሚፈለገው ልክ እየሠራን አይደለም» ብለዋል። ለዚህም ምክንያቱ የውሃ መያዣ ፕላስቲኩን በሚሰበስቡና በሚያቀርቡት መካከል ደላሎችና ሌሎችም በመሰማራታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ጉተማ ሞረዳ ፤የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ከሚሠሩ ማህበራት ጋር በቅርበት እየሠሩ መሆኑን

ይናገራሉ። በተጨማሪም ከተረካቢ ድርጅቶች ለአብነትም ኮባ ኢምፓክትና ኢኬት ህጋዊ የፕላስቲክ ማቅለጫ ድርጅቶች ጋር ተባብረው የሚሠሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። እነዚህ ድርጅቶች ከማህበራት የተሰበሰቡ ፕላስቲኮችን በመረከብ አጥበውና ፈጭተው ወደ ውጭ ሀገር የሚልኩ መሆናቸውን ነግረውናል።

ድርጅቶቹንም ሆነ ማህበራቱን ባለሙያ በመላክ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ የሚገልጹት ኢንጅነር ጉተማ፤ ሌሎች ድርጅቶችም ይህንን ዓይነት ሥራ ለመሥራት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው። ለእነዚህም ድርጅቶች ወደ ፊት ፍቃድ ለመስጠት እንደተዘጋጁና መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት እንደሚያስተናግዷቸውም ጠቅሰዋል።

የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ኮሚሽን የደረቅና አደገኛ ቆሻሻ ህግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ኬኔ፤ ቆሻሻ ከምንጩ ጀምሮ ሳይንሳዊ

በሆነ መልኩ መያዝና እንደየባህሪያቱ መወገድ እንዳለበት ይናገራሉ።

እንደ አቶ ግርማ ገለፃ፤ በአሁኑ ወቅት በሀገር ደረጃ ከሚመረተው ጥቅል ቆሻሻ ከ9 እስከ 14 በመቶ የሚሆነው የሚሸፍነው ውዳቂ የፕላስቲክ ምርት ነው። ይህም ችግር ከፍተኛ በመሆኑ ተቋሙ ደረቅ ቆሻሻን ከመቀነስ አንፃር ብዙ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

ህብረተሰቡ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት የሚናገሩት አቶ ግርማ፤ የቆሻሻ አወጋገድ ሥር ዓቱ ላይ ትኩረት መስጠትና ጠጣር፣ ፈሳሽ፣ የሚ ቃጠል፣ የማይቃጠል፣ የሚበሰብስና የማይበሰብስ በማለት ለይቶ በማህበር ለተደራጁ አካላት ማስረ ከብ እንደሚገባው አሳስበዋል። ቆሻሻ በሥርዓት የማይወገድ ከሆነ በሰው፣ በአየር፣ በአፈርና በአጠቃላይ ህይወት ባለው ነገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ብለዋል።

ውስጥ የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠርና የኤክስፖርት መጠኑ እንዲቀንስ አድርጓል። ሆኖም መንግሥት በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚከናወኑ ፖሊሲዎችን በማውጣት መፍትሔ መስጠቱ የሚያስመሰግን መሆኑን ተናግረዋል።

የግል ዘርፉ ላይ ለመሥራት የታቀደው የመንግሥት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር መሞከሩ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ የግል ዘርፉ ሊበረታታበት የታሰበው ሥራ አዳዲስ አሠራሮችን በማምጣት የውጭ ምንዛሬን ያስገኛል። መንግሥትንም ካልተገባ ወጪ ይታ ደጋል። ስለሆነም የተጀመረውን ተግባር ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የህዝብ ብዛቱ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር አለመመጣጠኑ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና መፍጠሩን ገልጸው ሰላምና መረጋጋት ያለመኖሩም

ኢኮኖሚውን በሚፈለገው ደረጃ እንዳያድግ ገድቦታል። ብዙው ህዝብ ፖለቲካ እንጂ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ላይ ትኩረት እንዳይሰጥ ሆኗል።

የሚፈናቀለውና ሜዳ ላይ የሚውለው ወጣት መብዛትም ሌላው በኢኮኖሚው ላይ የታየ ችግር ነው የሚሉት አቶ ሙሼ፤ መንግሥት ተፈናቃዮችን ሲደግፍ ገንዘቡን ወደ ልማት ማዋል እንዳይችል አድርጎታል። የኢኮኖሚው ትልቁ ሞተር መንግሥት በመሆኑና ታክስን ሰብስቦ ዕዳ መክፈል ላይ ብቻ ማዋሉም ሌላው ችግር እንደሆነ ያነሳሉ። መንግሥት ብዙዎቹን የኮንስትራክሽን ዘርፎች በመያዙም እንዲሁ የሥራ አጥ ቁጥር እንዲበራከት አድርጓል። የግል ሴክተሩ በስፋት እንዳይሠራም ገድቦታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ በተወካዮች ምክር ቤት የስምንት ወር

ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ባንኩ እንደገና መሠራት ያስፈልገዋል። በዚህም ከልማት ባንክ ጋር በመሆን የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች ተጀምረዋል። ይህ ሥራ ደግሞ ባንኩን ከማዳን በተጨማሪ እግረመንገዱን ተልዕኮውን እንዲያሳካ የሚያስችለውም ይሆናል።

አገሪቱ ኢኮኖሚ ችግር ውስጥ እንዳትገባ እዳ መክፈል ግድ ነው ያሉት ዶክተር ይናገር፤ ለብድር ክፍያው ቅድሚያ በመስጠት ተቋሙ ራሱን ችሎ እንዲቆም ማድረግ ላይ ይሠራል ብለዋል። የንግድ ሚዛን ጉድለት እንዲሁ በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱንና በስምንት ወር ብቻ 8 ነጥብ ስድስት ቢሊየን ዶላር መድረሱንም አንስተዋል።

የአገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 9ነጥብ 4 በመቶ ያነሰ ነው ተብሏል።

የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ከተለመደ ሥራቸው አለመላቀቃቸውና መሰል ጉዳዮችም ለኢኮኖሚው ችግር መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ጥቅማቸውን የጨረሱ ፖሊሲዎች መስተካከልና መውጣት ሲኖርባቸው ባሉበት መቀጠላቸው፤ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚበደረውን ገንዘብ በአዋጅ መገደብ አለመቻሉ፤ የፋይናንስ ተቋማትን ማሻሻል ላይ ማስተካከያ አለመውሰዱ በችግርነት ይነሳል።

የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው እንዳሉት ፤የግብይት ስርዓቱ በሰላምና መረጋጋቱ ችግር ምክንያት መቋረጡ፤ ሥራዎች እንደተፈለገው መሠራት አለመቻላቸውም በአንድ ዓመት ውስጥ ከነበሩ ችግሮች የሚጠቀስ ነው። የውጭ ምንዛሬ አቅርቦቱ በአገሪቱ መቋቋም በማይቻልበት ሁኔታ ዝቅ ብሎ መቆየቱ በአገር

እስኪደርስ ደግሞ ሁሉም ዜጋ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ድጋፉን በተነቃቃ መልኩ መቀጠል አለበት ብለዋል።

«እኔ በበኩሌ ከዚህ በፊት ሳደርግ የነበረውን ድጋፍ ለመቀጠል ዝግጁ ነኝ፤ ሌላውም ሰው ይሄንን ሃሳብ ይደግፋል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም ግን ባለፈው አንድ ዓመት ለግድቡ የተሰጠው ትኩረት የተቀዛቀዘ ይመስላል። መቀዛቀዝ እንዳይኖር ህዝቡን የማነቃቃት ሥራ በመንግሥት በኩል ሊሠራ ይገባል» ብለዋል።

«የህዳሴው ግድብ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ሀገሮች ተስፋ ነው፤እኛም የአቅማችንን ቦንድ ስንገዛ ነው የኖርነው። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝቡን ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ሲወጡ ሰምተናል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ድጋፉ ላይ መቀዛቀዝ

ታይቷል» በማለት የተናገሩት ደግሞ የአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪ አቶ ኤርሚያስ ተድላ ናቸው።

የህዳሴው ግድብ የሚታይ፣ የሚዳሰስና የሚጨበጥ በመሆኑ መንግሥት ታአማኒነት ያለው መረጃን ለህዝቡ በማቅረብና ህዝብን በማስጎብኘት ወደ ሥራ መግባት አለበት ሲሉም አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኛ የሆኑት ወይዘሮ መሰረት መኮንን በበኩላቸው፤ ከግንባታው ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ስሜታችን ተነክቷል። አሁንም ህዝቡን በየእድሩ፣ በየማህበር፣ በእቁብ፣ በእምነት ተቋማት፣ በመስሪያ ቤትና በመሳሰሉ ቦታዎች የቅስቀሳ ሥራ በመሥራት በአዲስ መንፈስ እንዲነቃቃ ማድረግ ያስፈልጋል::

የህዳሴ ግድቡ ግንባታን አስመልክቶ ቀደም ሲል ችግሮች እንደነበሩ ቢታወቅም አሁን ግን

በትክክለኛው መንገድ ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ህዝቡን ማሳወቅና ለቀጣዩ ሥራም ድጋፍ እንዲያደርግ ማነቃቃት አስፈላጊ መሆኑን ወይዘሮ መሰረት ገልጸዋል። «መንግሥት ትኩረት ከሰጠው እንደ እኔ በፅዳትና በጉሊት የተሰማሩ ሁሉ ሳይቀሩ ለአባይ ይቆጥባሉ» ያሉት ወይዘሮ መሰረት ይህን ስሜት በመመለስ በኩል ትልቅ ሥራ መሠራት አለበት ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንደገለጹት፤ በፕሮጀክቱ ግንባታ በኩል ምንም ዓይነት መቀዛቀዝ እንደሌለ ገልጸው የህዳሴ ግድቡ መዘግየት ዋናው ምክንያት ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽ በገባው ውል መሰረት ሥራውን ባለመሥራቱ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት

በወሰደው ዕርምጃ ከብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በንዑስ ኮንትራክተርነት ሲሠሩ የነበሩ ሰባት ኮንትራክተሮች ሙሉ ኃላፊነት ተሰጥ ቷቸው ወደ ሥራውን መግባታቸውን ተናግረዋል።

የህዝብን አመኔታ ሙሉ ለሙሉ መመለስ የሚቻለው ሥራው መሠራቱን በዓይኑ ዓይቶ ሲረዳ ብቻ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም ለማድርግ የተሠራውን ሥራ መገናኛ ብዙሃን እንዲያዩትና እውነታውን ለህዝቡ እንዲያቀርቡ ይደረጋል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ግድቡ 66 ነጥብ 24 በመቶ የደረሰ ሲሆን በ2012 የመጀመሪያውን 750 ሜጋ ዋት ኃይል ያመጫል ተብሎ ይጠ በቃል።

«ከመጋቢት እስከ መጋቢት» የፎቶ ዐውደ ርዕይ ዛሬ ይከፈታል

«ከመጋቢት እስከ መጋቢት» የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን የአንድ ዓመት ቆይታ የሚያሳየው የፎቶ ዐውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት ይከፈታል። በዓውደ ርዕዩ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዲፕ ሎማሲ፣ በማህበራዊ፣ በፖለ ቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያከና ወኗቸው አበይት ተግባራት በፎቶ የሚታዩ ይሆናል።

የፎቶ አውደ ርዕዩ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደ ሲሆን፤ ለአራት ተከታታይ ቀናት ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል። የፎቶ አውደ ርዕዩ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተዘጋጀ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

«ኢትዮጵያዊው ሱራፊ» መጽሐፍ የማጠቃለያ ምርቃት ነገ ይካሄዳልበሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት የተዘ ጋጀው፤

ከአስር ዓመታት በላይ የተደከመበትና በቅርቡ ለንባብ የበቃው «ኢትዮጵያዊው ሱራፊ» የተሰኘው በፃድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት ታሪክ ላይ የሚያተኩረው ታላቅ መጽሐፍ የማጠቃለያ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ነገ መጋቢት 23 ቀን 2011ዓ.ም ማምሻውን በብሔራዊ ቴአትር ይከናወናል።

በዕለቱ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ፣ ዶክተር ዳዊት ወንድምአገኝ፣ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ ቀሲስ ዶክተር መዝገቡ፣ መምህር ግርማ ባቱ፣ መምህር ቀለመወርቅ ሚደቅሳ፣ ቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ ይገኛሉ፤ የሲሳይ በገና ትምህርት ቤት የበገና ድርደራ ይቀርባል ተብሏል።

«ማምሻ» ጥበባዊ የምሽት ክዋኔ ልደቱን ያከብራል

ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው «ማ ምሻ»ባለዐይነት የመድረክ ትዕ ይንት ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2011ዓ.ም ማምሻውን ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አንደኛ ዓመቱን ያከብራል።

«ነገረ ማምሻ» ባሉት በዚህ መድ ረክ ግጥሞች ይቀርባሉ፤ ሙዚቃና የተለያዩ ጨዋታዎችም ይኖራሉ። «ማምሻ» በየወሩ የመጨረሻ ማክሰኞ ቀን የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት በሥነ ግጥም፣ በወግና በትወና መሰል ጥበባዊ ክዋኔዎችን ለታዳሚ ሲያቀርበ መቆየቱ ይታወሳል።

ጎህ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል

ለሦስተኛ ጊዜ የሚደረገው ወርሐዊው ጎህ የኪነ ጥበብ ዝግጅት የፊታችን ረቡዕ መጋቢት 25 ቀን ከቀኑ በ11 ሰዓት 30ይካሄዳል።

ዝግጅቱ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የሚከናወን ሲሆን፤ በእለቱ ገጣሚ ምንተስኖት ማሞ፣ ህሊና ደሳለኝ፣ መልዕቲ ኪሮስ፣ መስፍን ወለተሰናይ እን ዲሁም ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል። የአንድ ሰው ተውኔት በተስፋሁን ከበደ ፣ ወግ በእንዳልካቸው ዘነበ እና በፍቅር ይልቃል እንደሚቀርብም ሰምተናል። በተጨማሪ ሙዚቃ መሳይ ተፈራ ካሳ ከመሶብ ባህላዊ ባንድ ጋር እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡

የኪነጥበቡ ምሽት አዘጋጆች ሄኖክ የእታገኝ ልጅ እና ተወዳጁ ገጣሚ በላይ በቀለወያ ናቸው፡፡

16ኛው ሰምና ወርቅ የኪነጥበብ ምሽት ሐሙስ ይካሄዳል

በየወሩ ማብቂያ ዕለተ ሐሙስ የሚካሄደው ሰምና ወርቅ የኪነጥበብ ምሽት መጋቢት 26 ቀን 2011ዓ.ም ማምሻውን ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በቫምዳስ መዝናኛ ማዕከል ይካሄዳል።

በዚህ መርሐ ግብር ዶክተር አሉላ ፓንክ ረስት፣ ዶክተር አዲል አብደላ፣ ዶክተር ሙላቱ በላይነህ፣ ኮኔል ደራርቱ ቱሉ፣ አርቲስት ኃይሉ ፀጋዬ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው፣ ኤፍሬኽ ለማ፣ መምህርት እፀገነት ከበደ፣ መምህር ኤልያስ መዳ እንዲሁም ገጣሚ ቴዎድሮስ ነጋሽ የገኛሉ፤ የተለያዩ ሃሳቦችንና ኪነጥበባዊ ሥራዎቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

በቀጣይ ሳምንት የሚካሄዱ የመጻሕፍት ምርቃት መርሐ ግብራት

«ባዶ ሰው በባዶ ቤት» የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በአንዱ ጌታቸው የተዘጋጀና «ባዶ ሰው በባዶ ቤት» የተሰኘ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነገ መጋቢት 23 ቀን 2011ዓ.ም ማመሻውን ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በቫምዳስ የመዝናኛ ማዕከል ሲኒማ አዳራሽ ይመረቃል።

አርቲስት ሻንበል ለማ ጉያ የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ተመረቀ

በስዕል ሥራቸው የሚታወቁት አርቲስት ሻን በል ለማ ጉያ የህይወት ታሪካቸውን በመጻፍ ትልልቅ የአርትኦት ሥራ በሠሩ ምሁራን አሳርመው ለንባብ ይበቃ ዘንድ ከትናት በስተያ በስካይ ላይን ሆቴል አስመርቀዋል።

284 ገጾችን የያዘው ይህ መጽሐፍ ዘጠኝ ምዕራፎችን የያዘ ሲሆን፤ የባለታሪኩን ሽልማ ቶችና ትልልቅ ሥራዎችንም ያካተተ ነው። በ200 ብር ዋጋም ለገበያ ቀርቧል። በምረቃው ወቅትም የተለያዩ የውጭ አንባሳደሮች ተገኝተው ስለእርሳቸው ምስክርነቶችንም ሰጥተውበታል።

የንባብ ሳምንት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ከጅማ ዮኒቨርሲቲ እና ጅማ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የንባብ ሳምንት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

«ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል» በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው በዚህ የንባብ ሳምንት፤ የመጻሕፍት ሽያጭና አውደ ርዕይ እንዲሁም የሥነጽሑፍ ምሽቶች ይከናወናሉ። በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ የውይይት መርሐ ግብራት ይኖራሉ። ትናንት መጋቢት 21 ቀን 2011ዓ.ም የተጀመረው ይህ የንባብ ሳምንት እስከ መጋቢት 25 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።

ደንዲ፡- ደንዲ ወረዳ የሚገኙ ቅርሶችን ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ ባለመንከባከቡና ለችግሮች መፍትሄ ባለመሰጠቱ ቅርሶቹ ለከባድ አደጋ እየተጋለጡ መሆኑን የወረዳው ነዋሪዎችና አባገዳዎች ገለፁ።

የሬንቦ የመኪና ኪራይና አስጎብኝ ድርጅት ሥራ አስኪያጅና የአካባቢው ተወላጅ አቶ ታፈሰ ሳህሌ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ አካባቢው በተፈጥሯዊ አቀማመጡ ውብና ለአ ዲስ አበባ ቅርብ ከሆኑ ከተሞች አንዱ ቢሆንም 12 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ባለመሠራቱ ለትውልድ መተላለፍ ያለባቸው ቅርሶች አደጋ አንዣቦባቸዋል።

በርካታ የቱሪስት መስህቦችን የያዘው ደንዲ ወረዳ ተመልካች በማጣቱ ታሪካዊነቱን እያጣ እንደሆነ የሚገልፁት አቶ ታፈሰ፤ በተለይ ሐይቁ የብዙ ቱሪስቶች መስህብ መሆን ቢችልም እድሉን ግን አላገኘም ብለዋል። ይህ ደግሞ መንገዱ ባለመሠራቱ፣ አመራሩም በተገቢው መንገድ ቅርሶቹ እንዲያዙ ባለመሥራቱና ሀብቱንም ባለማስተዋወቁ የመጣ ችግር መሆኑን ተናግረዋል።

በቦታው ላይ ቅርስ እንዲያስጠብቁና እንዲ ያስተዋውቁ በኃላፊነት የተቀመጡ አካላት የመጀ መሪያ ተግባራቸው በአካባቢው ያለውን ቅርስ አውቆ ማሳወቅ ቢሆንም ሥራቸውን በተገቢው መንገድ አልሠሩም የሚሉት አቶ ታፈሰ፤ «እኛም ቅርስ መኖሩን አናውቀውም» በሚል አስተያየት ሊያልፉት እንደማይገባ አስረድተዋል።

የፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ አራተኛ ትውልድ ልጅ የሆኑት አቶ ታደለ ደበበ በበኩላቸው፤ አካባቢው የብዙ ቅርሶች ባለቤት መሆኑን በቅርቡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የጀርመን ምሁራን ባደረጉት የአርኪዎሎጂ ምርመራ ውጤት አረጋግጠዋል። በደጋ አካባቢ ከሚገኙ ቅርሶች መካከል የጥንት ሰዎች መጠቀሚያ መሣሪያ የተገኘበትም ስፍራ መሆኑንም አስረድተዋል። ነገር ግን ሀብቱ ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ህዝቡ ባለው ሀብት እንዳይጠቀም ሆኗል። ቅርሶቹም ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጥፋት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

የአካባቢው አባ ገዳዎች በበኩላቸው ‹‹እኛን አይቶ

ቅርሶቹን መታደግ ያለበት አካል ሥራውን ባለመሥራቱ ቅርሶቹ አደጋ ላይ ናቸው

ጽጌረዳ ጫንያለው መፍትሄ የሚሰጠን አጥተናል። ለ12 ኪሎሜትር አስፋልት ብዙ ነገር እየከፈልንበት ነው። ለሀብታሙ አካባቢያችን መፍትሄ የሚሰጥ መንግሥት የለም። የአካባቢው አመራሮች ያላወቁትና ያልሠሩበት በመሆኑ አካባቢው ምድረ በዳ ሊሆን ነው በሚል ሥጋት ውስጥ ነን» ይላሉ።

እርቃኑን የቀረው የፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ቤተ መንግሥት፤ ስምንት ቁጥር ቅርጽ የያዘውና በ700 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የደንዲ ሐይቅ፤ ቋፍ ላይ ያለው የማርያም ቤተክርስቲያን ጥንታዊ ስዕሎችና ሳይቋረጥ ዘመናትን ያስቆጠረው የወሊሶ የገዳ ሥርዓት መተግበሪያ ማዕከል በቦታው ድንቅዬ ቅርሶች ናቸው። ሆኖም የሚሠራለት በማጣቱ ከጥቅም ውጭ እየሆነ መምጣቱንም አንስተዋል።

«ደንዲ ሐይቅን በተፈጥሮ ሐይቅነቱ እንጂ ከበስተጎኑ የተለያዩ የታሪክና የቅርስ ቦታ መገኛ መሆኑን አናውቅም። ሌሎች ቅርሶች መኖራቸውን እኔም ከእናንተ እኩል ነው ያየሁት›› የሚሉት የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ልማት ቡድን መሪ አቶ አበራ ታደሰ፤ በስፍራው በ2010 ዓ.ም የቱሪዝም ቀን ቢከበርም ይህንን ቦታ ባለመጎብኘቱ ችግሩ እንዲገዝፍ እንዳደረገው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አሁንም አደጋ ውስጥ እንደሆነ ቢታወቅም በመንግሥት አሠራር ምክንያት በቀጣይም ቶሎ ለመድረስ እንደሚያስቸግር ገልፀዋል።

«ቅርሶቹ የሚገኙት በአደዋው አርበኛ ‘አባ መላ’ ተብለው በሚታወቁት ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴና በአንጋፋውና በገጣሚ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድን የትውልድ ቦታ ቢሆንም ለታሪክነታቸው ሲባል እንኳን መጠበቅ ነበረባቸው» የሚሉት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባንቲ ለሚ ናቸው።

እርሳቸው እንዳነሱት፤ የችግሩ መከሰት ዋነኛ መንስኤ የአመራሩ ትኩረት ያለመስጠት ነው። ቦታውን በሚገባ አይቶ ቅርሶቹን ማሳወቅ ላይ አልተሠራም። ከራሴ ጀምሮ ከጎብኚ እኩል ማየቴ ትክክል አይደለም። በመሆኑም በቀጣይ ችግሩን ለመቀነስ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር ጊዜያዊ መፍትሄ ለማምጣት ይሠራል። ይሁንና ከፍ ያሉት የመንግሥት አካላት ግን ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብን ወቅታዊ አቋም የሚቃኝ ግምገማ ተደረገ

አብርሃም ተወልደ

አዲስ አበባ፡- የአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገድ ግንባታ ከታቀደው ጊዜ በላይ መጓተቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ፡፡

በምክር ቤቱ የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን የመስክ ምልከታ ካደረገባቸው ቦታዎች የአዋሽ አርባ ዱለቻ የመንድ ግንባታ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን በምልከታው ወቅት የመንገዱን መጓ ተት ለማየት ችሏል። የአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገዶች መስፋፋት የአርብቶ አደሩን ጥቅም ለማጉላት ታቅዶ መሥራቱን አድንቆ ሆኖም ግን ፕሮጀክቱ ከታቀደው በላይ ጊዜ መውሰዱን እንደ ድክመት አንስቷል፡፡

የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች በበኩላቸው የግንባ ታው መዘግየት ከግብዓት፣ ከበጀትና ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ የተፈጠረ መሆኑን አስረድ ተዋል፡፡ በተለይ ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ በአካባቢው ካሳ ተከፍሏቸው ከስፍራው ያል ተነሱ አርብቶ አደሮች በመኖራቸው ለሥራው እንቅፋት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊዎቹ አክለው እንደገለፁት በዱለቻ በኩል 10 ኪሎ ሜትር መሬት ረግረጋማ በመሆኑ መንገዱን ለመሥራት ከባድ እና ረዘም ያለም ጊዜ እንዲ ወስድ እንዳደረገው ጠቅሰዋል።

በተያያዘም ቋሚ ኮሚቴው በአፋር ክልል በዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌና አሚባራ ወረዳ ያሉ አርብቶ አደሮችንና በሶማሊያ ክልል ቸረር ዞን ደገሃቡር ወረዳ በአመድሌ የእንስሳት ማቆያ የመስክ ምልከታም አካሂደዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በጉብኝቱ ወቅትም በወረዳው ያሉ አርብቶ አደሮችን ሰብሰቦ አነጋግሯል። በውይይቱም ከታቀዱ አራት ዓመታትን ያሳለፉ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና፣ በውሃ እና በእንስሳት ልማት አርብቶ አደሩን ተሳታፊ ለማድረግ የታቀዱ ሥራዎች እየተሠሩ ቢሆንም በርካታ ሥራዎች እንደሚቀሩም መታዘቡን አስታውቋል፡፡

የአዋሽ አርባ ዱለቻ የመንገድ ግንባታ ተጓቷል

አብርሃም ተወልደ

ባለስምንት ቁጥሩ የደንዲ ኃይቅ ቱሪስቱን ይጣራል፤

Page 5: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 5

ሊድያ ተስፋዬ

ስድስተኛው የጉማ ሽልማት ባሳለፍነው ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን 2011 ዓ.ም በብሔራዊ ቴአትር በድምቀት ተከናውኗል። ባለሰማያዊ ምንጣፉ፣ በኢትዮ ፊልም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ የፊልም ሽልማት ዝግጅት፤ የፊልም ባለሙያዎች የሚገናኙበትና ደም ቀው የሚታዩበት መድረክም ነው።

በሽልማት ዝግጅቱ አዳዲስ ብቅ ያሉ የሥነ-ራዕይ (የፊልም) ባለሙያዎች ይበረታታሉ፣ ነባሮቹም ልምዳቸውን ያካፍሉበታል፤ አቅማ ቸውንም ያሳዩበታል። ከውድድሩ ማግስት፤ አሸናፊዎች ብሎም እጩዎች ይፋ ከሆኑ በኋላ ጥሩ ተብለው የተሸለሙ ፊልሞች ከያሉበት ዳግም ለእይታ ይናፈቃሉ፣ ምርጥ የተባሉ ተዋንያን ለበለጡና ለተሻሉ ሥራዎች ይተጋሉ።

ይህን እንደ አንዱ የፊልም ሽልማት ጥቅም ልናየው እንችላለን እንጂ የፊልም ሽልማቶች ለፊልሙ ዘርፍ እድገት ምን አበርክተዋል የሚለው ጠለቅ ያለ ዳሰሳ የሚፈልግ ሳይሆን አይቀርም። ጉማ የፊልም ሽልማትም በፊልም ባለሙያው ዮናስ ብርሃነ መዋ መሠረቱ ተጥሎና በተለያዩ የጥበብ ተባባሪ የሆኑ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እያገኘ ስድስት ዓመታትን ዘልቋል።

ጉዞን አለማቆም የመጀመሪያው ስኬት እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉና፤ ጉማ እየደመቀ መቀጠሉ እንደ አንድ ስኬት የሚያዝ ነው። እንደምን ቢባል የተለያዩ ክዋኔዎች ተጀምረው እየቀሩ፣ ወረት እየሆኑና በሳምንታቸው እየተረሱ እያየን ብሎም አንድ ጭብጨባ እያዳለጣቸው የሚወድቁ ብዙዎችን እየተመለከትን በመሆኑ ነው። እናም የጉማ አዘጋጆች «ጉማ ሁሌም ይቀጥላል!» ብለው መሪ ሃሳባቸውን ከፍ አድርገው ሲያሰሙ፤ እኛም ይበል ይቀጥል እንላለን።

ወዲህ ደግሞ መለስ ብለን በዛሬው የኪነጥበብ አምድ የጉማ ፊልም ሽልማትን ጉዞ እንዲሁም የዘንድሮውን የሽልማት ስነ ሥርዓት እንዳስሳለን። እንደወትሮው በደሌ ስፔሻል በሙሉ ስፖንሰርነት በደገፈው በዘንድሮው የጉማ ሽልማት ላይ፤ በቁጥር 61 የሚደርሱ ፊልሞች ተመዝግበው 25 የሚሆኑት ለውድድር ቀርበዋል። ፊልሞቹም በኢዮሃ ሲኒማ ለዳኞች እይታ ቀርበዋል፤ ታይተውም ውሳኔ አግኝተዋል።

ፊልምና የፊልም ሽልማትየፊልም ባለሙያው ብርሃኑ ሽብሩ ሥነ-

ራዕይ ይለዋል፤ ፊልምን። የፊልም ዘርፍ የጥበባትን ቡድን ከተቀላቀለ አንድ መቶ ሃምሳ ዓመት እንኳ አልሞላውም። ይህ ማለት ከሥነ ጽሑፍና መሰል የጥበብ ዘርፎች ጋር ሲወዳደር እድሜው እጅግ ለጋ የሚባል ነው ማለት ይቻላል። ይሁንና ግብዓቶቹ እድሜ ጠገብ የሆኑ ጥበባት በመሆናቸውና ወሳኙ የካሜራና ሲኒማቶግራፊ ጥበብ ደግሞ በየጊዜው እየተሻሻለና እያደገ ስለመጣ ከሁሉም በተሻለ በአጭር ጊዜ ተጽዕኖ መፍጠር የቻለ ዘርፍ ሆኗል።

የፊልም ሽልማት መርሃ ግብራትም ለዚህ ነው ከሌሎች ጥበባዊ ዘርፎች በተሻለ፤ ከሙዚቃም በደመቀ ሁኔታ ጎልተው የሚሰማሙት። እንደሚታወቀውም በዓ ለም አቀፍ ደረጃ በመዝናኛው ዘርፍ ላይ የሚሠሩትም ሆነ የተቀሩት መገናኛ ለእነዚህ ሽልማቶች ትኩረት ይሰጣሉ። ከነ ኦስካር መንደር የዘርና የቆዳ ቀለም ጉዳይ፣ የፆታ ነገርና የታሪኮች ዓይነት ገና ከውድድሩ ቀደም ብሎ መነጋገሪያ ሆኖ ሲሰነብት ታዝበናል።

ባለሙያዎችም እንደ ጥበብ አፍቃሪ እርካታን የሚሰጣቸውን ሥራ ከመሥራት በተጓዳኝ እነዚህን ውድድሮች ታሳቢ በማድረግ በየጊዜው በሥራዎቻቸው ላይ ለውጦችን ያሳያሉ። ያም ለውጥ ማጣቀሻ (Bench mark) ሆኖ ይቀመጥና፤ ሌሎች የፊልም ባለሙያዎች ደግሞ ከዛ በበለጠና በተለየ መንገድ ለመሥራት አዳዲስ መንገዶችን ቀይሰው በሥራዎቻቸው ያስቃኛሉ።

ይህ ቅብብል ለሂደቱ ደረጃ ሆኖለት፤ ባለሙያዎቹን ከዓመት ዓመት ከፍ እያደረገ የፊልምንም ጥበብ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ማድረስ ችሏል። እንደተባለው ደግሞ የፊልም ሽልማቶች በዚህ ላይ ያደረጉት አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም። አሁንም ሻገር ብለን በጥበቡ አንጋፋ ከሆኑት የፊልም መንደሮች ስንቃኝ፤ እንደ ኦስካር እና ባፍታ ያሉ ሽልማቶች ይነሳሉ። በእነዛ ውድድሮች ላይ «በውጭ አገር ቋንቋ የተሠራ» ዘርፍ ላይ ከስንት አንዴ ከመሳተፍ ውጭ ለአገራችን

የፊልም ዘርፍም እንዲህ ያለ ዕድል ቢፈጠር መመኘታችን አልቀረም።

ነገሩን የፊልም ወዳጆች የሆኑ ብርቱ ባለሙያዎች አጢነው ዝም አላሉም፤ የፊልም ሽልማቶችን በአገራችን ጀምረዋል። ለዚህ ደግሞ ጉማ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው። ጉማ የፊልም ሽልማት ለብቻው እንደ ሽልማት የቀረበ ሲሆን፤ በፊልም ፌስቲቫል መልክ ተዘጋጅተው መዝጊያቸውን ሽልማት ያደረጉ ድርጅቶችም ተፈጥረዋል። ለዚህ የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፌልም ፌስቲቫል እንዲሁም የአዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫልን በዋናነት መጥቀስ ይቻላል።

ጉማ ሲጀመርጉማ የፊልም ሽልማት መጠሪያውን

ያገኘው ከአርባ ሦስት ዓመታት ቀደም ብሎ በሚሼል ፓፓታኪስ ከተሰራው ‹ጉማ› የተሰኘ ፊልም ነው። ጉማ ሽልማት የተዘነጉትን በማስታወስ፣ ብዙ የሠሩ ግን ያልታወቁትን በማጉላት፣ ትኩረት ሳይሰጣቸው የቆየ ከፊልም ጋር የተያያዙ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ለማድረግ እንዲያስችል በመወዳደሪያ ዘርፎች ውስጥ አዳዲስ ዘርፎችን በማካተት ቀላል የማይባል ሥራ ሲሠራ የቆየ የፊልም ሽልማት ነው።

ጉማ የፊልም ሽልማት አስቀድሞም ሙያው ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎችን እውቅና ለመስጠት ታስቦ እንደተዘጋጀ ነው በተለያየ ጊዜ ሲዘገብ የነበረው። « ታድያ የፊልም ዘርፉን ምን ጠቀመው ? » የተባለ እንደሆነ አስቀድሞ እንዳልነው መጠነኛ የዳሰሳ ጥናት ሳይጠይቅ አይቀርም። ይሁንና በግልጽ የሚታዩና ሽልማቶች ለፊልሙ ዘርፍ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አለ። ይህንን የውድድር መንፈስ መፍጠርና ባለሙያዎች በሥራቸው ለእያንዳንዱ ነገር እንዲጨነቁ የሚያደርጋቸው መሆኑ ነው።

ከሦስት ዓመታት በፊት በዚሁ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ኪነጥበብ አምድ ላይ «“ጉማ የፊልም ሽልማት” ለሲኒማው እድገት ምን አበረከተ?» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ዘገባ ነበር። በዚህም ስለ መጀመሪያው የጉማ ፊልም ሽልማት ከሰፈረው ላስታውስ። እንዲህ ነው፤ በመጀመሪያው የጉማ ሽልማት ዝግጅት ላይ ለውድድር የቀረቡት በ2004 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ የቀረቡ ፊልሞች ናቸው።

በዚህ የመጀመሪያው ውድድር 33 ፊልሞች ተመዝግበው፤ ከ87 በላይ በሆኑ ዳኞች ተሳትፈው ለውድድር ከቀረቡት 33 ፊልሞች መካከል ያለፉት 23ቱ ነበሩ። በዚህ ጊዜ የውድድር ዘርፎቹም በቁጥር 17 ይጠጋሉ። ከእነዚህ ዘርፎች በተጨማሪ ውድድር የሌለው «የሕይወት ዘመን ተሸላሚ» የተሰኘ ዘርፍ ሲሆን፤ በልዩ ሁኔታና ምልከታ ነው ተሸላሚውም የሚመረጠው።

ታድያ እንዲህ ብሎ ያለ ስፖንሰርና ድጋፍ በአዘጋጁ ኢትዮ ፊልም ጥረት ብቻ አሃዱ ብሎ ጀመረ። ከዚህ ጊዜም ጀምሮ እያለ እያለ ቀጥለው በተካሄዱት የጉማ ሽልማቶች ላይ የተሳታፊ ፊልሞች ተሳትፎ ከፍ እያለ፤ መወዳደሪያ ዘርፎቹ በዓይነትና በቁጥር ብሎም በጥራት እየጨመሩ መጥተዋል። ሽልማት ሆኖ የሚቀርበው የጉማ ዋንጫም በቅርጽ ይዘቱ እየተቀየረና በባለሙያዎች እይታ እየተሻሻለ አሁን ያለበትን ቅርጽ ይዟል።

የዘንድሮው ጉማስደስተኛው የጉማ ፊልም ሽልማት

ባሳለፍነው ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን 2011ዓ.ም በብሔራዊ ቴአትር ሲካሄድ በአዳራሹ የፊልም ሙያ እንቁና ፈርጦች ሁሉ ተገኝተው ነበር። የሽልማት መርሃ ግብሩ ከ17 ቀናት በፊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የህሊና ጸሎት በማድረግ ተጀምሯል። የፊልም ባለሙያና ታዋቂ ሰዎች ባሉበት የካሜራ ባለሙያና ፎቶ አይታጡምና፤ ዝግጅቱ የጀመረው ማምሻውን አንድ ሰዓት ላይ ነው።

የጉማ ሽልማት በአያሌው የሚመሰገንበት አንድ ነገር አለ። ይህም ብዙ ሥራ የሠሩ ነገር ግን ራሳቸውን በሥራቸው ልክ ያላስተዋወቁ፤ የተዘነጉ ሰዎችን የማስታወሱ ነገር ሲሆን፤ በዘንድሮውም ሽልማት ይኸው ጉዳይ በሰፊው የታየበት መድረክ ነበር። ምንአልባትም ሸላሚ ሆነው በመድረኩ ላይ የተገኙ ባለሙያዎች ራሳቸው ተሸላሚዎችና አንደኞች መሆናቸው ለሽልማቱ ካባና ሞገስ ሳይሆነው አይቀርም።

እዚህ ላይ ልያዛችሁና በመድረኩ እጩዎችን በመግለጽና አሸናፊዎቹን ይፋ አድረጎ በመሸለም የተሳተፉትን እነዚህን ባለሙያዎች ልጥቀስ። ከባለሙያዎቹ አብዛኞቹ ያልተዘመረላቸው የሚባሉ ናቸው።

ከእነዚህም መካከል አንደኛው ብርሃኑ ሽብሩ ነው። ብርሃኑ በፊልም ሙያ ጥበብና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከአገር ውስጥ አልፎ ባህር ማዶ ትምህርቶችንና ልምዶችን የቀሰመና የሚያውቀውን ለጠየቀው ሁሉ ከማካፈል የማይቦዝን ባለሙያ ነው። እጅግ በርካታ በሆኑ ፊልሞች ላይ በሥራ መሪነት ወይም ዳይሬክተርነት ሠርቷል።

እንደዚሁ ሁሉ በማስተር ቪዲዮግራፊ በአሰልጣኝነት ለ14 ዓመታት ያገለገሉት አቶ ወንድሙ ካሳዬ፣ በማስታወቂያ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በካሜራ ባለሙያነት ያገለገሉና «ባለንስር ዓይኑ» የሚባሉት የካሜራ ባለሙያ አቶ እንዳልክ አያሌው፣ በሙዚቃ ድርሰት አንቱታን ያተረፉትና በክቡር ዘበኛ በድምፃዊነት፣ ተወዛዋዥነትና አሰልጣኝነት ለ34 ዓመታት በማገልገል ብሎም በድምሩ በሙዚቃው 62 ዓመታትን ያሳለፉት አየለ ማሞ እጩዎችን ለማሳወቅና አሸናፊውን ለመሸለም ከብሔራዊ ቴአትሩ መድረክ ተሰይመዋል።

እነርሱም ብቻ አይደሉምና ልቀጥል፤ በተለያዩ የዓለማችን አገራት የሥነ ስዕል ጥበብ የደረሰበትን ደረጃ ቀስመው ወደሥራ የገቡትና በፊልም ኮርፖሬሽን በፖስተር ዲዛይነርነት ለዓመታት ያገለገሉ ሰዓሊ ዜና አስፋው፣ በረጅም ልብወለድ የመጀመሪያዋ ሴት ደራሲትና በርካታ መጻሕፍትን ለአንባብያን ያደረሰችው ፀሐይ መላኩ፣ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በፕሮግራም ፕሮዳክሽን ክፍል፣ ፊልም ማንሳትና ላቦራቶሪ ቅንብር የሠሩ ብሎም በርካታ ዘጋቢ ፊልሞችን በካሜራቸው በምስል ያስቀሩ «ተንቀሳቃሽ የምስል ላይብረሪ» የተባለላቸው የካሜራ ባለሙያ አቶ ኤልያስ ብሩም ነበሩ።

ከሃያ በላይ ቴአትሮች ላይ የተወነውና በሬድዮና ቴሌቭዥን ድራማና ትረካዎችም የተሳተፈ፤ «የእግዜር ጣት» የተሰኘውን ቴአትር የጻፈው ደረጀ ደመቀ፣ በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ ለ28 ዓመታት በትወና እና በውዝዋዜ ያገለገለችው መርከብ ባልሔር፣ ላለፉት 38 ዓመታት በኪነጥበብ ዘርፉ ያገለገለ ተዋናይ፣ አዘጋጅ፣ ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ተርጓሚ ጋዜጠኛ ተፈሪ ዓለሙ፣ ከ63 ዓመት በፊት ዘርፉን ተቀላቅላ በትወና፣ በድምፃዊነትና በተወዛዋዥነት ያገለገለችው የሺ ተክለወልድ፣ ተዋናይና የቴአትር ባለሙያ ተክሌ ደስታም በተመሳሳይ እለቱን ሞገስ ሆነውታል።

የሲኒማቶግራፊ ባለሙያና በቶም ቪድዮና ፎቶ ግራፍ ማሰልጠኛ ለዓመታት በማገልገል ብዙ ተማሪዎችን ያሰለጠነው ኢዮብ ስብሐቱ፣ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ብቅ ካሉ የሙዚቃ አቀናባሪዎች መካከል የሆነውና በርካታ ሙዚቃዎች ላይ አሻራው የሚገኘው አቤል ጳውሎስ፣ አምስት

አልበሞችን ለአድማጭ ያደረሰችና በኮራ እንዲሁም በአፍሪማ የሙዚቃ ውድድሮች ተሳትፋ የአገራችንን ስም ያስጠራችው ድምፃዊት ጸደንያ ገብረማርቆስ አይዘነጉም።

በርካታ ፊልሞችን በድርሰትና በማዘጋጀት በጉማ ሽልማትም ብዙ ዋንጫዎችን በመቀበል ክብረ ወሰኑን የያዘችው ቅድስት ይልማ፣ የኢዮሃ አዲስ ኤግዚቢሽንና ኢዮሃ ሲኒማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዩ ዓለሙ፣ በትወና እና ሞዴሊንግ ሥራ፤ በፊልም ዘርፍም በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበችው መቅደስ ጸጋዬ። እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ባለሙያዎች በስድስተኛው የጉማ የፊልም ሽልማት ላይ ሸላሚ ሆነው የተገኙ ናቸው።

ከሽልማቱና ከዋንጫው እኩል የሸላሚዎቹ ማንነት ለአሸናፊዎቹም ሆነ ለሽልማቱ ክብር አይጨምርም ትላላችሁ? አንጋፎችን በማስታወስና በአዲሱ ትውልድ እንዲታወቁ በማድረግ በኩል ጉማ ሽልማት ድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላልና ይህ ይቀጥል የሚባል ነጥብ ይሆናል።

ወዲህ ደግሞ ከሸላሚዎቹ ወደ አሸናፊ ዎቹ እንመለስ፤ የስድስተኛው የጉማ ሽል ማት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ናቸው። በእርግጥም ፕሮፌሰር ኃይሌ ከዚህም በላይ የሚገባቸው ባለሙያና ሙያቸውን አፍቃሪ ናቸው። የሕይወት ታሪካቸው እንደሚያስረዳውም ባህርማዶ ባሉ እውቅና አንጋፋ ትምህርት ቤቶች በፊልም ጥበብ ሙያ ተምረዋል። በአሁኑ ጊዜም በሀዋርድ ጠቅላይ መካነ ጥናት የፊልም ጥበብ ፕሮፌሰር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

ፕሮፌሰር ኃይሌን የፊልም ተመልካች ጤዛ በተሰኘው ሥራቸው ያስታውሳቸዋል፤ አይረሳቸውም። ከዛም ባለፈ በጥቂቱ እንጥቀስ ከተባለ «ዓድዋ»፣ «ሳንኮፋ፣ ከክረምት በኋላ»፣ «አመድና ፍሞች»፣ «ቡሽ ማማ» እና ሌሎች በርካታ ልብወለዳዊ ፊልሞችና ዘጋቢ ፊልሞችን ለእይታ አቅርበዋል። ከዚህ ባሻገር እጅግ በርካታ ሽልማቶችን ከተለያዩ የዓለም አገራትና የፊልም ጥበብ ዘርፍ ሸላሚዎች ተረክበዋል። በተለይም «ጤዛ» በተሰኘው ፊልም በግሪክ ታሳሎንኪ፣ በፈረንሳይ አሚየንስ፣ በቱኒዝያ ካርቴጅ፣ በሮተርዳም፣ በቡርኪናፋሶ፣ በቶሮንቶ የሥነ ርዕይ ትርዒቶች ላይ የተቀበሏቸው ሽልማቶች በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

በጉማ ሽልማት ላይ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ የሆኑት ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ፤ ምንም እንኳ ሽልማቱን ለመቀበል በአገር ውስጥም ሆነ በአዳራሹ መገኘት ባይችሉም፤ የኪነጥበብ ባለሙያው ሙያውን እንዲወድና ሕዝቡን እንዲያከብር መልዕክታቸው ለታዳሚው ደርሷል።

ከዚህ ባሻገር በነበሩት አሥራ ስድስት ዘርፎችና ሁለት ልዩ ሽልማቶች የፊልም ባለሙያዎች የድካማቸውን ፍሬ አሳይተዋል፤

ላደረጉት አስተዋጽኦም ምስጋናን ከጉማ ሽልማት ተቀበለዋል። በዚህ መሰረት «በእናት መንገድ» የተሰኘው የበኃይሉ ዋሴ /ዋጄ/ ፊልም ሦስት ሽልማት በመውሰድ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ «ሲመት»፣ «ወደ ኋላ» እንዲሁም «ሚስቴን ዳርኳት» እያንዳ ንዳቸው በሁለት ዘርፎች ሽልማቶችን ወስደ ዋል።

በዘንድሮ የጉማ ፊልም ሽልማት ከመደበ ኛዎቹ ዘርፎች በተጓዳኝ በአጭር የተማሪዎች ፊልም አማኑኤል ዘሪሁን (ሙኑመ እረከበ) እንዲሁም በምርጥ አጭር ፊልም የአብስራ ዶጮ (ሌላው ጀግና) ተሸላሚ ሆነዋል። በተቀሩት ዘርፎች አሸናፊዎቹ የሚከተሉት ናቸው፤

በምርጥ ድምጽ አናኒያ ኃይሉ (ድንግሉ)፤

በምርጥ የፊልም ሙዚቃ ድምፃዊ መሳይ ተፈራ፣ ዜማ አህመድ ተሾመ /ዲንቢ/ እና ግጥም ወንደሰን ይሁብ (ሚስቴን ዳርኳት)፤

በምርጥ የፊልም ስኮር ሱልጣን ኑሪ (በሲመት)፤

በምርጥ የፊልም ሜክአፕ መሰረት መኮንን (በሲመት)፤

በምርጥ የፊልም ስክሪፕት በኃይሉ ዋሴ (ዋጄ) በእናት መንገድ፤

በምርጥ የፊልም ቅንብር (editing) ልኡል አባዲ (ወደ ኋላ)፤

በምርጥ ፊልም ቀራፂ (Cinematography) እውነት አሳሳኸኝ (ውሃ እና ወርቅ)፤

በምርጥ ተስፋ የተጣለባት ሴት ተዋናይት ሕፃን ማክቤል (ሞኙ ያራዳ ልጅ ቁጥር 4)፤

በምርጥ ተስፋ የተጣለበት ወንድ ተዋናይ በኃይሉ እንግዳ (ጃሎ)፤

በምርጥ ሴት ረዳት ተዋናይት ዘነቡ ገሠሠ (ትህትና)፤

በምርጥ ረዳት ተዋናይ ካሳሁን ፍስሀ ማንዴላ (ወደ ኋላ)፣

በምርጥ ሴት መሪ ተዋናይት ሶኒያ ኖዌል (አንድ እኩል)፤

በምርጥ ወንድ መሪ ተዋናይ ኤርሚያስ ታደስ (አላበድኩም)፤

በደሌ ስፔሻል የተመልካቾች ምርጫ (ሚስቴን ዳርኳት)፤

ምርጥ የሥራ መሪ (ዳይሬክተር) በኃይሉ ዋሴ (በእናት መንገድ)፣

የዓመቱ ምርጥ ፊልም (በእናት መንገድ) አሸናፊ ሆነዋል።

ጉማ ይቀጥልየጉማ ፊልም ሽልማት በበጎ ጎን እንደ

ሚነሱ ብዙ መልካም ነገሮቹ ሁሉ ቢስተካከሉ የሚባሉ ነገሮችንም በቀላሉ መታዘብ እንችላለን። ከዚህ መካከል አንዱና ዋነኛው የሰዓት አጠቃቀም ጉዳይ ነው። ምንም እንኳ ይህ እንደ አገር ሁላችንም የምንወቀስበት ችግር ቢሆንም እንዲህ ያሉ ትልቅ የሚባሉ ክዋኔዎች ግን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መጠበቃችንና መጠየቃችን አይቀርም።

በስፍራው የባከነ ሰዓት አለ ለማለት ባልደፍርም፤ የመክፈቻና የመርሃ ግብሩ መጀመሪያ ሰዓት ቀደም ቢል ግን ነገሩ ቀላል ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው። 6ኛው የጉማ ሽልማት እንግዶቹን ከ11፡00 ጀምሮ ተቀብሎ ልክ 12፡00 ሰዓት ላይ በአጫዋች ሙዚቃዎች አቆይቶ ዋናው መርሃ ግብር የጀመረው ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ነው። ሰዓቱ ቀደም ቢል ምናልባት ፎቶ የሚነሱት ባለሙያዎች ሰፊ ጊዜ ያገኛሉ፤ በዝግጅቱ ማብቂያም ላይ አዳራሹን ለቅቆ ለሚወጣ ታዳሚ ነገሩ አስቸጋሪ አይሆንበትምና ይህ ቢስተካከል እንላለን።

ተዋናይና የፊልም ባለሙያው ደሳለኝ ኃይሉ ከዚህ ቀደም ስለ ጉማ ፊልም ሽልማት ተጠይቆ ነበር። እርሱም ሲመልስ ጉማ የፊልም ሽልማት ስነ-ስርዓት አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የቪዲዮ ፊልሞች ምርት መሰረት የጣሉትን ሰዎች ያስታወሰ፤ በዳኝነትም ቢሆን አንጋፋ የፊልም ተዋናዮችን ታሳቢ ያደረገ መድረክ ነው ብሏል።

የጉማ ፊልም ሽልማት መሥራችና የፊልም ባለሙያው ዮናስ ብርሃነ መዋ በበኩሉ፤ በንግግሩ ለዝግጅቱ መሳካት ድጋፋቸው ላለተለየው ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል። 5ኛው የጉማ ሽልማትን ባተተው መጽሔት ላይ በሰፈረው ሃሳቡ ደግሞ በየዓመቱ ሳይታክቱ የሽልማት ዝግጅቱን ለሚያግዙ ምስጋናን አቅርቧል። ጉማ የፊልም ሽልማት ይዟቸው የተነሳው ሃሳቦችና ግቦች በየዓመቱ እየጠነከሩ፣ እየተሻሻሉ እና እየተስፋፉ መምጣታቸውንም አንስቶ፤ «ጉማ ሁሌም ይቀጥላል» ብሏል። እኛም አልን፤ ወደፊት እየተራመደ እንጂ ስንዝር ሳይመለስ ጉማ ይቀጥል። ሠላም!

ጉማ የፊልም ሽልማት...ይቀጥል!

Page 6: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 7

ጽጌረዳ ጫንያለው

የሰለጠኑ አገራት የማደጋቸውና የሥልጣኔያቸው መነሻም ሆነ መድረሻ ታሪካቸውን ማወቅ፣ መማርና መጠበቅ ነው። በታሪክ አጋጣሚ የተከወኑ መጥፎ ስህተቶች እንኳን ቢኖሩ ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ከሚያስተምሩበት መንገድ አንዱ ታሪክን ጽፎ ትውልድ እንዲያውቀውና እንዲማርበት ማድረግ ነው።

ታሪኩ የተከናወነበትን ቦታ በመከለል፣ አክብረውና ተንከባክበው በማቆየት ትውልድ ከዚያ ታሪክ መልካሙን እንዲያበለጽግ፣ ከስህተቱ ደግሞ እንዲማር ያደርጋሉ። ታሪኩን ለአዲሱ ትውልድ እየነገሩም ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ ይደረጋል። የተፈጠረው ታሪክም በጎ ይሁን አስከፊ በኩራት «ታሪካችን ነው» ሲሉ ይደመጣሉ። የብዙ ሺ ዓመታት መልካም ባህሎችና ታሪኮች ያላት ኢትዮጵያ ግን ታሪክ ነጋሪ ቅርሶቿን እየተንከባከበች አይደለም።

ለዚህ እንደማሳያ በዋናነት የምናነሳው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ የሚገኘው የፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ቤተመንግሥት ነው። ይህ ቤተ መንግሥት ስለ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ መስዋዕትነት የሚተርክ ቋሚ ምስክር ነው። ሆኖም ማንም ቅርሱን የሚንከባከብ፣ ስለታሪኩም የሚናገር ስላልነበረ ዛሬ እንዳልነበር ሆኗል። ይህንን ታሪካዊ ቦታ ከአካባቢው ተወላጆችና በስፍራው ካሉ ነዋሪዎች በቀር የሚያውቀው የለም። ላለመታወቁ የመጀመሪያው ምክንያት የመንገድ አለመኖር ነው።

ያም ሆኖ ግን የመንገድ አለመኖር ችግር ሳይሆንባቸው ጥቂት የማይባሉ ከተለያዩ አገራት የመጡ የውጭ ዜጎች ጎብኝተውታል፤ ምክንያቱም ለታሪክ የሚሰጡት ቦታ ከፍ ያለ ነውና። ይህንን ቦታ ለተመለከተው ደግሞ ማንም ሊርቀው አይወድም። ይሁንና በሚገባ ባለመታወቁ የቱሪስት መዳረሻ ሊሆን አልቻለም። ፈልጎ ማየትስ ለምን አልተቻለም ከተባለ ቸልተኝነት ከሚለው ውጪ የሚገልጸው አይኖርም። ምክንያቱም ቦታው ከጊንጪ ከተማ ብዙም አይርቅም። የጥርጊያ መንገዱን ይዞ ሽር ላለ ብዙም መንገድ ሳይጎዳው ይህንን ታላቅ የታሪክ ቦታ ይጎበኛል።

ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ በዳግማዊ ምኒልክ መንግሥት ጦር ስር ከተራ ወታደርነት ተነስተው እስከ ጦር ሚኒስትርነት የደረሱ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው። በምክር አዋቂነታቸው እና በፍርድ ችሎታቸውም «አባ መላ» በሚል ቅጽል ስም እስከመጠራት የደረሱም ስለመሆናቸው ብዙ መላ ያበጁለትን ችግር በማንሳት የአካባቢው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በተካሄዱት በአብዛኛዎቹ ትልልቅ የጦር ዘመቻዎች የተሳተፉ፤ በኋላም በአድዋ ጦርነት ሲዋጉ የቆዩና ፊታውራሪ ገበየውን ተክተው የጦር አበጋዝ ሆነው ያገለገሉ ለመሆናቸው ታሪክ ይናገራል። የእኝህን የሀገር ባለውለታ ታሪክ ሊናገር የሚችለው ቤተመንግሥት ግን

የቤተመንግሥቱ «ጥሪ»

ዛሬ አይሆኑ ሆኖ ፈርሷል። ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ከእህቶቻቸው

ጋር አገርን ለማቅናት ነበር ወደ ምኒልክ ዘንድ የተወሰዱት። እህቶቻቸው ወደ ቤተሰብ ሲመለሱ እርሳቸውን በዚያ ምኒልክ አስቀሯቸውና በዚያው ኖሩ። ልጅነት ጭምር ስላለ ከአካባቢያቸው ተሰውረው እንዳይቀሩ በወቅቱ እናታቸው ሲሸኟቸው አንድ ነገር ብለዋቸው በአንገታቸውም ላይ ክታብ አስረው እንደተሰናበቷቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

“ስታድግና ስትማር ይህንን አንብበህ የት እንደነበርክና የማን ልጅ እንደሆንክ ታውቃለህ።” ሲሉ ነግረዋቸዋልም ይባ ላል። እርሳቸውም የተባሉትን ተግባራዊ ያደረጉት አድገውና ተምረው እንዲሁም በብዙ ሹመቶች ላይ ካለፉ በኋላ ነው። የአንገታቸው ክታብ ትውልድ ስፍራቸውን መርታቸው ሄዱ። ቦታው ላይ ሲደርሱ ግን ያሰቡትን ሁሉ አላገኙትም፤ እናታቸው በሕይወት አልነበሩም፤ አባታቸውን በማግኘታቸው ብዙም ሳይከፉ እርሳቸው የሚያስደስታቸውን ለማድረግ ቃል ገብተው መትጋት ጀመሩ። ቤተመንግሥቱ በትውልድ ቀያቸው ላይ የተሰራውም ለዚህ ነው። በራሳቸው በፊታውራሪው እንደተሰራም ይወሳል።

የፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ አራተኛ ትውልድና ቀደም ሲልም የአካባቢውን ቀበሌ በሊቀመንበርነት ያስተዳደሩት አቶ ታደለ

ደበበ ታሪኩን መለስ ብለው በማስታወስ ሲናገሩ፤ አቶ ዲነግዴ ልጃቸው ሦስት ነገሮችን እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋቸው ነበር። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እዚህ ቦታ ቤተመንግሥት እንዲያቆሙ ነበር። እርሳቸው የአባታቸውን ቃልአክብረው ቤተመንግሥቱን ቢያቆሙም ትውልዱ ግን የአባቶቹን ታሪክ ሊጠብቅ አልቻለም። ቃላቸውን አክባሪነታቸው፤ ለእያንዳንዱ ነገር መላ ሰጪነታቸውን አልተከተለም። አሁን ታሪክ ተረካቢ በመጥፋቱ፣ ባለቤት ነኝ የሚል ተቋም ባለመኖሩ ቅርሱ የቱሪስት መስህብ መሆን አልቻለም፤ ቤተመንግሥቱም እየፈራረሰ ይገኛል።

አባ መላ የመላ ባለቤት ቢሆኑም መላቸውን ተከትሎ ማንነታቸውን ሊነግርላ ቸው የሚችል ሰው መጥፋቱ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ታደለ፤ የሰዎች ማንነት የሚታወቀው በሰሯቸው ሥራዎች ቢሆንም በቅርስ መልኩ የተቀመጠና ለትውልድ የሚተላለፍ መሆን አለበት። ይህ ደግሞ ስለ እርሳቸው አገሬው ብቻ ሳይሆን ዓለምም ጭምር ታሪኩን እንዲያውቅ ዕድል ይሰጠዋል። ነገር ግን የእርሳቸውን መርህ መከተል ያልቻለው ትውልድ ቤተመን ግሥቱ እስኪፈርስ ጠብቆታል ይላሉ።

«ቤተመንግሥቱ የተለያዩ የአገር ባለውለታዎችን የሸሸገ ነው። እነ ራስ ሚካኤል ዓመታትን ያሳለፉበት እንደነበረም ይነገርለታል። በተለይ በግዞት የነበሩ ትልልቅ

የዘመኑ ሹማምንት ብዙ ቆይተውበታል» ያሉት ደግሞ የአካባቢው ተወላጅ አዛውንት አቶ ዳመነ ኃይሉ ናቸው። በቤተመንግሥቱ ውስጥ ሙሉ የጥንት ቅርሶቸ እንደነበሩ እርሳቸው የዓይን እማኝ እንደሆኑ ይናገራሉ። ይሁንና ይህም ዛሬ የለም። ማን እጅ ውስጥ እንዳለ አይታወቅም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የተለያየ እንደሆነ ያነሳሉ። የአካባቢው ሰው ስለ ታሪካዊ ቅርሶች የሚያውቀው ነገር ያለመኖሩ፤ ስለቤተመንግሥቱ ታላቅነትም ማንም አለመናገሩና ስለቅርስ ምንነት የሚያስተምር በአካባቢው ዘንድ ስለሌለ የነበሩ ቅርሶች ሁሉ ሲጠፉ ሀይ ያለ አልነበረም ሲሉ ይቆጫሉ።

የአካባቢው ማህበረሰብ ቤተመንግሥቱ ያለበትን ስፍራ መንከባከብ ትቶ ቦታውን እያሰፋ ለራሱ የእርሻ መሬት እያደረገው ይገኛል። ለዚህም በዋናነት ተወቃሹ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ መሆኑን ይናገራሉ። አሁንም ለዚህ ቤተመንግሥት መኖር የሚያስፈልገው ወሬ ሳይሆን ተግባር ነውና የድረሱልኝ ጥሪውን ሁሉም ይስማና መፍትሄ ይስጠው ሲሉ ያሳስባሉ።

«አካባቢው ለአዲስ አበባም ሆነ ለኦሮሚያ ክልል ከተሞች በጣም ቅርብ ነው። ከጊንጪ ትንሽ ጉዞ ተደርጎ የጠጠር መንገዱ 12 ኪሎ ሜትር ብቻ ነው የሚኬደው። ይሁንና ማንም ዝር ብሎበት አያውቅም። ስለዚህም ታሪክን በታሪክ መክፈል ይገባልና ዛሬ ላለን ቅርስ እንድረስ። ትውልድ ወቃሽና አስወቃሽ እንዳንሆንም

እንስራ» ሲሉም አባ ገዳዎች በእንባ ጭምር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተለይ በቱሪዝም ዘርፍ የሚሰሩ ባለሙያዎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ቢሮዎች ሀብቱን በማሳወቅ ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት።

የደንዲ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽሕ ፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባንቲ ለሚ ዘርፉን ከተቀላቀሉ አጭር ጊዜያቸው መሆኑን ይናገራሉ። በመሆኑም በወረዳው ያሉትን ሀብቶች በሙሉ ለማየትና የድጋፍ ሥራ ለመስራት አልቻልኩም ይላሉ። አሁንም ቤተመንግሥቱ በዚህ ደረጃ ወድቆ መመልከታቸው እጅጉን አሳስቧቸዋል። ከጉብኚዎች እኩል ሰሞ ኑን ቤተ መንግሥቱን ማየታቸውም ትክ ክል እንዳልሆነ ይጠቅሳሉ። በቀጣይ ለመ ማርና ከስህተት ለመታረም ጥሩ ዕድል ይሰጣል፤ ችግሮቹ የሚፈቱበትን ሁኔታ ለማመቻቸትም ተነሳሽነት እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በዚህ ቦታ በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም ሀብቶች መኖራቸውን ዛሬ በስፋት እንዳዩ ገልጸውም፤ ቦታው ባለመታወቁና ባለመታየቱ ምክንያት ቤተመንግሥቱ የመፍረስ አደጋ ደርሶበታል። ስለዚህ ብዙ ተግባር ማከናወን እንዳለብን ተረድተናልም ብለዋል። በዚህ ዕድል መነሻነትም በቀጣይ በጥልቀት አይቶ ለመስራት ይሞከራል። ከዚህ በኋላ በአጭር ጊዜ ጥገና እንዲደረግና ሀብቱን ወደ ገንዘብ የመለወጥ ተግባር እንደሚከናወንም ቃል ገብተዋል።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ልማት ቡድን መሪ አቶ አበራ ታደሰ እንደተናገሩት፤ በ2010 ዓ.ም በቦታው ላይ የቱሪዝም ቀን ተከብሯል። ቀደም ሲል ቦታው አይታወቅም ነበር። ይህም ቤተመንግሥቱ ዛሬ ላለበት ሁኔታ እንዲበቃ አድርጎታል። ሁኔታው በጣም ያሳዝናል። እኛም አለማየታችንና አላማሳወቃችን ለውድቀት አጋልጦታል። በመሆኑም የመጀመሪያ እርምጃ መሆን ያለበት የመንገድ ግንባታው ነውና እርሱ ላይ ይሰራል። በዚህ ዓመት በጀት አልተያዘም። ያለዕቅድ መስራት ደግሞ አዳጋች ነው። ስለሆነም እየተመካከርን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል።

ለቤተመንግሥቱ አለመታወቅና መፈራረስ ሁሉም ምክንያት ያሉትን ቢደረድሩም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ታሪክን እየፈለገ ለትውልድ እንዲታወቅ አለማድረጉ ሰፊ ችግር ሆኖ ይታያል። ዛሬ እርቃኑን የቆመው ቤተመንግሥትም ለታሪክ መጥፋት አንዱ ምስክር ነው።

በወቅቱ አምስት ትልልቅ ግቢዎችና እርከኖችን አልፎ ዋናው ቤተመንግሥት ውስጥ እንደሚገባ የተነገረለት ቤተመንግ ሥት ዛሬ ያለከልካይ ዘው ብሎ ይገባበታል። ቤተመንግሥቱ ምንም ዓይነት በርና መስኮት የለውም። ይባስ ብሎ ቤቱን በምሰሶነት የያዘው እንጨት ሳይቀር ተነቅሎ ይታያል። በአጠቃላይ አጽመ ታሪኩ ቀርቷል። እኛም ትውልድ ይፍረደኝ አቤቱታውን አይተንና ሰምተን «እንታደገው» አለን። ሰላም!

ፎቶ

- በፅ

ጌረዳ

ጫንያ

ለው

ሐመር - የ‹‹ካራ ፣ኦሪ ፣መርሲ›› ውህድ

በመፈራረስ ላይ የሚገኘው የፊታውራሪ ሀብተጊየርጊስ ዲነግዴ ቤተመንግስት

በጋዜጣው ሪፖርተር

የሐመር ብሔረሰብ በደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ ብሔረሰቦች አንዱ ሲሆን በዋናነት በዞኑ ውስጥ በሐመር ወረዳ ይኖራል። ሐመሮች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ‹‹ሐመር አፎ›› በማለት የሚጠሩ ሲሆን፣ ሌሎች ግን ‹‹ ሐመርኛ›› ይሉታል። ሀመር በኦሞአዊ የቋንቋ ቤተሰብ ሥር የሚመደበው ሲሆን የብሔረሰቡ አባላት ከራሳቸው ቋንቋ በተጨማሪ የ1በና፣ የአርቦሬ፣ የካራ እና የዳሰነች ብሔረሰቦች ቋንቋዎችን በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ። የሐመር ቋንቋ ከንግግር ወይንም ከመግባቢያነት አልፎ የትምህርት ወይም የሥራ ቋንቋ ለመሆን አልበቃም።በ1999 ዓ.ም በተደረገ የሕዝብና ቤቶች የቆጠራ ውጤት መሠረትም የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 46ሺ532 መድረሱ ይታወቃል።

‹‹ሐመር›› የሚለው ቃል የብሐረሰቡ መጠሪያ ቃል በብሔረሰቡ ቋንቋ ‹‹በተራራ እና በድንጋይ መካከል የሚኖሩ፣ የተዋሃዱና የተቀላቀሉ ሕዝቦች›› የሚል ፍቺ እንዳለውና ይህም ትርጉም ታሪካዊ መሠረት እንደያዘ ከብሔረሰቡ አዛውንቶች የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሞ ዊኪፒዲያ የተሰኘ ድረ ገጽ አስነብቧል። ይህ ትውፊት ሐመሮች ከጥንት ዘመን አንስቶ በትላልቅና ሰንሰለታማ ተራሮች መካከል የሚገኙ የተቦረቦሩ ቋጥኞች ውስጥ ይኖሩ እንደነበር የሚያመላክት እንደሆነ የመረጃ ምንጩ አትቷል። የብሔረሰቡ አባላት ዋነኛ መተዳደሪያ ከብት እርባታ ሲሆን፣ ከዚህ

ጐን ለጐን ንብ በማነብ እና በዝቅተኛ ደረጃ ደግሞ በቆሎና ማሽላ ለዕለት ፍጆታ በማምረት ኑሮአቸውን ይመራሉ።

የብሔረሰቡ ታሪካዊ አመጣጥ ጥንት ከ ‹‹ካራ››፣ ከ‹‹ኦሪ›› እና ከ‹‹መርሲ›› በመጡ የተለያዩ ማህበራዊ ቡድኖች ውህደት የዛሬው የሐመር ብሔረሰብ እንደተገኘ ከብሔረሰቡ ታዋቂ ግለሰቦችና የሀገር ሽማግሌዎች የተገኘ አፍአዊ መረጃ ያስረዳል። ከእዚህ የትውፊት መረጃ እና ከላይ የተጠቀሱትን አራት መነሻ ሥፍራዎች መሠረት በማድረግ ብሔረሰቡ ውስጥ ስድስት ማኀበራዊ ቡድኖች መኖራቸውን ይናገራል። ‹‹ቶርቶሮ›› የሐመር ብሔረሰብ አባላት በአመት አንድ ጊዜ አደባባይ በመውጣት የሚያከብሩት ባህላዊ በዓላቸው ነው።

የሚከበረውም በሰኔ ወር መባቻ በእሸት ወቅት ነው። በዓሉም በድግስና በጭፈራ ይከበራል። የጭፈራው ዋነኛ ተዋናዮችም ያገቡ ወጣቶች ጎልማሶችና አዛውንቶች ሲሆኑ ፣ ያላገቡ ወጣቶችና ኮረዶች ሚና ደግሞ ድግሱን በማዘጋጀትና በማስተናገድ ላይ የተወሰነ ነው። ‹‹ኢቫንጋዲ ›› የሐመር ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች ብቻ የሚሳትፉበት ባህላዊ ጭፈራ ነው። ጭፈራውም በየሦስት ቀን አንዴ እያሰለሰ በሐመር መንደሮች በምሽት ጨረቃ ይካሄዳል።

‹‹ኢቫንጋዲ›› በአዝመራ ወቅት በሥራ የደከመን አእምሮና አካል ለማዝናናት ሲባል የሚደረግ ባህላዊ ጭፈራ ነው።የሐመር ወጣቶች ከማህበራዊ ሕይወት ጋር

የሚተዋወቁበት አዳዲስ ባህላዊ ዘፈኖችና የአጨፋፈር ስልቶችን የሚቀስሙበት አጋጣሚ ነው። ከእነዚህ በተጨማሪ ሐመሮች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ምክንያት በማድረግ የሚጫወቱት ‹‹ኤሬ›› የተባለ ባህላዊ ጨዋታ አላቸው። ኤሬ ወደ ሌላ አካባቢ ወይም ወደ ዘመቻ ለመሄድ ሲታሰብ በፉከራ መልክ የሚከወን ባህላዊ ጨዋታ ነው። የሐመሮች ባህላዊ ቤት ከእንጨት የሚሠራ ሲሆን፣ ጣሪያው በሣር ይከደናል።ነብሳት በግድግዳ ላይ እንዳይራቡ ለመከላከል በሚል ግድግዳው በምንም አይመረግም። ባህላዊ ቤቱ የውስጥ

ክፍሎች የሌሉት ልቅ በመሆኑ የቤት ውስጥ የመገልገያ ቁሳቁስ ከቆጥ ላይ ይሰቀላል። በቤት ግንባታው ሂደት ዋነኛውን ሚና የሚጫወቱት ወንዶች ሲሆኑ፣ ሴቶች ደግሞ በሣር አቅርቦት ይሳተፋሉ።

የአመጋገብ ስርዓት ‹‹ሙና መቱቆ›› ወይም ኩርኩፋ፣ ‹‹

በላሽ›› ወይም በማሽላ ቂጣ፣ ‹‹ዳንጵደ›› ወይም ፎሰሴ እና ዝጉ ወይም ከማሽላና ከበቆሎ የሚዘጋጅ ቂጣ ዋነኛ የሐመሮች ባህላዊ ምግቦች ናቸው። ‹‹ፐርሴ›› (ቦርዴ) እና ‹‹አላ›› (የማር ብርዝ) ደግሞ

ባህላዊ መጠጦቻቸው ናቸው። የአመጋገብ ሥርዓታቸውን በተመለከተ የቤቱ አባወራ ከሁሉም ቀድሞ ይመገባል ። እናት በመጨረሻ ለብቻዋ የምትመገብ ሲሆን፣ አንዳንዴም ከልጆቿ ጋር ትመገባለች። ሆኖም ግን አባወራው በምንም አጋጣሚ ከመጀመሪያ ወንድ ልጁ ጋር አይመገብም፤ ይህን እንዳይፈጽም ባህላዊ ሥርዓቱ እንደሚከለክለው የብሔረሰቡ አዛውንቶች ይናገራሉ።

የዚህ ብሔረሰብ አብሮ የመኖር ጥበብ ባህልን እንደ አገር ብንጠቀምበት፤ተቻችሎ ለመኖር፣ ለመከባበር፣ ለአንድነት እና ለሰላም እንዲሁም ፍትሃዊነትን ለማምጣት ይጠቅማል። አገራችን ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ የሆኑ ብሔር ብሔረሶች የሚኖሩባት እንዲሁም ህዝቦቿ ያለ ምንም የዘርና የቋንቋ ልዩነት ተጋብተው እና ተዋልደው ያቆሟት ውህድ የብሔረሰቦች ስብስብ አገር ናት። አሁን ባለንበት ወቅት እዚህም እዚያም ጊዜ እየጠበቁ የሚነሱ ግጭቶች፣ መፈናቀሎች፣ ዋልታ ረገጥ የሆኑ አስተሳሰቦች እንዲሁም «እኔ እና የእኔ ብቻ» ከሚል ግለኝነት ለመውጣት ከሐመሮች ባህል ብዙ ልንማር ይገባናል።

አንደኛው የሌላውን መብት እያከበረ፣ እየተቻቻለ እና የወንድማማች መንፈስን እያዳበረ በፍቅር ለፍቅር መኖር እንደሚቻል ካሉን ወርቃማ ባህል እና እሴት ካላቸው ብሔረሰብ የሐመር ባህል አንዱ ማሳያ ነው። እኛም ያሉንን ባህላዊ እሴቶቻችንን በመጠቀም ለአገር አንድነት እና ሰላም ልንሰራ ይገባል እንላለን። ሰላም!

የሐመር ገበያ

Page 7: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

መገቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 9

ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት ሙያና በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ሕይወታቸውን አሳልፈ ዋል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችም ከመጀመ ሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ በመምህ ርነት ሠርተዋል፤ በአመራርነትም አገልግለዋል። በሚጽፏቸው ጽሑፎችና በሚያደርጓቸው ንግግሮች እንዲሁም በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በርካታ ውጣ ውረድ አጋጥሟቸዋል። በእስር ቤት ስቃይና እንግልት ቀምሰዋል። በአሁን ወቅት በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል እየተረዱም ደግሞም ባላቸው ዕውቀት እና ልምድ በጉዳይ አስፈጻሚነት፣ በእንግዳ ተቀባይነት እያገለገሉ ይገኛሉ። የዛሬ የ‹‹ሕይወት እንዲህ ናት›› እንግዳችን አቶ ተከስተ ብርሃን መንክር፤ መልካም ንባብ!ልጅነት - ከጎንደር እስከ አዲስ አበባ

በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ነበር ብርቱ፤ የአልሸነፍም ባይነት ምሳሌ የሆኑት አቶ ተከስተ ብርሃን መንክር በ1938 ዓ.ም የተወለዱት።ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም አባታቸው ካህን ስለነበሩ ዳዊት እንዲደግሙ ከጥንታዊው የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ትምህርት ጣዕም እንዲቀምሱ የተወሰነ ጥረት ቢያደርጉም እርሳቸው ግን ወደ ዘመናዊው ትምህርት ተሳቡ።

ቤተሰቦቻቸው ዝቅተኛ በሚባለው የኑሮ ደረጃ ውስጥ ሆነው እንዳሳደጓቸውም ያወሳሉ።በተለይ እናታቸው ጠላ እየሸጡ የቤተሰቡን ኑሮ ለማቆም ይታትሩ ነበር። ትምህርታቸውን በጥንካሬ ለማስኬ ድም ቤተሰቦቻቸው ጫና እንዳይሰማቸው “ፒስኮር” የተሰኘ ከአሜሪካ የመጣው እና የተቸገሩ ዜጎችን የሚረዳውን ድርጅት ተቀላቀሉ።“የፒስኮር ጓድ” በመሆን እና ከእነርሱም ጋር በመተባበር አንዳንድ ሥራዎችን በመሥራት ራሳቸውን ለመደገፍ ጥረዋል። አምስተኛ ክፍል እስኪደርሱ ድረስ ለእግራቸው ጫማ እንኳን እንዳልነበራቸው የሚናገሩት አቶ ተከስተብርሃን ስድስተኛ ክፍል ሲገቡ “ከፒስኮሮች” በአራት ብር ሸራ ጫማ ገዝተው ማድረግ እንደጀመሩ ያስታውሳሉ። እጀጠባብ ይለብሱ፤ ቁምጣም ይታጠቁ ነበር።

የተማሩት በጎንደር ፋሲለደስ ሲሆን በትምህር ታቸው እጅግ ጎበዝ ነበሩ፤ እስከ ስምንተኛ ክፍል በነበራቸው ቆይታ የክፍል ደረጃቸው ከአንደኛነት ዝቅ አላሉም።በጊዜው የእንዲህ ዓይነት ጎበዝ ተማሪዎች መጠሪያ እንደአሁኑ ‹‹ሰቃይ›› ሳይሆን ‹‹ሸምዳጅ›› ነበርና ይሄን ስም ለማግኘት የካህኑ አባታቸው ቃላዊ የሆነው የትምህርት እና የማስተማር ዘይቤ ጠቅሟቸዋል።

በዚያ የትምህርት ጅማሬ ዘመናቸው የሚታተሙ መጻሕፍትን ያነባሉ።ዛሬ ድረስ ላላቸው የማንበብ ፍቅርም መሠረቱ በዚያን ጊዜ የተጣለ እንደሆነ ነው የሚያስቡት።ይህ ሁሉ ሆኖ የአንደኛ ደረጃ እና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲያገባድዱ የጎንደር እህል ውሃቸውም ለጊዜው ተቋረጠ።ቀጣዩ የትምህርት ጉዟቸው ማዕከል አዲስ አበባ ሆነች።

አዲስ አበባ በ1962 ዓ.ም ሲደርሱ የንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተከፈተበት ጊዜ ነበር።ያኔ ታዲያ በዚያ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ቀጠሉ።በጊዜው የነበረው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ጠንካራ ስለነበር ትምህርትን በጥንካሬ ለመወጣት መትጋት የግድ ነበር።በጊዜው በትምህርት ቤት ውስጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ንቁ ተሳታፊ የነበሩት አቶ ተከስተብርሃን የሻይ ክበብ፣ የውይይት ክበብ፣ የጋዜጠኝነት፣ የሥነ ጽሑፍ ክበብ ወዘተ እየተባሉ በሚቋቋሙ ተጓዳኝ ትምህርት እና ስልጠና ክበባት ንቁ ተሳታፊ ነበሩ። በተለይ የነበራቸው የተሻለ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንግግር ችሎታ ተማሪዎች እና መምህራኑን ቀልብ ይስብ እንደነበር ያስታውሳሉ።

በሀገራዊ ጉዳዮች ቀጣዩ የትምህርታቸው ምዕራፍ ኮተቤ የሚገኘው

መምህራን ኮሌጅ ሆነ። አቶ ተከስተ ብርሃን ኮሌጁን የተቀላቀሉት በኢትዮጵያ የዘውድ ሥርዓት ላይ ታላቅ ተቃውሞ እየተቀሰቀሰ በነበረበት፣ የለውጥ ጥሪዎች በመላው ሀገሪቱ እየተስተጋቡ በመጡበት በ1966 ዓ.ም ነው። በአቶ ተከስተ ብርሃን ታሪክ ውስጥ በሀገራዊ ጉዳዮች አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉበትን ዕድል ያገኙት ገና ወደ ኮሌጁ እንደተቀላቀሉ ነበር።በነበራቸው ንቁ ተሳታፊነት ምክንያት የተማሪዎች ፕሬዚዳንት በመሆን የኮሌጁ ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ ለመዘወር ሰፊ ዕድል አገኙ።

በዚያን ጊዜ ኃላፊነትን መቀበል ቀላል አልነበረም፤ ሰፋ ያለ የፖለቲካ ግንዛቤና አመለካከት ያስፈልጋል። ከዚያ ባለፈ ደግሞ ጥላሁን ግዛው በ1962 ዓ.ም ከሞተ በኋላ በኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መማክርት እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ ከመቆየቱም በላይ ፕሬዚዳንት መርጠው የሚንቀሳቀሱበት ዕድል አልነበረም። በ1966 ዓ.ም ግን በድጋሚ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ መደራጀት እና በአግባቡ መምራቱን ቀጠለ።

በዚያን ጊዜ የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር አቶ ሚሊዮን ነቅንቅ ይባላሉ።እርሳቸው የሚመሩት መሥሪያ ቤት በአጋጣሚ “ሴክተር ሪቪዉ” የሚባል ትምህርት ፖሊሲ በአሜሪካን ኤክስፐርቶች ተጠንቶ ተዘጋጅቶ ቀረበ።ፖሊሲው ትምህርትን እስከ አራተኛ

ክፍል የሚገድብ ሆኖ የተዘጋጀ ነበር።ፖሊሲው የደሃ ልጆች በትምህርት እንዳይገፉ፣ የፊውዳል ልጆች ብቻ በትምህርቱ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ እና የሀገሪቱንም የኢኮኖሚ ልማት የሚጎዳ ነው በሚል ተቃውሞ ተነሳበት።ያንን እንቅስቃሴ በኮሌጅ ደረጃ የሚመሩት ደግሞ አቶ ተከስተ ብርሃን ነበሩ።

ሌላው ከፖሊሲ ጋር ተያይዞ በመንግሥት በኩል የነበረው ችግር በሀገሪቱ ከነበሩ አራት የመምህራን ኮሌጅ ተምረው የሚወጡ ተመራቂዎች ወደ ሥራ ዓለም ሲገቡ የሚስተናገዱበት ፍትሐዊ ያልሆነ አሠራር መታየቱ ነው።በጊዜው የነበሩት አራቱ የመምህራን ማሰልጠኛዎች ሐረር፣ አሥመራ፣ ኮተቤ እና ደብረብርሃን ነበሩ።በእነዚህ ማሰልጠኛዎች ውስጥ መምህራን የሚሠለጥኑበት ሁኔታ ሁለት መልክ ነበረው።አንዱ ዐሥር ሲደመር ሁለት እና ዐሥራ ሁለት ሲደመር አንድ ነበር።ደብረ ብርሃን ዐሥር ሲደመር ሁለት በሚባለው መንገድ ከዐሥረኛ ክፍል ተቀብሎ ለሁለት ዓመታት የሚያሠለጥን ሲሆን፣ ሌሎቹ ግን በዐሥራ ሁለት ሲደመር አንድ የሚሠለጥኑ ነበሩ።

ያንን መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ ሲታይ ግን ከደብረ ብርሃን ለሚመረቁት 230 ብር ከሌሎቹ ተቋማት ለሚወጡት ግን 153 ብር ይከፈል የሚል ዕቅድ ተዘጋጀ።እናም ለዕኩል ሥራ የተለያየ ክፍያ መፈጸም ተገቢ አይደለም በሚል ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። የዚህ እንቅስቃሴ በኮተቤ ኮሌጅም እንዲስፋፋ ካደረጉት ሰዎች አንዱ አቶ ተከስተ ብርሃን መንክር ነበሩ።

አቶ ተከስተ ብርሃን በተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዴት ንቁ ሆነው ይንቀሳቀሱ እንደነበር ሲያስታውሱ «ይህ ጉዳይ በተማሪዎች መካከል የውይይት ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ እያለ አጋጣሚ ጃንሆይ ወደ ሰንደፋ ለጉብኝት እንደሚሄዱ ሰማሁ፤ የሚያልፉት በእኛ በኩል ስለሆነ፤ ተማሪዎችን አስተባብሬ መንገድ ዘግተን ባንዲራ አንጥፈን ጠበቅናቸው።እንቅስቃሴያቸውን የማገት ያህል ነበር፤ ወደ ኮሌጁ ገብተው ለማነጋገር ተገደዱ።

ጃንሆይ ብዙ ጊዜ ጉብኝት ሲያደርጉ አንድ፣ አንድ አዳዲስ ብር የማደል ልምድ ነበራቸው፤ እርሱን ለማግኘት የሚደክሙ የሚለፉ ብዙዎች ናቸው፤ ከተቀበሉ በኋላ ለዘመናት እንደ ቅርስ ይዘውት እንደሚቆዩ አውቃለሁ።እርሳቸውም ተማሪዎችን አሰልፈው ብር እየሰጡ ሳለ መካከል ላይ እኔ ዘንድ ሲደርሱ ‹አልቀበልም› አልኳቸው፤ ከንጉሡ ገንዘብ አልቀበልም ማለት በዚያን ጊዜ ከባድ ነገር ነው፤ ክብር ለመስጠት ግን እግራቸው ላይ ወድቄ ነበር፤

‹ምንድነው ችግርህ?› አሉኝ፤ ‹ግርማዊነትዎ አቤቱታ አለኝ› አልኳቸው። ያን ጊዜ ጀግናው አብዲሳ አጋ በጡረታ ጊዜው የእርሳቸው አጃቢ ሆኖ አብሯቸው ይንቀሳቀስ ነበር፤ እንደዚያ የተቃውሞ ስሜቴን ሲረዳ ከሌሎች አጃቢዎች ጋር ሆኖ ሳብ አድርጎ ወደ ጎን አቆመኝ፤ ንጉሡ ብር ሰጥተው እስኪጨርሱ መጠበቅ ነበረብኝ።

መጨረሻ ላይ ‹ምንድነው ችግርህ?› አሉኝ፤ እኔም ‹ግርማዊ ሆይ እኔ የተማሪዎች ወኪል ነኝ፤ በእርስዎ ግዛት ውስጥ ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል መታየት ሲገባው እኛ ግን መብት መጓደል ደርሶብናል፤ በተለይ ከዚህ ዓመት ተማሪዎች ጀምሮ ደመወዝ ክፍያ ላይ እኩል እንዳንሆን የሚያደርግ መመሪያ ወጥቶብናል፤ ይህ እንዲስተካከልልን ለመጠየቅ እንፈልጋለን› አልኳቸው።በዚያን ጊዜ አቶ ተካልኝ ሰሎሞን የሚባሉ ምክትል ሚኒስትር ነበሩ።እርሳቸውን ተጠርተው ጠዋት ቤተ መንግሥት እንዲመጡ አድርጓቸው ብለው አዘዟቸው።» በማለት የሆነውን ያስታውሳሉ።

እንደተባለውም አቶ ተከስተብርሃንና ሌሎች የተማሪ ተወካዮችን ደብዳቤ ጽፈው ጠዋት በጋራ ወደ ቤተ መንግሥት ተጓዙ።ከአቶ ተከስተ ብርሃን ጋር የነበሩት የተማሪዎች ተወካዮች ሦስት ነበሩ።በቤተመንግሥት የሆነውን ሲያወሱ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፤

«በዚያን ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱ በአፍሪካ በነበራቸው ክብር እና የመሪነት ሥፍራ ምክንያት የሦስተኛው ዓለም /የአፍሪካ/መሪ ኮከብ ይባሉ ስለነበር እኛም በደብዳቤያችን መግቢያ ‹የአፍሪካ/የሦስተኛው ዓለም/ አንጸባራቂ መሪ ኮከብ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ……› የሚለውን ክብር ሰጥተን ነበር።ከዚያም በደብዳቤው የመምህራን የደመወዝ አቤቱታ በሥርዐት ተካቶ ነበር።አቤቱታችንን በንባብ አሰማን።»

የተማሪዎች አቤቱታ በቤተመንግሥት ከቀረበ በኋላ ንጉሡ አማካሪዎቻቸውን እነራስ መስፍን ስለሺ፣ አክሊሉ ሀብተወልድ፣ ብላታ አድማሱ ረታ እና ሌሎች የትምህርት ሚኒስቴርም ሰዎች በነበሩበት በጉዳዩ ተወያዩበት። ከዚያ ውይይት በኋላ ውሳኔ እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶ በክብር መሸኘታቸውን ይገልጻሉ።

«አሁን ሂዱ ተባልን፤ በሦስተኛው ቀን ውሳኔው መጣ። ደመወዛችን ከ153 ብር ወደ 182 ብር ተሻሽሎ እንዲከፈለን ነው ውሳኔው። ለአራቱም መምህራን ማሰልጠኛዎች በዚሁ መንገድ እንዲከፈል ተደረገ። በዚህ የለውጥ እና የማሻሻያ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ነበረኝ።» ይላሉ።

የሥራ ዓለምአቶ ተከስተብርሃን በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ

የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው በኅብረተሰብ ትምህርት ተመርቀው ወደ ሥራው ዓለም ሲገቡ

የተመደቡበት ክፍለ ሀገር አርሲ ነበር።ወዲያውኑ እንደተመረቁ የአርሲዋ አሰላ በክብር ተቀበለቻቸው።

በትምህርት ዓለም እያሉ የነበራቸው ንቁ የዜግነት እና የኃላፊነት ስሜት ሳይለያቸው በደረሱበት በአሰላ ከተማ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አቋቁመው በዚያ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር በመሆን ማገልገል ጀመሩ።ያቋቋሙት ትምህርት ቤት «ቲቢላ» ይባል ነበር።

እናም በዚህ የሥራ ኃላፊነታቸው ሳይወሰኑ አድማስ የሚሻገር ሀገራዊ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉበት አደረጃጀት ውስጥ መሳተፋቸውን ቀጠሉ፤ ያም አደረጃጀት የመምህራን ማኅበር ነበር።ስለዚህ ገና በትምህርት ተቋም እያሉ ያደርጉት የነበረውን ለሙያተኞቹ የመታገል ጅምር አጠናክረው ቀጠሉ።ማኅበሩ በየዓመቱ ስብሰባ ያዘጋጅ ስለነበር እርሳቸውም የመሳተፉን ዕድል ያገኙ ነበር።

በ1967 ዓ.ም የመምህራን ማኅበሩ በጂማ ከተማ ጉባኤ አዘጋጅቶ ነበር።በዚህ ረገድ የሚያስታውሱት የ1966 ዓ.ም የእርሳቸውን ዘመነኛ ተመራቂዎችን በመወከል ማኅበሩ አዘጋጅቶት በነበረው ጉባኤ ተሳትፈው ነበር።ከዚያም ቀጣዩ ነቀምት ላይ ሲዘጋጅ በዚያም ተሳትፈዋል።በዚያ ጉባኤ ከተደረጉት ነገሮች የማይረሱት ‹‹ዘውድና ሕገ መንግሥት›› የሚል አንድ የመፍትሔ ሃሳብ ተዘጋጅቶ ነበር።

ደርግ ጃንሆይ ከስልጣን ሲወርዱ በንባብ ያሰማው የድል መግለጫ ያኔ መምህራን ማኅበር ነቀምት ላይ ያረቀቀውን ነበር።ታዲያ! ለአቶ ተከስተብርሃን ከሚቆጯቸው የሕይወት አጋጣሚዎች አንዱም ሆኖ ይጠቅሱታል።በዚያ የመፍትሔ ሐሳብ ረቂቅ ዝግጅት ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው ዛሬ ይቆጫቸዋል።ምክንያቱም ጊዜውን ያገናዘበና ችኩልነት የተሞላበት ዕርምጃ ስለነበር ነገሩን ዛሬ ላይ ሲያጤኑት የጸጸት ስሜት ያሳድርባቸዋል።

የሥራ ዓለማቸው ደግሞ በአርሲ ሳይወሰን በጅማ፣ በሐረርጌ ክፍለሀገር ተዘዋውረው ሠርተ ዋል። በኋላ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ለመማር ዕድሉን ባገኙ ጊዜ ሶሲዮሎጂ ተምረው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1972 ዓ.ም ያዙ።ወዲያውም ተመልስው የተመደቡትም ወደ አርሲ ክፍለ ሀገር ነበር።በዚያ በመምህርነት መሥራታቸው እንዳለ ሆኖ የመምህራን ማኅበር ረዳት ጸሐፊ ሆነው ማገልገል ጀመሩ። ከመምህርነቱም ባሻገር ፖለቲካዊ ሥራዎች የሚያመዝኑበት እንቅስቃሴ ለማድረግ ተገደዱ።በጊዜው የወጣውንም የመፍትሔ ሃሳብ ለማስተግበር በየቦታው መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነበር።በየትምህርት ቤቶችም መመላለስ ግድ ነበር።

በዚህ ውጣ ውረድ ውስጥ እንቅስቃሴው በፈረስ በበቅሎ ስለነበር ይፈትናሉ።በተደጋጋሚም ከበቅሎ መውደቃቸውን ያስታውሳሉ።በአርሲ የፈረቀሳ/ወምባ/ን ተራራማ እና ኮረብታማ ስፍራዎች እንዴት እንደተመላለሱባቸው አይዘነጉም።የሚያስገርማቸው ደግሞ ይህ ሁሉ ተግባር ሲከናወን እንቅስቃሴቸው ያለምንም ከፍያ የሚፈጽሙት ነበር።በጊዜው ከ8-12 ብር አበል ይከፈል ነበር፤ ይሁን እንጂ ኑሮው ለክፉ የሚሰጥ ስላልነበር ለሁሉም እንቅስቃሴ ተከታትሎ፣ ተጠያይቆ አበል ለመውሰድ አይንደረደሩም።

በጊዜው መምህር የሚከበርበት ዘመን ስለነበር ከአስተዳዳሪ እስከ ተማሪ ሁሉም በአቅሙ ጋባዥ እና ተንከባካቢ ነበር።በሂደት የአቶ ተከስተብርሃን ሀገራዊ ተሳትፎ ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ ሆነ።ይህ ሁሉ የሆነው እስከ 1976 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ነበር።

የዩኒቨርሲቲው መምህር ከዚያ በኋላ ስለሆነው ደግሞ እንዲህ

እያሉ ያወጉናል፤ «በ1976 ዓ.ም ላይ የውጭ የትምህርት ዕድል አግኝቼ ወደ ጀርመን ሄድኩ።» በዚያም የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሶሲዮሎጂ ሠሩ።ቀጥለውም አሉ፤ «ተመልሼ በባህርዳር ፔዳጎጂካል ስኩል ሱፐርቫይዘር ሆኜ ሠራሁ።ከዚያ በኋላም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ለአራት ዓመታት አገለገልኩ።”

አቶ ተከስተ ብርሃን ይናገራሉ የ1970ዎቹ መጨረሻ የ1980ዎቹ መጀመሪያ በሀገሪቱ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ውጥረት ነበር፤ በዚያን ወቅት ከጎንደር አካባቢ ወደ በረሃ ሄደው ደርግን ለመጣል ይታገሉ ለነበሩ ሰዎች ድጋፍ ይሰጡ ነበር።ጎንደር እያሉ የራሳቸውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጉ

ነበር።በተለይ ዛሬ ከፍተኛ ሹማምንት ከሚባሉት እና ደርግን ለመጣል ከታገሉ ግለሰቦች ታዋቂዎቹን ወደ በረሃ በመላክ በኩልም ተሳትፎ ማድረጋቸውን ያወሳሉ።

ፈታኝ ዘመንበኋላ ነገሮች አልፈው በ1983 ዓ.ም ሥርዓቱ

ሲለወጥ ጡረታ ወጡ። በጊዜው የተወሰነ ገንዘብ ስለነበራቸው በአንዳንድ ኢንቨስትመንት ሥራዎች ውስጥ ለመሳተፍ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ።ጡረታ ሲወጡም ያለፍላጎታቸው /በተጽእኖ/ እንደነበር ይጠቅሳሉ።ከለውጡ በኋላ ለሰባት ዓመታት በእስር ቤትም ቆይተዋል።

ይህ ጊዜ ግን ለአቶ ተከስተ ብርሃን ቀላል አልነበረም።በእስራት እና በእንግልት ማሳለፋቸው ለጤና ችግርም አጋልጧቸዋል።በተለይ ደግሞ ወደ ኢንቨስትምንቱ ሲገቡ ለጊዜው ሊገልጹአቸው ባልፈለጓቸው አንዳንድ ምክንያቶች ሳይሳካለቸው መቅረቱ ለአዕምሮና ለስኳር ሕመም እንደዳረጋቸው ያስታውሳሉ።

ከኢንቨስትምንቱ የተረፋቸውን ገንዘብም ያዋሉት የስኳር ሕምማቸውን ለመታከሚያነት ነው።አሳዛኙ ነገር ከህመማቸው ጽኑነት የተነሳ ሳይደክሙ ለአንድ ሰዓት በተከታታይ የሜዳ ቴኒስ ይሯሯጡበት የነበረ እግራቸውን ለመቆረጥ ተገደዱ።በዚያም ምክንያት አንድ እግራቸው ተቆረጠ።«ይህ በፈጣሪ ፈቃድ የሆነ ነው» ይላሉ።

ከሆስፒታል ከወጡ በኋላ ማዘር ቴሬዛ የእንክብካቤ ማዕከል ገቡ።ለአንድ ዓመት በእዚያ ቆዩ። ‹‹መሐል ላይ የመቄዶንያ መሥራች የክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ባለቤት ወ/ሮ እሌኒ ገብረኢየሱስ ታሪኬን ሰምታ ልትጎበኘኝ መጣች፤ አዋየችኝ። ከዚያ ከማዘር ቴሬዛ ብወጣ መጨረሻዬ ጎዳና ላይ መውጣት ነበር።እግሬን ከተቆረጥኩ በኋላ የምሔደው በዊልቼር ነው።ከዚያ በምክር ወደ መቄዶንያ መጣሁ።በጊዜው እጅግ በጣም ሰውነቴ ተጎድቶ ነበር።ስኳር ሲጀምረኝ አንደ መቶ ዐሥራ ሦስት ኪሎ ነበርኩ ፤ያን ጊዜ ግን ከጉዳቴ ብዛት የተነሣ አርባ አምስት ኪሎ ሆኜ ነበር።በዚህ በመቄዶንያ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ተደረገልኝ። በተጨማሪ ለተቆረጠ እግሬ ሰው ሠራሽ እግር አስተከለልኝ እኔም እየዳንኩ መጣሁ።»

ዕድሜ ያልገደበው ተሳትፎአቶ ተከስተ ብርሃን ዛሬ ዕድሜ ሳይበግራቸው፤

ህመም ሳይፈትናቸው በትልቅ የሥራ ኃላፊነት ተሰማርተው በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በጉዳይ አስፈጻሚነትና በእንግዳ ተቀባይነት እያገለገሉ ይገኛሉ።

«እኔ አሁንም ሀገሬን እያገለገልኩ ነው። ሀገርን ሲያገለግሉ ኖረው፤ ዛሬ በእርጅና በድካም፣ በሕመም፣ በማጣት ለመረዳት በዚህ ማዕከል የገቡትን ማገልገል ራሱ ሀገርን ማገልገል ነው።ብዙዎቹ ትናንት ቤተሰብ ነበራቸው፣ እኔ ነኝ ያሉ ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱን በማገለገል እበረታለሁ።» ብለውናል።ያላቸውንም ቀሪ የሕይወት ዘመን ለዚህ በጎ ሥራ ሰጥተዋል።

አቶ ተከስተብርሃን በሕይወታቸው የተረዱት አንድ ታላቅ ነገር አለ፤ ይሄውም «የአካል መቆረጥ

አብርሃም ተወልደ

ወይም ገንዘብ እና ንብረት ማጣት የሕይወት ፍጻሜ አለመሆኑን።» በእርግጥም ከዚያ ወጥተውም ዛሬ ላይ የአረጋውያን ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ናቸው።«ትናንት ሞቼ ነበር።ከዚያ ተነስቼ አሁን አለሁበት ደረጃ ከደረስኩ አረጋውያንን በማገዝ መቄዶንያን በማገልገል እኖራለሁ፤ ይህ ለእኔ አዲስ ሕይወት ነው፤ ከዚህ በላይም ደስታ ሊኖረኝ ወይም ላገኝ አልችልም።» ይላሉ።

ለምን? ያለ ቤተሰብ«ለምን ቤተሰብ ሳይመሠርቱ ኖሩ?» የአቶ

ተከስተብርሃን መልስ ተከታዩ ነበር፤ «በእርግጥ በዕጣ ፈንታም አምናለሁ።ይሁንና… ከሁለተኛ ዲግሪዬ በኋላም የፒኤች ዲ ትምህርት ለመከታተል እቅድ ነበረኝ፤ በጊዜው በነበረኝ ስሌት ቤተሰብ ያልመሰረትኩትም ከዛሬ ነገ እያልኩ ነበር፤ የፍቅር ጊዜ ሰጥቶ፣ በአግባቡ አግብቶ ወልዶ ለማሳደግ ጊዜ አልነበረኝም።

ንባብ እና ፖለቲካ ተጫጭኖኝ ኖሯል።ለሰዎች በቂ ምክንያት ላይመስል ቢችልም ለእኔ ግን ጊዜ አልነበረኝም።አንዳንዴ ደግሞ ለምን ብዬ ስጠይቅ ለራሴም የማይገባኝ ምስጢር አለ፤ ወልዶ መሳም የሚገባ እና የተሟላ ስብእና መገለጫ ሆኖ እያለ ወደ ዚያ ያልደረስኩበት ምስጢር ለምንድነው የሚለውን ልረዳው አልችልም፤ቁጭትም ይፈጥርብኛል።»

የንባብ ሕይወትሌላው የአቶ ተከስተብርሃን ማራኪ የሕይወታ

ቸው ገጽታ አንባቢነታቸው ነው። 870 መጻሕፍትን ማንበባቸውን ይናገራሉ። ዛሬም እንኳን በእጃቸው 840 መጻሕፍት አሏቸው። በማደሪያ ክፍላቸው በክብር ተቀምጠዋል።ማንበብ መማር እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ተከስተብርሃን አሁንም ዘርፈ ብዙ ዕውቀትን ትምህርት ቤት ሳይሄዱ ከመጻሕፍት ገብይተዋል፤ እየገበዩም ነው።

መልዕክትና ምክርአቶ ተከስተብርሃን የቀጣዩ ትውልድ ዕጣ ፈንታ

ያሳስባቸዋል።ስለዚህ ለትውልዱ የሚሰጡት ምክር አለ፤ «ከሀገር የበለጠ ምንም ነገር የለም፤ ሁሉም ሰው ሀገሩን ቢያስቀድም ደስ ይለኛል። አንድ ሀገር ያላት ዋናው ሀብት ህዝብ ነው፤ የህዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ ደግሞ ዋናው ሰላም ነው፤ እስከዛሬም ያለንን ሀብት በአግባቡ መጠቀም ያልቻልነው ሰላም ስላልነበረን ነው፤ ኢትዮጵያ አንድነቷ ከተጠበቀ ሰላም ካላት የማታድግበት ምንም ምክንያት የለም።

ስለዚህ ቀጣዩ ትውልድ ለሀገሩ ቅድሚያ ይስጥ። ቀደም ሲል ‘ቻይናዎች ጠፍር ይበሉ ነበር’፤ ዛሬ ላይ ግን ከፍተኛ ደረጃ ደርሰዋል፤ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ለአሜሪካ 65 ሺህ ዶላር ዕርዳታ የሰጠችበት ጊዜ ነበር፤ኢትዮጵያ አሜሪካንን ረድታለች፤ ዛሬ ግን የት ነው ያለነው? ያንን ማስቀጠል አልተቻለም። ይህንን ትውልዱ ሊያስብብት ይገባል። ነገ ኢትዮጵያ አሜሪካንን የምትረዳበት ዘመን እንደሚመጣ ተስፋ አድርጋለሁ፤ ይሄንን እውን የሚያደርገው ይህ ትውልድ ነው።ይህ የሚሆነው ለሀገር በማሰብ እና ፍቅር እና ሰላምን ማጽናት ከተቻለ ነው።›› ብለዋል። እኛም ዕድሜ ከጤና ጋር ያብዛልዎት አልን። ሰላም!

የመምህር ተከስተብርሃን መንክር - አዲስ ህይወት

ፎቶ

፡-

በፀሐ

ይ ን

ጉሤ

ከሀገር የበለጠ ምንም ነገር የለም፤ ሁሉም ሰው ሀገሩን ቢያስቀድም ደስ ይለኛል። አንድ ሀገር ያላት ዋናው

ሀብት ህዝብ ነው፤ የህዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ ደግሞ

ዋናው ሰላም ነው፤...

Page 8: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

መዝናኛ መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ ዘመን 11

በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር በመተበባር በየሳምንቱ እሁድ የሚቀርብ

በቅርቡ በብሔራዊ ቴአትር አንድ መድረክ ተዘጋጅቶ ልታደም ሄጄ ነበር። በእርግጥ በብሔራዊ ቴአትር የሚዘጋጁ መድረኮች ላይ ብዙ ጊዜ ሄጃለሁ። እንዲያውም ይሄ አሁን የምነግራችሁ ገጠመኝ ያጋጠመኝ ብዙ ጊዜ በመሄዴ ነው። ከዚያ በፊት ግን መድረኩ ምን መሰላችሁ? የወግ፣ የዲስኩር እና የግጥም ሥራዎች የሚቀርቡበት ነው። በተለይ በዲስኩር ደግሞ በጣፋጭ ንግግሮቻቸው የሚታወቁት እነ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና ዑስታዝ አቡበከር ቀድመው ተዋውቀዋል።

እነዚህ ሰዎች ያሉበት ብዙ መድረክ ታድሚያለሁ፤ እዚያው ብሔራዊ ቴአትርም ታድሜያለሁ። እንደሚታወቀው እነርሱ አሉ ከተባለ አዳራሹ ይሞላል፤ ቢሆንም ግን መቆሚያ መቀመጫ የለም እስከሚባል አይደለም።

የሰሞኑን መድረክ የተሸወድኩበት ምክንያት እንዲህ ነው!

መድረኩ 100 ብር መግቢያ አለው። የሚጀመረው 11፡00 ነው። በክፍያ መሆኑን ሳውቅ ምን ተሸወድኩ መሰላችሁ? ክፍያ ስላለው ሰው አይበዛም፤ ስለዚህ ቦታ አይጠፋም ብዬ ተሸወድኩ። በነፃ በሚገባባቸው መድረኮች እስከመጨረሻው ትርፍ ወንበር እንዳለ ሳስተውል ነው የቆየሁ። እናም 11፡00 ለሚጀመረው

ፕሮግራም 10፡30 ደረስኩ(በኔ ቤት ቀድሜ መድረሴ ነበር!) ስደርስ ሁለቱም አቅጣጫ አሞራ ዞሮ የማይጨርሰው ሰልፍ አለ። ሌላም ነገር አለ ይሆን ብዬ ተጠራጥሬ ስጠይቅ ያው እኔው የመጣሁበት ጉዳይ ነው። ከተጀመረ በኋላም እንኳን መቀመጫ መቆሚያም አልነበረም። ያለምንም ማገነን ከኋላ ያሉ ሰዎች ምንም ማየት ስላልቻሉ ተመልሰው ወጥተዋል።

የብሔራዊ ቴአትሩን ይህን ያህል ከነገርኳችሁ አይበቃም? እንዲያው ነገር ስለማንዛዛ እንጂ ዋና ጉዳዬ እኮ ስለዚያ መድረክ አልነበረም። ቢሆንም ግን ቀጥሎ ከማወራው ጋር ስለሚገናኝ መግቢያ ቢሆነኝ ብዬ ነው(መግቢያው እንዲህ የረዘመ ዋናው እንዴት ሊሆን ነው እንዳትሉ?)

ባህሪያችን ሆኖብን የተወደደ ነገር እንወዳለን። ይሄ የነገርኳችሁ ገጠመኝ እኮ ብዙ ጊዜ በነፃ ሲቀርብ የነበረ ነው። ክፍያ አለው ሲባል ግን ሰው በጣም በዛ። በዚያ ላይ ደግሞ አብዛኛው ጥንድ ጥንድ የሆነ ነው። እርስበርስ እየተገባበዙ መሆኑ ነው(አቤት ግብዣ ስንወድ!) በቃ ግብዣ ነው ከተባለ እኮ የምንወደውን ነገር ራሱ እንወደዋለን አይደል? በግብዣ ነበር እኛን የአዲስ አበባን ቆሻሻ ማስጠረግ!

አንድ ነገር በነፃ ከሆነ ፍላጎታችን ይቀንሳል። እንኳን በነፃ ዋጋው ዝቅተኛ የሆነ እና ከፍተኛ የሆነ ራሱ ይለያያል። አገልግሎቱ አንድ ዓይነት ቢሆን ራሱ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ነው ደስ የሚለን። ለምሳሌ የልብስ ምርጫችንን ልብ በሉ። የሚታየው ጥንካሬው መሆኑ ቀርቷል። በቃ ዋጋውና እነማን ለብሰውታል የሚለው ነው ሚታይ!

የምግብ ምርጫችንንም ልብ በሉ! በነገራችን ላይ እነዚህ ኮንቴነር ውስጥ ያሉ በተለምዶ ‹‹ማዘር ቤቶች›› የሚባሉ ምግብ ቤቶች በጣም ነው የሚጣፍጡ! ፍርፍርና ሽሮ። ኢንተርናሽናል

ሆቴል ውስጥ ከምጋበዝ እነዚህ ቤቶች ውስጥ ከፍዬ ብበላ ይሻለኛል። አሁን እኔ ታዋቂ ወይም ሀብታም ብሆን ብላችሁ አስቡት፤ እነዚህ ቤቶች ገብቼ ብበላ ሰው ምን ይለኝ ነበር? አያችሁ አይደል ልማዳችንን?

ደግነቱ ፈጣሪ ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በተፈጥሮ የሚገኙ አደረገልን እንጂ እንደ እኛ የተወደደ ነገር መውደድ ቢሆን ኖሮ ድሃ አልቆ ነበር። እስኪ አስቡት! ውሃ በኢንተርናሽናል ሆቴል ውስጥ ብቻ የሚገኝ ቢሆን፣ አየር የሚገዛ ቢሆን ምን ይበጀን ነበር?

የተወደደ ነገር እንወዳለን። እንዲያውም አሁን አሁን ሳስበው ደራሲዎች የመጽሐፍን ዋጋ ከፍተኛ ያደረጉት ለብሩ ሳይሆን በብዛት እንዲሸጥላቸው ይመስለኛል። ግደላችሁም እውነትነት አለው። እስኪ እንገምት! አንድ ጥልቅ የፖለቲካ ትንታኔ ወይም የአገሪቱን ጓዳ ጎድጓዳ ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ታተመ እንበል። ይሄ መጽሐፍ ‹‹በነፃ የሚታደል›› የሚል በደማቁ ቢጻፍበት የሚወስደው ያለ ይመስላችኋል? ከዚያ ይልቅ በአንድ ጀንበር የተጻፈ መጽሐፍ ከፍተኛ ዋጋ ቢጫንበት በርብርብ ይገዛል።

እኔ እኮ ግን ያልገባኝ ነገር! እዚህ ጋ ‹‹አጣን! ተቸገርን! ኑሮ ተወደደ!›› የሚል ሮሮ አለ። እዚህ ጋ ደግሞ በአነስተኛ ዋጋ ለዚያውም ለጤና ተስማሚ የሆነ ምግብ እያለ ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ለቁርጠት የሚዳረግ ሰው አለ።

ሰውነትን ከብድርም ሆነ ከፀሐይ የሚከላከል፣ ጥንካሬ ያለው ልብስ በአነስተና ዋጋ መግዛት እየተቻለ ቁራጭ ልብስ በከፍተኛ ዋጋ ገዝተው ፀሐይና ብርድ የሚፈራረቅባቸው አሉ። ይሄ ሁሉ የሆነው እንግዲህ የተወደደ ነገር ስለምንወድ ነው።

በነገራችን ላይ የተወደደ ነገር መውደዳችን በዋጋ ላይ ብቻ አይደለም። እስኪ ነገሩን ወደ

ሰውም እናምጣው። ታዋቂ የሆነ ሰው እንወዳለን። አንድ ታዋቂ ያልሆነ ሰው የቱንም ያህል ምርጥ ንግግር ቢያደርግ፣ የቱንም ያህል ማራኪ ጽሑፍ ቢጽፍ፤ አንድ ታዋቂ የሆነ ሰው የተናገረው ወይም የጻፈው ትርኪ ምርኪ ነገር የበለጠ በሰዎች ዘንድ ይዳረሳል።

ጥቅስ ተብለው በየግድግዳው የተለጠፉ፣ በየንግግሩና በየጽሑፉ የመግቢያ ማጣፈጫ የተደረጉ ‹‹የእገሌ አባባል›› ተብለው የሚጠቀሱ ሃሳቦችን ልብ ብዬ አስተውላለሁ። አንዳንዶቹ የጎረቤታችን ሽምግሌዎች ሲናገሩት የምሰማው ነው። አንዳንዶቹም ማንም ሰው ሊላቸው የሚችል ቀላል ትርጉም ያላቸው ይሆኑብኛል። የተናገራቸው ሰው የአገር መሪ ከሆነ (በተለይም የኃያላን አገር)፣ ታዋቂ ከሆነ ሃሳቡ የተለየ ትርጉም የሰጠ ይመስለናል። ያንኑ አባባል አንድ ተራ ግለሰብ ሲለው ብንሰማ ግን ከምንም አንቆጥረውም። ፌስቡክ ላይ እንኳን ያለውን ነገር ልብ በሉ!

ብዙ ተከታይ ያለው ሰው ምንም ተራ ነገር ይጻፍ ብዙ ወዳጅና ተጋሪ አለው። በእርግጥ ፌስቡክ ላይ ብዙ ተከታይ የሚኖረው ሰው መጀመሪያ በሌላ ነገር ታዋቂ ከሆነ ነው። ለምሳሌ በቴሌቪዥን ታዋቂ ከሆነ፣ ወይም በፖለቲካም ይሁን በሌላ ነገር ሰው ካወቀው ነው ብዙ ተከታይ የሚኖረው። ይሄ እንግዲህ የሚያሳየን ሃሳብ ዓይተን እንደማናደንቅ ነው። የምናደንቀው ሌላ ሰው ሲያደንቀው ስላየን ነው። ምናልባት በዚህ ልማዳችን ይሆን ፖለቲካችንም የመንጋ ጋጋት የበዛበት?

በነገራችን ላይ የተወደደ ነገር የሚበረታታባቸው ብዙ ልማዶች አሉን። እስኪ አሁን ደግሞ የጠላ ቤት አመራረጥን ልንገራችሁ (አይ የገጠር ልጅ ነገር!) ሰዎች የጠላን ጥራት

የተወደደይወደዳል!

ዋለልኝ አየለ

ሞገስ ተስፋ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት

ላይ የባቡር ትራንስፖርት አሻራ ዕድሜ ጠገብ ቢሆንም የዕድሜውን ያህል ሳይስፋፋ ቆይቷል:: ይህም በኢትዮ ጅቡቲ መስመር ላይ ተወስኖ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል። በወቅቱም ስለኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር አርቲስቶች እንዲህ ሲሉ አቀነቀኑለት፣<< እልም አለ ባቡሩ ወጣት ይዞ በሙሉ>> እያሉ ልክ አባት እና እናት ልጆቻቸውን በመናፈቅ የተለየ የፍቅር ስሜት እንደሚፈጥርባቸው ሁሉ የባቡር መስመሩም በእንክብካቤና በዜማ ታጅቦ ቢመጣም አይናፋር ሆኖ ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በአዲስ ምዕራፍ የባቡር መሰረተ ልማቶች የመገንባትና አገልግሎት ላይ የሚውሉበት ሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወሰንበት ሥርዓት መዘርጋት የሚያስፈልግ በመሆኑ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 55(ሐ) መሰረት ታውጇል:: በዚህ አዋጅ መሰረትም የባቡር አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1048/2009 ተብሎ ተጠቅሷል። ስለሆነም በዚህ መሰረት የትራንስፖርት አገልግሎቱን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ ሲባል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሰራ ይገኛል። የዚህ አንዱ አካል የሆነው ደግሞ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ነው።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በመዲናይቱ ለሚታየው ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ሁነኛ አማራጭ ለማድረግ የተገነባ ነው። ይህ ግንባታም ዕውን የሆነው 85 በመቶ ከቻይና መንግስት በተገኘ በ475 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብድር የባቡር መስመሩ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሦስት ዓመት አስቆጥሯል። ይህ የቀላል ባቡር መስመር ከተማዋን በአራት አቅጣጫዎች ማለትም ከሰሜን- ደቡብ እና ከምስራቅ ምዕራብ በ34 ኪ.ሜ ርዝመት ላይ የተዘረጋ ሲሆን 39 የባቡር ጣቢያዎች አሉት። የአገልግሎት አሰጣጡም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4፡

ዘመናዊ የደህንነት ቁጥጥር ሥርዓት ለባቡር ትራንስፖርት ወሳኝ ነው

00 ሰዓት በአማካኝ በቀን 130ሺ ተሳፋሪዎችን በማስተናገድ በህብረተሰቡ ዘንድ ተመራጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

ለዚህ አገልግሎት ደግሞ ሁነኛ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። ስለሆነም የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በሚፈለገው መጠን አገልግሎቱን ለማሳለጥ የሚያስችል የመቆጣጠሪያ ሥርዓት በመዘርጋት ስራውን ያከናውናል። ይህ የቁጥጥር ስራ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት የመቆጣጠሪያ አገልግሎት ኃላፊ ከሆኑት አቶ ብስራት ዘውዱ ጋር የነበረንን የቃለ መጠይቅ ቆይታ ለአንባቢያን በሚያመች መልኩ እንደሚከተለው አዘጋጅተን አቀረብነው።

እንደ አቶ ብስራት ገለጻ፣ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መቆጣጠሪያ ማዕከል ስራውን የጀመረው ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ስራው ከፍት በሆነበት ወቅት ነው። ማዕከሉ የባቡሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ተግባርና ሃላፊነቱን በብቃት እየተወጣ ይገኛል:: በዚህ የቁጥጥር ማቀፍ የመንገደኞችን ፍሰት፣ ደህንነትና ሌሎች ከአገልግሎቱ ጋር ተያይዘው ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን የመቆጣጠር ስራን ይተገብራል። ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠር ፍላጎቱን እና አቅርቦቱን አመጣጥኖ ለመጓዝ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት ትኩረት የተሰጠው ነው።

የቁጥጥር ማቀፉ የባቡሩን ደህንነት መረጃ በመሰብሰብና በመስጠት የደህንነት ራዳር ሆኖ ስለሚያገለግል ደህንነቱ ለተጠበቀ ትራንስፖርት እንደ መፍቻ ቁልፍ በመሆን መሰረታዊ የሆነ ተግባር ይሰራል። ምክንያቱም ይላሉ ኃላፊው፣ የቁጥጥር ሥርዓቱ የባቡሩ የዓይን ብሌን ሆኖ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው ይህ ማዕከል ነው። ለምሳሌ የደንበኞችን ፍሰት፣ ከባቡሩ የመጫን አቅም ጋር ያለውን ሂደት በመመልከት እንደአስፈላጊነቱም ሥርዓት ይዘው እንዲጓዙ መልዕክት በማስተላለፍና መቆጣጠር ነው። ይህም የሚከናወነው የጊዜ ሰሌዳ ተበጅቶለት በምን ያህል ፍጥነት፣ በስንት ሰዓት ከጣቢያው መውጣት እና መግባት እንዳለበትም ጭምር ክትትል ይደረጋል። ይህ ዘዴ በሁለቱም መስመር ያሉት ባቡሮች ያላቸውን ፍጥነት እንደአስፈላጊነቱ የሚወስንና የሚቆጣጠር ሰዓት ነው። በዚህ መሰረትም የሁለቱም ባቡሮች መዳረሻ ፍጥነት፣ የቃሊቲ ፒያሳ 15 ደቂቃ ሲሆን ሃያት ደግሞ 12 ደቂቃ ነው። ይህን ወደ ተመሳሳይ ፍጥነት ለማምጣት በመጨው መጋቢት ወር ላይ እኩል እንዲሆኑ እየተሰራ ነው።

አንድ ባቡር ማሳፈር ያለበት 312 ሰዎችን ቢሆንም ቅሉ ካለው የአገልግሎት ተጠቃሚ አንጻር ሲታይ ግን ከ500 በላይ ሰዎችን

በማጓጓዝ ላይ ይገኛል። ይህን አገልግሎት ተሳፋሪውን ከባቡሩ ቁጥር ጋር ለማጣጣም በዚሁ የቁጥጥር ማቀፍ ውስጥ ሆኖ ከሚመለከተው አካል ጋር እየተሰራ ነው። በዚህ የቁጥጥር ማዕከል የሚሰሩ ባለሙያዎች አገልግሎቱ በሚፈለገው መጠን እንዲከናወን የ24፡00 ሰዓት ስራ የሚሰሩ ሲሆን አንድ ባለሙያ 12 ሰዓት ሸፍኖ ይሰራል። በዚህ አግባበም ሰዓቱን አክብሮ የሚሰራ የሚበረታታበት፣ የማይሰራም እንዲሰራ የሚደረግበት የአሰራር ማዕቀፍ ከቻይና ተሞክሮ በመቀመር እየተሰራበት ያለ አንዱ የማጠናከሪያ ሥርዓት ነው። ይህ መሆኑ ደግሞ እግረ መንገዱን የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር እንዲከናወን አስችሏል ። ለዚህ ሁነኛ ማሳያውም በቻይናዎች ይመራና ይተዳደር የነበረው የአስተዳደር እንዲሁም የኦፕሬሽን ስራ አሁን ላይ በኢትዮጵያውያን ሙሉ በሙሉ መመራት ጀምሯል። በዚህ መሰረትም የባቡር እንቅስቃሴው ቁጥጥር በኢትዮጵያውያን መሰራት ከጀመረ ሁለት ዓመት አስቆጥሯል:: የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግሩም በባቡር አሽከርካሪነት፣ በባቡር ቁጥጥር ማዕከል፣ በባቡር ጥገና እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የሰው ሃይል በማሰልጠን በጥራት መስራት እየተቻለ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ተቋሙ ከጊዜው ጋር እንዲዘምን ለማድረግ

አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት በክህሎታቸውና በዕውቀታቸው ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በመመደብ በትኩረት እየሰራ ነው። ለዚህም አንዱ ማሳያው በቅርቡ ተጨማሪ 19 ረዳት የቁጥጥር ባለሙያዎችን ወደ ቻይና በመላክ ስልጠና ወስደው ወደስራ እንዲገቡ ተደርጓል:: ባለሙያዎች ቻይና ሂደው ስልጠና አግኝተው መምጣታቸው ስራውን በባለቤትነት እንዴት መስራት እንዳለባቸው ልምድ የቀሰሙበት ነው ብለዋል።

ባቡሩ ስምንት የታወቁ መቆጣጠሪያ ቦታዎች ያሉት ሲሆን በመስመሩ ላይ ክፍተት በሚፈጠርበት ወቅትም አስፈላጊውን የእርምት አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ቁጥጥና ክትትል ይደረግለታል። ስለዚህ ባቡሩ ችግር በተፈጠረበት ሰዓትም መስመሩ መሃል ላይ መዞር እንዲያስችለው የሚያደርግ ስራ በመኖሩ በከፊል አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል። በከፊል አገልግሎት እማይሰጥባቸው ቦታዎች ከስታዲየም እስከ ልደታ ሲሆን ይህም የሆነው መታጠፊያ ባለመኖሩ ነው። እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የሚያግዙ በ13 የማቋረጫ ጣቢያዎች የደህንነት ካሜራዎች ያሉ ሲሆን ከመቆጣጠሪያው ማዕከል ጋር በቅንጅት መስራታቸውን በዲስፕሌይ በማሳየት ይከታተላሉ። በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የኦፕሬሽን መቆጣጠሪያ ማዕከል ከሚከናወኑ ተግባራት መካከልም የተሳፋሪዎችን እንቅስቃሴ መቆጣጠርና መልዕክት እንዲደርስ ማድረግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የአገልግሎት አሰጣጣችን የሚፈለገው ደረጃ ላይ ስላልደረሰንና የህዝቡ የአገልግሎት ፍላጎት እየጨመረ ስለመጣ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋምና ባለድርሻ አካላት የቻሉትን ያህል ዕሴት ቢጨምሩ መልካም ነው:: በቴክኖሎጂው ዘርፍም ፍላጎት ያላቸው ሰዎች አብረው ቢሳተፉ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል። በተለይ የአካባቢ ውበትና የአረንጓዴ ልማት ላይ ቢሰራ መልካም ነው በማለት ኃላፊው መልዕክት አዘል ሃሳባቸውን አስተላልፈዋል።

አቶ ብስራት ዘውዱ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የመቆጣጠሪያ ማዕከል

የሚለኩት በጠላ ቤቱ ውስጥ ባሉት ሰዎች ብዛት ነው። በጠላ ቤቱ ውስጥ ብዙ ሰው ካለ ጠላው ጥሩ ነው ማለት ነው፤ ትንሽ ከሆኑ ግን አይረባም ማለት ነው።

ገጠርን ምሳሌ ያደረኩት አዲስ አበባ ለዚህ ምሳሌ ስለማይመች ነው፤ ምክንያቱም እንኳን ምግብ ቤትና መጠጥ ቤት መንገድ እንኳን ስትሄድ በወረፋ ነው። ስለዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የተጨናነቀ ቦታ ቢታይ የጥራት ምልክት ሳይሆን የሕዝብ ብዛት ችግር ነው። በዚያ ላይ ደግሞ የሚጠጣውም ሆነ የሚበላው ነገር ተመሳሳይ ስለሆነ ሙያ የሚለካበት አይደለም። ለምሳሌ ጃምቦና ቢራ የትም ቢገቡ አንድ ዓይነት ነው። ስለዚህ የወረፋ ሱስ ካልሆነ በስተቀር ሰው የበዛበት ቦታ መሄድ አይጠበቅብንም ማለት ነው። ለነገሩ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሰልፍ ሱስ አለበት። ግደላችሁም ማሳያ አለኝ። የ10 ደቂቃ መንገድ ለመሄድ 30 እና 40 ደቂቃ የሚሰለፍ ሕዝብ እኮ ነው ያለው!

በታክሲ ሰልፍ ላይ አማራጭ እንኳን አይጠቀምም። ለምሳሌ ከመገናኛ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የሚፈልግ ሰው መተባበር ሕንፃ ጋ ይሰለፋል። የካ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ምንም ሰልፍ የለም። ሌላው ልዩነት ደግሞ ልብ በሉ። መተባበር ሕንፃ ጋ ያሉ ታክሲዎች በአራት ኪሎ አንሄድም እያሉ ጭቅጭቅ ነው፤ ከክፍለ ከተማው ፊት ለፊት የሚነሱት ግን የግድ በአራት ኪሎ ነው የሚሄዱት። ሰው ግን ይሄን አማራጭ አይጠቀምም። በሁለት ወይም ሦስት ደቂቃ የሚደርሰውን ግማሽ ሰዓት ቆሞ ይሰለፋል። እንዲህ ነን እንግዲህ! የግድ ሰው የበዛበት ብቻ ነው ሚታየን።

እባካችሁ ሰዎች የተወደደ ነገር ብቻ አንውደድ!

Page 9: 78 የሥራን ክቡርነትን በተግባር - press.et · መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ግንባታው

24 መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም

• ለኤችአይቪይበልጥተጋላጭነን!

እንመርመርራሳችንንእንወቅ።

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

የማዘውተሪያ ስፍራ የፈተነው የሰርከስ ስፖርትዳግም ከበደ

እአአ 1768 ፍሊፕ አስትሌ የተባለ እንግሊዛዊ ለዘመናዊው ዓለም አንድ አዲስ በትርዒት የታጀበ እና ተመልካችን ያስደነቀ ትእይንት አስተዋ ወቀ። በስፖርቱ እና በመዝናኛ መድረኮች ላይ ልዩ ተቀባይነት ያለው ይህ የመድረክ ትእይንት በሰፋፊ ድንኳኖች ውስጥ ከከፍታ ላይ በተንጠለጠሉ ገመዶች የጅምናስቲክ (ትራፔዝ)፣ የአክሮባት፣የዳንስ፣በሚያዝናኑ አሻንጉሊቶች ፊትን በመሸፈን በትናንሽ ኳሶች ትእይንት ማሳየት፣ የሀስማት ጥበብ እንዲሁም የተለያዩ ስፖርታዊ እና አዝናኝ ዝግጅቶችን የሚቀርቡበት ነበር። በዘመናችን በስፋት ተቀባይነት ካገኙት የመድረክ ላይ ትእይንቶች የሚመደበው ሰርከስ።

ፍሊፕ አስትሌ ይህንን ስፖርታዊ ትእይንት ነው በዘመናዊ መንገድ እና በአዲስ አቀራረብ ከላይ በጠቀስነው ዓመት ለታዳሚዎች ማቅረብ የጀመረው። አስትሌ የሰርከስ ስፖርትን በቀዳሚነት የጀመረ ባይሆንም አዳዲስ ትርዒቶችን ማስተዋወቅ ስለቻለ «የዘመናዊው ሰርከስ አባት» በመባል ይታወቃል።

በወቅቱ አስደናቂ ከሆኑት ትእይንቶቹ ውስጥ «ትሪክ ራይዲንግ» ወይም ፈረሶችን ግርምትን በሚያጭሩ ድርጊት ውስጥ እየሆኑ መጋለብን አስተዋውቋል። በተለይ ደግሞ ሌሎች ትርዒት የሚያሳዩ ተቀናቃኞቹ ማድረግ ከሚችሉት በተሻለ በክብ ቦታ ላይ ግልቢያ ያደርግ ነበር። በኋላም እርሱ የጀመረው አዲስ ትዕይንት «ሰርከስ» የሚል ስያሜ ማግኘት ቻለ። በ1770 የተለያየ አስደናቂ ክህሎት ያላቸውን የሰርከስ ስፖርተኞች በመቅጠር ሥራዎቹን በስፋት ማቅረብ ጀመረ።

ፈር ቀዳጁ አስትሌ ትእይንቱን በዘመናዊ መልክ ካስተዋወቀ በኋላ በቀጣዮቹ 50 ዓመታት በጣም በርካታ ማሻሻያዎች እየተጨመሩበት ማሳየት ጀመረ። ሙዚቃዎች በሰርከስ ትርዒት «በኪሮግራፈሮች» እየተቀመሙ መቅረብ ጀመሩ። በስፖርታዊ ትእይንቱ ላይም ለማመን የሚያስቸግር ብቃት ያላቸው ሰዎች መታየት ጀመሩ። በጊዜው በተጣበበ እና ክፍት በሆኑ ቦታዎች ላይ ትርዒቶች ይቀርቡ ነበር። ሆኖም አስትሌ እና የስፖርታዊ ትርዒቱ አቅራቢ ጓደኞቹ ለዘመናዊ ሰርከስ መፈጠር ጥረት በማድረጋቸው በሰፋፊ ቦታዎች ላይ ትዕይንቶች መቅረብ ጀመሩ። በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከእንጨት እና ከተለያዩ ባህላዊ መሳሪያዎች በሚዘጋጁ ቁሶች የትእይንት ቦታዎችን አዘጋጁ። ተወዳጅነቱ እጅግ እየሰፋ እና በመላው ዓለም ትኩረት እያገኘ መምጣቱ የመታደሚያ ስፍራዎች ዘመናዊ እንዲሆኑ እና የትርዒት ማሳያ መሳሪያዎች እንዲሻሻሉ በር ከፍቷል። በዚህም በተለምዶ «ቴንት» እና «ቢግ ቶፕ» በመባል የሚታወቁ ትላልቅ ትርዒት ማሳያ ድንኳኖች በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተዋወቁ። ቴንት አሁንም ድረስ በሰርከስ ስፖርታዊ ትእይንት በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውል መሳሪያ ሆኗል።

በ1980ዎቹ እጅጉን የዘመነ ወይንም «ኮንቴምፖራሪ ሰርከስ» እየተፈጠረ መጣ። የዓለምን የጅምናስቲክ እና ብዛት ያላቸው ትዕይንቶችን በአንድ

ላይ መታደም የሚፈልጉ ሰዎች ቀልብ መቆጣጠር ቻለ። በዚህም በዓለማችን ላይ በጣም በርካታ የሰርከስ ቡድን አባላት እየተፈጠሩ፤ አንዳቸው ከአንደኛቸው እየተማሩ አንዳንዴም እየተፎካከሩ በሰው ልጅ ክህሎት አይሞከሩም የተባሉ ድርጊቶችን ማቅረብ ጀመሩ። ከተለመደው ያፈነገጡ፣ አንዳንዴም ለአደጋ የሚያ ጋልጡ፣ ልዩ የሆነ ተሰጦን የሚጠይቁ እንዲሁም ተአምር የሚመስሉ ድርጊቶች በሰርከስ ትእይንት ላይ እየቀረቡ የብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ቀልብ መያዝ ቻሉ።

ሮማውያን ‹‹ግላዲያተሮቻቸውን›› ለማ ፋለም፣ የፈረስ ውድድሮችን ለማድረግ፣ በመድረክ ላይ ዝግጅቶችን ለማሰናዳት እንዲሁም ያሰለጠኗቸውን የዱር እንስሳቶች ትርዒት ለህዝብ ለማቅረብ በማሰብ የጀመሩት የሰርከስ ትርዒት አሁን ላይ ቅርፁን አስፍቶ በዘመናዊ መንገድ መቅረብ ጀምሯል። በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሞናርኪያል ዘመን የተገነባው «ሰርከስ ማክሲመስ» የተባለው ከእንጨት እና ከተለያዩ ቁሶች የተሠራው ትርዒት ማሳያ ነበር። ይህ ማሳያ እስከ 250 ሺ ታዳሚዎችን የመያዝ አቅም ነበረው። በሮም ስልጣኔ ከተገነቡ ትልቅ ስታዲዮሞች መካከልም ነው።

በዓለማችን ለቁጥር የሚከብዱ የሰርከስ ማሳያ ስፍራዎች ይገኛሉ። በዚያኑ ልክ የስፖርታዊ ትዕይንቱ በላቀ ሁኔታ አመርቂ ለውጦችን ማስመዝ ገብ ችሏል። በቴክኖሎጂ እየታገዘ ፈጣን የሆነ ለውጥም አምጥቷል። ስፖርት በተለይም የሰርከስ ትርዒት ታዳሚያንን በአንድ ላይ በማሰባሰብ፣ በጎ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ይታወቃል። የተለያዩ ባህሎችን በአንድነት በማሰባሰብ ፍቅርን፣አንድነትን እና መልካምነትን የመስበክ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑም ይነገርለታል።

ሰርከስ በኢትዮጵያሰርከስ ውስብስብ ሳይንስ መሆኑን ባለሙያ ዎች

ይናገራሉ። አንድ ነገር ለመከወን ከጊዜ፣ ከዕውቀት እና ከቅልጥፍና ጋር መቀናጀት ያስፈል ጋል። ከባድ የአዕምሮ እና የአካል እንቅስቃሴ የሚጠይቅም ነው። አንዳንድ ከሰውነት ቅርፅ እና ቁመና ጋር የሚያያዙ ሥራዎችም አሉት። ጅምና ስቲኩ በከባድ ድርጊት ስለሚታጀብ ተመልካ ቾች ባለሙያው በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆን ጉዳት እንዳይደርስበት ስጋት ያድርባቸዋል። ነገር ግን የተሰጦው ባለቤቶች «በልምምድ እና በሂደት ሁሉም ለውጥ ይመጣል» ይላሉ። ማናቸውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ፈተና ማጋጠሙ እንደማይቀርም ነው የሚገልጹት።

በዓለማችን ላይ የተለየ ትኩረት አግኝቶ ተሰጦ ያላቸውን ሰዎች በስፋት የሚያሳትፈው ስፖርታዊ ትዕይንት በኢትዮጵያም የቅርብ ጊዜ ትዝታ አለው። ስፖርታዊ ትርዒቱ በፕሮፌሽናል ደረጃ ተግባር ላይ መዋል ከጀመረ ሦስት አስር ዓመታት እንኳን አላስቆጠረም። ነገር ግን ይህን ሙያ ጠንቅቀው የሚያውቁት ሰዎች ሲናገሩ «በተጠና እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ስፖርቱ በሰርከስ ትርዒት መልክ ለታዳሚያን ባለመቅረቡ እንጂ ከድሮም የነበረ ነው» ይላሉ። ባህላዊ በሆነ መንገድ ዕቃ በጭንቅላታቸው በመሸከም ብዙ ርቀት ሚዛናቸውን ጠብቀው የሚጓዙ የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ እናቶች፣ የተለያዩ የዳንስ

እና የጅምናስቲክ ትርዒት የሚያሳዩ ብሄር ብሄረሰቦች ለዚህ ትክክለኛ ምሳሌ እንደሚሆኑም ይገልጻሉ።

ሰርከስ በኢትዮጵያ ውስጥ በፕሮፌሽናል ደረጃ የተጀመረ ሰሞን ተስፋ የሚሰጡ እንቅስቃሴዎች ተስተውለውበት ነበር። ይህ የሆነው ደግሞ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ከተለያዩ አካላት ይገኝ ስለነበረ መሆኑን ለስፖርቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ።

ይህ ዓይነት ድጋፍ በስፖርቱ ላይ ለውጥ ማምጣት ችሎ ነበር። በርከት ያሉ ትዕይንቶችም ይዘጋጁ ነበር። ሆኖም ስፖርታዊ ትዕይንቱ አሁን ላይ ከምንጊዜው በበለጠ በመቀዛቀዝ ላይ ይገኛል። የተወሰኑ የሰርከስ ቡድን አባላት በራሳቸው የግል ተነሳሽነት ስፖርቱ እንዳይዳከም ከሚያደርጉት ጥረት በዘለለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ትኩረት የተነፈጉት ይመስላል።

በአሁን ሰዓት በርካታ ብቃት ያላቸው ልጆች እራሳቸውን በራሳቸው የሚያሰለጥኑ እና ብዙም ድጋፍ የማያገኙ ናቸው። በመስኩም ከመንግሥት እና ከስፖርት አካላት ያለው ግንዛቤ ደካማ ነው። በተለያየ ቦታ ክህሎት ኖሯቸው በተበታተነ ሁኔታ የሚሠሩ ልጆችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚደረገው ሙከራ ውስን ነው። በተለይ የልምምድ ስፍራ በቀላሉ አለማግኘት እና ያሉትም ቦታዎች ምቾት የጎደላቸው መሆናቸው ዋናው እንቅፋት እየሆነ መጥቷል።

ሰርከስ በኢትዮጵያ ጅምር እና ያልጠነከረ ታሪክ ያለው ከመሆኑም በላይ ትኩረት መነፈጉ ስፖርቱ ብዙ ሳይጓዝ ጭርሱኑ እንዳይመናመን ስጋት ይፈጥራል። ሆኖም ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት በግላቸው ጥረት

የሚያደርጉ አካላት አልጠፉም። ከተመሰረተ ሦስት ዓመታት ያስቆጠረው የጋሞ ሰርከስ ቡድን ከ80 በላይ ልጆችን በማፍራት ኢንተርናሽናል ትርዒቶችን በማሳየት እና የተስፋ ብልጭታ በመስጠት ከሚጠቀሱት መካከል ነው። በተጨማሪ በተገቢው መንገድ ድጋፍ የሚደረግላቸው ከሆነ ለወደፊት በሰርከስ እና ጅምናስቲክ ስፖርት አገሪቷ የተሻለ ተስፋ እንደሚኖራት የሚያመላክት አቅም ያላቸው አንዳንድ የሰርከስ ቡድኖችንም መጥቀስ ይቻላል።

«ሰርከስ ደብረብርሃን»በኢትዮጵያ ውስጥ የሰርከስ ቡድን መስርቶ

ለበርካታ ዓመታት ይህን የስፖርት ዘርፍ ለማሳደግ ጥረት ከሚያደርጉ መካከል «ሰርከስ ደብረብርሃን» አንዱ ነው። የዚህ ፅሑፍ አዘጋጅ ከቡድኑ ኃላፊ ጋር ጥቂት ቆይታ አድርጎ ነበር።

አቶ ተክሉ አሻግር የሰርከስ ደብረ ብርሀን ኤክሲኩቲቭ እና አርቲስቲክ ዳይሬክተር ነው። ቡድኑ ከኢትዮጵያዊ ባህላዊ እሴት ጋር የሰርከስ ስፖርትን አመጋግቦ የመሥራት እቅድ እንዳለው ይናገራል። ሙዚቃው እና ስፖርቱ እንዲሁም የተለያዩ ትዕይንቶችን ማቀናጀት አስፈላጊ ነው ይላል። ሰርከስ ደብረ ብርሃን ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ የኪነ ጥበብ ማዕከል የመገንባት ዓላማንም አንግቦ ይሠራል። በአገሪቱም ሆነ በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የመሆን ህልምም እንዳላቸው ይገልጻል። ሆኖም ግን የሰርከስ ስፖርታዊ ትዕይንት ብዙ ፈተናዎች እያጋጠሙት እንደሆነ ይገልፃል።

ለሰርከስ ስፖርት ጎልቶ ያለመውጣት ዋንኛ እንቅፋት በወረቀት ላይ የተቀመጡ አሠራሮች ወደ

ተግባር መቀየር አለመቻላቸው እንደሆነ ይናገራል። አስፈላጊውን ትኩረት እና ድጋፍ ማድረግ እና ህጉን ወደ ተግባር መቀየር ቢቻል የዓለምን መድረክ መቆጣጠር የሚያስችል አቅም ያላቸው ልጆች መኖራቸውን ይናገራል።

ሰርከስ ደብረብርሃን ምንም እንኳን ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ስኬቶች እንዳስመዘገበ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከ100 በላይ የምስጋና ሰርተፍኬቶች በሥራዎቻቸው አግኝተዋል። ከአራት ዓመት በፊትም ከስዊድን የዓመቱ ምርጥ ፕሮዳክሽን በሚል ሽልማት ተቀብለዋል። ሰርከስ ደብረብርሃን በርካታ ሥራዎችን የሠራ ቡድን ነው። ሥራዎቻ ቸው ኢትዮጵያዊነትን የሚያንፀባርቁ መሆናቸው ተወዳጅ አድርጓቸዋል። በተለያየ አጋጣሚ ሲሲቲቪ፣ ቢቢሲ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የህትመት ሚዲያዎች ሽፋን ሰጥተውታል።

በሁለተኛው መሪ ርዕሳችን ላይ ሰርከስ በኢት ዮጵያ ውስጥ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማሳ የት ሙከራ አድርገናል። በዚህም የዘርፉን ችግሮች እና ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎችን በጥቂቱ ዳስሰናል። ከዚህ በመነሳት የዝግጅት ክፍላችን በቀጥታ ስፖርቱን ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ ላይ በቀዳሚነት ተሳታፊ ከሆኑት ባለድርሻ አካላት በተጨማሪ የተለያዩ የሰርከስ ፌስቲቫሎችን እና ውድድሮችን ማዘጋጀት የሚችሉ አካላት ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው ያምናል። በስፖንሰር ደረጃ ባለሀብቶች ገብተው ዘርፉን ሊደግፉትም ይገባል። ብዙዎች በሰርከስ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ማስተካከል እንዳለባቸውም ለማስገንዘብ እንወዳለን።

ዳግም ከበደ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ላይ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን እና የውይይት መድረክ ከትላንት በስቲያ በካፒታል ሆቴል መደረጉን ሶከር ኢትዮጵያ በድረ ገፁ ላይ አስነብቧል። 15 ዩኒቨርሲቲዎች የሚሳተፉበት ይህ የልማት ፕሮግራም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የባለሙያ እና የገንዘብ አቅምን ከአካባቢው የእግርኳስ እምቅ አቅም ጋር በማቀናጀት በእግርኳሱ ላይ ለውጥ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ነው ድረ ገፁ የዘገበው።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም፣ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ፣ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዎች ምሁራንና ተወካዮች በዕለቱ የተገኙ ሲሆን አቶ ኢሳይያስ ጂራ በመክፈቻ ንግግራቸው ‹‹በዓለም ላይ እግር ኳስ ተወዳጅ ስፖርት ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያም ይህን ተወዳጅ ስፖርት በአፍሪካ ከመሰረቱት አንዷ ናት። ሆኖም ከጊዜ ወደ ጊዜ በውጤትም ሆነ በዕድገቷ ወደ ኋላ እየቀረች ነው። ይህን ከስር መሠረቱ ለማስቀረት እና ውጤታማ

ለመሆን በወጣቶች ላይ ጠንክሮ ለመሥራት ቆርጠን ተነስተናል። ለዚህም ደግሞ ዩኒቨርሲዎች ትልቁን ሚና ይወስዳሉ። እኛም በእናንተ እምነቱ ስላለን በጋራ ለመሥራት ተዘጋጅተናል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ለዓላማው ቁርጠኛ በመሆን ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናዬን ማቅረብም ፈልጋለሁ›› ብለዋል።

ከአቶ ኢሳይያስ ንግግር በኋላ የዚህ መድረክ መዘጋጀት እና ከዩኒቨርሲቲዎቹ ጋር መሥራት ባለባቸው የታዳጊዎች ልማት ዙሪያ የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ዲፓርትመንት ተወካይ በአቶ መኮንን ኩሩ ጥናታዊ ፅሑፍ ቀርቧል። አቶ መኮንን በገለጻቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ ስላሉ ዲፓርትመንቶች፣ ስለ ፌዴሬሽኑ አሠራር፣ በእግር ኳሱ ስላሉ ችግሮች እና መፍትሔዎች ላይ ያተኮሩ ሲሆን በመቀጠል ስለ ዛሬው ጉዳይ ሰነድ አቅርበዋል።

ከተነሱት ውስጥ ግብ ጠባቂዎች ላይ ትኩረትን በማድረግ ልዩ የግብ ጠባቂዎች ብቻ አካዳሚ ማቋቋም ይገኝበታል። በአንድ ዩኒቨርሲቲ ዕድሜያቸው ከ13 እና ከ15 በታች የሆናቸው በሁለቱም ፆታ ወደፊት ቁጥሩ የሚያድግ ከ120 በላይ ተጫዋቾችን በማቀፍ እንዲሠሩ ማድረግ፤ ለእነዚህም ድጋፍና ክትትል ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲሁም ከፌዴሬሽኑ ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሥራት ከሁለት ዓመታት በኋላ ከ13 ዓመት

በታዳጊዎች ላይ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

በታች ብቻ ያሉትን አቅፎ ለመሥራት እንደታሰበም ባቀረቡት ጥናት ተጠቅሷል።

በመጀመሪያው ዙር ከ1 ሺ 800 በላይ ሰልጣኞችን የሚያቅፈው ይህ ፕሮግራም ለጊዜው 15 ዩኒቨርሲቲዎችን አሳታፊ ያደረገ ሲሆን በሂደት ግን ቀሪዎቹን ዩኒቨርሲቲዎች በተመሳሳይ በሁለተኛው ዙር በመጥራት በጋራ ለመሥራት በቀጣይ ታስቧል። በመጀመርያው ዙር የሚሳተፉትና በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት ሃዋሳ፣ ባህርዳር፣ ወለጋ፣ አርባምንጭ፣ ሶዶ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ሀሮማያ፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ አዲስ አበባ፣ መቐለ፣ ዓዲግራት፣ ድሬዳዋ እና አሶሳ ዩኒቨርሲዎች ናቸው።

በአቶ ኢሳይያስ መድረክ መሪነት ከተሳ ታፊ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች እና ሃሳቦች ዙሪያ ምላሽ ከተሰጠ በኋላ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደገብርኤል የመዝጊያ ንግግርን አድርገዋል። ‹‹የዛሬው የሰነድ መፈራረማችን የነገውን አዳነ ግርማ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ሳላሀዲን ሰዒድ፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ እና ሎዛ አበራን የመሳሰሉ ተጫዋቾች ለማፍራት ይረዳናል። የእግር ኳስ ልማት ሥራ ለፌዴሬሽኑ ብቻ የሚተው አይደለም። የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ አቅሙ ስላለ የመፍትሔው አካል ለመሆን በጋራ መሥራቱ እግር ኳሱን አንድ ዕርምጃ እንዲራመድ ይረዳል ብለዋል።

አብርሃም ተወልደ

ኢትዮጵያ በዴንማርክ አርሁስ እየተካሄደ በሚገኘው 43ኛው የአለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በድብልቅ ሪሌይ የመጀመሪያው ወርቅ አገኘች፡፡

በተመሳሳይ በድብልቅ ሪሌይ በግል አለሚቱ ታሪኩ እና ፅጌ ገ/ሰላማ ብርና ነሃስ ማስመዝገብ ችለዋል፡፡

ከ20 አመት በታች ሴቶች በ6 ኪሎ ሜትር ፍፃሜ ሚዛን አለም፣ መሰሉ በርኸ፣ ፅጌ ገ/ሰላም፣ ግርማዊት ገ/ኢግዚአብሄር፣ ውዴ ከፈላ፣ አለሚቱ ታሪኩ አገራቸዉን ወክለው ይሮጣሉ፡፡

በተመሳሳይ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች የ8

ኪሎ ሜትር የፍፃሜ ዉድድር አትሌት ፀጋዬ ኪዳኑ፣ ሚልኬሳ መንገሻ፣ ገ/ጊዮርጊስ ተክላይ፣ ታደሰ ወርቁ፣ ጌትነት የትዋለና ድንቃለም አየለ ኢትዮጵያን በመወከል ተሳታፊ ናቸው፡፡

በአዋቂ ሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ደራ ዲዳ፣ ሃዊ ፈይሳ፣ ዘነቡ ፍቃዱ፣ ፀሐይ ገመቹ፣ ለተሰንበት ግዴይ እና ፎተን ተስፋይ ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአዋቂ ወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ደግሞ ሰለሞን ባረጋ፤ ቦንሳ ዲዳ፣ አብዲ ፉፋ፣ እንየው መኮንን፣ አንዳምላክ በልሁ እና ሞገስ ጥዑማይ ናቸው ኢትዮጵያን የሚወክሉት የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የመጀመሪያው ወርቅ አገኘች