Top Banner
በበበበበ በበበበበ በበ በበበበበ በበበ በበበበበ በበበ በበ በበበ በበበበበ (REDD+ Secretariat) 2007 በበበ በበበ በበበበ በበበበ በበበበበ በበበበ 0
63

· Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

Mar 10, 2018

Download

Documents

vuongliem
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

በኢፌዲሪ አካባቢና ደን ሚኒስቴር

ከደን የሚለቀቅ በካይ ጋዝ ቅነሳ ፕሮጀክት (REDD+ Secretariat)

የ2007 በጀት ዓመት ዓመታዊ የእቅድ

አፈጻጸም ሪፖርት

ሰኔ 2007 ዓ.ም አዲስ አበባ

0

Page 2:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

በአካባቢና ደን ሚኒስቴር

ከደን የሚለቀቅ በካይ ጋዝ ቅነሳ (REDD+) ፕሮጀክት

የ2007 በጀት ዓመት

ዓመታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት

1.መግቢያ

1.1. የዝግጅት ምዕራፍ ዳራና ዓላማው

ከ አየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ተዳጊ ሀገሮች ከደን ዘርፍ የደን ጭፍጨፋና መራቆትን በመከላከል ለሚያደረጉት የበካይ ጋዝ ቅነሳና በደን ልማት አማካኝነት ከከባቢ አየር ለሚመጡት ካርቦን (carbon sequestration) የገንዘብ ድጋፍ የሚያስገኝ የ Reducing Emissions from Deforestation and Forest

Degradation (REDD+) ፖሊሲ ስርዓት በመዘርጋቱ በርካታ ሀገራት የአቅም ግንባታ፣ የቴክኒክና የስልት ዝግጅት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያም ለዝግጅት ምዕራፍ ድጋፍ ካገኙ ሀገሮች አንዷ ሆናለች፡፡

ከፕሮግራሙ ውስብስብነት የተነሳ ታዳጊ አገራት ለዓለም አቀፉ REDD+ ፕሮገራም ትግበራ የህጋዊ ማዕቀፍ፣ የተቋማትና የአቅም ግንባታ ዝግጅት አንዲያደረጉ ይጠመቅባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያም የ 13.6 ሚሊዮን ዶላር ከደን

ካረበን ፓርትነርሺፕ ፋሲሊቲ፤ ከኖርዌይ እንዲሁም ከእንግሊዝ መንግስት የገንዘብ ድገፍ በማግኘት የዝግጅት ምዕራፍ 2005 ዓ/ ም ጀምሮ ይህንኑ የዝግጅት ምዕራፍ በመተግበር ላይ ትገኛለች፡፡ ይህ ፕሮግራም ኢትዮጵያ በእርሻ

መስፋፋትና በማገዶ ምክንያት እየወደመ የመጣውን ደኗን ከቀጣይ ውድምት ለመከላከልና የደን ሀብት በስፋት ለማልማት የሚያስችላትን የዝግጅት ምዕራፍ በጥር 2005 ዓ/ ም ጀምራ በ 2008 መጨረሻ ለማጠናቀቅ

በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች፡፡

1.2. የዝግጅት ምዕራፍ ዋና ዋና ተግባራት

ከደን የሚለቀቅ በካይ ጋዝ ቅነሳ የዝግጅት ምዕራፍ (REDD+ Readiness Phase) በአካባቢና ደን ሚኒሰቴር ስር በተቋቋመው REDD+ ሴክሬታሪያት አማካኝነት ከዓለም ባንክ፤ እንዲሁም ከኖርዋይና እንግሊዝ መንግስታት

ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት እስከ ሦስት ዓመት የሚከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነሱም፡- (1) በፕሮግራሙ ዙሪያ አጠቃላይ ሀገር አቀፍ አቅም ግንባታ ማድረግ (capacity building on REDD+)፣ (2) ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መስራት (consultation and participation) ፣ (3) የዝግጅት ምዕራፉን ለማሳካትና ቀጣይ የፕሮግራሙን ትግበራ የሚመራና ትግበራውን

የሚያስተባብር ተቋም መገንባትና የአመራርና የቴክኒክ ቡደን አካላትን መመስረት (establishing REDD+ Management Structure) ፣ (4) ለፕሮግራሙ ስልት መንደፍ (developing REDD+ Strategy)፣ (5) ለፕሮግራሙ ትግበራ የሚያስችሉ አጠቃላይ ተቋማዊ፤ የፖሊሲ፤ የህግና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣(6)

1

Page 3:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ከፕሮግራሙ ትግበራ በፊት ሀገሪቱ በየዓመቱ ከደን ዘርፍ የምትለቀውን በካይ ( ሙቀት አማቂ) ጋዝ ልክ የዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በመከተል በትክክል መመጠን (establishing baseline emissions/forest reference

levels/forest reference emissions level) ፣ (7) በትግበራ ወቅት የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለመለካትና የክፍያ መጠን ለመወሰን የሚያስችል የልኬት፤ ዘገባና ኦዲት ስርዓትን መዘርጋት (establishing

measurement, reporting and verification, MRV system) ፤ እና (8) የዝግጅት ምዕራፉን መከታተያና ግምገማ ስርዓት መዘርጋት (developing REDD+ readiness monitoring and

evaluation framework) ይገኙበታል፡፡

ከዝግጅት ምዕራፍ ትግበራ ጎን ለጎን ለወደፊቱ የፕሮግረሙን ስልት በሰፊው ለመተገበር ትምህርት ለመውሰድ የሚያስችሉ የተለያዩ የREDD+ ፓይለቶችን በአራት ክልሎች ለመተግበር እቅድ ተይዞ የኦሮሚያው ፕሮግራም ዲዛይን በዚህ ዓመት

በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

1.3. ሪፖርቱ የሚሸፍነው ጊዜና ዓላማው

ከዝግጅት ምዕራፍ ተግበራት ውስጥ በዚህ ዓመት ለመተግበር ከዝግጅት ምእራፍ የእቅድና ትግበራ ክትትል ማዕቀፍ (REDD+ Readiness Monitoring and Evaluation Framework) በመነሳት በርካታ ዝርዝር

እቅዶችን በማዘጋጅት ለብሔራዊ ስቲሪንግ ኮሚቴ በማቅረብና በመስሪያ ቤቱ የበላይ አካል አገዛ በማሻሻልና በማፀደቅ ወደ ትግበራ ተግብቷል፡፡ ይህም ሪፖርት በዚህ በጀት ዓመት የታቀዱና የተከናወኑ ትግባራትን በዝርዝር በቃላትና

በሰንጠረዥ በመዘገብ ለባለድርሻ አካላት የማሳወቅ ዓላማ ያለው ሲሆን በትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት የተወሰዱ እርምጃዎችንና ለተሻለ ትግበራ መወሰድ የሚኖርባቸውን እርምጃዎች ለመጠቆም ይሞክራል፡፡

2. የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ክንውን አጠቃላይ ሁኔታ

በዚህ በጀት ዓመት በዋናነት የታቀዱ ስራዎች የሚከተሉት ነበሩ፡፡ እነርሱም (1) REDD+ ሴክሬታሪያትን በሙሉ የሰውሃይልና ቁሳቁስ በማደራጀት በሙሉ አቅሙ እንዲፈፅም ማድረግ፣ (2) የፕሮጀክቱን ትልልቅ ግዥዎች መፈፀምና

በዝግጅት ምዕራፉ ወሳኝ አገር አቀፍና ክልላዊ ጥናቶችን በአማካሪ ድርጅቶች ማስፈገፀም፣ (3) ሰፊ የግንዘቤ ማስጨበጫ ስራን በፌዴራልና በክልል ደረጃ መፈፀም፣ (4) በሰቲሪንግ ኮሚቴ ምክር መሰረት ክልሎችን በፕሮግራሙ

እንስቃሴ ቀድሞ ማሳተፍ፣ (5) የአገር አቀፍ የደን ቅኝትና ምዝገባ ስርዓት (continuing the implementation of National Forest Inventory, establishing National Forest Monitoring System and MRV) ከዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ጋር በመሆን ማስጀመርና በፍጥነት

እንዲተገበር ማድረግ እና (6) ቀድሞ የተጀመረውን የኦሮሚያ REDD+ ፓይለት ፕሮግራም ዲዛይን ማፋጠን ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ክንውን አጥጋቢ በሚባል ደረጃ የተፈፀመ ሲሆን ሀገሪቱ በአለም ዓቀፉ መስፈርት

መሰረት የሚጠበቅባትን የዝግጅት ምዕራፍ ቀደሞ ለማጠናቀቅ በሚያስችለን ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡

2

Page 4:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

2.1 የዓመቱ ዕቅድ ክንውን ዝርዝር ማብራሪያ

2.1. ክፍል 1. የዝግጅት አደረጃጀትና ምክክር

2.1.1. ንዑስ ክፍል 1.1. ብሔራዊ የሬድ ፕላስ ሥራ አመራር አደረጃጀት

የሴክሪታሪያቱን ( ዝግጅት ምእራፍ) ሥራዎች በበላይነት የሚከታተለውና አመራር የሚሰጠው የስቲሪንግ ኮሚቴ ሁለት ስብሰባዎች ታቅደው እስካሁን ወቅቱን ጠብቆ አንድ ጊዜ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ተሰብስቦ የ 2006 በጀት ዓመት

የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መገምገምና የ 2007 በጀት ዓመት ሥራዎችን በዝርዝር አይቷል፡፡ በሁለተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ የስቲሪንግ ኮሚቴው ስብሰባ ለማካሄድ እቅድ የተያዘ ቢሆንም በሥራ መደራረብ እስከአሁን ባይካሄድም በዚህ

በጀት ዓመት መጨረሻ ለማካሄድ የስቲሪንግ ኮሚቴ አባላት የሚመቻቸውን ጊዜ በማማከር እንዲወስኑ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

የቴክኒክ ድጋፍ የሚሰጡት ሶስት (3) ግብረ ሃይል ኮሚቴዎች ወቅታቸውን ጠብቀው እስካሁን ከታቀዱት 12 ስብሰባዎች 11 ጊዜ በመሰብሰብ ሞያዊ ድጋፍና ክትትል አድርገዋል፡፡ የ MRV ግብረ ሀይል የ MRV ሥራዎች ማስጀመሪያ ዓውደ ጥናት፣ በዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት አማካኝነት በመከናወን ላይ ያለውን የደን ቆጠራና በልኬት፤

ዘገባና ማረጋገጥ (baseline emissions and MRV system) ዋና ዋና ሥራዎች ያሉበት ደረጃዎችና የታቀዱትን ዝርዝር ሥራዎችን በማየት ድጋፍና ክትትል የደረገ ሲሆን የስትራቴጂ ግብረ ሀይል በመዘጋጀት ላይ ያለውን

የREDD+ የትግበራ ስትራቴጂ ንድፍና በአዘጋጅ አባላት የቀረበውን ረቂቅ ጽሁፍ በጥልቀት በማየት ማዳበሪያ ሀሣቦችን በማካተት ቅርጽ እንዲይዝ በማድረግ ረቂቁ ሊማ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ በአራተኛው ሩብ ዓመት ስብሰባ የተከናወኑትንና በመከናወን ላይ ያሉትን የጥናት ውጤቶች ግብዓት በመጠቀም ስትራቴጅውን መጨረሻ ደረጃ ጥንቅር ለማዘጋጀት አማካሪ ተቀጥሮ በጥራትና በሚጠበቀው ደረጃ እንዲዘጋጅ ምክር

ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ግበረ ሀይሉ የሀገሪቱን የደን ትርጉም በዝርዝር በማየት ማዳበሪያ ሀሣቦችንም ሰጥቷል፡፡ ሌላው የ SESA ግብረ ሀይል እስከ አሁን የ SESA/ESMF ብሔራዊ ጥናት የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም ግብረ ሀይሉ

በጥናት ሂደት የሚኖራቸዉ ተሣትፎ/ ሀላፊነትን ለመወጣት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም የሀገር አቀፍ የምክክርና ተሣትፎ እቅድ (Consultation and Participation Plan) ለማዘጋጀት ምን

መድረግ እንዳለበት በጥልቀት በመወያየት ሰነድ ዝግጅት ላይ ግበረ ሀይሉ እየተሳተፈ ሲሆን በሰነዱ የሚካተቱ ጉዳዮች የምክክርና ተሣትፎ ዘዴዎችን፣ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለምክክር የሚቀርቡ ሀሳቦችን፣ የማኔጅመንት

አደረጃጀትን፣ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት ጉዳዮችን ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል የኦሮሚያ ቴክኒክ ኮሚቴ (TWG) በበጀት ዓመቱ ሦስት ጊዜ ለመሰብሰብ ታቀዶ ሁለት ጊዜ

በመሰብሰብ በክልሉ ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኙትን የደን ምንጣሮ እና መመናመን መንስዔዎች ጥናት በአማካሪው በቀረበው የመነሻ ግኝቶች ላይ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በመጀመሪያ ስልታዊ አማራጮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለፕሮጀክቱ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የስቲሪንግ ኮሚቴ ሁለት ጊዜ ለመሰብሰብ ታቅዶ አንዱ የተከናወነ ሲሆን አንዱ

3

Page 5:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

የክልሉ ከፍተኛ ሀላፊዎች ሥራ መደራረብ ምክንያት ወቅቱን ጠብቆ አልተካሄደም፡፡ በሌሎች ሦስት ክልሎች (አማራ፣ ትግራይና ደቡብ ክልሎች) የREDD+ ማስተባበሪያ ዩኒቶች ለማቋቋም ታቅዶ በበጀት ዓመቱ አስተባባሪዎችን በመቅጠር አሃዶቹን የማቋቋም ስራ የተጀመረ ሲሆን ክልሎቹ የሚያካሂዱት የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ዩኒቱን ለመመስረት

ጊዜ በመውሰዱ ተደራጅተው ስብሰባ ማካሄድ አልጀመሩም፡፡

ከላይ የተገለጹት የፕሮጀክቱ አደረጃጀት ኮሚቴዎች በበጀት ዓመቱ በአማካኝ 83 በመቶ አባላት በስብሰባዎች ተገኝተው አመራርና ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ይህም በእቅድ የተቀመጠውን 67 በመቶ ተሣትፎ ያሟላና ያለፈ ነው፡፡

የብሔራዊ ሴክሪታሪያቱንና የኦሮሚያ ማስተባበሪያ ዩኒት የሰው ሀይል መቶ በመቶ ለማሟላት እቅድ ተይዞ የሴክሬታሪያቱ 14 ሀገር ውሰጥ ሰራተኞችና 1 የውጪ ሀገር ባለሞያ ቅጥር በማድረግ መቶ በመቶ ሲያሟል በኦሮሚያ ዩኒትም መቶ

በመቶ የሰው ሀይል አሟልቷል፡፡ በሦስት ክልሎች ( አማራ፣ ትግራይና ደቡብ ክልሎች) የREDD+ ማስተባበሪያ አሀዶች (ዩኒቶች) ታቅዶ እስካሁን የሶስቱም ክልሎች ( ትግራይ፣ አማራና ደቡብ) አስተባባሪዎች ቅጥር የተጠናቀቀ ሲሆን

አስተባባሪዎቹ አሃዶቹን አደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

በሌላ አንፃር ለተሻለ ትግበራ የሴክሬታሪያቱን የአቅም ግንባታና ሥልጠናን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ ለአስር ባለሙያዎች የውጭ ሃገርና ሀገር ውስጥ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለሁለት የሂሳብ ባለሙያዎች ( የሬድ ፕላስ ሂሳብ ባለሙያና የሚ/ር

መ/ ቤቱ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር) በውጭ ሀገር ሥልጠና እና የሴክሬታሪያቱ ፀሃፊ በቢሾፍቱ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ስልጠና አግኝተዋል፡፡ ይህም 30 በመቶ አፈጻጸም ያሳያል፡፡ ሌላው በሊማ- ፔሩ በተካሄደው የአየር ንብረት

ለውጥ ጉባዔ የሴክሬታሪያቱንና ሌሎች ባለድሻ አካላት 3 ባለሙያዎችን ለማሣተፍ ታቅዶ 5 ተሣታፊዎች እንዲካፈሉ የተደገ ሲሆን በኦሮሚያ ማተባበሪያ ዩኒት 4 ለማሳተፍ ታቅዶ 2 ተሣታፊዎችን ተካፍለዋል፡፡ በአጠቃላይ በእቅድ የተያዘው

7 ባለሙያዎችን ማሳተፍ መቶ በመቶ ተፈጽሟል፡፡

ከፌዴራልና ክልል ቁልፍ ባለድርሻ አካላት 31 አባላትን በሁለት ዙር በ REDD+ ዝግጅት የተሻለ ደረጃ ከደረሱ ሀገራት የልምድ ልውውጥና ተሞክሮ እንዲያገኙ ታቅዶ ከጥር 10-20 2007 ዓ. ም የሚኒስትር መ/ ቤቱ ከፍተኛ ሀላፊ፣ የክልል

ሀላፊዎችንና የሴክሬታሪያቱን ባለሙያዎች 9 አባላት በሴክሬታሪያቱና UNDP ገንዘብ ድጋፍና 2 በCIFOR ወጪ የተደገፉ 11 አባላትን ያካተተ ጉብኝት ሴክሬታሪያቱ አስተባብሮ አስፈፅሟል፡፡ ሁለተኛውን ዙር የልምድ ልውውጥ ለከፍተኛ የፌዴራል ክልል ኃላፊዎች በሜክሲኮ ለማካሄድ በሰኔ ወር ዝግጅቱ ተጠናቆ በስራ መደራረብ ምክንያት ለቀጣይ

ተላልፏል፡፡

በሌላ በኩል የሂሳብ አያያዝን ለማስመርመር ዕቅድ ተይዞ ብሄራዊ ሴክሬታሪቱ እስከ አሁን ያካሄዳቸውን የሂሣብ እንቅስቃሴዎች ደረጃውን በጠበቀና የሙያ ፈቃድ ባለው አካል ሂሣቡን ለማስመርመር በተያዘው እቅድ መሠረት የኦዲት

4

Page 6:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

አማካሪዎች ተለይቶ የሂሣብ ምርመራ ተጠናቀቆ ሪፖርቱ ለሚመለከተው አካል ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም በውስጥ ኦዲት ሂሳቡ ተመርምሮ በተመሳሳይ ሁኔታ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ተደርጓል፡፡

2.1.2. ንዑስ ክፍል 1.2. ምክክር፣ ተሣትፎና ተደራሽነት

የዝግጅት ምዕራፍ የመረጃ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ ግንዛቤን ለመፍጠርና በተገቢው ኮሚኒኬሽን ለሰፊው ማህበረሰብ ለማድረስ በርካታ ስራዎች ታቅደው ነበር፡፡ ከነዚህም ተደረሽነትን ለመጨመር የሚያስችል

የተግባቦት ስትራቴጂ እንዲነደፍ በተያዘው እቅድ መሠረት አማካሪ ባለሙያ ተቀጥሮ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን አማካሪውም በስትራቴጂው ዝግጅት ሂደት የዘርፉን ባለሙያዎችና በፌደራል የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ

ሰፊ ግብዓት ለማካተት ጥረት አድርጓል፡፡

በመሆኑም እስከ እቅድ ዘመኑ ማጠናቀቂያ ድረስ በተግባቦት ስትራቴጂው ከተቀመጡት የኮሙኒኬሽን መሣሪያዎች ውስጥ 30 በመቶውን ጥቅም ላይ ለማዋል ታቅዶ 20 በመቶውን በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ ጥረት የተደረገ ሲሆን አፈጻጸሙ 67 በመቶ ደርሷል፡፡ በዚህ መሠረት

ስድስት የተለያዩ የህትመት ሚዲያዎችን በመጠቀም ማለትም መልካም አዲስ ዓመት ፖስት ካርድ፣ ካላንደር፣ የቁልፍ መያዣ፣ እስክብሪቶ፣ ኮፍያ፣ ካናቴራ፣ ብሮሸር በመጠቀም ግንዛቤ ለመፍጠር በታቀደው መሰረት ስራዎቹ ተከናውነዋል፡፡ ከተከናወኑት ውስጥ 2500 ፖስት ካርድና 2500 ካላንደር ታትመው በአዲስ ዓመት

መለወጫ ወቅት የተሰረጩ ሲሆን የ REDD+ logo የያዙ 1000 እስክሪፒቶ፣ 3000 ካናቴራና 3000 ኮፍያዎም ታትመው በመሰረጨት ላይ እንገኛለን፡፡ በኦሮሚያ REDD+ ማስተባበሪያ ዩኒት ለመስራት በእቅድ ከተያዙት የኮሚኒኬሽን ማቴሪያሎች ስርጭት ውስጥ 1500 ማስታወሻ ደብተር፣ 750 ቲ- ሸርትና 750 ኮፍያ

የሬድ አርማ ያለበት ታትሞ እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡ በሴክሬታሪያቱ በአራት ቋንቋዎች ብሮሸር ለማዘጋጀት የታቀደ ቢሆንም ብሮሸሩ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ በትግሪኛ፣ አማርኛ፣ በከፋኛ ወዘተ እስከ 10 ቋንቋዎች

ለመተርጎም በሂደት ላይ ነው፡፡

የጋዜጣ ደንበኛ በመሆን በሬድ ፕላስ ዙሪያ የሚሰራጩ ሀሣቦችን ለመከታተል ከአምስት በላይ ጋዜጦችን የደንበኝነት ጥያቄ በማቅረብ ሪፖርተር ( አማርኛና እንግሊዝኛ ህትመት) ፣ ካፒታል፣ ፎርቹን፣ ዴይሊ ሞኒተር እና

ቢዝነስ ሪቪው መጠቀም ጀምረናል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሦስት የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ማለትም የጽሁፍ መልዕክት በሞባይል፣ የሬዲዮ ቶክ ሾው፣ የቴሌቪዥን ጥያቄና መልስ፣ ለሪፖርተር ጋዜጣ፣ ለሬዲዮና ቴሊቪዥን ቃለ መጠይቅ መስጠት በመጠቀም

REDD+ ን ግንዛቤ ለማሳደግ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት የሴከሩታሪያቱን ስም በመጥቀስ ለ 12

5

Page 7:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ሚሊዮን የሞባይል ደንበኞች ችግኝ እንዲተክልና እንዲንከባከብ በክረምት ወቅት መልእክት አስተላልፈናል፣ በሬዲዮ ፋና ሁለት ጊዜ የሬዲዮ ቶክ ሾው የሚኒስቴር መ/ ቤቱ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ከፍተኛ ውይይት አካሂደናል፤ አስተባባሪው ለሪፖርተር ጋዜጣ፣ ለሬዲዮ ( ለብስራት ሬዲዮ - ከሸልፍ ላይ ፕሮግራም፣ ኤመነንስ የግል መጽሔት ጋር ቃለ መጠይቅን ጨምሮ) እና ለቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ በመስጠት) በመስጠት

ስለሚኒስቴር መ/ ቤቱና ሴክሬታሪያቱ ስለሚፈፅመው ተግባር አስተዋዉቀዋል፡፡ በተለይ በሬዲዮ ፋና በርካታ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ REDD+ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ውይይት ማካሄዳችን እና በሁለት ዙር

ከታሚ ሶል ኮሚኒኬሽን ጋር በመተባባር የጥያቄና መልስ ውድድር ማድረጋችን ስለ ስራችንና REDD+ ለሰፊው ማህበረ ሰብ የሰፊውን ህስብ ተደራሽነት ለማረጋገጥ የሚስችል ተግባር በበጀት ዓመቱ ተከናዉኗል፡፡ በተጓዳኝ የሬዲዮ ቶክ ሾውና የባለድርሻ አካላት ውይይት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዲሁም በኢብኮ ጥያቄና መልስ ፕሮግራም ሲሰራ በቀጥታና ተቀርጾ ሲተላለፍ በፕሮግራሙ መግቢያና መውጫ ሰዓት

ማስታወቂያ በአጠቃላይ ከአስር ጊዜ በመልቀቅ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደርሷል ተብሎ ይታሰባል፡፡

ደረጃውን የጠበቀ የREDD+ ድረ ገጽ አማካሪ ባለሞያ ለማዘጋጀት በወጣው ጨረታ መሠረት በዝርዝር ስራ አግባብ የቀረቡትን የአማሪ ባለሙያዎችን የፍላጎት መግለጫ ሰነዶችን በመመርመር ባለሙያውን ለመለየት

የአማሪዎች ግምገማ ተጠናቋል፣ የግምገማው ውጤት ለበላይ ኃላፊ ለውሳኔ ቀርቧል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ለጊዜው በሴክሬታሪያቱ የሚከናወኑ ሥራዎችንና መረጃዎችን ለሁሉም አካላት ተደራሽ ለማድረግ አንድ ብሎግ

( አድረሻው reddplusethiopia.wordpress.com) የሆነ ጊዚያዊ ዌብሳይት የተዘጋጀ ሲሆን መረጃዎችን በመጫን ለተጠቃሚዎች በማድረስ ላይ እንገኛለን፡፡

በርካታ የክልል ባለሞያዎችን፤ የህዝብ ግንኙነትና የጋዜጠኞችን እንዲሁም የደን አካባቢ ማህበረተሰብ መሪዎች አቅም በመገንባት የተፋጠነ አገራዊ ዝግጅት ለማገዝ አጫጭር የአሰልጣኞች ስልጠናዎችን ለመስጠት የወንዶ

ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በአየርንብረት ለውጥ፣ በ REDD+ ፤ በደን አያያዝና ካርቦን ፋይናንስ ዙሪያ ሥልጠናዎቹን እንዲሰጥ ብቸኛ ተቋም መሆኑን ከዓለም ባንክ ጋር በመነጋገር ተቀባይነት በማግኘቱ ከኮሌጁ

ጋር የሁለት ዓመት የስልጠና ስምምነት ተፈፅሟል፤የሥልጠና ማንዋሎችን ተዘጋጅተው ሥልጠናውን በተደጋጋሚ ዙር በተለይ በክረምት ወቅት ለማስፈፀም ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩል የኦሮሚያ ማስተባበሪያ ዩኒት

ለባለሙያዎች በ REDD+ መሠረታዊ ሀሣቦች፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በMRV ፣ ካርቦን ዳሰሳ ሥልጠና ለማዘጋጀት የአሰልጣኝ አማካሪ ጨረታ ሁለት ቢወጣም የሥራ ልምዱን የሚመጥን አማካሪ ባለመገኘቱ የሥራ

መዘርዝሩ እንደገና ተከልሶ ለሶስተኛ ጊዜ ለአማካሪዎች ተጋብዟል፡፡

6

Page 8:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

በደቡብ - ደቡብ (South-South Exchange) የመማማሪያ መድረኮች ላይ በሴክሬታሪያቱ የገንዘብ ድጋፍ 3 ባለሙያዎች እንዲሰተፉ የተደረገ ሲሆን የኦሮሚያ የህብረተሰብ ምክክርና ተሣትፎ እቅድ በፋርም አፍሪካ

ድጋፍ ተጠናቆ ከክልል እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የመንግስት አካላት ውይይትና ምክክር እያካሄዱ ነው፡፡

በሁሉም ክልሎች በክልል ደረጃ REDD+ ን ከማስተዋወቅ አንፃር በአራት ክልሎች ለክልል ባለድርሻ አካላት በREDD+ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር በተያዘው እቅድ መሠረት በአራቱም ክልሎች ስራው ተከናውኗል፡፡ በዚሁ

መሰረት በአማራ ክልል ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ለሁለት ቀናት በባህር ዳር ከተማ ለ 38 ተሣታፊዎች ( ሴት 3 እና ወንድ 35 ተሣታፊዎች) ፣ በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ ለ 37 ተሣታፊዎች ( ሴት 5 እና ወንድ 32)፣

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ ለ 38 ተሣታፊዎች ( ሴት 5 እና ወንድ 33) ፣ በሶማሌ ክልል በጅጅጋ ከተማ ለ 31 ተሣታፊዎች ( ሴት 4 እና ወንድ 27) ፣ በጋምቤላ ክልል በጋምቤላ ከተማ ለ 43 ተሣታፊዎች

( ሴት 9 እና ወንድ 34) እና በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ ለ 27 ተሳታፊዎች ( ሴት 5 እና ወንድ 22) በአጠቃላይ ለ 258 ተሣታፊዎች ( ሴት 35 እና ወንድ 223) በተገኙበት REDD+ መሠረታዊ ጽንሰ

ሀሣቦችና አየርንብረት ለውጥ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጥሮአል፡፡ እንዲሁም የኦሮሚያ ሬድ ፕላስ ማስተባሪያ ዩኒት ለባለድርሻ አካላት የልምድ ልውውጥ በሁምቦና ሶዶ ሲዲኤም ፕሮጀክቶች ላይ ለ 28 ተሣፊዎች (28

ወንድና 4 ሴቶች) ከመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያካተተ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ በዚህም መልካም ተሞክሮ እንዳገኙበት ተሣታፊዎች አስያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም በካርቦን ፕሮጀክትና REDD+ ተጨባጭ ልምድ ለክልሎች ለማካፈል ታስቦ በበጀት ዓመቱ 1 ብሔራዊና 4 ከልላዊ REDD+ ኮንፈረንሶች ለማካሄድ በተያዘው እቅድ መሠረት Early Lessons from

ongoing REDD+ Project initiatives በሚል ጭብጥ በ ተለያዩ አስተዳደር መዋቅር ደረጃ የሚገኙና ከተለያዩ ህበረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ባ ለድርሻ አካላት በተገኙበት 1 በሀገር አቀፍ እና በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ ደቡብና ትግራይ ክልሎች ኮንፈረንሶቹ ተከናውነዋል፡፡ በኦሮሚያ ከክልሉና ዞኖች የተውጣጡ የአስተዳደር አካላት፣ የሴቶችና ወጣቶችና ማህበር ተወካዮች፣ በደን ጥገኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ( የደን ውጤቶች

ህ/ሥ/ ማህበር አመራች) ፣ የግብርና ቢሮና ሌሎች ባለድርሻ አካት በተገኙበት የባሌ ሬድ ፕላስ ፕሮጀክት፣ የሁምቦ ሲዲኤም ፕሮጀክት፣ የጊምቢ ቡና ፕሮጀክት እና NTFP Project መልካም ተሞክሮዎችን በማቅረብ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡ በደቡብ ክልል በተመሳሳይ ሁኔታ የሁምቦ ሲዲኤም ፕሮጀክት እና ሌሎች የደን አስተዳደር

ተሞክሮዎችን ተሣታፊዎች ቀርቦ ግንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን በሁምቦ ሲዲኤም ፕሮጀክት የአንድ ቀን የመስክ ጉብኝት ተደርጓል፡፡ በአማራ ክልል በደሴ ከተማ በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ ተመሳሳይ ኮንፈረንስ

ተከናውኗል፡፡ በነዚህም ኮንፈረንሶች ላይ በሴክሬታሪያቱ የተዘጋጁትን የተለያዩ የኮሚኒኬሽን ማቴሪያሎች ለማቅረብ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ በተካሄዱት ኮንፈረንሶች 615 ተሣታፊዎች ( ሴት 124 እና ወንድ 493)

7

Page 9:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

በፕሮገራማችን ዙሪያ ያሉትን ፅንሰ ሀሳብና በደን ካርቦን ፕሮጀክት ዙሪያ የየክልል ተሞክሮዎችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተሞክሯል፡፡ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በመስክ ጉብኝት የታገዝ ልምድ ልውውጥ ስላገኙ የደን

ካርቦን ስራ ምን ያህል ተጨባጭና ከተለመደው ስራ ብዙ የተለየ አለመሆኑን ለመገንዘብ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡

ተደራሽነትን ከማስፋት አንፃር በበጀት ዓመቱ የደን ባለሞያዎች ዓመታዊ ስብሰባውን ከሴክሬታሪያቱ ጋር በመተባበር በባህር ዳር ከተማ ያካሄደ ሲሆን ሴክሬታሪያቱ የገንዘብና የሎጂስቲክስ ድጋፍ በማድረግ በርካታ

አባላትና ተሳታፊዎች በተገኙበት REDD+ ን ለማስተዋወቅ መድረኩን ተጠቅሟል፡፡

የኦሮሚያ ማስተባበሪያ ዩኒት የተዘጋጀውን ክልላዊ የምክክርና ተሣትፎ ሰነድ በመጠቀም በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ለመፍጠር በተያዘው እቅድ መሠረት በቾ ወረዳ ( ኢሉአባቦራ ዞን) እና በአዶላ ረዴ ወረዳ ( ጉጂ ዞን)

ለ 511 የአካባቢው ማህበረሰብ ተሣታፊዎች (12 ሴቶችና 499 ወንዶች) እንዲሁም ለ 105 መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሣታፊዎች (6 ሴቶችና 97 ወንዶች) የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት

ተካሂዷል፡፡ በደን ጥገኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሬድ ፕላስ አደረጃጀት ውስጥ ውክልናና ተሣትፎአቸውን ለማስጠበቅ በኦሮሚያ በተቋቋመው የሬድ ፕላስ TWG ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው የተደረገ ሲሆን

እንዲሁም በሚካሄዱት የባላድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ውክልናቸውን በማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የREDD+ ጽንስ ሀሣብና ትግበራ ቀጣይነትን ከማረጋገጥ አኳያ በዘላቂነት አቅም ለመገንባት አንድ በመጀመሪያ ዲግሪና አንድ በሁለተኛ ዲግሪ በስርዓተ ትምህርት ለማካተት ታቅዶ በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ

ዲግሪና በሐረማያ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዲግሪ REDD+ ከሪኩለም እንዲካተት ስምምነት ተደርሶ የሲለበስ ዝግጅት ተጠናቆ ሁለቱም ዩኒቨርስቲዎች የማስተቻ ወርክሾፕ አዘጋጅተው ሀሣብ በማሰባሰብ ሲለበሱን

እንዲዳብር አድርገዋል፡፡ በቀጣይ የክለሳ ሥራውን ለማዳበር በርካታ ዩኒቨርሲቲዎችን በመጥራት አገር አቀፍ ስብሰባ ይጠራል፡፡ የመጨረሻ ደረጃ ሲደርስ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ኮርሱን በፍላጎት ከሪኩለማቸው ውስጥ

በማካተት እንዲያስተምሩ ይጋበዛሉ፡፡

2.2. ክፍል 2. የREDD+ ስትራቴጂ ማዘጋጀት

2.2.1. ንዑስ ክፍል 2.1. በመሬት አጠቃቀም፣ የመሬት አጠቃቀም ለውጥ መንስዔዎች፣

በደን ህግ፣ ፖሊሲና አስተዳደር ላይ ጥናት ማካሄድ፣

በበጀት ዓመቱ ለREDD+ ስትራቴጂ ዝግጅት ወሳኝ ግብዓት የሚሆኑና በኋላም ለፕሮግራሙ ትግበራ አመቺ የፖሊሲ፣ ህግና የተቋማት ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ ሶስት አገር አቀፍ ጥናቶችን በዓለም አቀፍና አገር አቀፍ

8

Page 10:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

አማካሪ ድርጅቶች ቅንጅት ለማስጠናት ( አንዱ በዓለም ባንክ አማካይነት) በታቀደው መሰረት የፖሊሲ፣ ህግና የተቋማት ማእቀፍ ጥናት ሲጠናቀቅ የደን ምንጣሮና መመናመን መንስዔዎቸ ላይ የሚካሄደው ተጀምሮ በሐምሌ ወር ይጠናቀቃል፡፡ የዳሰሳ ጥናት በኦሮሚያ ክልል ተካሂዶ የተጠናቀቀ ሲሆን በኦሮሚያና በአገር አቀፍ

ጥናት ውጤቶች ላይ ባለድርሻ አካላት ተሰብሰበው በአውደ ጥናት ውይይት ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ሶስተኛው ጥናት በ REDD+ ትግበራ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ አካባቢያዊና ማህበረሰብ ተፅዕኖዎችን በመለየት የመከላከያ ዘዴዎችን የሚጠቁም ጥናትና አስፈላጊ ሰነዶችን የሚያዘጋጀው ሲሆን በየካቲት ተጀምሮ

በነሐሴ ወር ይጠናቀቃል፡፡

2.2.2. ንዑስ ክፍል 2.2. የREDD+ ስልታዊ አማራጮች

በበጀት ዓመቱ ረቂቅ የ REDD+ የትግበራ ስትራቴጂ ለማዘጋጀት ታቅዶ ለዚሁ ስራ በተዋቀረው ጊዜያዊ ኮሚቴ መሪነት ሁሉም ባለድርሻ አካላትን ባሣተፈ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን ለሊማ- ፔሩ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ቀርቧል፤ ውጤቱም ለሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ግብዓት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በአማራ፣ ትግራይና

ደቡብ ክልሎች የ REDD+ ፓይለት ቦታዎችን መረጣ ጥናትና የፕሮጀክት ፅንስ ዝግጅት አማካሪ ባለሙያ ተቀጥሮ በርካታ ደረጃዎችን አጠናቆ ስራው በሐምሌ ወር ይጠናቀቃል፡፡

ከዚህ ጋር በማያያዝ የስልት ዝግጅቱን የሚደግፍና እውቀትና ልምዶችን ለመለዋወጥ የ REDD+ ፓይለቲንግ የመማማሪያ ኔትወርክ ለመመስረት ታቅዶ የሚመለከታቸውን 7 በREDD+ ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ በመስክ

ተመክሮ የሚታወቁ ድርጅቶች በመለየት የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ኔትወርኩን ለመመስረት የሚመክር የመጀመሪያ ዙር ስብሰባ ተካሄዷል፡፡ በዚህ ስብሰባ በቀጣይ የኔትወርኩ የአሰራር ሞዳሊቲዎችና ሌሎችን

ጉዳዮች በማደራጀት የሚያከናውን የሥራ ክፍፍል በማድረግ በቀጣይ ወር በመገናኘትና ለማስቀጠል ስምምነት ተደርሷል፡፡ ቀጣይ ስብሰባ በሐምሌ ወር ይካሄዳል፡፡

2.2.3. ንዑስ ክፍል 2.4. ማህበራዊና አካባቢያዊ ተጽዕኖ

በበጀት ዓመቱ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ብሔራዊ የ REDD+ ፕሮግራም ትግበራ ሊያስከትል የሚችለውን የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ በመለየት አስፈላጊ ኢንስተሩሜነቶችን ለማዘጋጀት በታቀደው መሰረት

አማካሪ ድርጅት ተቀጽሮ በየካቲት ወር ሥራውን የጀመረ ሲሆን የመጀመሪያውን ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአውደ ጥናት አቅርቦ በማስተቸት የተሰጡትን አስተያየቶች አካቶ ሪፖርቱን (Inception

Report) አቅርቧል፡፡ አማካሪ ድርጅቱ አራት ዓለም አቀፍ ዶነሮች የሚፈለጉዋቸውን ኢንስትሩሜንቶችን ማለትም (Strategic Environemntal and Social Assessment/SESA/, Environmental

and Social Management Framework/ESMF/ Resettlement Process

9

Page 11:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

Framework/ረጰፈ/ እና Process Framework/PF/) በማዘጋጀት ስራውን በነሐሴ ወር እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል፡፡

2.3. ክፍል 3. የደን ዘርፍ የልቀት መጠን (Reference Emissions) መወሰንና የልኬት

ዘገባና ኦዲት (MRV) ስርዓት ዝግጅት

ከዝግጅት ምዕራፉ ዋና ዋና ስራዎች ውስጥ የደን ዘርፍ የልቀት መጠን (Reference Emissions) መወሰንና የልኬት ዘገባና ኦዲት (MRV) ስርዓት ዝግጅት ቅልፍ ጉዳይ ሲሆን ይህ ስራ በቴክኒክ ይዘቱ ውስብስብ ከመሆኑ አንፃር በዚህ ረገድ ከፍተኛ ልምድ ካለው የዓለም እርሻና ምግብ ድርጅት ቴክኒካዊ ድጋፍና

በሴክሬታሪያቱ ዓለም አቀፍ ባለሞያ አማካኝነት በመመራት ትግበራ ላይ ይገኛል፡፡ በበጀት ዓመቱ ከዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ጋር የቴክኒክ ድጋፍ በመፈራረም ይህን ሰፊ ስራ ማስጀመርና በፍጥነት እንዲተገበር ለማድረግ

እቅድ ተይዞ በታቀደው መሰረት ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ጋር ቴክኒካዊ ድጋፍ ስምምነት በነሐሴ ወር 2006 ዓ/ ም ባለፈው በጀት ዓመት የተዘጋጀውን የMRV ፕሮጀክት ዓለም አቀፍ ተቀበይነት ያለው

ስታንዳርድ በመጠቀም ለማስፈፀም የ 3.9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የቴክኒክ ድጋፍ ስምምነት በመፈራረም ከመስከረም ጀምሮ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ የMRV ፕሮጀክት 2.5 ዓመት የሚፈጅ ፕሮጀክት ሲሆን ዳራው ሰፋ

ብሎ የአገር አቀፍ የደን ቅኝትና ምዝገባ ስርዓት በመዘረጋት ማላትም (Implementation of National Forest Inventory, establishing National Forest Monitoring System, establishing Forest Reference levels, FRLs and designing the MRV system) እና

አስፈላጊውን ሀገራዊ አቅም ግንባታ በመፍጠር ላይ ትኩረት አድርጎ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ ዝርዝር ተግባራትና ተጠባቂ ውጤቶች በፕሮጀክት ሰነዱ ውስጥ ማግኘት ይቻላል፡፡

በዚህ በጀት ዓመት ለመተግበር ታቅደው የነበሩት ተግባራትና አፈፃፀም ደረጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1. የብሔራዊ MRV ተቋም ከመገንባትና የመረጃ አያያዝ ስርዓት ከመዳሰስ አኳያ የብሔራዊ MRV አሀድ (MRV Unit) በአካባቢና ደን ሚኒስቴር ደን ዘርፍ ክፍል ውስጥ ተመስርቶ ለአሀዱ አስፈላጊ የሆኑ የቁሳቁስ ግዥ

ለማካሄድ የግዥ አቅድ ወጥቶ በዓለም ባንክ ይሁንታን የገኘ ሲሆን በቅርቡ የግዥ ጨረታው ለዓለም ዓቀፍ ጨረታ ይወጣል፡፡ አሀዱ በአሁኑ ሰዓት ባለው መጠነኛ ፋሲሊቲ በመጠቀም የደን ቆጠራ መረጃ ወደ ኮምፒውተር ማስገባትና የደን ካርታ ስራ እየተከናወነበት ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደፊት በሔራዊወን የ MRV ስርዓት በሀገር

አቅም ከማስፈፀም አንፃር የመ/ ቤቱንና የተዛማጅ መ/ ቤቶች አቅም ግንባት ፍላጎትና የመረጃ አያያዝ ስርዓት የመፈተሸ ስራ ተጀምሯል፡፡

2. ሌላው በዚህ ዓመት የታቀደው የሀገሪቱን የደን ሽፋን ካርታ መስራት (preparing forest cover map) እና የዘርፉን ልቀት ለመለካት ከሚያስፈልጉ መረጃዎች መካካል የውድመት መጠን መለካት (estimation of

10

Page 12:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

forest cover and historical forest cover change assessment/REDD+ activity data) ሲሆን መ/ ቤቱ ባወጣው ደን ትርጉም መሰረት (forest definition: smallest area ≥0.5 ha, tree height ≥2m and smallest canopy cover ≥20%) የደን ካርታ ስራ

ተሰርቶ የመስክ ማረጋገጫ ስራ ይቀረዋል፤ የተለያዩ የሳተላይት መረጃዎችን በመጠቀም የደን ውድመት መጠንም ተገምቷል፡፡ በቀጣይ መስከረም ላይ የበለጠ የማጥራት ስራ ተሰርቶ የደን ውድመት መጠን በሚጠበቅ ደረጃ ይቀመጣል፡፡ በዚህ ዙሪያ ለተግባሪ ባለሞያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሁለት የስልጠና ድጋፎች ተደርገዋል፡፡

ከደን ቆጠራና ደን ካርታ ስራ ጋር ተያይዞ ለመነሻ በቀረበው ደን ትርጉም ላይ የምክክር ዓውደ ጥናት ለማካሄድ እቅድ የተያዘ ቢሆንም ባለመሳካቱ በአማራጭነት የስትራቴጂ ግብረ ሀይል በጥልቀት

እንዲወያይበት በማድረግ ግብዓት የሚሆኑ ሀሣቦች ተገኝተው በMRV ባለሞያችን ሞያዊ ትንተና ተደርጎበት የደን ትርጉም በሚኒስቴር መ/ ቤቱ በኩል እንዲወሰን ተደርጓል፡፡ ለቀጣይም የቀረቡ ማዳበሪያ ሀሣቦችን ለማካተት የባለድርሻ ዓውደ ጥናት ለማካሄድ ከሚኒስቴር መ/ ቤቱ በጋራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

3. ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ተጀምሮ በዚህ በጀት ዓመት የቀጠለው የብሔራዊ ደን ቆጠራ (National Forest Inventory, NFI) ስራን ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ የመረጃ ስብሰባና ትንተና ስራዎችን ለማስፈፀም የታቀደ

ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚተገበረው 631 የናሙና ቦታዎች ማካከል በ 370 ያህሉ ቆጠራው የተጠናቀቀ ሲሆን የመረጃ ስብሰባው በህዳር 2008 ዓ/ ም እንዲጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ በመተግበር ላይ

ይገኛል፡፡ የደን ቆጠራ የጥራት ፍተሻና የስልጠና ድጋፍ (2) ስራዎች በ FAO እና በመ/ ቤቱ በኩል ተግባረዊ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ከ REDD MRV/FREL አንፃር የNFI ፈይዳ አሃደዊ የልቀት መጠን መረጃን (Emission

Factors, EFs) በላቀ ደረጃ ለመለካት የሚያስችል ሲሆን በቁጥር ሁለት ከሚገኘው መረጃ ጋር (REDD+ activity data) የዘርፉን ልቀት መጠን ለማስቀመጥ ነው፡፡ የደን ቆጠራ ሥራውን ለማሣለጥ ስድስት

ተሽከርካሪዎች የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ገዝቶ እንዲያቀርብ በወሰደው የፕሮጀክት ስምምነት መሠረት ተሸከርካሪዎቹ በ REDD+ ዝግጅት ምዕራፉ በጀት ተገዝተው የቀረቡ ሲሆን የስድስት ሾፌር ቅጥርም ተፈጽሟል፡፡ ሴክሬታሪያቱም የፋይናንስ ድጋፍ ከማድረጉም ባሻገር አስፈላጊ የሆነውን ውሳኝ የቴክኒክ ድጋፍና ክትትል በሴክሬታሪያቱ ዓለም አቀፍ MRV ባለሙያ አማካኝነት እያካሄደ ይገኛል፡፡

4. ሌላው በዓመቱ የታቀደው የዘርፉን ልቀት መጠን መመጠን (calculating National Forest Referecne Level(s)/FRL(s)/FRLs) ሲሆን ለዚህ ስራ አስፈላጊ የመረጃ ግብዓቶች ተደራጅተዋል፤

በሐምሌ ወር የመጀመሪ ደረጃ የልቀት መጠን መረጃ ወጥቶ በመስከረም ወር የተሸሻለ መረጃ ይወጣል፡፡ በዚህ አንፃር አንድ ስልጠና በመጋቢት ወር በ FAO ከፍተኛ ባለሞያ ለ 25 ሰዎች ተሰጥቷል፡፡

5. በተመሳሳይ በኦሮሚያ ለሚካሄደው ክልላዊ የየ REDD+ ፕሮገራም የMRV ስርዓት ዝረጋታ እና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎች በክልል ደረጃ በዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት፣ በሴክሬታሪየቱ MRV ባለሞያና በዓለም ባንክ

ቴክኒክ ድጋፍ አማካኝነት በበጀት አመቱ ተሰርቶ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ሲገኝ የኮነትራቱ የመጨረሻ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

11

Page 13:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

በአጠቃላይ የMRV ፕሮጀክት አፈፃፀም ቀደም ሲል የመዘገየት አዝማሚያ ቢያሳም አሁን በፍጥነት እየተተገበረ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አፈፃጸም በዚህ ከቀጠለ ሀገሪቱ በዚህ አንፃር የሚጠበቅባትን የስርዓትና አቅም ግንባታ ዝግጅት

ቀድማ እንደምታሳካ የሚያመላክት ነው፡፡

ክፍል 6 ፡ ክትትል፣ ግምገማና ሪፖርት

በዚህ ዓመት የREDD+ ሀገር አቀፍ የዝግጅት ሂደቱን ውጤትን መሠረት ባደረገ ማዕቀፍ ለመቅረጽ በተደረገው ጥረት አማካሪ ባለሙያ ከዓለም ባንክ በተደረገ ድጋፍ የአፈጻጸም መለኪያ ማዕቀፍ (REDD+

Readiness M&E Framework) R-PP ውን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡ እንዲሁም ለ FCPF ወቅቱን

የተጠበቀ 2 የስድስት ወራት ዘገባ በባንኩ የዘገባ ቴምፕት ተዘጋጅቶ ተልኳል፤ ለመስሪያ ቤቱም አስፈላጊው

የየሩብ ዓመት ሪፖርቶች ( ይህንን ጨምሮ) በወቅቱ ተዘጋጅተው ተልከዋል፡፡

የዝግጅት ምዕራፍ የአጋማሽ የትግበራ ዘመን (Mid-Term Report) ግምገማና ሪፖርት በአማካሪ ባለሞያ

ለማሰራት በተያዘው እቅድ መሠረት የዓለም ባንክ ወደ መስከረም እንዲተላለፍ በሰጠው አቅጣጫ መሠረት

የሪፖርቱ ዝግጅት እንዲዘገይ የተደረገ ቢሆንም በአሁን ወቅት የአማካሪ ባለሙያ ጨረታ የፍላጎት መግለጫቸውን

ግምገማ ተጠናቆ የተመረጡት ባለሙያ INCEPTION REPORT በማቅረብ ስራ እንዲጀምሩ ተጋበዘዋል፡፡

12

Page 14:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

3. የፊዚካል ሥራዎች አፈጻጸም ሠንጠረዥ

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

1 ክፍል 1. የዝግጅት አደረጃጀትና ምክክር

1.1 ንዑስ ክፍል 1.1. ብሔራዊ የሬድ ፕላስ ሥራ አመራር አደረጃጀት

1.1.1

ውጤት፡ የተደራጀና በሥራ ላይ ያሉ ቁልፍ የሬድ ፕላስ አደረጃጀት መዋቅር

ሀ ብሔራዊና ክልላዊ የ REDD+ SC, TWG and TF ስብሰባዎች

ማድረግ

ብሔራዊ የፕሮጀክቱ ስቲሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ በቁጥር 2 1 - - 2 1 50 ብሔራዊ የፕሮጀክቱ TWG ስብሰባ በቁጥር 2 1 1 100 2 2 100 ብሔራዊ የፕሮጀክቱ ግብረ ሀይል ስብሰባ (SESA, MRV, Strategy

TF)በቁጥር 12 3 3 100 12 11 92

ክልላዊ የፕሮጀክቱ ስቲሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ በቁጥር 5 - - - 5 1 20 ክልላዊ የፕሮጀክቱ TWG ስብሰባ በቁጥር 6 2 - - 6 2 33

ለ የአባላትን የስብሰባ ተሣትፎ ማረጋገጥ ተሣትፎ በመቶኛ

67 67 80 >100 67 80 >100

1.1.2

ውጤት፡ ያደገ ብሔራዊ የቴክኒክ ሱፐቪዥን እና ፈንድ አስተዳደር አቅም፣

ሀ የሬድ ፕላስ ሴክሬታሪያት የሰው ሃይል ማሟላት በመቶኛ 100 - - - 100 100 100ለ የኦሮሚያ ሬድ ፕላስ ማስተባበሪያ ዩኒት የሰው ሀይል ማሟላት በመቶኛ 100 100 100 100 100 100 100ሐ ክልላዊ የሬድ ፕላስ ማስተባበሪያ ዩኒት ማቋቋም ( የተቋቋመ ዩኒት ብዛት) በቁጥር 3 3 3 100መ ለሴክሬታሪያቱ የተሸከርካሪ ግዥ ማካሄድ፣ በቁጥር 17 17

ሠ ለሴክሬታሪቱና ለክልል ማስተባበሪያ ዩኒት ባለሙያች የአቅም ግንባታ በቁጥር 10 1 - 10 3 30

13

Page 15:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

ሥልጠና መስጠት፣

ረ የ COP ተሣታፊ መደገፍ ( ለሬድ ሴክሬታሪያትና አደሚ1) በቁጥር 3 - - - 3 5 >100ሰ የውጭ ሀገር የልምድ ልውውጥ ጉብኝት በሬድ ፕላስ የተሻሉ ላይ ሀገሮች

ማካሄድ ( ለሬድና አደሚ)፣በቁጥር 15 - - - 15 11 73

ሸ የውጭ ሀገር የልምድ ልውውጥ ጉብኝት በሬድ ፕላስ የተሻሉ ላይ ሀገሮች ማካሄድ ( ለክልል ሀላፊዎች)፣

በቁጥር 16 - 16 -

ቀ በሬድ መሠረታዊ ሀሣቦች፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በ MRV ፣ ካርቦን

ዳሰሳ ሥልጠና ማዘጋጀት ( ኦሮሚያ ማስተባበሪያ ዩኒት)፣በቁጥር 20 - - - 20 - -

በ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ማካሄድ ( በተካሄደ የልምድ ልውውጥ) ( ኦሮሚያ ማስተባበሪያ ዩኒት)፣

በቁጥር 1 1 - - 1 - -

ተ የ COP ተሣታፊ መደገፍ ( በተሣታፊ ብዛት) ( ኦሮሚያ ማስተባበሪያ

ዩኒት)በቁጥር 4 - - - 4 2 50

ቸ የሴክሬታሪያቱን ሂሣብ አሰራር ኦዲት ማድረግ፣ በቁጥር 1 - - - 1 1 1001.2 ንዑስ ክፍል 1.2. ምክክር፣ ተሣትፎና ተደራሽነት

1.2.1

ውጤት፡ ያደገና የተተገበረ ውጤታማ የተግባቦት መካኒዝም ከሬድ ፕላስ ጋር የሚስማማ በሁሉም ደረጃ በተገቢው የመረጃ ፎርማት አስፈላጊውን መረጃ ማሰራጨት፣

ሀ የተግባቦት (ኮሙኒኬሽን) ስትራቴጂ ማዘጋጀት በተዘጋጀ ሰነድ

1 - 1 - 1 1 100

ለ የተዘጋጀውን የተግባቦት (ኮሙኒኬሽን) ስትራቴጂ ተግባራዊ ማድረግ በመቶኛ 30 10 10 100 30 20 67ሐ የኮሚኒኬሽን ሚዲያ በመጠቀም መረጃ ማድረስ

1. የህትመት ሚዲያ መጠቀም በተጠቀምነው ሚዲያ በቁጥር

4 4 6 >100 በአራት ቋንቋዎች ብሮሸር ማዘጋጀት በቁጥር 40000 1000 40000

1 አደሚ = አካባቢና ደን ሚኒስቴር

14

Page 16:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

0

የዜና መጽሔት ( ስድስት ወር) ማዘጋጀትበቁጥር 6000

3000

- - 6000 - -

የግድግዳ ካለንደር ማዘጋጀት በቁጥር 2500 - - - 2500 2500 100 የተለያዩ የጋዜጣ ህትመቶች ደንበኛ መሆን ( በጋዜጣ ዓይነት

ብዛት)በቁጥር 5 5 5 100 5 5 100

ሌሎች የኮሚኒኬሽን ቁሣቁሶችን መጠቀም ( በተጠቀምነው

የማቴሪያል ብዛት)በቁጥር 4 4 4 100

2. የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ መጠቀም በተጠቀምነው ሚዲያ በቁጥር

3 3 3 100 3 4 >100 ቶክ ሾው ማዘጋጀት (1 በሬዲዮ እና 1 በቲቪ) በቁጥር 2 - - - 2 4 >100 የሚዲያ ሽፋን ማግኘት (1 በሬዲዮና 1 ቲቪ) በቁጥር 2 1 1 100 2 2 100

ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት በቁጥር 2 1 - - 2 - -

በሬድ ፕላስ ቃለ መጠይቅ መስጠት በቁጥር 2 - - - 2 3 >100 የጽሁፍ መልእክት በሬድ ዙሪያ ለሞባይል ተጠቃሚዎች

ማሰራጨትበቁጥር

12 ሚሊዮን

- - -12

ሚሊዮን

12 ሚሊዮን

100

3. በሚዲያ ማስታወቂያ መጠቀም ( ሬዲዮ፣ ቴሌቪዢንና ጋዜጣ) በድግግሞሽ 30 10 - - 30 10 334. ማህበራዊ ድረ ገጾችን (face book, linkedin, Twitter etc.)

በመጠቀም ሬድን ማስተዋወቅ ( በሣምንት አንድ ጊዜ በእያንዳንዱ

ድረ ገጽ)

በማህበራዊ ድረ ገጽ ብዛት

2 2 2 100 2 2 100

በቁጥር 48 12 12 100 48 48 100

5. ሚዲያ ሞኒተሪንግ ማካሄድ ( ሬድ ፕላስን በተመለከተ) በሁለት

ሣምንት አንድ ጊዜ

በክትትል ብዛት

24 6 6 100 24 24 100

መ ድረ ገጽ ማዘጋጀት ( በአማርኛና በእንግሊዘኛ) በብዛት 1 1 1 100

15

Page 17:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

ሠ የኮሚኒኬሽን መሣሪያዎች ግዥ ማካሄድ ( ፎቶ ካሜራ፣ ቪዲዮ ካሜራ እና መቅረጸ ድምጽ)

በብዛት 3 3

ረ በኦሮሚያ ሬድ ፕላስ ዩኒት የተግባቦት ዘዴዎች አጠቃቀም

የዜና መጽሔት ( ቡክ ሌት) ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣ በቁጥር 5000 - - - 5000 - - ብሮሸር ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣

በቁጥር 3000 -1000

- 3000 1000 33

በራሪ ወረቀቶችን (ሊፍሌት) ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣ በቁጥር 5000 - - - 5000 - - የዜና ዝግጅት (ኒውስሌተር) መጽሔት ማዘጋጀት፣ በቁጥር 2000 - - - 2000 - -

ማስታወሣ ደብትር ( የሬድ አርማ ያለበት) ማዘጋጀትና መጠቀም በቁጥር 1000 - - - 1500 1500 100ቲ- ሸርት ማዘጋጀት ( የሬድ አርማ ያለበት)፣ በቁጥር 750 - - - 750 750 100

ኮፍያ ማዘጋጀት ( የሬድ አርማ ያለበት)፣ በቁጥር 750 - - - 750 750 1001.2.

2 ውጤት፡ በሬድ ፕላስ የጨመረ የሥልጠናና ግንዛቤ የመፍጠር አቅም ( በአሠልጣኞች ሥልጠና)፣

ሀ የሥልጠና ጥራዝ በሬድ ፕላስ ላይ ማዘጋጀትና ማሻሻል

ቴክኒካል የሥልጠና ጥራዝ ( በደን ማኔጅመንት፣ ሬድ ፕላስ፣ ካርቦን

…ፋይናንስ .) ማዘጋጀት፣በተዘጋጀ ጥራዝ

4 - - - 4 4 100

የሥልጠና ጥራዞችን ማሣተም (100 ቅጅ እያንዳንዱን አራት

ጥራዝ)፣ በቅጂ ብዛት 400 - 400 - -

ለጋዜጠኞችና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሥልጠና መስጠት በቁጥር 50 - 50 - - ለደን ባለሙያዎች በደን አስተዳር ዙሪያ ሥልጠና መስጠት በቁጥር 16 - 16 - -

ለ በሬድ ፕላስ ዙሪያ ለትምህርትና ምርምር ተቋማት ገለጻ መስጠት በገለጻ ብዛት 3 - - - 3 1 33ሐ ሬድ ፕላስን በዩኒቨርስቲዎች የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ካሪኩለም

እንዲካተት ማድረግ፣ በኮርስ ብዛት 2 2 2 100 2 2 100

16

Page 18:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

የካሪኩለም ክለሳ ውይይቶች መደገፍ በተደረገ ድጋፍ

1 1 1 100 1 1 100

መ በደቡብ- ደቡብ የመማማሪያ ተግባራት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎችን

ማሣተፍ (5 በሬድ ፕላስ የሚደገፍ)፣በተሣታ ብዛት

15 - - - 15 3 20

ሠ ሥልጠናና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችን በሬድ ፕላስ ዙሪያ በክልሎች

ማካሄድ፣

በሥልጠና መድረክ ብዛት

4 1 2 >100 4 7 >100

ረ የምክክርና ተሣትፎ የሥራ እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ( በፋርም አፍሪካ

የተዘጋጀውን - ኦሮሚያ ሬድ ፕላስ ዩኒት)በእቅዱ መሰረት

ሰ የሀገር ውስጥ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ማካሄድ (ኦማዩ) በተሣታፊ ብዛት

20 - - - 20 28 >100

ሸ በአየር ንብረት ለውጥና በመሠረታዊ ሬድ ፕላስ ጽንሰ ሀሣብ ዙሪያ

ለባለሙያዎች ሥልጠና መስጠት፣ (ኦማዩ)በሥልጠና ብዛት

1 - - - 2 - -

1.2.3

ውጤት፡ ከደን ጋር የተያያዙ የህብረተሰብ ክፍሎች የጨመረ አቅም፣

ሀ ለማህበረተሰብ አደረጃጀቶችና ለተወካዮች በእቅድ፣ አቀራረብና በድርድር

ክህሎት ዙሪያ ሥልጠና መስጠት፣በቁጥር 100 - - - 100

ለ በደን ጥገኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሬድ ፕላስ አደረጃጀት ውስጥ

ውክልናና ተሣትፎ ማድረግ፣

በሁሉም ክልላዊ የሬድ ፕላስ TWG ውስጥ ያላቸው ውክልና የሚጨምር ቢያንስ 1

በባላድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ያላቸው ውክልና የሚጨምር ቢያንስ 5

1.2.4

ውጤት፡ የተረጋገጠ ምክክር በባለድርሻ አካላት፣ በደን ጥገኛ የሆኑ ህብረተሰብና የአካባቢው ማህበረሰብ በብሔራዊ፣ ክልላዊና በአካባቢ ደረጃ የተካሄደ፣

ሀ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሬድ ፕላስ ኮንፈረንስ ማካሄድ፣ በኮንፈረንስ 1 1 1 100 1 1 100

17

Page 19:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

ብዛት

ለ ክልላዊ የሬድ ፕላስ ኮንፈረንስ ማካሄድ በኮንፈረንስ ብዛት

4 1 1 100 4 4 100

ሐ በሁሉም ወረዳዎች የባለድርሻ አካላት ፕሮፋይል ማዘጋጀት ( በክልል

ማስተባበሪያ ዩኒቶች)በክልል ብዛት

1 1 - - - - -

2 ክፍል 2. የሬድ ፕላስ ስትራቴጂ ማዘጋጀት

2.1 ንዑስ ክፍል 2.1. በመሬት አጠቃቀም፣ የመሬት አጠቃቀም ለውጥ መንስዔዎች፣ በደን ህግ፣ ፖሊሲና አስተዳደር ላይ ጥናት ማካሄድ፣

2.1.1

ውጤት፡ በደን ምንጣሮና መመናመን መንስዔዎች የተደረገ ትንተና (ጥናት) ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደ ውይይት፣ በቅደም ተከተል የተለየና የተሠራጨ የጥናት

ውጤት መረጃ፣

ሀ የደን ምንጣሮና መመናመን መንስዔዎች ጥናት ማጠናቀቅ በጥናት ብዛት

2 - 1 - 2 1.75 87.5

ለ በጥናቱ ግኝቶች ላይ የሀገራዊና ክልላዊ ምክክር መድረክ ማዘጋጀት፣ በመድረክ ብዛት

2 1 1 100 2 1 50

ሐ የጥናቱን ውጤት በሬድ ፕላስ ድረ ገጽ ማሠራጨት በተሰራጨ ሰነድ

1 - - - 2 - -

2.1.2

ውጤት፡ ለሬድ ፕላስ ትግበራ የተለዩ ህጋዊና ተቋማዊ ክፍተቶችና የታቀዱ አስፈላጊ ድርጊቶች፣

ሀ በህጋዊና ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ጥናቱን ማጠናቀቅ በጥናት ብዛት

1 - 1 - 1 1 100

ለ በጥናቱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሀገራዊና ክልላዊ ምክክር ማካሄድ በመድረክ ብዛት

2 2 2 100 2 2 100

ሐ የጥናቱን ውጤት በሬድ ፕላስ ድረ ገጽ ማሠራጨት በተሰራጨ ሰነድ

1 1 1 100 1 1 100

2.2 ንዑስ ክፍል 2.2. የሬድ ፕላስ ስልታዊ አማራጮች

2.2. ውጤት፡ የተተነተነ፣ ምክክር የተደረገበትና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ስልታዊ አማራጮች፣

18

Page 20:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

1ሀ በሁሉም ደረጃ ማስረጃ መሠረት ያደረጉ የሬድ ፕላስ ጥናቶችን ማሳተም

(1 በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ 1 ክልል አቀፍ እና 3 በማህበረሰብ ወይም

ፓይለት ደረጃ)

በታተሙ ሰነዶች ብዛት

5 3 - - 5 - -

ለ በተመረጡ ስልታዊ ስልቶች ላይ የአዋጭነት ጥናት ሰነድ ማዘጋጀት በተዘጋጀ ሰነድ

1 - - - - - -

ሐ ረቂቅ የሬድ ፕላስ የትግበራ ስልት ማዘጋጀት በተዘጋጀ ሰነድ

1 1 1 100 1 1 1002.2.2

ውጤት፡ በፓይለት ቦታዎች የተሞከሩና የጸደቁ ስልታዊ አማራጮች፣

ሀ የፓይለት ቦታዎች መረጣ ጥናት ማካሄድ በጥናት ብዛት

1 1 80 በመቶ 80

ለ በጥናቱ ውጤቶች ላይ የምክክር ዓውደ ጥናት ማካሄድ በዓውደ ጥናት ብዛት

3 - - - 3 - -

ሐ የጥናቱን ውጤትና የተሰጡ ቁልፍ አስተያየቶች በድረ ገጽ ማሰራጨት በህትመት ብዛት

1 - - - 1 - -

መ የፓለት የአቅም ግንባታ ሥራዎች

1 ለፓይለት ተግባሪዎችና ሥራ ሃላፊዎች ሥልጠና መስጠት

በፕሮጀክት አመራር ሥልጠና መስጠት በሠልጣኝ ብዛት

20 20 - - 20 - -- -

- በሬድ ፕላስ ፓይለት ዲዛይን፣ ካርቦን ክትትል፣ ወዘተ ሥልጠና መስጠት በሠልጣኝ ብዛት

10 10 - - 10 - -

2 የባለድርሻ አካላት ምክክር

ከተጎጂ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የምክክር፣ ተሣትፎና ማኔጅንት ኦፍ

ኤክስፔክቴሽን፣

በምክክር ብዛት

1 1 - - 1 - -

19

Page 21:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

የመረጃ ስርጭትና ግንዛቤ ማስጨበጥ ለሰፊ ባለድርሻ አካላት በቁጥር 1 1 - - 1 - -3 ጥናቶችን ማካሄድ

ቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA

and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites) ማካሄድ፣

በሳይት ቁጥር

1 1 - - 1 - -

የሬድ ፕላስ የመማማሪያ ኔትወርክ መመስረት፣ በብዛት 1 1 1 100 1 1 100 የማገዶና እና ግንባታ እንጨት አቅርቦትና ፍላጎት ጥናት በፓይለት ቦታዎች

ማካሄድ፣

በጥናት ብዛት

1 - - - 1 - -

4 ለአሳታፊ ደን አስተዳዳር የዝግጅት ሥራዎች

የአቅም ግንባታ ሥራዎች ማከናወን - ለማህበራት በማህበራት ብዛት

3 2 - - 3 - -

2.4 ንዑስ ክፍል 2.4. ማህበራዊና አካባቢያዊ ተጽዕኖ

2.4.1

ውጤት፡ የተጠናቀቀ የ SESA ጥናትና ግኝቶች ከሬድ ስልት ጋር የተዋሀደ፣

ሀ የ SESA ጥናት ማጠናቀቅ በጥናት ብዛት

1 1 75 በመቶ 75

ለ የምክክር ዓውደ ጥናት በጥናት ውጤቱ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር

ማካሄድ

በዓውደ ጥናት ብዛት

1 1 - - 1 - -

ሐ ሀገር አቀፍ ሥልጠና በ SESA ዙሪያ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ማካሄድ በተሣታፊ ብዛት

95 95 - - 95 - -

2.4.2

ውጤት፡ የተጠናቀቀ የ ESMF ጥናትና ግኝቶች ከሬድ ስልት ጋር የተዋሀደ

ሀ ESMF ማዘጋጀት በተዘጋጀ ሰነድ

1 - - - 1 75 በመቶ

75

20

Page 22:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

ለ የምክክር ዓውደ ጥናት በሁሉም የባለድርሻ አካላት ተሣትፎ ማካሄድ፣ በዓውደ ጥናት ብዛት

1 1 - - 1 - -

3 ክፍል 3. የልቀት መነሻ ደረጃ/ ማጣቀሻ ደረጃ

3.1.1

ውጤት፡ የተቆጠረ የደን ሀብት፣ የተጠናና በካርታ የተለየ ታሪካዊ የደን ሽፋን ለውጥ

ሀ በቀረበው የደን ትርጉም ላይ የምክክር ዓውደ ጥናት ማካሄድ በዓውደ ጥናት 1 1 - 1 - -ለ የጸደቀ ሀገር አቀፍ የደን ትርጉም በቁጥር 1 1 - - 1 1 100ሐ ሀገር አቀፍ የደን ቆጠራ ማካሄድ በተገኘ መረጃ 1

መ ለደን ቆጠራ የሚያገለግሉ ተሸከርካሪ ግዥ በተሽከርካሪ ብዛት

6 - - - 6 6 100

ሠ ለኦሮሚያ የአቅም ግንባታ ሥራዎች - ለደን ቆጠራ የሚያገለግል

የተለያዩ የደን ቁሣቁስ ግዥ ማካሄድ ( ጂአይኤስ፣ ኮምፒዩተር፣

…ፕሮጀክተር .)በጥቅል 1 - - - 1 - -

የተሽከርካሪ ግዥ ( ፎር ዊል ድራይቭ 2 ዳብል ጋቢና) በተሸከርካሪ ብዛት

2 - - - 2

4 ክፍል 4. ለደንና ለደህንነት ( ማህበራዊና አካባቢያዊ ሴፍጋርድ) የክትትል ሥርዓት

4.1 ንዑስ ክፍል 4.1. ብሔራዊ የደን ክትትል ሥርዓት

4.1.1

ውጤት፡ በMRV ላይ የመንግስታዊ፣ የምርምርና እና የሲቪል ማህበራት ተዋናይ የጨመረ አቅም በሀገር አቀፍና ባልተማከለ ደረጃ፣

ሀ የዳሰሳ ሪፖርት በአስፈላጊ ሶሺዎ ኢኮኖሚ እና አካባቢያዊ የደን ቆጠራ

መረጃዎችን ለማዘጋጀት መረጃዎችን መሰብሰብ እና መረጃውን

ለሴፍጋርድን መጠቀም፣

በሪፖርት ብዛት

1 1 - - - - -

ለ ለመስክ ክሩ ሠራተኞች በደን ቆጠራ ለሚሣተፉ በመረጃ አሰባሰብ፣

ጂፒኤስ/ ጂአይኤስ አጠቃቀም ሥልጠና መስጠት

በሥልጠና ብዛት

2 1 1 100 2 2 100

21

Page 23:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ተ.ቁ የተግባራት ዝርዝር መለኪያየዓመቱ እቅድ

የ 4 ኛው ሩብ ዓመት እስከዚህ ሩብ ዓመት

ምርመራእቅድ ክንውን

አፈጻጸም በመቶኛ

እቅድ ክንውንአፈጻጸም በመቶኛ

4.1.2

ውጤት፡ የሚሰራ ለዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ፣ ለሌሎች ፋይዳ፣ ለአስተዳደርና

ለሴፍጋርድ ያካተተ የጋራ የመረጃ ሥርዓት

ሀ ሥልጠና በፕሮጀክት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዙሪያ መስጠት፡- ለሬድ ፕላስ ባለድርሻ አካላትና ለክልል ባሙያዎች

በሠልጣኝ ብዛት

20 20 22 >100 20 22 >100

6 ክፍል 6 ፡ ክትትል፣ ግምገማና ሪፖርት

6.1.1

ውጤት፡ በመስራት ላይ ያለ የተመከረበት የፕሮግራም ክትትልና ግምገማ ማዕቀፍ

ሀ የ PMF ( የአፈጻጸም መለኪያ ማዕቀፍ) ሰነድ ማዘጋጀት በተዘጋጀ ሰነድ 1 - - - 1 1 100ለ የሩብ ዓመት ሪፖርት ማዘጋጀት በሪፖርት ብዛት 4 1 1 100 4 4 100ሐ የግማሽ ዓመት ሪፖርት ማዘጋጀት (FCPF ሪፖርት) በሪፖርት ብዛት 2 - - - 2 2 100

6.1.2

ውጤት፡ የተገመገመ የሬድ ፕላስ ዝግጁነት

ሀ የግማሽ ዘመን ግምገማ ማካሄድ በቁጥር 1 1 1

= ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

22

Page 24:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

4. የፕሮጀክቱ ትልልቅ ግዥዎች ያሉበት ሁኔታ

በዚህ በጀት ዓመት ትልልቅ የአገልግሎትና የቁሳቀቁስ ግዥዎች ታቅደዋል፡፡ አብዛኛው የፕሮጀክቱ የአልግሎት ግዥ የለበት ደረጃ ከላይ በተለያዩ ክፍሎች ለመጠቆም ተሞክሯል፡፡ በዚህ ክፍል በበጀት ዓመቱ የተያዙ ዋና ዋና የዕቃ ግዥዎች አፈጻጸም ቀርቧል፡፡

በበጀት ዓመቱ 5 ለክልል REDD+ ማስተባበሪያ ዩኒቶች እና 1 ለሴክሬታሪያቱ የሚዉል በጠቅላላ 6 ፒክ አፕ የመስክ መኪኖች ግዥ ለመፈፀም አቅደን የስድስቱ መኪናዎች በቴክኒክና ዋጋ ላሸነፈው

ድርጅት ተሸከርካሪቹን እንዲያቀርብ አስታውቀናል፤ የሌተር ኦፍ ክሬዲት መክፈት ስራ ጀምረናል፡፡

በተጨማሪም ከመስሪያ ቤቱ አዲስነት አንፃር ብዙ የአቅም ግንባታ ስራ አስፈላጊነት የክልል አቅምን ከመደገፍ አኳያ የዓለም ባንክን ድጋፍ በማግኘት በዚህ ዓመት አጋማሽ አካባቢ የዕቅድ ክለሳ በማድረግ 11 የመስክ ተሸከርካሪ መኪናዎችና 50 ሞተር ሣይክሎች ለመግዛት በባንኩ በፈቀደው

መሠረት የግዥ ኮንታራቱን መ/ ቤቱ ከተመረጡ አቅራቢዎች ጋር ተፈራርሟል፤ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ተከፍቷል፡፡ ከመኪናዎቹ ውስጥ አንዱ መኪና የሴክሬታሪያቱ ሲሆን ድጋሜ በወጣው ጨረታ ውስጥ

የተካተተ ነው፡፡

ለሚኒሰቴር መ/ ቤቱ የተለያዩ ክፍሎች እና ለኦሮሚያ REDD+ ማስተባበሪያ ዩኒት የቢሮ ዕቃዎችና ኮምፒውተሮች እና ሌሎች የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ግዥ ተካሂዶ ተሰራጭቷል፡፡

5. ከዕቅድ ውጭ የተከናወኑ ተግባራት

በ በጀት ዓመቱ በርካታ ከዕቅድ ውጭ የተከናወኑ ስራዎች ተስርተው በዋናነት የሚከተሉትን ያካታተ ሲሆን በግምት የሴክሬታሪያቱን 6 ሳምንታት ያህል ፈጅተዋል፡፡ እነርሱም፤

አራት የዓለም ባንክ ሚሽኖች፣

ሁለት የኖርዋይ ሚሽኖች፣

በርካታ የዓለምና እርሻ ድርጅት ሚሽኖችና የማስተባበር ስራዎች ( ፕሮጀክቱን ማስተባበር ጨምሮ) ናቸው፡፡ ለቀጣይ እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ዕቅድ ይነደፋል፡፡

6. የፋይናንስ አጠቃቀም

ከዓለም ባንክ ለእቅድ ዘመኑ ሥራዎች ማስፈጸሚያ እስከዚህ ሩብ ዓመት ከተመደበው ብር 91,360,427.00 በጀት ውስጥ ብር 22,188,331.50 ገንዘብ የመንግስትን የፋይናንስ ህግ

በተከተለ አግባብ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን አፈጻጸሙም 24.3 በመቶ ነው፡፡ ሆኖም ግን ለአራት በአማካሪ

23

Page 25:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

ለሚከናወኑ ጥናቶች፣ ለአስራ ሰባት ተሸከርካሪ መኪኖችና ለሃምሳ ሞተር ሳይክሎች ውል የተያዘባቸውና የግዥ ሂደታቸው ተጠናቆ ቅድሚያ የመጀመሪያ ክፍያ ተፈጽሞ ሥራው በመፋጠን ላይ ያሉ ተግባራት ወጪያቸው አስገዳጅ ስለሆነ በቀጣዩ አዲሱ የበጀት ዘመን መጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ እስከ ሁለተኛው ወር የሚጠናቀቁ

ናቸው፡፡ ለነዚህም ተግባራት ብር 48,176,059.50 በበጀት ዓመቱ ቀሪ ክፍያ የተያዘላቸው ሥራዎች ናቸው፡፡ ውል የተገባባቸውን ክፍያዎች ከግምት ውስጥ ስናስገባ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ብር

70,364,391.00 ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን አፈጻጸሙም 77 በመቶ ይሆናል፡፡

7. ያጋጠሙ ችግሮች

በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ በትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች፡- በመካሄድ ላይ ያሉ ጥናቶች መጓተት

በውስጥ አሰራር መጓተት፣

ክፍያ በወቅቱ ባለመፈጸም፣

በባንኩ በሚሰጥ ተለዋዋጭ የዲዛይን እቅድ፣

የባንኩ የግዥ ሂደት መርዘምና ይህንንም ያገናዘበ ውስጣዊ ቅድመ እቅድ ዝግጅት ያለማድረግ፣

የውጭ ሀገር ልምድ ልውውጥ ጉብኝቶች ከተባባሪ ሀገሮች ጋር የሚተገበር በመሆኑ ለማከናወን ጊዜ መውሰዱ፤

የውጭ ሥልጠናዎች በተለያዩ ምክንያቶች በእቅዱ መሠረት አለማካሄድ፣

አንዳንድ የግዥ ሥራዎች በወቅቱ አለመተግበር፣

የተሽከርካሪ ግዥ፣

የቢሮ እቃዎችና ቁሣቁስ፣

የፋይናንስ አጠቃቀም ዝቅተኛ መሆን ምክንያቶችም፡- የአንድ ተሸከርካሪ ግዥ በስፔሲፊኬሽን ችግር ምክንያት በመሰረዙና ድጋሚ እንዲሰራ መመሪያ

በመሰጠቱ የተመደበውን በጀት በጊዜው ጥቅም ላይ አለማዋል፣

እንዲሁም 16 የመኪናዎች ግዥ ዕቅድ ክለሳ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ በጀት በማሳየቱ፣

አንድ የውጭ ሀገር የልምድ ልውውጥ ጉዞ በወቅቱ አለመካሄዱ፣

የጥናቶች መጓተት ጋር ተያይዞ በወቅቱ ሊከፈል የሚገባው ገንዘብ አለመከፈሉ፣

የውጭ ሥልጠና ዕድልን በተለያዩ ምክንያቶች በወቅቱ ያለመካሄድ ናቸው፡፡

8. የተወሰዱ የመፍትሔ ሀሣቦች

ትልቁ ችግር የግዥ ሂደትና የጥናቶች ትግበራ መጓተት ሲሆን በመስሪያ ቤታችን ልዩ ከፍተኛ አመራር ጀምሮ ትኩረት እንዲሰጣቸው መመሪያ በማስተላለፍ የሚመለከተው ሁሉ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ለቀጣይ የባንኩን

24

Page 26:   · Web viewቴክኒካል ጥናቶችን በሬድ ፕላስ ፓለት ዙሪያ (RL/REL, C & P, SESA and Drivers of D & D; a total of 12 studies for 3 pilot sites)

የግዥ ሂደት ባገናዘበ መልኩ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በቂ ጊዜ በመስጠት የግዥ ሂደቶችን ለማቀላጠፍ ዝግጅት ይደረጋል፡፡

25