Top Banner
7/11 ቃና ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድ አንደኛ ዓመት ቁጥር 003 አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ነፃነትን በኡጋንዳ ፈለጋት ግና... የኢትዮጵያን ቪሌጅ ባለቤት ምን ይላሉ? ሞትን ማምለጥ ማን ይናገር… ፎቶዎች (ልዩ ዘገባ) በእዚህ ዕትም m የእኛ ሰው በሲድኒ m ኢትዮጵያዊቷ በኒውዮርክ m የ“3ቱ ወፎች” ኮከብ በካምፓላ m “የዘር ግንዳችን ከኢትዮጵያ ነው” m“አለምዬ ሶራ”በካባካ ቤተመንግስት ገጽ 4- 8
24

Habeshawi Kana 003

Mar 08, 2016

Download

Documents

Habeshawi Kana

Vol 1, 3rd edition
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 1

7/11ቃናሐበሻዊ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድአንደኛ ዓመት ቁጥር 003

አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ነፃነትን በኡጋንዳ ፈለጋት ግና... የኢትዮጵያን ቪሌጅ ባለቤት ምን ይላሉ? ሞትን ማምለጥ ማን ይናገር… ፎቶዎች

(ልዩ ዘገባ)

በእዚህ ዕትምm የእኛ ሰው በሲድኒ

m ኢትዮጵያዊቷ በኒውዮርክ

m የ“3ቱ ወፎች” ኮከብ በካምፓላ

m “የዘር ግንዳችን ከኢትዮጵያ ነው”

m“አለምዬ ሶራ”በካባካ ቤተመንግስት

ገጽ 4- 8

Page 2: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና2

ዜና

ቃናሐበሻዊበሐበሻ ኮሚዩኒኬሽን ሊትድ በየ15 ቀኑ

የሚታተም ጋዜጣ

ዋና አዘጋጅ- ተስፋለም ወልደየስ

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ

ዩጋንዳ ካምፓላ

ጋባ ሮድ-ካንሳንጋ

ዲዲስ ወርልድ አጠገብ ባለው የናይል ቢራ

ማከፋፈያ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 6

ስልክ +256-778-693669

ኢሜይል [email protected]

ከተመሰረተ ከአስር ዓመታት በላይ ያስቆጠረው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኡጋንዳ መካነ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በካምፓላ ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው፡፡እሁድ ሐምሌ 3 ቀን 2003 ዓ.ም ይካ

ሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ጠቅላላ ጉባኤ ከተያዙት አጀንዳዎች መካከል በተሻሻለው የቤተክርስቲያኒቱ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ላይ መወያየትና ማጽደቅ እንደዚሁም ለአዳዲስ የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ ይገኝበታል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ መተዳደሪያ ደንብ

ተሻሽሎ እንዲዘጋጅ የተደረገው ስልጣንና ኃላፊነትን በመለየት አንዳንድ ጉድለቶች አሉበት፣ ከዘመኑ ጋርም የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም በሚል ነው። አሁን በስራ ላይ ያለው ደንብ ቤተክርስቲያኒቱ ከተመሰረተች ጀምሮ ሲሰራበት የቆየ ነው።ከደንብ ማሻሻል በተጨማሪ እንደ አጀ

ንዳ የቀረበው የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ “መተዳደሪያ ደንቡ ከሚፈቅደው ውጪ ስልጣን ላይ ቆይተዋል” በሚል ነው፡፡ “ለረጅም ጊዜ ቦታው ላይ ከመቆየታቸው የተነሳም መሰላቸት ይታይባቸዋል” በሚል ቅሬታ ነው አዲስ ስራ አስፈጻሚ ለመምረጥ ሀ

ሳብ የቀረበው፡፡ በጠቅላላ ጉባኤው እንደሚመረጥ የሚ

ጠበቀው አስመራጭ ኮሚቴ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለስራ አስፈጻሚነት ብቁ ናቸው ያላቸውን እጩዎች በማቅረብ በጠቅላላ ጉባኤው እንደሚያስመርጥ ይጠበቃል፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተክርስቲያኒቱ

አስተዳዳሪ በአባ ኃይለእየሱስ እማኘውና በስራ አስፈጻሚው መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ተከትሎ ከ15 ቀን በፊት የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ መድረክ በባለአደራ ቦርዱ አማካኝነት ተጠርቶ ነበር። መድረኩን የመሩት የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ባንቲሁን ኃይሌ አሉ ያሏቸውን ችግሮች አቅርበው ምዕመኑ እንዲወያይባቸው አድርገዋል፡፡ይህንን ተከትሎም ሁለቱም ወገን (ስ

ራ አስፈጻሚውና የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ) ተከስተዋል ያሏቸውን ችግሮችና ለችግሮቹም መንስኤ ሆነዋል ያሏቸውን ጉዳዮች ለተሰብሳቢው አሰምተዋል፡፡የስራ አስፈጻሚውን በመወከል ንግግር

ያደረጉት የመቶ አለቃ አባተ በቤተክርሰቲያኗ ውስጥ ለተከሰተው ችግር አስተዳዳደሪውን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ከስራ አስፈጻሚው ጋር ተባብረው አይሰሩም፣ ህግም አያከብሩም የቤተክርሰቲያኒቱ ንብረትም እየተመዘበረ ነው በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡የስራ አስፈጻሚውን ንግግር ተከትሎ

ምላሽ የሰጡት የቤተክርስቲያኒቱ አስተደዳሪ አባ ኃይለእየሱስ እማኘው በበኩላቸው ህግ ያፈረስኩት እኔ ሳልሆን ስራ አስፈጻሚው ነው በማለት ምላሽ የሰጡ ሲሆን “ህግን ጥሶ ህጋዊ መሆን አይቻልም” ብለዋል፡፡ አስተዳዳሪው እንዳሉት በቤተክርስቲያኒቱ እየተፈጠረ ላለው ችግር መንስኤ አንዳንድ ካህናት ለህዝበ ክርስቲያን አለማሰብና የስራ አስፈጻሚው ለህግ ተገዥ አለመሆን ናቸው፡፡ በእለቱ የተሰበሰበው ቁጥሩ ከፍ ያለ ህ

ዝበ ክርስቲያም ከሁለቱም ወገን የቀረቡ ሀሳቦችን መነሻ በማድረግ ለችግሩ መንስኤ ያላቸውንና መፍትሄዎቻቸውን ጠቁሟል፡፡ ተሳታፊዎቹ እንዳሉት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ችግር ሲፈጠር እርስ በእርሳቸው በመነጋገር ሊፈቱት ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ሁሉም የቤተክርስቲያኒቱን ህግ እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡በሁለቱ ወገኖች መካከል የተከሰተውን

አለመግባባት ተከትሎ አስተዳዳሪው ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከአውሮፓና ምስራቅ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤሊያስ የደረሳቸው ሲሆን በስብሰባው ላይ አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት አስተዳዳሪው ከስልጣን መነሳት ህግን ያልተከተለና አግባብነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአስተዳዳሪውን ከስልጣን መነሳት እንቃወማለን ያሉ ምዕመናንም የአቤቱታ ፊርማ በማሰባሰብ ለባለአደራ ቦርዱ አቅርበዋል፡፡

የካምፓላ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው

ፖ.ሳ.ቁ-28268ካምፓላ-ኡጋንዳ

ለዓመታት በታንዛንያ እስር ቤት ውስጥ ታስረው የቆዩ ወደ 600 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ የሁለቱ ሀገራት መንግስታት እየተደራደሩ ነው። ኢትዮጵያዊኑ ለእስር የበቁት ወደ ታ

ንዛኒያ በህገወጥ መንገድ ለመግባት ሞክሯችኋል ተብለው ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን ከኬንያ በመነሳት በታንዛኒያ በኩል አድርገው ወደ ማላዊ በመግባት የመጨረሻ መድረሻቸው ወደ ሆነው ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ይሞክራሉ። ስደተኞቹ በደቡብ አፍሪካ የተሻለ ስራ

እና ገንዘብ እናገኛለን የሚል እምነት አላቸው። ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በአጓጓዥ “ኤጀንሲዎች” የሚጠየቀው ገንዘብ ከፍተኛ በመሆኑ አንዳንዶች ንብረቶቻቸውን ሸጠው ነው ለጉዞ የሚነሱት። ለስደተኞች መጠለያ የማትሰጠው ታንዛኒያ በበኩሏ እንደዚህ ዓይነት ድንበር ተሻጋሪ የውጭ ዜጎችን ያለ ህጋዊ መረጃ ስታገኝ በቀጥታ ወደ እስር ቤት ነው የምትልከው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ የታሰሩት ኢትዮ

ጵያውያን ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ናቸው። በታንዛኒያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙ ወ

ገኖቻቸውን ገንዘብ በማዋጣት ሲረዱ ቆይተዋል። ለአንዳንዶቹም የትራንስፖርት ወጪያቸውን በመሸፈን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ አድርገዋል። የታንዛኒያን ድንበር ሲያቋርጡ የሚያዙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በመበርከቱ ምክንያት የስደተኞቹን የትራንስፖርት ወጪ ሸፍኖ ወደ አገር ቤት መመለስ አዳጋች ሆኗል። የስደተኞቹ ጉዳይ በዚህ ሁኔታ ላይ እ

ንዳለ ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከታንዛኒያ መንግስት ጋር መደራደር ይጀምራል። እንደ ኤምባሲው ምንጭ ከሆነ ድርድሩ ተሳክቶ ከታንዛኒያ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል። የታንዛኒያ መንግስት 600 የሚጠጉትን ስደተኞች ለመልቀቅ የተስማማ ሲሆን የዓለም የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) የትራንስፖርት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገብቷል። የስደተኞች ጉዳይ ያስመረረው የታንዛ

ኒያ መንግስት ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ለምን ኤምባሲ እንደማትከፍት በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ግን በአሁኑ ወቅት አዲስ ኤምባሲ ለመክፈት በጀቱ የለኝም የሚል ምላሽ ያቀርባል።

የባለአደራ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ባንቲሁንም ከሁለቱም ወገን አሉ የተባሉት ችግሮች ለህዝብ መቅረባቸውና ውይይት መደረጉ ለቤተክርስቲያንቱ ሰላም የሚበጅ መሆኑን ገልጸው በጠቅላላ ጉባኤው ወቅትም መምረጥና መመረጥ መብት ባላቸው የሰበካ ጉባኤው አባላት የህዝበ ክርስቲያኑ ጥያቄ ምላሽ እንደሚያገኝ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ብዙው ምዕመን የሰበካ ጉ

ባኤው አባል ባለመሆኑና አባል የሆነውም ጠቅላላ ጉባኤ ሲጠራ ስለማይገኝ ኮሚቴና የተለያዩ ኃላፊዎችን በመምረጡ ሂደት ችግር እየተፈጠረ መሆኑን ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ምዕመኑ ችግር ሲፈጠር ከመማረር የሰበካ ጉባኤው አባል እንዲሆንና በስብሰባዎችም እየተሳተፈ መብቱን እንዲያስከብር አሳስበዋል፡፡ እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ አንዳንድ

ተሰብሳቢዎች ግን አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርበው መከልከላቸውን በመድረኩ ላይ ገልጸዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ሁለት አስተባባሪዎች ከስራአስፈጻሚ ኮሚቴው ጋር ሆነው እስከ ጠቅላላ ጉባኤው ድረስ አዳዲስ አባላትን እንዲመዘግቡ ከስምምነት ተደርሷል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው እስከ አሁን ሲንከባለ

ሉ ለመጡት ችግሮች መፍትሄ እንደሚሰጥና የቤተክርስቲያኗን ቀጣይ አካሄድ እንደሚጠቁም ይጠበቃል፡፡

የኡጋንዳ መካነ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በካምፓላ

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ፎቶ

- ተስፋ

ለም ወ

ልደየ

በታንዛንያ የታሰሩ 600 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን

ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነውበስመኝሽ ይቆዬ

በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

ደቡብ ሱዳንበጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር ምክንያት

ከቀናት በፊት ጭርታ ይስተዋልባት የነበረችው የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የሆነችው ጁባ ቅዳሜ ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም መተንፈሻ አጥታ ውላለች። የሀገሪቱ አባት የሚባሉት ጆን ጋራንግ መካነ መቃብር የሚገኝበት በተለምዶ “ከስተምስ” ተብሎ የሚጠራው ቦታ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አጥልቅለቅውት ነበር። ፊታቸው ላይ ደስታ እና እፎይታ የ

ሚነበብባቸው ደቡብ ሱዳንውያን የአዲሰቱ አገራቸውን ውልደት ለማክበር ማልደው ነበር በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ መትመም የጀመሩት። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ደቡብ ሱዳናውያን ግን በዓሉን አስቀድመው ነበር የጀመሩት:፡ ደስታቸውን ለመግለጽ ንጋትን አልጠበቁም። አርብ እኩለ ለሊት ላይ የተተኮሰውን የደስታ ርችት ተከትለው በርካቶች አቧራማ በሆኑት የጁባ መንገዶች ላይ ደስታቸውን ለመግለጽ ወጥተዋል። የሰሜን ሱዳን ግልባጭ የሆነውን ባ

ንዲራቸውን እያውለበለቡ፣ በየመኪናው ላይ እየተንጠላጠሉ፣ እየዘፈኑ እ

ና እየጨፈሩ የጁባን በጣት የሚቆጠሩ የአስፋልት መንገዶች አድምቀዋት አንግተዋል። ከአፋቸው የማይጠፋው አንድ ቃል ነበር። “ነጻነት”። ደቡብ ሱዳንውያን ነጻነታቸውን ከማግኘታቸው በፊት ለአምስት አስርት ዓመታት ከሱዳን መንግስት ጋር ተዋግተዋል። በውጤቱም ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ደቡብ ሱዳንውያን ህይወታቸውን አጥተዋል። የቅዳሜውን በዓል ለማክበር ወደ አደ

ባባይ ከወጡት ብዙዎቹ ቢያንስ አንድ የቤተሰብ አባላቸውን በጦርነቱ ያጡ ናቸው። ለዚህም ይመስላል ስለበዓሉ ሲጠየቁ በስሜት የሚሞሉት። የአረብ ዝርያ ባላቸው ሱዳንውያን ከተሞላው ሰሜን ሱዳን ራሳቸውን ለመገንጠል ባደረጉት ትግል አባቶቻቸው፣ እናቶቻቸው አሊያም ልጆቻቸውን ገብረዋል:፡ እንግሊዘኛ አስተማሪ የሆነው ጆርጅ ጋራንግ አባቱን ወንድ አያቱን እና 11 ወንድሞቹን በጦርነቱ አጥቷል። በደቡብ ሱዳን የ“ልደት ቀን” የተሰማውን ለ በ “ኒውዮርክ ታይምስ” ጋዜጣ አጋርቷል። “መላ ሰውነቴ በደስታ ተሞልቷል”ይላል ጋራንግ። ከጋራንግ የደስታ ስሜት ከፍ ባለ ስሜ

ት ውስጥ የገቡ አንዳንድ የኦፊሴሊያዊ በዓሉ ታዳሚዎች ገና የሀገሪቱ ነጻነት ሳይታወጅ ራሳቸውን ስተው ሲወድቁ ተስተውለዋል። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜ

ጠኛ ጄፍሪ ጌትልማን አንዲት ሴት ከጠዋቱ ሶስት አካባቢ ራሷን ስታ ከወደቀች በኋላ ስትወስድ ተመልክቷል። ረፋድ ሆኖም የገገረውን ጸሀይ ያስተዋለው ጋዜጠኛ ከታዳሚዎቹ መካከል አንዱን ምን ሆና እንደሆነ ይጠይቀዋል። “ራሷን ያሳተችው በደስታ ነው። ዛሬ ሌሎች በርካቶች ይኖራሉ” ሲል መልሶለታል። ልክ ከቀኑ ሰባት ሰዓት 20 ሲል ደቡ

ብ ሱዳንውያን በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ነገር ሆነ። ደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የሚል ስያሜ ስያሜ የያዘችው ሀገራቸው በይፋ ተወለደች። የሀገሪቱ የህግም መወሰኛ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት ጄምስ ዋኒ ኢጋ “ረጅሙን እና ጀግንነት የተሞላበትን የህዝባችንን ትግል በማስታወስ” ሲሉ ስነስርዓቱን አስጀመሩ። ጥቂት ደቂቃዎች ቆይቶ የሱዳን ባንዲራ ወርዶ የደቡብ ሱዳን ባንዲራ ተሰቀለ። የደቡብ ሱዳን ባንዲራ እንደ ሱዳን አቻው ተመሳሳይ ቀለማት ያለው ሲሆን የሚለየው በአደራደሩ ነው። ጥቁር አፍሪካውያን እንጂ አረብ አይደለንም የሚሉት ደቡብ ሱዳንውያን በሱዳን ባንዲራ ከታች ያለውን ጥቁር ቀለም ወደ ላይ አምጥተውታል። የሱዳን ባንዲራ ከታች ወደ ላይ ከመገልበጡ ሌላ ኮከብም ታክሎበታል። የባንዲራ መስቀል ስነስርዓት ሲካሄድ

ታዳሚው አካባቢውን በደስታ ጩኸት አናጋው። “መብሩክ ጃኑብ ሱዳን” ሲሉም ከሰሜን ሱዳን በወረሱት አረብኛ ቋንቋ ከፍ አድርገው ጮኹ። “ደቡብ ሱዳን እንኳን ደስ ያለሽ”። የሚታወቁበትን ባርኔጣ ያደረጉት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪየር የሽግግር ጊዜ ሕገ መንግስቱ ላይ ፈረሙ። ከዚያ ረጃጅሞቹ ንግግሮች ተከተሉ። “ዛሬ ለአፍሪካ ውብ ቀን ነው። ረጅም

ጊዜ የወሰደው ግጭት መቆሙ ትልቅ ስኬት ነው” የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ጆሴፍ ዴይሲስ በሚያዩት ነገር ተደስተው ተናግረዋል። የ54ኛዋ የአፍሪካ አገር አፈጣጠር በእርግጥም ለብዙዎች እንደተአምር የሚታይ ነው። ትላንት ሲጋደሉ የነበሩት የሰሜን ሱዳን መንግስት ሰዎች እና የደቡብ ሱዳን አማጽያን ዛሬ በፕሬዝዳንቶቻቸው ተወክለው በዓል እያከበሩ ነው። ትላንት ከደቡብ ሱዳን ጋር ጦርነት ገጥመው የዛሬው ቀን እንዳይመያጣ ሲከላከሉ የነበሩት ፕሬዝዳት ኦማር ሀሰን አልበሽር ዛሬ የሀገሪቱን ነጻነት ተቀብለው የክብር እንግዳ ሆነው ጁባ ተገኝተዋል። እንደእርሳቸው ሁሉ አሉ የተባሉ የአ

ፍሪካ መሪዎች የበዓሉ ተካፋዮች ሆነዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለ

በጄፍሪ ጌትልማን

ኒውዮርክ ታይምስ

Page 3: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 3

ወይም በኢሜይል [email protected] አድርሱን።

በ+256-778-693669 ይደውሉልን።

q አስተያየት

q ጥቆማ…q ጸሁፍ

ዜና

በሐበሻዊ ቃና ፖስታ አድራሻ

ፖ.ሳ.ቁ 28268

ካምፓላ-ኡጋንዳ ብለው ይጻፉልን።

የዓለም 193ኛ አገር ሆነችስ ዜናዊን ጨምሮ የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ፣ የኬንያው ሞዋይ ኪባኪ፣ የደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዞማ፣ የዚምባቤው ሮበርት ሙጋቤ አልቀሩም። እነዚህ ሁሉ የሀገር መሪዎች በበዓሉ ስፍራ ሲደርሱ ያልተደረገው ነበር ለአልበሽር የተደረገላቸው። የበዓሉ ታዳሚ በደማቅ ጭብጨባ ነበር የተቀበላቸው። ዳንኤል አቴም የተባለ ደቡብ ሱዳናዊ ጭብጨባው እና ሞቅ ያለው አቀባበል “የደስታ አይደለም” ባይ ነው። ለበዓሉ ሱፉን ግጥም አድርጎ እና አነስተኛ ባንዲራ የያዘው ዳንኤል “ጠላትህን ስታነጋግር አንተ እኮ መጥፎ ነህ እያልክ አይደለም። በልብህ ያለውን አንተ ታውቃለህ” ሲል ደቡብ ሱዳናውያን ለአልበሽር አሁንም ድረስ ያልተለወጠ አመለካከት እንዳላቸው አስረድቷል።

(ይህ ዘገባ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል)

ፎቶዎች-(በስተግራ ከላይ) በሺህዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ደስታቸውን ለመግለጽ በእኩለ ለሊት በጁባ መንገዶች ወጥተዋል።

(በስተግራ ከታች) ትላንት ሲጋደሉ የነበሩት የሰሜን ሱዳን መንግስት ሰዎች እና የደቡብ ሱዳን አማጽያን ዛሬ በፕሬዝዳንቶቻቸው በኦማር ሀሰን አልበሽር እና ሳልቫ ኪር ተወክለው የነጻነት በዓል አክብረዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳንውያን በሀገራቸው ውልደት ላይ ለማክበር የሀገሪቱ አባት በሚባሉት

ጆን ጋራንግ መካነ መቃብር ተገኝተው ነበር

የደቡብ ሱዳን ባንዲራ እንደ ሱዳን አቻው ተመሳሳይ ቀለማት ያለው ሲሆን የሚለየው በአደራደሩ ነው

ፎቶ

- ኤ ኤ

ፍ ፒ

ፎቶ

- ኤ ኤ

ፍ ፒ

ፎቶ

- ሮይ

ተርስ

ፎቶ

- ሮይ

ተርስ

Page 4: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና4የማይረሳው ዕለት

አንደኛ ዓመት መታሰቢያልዩ ዘገባ

አቶ ዮሐንስ ምህረት ከአገሩ ከኢትዮጵያ የመጣው ሠላምን እና ነፃነትን ፈልጎ ሲኾን ለሦስት ዓመታትም ይህንኑ የሚፈልገውን ነገር ከኡጋንዳ አግኝቷል። ይህ ግን በሽብርተኞች እንደተፈጸመ በተጠረጠረው የቦምብ ፍንዳታ ሰበብ 76 ሰዎች ሞተው በመቶ የሚቆጠሩ ሌሎችን ቁስለኛ እስከኾኑበት እስከ ጁላይ 11 ቀን 2010 ድረስ ብቻ ነበር የቀጠለው።

በዚያች ሰንበት ዩሐንስ እና ጓደኞቹ የዓለም ዋንጫውን ፍፃሜ በማስመልከት መዝናናት የጀመሩት ጨዋታው ከሚተላለፍበት ቀደም ብለው ነው። ከአንዱ ቡና ቤት ወደሌላው ሲሉ ይቆዩ እና በመጨረሻ ካባላጋላ በሚገኘው የኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት ማረፊያቸውን አደረጉ። ከቆይታ በኋላ በዚያ ቦታ መልአከ ሞት መቅሰፍቱን አወረደ። ዩሐንስ በጣም ከባድ ፍንዳታ እንደሰማ እና ግርግር እንደተፈጠረ ያስታውሳል። የመጨረሻው ቆጠራ ሲደረግ 15 ሰ

ዎች መሞታቸው ተረጋገጠ። እንደመታደል ኾኖ ዮሐንስ እና አምስት ጓደኞቹ ተረፉ። ነገር ግን ጠባሳው አልቀረላቸውም።

አካል ጉዳተኝነትን ፍራቻ!“በጣም አስቀያሚ ቀን ነበር፤ ማውራትም አልፈልግም” ያለው ስለጉዳዩ የበለጠ እንዲነግረኝ ስጎተጉተው ነበር።ከአደጋው በፊት ዮሐንስ ባለቤቱን እና ልጁን በከባድ መኪና ሾፌርነት ተቀጥሮ በሚያገኘው ገቢ ያስተዳድር ነበር፤ ያ

ሁሉ አሁን ቀርቷል። ፍንዳታዎቹ ሕብለ ሰረሰሩን (ስፓይናል ኮርዱን) ጎድቶታል። ጀርባውን ስለሚያመውም ለረጅም ሰዓት ቀጥ ብሎ መቀመጥ አይችልም። ከአደጋው በኋላ በሦስት ወር ውስጥ ቀዶ ሕክምና ሊደረግለት ይገባ ነበር። ነገር ግን ከአንድ ዓመት በኋላም ቀዶ ህክምናውን አሁንም እየጠበቀ ይገኛል። “አንዳንድ ዶክተሮች ጉዳቱ ከፍ ያለ ስለኾነ እዚህ ቀዶ ሕክምናው ሊደረግልኝ እንደማይችል ተናግረዋል። እኔም እዚ

ህ ማድረግ እንደሌለብኝ ይሰማኛል። አለበለዚያ አካል ጉዳተኛ ኾኜ መቅረቴ ነው” ይላል። “አንዳንዶች ግን እዚሁ ቀዶ ህክምናውን ማድረግ እንደምችል ይነግሩኛል ” ሲል ጨምሮ ይናገራል።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ቀዶ ሕክምናው የትም ይደረግ የት “ስፖን

ሰር” ሊያደርገው ፈቃደኛ ነው። ይህን ሊያደርግ የሚችለው ግን ከሙላጎ ሆስፒታል በሚያገኘው ይሁንታ ብቻ ነው። ዩሐንስ ይህን ይሁንታ ለማግኘት በተደጋጋሚ በሐኪም ቢታይም ሊሳካለት እንዳልቻለ ይናገራል። “ዶክተር አይደለሁም ግን አንድ ሐኪም ሕክምናውን እዚህ ማድረግ አደገኛ ነው ካለ ጥሩ ምክር ይመስለኛል፤ ለሕ

ይወቴም የሰጋሁት በዚህ ምክንያት ነው” ይላል ዮሐንስ።የዩሐንስ ባለቤትም የራሷ ስጋቶች አሏት። ፍንዳታውን ተከትሎ ባለቤቷ በካምፓላ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል እንዲተ

ኛ ሲደረግ ለሦስት ቀናት የህክምና ክትትል የሚያደርግለት አልነበርም። ምክንያቱ ደግሞ ጥንዶቹ ለህክምናው የሚከፍሉት ገንዘብ ስላልነበራቸው ነው። “በጣም ተጎድቶ ነበር። የምንከፍለው ስለሌለን አንዳንድ ዶክተሮች ወደ ቤቱ እንድንወስደው ነግረውን ነበር። ነገር ግን ከሦስት ቀናት በኋላ የፖሊሱ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ካሌ ካዩሁራ በመምጣታቸው ሕክምናው ተጀመረ” ትላለች። እንደ እርሷ አባባል ጄኔራል ካዩሁራ ቁስለኞቹ ክፍያ ከመፈጸማቸው በፊት መታከም እንዲጀምሩ መመሪያ በመስጠታቸው ምክንያት በብዙ ታማሚዎች ዘንድ ተወድደዋል።

መዝሙር እና መብራትዮሐንስ በሆዱ፣ በደረቱ እና በአንጀቱ ውስጥ ያሉ የቦምብ ቁርጥራጮችን ለማውጣት ያኔ ቀዶ ሕክምና ማድረጉን እና

ውጤታማም እንደነበረ ይናገራል። ተጨማሪ ቀዶ ሕክምና እንዲረግለት የሚጠብቀው ዮሐንስ አእምሮውን ዕረፍት ከሚነሱት ፍርሃቶች ጋር እየታገለ ይገኛል። “ሕዝብ የሚሰበሰብበት ማንኛውም ቦታ መሔድ አልችልም” ይላል ዮሐንስ። “ብዙ ሰውም አጠገቤ ሲሰበሰብ እረበሻለሁ፣ እፈራለሁ። ሆቴል እና ካፍቴሪያም መሔድ አልፈልግም።”ከአደጋው በኋላ የተፈጠረው ለጨለማ ያለው ፍርሃት እስካለፈው ወር ድረስ ቆይቷል። መብራት ከጠፋ መተኛት ይ

ቸገርም ነበር። ሰዎች ተሰብስበው ኳስ ጨዋታ ሲመለከቱም ይረበሻል። በራሱ ወጪ ለረጅም ጊዜ የቆየ የ“ሳይኮሎጂ” ሕክምና ካደረገ በኋላ ግን ወደ ጤናማ ኑሮው ለመመለስ እየሞከረ ነው።ባለቤቱ “ሌሊቱን ሙሉ መዝሙር እየሰማን ነው የምናድረው” ትላለች። “ሲነቃ መብራት ጠፍቶ ካገኘ ወይም መዝ

ሙር ከሌለ በጣም ይፈራል” ስትል የዮሐንስን ጭንቀት ታስረዳለች። ዮሐንስ በበኩሉ ጀርባው ላይ በሚሰማው የማቃጠል ስሜት ከእንቅልፉ እንደሚባንን እና አንዳንድ ጊዜም አንድ እግሩ እንደሚደነዝዝ ይናገራል። አንዳንድ ምሽቶችም የማይመቹ እንደሚኾኑበት ይናገራል። “ምንም አይነት ቀዶ ህክምና ስላላደረግሁ ዝም ብዬ አምላኬን የሚያመጣውን እየጠበቅሁ ነኝ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም” ሲል ያለበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያስረዳል።

ነፃነትን በኡጋንዳ ፈለጋት ግና ሕማምን አገኘ!

ዕለታዊው የኡጋንዳ ጋዜጣ “ዴይሊ ሞኒተር” ከዓመት በፊት በካምፓላ የደረሰውን የቦምብ አደጋ ለማስታወስ የጥቃቱ ሰለባ ሰዎችን ታሪክ ለአንድ

ወር ያህል በተከታታይ አትሟል። እ.ኤ.አ በጁን 21 ቀን 2011 በወጣው እትሙ ነፃነትን እና ሠላምን ፈልጎ ወደ ኡጋንዳ ስለመጣ ነገር ግን በአደጋው ምክንያት ከቆሰለ በኋላ እስካሁንም ድረስ በጀርባ አጥንት ህመም የሚሰቃይ ኢትዮጵያዊ ታሪክ አውጥቷል። የጋዜጣው ዘጋቢ ፍላቪያ ላኜሮ የጻፈችውን

እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

የሚጠበቀው ስልክ ቤተሰቡን ለመርዳት ሲል መኪና ለማሽከርከር ይሞክራል። ነገር

ግን ቀኑን ሙሉ መንዳት አይችልም። ቤተሰቡ ኑሮን እየገፋ ያለው በጎረቤቶች እና በበጎ አድራጊዎች ድጋፍ ነው። ዮሐንስ ምንም እንኳን በዚህ አሳዛኝ አደጋ ውስጥ ቢያልፍም አሁ

ንም ለኡጋንዳውያን ያለው ክብር ትልቅ ነው። እነርሱን ሲገልጻቸውም “ደግ እና ሰላማዊ ናቸው” እያለ ነው። “በእኔ አገር ሰዎች ሲጠጡ ይጣላሉ። ብዙውን ጊዜም ረብሻ አይጠፋም” ይላል ሰላማዊነታቸውን ለማጠየቅ። “ኡጋንዳን እወዳታለሁ። የኡጋንዳን መንግሥትም አመሰግናለሁ” ይላል። ዮሐንስ ወደ ሬስቶራንት እና ካፌዎች መሄድ ቢያስፈራውም አሁ

ንም አልፎ አልፎ አደጋው ወደ ደረሰበት የ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት” ጎራ ይላል። በምግብ ቤቱ የተሰራው መታሰቢያ በተመረቀበት ቀን እዚያው ነበር። የኢትዮጵያ በዓላት ሲከበሩም ወደ ምግብ ቤቱ ይሔዳል። በእግዚአብሔር እና ከአማኞች ጋር ባለው ግንኙነት የሚጽናናው

ዮሐንስ አሁንም ቢሆን መረጋጋት አልቻለም። ከዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እስኪደወልለት እና እንዴት እንደሚኾን እስከሚነገረው ልቡ እንደተንጠለጠለ አለ።

ጌታ ያውቃል ተሰማ

ፎቶ

- ፍላቪ

ያ ላኜ

ኤፍሬም ተስፋገርጊስ

ስምዖን የማነ

ሃብቶም ግርማይ

ኤፍሬም ንዋይ

ካሌብ ተከስተ

ናርዶስ መብራሃቱ

ዩሐንስ ምህረት ከባለቤቱ እና ልጁ ጋር

Page 5: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 5የማይረሳው ዕለት

አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ልዩ ዘገባ

አደጋው የተከሰተበትን ቅጽበት መለስ ብለሽ አስታውሽን?ትንሽ ደቂቃ ነበር የቀረው። በዚያን ሰዓት በጣ

ም ብዙ እንግዳ ስለነበር ምግብ እየሰራን፣ ሰው እያስተናገድን፣ መቀመጫ ጠፍቶ ነበር። እኔ ራሴ ነኝ የመጨረሻውን መስተንግዶ ያደረግኩት። አምስት ኢትዮጵያኖች ነበሩ። ገንዘብ ሰጥተውኝ ታዘዝኳቸው። ለእነሱ ቢራ ከፈትኩላቸው። ቢራ እንድቀይርላቸው ጠይቀውኝ ነበርና ቅያሬውን ተመልሼ ይዤ ሄድኩኝ። ከዚያ ሁለት ደቂቃ አይሞላም። በጣም ኃይለኛ ድምጽ ተሰማ። እኔ ፕሮጀክተሩ ነበር የመሰለኝ። “ማናጀሩን” ጮኼ ተጣርቼ “ምንድነው? ፕሮጀክተሩ ነው?” አልኩት። ማናጀሩ እየሮጠ ወደዚያ ሲሄድ እኔም ተከትየው ሮጥኩ። “አይ ማሜ! አይዞሽ በርቺ። አደጋ ነው” አለኝ። “ምን?” ብዬ ስሮጥ እነዚያ ያስተናገድኳቸው ልጆች ከወንበር ላይ ወድቀው አየኋቸው። ወድቀው “አይዞሽ ማሜ፣ አይዞሽ” ሲሉኝ በቃ መፈጠሬን ጠላሁት። በሀገራችንም ባህል ወደ አንተ የመጣን እንግዳ

አስተናግደህ በሰላም ከቤትህ ሲሄድ ነው ደስ የሚለው። እንኳንስ እንደዚህ ዓይነት መጥፎ አደጋ ቀርቶ ሰው ትን እንዲለው እንኳ አትፈልግም። ውሃ ለመስጠት እንኳ ትሯሯጣለህ። እና የተከሰተው ነገር በጣም ነው ያስደነገጠኝ።

በዚያ ድንጋጤ ውስጥም ሆነሽ ሰዎችን ለመርዳት ትሞክሪ ነበር…. ሁኔታው ሲከሰት እጅግ በጣም ያሳዝናል። ሆኖ

ም ግን እጅግ ቢያስደነግጥም ወዲያውኑ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው የሚደሙ “እርዱን” የሚሉ ሰዎች ስለነበሩ መፍትሄው ከማልቀስ ይልቅ መርዳት ነው። ፈረንጆች በጣም ተጎድተው እየደሙ ነበር። ቆሜ ሳስበው ደግሞ ከመርዳት ሌላ ምንም ዓይነት ምርጫ የለም። እና የ“ሬስቶራንቱም” ባለቤት ስለሆንኩኝ ከመሸበር ተቆጥቤ ሰራተኞቹን ማስተባበር፣ የመንግስት አካላት ጋር ደውሎ እርዳታ መጠየቅ፣ የተጎዱትን ሰዎች ወደ ሆስፒታል ማድረስ፣ የሞቱትን ደግሞ አስክሬናቸው ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ ማድረግ ነበረብኝ። ያን ቀን መቼም አልተኛንም። በሚቀጥለው ቀን

ከባልደረቦቼ ጋር በሆስፒታል የተኙትን ቁስለኞች በየቦታው፣ በየክፍላቸው ሄደን በግል አይተናቸዋል። የህክምና እርዳታ እንዲሰጣቸው መንግስትን ጠይቀን ተፈቅዶልናል።ሰው ሲሞት፣ ሰው ደም በደም ሆኖ አይቼ አላ

ውቅም። እንደዚህ ዓይነት ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይ ነው። እኔ ምግብ ማቅረብ፣ ሰው ማስተ

ናገድ፣ አገልግሎት መስጠት ነው እንጂ አንደዚህ ዓይነት ነገር አይቼ አላወቅም። እንደውም ጎበዝ ነበርኩ። ሴት ልጅ ሆኜ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲከሰት ከባድ ነው። አንኳን ለእኔ ለማንም ሰው የሚያስደነግጥ ነውና። ከባድ ነው። በጣም ከባድ ነው። በቃላት አይገለጽም። ያን ሁሉ ሰው አስተናግዳለሁ ብለህ ከቤትህ አስክሬን ሲወጣ በጣም ከባድ ነው። ውሎ ሲያድር ነገሩ እየረገበ ይሄዳል። ግን በጣ

ም ነው የሚያሳዝነው። አሁንም ቢሆን ከህሊናዬ የማይጠፋው የ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” አፍቃሪ የሆኑ ደንበኞች እዚህ መጥተው ይህ አደጋ ተከስቶባቸው በማየቴ ህመሙ እስካሁንም አለ። የሚረሳ ነገር አይደለም። አደጋው በአልሻባብ አሸባሪዎች አጥፍቶ ጠፊዎ

ች እንደተፈጸመ ተነግሯል። ግን እንዴት እንደተከሰተ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር አለ? እኔ በእውነት ለመናገር በዚያን ጊዜ ይሄኛው ነ

ው ይዞ የገባው፣ ያኛው ነው የሚባል አይደለም። ከ350 እስከ 400 ሰው ለማየት በጣም አስቸጋሪ ነው። ሁሉም ደንበኛ ነው። እኛ ማስተናገድ ነው። እያንዳንዱ ጠረጴዛ እየሄድን አስተናግደናል። በጣም ደስ የሚል ሆኖ ፍጻሜው ግን በአደጋው ምክንያት አሳዛኝ ሆኗል። ማንም ይሁን ያደረገው ማን፤ እኔ በዜና ላይ ሰማሁ እንጂ ይኼኛውን ነው ብሎ ለመናገር በእኔ በኩል በጣም አስቸጋሪ ነው። እኔ የ“ቢዝነስ” ሰው ነኝ። እንደዚህ ዓይነት ነገር ተከስቶ አያውቅም። በሬስቶራንት ውስጥ በሃያ ዓመት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ነው።

አደጋው በደረሰ በሁለተኛው ቀን ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ መጥተው ቤቱን ጎብኝተዋል። ካንቺ ጋርም ተነጋግረዋል። እንዴት ነበር ያን ቀን የነበረው ሁኔታ? ፕሬዝዳንቱም ባለስልጣኖችም ነበሩ። “አይዞሽ፤

ብቻሽን አይደለሽም፤ በርቺ፤ ቢዝነሱ ወደ ነበረበት ይመለሳል፤ የምንችለውን ሁሉ ደግሞ እንረዳለን” የሚል ቃል ከአንድ ፕሬዝዳንት ሲሰማ በጣም ያስደስታል። በተከሰተው ሁኔታ በጣም ደንግጬ ነበርና እንደዚህ ዓይነት ድጋፍ በዚያ ሰዓት ሲሰማ እጅግ በጣም ያስደስታል። ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር የደረሰውን ሁኔታ ተነጋግረን እጅግ በጣም ረድተውናል። ተረባርበውልናል። በዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው የልጆቼ አባ

ት በሶስተኛው ቀን ከውጭ መጥቶ የደረሰው። የመጀመሪያ እርዳታ ያደረገልን እርሱ ነው። በዚህ በአደጋው አጠገቤ ለቆሙት እና በሁለት እግሬ እንድቆም ላደረጉኝ ቤተሰቦቼ፣ ወንድሞቼ፣ ዘመዶቼ እና ጓደኞቼ አመሰግናለሁ።

ከአደጋው በኋላ የነበሩት ሳምንታት ለአንቺ በጣም አስቸጋሪ ነበሩ። ከሀዘኑ ለመጽናናት በጣም ከባድ አንደሆነብሽ አይቻለሁ። የቆሰሉትን በሆስፒታል ሄደሽ ጠይቀሻል። አስክሬን ወደየሀገራቱ ሲሸኝ በሁለቱም ቦታዎች ነበርሽ። በጣም ጥልቅ የሀዘን ስሜት ውስጥ እንደነበርሽ አስታውሳለሁ።የሞቱት ልጆች ደንበኞቼ ናቸው። አውቃቸዋለ

ሁ። በዚያ ላይ ደግሞ ወጣቶች ናቸው። ይሄ ለእነሱ አይገባም። ኳስ አይተው ተዝናንተው ሊሄዱ ሲሉ ይሄ መሆኑ ያሳዝናል። ፎቶግራፋቸውን ስመለከት መቋቋም ያቅተኛል። እኔ ምንም ዓይነት አደጋ ቢደርስብኝ ከዚህ የበለጠ ሊሆን አይችልም። ሀዘን ላይ የሰው ልጅ ስጋህ ወይም ወንድምህ መሆን የለበትም። በእኔ ቤተሰብ ላይ አንደዚህ ዓይነት አደጋ ቢደርስብኝ ከዚህ የበለጠ ላዝን አልችልም። የሚቀየር ቢሆን በእነሱ ፋንታ እኔ ብሆን ቅንጣት ታህል አይሰማኝም።

አደጋው በግል ህይወትሽ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አላሳደረብሽም? አደጋው ከባድ ነው። ግን ከአደጋው በፊት በጣ

ም የምወዳት ልጄ የምላት እህቴ ስለሞተች፣ ከዚያ ይሄ አደጋ ሲጨመር፣ ደግሞም ወንድሜ ስለሞተ ሁሉም ነገር ተደራራበና ትንሽ ከባድ ነበር። እና አሁን ግን ሁሉንም ተቀብየዋለሁ። የመጣውን ነገር ተቀብዬ እኔ ጎበዝ ሆኜ ባልደረቦቼን ካልመራሁ ቢዝነሱም መስመሩን ስለሚስት፣ ስራዬም ስለሆነ እየሰራሁ ነው። የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱም እየተቀየረ ነው። እዚህ ካምፓላ ውስጥ የሚመጣ ማንኛውም ሰው፣ ለስራም የመጣ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ሳያይ አይሄድም። እግዚያብሔር ይመሰገን።

አሁን ድሮ የነበሩት ደንበኞቼ ተመልሰውልኛል ትያለሽ? ይሄ ቤት ለሐበሻው መሰባሰቢያ ቦታው፣ አመት በዓሎችን የሚያከብርበት ነበር። ከስሙ ጀምሮ ብዙ ሰው ስለ ኢትዮጵያ ሬስቶራንት ሲያስብ መጀመሪያ የሚመጣለት “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ነውና እንደቀድሞው ሆኗል። ፈረንጆችስ እንደድሮው ይመጣሉ?እኔ ምንም አላስብም። እኔ እኮ ደንበኞቼ ላይ ያ

ደረግኩትም ምንም ዓይነት ነገር የለም። እኔም ደንበኞቼም የደረሰብን አብረን ነው። እርግጥ እኔ አልሞትኩም እንጂ በቀላሉ አይደለም የተጎዳሁት። አንድ ቢዝነሴ ተመትቷል። ሁለተኛ ደግሞ ንብረቴ እና ገንዘቤ ወድሟል። ነገር ግን ከሰው ህይወት አይበልጥም። አንድ ሚዛን ላይ ቢቀመጥ የአንድን ነፍስ ዋጋ ሩብ አይሆንም። ከህይወት ጋር የሚነጻጸር ጉዳይ አይደለም። ህይወት ስለሚበልጥ፤ የእኔ ቢዝነስ ቢበላሽም፤ ምንም ነገር ቢሆን፤ በአደጋው ሰዓት ምንም የሚሰማ ነገር አይደለም። ግን ሲቆይ…እንግዲህ የሞተውም ይቀበራል፣ የቆሰለውም ይታከማል። የእኔ ቁስል ደግሞ ከባድ ነው። የእኔ ደግሞ ሃያ ዓመት የተለፋ ድካም ነው። እንደዚህ የኮራሁባቸው ደንበኞቼ ጎኔ ባይቆሙ ኖሮ የሚመጣውን አደጋ እንግዲህ የዓለም ህዝብ መፍረድ ይችላል። ግን እጅግ በጣም የሚያኮሩ ናቸው። ወደፊት ደግሞ ጠንክሬ እንደሰራ የሚያደርግ ግፊት አለው። ስራዬን ብቻ ሳይሆን በደንበኞቼ ተማምኜ ምን

ም እንደማልሆን፣ ቤቱ ቢከፈት ቅንጣት ታህል ከድሮው ሁኔታ እንደማይበላሽ በመተማመን ልክ በሁለተኛው ወር ተከፈተ። እርግጥ ነው አስደንጋጭ ነው። ቀላል አይደለም። አንድ ወር፣ ሁለት ወር፣ ሶስት ወር እያለ ቀስ በቀስ ቢዝነሱ እየተነሳ አሁን ባለበት ደርሷል።

ማሜ እና “ቪሌጅ” ከዓመት በኋላአንዳንድ ደንበኞች ግን ቤቱ የሰው ህይወት ያለፈበት ከመሆኑ አንጻር አንቺም ሁልጊዜ ባየሽው ቁጥር የምታስታውሽው ስለሚሆን ለምንድነው ወደ ሌላ ቢዝነስ ያልቀየረችው የሚሉ አሉ? መሬቱን የገዛሽው እንደመሆኑ ወይ ህንጻ ብትገነባበት አሊያም ሌላ ቢዝነስ ብትቀየር ይሻል ነበር ይላሉ። ብዙ አስተያየት ትሰማለህ። ጓደኞቼ ሳይቀ

ሩ “ስሙን ብትቀይሪው” ብለውኛል። ቢዝነስ እንግዲህ የራስህ አቋም ነው። ሰው የሚያዋጣውን ነው የሚይዘው። እኔ አለቃዬ ስራዬ ነው። ደንበኞዬ ደግሞ ህዝብ ነው። የእኔ ደንበኛ ይመጣል የሚል ሙሉ እምነት ካለኝ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ምን አደረገ? “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ማለት እኔ ነኝ ባለቤቷ። እንደገና ይታደሳል። ማንም ሰው አደጋ ያጋጥመዋል። መኪና ይጋ

ጫል። ይጠገናል፤ ይሄዳል። ሰው አባቱ ይሞታል፤ አባቱ የሞተበትን ቤት ጥሎ አይሮጥም። እናቱ የሞተችበትን ቤት ጥሎ አይሄድም። አባቴ ስለሞተ በአባቴ ስም አልጠራም አይባልም። እና ለምንድነው ስሙ የሚቀየረው? ስሙ አይደለም ጥፋቱ። አደጋ በመጣ ቁጥር ሰው የአባቱን ስም እንደማይቀይር ሁሉ እኔም ደግሞ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ልክ እንደዚያ ነው የሚሰማኝ። ብቅይረው ደግሞ ልክ እንደዚህ አይመጣም። ሃያ ዓመት ያሳደግሁት ልጅ ስሙ ሲቀየር ማለት ተቀበረ ማለት ነው። በአዲስ አንደገና ለመጀመር ከባድ ነው። ቦታ መለወጥ ላይ ያለሽ አቋምም ተመሳሳይ ነው?አዎ ቦታውም ለምን ይቀየራል? ስሙም እን

ዳለ ሆኖ ቦታውም ላይ እንዳለ ሆኖ አካባቢውን ሌላ አይነት ማድረግ ነው። የአደጋው አካባቢ ለምሳሌ ተቀይሯል። አደጋ የደረሰበት አይመስልም። አሁን ፈረንጆች ሲመጡ “የቱ ጋር ነው አደጋ የደረሰው?” ይላሉ።ምግብ ቤቱ አገልግሎቱን እንደገና ሲጀምር

ለሟቾች ያሰራሽውም መታሰቢያ ለዕይታ በቅቷል መታሰቢያ የተዘጋጀበት ምክንያት ደንብ ነ

ው። በዓለም ላይ እንደዚህ አይነት ነገር ሲከሰት መታሰቢያ ይደረጋል። እኔ ለደንበኞቼ የምሰጣቸው ስጦታ ባጣ በድርጅቱ ስም ግቢ ውስጥ መታሰቢያ አድርጌያለሁ። ለደንበኞቼ ምን ልስጣቸው? አደጋ ሲደርስባቸው አልቅሻለሁ፣

ማሜ መንገሻ “የኢትዮጵያውያን ገጠር ምግብ ቤት” (ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት) ባለቤት እና ዋና ስራ

አስኪያጅ ናት። የዛሬ ዓመት ግድም በምግብ ቤቷ ስለተከሰተው እና ለ15

ሰዎች ሞት ምክንያት ስለሆነው የቦምብ ፍንዳታ፣ ከአደጋው በኋላ ስለነበረው

ሁኔታ እና ስለ ወደፊት አቅዷ ከ“ሐበሻዊ ቃናው” ተስፋለም ወልደየስ ጋር ቆይታ

አድርጋለች።

ለደንበኞቼ ምን ልስጣቸው? አደጋ

ሲደርስባቸው አልቅሻለሁ፣ አዝኛለሁ። አንድ

መታሰቢያ ማድረግ እንጂ ሌላ አቅም የለኝም።

ወደ ገጽ 21 ዞሯል

ፎቶ

- ተስፋ

ለም ወ

ልደየ

ፎቶ

- ሬድ

ዬ ኔዘ

ርላንድ

Page 6: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና6

ልዩ ዘገባ

የማይረሳው ዕለት

አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

“ሕይወት አጭር ናት” የሚለውን አባባል ከልብ አማኝ ብሆንም ከሁለት ደቂቃም ባነሰ ሊያጥር እንደሚችል ግን መቼውንም አስቤ አላውቅም። ኡጋንዳ ካምፓላ ካባላጋላ በሚገኘው የ“ኢት

ዮጵያን ቪሌጅ” ምግብ ቤት በሰፊው በግድግዳ ላይ የተዘረጋው ነጩ አቡጀዲ ስክሪን ሁለት ደቂቃዎች መጨመራቸውን እያመላከተ ነው። ጭማሪው ደቂቃ የተሰጠው ለዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የመዝጊያ ጨዋታ እየተፋለሙ ለሚገኙት ስፔን እና ኔዘርላንድስ ነበር። የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ እየተገባደደ ነው። እደግፈው የነበረው የሆላንድ ቡድን ለእረፍት ከመውጣቱ በፊት አንድ ጎል ቢያስቆጥር የጨዋታውን አካሄድ ይቀይረዋል እያልኩ ማሰብ ይዤአለሁ። ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ የሚሆነው ግን የህይወቴን አካሄድ እንደሚቀይረው ግን የማውቅበት መንገድ አልነበረኝም። “ቡም”!!! ይህንን ነበር በሰከንዶች ልዩነት ው

ስጥ የሰማሁት። ጨዋታውን ያስተላልፍ የነበረው ስክሪን ወዲያውኑ ወደ ጥቁርነት ተለወጠ። አደንቋሪውን ድምጽ ተከትሎ በተቀመጥኩበት ደንዝዤ ቀረሁ። ጩኸት አየሩን ሞላው። መጀመሪያ የመሰለኝ ጆሮ አሳማሚ ድምጽ የወጣው የጋለው ፕሮጀክተር ሲቃጠል የፈጠረው መስሎኝ ነበር። “ዚንንንንንንንንን….” የሚለው እና ጆሮዬ ላይ የቀረው ድምጽ ግን የቦምብ ፍንዳታ እንደሆነ እንድደመድም አደረገኝ። ራሴን አረጋግቼ እርምጃ ከመውሰዴ በፊት

ግን ሰዎች ወደእኔ ሲንጋጉ ተመለከትኩ። የተቀመጥኩት በመተላለፊያ አጠገብ ነበር። ፊት ለፊታቸው በነበሩ የፕላስቲክ ወንበሮች ላይ እየዘለሉ ነፍሳቸውን ለማዳን የሚሯሯጡ ሰዎችን ፈዝዤ እመለከታለሁ። ይሄኔ እኔም ከለላ መያዝ እንዳለብኝ ተረዳሁ እና ወደ ሽንት ቤት ወደ ሚወስደው መተላለፊያ ሮጥኩ። መተላለፊያው ጋር ቆሜ ዙሪያ ገባውን በቅ

ጡ መመልከት ጀመርኩ። የቆሰሉ ሰዎች ይታዩኛል። የምግብ ቤቱን ውጭ ሞልተው የነበሩት ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች እዚህና እዚያ ወድቀው ይታያሉ። ፊት ለፊቴ የተዝረከረኩትን ወንበሮች ወደ ጎን እያደረግኩ አብረውኝ ወደ ምግቤቱ የመጡ ጓደኞቼን መፈለግ ጀመርኩ። ሶስቱ ጓደኞቼ ጨዋታውን ይከታተሉ የነበ

ረው ከእኔ በስተቀኝ በኩል ባለው አነስተኛ ክፍል ውስጥ ነበር። ከጓደኞቼ መካከል ይበልጥ የሰጋሁት ግን ከሳምንት በፊት ለስራ ጉዳይ ወደ ካምፓላ ለመጣችውን ጓደኛዬ ህሊና አለሙ ነበር። በሙያዋ ጋዜጠኛ የሆነችው ህሊናን ወደ ምግብ ቤቱ ይዤያት የመጣሁት እኔ ነበርኩ። እርሷንም ሆነ ጓደኞቼን በህይወት ማግኘቴ የፈጠረበኝን ስሜት በቃላት መግለጽ ይከብደኛል። ህሊናን ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር ካገናኘሁ በኋላ እንደገና አደጋው ወደደረሰበት ቦታ ተመለስኩ። አሁን ለሌሎች ሰዎች እርዳታ የመስጪያ ጊ

ዜ ነው። ጓደኞቼ ጨዋታውን ይከታተሉበት ወደነበረው ክፍል እየተመለስኩ እያለ በጣም ከመጎዳቱ የተነሳ መራመድ እንኳን ያቃተው አንድ ሐበሻ ተመለከትኩ። ሁለት ጓደኞቹ ከግራ እና ቀኝ ተሸክመውት በተዝረከረኩት ወንበሮች መሃል ለመራመድ ተቸግረዋል። ሌላ የሐበሻ ሴት እያለቀሰች እነርሱን ለመርዳት ትሞክራለች። የሚያዩትን ማመን ያቃታቸው ጓደኞቹ ተጎጂውን ወዲያውኑ ለህክምና መውሰድ አቅቷቸዋል። “እሺ…አሁን አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ” አ

ልኩ ለራሴ። ሰዎቹን አላስኬድ ብሏቸው ያስ

ቸገራቸውን ወንበር እያነሳሁ መወርወር ጀመርኩ። ጓደኞቹ ይዘውት ከግቢ ውጭ ሲወጡ ጓደኞቼ ተቀምጠውበት ክፍል ወደነበረው ክፍል ገባሁ። ሶስት ነጮች ወለሉ ላይ ተኝተው ተመለከትኩ። ሁሉም በደም ተሸፍነዋል። ሁለቱ ወንዶች ናቸው። ሰዎቹን እየተመለከትኩ አንድ ኡጋንዳዊ ሰውን ለማረጋጋት ይናገር የነበረውን አስታወስኩ። “ስክሪኑ ነው…ቦምብ አይደለም…ተረጋጉ…ተረጋጉ”። እነዚህን የውጭ ዜጎች ከተመለከትኩ በኋላ ግን የጠረጠርኩትን አረጋገጥኩ። “ወይኔ ቦምብ ነው…..” ከተጎዱት ነጮች ፊት ከአነጋገሩ ዘዬ አሜሪካ

ዊ የሚመስል ሰው ተረጋግቶ ቆሞ ሊረዳቸው ይሞክራል። ተጎጂዎቹን ጮክ ብሎ ሊያነጋግር ይሞክራል። ሶስቱ ነጮች አይመልሱም። አሜሪካዊ መሳዩ አጠገቡ ያለውን ወንበር ጎትቶ በጣም የተጎዳውን አንዱን በጥንቃቄ አንስቶ ወንበር ላይ አስቀመጠው። እንዲሁ ሌላ ወንበር ጎትቶ የተጎጂውን እግሮች አስቀመጠባቸው። ይሄ ሁሉ ሲደረግ ግን ተጎጂው ምንም ዓይነት እንቅስ

ቃሴ አያሳይም ነበር። የተቃጠሉት እግሮቹ በደም ተሸፍነዋል። አሜሪካዊ መሳዩ ሌላኛዋን ተጎጂ መርዳት ጀመ

ረ። ወንበር ላይ ሲያስቀምጣት አገዝኩት። እርሱ ሲያደርግ እንዳየሁት ወንበር ጎትቼ እግሮቿን ወንበር ላይ ለማስቀመጥ አናግራት ጀመር። ምንም አትመልስም። ደጋግሜ ሞከርኩ። አይኖቿ እንደቦዘዙ ናቸው። ምንም የምትሰማ አትመስልም። እግሮቿን ወንበር ላይ አስቀምጬ ወደ ሌላው ተጎጂ ሄድኩ። እንደሌሎቹ ተጎጂዎች ይሄኛውም ያደረገው ቁ

ምጣ ነው። ስጠጋው ጉልበት ላዩ ትልቅ ቁስል እንዳለ ተመለከትኩ። እግሮቹ በደም በደም ሆነዋል። “እርዱኝ” አለ። እርሱን እየረዳሁ እያለሁ ፕሮጀክተሩ አጠገብ መሬት ላይ እየተንፈራፈረች በስቃይ የትጮኽ ተጎጂ ተመለከትኩ። “የጀመርከውን ጨርስ” አልኩ ለራሴ። ከአንድ አስተናጋጅ ጋር ተባብረን የተጎዳውን ሰ

ው ወንበር ላይ አስቀመጥነው። ተጎጂው ቦርሳውን እንድናመጣለት ጠየቀ። ጓደኛዬ አመጣለት። ክፍት የነበረውን ቦርሳ ለመዝጋት መታገል ጀመርኩ። ቦርሳውን ብዘጋውም ትርጉም አልነበረውም። በፍንዳታው ምክንያት በአንድ ወገኑ ተቦትርፏል። ቁስለኞቹን ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ መኪና መጠየቅ ጀመርን። ይሄኔ የምግብ ቤቱ ባለቤት የሆነችው ማሜ መንገሻ እርዳታችንን ፍለጋ መማጸን የጀመረችው። “እባካችሁ ትታችሁኝ አትሂዱ….እባካችሁ እር

ዱኝ” ትላለች እያለቀሰች። ለመርዳት መኪና እንደሚያስፈልግ ነገርናት።

ይህን በቅጡ ከማገናዘቤ በፊት መንገድ ዳር ጓደኞቹ አጠገብ በጀርባው የተዘረጋ ሐበሻ ተመለከትኩ። በካባዱ የቆሰለው ይህ ወጣት አተነፋፈሱ ልክ አይደለም። ደረቱም ባልተለመደ ሁኔታ ከፍ እና ዝቅ ይላል። በሁኔታው የተረበሹት የሚመስሉት ሶስቱ ጓደኞቹ አጠገቡ ሆነው ሁኔታውን ያስተውላሉ። ጓደኛቸውን ወደ ህክምና ለመውሰድ መኪና መጣታቸውን ከሁኔታቸው ተረዳሁ። በስተኋላ ላይ ጓደኞቹ መኪና አግኝተው ወደ ሙላጎ ሆስፒታል ቢወስዱትም ብዙም ሳይቆይ መሞቱን ሰማሁ። ፖሊስ ሲመጣ ከአካባቢው ጨርሶ መራቅ አል

ሆነልንምና ከጓደኞቼ ጋር ሆነን ወደ “ፈንቅል” ምግብ ቤት ሄድን። በከተማዋ እንዳሉ ሌሎች ምግበ ቤቶች እና ቡና ቤቶች ሁሉ እዚህም በርካቶች ስክሪን ላይ አፍጥጠው የመጨረሻው ጨዋታ ሁለተኛውን አጋማሽ በጉጉት እየተከታተሉ ነው። በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ካለ ቦታ አደንቋሪ ጩኸት ቢሰሙም ምንም አንዳልተከሰተ ሁሉ ጨዋታቸውን መመልከት ቀጥለዋል። ስክሪኑ

ን ወደማይታይበት በረንዳ ወጥተን ከተቀመጥን በኋላ ስለሆነው ነገር መረጃ ለማግኘት ሞከረን። ብዙም ሳይቆይ በቻይዶንዶ የራግቢ መጫወቻ ሜዳ ተስብሰበው ጨዋታውን በመመልከት ላይ ባሉ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች መሃል ሌላ ቦምብ መፈንዳቱን ሰማን። ያኔ ነው ነገርየው የአሸባሪዎች ጥቃት መሆኑን የተረዳሁት። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከ“ኢትዮጵያን ቪሌ

ጅ” እንድንወጣ ደውሎ ያስጠነቀቀኝ ጓደኛዬ በድጋሚ ደውሎ ከተማ ውስጥ የሚወራውን አረዳኝ። ከቻይዶንዶ ሌላ ንቲንዳ በተሰኘው ቦታ ሌላ ቦምብ ፈንድቷል መባሉን ነገረኝ። “ኦ….እግዚያብሔር….”። ከዚህ በላይስ አልችልም። እንባ ጉንጮቼን አቋርጦ መውረድ ጀመረ። ከጓደኛዬ ጋር ስለአደጋው ይበልጥ መረጃ በተቀበልኩ ቁጥር ተጨማሪ እንባ በፊቴ ላይ መፍሰሱን አላቋርጥ አለ። ሀዘኔን ያበዛው ደግሞ በአደጋው ወቅት አብረውኝ የነበሩትን ጓደኞቼን ወደ ቦታው እንዲመጡ እና አብረን ኳስ እንድንመለከት ሀሳብ ያቀረብኩት እኔ በመሆኔ ነበር። ወደ ምግብ ቤቱ የደረሰነው በጣም አርፈደን ነ

በር። ቤቱ ግጥም ብሎ ከመሙላቱ የተነሳ ብቸኛ ክፍት ቦታ የነበረው ከስክሪኑ ስር ነበር። ስክሪኑ አጠገብ የነበሩ ሰዎች ክፉኛ መጎዳታቸውን ሳስታውስ ህይወታችንን ያተረፈውን አንድ አስተናጋጅ እንደነበር ትዝ አለ። አስተናጋጁን ስክሪኑ ፊት ወንበር እንዲያስቀመጥልን ስንጠይቀው በነበረው ክፍት ቦታ ወደ ስክሪኑ በጣም ስለምንቀርብ ጨዋታውን በትክክል መመልከት እንደማንችል አስረድቶን ሌላ አማራጭ አቀረበልን። ከ

ስክሪኑ ጎን ያለችውን አነስተኛ ክፍል እያሳየን እዚያ ውስጥ እንድንገባ እና ወንበር ከቢሮም ቢሆን ፈልጎ እንደሚያመጣ ቃል ገባልን። እንዳለው አደረግን። እርሱም ቃሉን ጠብቆ ወንበሮች ይዞልን መጣ። ጨዋታው ከተጀመረ በኋላ ወንበር ለውጬ መተላለፊያ አጠገብ ተመልካቹ መሃል ተቀመጥኩ። ከፊቴ የተቀመጠች ሴት የያዘችውን ቢጫ “ቩ

ቩዜላ” በድጋድ ስሜት በተደጋጋሚ ስትነፋ እንደነበር አስታውሳለሁ። ግቢውን ግጥም አድርገው እንደሞሉት አብዛኞቹ ተመልካቾች እርሷም የኔዘርላንድስ ደጋፊ ነበረች። ተመልካቹ ለመላወሻ የተተውን ቦታ ሁሉ በመያዙ ቦታው ሁሉ ተጨናንቆ ነበር። በ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” እንደዚህ ህዝብ ጢም ብሎ ሞልቶ የሚታየው በበዓላት ቀን ብቻ ነው። ያኔም ልክ እንደአሁኑ የአብዛኛው ዓይን ከስክሪኑ አይነቀልም። ስክሪኑም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሙዚቃ ክሊፖችን እያከታተለ ያስኮመኮማል። ምግብ ቤቱ የአገር ቤት ማስታወሻ ነው። በግ

ቢው ውስጥ የሚገኙት በሳር የተሸፈኑት ጎጆዎች የአገራችንን ገጠር ያስታውሰናል። በ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” በኩራት የሚውለበለበው የኢትዮጵያ ባንዲራም ከቤቱ ጋር ያለንን ቁርኝት ይበልጥ የሚያጠብቅ ነው። አሁን ሁሉም ነገር እንዳልነበር ሆኗል።ከ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” አቅራቢያ እስከ እኩለ

ለሊት ቆየን። ግን እስከዚያን ሰዓት ድረስም ቢሆን አደጋውን እንዴት ሊደርስ እንደቻለ በቅጡ መረዳት አልቻልንም። የመረጃ ረሃብ ላይ ነበርን። ወደ ቤት ተመልሰን ቴሌቪዥን ላይ አፈጠጥን። ያሉትን ጣቢያዎች በሙሉ እያቀያየርን ተመለከትን። ሁሉም ጣቢያዎች ስፔን የዓለም ዋንጫ አሸናፊ መሆኗን ነው የሚያበስሩት። ዘግየት ብሎ “አል ጀዚራ” ዜናውን ይዞ መጣ። ጣቢያው “ሰበር ዜና” ከሚለው በትልልቁ ከተጻፈው ጽሁፍ ስር 26 ሰዎች ካምፓላ ላይ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜን በመመልከት ላይ እያሉ መሞታቸውን አወጀ። የኡጋንዳው ኤንቲቪ ተከተለ። የኤንቲቪው ዘ

ገባ እንደ አልጀዚራ አጭር እና ምስል አልባ አልነበረም። አደጋው በደረሰባቸው በሁለቱም ቦታዎች ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ምስል በተደጋጋሚ ማስተላለፍ ያዘ። ከፊት ለፊቴ የነበረችው ሴት ይዛው የነበረውን ቢጫ “ቩቩዜላ” አሁን በፖሊስ እጅ ላይ ተመለከትኩት። ጣቢያው የፖሊስ ኢንስፔክተር ጄነራል የሆኑት ካሌ ካይሁራ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ፊት ለፊት ከሚዲያዎች ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ማሳየት ጀመረ። ኤንስፒክተር ጀነራሉ በ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸውን ተናገሩ። አደጋውን ያደረሰውም የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን የሆነው አልሻባብ እንደሆነ ለብዙሃን መገናኛዎች ገለጹ።ምንም ዓይነት አርትኦት ሳያደርግ ምስሎችን እ

ንደመጡለት ያስተላለፍ የነበረው ኤንቲቪ ከደቂቃዎች በኋላ በቻይዶንዶ ራግቢ ሜዳ የሆነውን ድርጊት እንደወረደ ማሳየት ጀመረ። ምስሎቹ ዘግናኝ የሚለው ቋንቋ ብቻ አይገልጻቸውም። ተቆርጦ የወደቀ አንገት የቴሌቭዥኑን ስክሪኑን ሞላው። በተቀመጡበት በዚያው የሞትን ጽዋ የቀመሱ ሰዎችንም ተመለከትን። እንባዬ በድጋሚ መውረድ ጀመረ። እስከ ለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጣቢያዎችን እየቀያየርን ስንመለከት ቆየን እና ጎናችንን ለማሳረፍ ወደ አልጋዎች አመራን። እንቅልፍ ግን ከየት ይምጣ። ከዚያን የመሰለ አደጋ በኋላ እንቅልፍ….? ማልጄ ነበር የተነሳሁት። መታጠቢያ ቤት ደር

ሼ ፊቴን ስመለከት የዓይን መነጽሬ በነጠብጣቦ

ሞትን ማምለጥ ይህ ጹሁፍ የዛሬ ዓመት አዲስ አበባ በሚታተመው “ፎርቹን” ሳምንታዊ የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ነበር።

በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለማስታወስ መጠነኛ ማሻሻያ በማድረግ ወደ አማርኛ መልሰን አትመነዋል።

“እባካችሁ የእኔን መኪና ውሰዱ እና ወደ ሆስፒታል ውሰዱልኝ” አለች በእንባ የምትታጠበው ማሜ። በምግብ ቤቱ አቅራቢያ ወዳለው ሆስፒታል ቁስለኞችን ለመውሰድ ስንዘጋጅ ሀሳባችንን የሚያስለውጥ ማስጠንቀቂያ ሰማን። “ወረቀት የሌላችሁ ሐበሾች አሁኑኑ ውጡ” የሚለው በአማርኛ የተነገረው ማስጠንቀቂያ የመጣው ከወደ በር አካባቢ ነበር። ይሄኔ ትዝ ሲለኝ መታወቂያም ሆነ ፓስፖርት

አልያዝኩም። በሰባት ወር ገደማ የኡጋንዳ ቆይታዬ መታወቂያ የተጠየቅኩት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው የተጠየቅኩት እያልኩ የማዳንቅ ነበርኩ። ምናልባትም ያ ይሆናል ያለምንም መታወቂያ ከቤት እንደወጣ ያደረገኝ። ወዲያውኑ አንድ ጓደኛዬ ደወሎ ከአካባቢው በአስቸኳይ እንድርቅ አስጠነቀቀኝ። ፖሊስ በአካባቢው ከደረሰ በኋላ ነገሮች ጥሩ እንደማይሆኑ ጨምሮ ነገረኝ። ምክሩን ተቀብዬ የምግብ ቤቱን ግቢ ከጓደኞቼ ጋር ወዲያውኑ ለቅቄ ወጣሁ። ከወጣን በኋላ ግን ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለ

ብን ግራ ተጋባን። ምግብ ቤቱ አጠገብ ቆምን እያለ እጄ ላይ የሚያሙለጨልጭ ነገር ተሰማኝ። የሚሙለጨለጨውን ነገር በሌባ እና በአውራ ጣቴ አጣብቄ ይዤ ምንነቱን ለማወቅ ወደ ብርሃን ተጠጋሁ። “ኦህህህህህህህህ…”። ለካንስ የሚሙለጨልጨው ነገር የሰው ስጋ እና ደም ቅይጥ ነው። ክንዶቼን ፈተሽኩ። በተበጣጠሰ የሰው ስጋ ተሸፍኗል። የለበስኩትን ቲ-ሸርት ስነካ ሻከረኝ። ቲ-ሸርቴም በተበጣጠሱ ስጋዎች ተሸፍኖ ነበር። “ኦ….እግዚያብሔር….”

አደጋው በደረሰ ማግስት የወጡ ጋዜጦች የፊት ለፊት ገጽ ይህንን ይመስል ነበር ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

Page 7: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 7

የማይረሳው ዕለት

አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ልዩ ዘገባ

ች ተሞልቶ ተመለከትኩ። መነጽሬን አውልቄ አስጠግቼ አየሁት። በመነጽሩ መስታወት ላይ ያሉ ነቁጦች የተበጣጠሰ የሰው ስጋ መሆኑን ስረዳ ክፉኛ አዘንኩ። ቀናት ቢያልፉም ይህ ነገር እንደማይለቀኝ ተሰማኝ። ከሰዓታት በኋላ የኡጋንዳ ፖሊስ ስለአደጋው ለማብራራት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝቼም ይሄው ስሜት አብሮኝ ነበር። አንደተከፋሁ ነበር። ውስጤም መረበሹን አላቆመም። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሚነገሩት ነገሮች ደግሞ ይህንን ስሜት የሚያባብሱ እንጂ የሚያረጋጉ አልነበሩም። በመግለጫው ከተባሉት ነገሮች አንዱ ደግሞ እስካሁን ያላሰብኩትን አሳወቀኝና ውስጤን ይበልጥ አተራመሰው። ጥቃቱ የተፈጸመው በአጥፍቶ ጠፊዎች እንደሆነ ፍንጮችን ማግኘቱን ፖሊስ ማሳወቁ ነበር የረበሸኝ። “እኔም የተረፍኩት ከአጥፍቶ ጠፊዎች ነው ማለት ነው?”። ጥያቄዬ በጆሮዬ ደጋግሞ አስተጋባ። እያንዳንዱ ደቂቃ ባለፈ ቁጥር አደጋውን አስመ

ልክቶ የሚደርሰኝ መረጃ ባገናዘብኩ ቁጥር ነገርየውን በፊልም የተመለከትኩት እንጂ በራሴ የደረሰ አልመስልህ አለኝ። ከአደጋው በኋላ ያሉት ቀናት ድንገት በሚገነፍሉ ስሜቶች የተሞሉ ነበሩ። በአደጋው ቦታ እንደምኖር የጠረጠሩ ጓደኞቼ ደህነቴ አስግቷቸው መልዕክቶችን ያጎርፋሉ። እነርሱን ለማረጋጋት በ“ፌስ ቡክ” ላይ “አለሁ…አልሞትኩም….ተርፌአለሁ” ማለት ነበረብኝ። ከዚህች አጭር መልዕክቴ ስር ያለው ቦታ በጓደኞቼ አጽናኝ መልዕክቶች ተጨናነቀ። እያንዳንዱን መልዕክት ባነበብኩ ቁጥር ጥንካሬ እንደሚሰጠኝ ሁሉ እንባዬንም ያመጣው ነበር።“እንዴ! ምን ሆኜ ነው ማልቀስ ማቆም ያቃተ

ኝ?” ስል ራሴን በተደጋጋሚ ጠይቄአለሁ። መልስ ግን ማግኘት አልቻልኩም። በጋዜጠኝነት ሙያዬ ውስጥ የቦምብ ፍንዳታን ጨምሮ ብዙ አደጋዎችን ተመልክቼአለሁ። የሞቱ፣ የቆሰሉ ሰዎችንም አይቼአለሁ። እንዲህ አይነት ልምድ ስለነበረኝም ምንም ነገር ቢመጣ ስሜቶቼን መቆጣጠር እችላለሁ ብዬ አስብ ነበር። ግን አልሆነም። ጥቂት ቆይቼ ራሴን የማገኘው ሳለቅስ ነው። ኢትዮጵያዊት በቲቪ ቀርባ የጠፋ ወንድሟን እንዲያፈላልጓት እያለቀሰች ስትጠይቅ ስመለከት እኔም እርሷን እከተላለሁ። ለሟቾች በተዘጋጀ የሽኝት ስነስርዓት ላይ ስታደም እንባዬ ይቀድማል። የሟቾችን ፎቶ ተመለከትኩ ቁጥር በጣም አዝናለሁ። ከአደጋው በኋላ የነበረው ጊዜ በስሜት መለዋ

ወጦች ብቻ የቆመ አልበረም። የስደተኞችን ሰላማዊ ህይወት እስከማናጋት ድረስ ሄዷል። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን አደጋውን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩተን ሶማሌዎችን ይመስላሉ በሚል ጥቃት እና መገለል ደርሶባቸዋል። እንደጋዜጦች ዘገባ ከሆነ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በአደጋው ተጠርጥረው ታስረዋል። በፖሊስ ጣቢያ ለቀናት ታስረው፣ ኃይል የተቀላቀለበት ምርመራ ተደርጎባቸው የተለቀቁም ነበሩ። ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ቦምቦች ተገኙ እየተባለ ከተማይቱ ስትታመስ ሰንብታለች። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ የገባቸው በርካታ ሐበሾች በር ዘግተው ቆይተዋል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን በእርግጠኝነት አንድ ነገ

ር ማለት ይቻላል። ጁላይ 11 ብዙ ነገሮች ለዋውጧል። ብዙዎች 13 ቁጥርን ከመጥፎ እድል ጋር ያይዛሉ። ለኡጋንዳውያን፣ ለአሜሪካኖች እና ለእኔ ግን 11 ቁጥር ሌላ ትርጉም አለው። እ.ኤ.አ በሴፕቴምበር 11 2009 በካምፓላ በተቀሰቀሰ ብጥብጥ በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ሞተዋል። በዚያኑ ቀን ከስምንት ዓመት፤ ኢትዮጵያኖች አዲስ አመታቸውን በሚያከብሩበት ዕለት፤ በኒው ዮርክ የአለም የንግድ ማዕከል መንትያ ህንጻዎች ላይ ደግሞ የሆነውን ሁላችንም እናስታውሳለን። አሁን ደግሞ ጁላይ 11 በኡጋንዳ ታሪክ “አሰቃቂ የአሸባሪዎች ጥቃት የደረሰበት” በሚል ተመዝግቧል። ለእኔ ግን ጁላይ 11 የማንቂያ ደውል ነበር….ንቃ…..ህይወት አጭር ናት….ከሁለት ደቂቃም

ያጠረች……q በተስፋለም ወልደየስ

ቀን አያውቁቀኑ እሁድ ነው፡፡ እናም ዘወትር በዚሁ እለት

እንደምናደርገው ወደ ሜዳ ወርደናል፡፡ በእግር ኳስ ሰበብ ፍቅርና ጨዋታን ልንገዛ መተጋጋዝና መተሳሰብን ልናጠናክር፡፡ በሁለት ወገን ተከፍለን ኳስን ከወዲያ ወዲህ፣ ሰውነታችንንም ከላይ ታች ስናንቀሳቀስ አርፍደን አሁን ወደማብቂያው ደርሰናል፡፡ የዛሬው ቀን በተለይ እግር ኳስ እንደ ነፍሳችን ለምንወደው ለእኛ ቡድን (ግሩፕ) የተለየ ነው፡፡ ምክንያቱም የውድድሮች ሁሉ ንጉስ የሆነው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ የሚያገኝበት እለት በመሆኑ፡፡ ሁላችንም የዓለም ዋንጫን ፍጻሜ ለማየት ጓጉተናል፡፡ ስፔንና ሆላንድ በእግራቸው ቅልጥፍናና ጥበብ ስሜታችንን እንዲያረኩት የፈለግንበትም ጊዜ እየተቃረበ ነው፡፡በተለይ ለእኔ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እንደ

ወትሮዎቹ አይደለም፡፡ አለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮችን ማየት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ እንደ የደቡብ አፍሪካው የአለም ዋንጫ በደንብ የተከታተልኩት የለም፡፡ ከመክፈቻው እስከ ፍጻሜው አንድም ሳይቀረኝ ስራዬንም ቤተሰቤንም እየተውኩ ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልክቼያለሁ፡፡ከማለዳ ጀምሮ ካረፍድንበት የእግር ኳስ ሜዳ

ወጥተን ዘወትር እንደምናደርገው ለምሳ “ሳሚ ምግብ ቤት”ተሰባሰብን፡፡ ትዝ ይለኛል አብነት የሚባለው ወዳጃችን ለመጀመሪያ ቀን ዶሮ ወጥ መሸጥ የጀመረበት ቀን ስለነበር እሱኑ ለማስተዋወቅ በሚል እኛም ምሳችንን ዶሮ ወጥ ነበር ተሰባስበን የበላነው፡፡ ማዕዱ ቀርቦ ከፍ እስኪልም ሳቅና ጨዋታ ከመካከላችን አልጠፋም ነበር፡፡ በእለቱ ከናይሮቢ በእንግድነት የመጣውና ኳስ አፍቃሪው ኤፍሬምም ከሜዳ ጀምሮ አብሮን ነበር፡፡ በዚህ መልኩ ምሳ ከበላን በኋላ የጓጓንለትን የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ውድድር ለማየት ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡ምሽት ሆነ፡፡ ዛሬም ድረስ በጥቁረቱ የማልረሳ

ው ለዘላለም የሚኖር የሚመስል ጨለማ፡፡ ስፔንና ሆላንድን በቴሌቪዥን መስኮት እያየን ለመደገፍ በቡድን ተከፋፍለናል፡፡ ዘላለምና ዘድንግል ከሚባሉት ጓደኞቼ ጋር ጨዋታውን ለማየት በሚል መጀመሪያ ያመራነው “መቹቼ” የሚባል የስዊዝ ሬስቶራንት ነበር፡፡ እዚያ ሄድን ከተቀመጥን የምንጠጣውንም ካዘዝን በኋላ ግን ‹‹የለም ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሄደን እንይ›› የሚል ሀሳብ ተሰነዘረ፡፡ ሀሳቡ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ ሳይረፍድብን እንሂድ ተባባልንና ወዲው ወደ ኢትዮጵያን ቪሌጅ ምግብ ቤት አመራን፡፡ እኔ የሆላንድ ቡድን ደጋፊ ነበርኩ፡፡

የ45 ደቂቃው ዓለምበእርግጥ ከዚህም በፊት ብዙውን ጊዜ ጨዋታ

ዎችን የምንመለከተው በቡድን እየተሰባሰብን ነበር፡፡ በዚህ የፍጻሜ ጨዋታ ቀን ግን አይቻቸው ከማላውቃቸው ልጆች ጋር ጭምር ኳስ አብረን ለማየት የተገባበዝንበት በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል፡፡ከእኛ ጋር የነበረው ዘላለም መቼም የኳስ ፍቅ

ሩ የተለየ ነው፡፡ እኛ ቁጭ ብለን ስናይ እሱ ግን ዘጠናውንም ደቂቃ ከእንቅስቃሴና ከንግግር ጋር ነው የሚያሳልፈው፡፡ በዚህም ከሰዎች ጋር ሊጋጭ ይችላል እያልን እንሳቀቅ ነበር፡፡ ያን ቀንም በዚሁ ምክንያት ከሰዎች ጋር እንዳይጋጭ በሚል “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ከገባን በኋላ ከፊት ይልቅ

ወደኋላ መቀመጡን መረጥን፡፡ ኢትዮጵያን ቪሌጅ የደረስነው ብዙ ሰው ከመግባቱ በፊት ነበር፡፡ ከእኛ በፊት የገቡ ዘጠኝ ያህል ነጮች ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል፡፡ እኛም ለሶስታችን የሚሆን መቀመጫ አዘጋጅተን ተቀመጥን፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ዘላለም ከፊት ካልተቀመጥን እያለ ይጎተጉተን ነበር፡፡ እኔ ግን “ለንፋሱም ይሄው ይሻላል” በሚል ለማግባባት ሞክሬ እዚያው ተቀመጥን፡፡ ኳሱ ሊጀመር ሲል ሰውም ቀስ በቀስ እየበዛ መጣ፡፡ ትዝ ይለኛል ዘላለም ከእኔ በተቃራኒው የስፔን ደጋፊ ነበር፡፡ ጨዋታው እየሞቀ የተመልካቹም ስሜት ከወዲያ ወዲህ መንጸባረቅ ቀጠለ፡፡ በእለቱ እኔ የምደግፈው የሆላንድ ቡድን ጉልበት የተሞላበት አጨዋወት ይከተል ስለነበር ብዙም አልተደሰትኩበትም፡፡ መሸነፉ እንደማይቀር ስለገመትኩ ስሜቴም መቀያር ጀምሮ ነበር፡፡ እንዲህ እየሆነ “ቪሌጅ” ከመጠን በላይ እየሞላ፣ ቦታ እየጠፋ መጣ፡፡ ጠረጴዛ ከመጥፋቱ የተነሳ የሚገቡት ሰዎች ወን

በር እየተሰጣቸው ወደፊት እየሄዱ ይቀመጣሉ፡፡ በዚያ መልኩ ቦታ ጠፍቶ እኛ የተቀመጥንበት አጠገብ ግን አንድ ባዶ ወይም ትርፍ መቀመጫ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አብሮን ኳስ ይጫወት የነበረው ካሌብ ከሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ጋር ሲገባ አየሁት፡፡ ልጠራው አሰብኩና ያለው አንድ ቦታ ብቻ ስለነበር ‹‹እሱን ጠርቼ ሌሎችን ልተዋቸው አይደል›› በሚል እሱንም ዝም አልኩትና ከፊት ሄዶ ተቀመጠ፡፡ኳስ ማየቱ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ልክ የመጀመሪ

ያው 45 ደቂቃ አልቆ የዕረፍት ፊሽካ ሊነፋ ሲል ሽንቴን ለመሽናት ብድግ ስል ሀይለኛ ፍንዳታ ግቢውን አናወጠው፡፡ በመጀመሪያ ፈንጂ ነው የሚል ምንም ግምት አልነበረኝም፡፡ እንዲያውም እኔ በግሌ ኳስ የሚታይበት ፕሮጄክተር የተቃጠለ ነበር የመሰለኝ፡፡ ምክንያቱም ከፕሮጄክተሩ ፊት ለፊት የተሰቀለው ስክሪን መሀሉ ተቀዷል፡፡ ቴሌቪዥኖቹ ይሰራሉ፡፡ መብራት አለ፡፡ ስለዚህ ቴ

ሌቪዥኖች ከሰሩ ፕሮጄክተሩ ፈንድቶ ነው አልኩ፡፡ ግምቴን ለሌሎች እያካፈልኩ ማረጋጋት ስሞክር ወዲያው ከፈነዳበት አካባቢ ደም በደም የሆኑ ሰዎች እየመጡ ከፊታችን መውደቅ ጀመሩ፡፡

አስከሬን እንደ ቅርጫ ስጋ ነገር ይሸታል አመድ ነገር ደግሞ ላያችን ላ

ይ ተበታትኗል፡፡ የዚያን ጊዜ በእጅጉ ደነገጥኩ፡፡ ወይ ወደውጪ አልሸሸሁ ወይ ወደ ፊት አልተጠጋሁ የቆምኩበት ደርቄ ቀረሁ፡፡ አስታውሳለሁ ሶስት አራት ደቂቃ ያህል ከቆምኩበት አልተንቀሳቀስኩም፡፡ ከዚያ በኋላ ተነስተን ወደ ሰዎቹ መሀል ገባን፡፡ ትንሽ እንደቆየ የደህንነት ኃይሎች ወዲያው መጡና ሰዎችን ማስወጣት የተጎዱትንም በመኪና እየጫኑ መውስድ ሲጀምሩ እኔ፤ ማሜ (የኢትዮጵያን ቪሌጅ ባለቤት)ና ማኔጀሩ ብቻ ቀረን፡፡ መጀመሪያ የደረሱት ፖሊሶች ነበሩ፡፡ እነሱ የ

እጅ ጓንት ለእኛ ሰጡንና ለጥበቃ በዙሪያው ተሰማሩ፡፡ በዚህ ጊዜ እኛ አስከሬን ማንሳት ጀመርን፡፡ በአደጋው የተሰባበሩ አሉ፡፡ እግራቸው የተቆረጠ አሉ፡፡ ሁሉም በድንጋጤ የሚያወራውን አያውቅም፡፡ ግማሾቹ ነጮች ‹‹ትታችሁን አትሂዱ ሀገራችን ስላልሆነ ነው ወይ›› ይላሉ፡፡ ህይወታቸው ያለፈ አሉ፡፡ የትኛውን ቅድሚያ ሰጥተን እንደምንረዳ ግራ ተጋባን፡፡ ስለራስ ደህንነት መጠንቀቅ የማይታሰብ ነበ

ር፡፡ ከፊታችን ያገኘነውን አንዱን ስናነሳ ሌላውን ወደመኪና ስናደርስ በሌላ በኩል ህይወቱ ያለፈውን ማንነት ለመለየት በምናደርገው ጥረት መዋከብ ሆነ፡፡ አንዳንዶቹ ያንቀላፉ እንጂ የሞቱ አይመስልም ነበር፡፡ ለምሳሌ ጌታ ያውቃል የሚባለው ወዳጃችን እንደሞተ ማንም አላወቀም ነበር፡፡ እኔም ሰው ህይወቱ ሲያልፍ አይኑ አካባቢ የሚስተዋለውን ለውጥ አይቼ ነው ህይወቱ ማለፉን ያወቅሁት፡፡ በጥቅሉ በህይወቴ ካየኋቸው አደጋዎች ሁሉ

እጅግ አሰቃቂውና አሳዛኙ ነበር፡፡ በተለይ ከሐበሾች መካከል ሁለት ልጆች አሟሟታቸው አሁንም ድረስ አይረሳኝም፡፡ ምክንያቱም የፈነዳው ቦምብ ከአንደኛው ጫፍ ወርውሮ ወደሌላኛው ስለወሰዳቸው እጅግ ተጎድተው ነበር፡፡ የሟቾቹን አስከሬን በምናነሳበት ወቅት የሰውነት አካላቸውን ለየብቻ ነበር ያገኘነው፡፡ እንዲህ እያደረግን ነበር የሰበሰብነው፡፡ አንዱን የሰውነት አካል እንዲያውም አሞራ ይዞት ወጥቶ የቤቱ ጣራ ላይ ተገኝቷል፡፡ ይሄም በዚያን ሰሞን በታተሙ ጋዜጦች በአንደኛው ላይ በፎቶ መውጣቱን አስታውሳለሁ፡፡ እንዲህ እያደረግን የተጎዱትን እየረዳን ህይወ

ታቸው ያለፈውን አስከሬን እየሰበሰብን እያለ የፖሊስ አዛዡ መጥቶ በአካባቢው የነበሩትን ማረጋጋት ሲጀምር ሌሎችም እኛን ማገዝ ጀመሩ፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን እኔና የምግብ ቤቱ ማኔጀር ብቻ ነበር እያነሳን ወደመኪና የምንወስደው፡፡ በወቅቱ አምቡላንስ እንኳን ባለመምጣቱ ፖሊሶች በራሳቸው መኪና ወዲያው ወዲያው እየተቀበሉ ወደ ሆስፒታል እየያዙ ይሄዳሉ፡፡

የጉድ ሌሊት አይነጋምተረቱ የጉድ ቀን አይመሽም ነበር፡፡ ለእኛ ግን

አሰቃቂው ሌሊት የሚነጋ ሁሉ እስከማይመስል ረዝሞብን ነበር፡፡ ይሁንና እንዳያልፍ የለም

ማን ይናገር የነበረ…አቶ ካሳ መንግስተዓብ ጁላይ 11 ምሽት በኢትዮጵያ ገጠር ምግብ ቤት (ኢትዮጵያን ቪሌጅ) የዓለም ዋንጫን የፍጻሜ

ውድድር በሚመለከቱ ወገኖች ላይ ከደረሰው የቦምብ አደጋ በህይወት ተርፈው ክስተቱን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ መመልከት ከቻሉት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ነውና አቶ ካሳ ‹‹አንድ ዓመት ሊሞላው

ቀርቶ ወር ሁለት ወር እንኳን የሆነው አይመስልም›› የሚሉትንና አስከሬን እንደ ቅርጫ ስጋ ከየቦታው የሰበሰቡበትን አሳዛኝ ክስተት እንደሚከተለው ይተርኩታል፡፡

ወደ ገጽ 21 ዞሯል

በህይወቴ ካየኋቸው አደጋዎች ሁሉ እጅግ አሰቃቂውና አሳዛኙ

ነበር፡፡ በተለይ ከሐበሾች መካከል ሁለት ልጆች አሟሟታቸው አሁንም

ድረስ አይረሳኝም፡፡ ምክንያቱም የፈነዳው

ቦምብ ከአንደኛው ጫፍ ወርውሮ ወደሌላኛው ስለወሰዳቸው እጅግ ተጎድተው ነበር፡፡

a b

d c

ፎቶ

-ቪኦኤ

ኢትዮጵያን ቪሌጅ ምግብ ቤት ከአደጋው በኋላ

Page 8: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና8

ልዩ ዘገባ

የማይረሳው ዕለት

አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

Page 9: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 9

የስደት ዓለም

እንዴት ነው ወደ አውስትራሊያ የሄድከው?በግል ስፖንሰር ነው የሄድኩት። እንደተለመደ

ው ፎርም ተሞላ። በጉዳይ (በኬዝ) ከማለት ይልቅ በአጋጣሚ ነው። ከአንድ ዓመት ከ 10 ወር በፊት እዚህ ካምፓላ ላይ አውስትራልያ ያመለከትን ሰዎች ጥሩ እድል አጋጥሞን ነበርና በዚያ ወቅት ነው የእዚያ ዕድል ተጠቃሚ ሆኜ ነው የሄድኩት።

እንደሄድክ በቀጥታ ሲድኒ ነው ያረፍከው ወይስ ሌሎች ቦታዎችን የመመልከት እድል አጋጥሞሃል?እንደሄድኩኝ ሲድኒ ነው ያረፍኩት። ኑሮዬ እስ

ካሁንም ሲድኒ ነው። ወደ ትምህርት ቤት ከመግባቴ በፊት ግን “ኩዊንስላንድ” የሚባል ስቴት አለ። እዚያ ሄጄ ነበር። አውስትራሊያ ውስጥ በቱሪስት መስብህነቷ በይበልጥ የምትታወቅ፣ እንደ “ጎልድ ኮስት”፣ “ሰንሻይን ኮስት” የሚባሉ ጥሩ የመዝናኛ ቦታዎች ያሉባት፣ “ብሪስበን” የምትባል ከተማን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ይህ ቦታ ከዓለም ቱሪስቶች እየመጡ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉበት ነው። በጣም የወደድኩት ቦታ ነው። ብዙ ጊዜ አንድ ቦታ ስሄድ አካባቢን የማወቅ፣ የተሻሉ ቦታዎችን የማየት፣ በአንደዚህ ዓይነት ነገሮች የመደሰት ባህሪው አለኝ። በዚያ ምክንያት ነው እነዚህን ቦታዎች ያየሁት።

በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደ አውስትራልያ ያሉ ሀገሮች ሲሄዱ ኑሮን ለማሸነፍ ላይ ታች መሮጥ ነው እንጂ ትምህርት ቤት አይገቡም። አንተ እንዴት ተሳካልህ?ከሰው ሰው ፍላጎቱ ይለያያል። እዚህ ሆነን ብ

ዙ ጊዜ ስናስብ በውጭው ዓለም ሄደን፣ ቶሎ ስራ አግኘተን፣ ትንሽ ሳንቲም ይዘን፣ ቤተሰብ ረድተን የሚሉ ነገሮች ናቸው አእምሮአችን ውስጥ የሚመጡት። ከዚህም ስሄድ “ከስደት ዓለም አንድ ነገር ማትረፍ አለብኝ” ብየ ነው የሄድኩት። ያ ነገር ገንዘብ ሊሆን አይገባውም። የምሰራ ከሆነ አዎ አገኛለሁ፣ እጠቀማለሁ። ነገር ግን ከዚያ ያለፈ ነገር መኖር አለበት የሚል ዕምነት ነው የነበረኝ። እዚህ ያሉ ወዳጆቼ ያውቃሉ። እማራለሁ ቢያንስ ቢያንስ እሷን ለማግኘት ነው የምሄደው ነው ያልኩት። እንደወሰንኩትም የመጀመሪያ ስራዬ የነበረው

በየዩኒቨርስቲዎቹ እየዞሩ መረጃዎችን ማሰባሰብ ነበር። ጊዜው የመረጃ ዘመን ነው። “ጎግል አድርገህ” ስለእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ አስፈላጊ ነገር መፈለግ ትችላለህ። በዚህ አይነት የሁሉንም ዩኒቨርስቲዎች ሁኔታ ካወቅሁና አካባቢውን እና የአገሩን ሁኔታ ካጠናሁ በኋላ የምፈልጋቸውን የትምህርት ዓይነቶች መረጥኩ።

የእኛ ሰው በሲድኒ

የመማር ዕድሉ ግን አለ? ብዙ ሰው ዕድሉ የለም፣ ከባድም ነው ብሎ ስለሚያስብ ይመስለኛል ወደ ትምህርቱ ዓለም የማይገባው። ገንዘብ ኖሮህ አይደለም ትምህርት የምትማረ

ው። መንግስት ይደጉመሃል። የምትበላው፣ የምትጠጣውን ለመሸፈን፣ መጠለያ እንዳያስቸግርህ፣ መንግስት በየ14 ቀኑ የተወሰነ ገንዘብ ይሰጣል። በዚያ ላይ “ሂዩማንቴሪያን ቪዛ” አግኝተህ ከሄድክ ከወለድ ነጻ የሆነ 86 ሺህ ዶላር ያህል የመማር መብት አለህ። እንደዚህ የተመቻቹ ሁኔታዎች ካሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ካልተማርን መቼ እና የት ልንማር እንችላለን? አውስትራልያ እንድትማር በጣም የሚገፋ ስርዓት ያለበት ሀገር ነው። ምን ያህሎቻችን በዚህ እድል ተጠቅመናል የሚለው ግን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚወድቅ ነው። ብዙዎቻችን ገንዘብ ያሸንፈናል። ገንዘብ አግኝ

ተን እዚያ ኑሮ እንጀምራለን። እዚያ እንግዲህ ኑሮ በተለያዩ ወጪዎች የተሞላ ነው። “ቢል” ይመጣል። ቤት በ“ሞርጌጅ” መግባት ይኖራል። አንዴ እዚያ ውስጥ ከገባህ በኋላ ወጥተህ ወደ ትም

ሞ ወደእዚህ ማምጣት ያስፈልጋል። መቼም በስደት ህይወቴን እስከመጨረሻው እገፋለሁ ብዬ አላምንም። በአንድ ወቅት ሁኔታዎች ሲመቻቹ ወደ አገር ቤት እመለሳለሁ ብዬ አስባለሁ። እና ባዶ እጄን መመለስ አልፈልግም። ምንድነው ይዤ ልገባ የምችለው ነገር? ይህን ዕድል ሳገኝ ሁኔታዎችን አይቼአለሁ።ፍላጎቴን እና የትምህርት ታሪኬን አውቃለሁ።

የሚገባኝን የሙያ መስክ የመረጥኩኝ ይመስለኛል። በዚያ ዙሪያ ስኬታማ ብሆንና አንድ ቀን ወደ አገሬ የተወሰነ እውቀት ይዤ ብገባ ምናልባት በዚያ ዙሪያ ዕውቀታቸውን ይዘው ከገቡ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አንድ ነገር በጋራ መስራት ነው የማስበው። የነበረውን ማሻሻል ሊሆን ይችላል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ ነገር ካለ ያንን አሰራር አገር ቤት ወስዶ ተግባራዊ ማድረግ ሊኖር ይገባል ብዬ አምናለሁ። በነገራችን ላይ የትኛውንም የትምህርት ዓይነት

ብትማር ፍላጎቱ ካለህ እና ከተማርክ በጥሩ ሁኔታ ትጨርሳለህ። በጥሩ ሁኔታ ከጨረስክ ደግሞ ምንም የምታጣው ነገር የለም። ይህንን ከጓ ወደ ገጽ 22 ዞሯል

5. የተለያዩ ሀገራት ስፖንሰር አግኝተው የሚጠብቁ ሰዎች ማመልከቻቸውን ካስገቡ በኋላ በዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ላይ ግፊት ከማድረግ በዘለለ “አፋጥኑልን” ለማለት ጉልበት አይኖራቸውም። ስለዚህ ውጤታችውን እስኪያውቁ ድረስ እዚያ ሲሄዱ ለሚጠብቃቸው ህይወት መማር እና መዘጋጀት አለባቸው።

መስፍን ገብረስላሴ ይባላል። አርባ አንደኛ ዓመቱን ያከበረው በቅርቡ ነው። ከአንድ ዓመት ከ10 ወር በፊት ወደ አውስትራልያ ከመሄዱ በፊት ካምፓላ ኡጋንዳ

ውስጥ ለበርካታ አመታት ኖሯል። አሁን የሚኖረው ሲድኒ አውስትራልያ ነው። ሲድኒ ባለው ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ በአንድ ጊዜ

ሁለት ዲግሪ ለማግኘት እየተማረ ይገኛል። ወደ ካምፓላ ለዕረፍት በመጣበት ወቅት ከ “ሐበሻዊ ቃናው” ጋር ተስፋለም ወልደየስ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ደኞቼ ተሞክሮ አይቼዋለሁ። ብዙዎቻችን ግን ያንን አለመዳፈር፣ ከእነሱ ጋር ተወዳድሬ ምን ያህል ውጤት ነው የማመጣው? የቋንቋ ችሎታዬ እያልን ብዙ ገደቦችን በራሳችን ላይ እንጥላለን። በእርግጥ ብዙ መሰናክሎች አሉብን ነገር ግን እነዚያን ሁሉ አልፎ ከሚፈለገው ቦታ መድረስ ይቻላል ብዬ አምናለሁ። ማንኛውም ሰው ራሱን ከዚህ አዘጋጅቶ ከሄደ፣

መማር እንዳለበት አስቦ ከሄደ ቋንቋ እንደ ምክንያት መነሳት የለበትም። በተለይ ከፍተኛ ትምህርት መማር የሚችሉ ሰዎች እዚህ ያላቸውን ጊዜ ቋንቋ ቢማሩበት፣ የመናገር እና የመጻፍ ችሎታቸውን ቢያዳብሩ እና የትምህርት ማስረጃዎችን ቢሰበስቡ እና ቢያዘጋጁ እዚያ በሚሄዱበት ጊዜ ነገሮችን ያቀልላቸዋል። ከሄዱ በኋላ መረጃ መፈለግ አለባቸው። የትኞቹ የትምህርት ዓይነቶች መልካም ናቸው? የእኔ ፍላጎት ምንድነው? የትኛው ቦታ ላይ ስኬታማ እሆናለሁ? ከዚያስ በኋላ ቀጣዩ ነገር ምን ይመስላል? የሚለውን ማየት አለባቸው። እዚያ ሲደርሱ ወደዚህም ወደዚያም ሳይሉ በቀጥታ ትምህርት ቤት ቢገቡ ይመረጣል።የትምህርት ማስረጃቸውን በቅርብ ማግኘት የ

ማይችሉ ወይም የጠፋባቸውስ? እኔ ለምሳሌ የትምህርት ማስረጃ አልነበረኝም።

የትምህርት ማስረጃ ለማምጣት ጥረት አድርጌ ነበር። ሊሳካልኝ አልቻለም። የትምህርት ማስረጃ ስሌለኝ የነበረኝ አማራጭ “እንዲህ ነበርኩ” ብዬ መናገር ነበር። አገሩ፣ ስርዓቱ ጥሩ ነው። እዚያ “ጀስቲስ ኦፊስ” ውስጥ የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎች አሉ። እነሱ ፊት እንዲህ “እንዲህ ነበርኩኝ” የሚል ቃሌን ጽፌ ይህ እውነተኛ ታሪኬ ነው ብዬ ፈረምኩኝ። እኔ በዚያ መልክ ነው ትምህርት ቤት የገባሁት። ያለ ትምህርት ማስረጃ። የትምህርት ማስረጃ ለማምጣት አንድ ሴሚስቴር አቃጥያለሁ። ግን ማምጣት አልቻልኩም። አንድ ሴሜስቴር ማባከን ቀላል ነገር አይደለም። በውጭው ዓለም አንድ ሴሚስቴር ማለት ብዙ ጊዜ ነው።

የትምህርት ማስረጃችሁን ማግኘት ባትችሉ ችግር የለም፣ ገንዘቡንም ቢሆን መጨነቅ አይገባችሁም አልክ። መማር ጀመርክ እንበል። አውስትራልያ ከምትከተለው የትምህርት ስርዓት በተለየ ሁኔታ ነው የተማርከው። በዚያ ላይ የዕድሜ ጉዳይም አለ። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ቋንቋውን አቀላጥፈው ከሚናገሩት ወጣት አውስትራልያውያን ጋርም ሆነ ከሌሎች ሀገር ዜጎች ጋር መወዳደር አይከብድም? አንድ እውነት አለ። እንደ እኔ አይነቱ በኢትዮጵ

ያ የተወለደ በሌሎች ቋንቋዎች አፉን የፈታ በእንግሊዘኛ አፉን ከፈታ ሰው ጋር በንግግር ቅላጼውም ሆነ በቋንቋ ክህሎት እኩል ሊሆን አይችልም። ይሄ ግልጽ ነው። አውስትራልያ ያለው በሙሉ ቋንቋውን በደንብ ይናገራል ማለት ግን አይደለም። እዚያ የተወለደው የሀገሩ ተወላጅ በመሆኑ ቋንቋውን በደንብ ሊናገር ይችላል። እንደኛው ግን ከተለያዩ አገሮች የመጡ አሉ። እኔ ከማውቀው ተነስቼ እንኳ ብነግርህ ጎረቤት አገሮች ከሆኑት ፊጂ፣ የሰሎሞን ደሴቶች፣ በጠቅላላው የፖለኔዥያን ደሴቶች ተብለው ከሚጠሩ ሀገሮች የሚመጡ አሉ። ከኮሪያ እና ከጃፓንም ጭምር የመጡት ይማራሉ። ክፍል ውስጥ ስትገባ እነዚህ ሁሉ አሉ። ግን በራስ መተማመነህ ይወስነዋል። ከእነሱ ጋር ቁጭ ብለህ ትማራለህ። ትፎካከራለህ። ቋንቋ ማወቅህ በራሱ የዕውቀት መመዘኛ ሆኖ

መታየት የለበትም። የምትማረውን በደንብ ጠንቅቀህ ካወቀኸው ያወቁትን ነገር መናገር ቀላል ነው። የሆነ ነገር ብትጠይቅ ስለዚያ ነገር እውቀቱ

ህርቱ ዓለም መመለስ በጣም አስቸጋሪ ነው። ብዙዎቻችን የመታለል ነገር አለብን። በገንዘብ መልኩም ካየነው ትምህርት ኢንቨስትመንት ነው። የተሻለ ክፍያ ታገኛለህ። ከመማር በኋላ በሚኖረው ህይወትህ ቢያንስ ቢያንስ ጉልበትህን ትቆጥባለህ። በደንብ ከተማርክ፣ ጊዜህን በደንብ ሰጥተህ የምትፈልገው ውጤት የምታስመዘግብ ከሆነ፤ እድሉ አለ፣ ስራው አለ። አብዛኞቹ እንደዚህ የትምህርት ዕድሎችን አይዳ

ፈሩትም። በተለይ በእድሜ የገፋ ሰው የነበረው የኋላ የትምህርት ታሪክ ጥሩ ካልነበረ እዚያ ሄዶ በትምህርት የሚያሳልፈውን ጊዜ ሲያስበው የመዘግየት ነገር ይሰማውና የእኔን ሁኔታ በምሳሌነት መውሰድ ትችላለህ። በእኔ እድሜ ትምህርት ቤት መግባት በጣም ደፋርነት ነው። መቼ ተምሮ፣ መቼ አግኝቶ፣ መቼ ሊኖር ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ለእኔ ግን ገንዘቡ አይደለም የሚቀድመው። አንድ የሆነ ነገር ባውቅ ብዬ ነው። መቼም እዚህ የሌሉ መልካምና የተሻሉ ነገሮች እዚያ አሉ። እዚያ የሌሉ ነገሮች ደግሞ እዚህ ሊኖሩ ይችላሉ። የእዚህን ልምድ ወደዚያ የዚያን ተሞክሮዎች ደግ

ስደተኞች ማወቅ የሚገባቸው

1. ስደተኞች በሁለት ዓይነት መንገድ ወደ አውስትራልያ መግባት ይችላሉ። አንደኛው ጉዳያቸውን ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር አይቶ ወደ አውስትራልያ እንዲሄዱ ከመራላቸው “ክላስ 200” የሚባል ቪዛ ያገኛሉ። መንግስት በሚያዘጋጀው ቦታ ለአንድ ወር ከተቀመጡ በኋላ ቤት እንዲፈልጉ ይደረጋል። ሁለተኛው መንገድ የግል ስፖንሰር አግኝቶ መሄድ ሲሆን “ክላስ 202” ነው። በኩል ለመሄድ መሞከር እንደ ፖሊሲያቸው ሁኔታ የሚጠብ የሚሰፋ ስለሆነ ከባድ ነው።

2. “ክላስ 200” ሆነ “ክላስ 202” የ“ሂዩማኒቴርያን ቪዛ” በመባል በጥቅሉ ይታወቃሉ። “ሂዩማኒቴርያን ቪዛ” ያገኘ ሰው ከመምረጥ መመረጥ መብት ውጭ ማንኛውም አውስትራልያዊ የሚያገኘውን ጥቅማ ጥቅም የማግኘት መብት አለው።

3. “ስኪልድ ማይግራንት” የሚባል በርካታ ኢትዮጵያውያን የማይጠቀሙበት የቪዛ ዓይነት አለ። በዚህ ቪዛ ወደ አውስትራልያ የሚገቡ ሰዎች በተለያየ ሙያ ተመረቁ ባለሙያዎች ሲሆኑ በሙያቸው ስራ እንዲሰሩ የሚፈቀድላቸው ናቸው። ስደተኞች አይደሉም። ጥቂት ኢትዮጵያውያን ይህንን ቪዛ ማግኘት ተሳክቶላቸው በአውስትራልያ ይሰራሉ።

4. ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ወደ ሶስተኛ ሀገር የመስፈር እድሉን የሚሰጠው አንድ ስደተኛ ባለበት ሀገር ለህይወቱ የሚያሰጋ የደህንነት ችግር አለበት ብሎ ካመነ ብቻ እነደሆነ ይታወቃል። ይህ በ ዩ. ኤን. ኤች.ሲ.አር በኩል የሚገኘውን ዕድል ጠባብ ያደርገዋል። አሳማኝ “ኬዝ” ያላቸው ሰዎች ሌት ተቀን መጎትጎት አለባቸው። በተለይ በ “ኮሚዩኒቲ” ደረጃ ተደራጅተው ድምጻቸውን ማሰማት ይኖርባቸዋል።

ነጥቦች 5

“ሂዩማንቴሪያን ቪዛ አግኝተህ ወደ አውስትራልያ ከሄድክ ከወለድ ነጻ የሆነ 86 ሺህ ዶላር ያህል የመማር መብት አለህ ” ፎ

ቶ- ተ

ስፋለም

ወል

ደየስ

ፎቶ

- ፎቶ

ኤቭ

ሪዌር

Page 10: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና10

ጥበብ

የግጥም ጥግ

ተይው እንተወው፤ …የዘመን ቃፊሩን ማለፍ አልቻልንናይህ ዓለም ጥበቱ አልመጠነንና፤ ተይው እንተወው፣…ውጥኑ ግብ ይሁን ጅማሬው ፍጻሜ፣ቅጽበቷ ሙሉ ዕድሜሽ ወቅቷ ዘላለሜ።

ተይው እንተወው

ደበበ ሰይፉu u u

በዕውቀት ላቀው[“ድንጋይ ይጣፍጣል” በሚል በቅርብ ከወጣው

የግጥም መድብል]

ግማሽ ሌሊት ሆነ

ሮጀር ሚላ- ካምፓላ

ልቤ ቅር እንዳለውልቤ እንደተዘጋ ልቤ ሲፈልግሽዝምታ ወርቅ ሆነዝምታ ራት ሆነ ምንም ሳናወራግማሽ ሌሊት ሆነ ።

u u u

ርሃብርሃብ ምን ይመስላል?ችግርስ? ብላችሁእንዳትጠይቁኝ ለኔ ለመልሳችሁጥጋብን ጠይቁኝ እነግራችኋለሁሲመጣ እንዳይጠፋኝ ሳጠናው ኖሬአለሁ።

u u u

ነጋዴ ደብቆት፣ ዋጋው ጣሪያ ደርሶየደሜ ስኳርም፣ ጤናዬን አቃውሶምስኪኑ ምላሴ ከላሰው ቆይቷልእስኪ አስታውሽኝ ውዴ…ስኳር ምን ምን ይላል?

እምጷ…!?

ዮሐንስ ሞላ

u u u

እኔ የአንተ ወዳጅ የምድሩ ምሶሶ፤ የአድባሩ መከታየባድማው ግርማ የፍትህ መሰረት የቀየው መከታእኔ ታዛዥ ባሪያህ የፍጡራን ንጉስ ልዑል ዘ አናብስትአጥንቷ የላላ ቀንዷ ያልጠነከረክፉ ደግ ያላየች ስጋዋ ያልገረረዱሩን ያላወቀች ፤ ጥርስ የማታስቸግር አንድ ጭቅላ አጋዘን፤አግኝቼ ካልበላሁ፤ውስጤ ላለው ጌታ መስዋ’ት ካላቀረብሁእንዴት በምድሪቱ ፍትህ ይበየናልሰላምስ ይሰፍናል?

ስማኝ አንተ ዳኛ

ግርማ ተስፋው

አንበሳው ጅቡን አሸንፎ ስላዩት አንበሳው አንበሳው አሉት፣አንበሳው ባይቀናው ኖሮ እኮ ጅቡ ጅቡ ነበር የሚሉት፣ጅቡንም ነበር አንበሳ ግቢ የሚያስገቡት።

ቲፎዞ

አባ አደራው

u u u

ጥላሁን ገሰሰ አዲስ አበባ ነው የተወለድኩት ይበል እንጂ አዲስ አበባ አለመወለዱን፣ ለምን እንደዋሸ የሚናገር መጻሕፍት በቅርቡ ታ

ትሞ ለገበያ ሊውል ነው፡፡ በቅርቡ ለሕዝብ እንደሚቀርብ የተነገረለት ይህ መጽሐፍ ከ450-500 ገጾች እንደሚኖሩት “ኢትዮፒካሊንክ” የሬድዬ ፕሮግራምን ጠቅሶ አዲስ ነገር ኦንላይን ዘግቧል። ይህ ብዙ ሚስጥር የሚገልጥ መጽሕፍ የጥላሁንን ጉዶች ዘክዝኳቸዋል ነው የተባለው፡፡ ለሕዝብ እስከዛሬም እንቆቅልሽ ሆኖ የቆየው “ሆድ ይፍጀው” በዚህ መጻሕፍ በስፋት ይተነተናል፡፡ ከጥላሁን ገሰሰ የቅርብ ቤተሰብ አንዱ ጥላሁን ገና የአንድ ዓመት ልጅ እያለ ማስታወሻ መያዝ ጀምሮ ነበር፡፡ ይህ ከቤተሰብ የተገኘ ማስታወሻ ለዚህ መጽሕፍ መነሻ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ በእጅ የተጻፈው ይኸው መረጃ በመጽሐፉ ውስጥ እንደሚካተት ተነግሯል፡፡ ከዚህ መረጃ ባሻገር እስከዛሬ ህዝብ ያላያቸው አስገራሚ የጥላሁን ፎቶዎችም ይካተታሉ ተብሏል፡፡

የጥላሁን ገሰሰ የ“ሆድ ይፍጀው” ቅኔ ሊፈታ ይሆን?

ጎሳዬ ከኤፍሬም ታምሩ ጋር የነበረውን ኮንሰርት በሐዘን ምክንያት ሰረዘ

ድምጻዊት አቢ ላቀው በፊልም ልትመጣ ነው

የዳዊቴ መኮንን አዲስ አልበም በካናዳ ሊመረቅ ነው

በየዓመቱ በአሜሪካ የሚከበረውን የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ውድድር ምክንያት በማድረግ ከኤፍሬም ታምሩ ጋር በአንድ መድረክ እንዲያቀንቅን ተጋብዞ የነበረው ጎሳዬ ተስፋዬ በሐዝን ምክንያት በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ሳይገኝ ቀረ። ጎሳዬን የሙዚቃ ዝግጅቱን እንዲሰርዝ ያስገደደው ከሁለት ዓመቱ ጀምሮ እንደ እናት ተንከባክበው ያሳደጉት አያቱ ሞት ነው። ጎሳዬ ለአያቱ ከፍተኛ ፍቅር እንደነበረው በቅርብ የሚያውቀው የ“ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮግራም አዘጋጅ ተወልደ በየነ (ተቦርነ) ይገልጻል። እንደተቦርነ አባባል ከሆነ ጎሳዬ የመጨረሻ አልበሙ በሆነው “ሳታማኻኝ ብላ” ላይ የተጫወተውን “እናትዬ” የተሰኘውን ዘፈን መታሰቢያ ያደረገው ለእኚሁ አያቱ ነው። የጎሳዬ ድንገተኛ ሀዘን አትላንታ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ እንደሰነበተ በቦታው ላይ የሚገኘው የ“ታዲያስ

አዲሱ” ሰይፉ ፋንታሁን ይናገራል። በሁኔታው የተደናገጡት የሙዚቃ ዝግጅቱ አዘጋጆች ነገርየውን ሲያስተባብሉ ቢቆዩም በስተመጨረሻ ጎሳዬ ከኤፍሬም ጋር መዝፈን እንደማይችል ለአፍቃሪዎቹ አስረድተዋል። ጎሳዬ ከኤፍሬም ጋር ዝግጀቱን ለማቅረብ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ለእሁድ ሰኔ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ነበር።

የታዋቂው ኦሮምኛ ዘፋኝ ዳዊቴ መኮንን አዲስ አልበም በካናዳ በድጋሚ ሊመረቅ ነው። “አኒ ዱፌን ጂራ” በተሰኘው ዘፈኑ ይበልጥ የሚታወቀው ዳዊቴ በቅርቡ የለቀቀው አዲሱ አልበሙ “ሶለኔ” ይሰኛል። ይህንኑ አልበም በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ በሚኒሶታ አሜሪካ በይፋ ያስመረቀ ሲሆን ሐምሌ 9 እና 10 በቶሮንቶ ካናዳ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሙዚቃ ዝግጅት በድጋሚ ያስመርቃል ተብሎ ይጠበቃል። የዳዊቴ አልበም በኦሮምኛ ሙዚቃ አድማጮች ዘንድ በከፍ

ተኛ ሁኔታ ይጠበቅ እንደነበር በኦሮሞ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩሩ ድረገጾች በተደጋጋሚ ዘግበዋል። ለአልበሙ መጠበቅ አንድ ምክንያት የነበረው አስቀድሞ የተለቀቀው ነጠላ ዜማ ነበር። “ኦሮሚያዊነቴን እወደዋለሁ” የተሰኘው እና በአማርኛና ኦሮምኛ ቅይጥ የተሰራው ዜማ ጠንከር ያሉ መልዕክቶችን ያዘለ ነበር። ዳዊቴ በዚህ ዘፈኑ “ሊነጋጋ ሲል ይጠቁራል ሰማይ” ይላል። በዚሁ ስንኝ “ንጉስ እና ዝናብ” ከላይ እንደሚወርድ ይጠቅስና “ያን ጊዜ ብሔር ከብሔር ጋር ተፋቅሮ” እንደሚኖር እና “አማረን ከጫላ መለየት ይቀራል” ሲል ይተነብያል። ይህ ነጠላ ዜማ ዳዊቴ ሚኒሶታ ከሚታተመው “ዘ ሐበሻ” ጋ

ር ባለፈው ዓመት ባደረገው ቃለ መጠይቅ ምክንያት ለደረሰበት ትችት የተሰጠ ምላሽ እንደሆነ ኦሮሞሲስ የተሰኘው ድረ ገጽ ዘግቧል። በቃለ መጠየቁ ድምጻዊው የኦነግ ደጋፊ እንደሆነ በግልጽ ተናግሯል። ስለ ኦሮሚያ መገንጠል ጉዳይ በቃለ ምልልሱ የተጠየቀው ዳዊቴ “ኦሮሚያ ከየት ነው የምትገነጠለው? መገንጠል ለሚፈልጉት ነጻነት እንሰጣለን እንጂ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ነዋሪነቷን ቴክሳስ አሜሪካ ያደረገችው ድምጻዊት አቢ ላቀው የኢትዮጵያ የገጠር ህይወት የሚያሳይ ፊልም ሰራች። ወደ መጣሁበት (ባክ ቱ ማይ ሩትስ) የተሰኘው ይሄው ፊልም በስንታየሁ አበበ ዳይሬክተርነት የተሰራ ሲሆን በቅርቡ ለዕይታ ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል። አቢ ለዚህ ፊልም ወደ 150 ሺህ ብር ገደማ እንደተከፈላት ምንጮች ከአዲስ አበባ ለ “ሐበሻዊ ቃና” ገልጸዋል።ፊልሙ አንድ የከተማ ልጅ ገጠር በሄደበት ወቅት በተ

መለከታት እንስት ሲማርክ እና እርሱን ተከትሎ የሚደርስበትን የሚያሳይ ነው። አቢ በዚህ ፊልም ላይ በገጠር ያለች ሴት ሆና ስትጫወት የከተማ ልጅነቱን ሚና ደግሞ ሳሙኤል በየነ ወስዷል። በሙያ ሳሙኤል እንደ አቢ ዘፋኝ ነው። የኤፍሬም ታምሩን ዘፈኖች አስመስሎ በመጫወት የሚታወቀው ሳሙኤል የራሱ ነጠላ ዜማዎችም አሉት።አቢ ለዚህ ፊልም ማጀቢያ የሚሆን ነጠላ ዜማ ከሶስ

ት ሳምንት በፊት ለቃለች። እንደ ፊልሙ ሁሉ “ወደ መጣሁበት” የሚል ስያሜ ያለው ነጠላ ዜማ አዲስ አበባ በሚገኙ የኤፍ. ኤም ሬድዬ ጣቢያዎች እየተደመጠ ቢሆንም “እንደተጠበቀው አይደለም” እንዳልሆነ ምንጮች ይናገራሉ። አቢ በዚህ ነጠላ ዜማ ከምትታወቅበት ዘመናዊ አዘፋፈን ወጣ ብላ “ችክችካ” ተብሎ በሚታወቀው በዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች የተቀናበረ ባህላዊ ስልት ያለው ዘፈን ሰርታለች።

ላለፉት ዘጠኝ ወራት ጁባ በሚገኘው ስታር ሆቴል ውስጥ የሙዚቃ ዝግጅቶችን ሲያቀርብ የቆየው የሙዚቃ ቡድን ባለፈው ሳምንት ሽኝት ተደረገለት። ለሙዚቃ ቡድኑ ሽኝቱን ያደረገላቸው የሆቴሉ አስተዳደር ነው። በሽኝቱ ስነስርዓት ላይ የሆቴሉ ባለቤቶች እና አጠቃላይ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን ለቡድኑ የምግብ እና መጠጥ ግብዣ ተደርጎለታል። የሙዚቃ ቡድኑ ወንድ እና ሴት ድምጻውያን እንደዚ

ሁም አምስት ሴት እና አንድ ወንድ ተወዛዋዥን ያካተተ ነው። ቡድኑ ከስታር ሆቴል ጋር የሶሰት ወር ኮንትራንት ተፈራርሞ ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ የመጣው የዛሬ ዘጠኝ ወር ግድም ነበር። በሙዚቃ ቡድኑ እንቅስቃሴ የተደሰተው የሆቴሉ አስተዳደር ሁለት ጊዜ ኮንትራቱን በማደሱ ተጨማሪ ስድስት ወር ቆይቷል። ቡድኑ ከማክሰኞ በስተቀር ሳምንቱን ሙሉ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና ሱዳን ሙዚቃዎችን ከውዝዋዜ ጋር ለተመልካች ያቀርብ ነበር። በጁባ ስታርን ጨምሮ “ጁባ ብሪጅ” እና “ኩዊን ኦፍ

ሼባ” የተሰኙት ሆቴሎች የሙዚቃ ቡድኖችን ከኢትዮጵያ በማስመጣት በዚያ ያለውን የሐበሻ ማህብረሰብ እና ደቡብ ሱዳንውያንን እያዝናኑ ይገኛሉ። አሁን ያቆሙ እንጂ “ኒውዮርክ” እና “ሄሮን” የተሰኙት ሆቴሎችም ከኢትዮጵያ ያስመጧቸው የየራሳቸው የሙዚቃ ቡድን ነበራቸው።

የጁባ ስታር ሆቴል የሙዚቃ ቡድን ሽኝት ተደረገለት

Page 11: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 11

ጥበብሰሞነኛ ፊልሞች

ሰሞነኛ ፊልሞች

ተዋንያን፦ ምኦን ጸጋዬ፣ ካሌብ ዋለልኝ፣ ሜሮን ጌትነት እና ሌሎችዳይሬክተር፦ ተገኝ ሳሙኤልየፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ 46 ደቂቃ

ዱካ

ላውንደሪ ቦይ ተዋንያን፦ ሳያት ደምሴ፣ ታሪኩ ብርሃኑ፣ ጌታቸው ስለሺ፣ መቅደስ መለሰ እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ጸጋ ዩሐንስ እና ልዑል ሰለሞን የፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ

በፋና ኤፍ ኤም በሚተላለፈው የ“ኢትዮፒካሊንክ” የሬድዮ ፕሮግራም ላይ የሚሰራው ስምኦን ጸጋዬ በዚህ ፊልም ላይም የወከለው ገጸ ባህርይ ከሙያው ጋር ይመሳሰላል። የምርመራ ጋዜጠኝነትን (ኢንቨስትጌቲቭ ጆርናሊዝም) ለመስራት የት ድረስ እንደሚኬድ ይህ ፊልም ያሳያል። ዋና ገጸ ባህርይው የመረጃ ዱካዎችን ለመከተል ራሱን ወደ ሴትነት ይቀይራል። ከዚያስ? ፊልሙ ምላሽ አለው።

ባባ እና ሊያድ በገጠር አብረው ያደጉ ናቸው። ወደከተማም ከመጡ በኋላ የማይነጣጠሉ ጓደኛሞች ሆነዋል። አንድ ቤት እየኖሩ በአንድ ላውንድሪ ቤት አብረው እየሰሩ እንድ እህት እና ወንድም ይኖራሉ። ጓደኛ ለማፍራት ወደ ምሽት ክለብ ሲሄዱ እንኳ አብረው ነው። ሳያት ደምሴ የምትጫወታት ሊያድ ባባን እንዴት ሴቶችን አንደሚያጠምድ የምትመክር ናት። ጨዋታ ወዳድ የሆነው ባባ ሴቶችን የሚያሳድድ ነው። ሊያድ ከባባ ጋር ያደገችበትን መንደር እንደገና ስትጎበኝ ግን በሁለቱ መካከል ያለው ትስስር ከጓደኝነትም በላይ እንደሆነ ትረዳለች። ከዚህ በኋላ በሁለቱም መካከል እያደገ የሚመጣው እንግዳ ስሜት የፊልሙ ማጠንጠኛ ነው።

ትዝታህ

ይህ ፊልም በ19 60ዎቹ የነበረውን ሁኔታ በምልሰት የሚተርክ ነው። በኬንያ የከፍተኛ ተቋም ትምህርቱን ያጠናቀቀው ወጣቱ መብራቱ ከብቶችን የሚያጠቃውን የደስታ በሽታ ለማጥፋት ወደ ሲዳሞ ይወርዳል። በሲዳሞ ጉዞው ስራውን ብቻ ሳይሆን የወደፊት ህይወቱን ሙሉ ለሙሉ የሚለውጥ ክስተት ያጋጥመዋል። መብራቱ በሲዳሞ ቆይታው አብራው ከምትሰራው ጽጌረዳ ጋር ፍቅር ይጀምራል። በስራው ላይ ባሳየው ትጋትም ሹመት ያገኛል። በመብራቱ ስኬት የተበሳጩት ሁለት የስራ ባልደረቦቹ ሊበቀሉት ይወጥናሉ። ውጥናቸው የታሰበለትን ኢላማ ቢስትም መብራቱ ልጅ ወልዶ እና ጎልማሳ ለመርሳት ያልቻለውን ሀዘን ያሸክመዋል።

ተዋንያን፦ ግሩም ኤርሚያስ፣ አንተነህ አስረስ፣ ሙሀመድ ሚፍታህ፣ ሜላት አሰፋ እና ሌሎችዳይሬክተር፦ ሀብታሙ ህብረወርቅ የፊልሙ ዘውግ፦ ድራማ የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ35 ደቂቃ

በዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉ

በ+256-778-693669ይደውሉልን

ጣዕመ ዳግም ወደካምፓላ መጣ

የኢትዮጵያ ድምጻውያን አትላንታ ላይ ከትመዋል

ለ2010 አዲስ ዓመት ወደ ኡጋንዳ በመምጣት የሙዚቃ ዝግጅቱን ያቀረበው ዝነኛው ኤርትራዊ ድምጻዊ ጣዕመ ወልደሚካኤል ወደ ካምፓላ ተመልሷል። የሙዚቃ ዝግጅቱን እሁድ ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም (ጁላይ 10) ቡጋንዳ ሮድ በሚገኘው ኦፕን ሀውስ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ጣዕመ ይህንን የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ከሚኖርበት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነው የሚመጣው። በዝግጅቱ ላይም የዛሬ ዓመት ገደማ ካወጣው አዲሱ አልበም ዘፈኖችን ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል። የጣዕመ የመጨረሻ አልበም “ይኩንለኪ” የሚሰኝ ሲሆን በኤርትራ ሙዚቃ ሀያስያን ዘንድ “ለረጅም

ጊዜ በሙዚቃ ውስጥ የመቆየቱን ኃይል” ያስመሰከረበት ነው ተብሎለታል። በዚህ አልበም ውስጥ 12 ዘፈኖች የተካተቱ ሲሆን በ“ጓይላ” እና ዘመናዊ ሙዚቃ ስልቶች የተሰሩ ናቸው። ጣዕመ የባህላዊ ትግርኛ ስልት በሆነው “ጓይላ” የተጫወታቸውን ዘፈኖች በኤርትራ እንዲዘጋጁ ያደረገ ሲሆን ዘመናዊ የ “ፖፕ” ስልት የተከተሉትን ዘፈኖች ደግሞ በአሜሪካ እንዲቀናበሩ አድርጓል። ይህ የመጨረሻ አልበሙ በአብዛኛው ያካተተው የፍቅር ዘፈኖችን ነው። ኤርትራውያን ለአመታት ጋብቻዎቻቸውን ያደምቁበት የነበረው “ሩሁስ ጋማ” የተሰኘው የሰርግ ዘፈንም የአልበሙ አካል ነው። ጣዕመ ለዚህ ዘፈን “አዲስ ህይወት” ነው የሰጠው ተብሎ ተወድሷል። ይህንን አልበም የገመገመው ቢኒያም ተክሌ የተባለ የሙዚቃ ሀያሲ “ጣዕመ እንደገና ተሳክቶለታል” ብ

ሎታል። “አልበሙ ከውስጡ ለብቻ ተነጥሎ የሚወጣ ዘፈን አላቀረበም። ነገር ግን አድማጭን የሚያስደስቱ ዘፈኖች በውስጡ የሞሉበት ነው” ብሎ ነበር። ስለ ጣዕመ ደግሞ ይህን ተናግሮ ነበር። “አንድ ድምጻዊ የተዋጣላት ድምጽ ቢኖረውም እንዴት ወደ አድማጭ ዘንድ እንደሚያደርሰው ካላወቀ ተፈጥሮ የሰጠችው ጸጋ ጥቅም የለሽ ነው የሚሆነው። በተቃራኒው አንድ ድምጻዊ የማይረባ ድምጽ ይዞ ነገር ግን እንዴት ማዋሃድ እንዳለበት ካወቀ ኮከብ ሊሆን ይችላል። ጣዕመ የተዋጣለት ድምጽ የለውም ግን አይረቤም አይደለም። በጊዜ ሂደትም እየተሻሻለ የመጣ ዘፋኝ ነው። ድምጹን ለማሻሻል ጠንክሮ የሚሰራ ነው። ልክ እንደ ቆየ ወይን ጠጅ ዕድሜው በጨመረ ቁጥር ምርጥ እየሆነ የመጣ ነው።”

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በየዓመቱ በሚካሄደው የእግር ኳስ እና ባህል ዝግጅት ላይ ለመገኘት በርካታ ድምጻውያን አትላንታ ላይ ከትመዋል። ከሰኔ 26 ቀን ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ዝግጅቶቻችን ለማቅረብ ከተገኙት ድምጻውያን መካከል ብርሃኑ ተዘራ፣ ታደለ ገመቹ፣ ታደለ ሮባ፣ ብዙአየሁ ደምሴ፣ ሳያት ደምሴ፣ ይርዳው ጤናው፣ እዮብ መኮንን፣ ቀመር ዩሱፍ፣ አበባ ደሳለኝ፣ አስቴር አወቀ እና ሄለን በርሄ ይገኙበታል። ነዋሪነታቸውን አሜሪካ ያደረጉት እንደ ኤፍሬም ታምሩ፣ ሳምቮድ እና ናቲ ሐይሌም ከቦታው አልቀሩም። የዚህን ዓመት የእግር ኳስ እና የባህል ዝግጅት ላይ ለመታ

ደም ወደ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ አትላንታ ይተማሉ ተብሎ ቅድሚያ ግምት ተሰጥቶ ነበር። ይህንን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ኢትዮጵያዊ ለማዝናናት የሙዚቃ አዘጋጅ ፕሮሞተሮች ቁጥሩ ከፍ ያለ ገንዘብ ከፍለው ዘፋኞችን ከኢትዮጵያ በየዓመቱ ያስመጣሉ። በአሜሪካ የሚኖሩትንም ጠርተው ያሰራሉ። በዓመታዊው ዝግጅት ላይ ሙዚቃቸውን እንዲያቀርቡ የሚጋበዙ ድምጻውያን ታዲያ ወቅታዊ ዝናቸው ከፍ ያለ አሊያም የምንግዜም ተወዳጅ የሆኑ ዘፋኞች ናቸው። በዚህ ዓመት ግን ነገሮች የተለዋወጡ ይመስላል። የ “ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነውና በቦታው የሚገኘው ሰይፉ ፋንታሁን ለባልደረቦቹ እንደተናገረው ከሆነ ለስራ ያልተጋበዙ ድምጻውያን ሳይቀር በአትላንታ ስራ ፍለጋ ታይተዋል። “ዘፋኝ ክብር ነበረው። ዘፋኞች ተጠይቀው ነበር የሙዚቃ

ኮንሰርት የሚሰሩት። አሁን ግን አንዳንድ ዘፋኞች ፕሮሞተሮች ጋር እየደወሉ ልሰራ እሰከማለት ድረስ ደርሰዋል” ብሏል ሰይፉ በሬድዬ ፕሮግራሙ ላይ በስልክ በሰጠው ቃለ ምልልስ። እንደ እርሱ አባባል ከሆነ ሌላውን ዜጋ የሸነቆጠው የኑሮ ውድነት የድምጻውያንንም በር አንኳኩቷል። “የበፊቱ የኮንሰርት ክብር እና ግርማ ሞገስ እየቀረ መጥቷል” ሲልም የተመለከተውን ተናግሯል። ድምጻውያን ከኮንሰርት ይልቅ ፈጠራ ላይ ቢያተኩሩ ይሻል ነበር የሚለው ሰይፉ የኑሮ ችግሩንም ለመፍታት ማድረግ ያለባቸውን ጠቁሟል። “ቁጭ ብለው በር ዘግተው ኮፒራይቱ እንዲስተካከል ስራ ቢሰራ እነሱም እዚህ ደረጃ ላይ የሚደርሱ አይመስለኝም” ይላል።

Page 12: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና12

ጥበብ

ኢትዮጵያዊቷ ፋሽን ዲዛይነር ለኒውዮርክ

ፓሪስ፣ ለንደን፣ ሚላን እና ኒውዮርክ። እዚህ አራት የአለማችን ድንቅ ከተሞ

ች የየራሳቸው መለያ ቢኖራቸውም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ግን አለ። ፋሽን። አራቱም ከተሞች በፋሽን ከተማነታቸው ይታወቃሉ። ፓሪስ ከጥበብ እና ፋሽን ጋር በነበራት የረጅም ጊዜ የታሪክ ትስስር እና አሁንም ድረስ መቀመጫቸውን በእርሷ ባደረጉ የፋሽን ቤቶች ትታወቃለች። ለንደን የክብር እና ማራኪ ፋሽን ከተማ ነች ይሏታል። ከከተማይቱ የሚወጡት ፋሽኖች ከገበያ ስኬት እና በብዙ ሰዎች እንዲለበሱ ከመሰራት ይልቅ ክብር እና የሚያተኩሩ ናቸው። ሚላን እና ኒውዮርክ ግን ከለንደን በተ

ቃራኒ ጠርዝ የተቀመጡ ናቸው። የሁለቱም ከተማዎች ፋሽኖች ገበያ ላይ ባላቸው ውጤታማነትም ሆነ በብዙሃን መገናኛ በሚያገኙት ሽፋን የገነኑ ናቸው። የሚላንም ሆነ የኒውዮርክ ፋሽኖች በውበታቸው እና ማራኪነታቸው የሚታሙ አይደሉም። አሰራራቸውም ጥንቅቅ ያለ ነው። እንዲያም ሆኖ ወዲያውኑ ተገዝተው የሚለበሱ አይነት ልብሶች የሞሉባችው ናቸው። ከነዚህን አራት የፋሽን ከተሞች ቆንጮ

ማን እንደሆነ ለመለየት በየጊዜው ውድድር ይደረጋል። እንደ “ግሎባል ላንጉዌጅ ሞኒተር” ዘገባ ኒውዮርክ እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ አመታት የበላይነት ክብሩን ተጎናጽፋለች። እ.ኤ.አ በ2009 የኢጣሊያኗ ሚላን ክብሯን ብትነጥቃትም ባለፈው ዓመት ግን መልሳ አምጥታዋለች። ኒውዮርክ በፋሽኑ ዓለም ያላትን ይህን ደረጃ የሚያውቁ የዘወትር ህልማቸው በከተማይቱ በሚካሄዱ ዝግጅቶች በአንዱ መካፈል ነው። የ30 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ዲዛይነር ፍቅርተ አዲስ ግን ወደ ፋሽኑ ዓለም ጠቅላላ በገባች በሁለተኛ ዓመቷ ይህንን እድል አግኝታለች።

የሞሪሸሷ “ንግስት” ፍቅርተ ከሐምሌ ሰባት እስከ ዘጠኝ በ

ኒውዮርክ በሚካሄደው “አፍሪካን ፋሽን ዊክ” እንዲሳተፉ ከተመረጡ 21 ዲዛየነ

ሮች አንዷ ሆናለች። በየዓመቱ በሚካሄደው፣ እውቅና ባለው እና ሰፊ መገናኛ ብዙሃን ሽፋን በሚያገኘው በዚህ ዝግጅት ላይ እንድትሳተፍ የተመረጠችው ግን አለ ምክንያት አልነበረም። ባለፈው መጋቢት ላይ በአፍረካዊቷ ሞሪሸስ ላይ ተካሄዶ በነበረው “ኦሪጅን አፍሪካ- ፋይበር ቱ ፋሽን” በተሰኘው ዓመታዊ ውድድር ካሸነፈች በኋላ ነበር በኒውዮርኩ የፋሽን ሳምንት አዘጋጆች አይን ውስጥ የገባችው። ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር በሞሪሽሱ ው

ድድር ለአሸናፊነት የበቃችው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ከተውጣጡ 12 ዲዛየነሮች ጋር ተወዳድራ ነበር። የውድድሩ ዓላማ አፍሪካን በአልባሳት እና ዲዛይን ዘርፍ አዳዲስ ሀሳቦች የሚፈልቁባት አህጉር ማድረግ ነው። በውድድሩ ላይ አሸናፊው የሚመረጠው የሚቀርቡት ዲዛይኖች በተለያዩ መስፈርቶች ከተመዘኑ በኋላ ነው። አልባሳቱ ሊሸጡ የሚችሉ ዓይነት መሆናቸው እና በየጊዜው መለበስ መቻላቸው በመመዘኛ መስፈርትነት ከተካተቱት መካከል ነው። የዲዛየነሩ የፈጠራ ብቃት፣ ቴክኒካዊ ችሎታው እና የሀገሩን ጥሬ ዕቃ የሚጠቀም መሆኑም ከግምት ውስጥ ይገባል። የሀገር ባህል አልባሳትን በዘመናዊ መን

ገድ ዲዛይን ማድረግ የሚያስደስታት ፍቅርተ በአወዳዳሪዎቹ የሚጠየቁትን መስፈርቶች ሳይጠየቅ ያሟላች ነበር። ፍቅርተ ለዚህ ወድድር ስምንት ያህል ስራዎቿን ነበር ይዛ የቀረበችው። ሞሪሸስ በሚገኙ ሞዴሎች አማካኝነት ለዕይታ የቀረቡት ቀሚሶቿ በተለይ ባህላዊን የሐበሻ ቀሚስ ከዘመናዊ ጋር በሚገባ የቀየጡ ነበሩ። ለወንዶች ያዘጋጀቻቸው አልባሳትም ቢሆን ኢትዮጵያ ቀለም ያላቸው ነበሩ። “እኛ ጋር ሁሌም ቢሆን የትኛው ነው ባ

ህላዊ? ወይ የትኛው ነው ዘመናዊ? የሚለው ክርክር አለ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የፋሽን ስታይል አለ። የእኛ የሆኑት አልባሳት ደግሞ አሉ። እኔ ያደረግኩት ለራሳችን ባህላዊ ልብስ መስሪያ የምንጠቀምባቸውን ጥሬ ዕቃዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ‘ስታይል’ መስጠት ነው” ስትል ለሪፖርተር ጋ

ዜጣ ተናግራለች። በሌላው ዓለም ያልተለመዱ ግን ዓ

ይን የሚገቡ ስራዎችን ይዛ በውድድሩ ላይ ብትገኝም አሸንፋለሁ የሚል ቅድሚያ ግምት እንዳልነበራት ግን ትናገራለች። “እኔ እንዲህ አልጠብቅም ነበር። “አሸንፋለሁ ብዬ አላስብኩም” ስትል ለታዲያስ አዲስ የሬድዬ ፕሮግራም ተናግራለች። በውድድሩ በርካታ ነገር መማሯንም ትናገራለች። “ከባድ እና አስደሳች ውድድር ነበር። ሁሉም አገራት የየራሳቸውን የሚስብ ባህል እና ስታይል ይዘው ነበር የመጡት። ለእኔ እንኳ አንዱን ከአንዱ ለመምረጥ ከባድ ነበር። ምክንያቱም ሁሉም ቆንጆዎች ነበሩ” ስትል ለውድድሯ የነበራትን ስሜት ለ “ኒውዮርክ ፋሽን ዊክ” ድረ ገጽ አካፍላለች።

የእናቴ ስፌት መኪና ፍቅርተ ሞሪሸስ ከመጓዟ፣ ለኒውዩ

ርክም ለመታጨት ከመብቃቷ ሁለት ዓመት በፊት ፋሽን የትርፍ ጊዜ ስራዋ ነበር። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው እና እስከ ማስተርስ የተማረችው ፍቅርተ በተማረችበት ሙያ የተለያዩ ቦታዎች ሰርታለች። የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም ግን ወደ ፋሽኑ ስራ ጠቅላላ ለመግባት በመወሰን የራሷን ሱቅ ከፍታለች። አሁን “የፍቅር” በሚል ስያሜ የአልባሳት ዲዛይኖቿን አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ በሚገኘው ሱቋ ለገበያ ታቀርባለች። ወደ ፋሽኑ ስራ ሙሉ ለሙሉ ከመ

ግባቷ በፊት ለዲዛይን ስራ መነሻ የሚሆኑ ነገሮችን ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለች ጀምሮ ታደርግ ነበር። የሚገዛላትን ልብስ ወደ እናቷ የስፌት መኪና በመውሰድ በሚጥማት እና እርሷ ጥሩ ነው ብላ በምታስበው “ስታይል” መልክ ታስተካክላች። “ሁለተኛ ደረጃ እያለሁ ሀሳቦቼን በስዕል አስፍራለሁ። ልብስ ተገዝቶልኝ ዲዛይኑን እለወጣለዋሁ። ሙከራዎች አድርግ ነበር” ስትል ለ“ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮግራም ተናግራለች። እንዲህ በአልባሷቷ ላይ ሙከራ ስ

ታደርግ ትቆይ እንጂ የመጀመሪያ ሙሉ የዲዛይን ስራ የሰራችው ግን በራሷ ልብስ ሳይሆን በእናቷ ቀሚስ ላይ ነበር። “በጣም የምታምር የእናቴ ቀሚስ ነበረች። ሰርቼው ለብሼ ወጣሁ” ትላለች ወደ ኋላ መለስ ብላ ስታስታውስ። ያቺ ቀሚስ አሁንም ድረስ በክብር ተቀምጣለች። በእናቷ ቀሚስ የጀመረችው የዲዛይን ስራ አሁን ባህር ማዶ ተሻግሯል። ኢትዮጵያንም በዓለም አቀፉ የኒውዮርክ ፋሽን ሳምንት ለመወከል የመጀመሪያው ሆናለች።

“የፍቅር” ኒውዮርክፍቅርተ በ“ኒውዮርክ ፋሽን ዊክ” 15 አ

ልባሳቶቿን ይዛ ትቀርባለች። አልባሳቶቹ ጥንቃቄ በሚያስፈልጋቸው የባህላዊ አልባሳት ጥሬ ዕቃዎች የተሰሩ ስለሆኑ ጥቂት ችግር ቢያጋጥማቸው የሚበላሹ ዓይነቶች ናቸው። የዚህ ዝግጅት ኦፌሲሊያዊ አጋር ከሆኑት አንዱ የሆነው “ዲ ኤች ኤል” ታዲያ ይህንን ችግር ለመፍታት መላ ይዞ መጣ። አንድን ልብስ ሳይተጣጠፍ በቁመናው ማጓጓዝ የሚያስችል እና ልዩ ትዕዛዝ የሚመጣ “ሀርበር ቦክስ” አዘጋጃላት። ለዚህም የፍቅርተም ኤፌሲሊያዊ የጉዞ አጋር ለመሆን መስማማቱን ለመግለጽ ሰኔ 23 ቀን በሸራተን አዲስ ሆቴል ግብዣ አሰድቶ ነበር። ፍቅርተ ለቅድመ ዝግጅት በሚል ሁለት አልባሳትን በዚህ ድርጅት በኩል አስቀድማ ልካ ነበር። አሁን ልብሶቹም ተዘጋጅተዋል። የቀረ

ነገር ቢኖር ሐምሌ 8 ቀን ከ17 ሌሎች ዲዛይነሮች ጋር ስራዎቿን ማቅረብ ነው። በዚህ ዝግጅት ከኡጋንዳ፣ ካሜሮን፣ ጋና፣ ጃማይካ፣ ናይጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ሴኔጋል፣ ሴራሊዮን፣ ደቡብ አፍሪካ እና ታንዛኒያ እንዲሳተፉ የተመረጡ እና የተጋበዙ ዲዛይነሮች ይገኙበታል። አልባሳቱን ለብሰው ሰበር ሰካ እንዲሉ ደግሞ ከጥቁር እስከ ሂስፓኒክ፣ ከነጭ እስከ እስያዊ ያሉ ሞዴሎች ተዘጋጅተዋል። ከኒውዮርኩ ከንቲባ ብሉምበርግ በየዓ

መቱ እንዲካሄድ ኦፊሲሊያዊ እውቅና የተሰጠው ይሄው ዝግጅት ባለፈው ዓመት ብቻ በፋሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ አሉ የተባሉ ወደ 1500 ሰዎችን በአንድ ቦታ ማሰባሰብ ችሎ ነበር።

“ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የፋሽን ስታይል አለ። የእኛ የሆኑት አልባሳት ደግሞ አሉ። እኔ ያደረግኩት ለራሳችን ባህላዊ ልብስ መስሪያ የምንጠቀምባቸውን ጥሬ ዕቃዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ‘ስታይል’ መስጠት ነው” ፎቶዎች- የፍቅርተ ፌስ ቡክ ገጽ፣ “አፍሪካን ፋሽን ዊክ”፣ ማይቤኑካፌ ድረ ገጽ ፣ ዩ ኤስ አይድ

ፍቅርተ ለሞሪሸሱ ወድድር ስምንት ያህል ስራዎቿን ይዛ ነበር

የቀረበችው

ፍቅርተ በሞሪሽሱ ውድድር ለአሸናፊነት የበቃችው ከ12 ዲዛየነሮች ጋር ተወዳድራ ነበር

Page 13: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 13

ጥበብ

የ“3ቱ ወፎች” ኮከብ በካምፓላ

ብዙዎች የሚያውቋት “ሶስቱ ወፎች” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው። ይህንን ድራማ ከመጫወቷ በፊት ግን “የልደት ጧፍ” በተሰኘ

ተከታታይ ድራማ መሪ ተዋናይ ሆና በሬድዬ አድማጮች ዘንድ አድናቆትን አትርፋለች። በትወና መነሻዋም ቢሆን

በወቅቱ አነጋጋሪ በሆኑ ትያትሮች ላይ ዋና ገጸባህሪ ወክላ በመጫወት የጥበብ አፍቃሪያን ልብ የገባች ነች። ይህቺ ተዋናይት ላምሮት ገብረሰንበት ትባላለች። በቅርቡ

በምትሰናበታት ካምፓላ ላይ ለሁለት ዓመት ግድም ቆይታለች። የ“ሐበሻዊ ቃናው” ተስፋለም ወልደየስ

ስለስራዎቿ እና የትወና ህይወቷ አነጋግሯት ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ሶስት ሴት ጓደኛሞች ናቸው። አንዷ የለየላት “አራዳ” የምትባል አይነት ነች። ሁለተኛዋ አራዳዋ የምታደ

ርጋችው ነገሮች ሁሉ አጋር ነች። ሶስተኛዋ ግን ሁለቱ በሚያደርጉት ሁሉ ብታካፈልም የሚሰሩት “ጥሩ እንዳይደለ” እንደሆነ ታስባለች። ሶስቱ ወፎች ማለት እንግዲህ እነዚህ ናቸው። እንዲህ እንደዛሬው በሀገሪቱ ሌላ ነገር

የሌለ እስኪመስል ድረስ አንድ የቴሌቪዥን ድራማ የወራት መነጋገሪያ ከመሆኑ በፊት ነበር “ሶስቱ ወፎች” የተሰራው። የቴሌቪዥን ድራማ አሰራርን ቀይረውታል የተባለላቸው “ገመና” እና “ሰው ለሰው” ከመምጣታቸውም በፊት ነበር ለዕይታ የበቃው። ሆኖም ዘወትር እሁድ ይቀርብ በነበረው የ“120” የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ መታየት ሲጀመር ግን የወቅቱ ተወዳጅ ድራማ ሆኖ ነበር። ከተሰራ ከዓመታቶች በኋላ በተለያየ ጊዜ በታየበት ወቅትም በድራማ ተከታታዮች ዘንድ ተወዳጅነቱ አልደበዘዘም። ድራማው ተወዳጅነት ማትረፉን ተከት

ሎ የተወደደባቸውን ምክንያቶች በወቅቱ በነበሩ ብዙሃን መገናኛዎች የዘረዘሩ ነበሩ። የመጀመሪያው ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው መንግስታዊው እና ብቸኛው የቴሌቪዥን ጣቢያ ለድራማው የመደበው ገንዘብ ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለድራማ መስሪያ ይመድብ ከነበረው በብዙ እጥፍ በላቀ ለዚህ ድራማ ገንዘብ እንዳፈሰሰ ተዘግቧል። በድራማዎች ላይ ባልተመለደ መልኩም በ“ሶስቱ ወፎች” የእያንዳንዱ ክፍል ማለቂያ ላይ የአካውንታንት ስም ከተዋንያን እና አዘጋጆች ዝርዝር ቀጥሎ ይነበብ ነበር።ለድራማው ተወዳጅነት በሁለተኛ ምክ

ንያት የሚጠቀሰው ድራማው ይዞት የተነሳው ጭብጥ በፊት ከነበሩት ለየት ያለ መሆኑ እና ቀረጻው በተለያዩ ቦታዎች ቀን እና ማታ ሳይመርጥ የተከናወነ መሆኑ ነበር። ሶስተኛውና ብዙዎችን የሚያስማማው ምክንያት ግን የተዋናዮቹ የትወና ብቃት ነበር። የድራማው መሪ ተዋንያኖች ሶስት እንስቶች ቢሆንም ቹቹ የተሰኘችውን የ“አራዳ ገጸ ባህርይ” ወክላ የተጫወተችው ላምሮት ገብረሰንበት ይበልጥ እውቅና አግኝታበታለች።

ቹቹ“እንዲህ ይሆናል ብዬ አይደለም የሰራ

ሁት” ትላለች ላምሮት ከድራማው ቀረጻ በፊት ስለነበራት ስሜት ስታስታውስ። ከዚህ ቀደም የቴሌቪዥን ድራማ ሰርታ የማታውቀው ላምሮት በልምምድ ወቅት ለ“ሶስቱ ወፎች” የነበራት ስሜት እምብዛም ነበር። “ትያትር (ድራማ) ልምምድ ላይ እንደምታስበው አይደለም። ስትዋሃድ ነው ስሜት የሚመጣልህ” ትላለች። ስድስት ወር በፈጀው ልምምድ ያልታየው መዋሃድ በአንድ ወሩ የድራማ ቀረጻ ወቅት መጣ። ቀረጻው ሲጀመር ላምሮት ሌላ ሰው ሆ

ነች። የተሰጠቻትን ደፋር፣ አታላይ እና አጭበርባሪ ገጸ ባህርይ በአሳማኝ ሁኔታ ተጫወተቻት። ገጸ ባህሪዋን በብዙዎች ልቦና ውስጥ እንድትቀር አደረገች። እስካሁንም ድረስ ሰዎች ሲያገኟት በገጸ ባህሪይዋ ስም ቹቹ እያሉ መጥራታቸው ምስክር ይሆናል። ላምሮትን ቹቹን በቃለ ተውኔቱ እንደተጻፈችው አድርጋ ለማምጣት ብዙ ደክማለች። የድራማው ዳይሬክተር የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥኑ ተስፋዬ ስንቄም አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው። “ቤትሽ ገብተሽ በመስታወት ራስሽን እያየሽ ስሪው ይለኝ ነበር” ትላለች ተስፋዬ እንዴት ገጸ ባህሪዋን በትክክል እንድታመጣ እንደረዳት ስትናገር። ላምሮት “ሶስቱ ወፎች” ተወዳጅ እንደ

ሚሆን ያወቅሁት “ቀረጻ ላይ እያለን” ነበር ትላለች። “ቀረጻ ላይ እያለን ፕሮዳክሽኑ የተሳካ እንደሆነ ገባኝ። እነርሱም ሲቀረጽ ደስተኞች ነበሩ” ትላለች ከቀረጻው ጀርባ የነበሩትን ባለሙያዎች ስታስታውስ። ድራማው የተሰራው በኢትዮጵያ ቴ

ሌቪዥን አማካኝነት እንደመሆኑ ባለሙያዎቹ በሙሉ የመጡትም ከዚያው ነበር። ብዙዎቹ ታዲያ ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያው ከመምጣታቸው በፊት ባለ 35 ሚሊ ሜትር ጭምር ፊልሞችን ይሰራ በነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ፊልም ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ነበሩ። ይህም ድራማው የፊልም ዓይነት ገጽታ እንዲላበስ አድርጎታል። “አሁን እንደምናያቸው ፊልሞች እንደ ፊልም ተቀርጾ ገበያ ላይ ቢውል ኖሮ በወቅቱ ትልቅ ገቢ ይኖረው ነበር” ስትል ላምሮትም ምስክርነቷን ትሰጣለች።

የአጋጣሚዎች ብዛትላምሮት “ከብዙ ስራዎቼ የገነነ ስለነበር

እስካሁንም ይዞኝ ቆይቷል” የምትልለትን “ሶስቱ ወፎችን” እንድትሰራ የተመረጠችው በአጋጣሚ ነበር። ያን ጊዜ ሀገር በቀል በሆነው “ፕሮ ፕራይድ” በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ መደበኛ ሰራተኛ ነበረች። በዚሁ ድርጅት ውስጥ ባለው “የባህል ማዕከል” አብራት ድራማዎችን የምትሰራው ሶፊያ መሐመድ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሰዎች ጋር ትግባባ ነበርና ዳይሬክተር ተስፋዬ ሊሰራ ላሰበው ድራማ ዋና ተዋናይ ሲፈልግ ትሰማለች። ወደ ሶፊያም ይመጣና “የምታውቂው ሰው ካለ ይዘሽ ነይ”ይላታል። ሶፊያ ላምሮትን ይዛ ወደ ኢቲቪ ትሄዳለች። ተስፋዬ ይመለከታት እና ለስራው ትመረጣለች። ይህ በአጋጣሚ ተመርጦ ዋና ተዋናይ የመሆን ነገር በላምሮት ላይ ተደጋግሞ ተከስቷል። በትያትር መድረክም ሆነ በሬድዬ ያሳወቋት ስራዎችን የሰራችው እንዲሁ በአጋጣሚ ነው። “የልደት ጧፍ” የተሰኘውን ተከታታይ

የሬድዬ ድራማ እንድትሰራ የሆነው በጓደኞቿ ጠቋሚነት ነበር። የድራማው ደራሲ የ“ቀን ቅኝት” የተሰኘውን ረጅም የሬድዬ ድራማ ከጻፉት ሶስት ደራሲያን መካከል አንዱ የሆነው መስፍን ጌታቸው ነው። ሴተኛ አዳሪ የሆነችውን ዋና ገጸ ባ

መሪያ ወደ መድረክ የመጣችበት ነበር። ትያትሩን እንድትሰራ የተመረጠችው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባህል ማዕከል “ልምምድ” ላድርግ ብላ በገባችበት ወቅት ነበር። እናቷ ዩኒቨርስቲ ይሰሩ ነበርና በባህል ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ጓደኛቸውን ጠይቃ በምርቃት ወቅት የሚዘመረውን “እንኳን ደስ ያላችሁ” የሚለውን ዘፈን መለማመድ ተጀምራለች። ይሄኔ ጸሀፌ ተውኔት እና ገጣሚ አያልነህ ሙላት የባህል ማዕከሉ ዳይሬክተር ሆነው ተሾመው ይመጣሉ። አቶ አያልነህ እጃቸው ላይ ያለቀ ትያት

ር ነበር። “ድሃ አደግ”። በባህል ማዕከሉ ለሚሰሩት “ልጅ የሆነች፣ የ17 ዓመት ካራክተር የምትሸፍን እፈልጋለሁ” ይሏቸዋል። ከላምሮት ጋር አብረው መዝሙር የሚያጠኑት እርሷን ይጠቁማሉ። የወቅቱ “ትኩሳት” የነበረውን የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጉዳይ ለሚዳስሰው ትያትር ዋና ተዋናይ ሆና ትመረጣለች። “ያኔ ትያትር ሰርቼ የማላወቅ “ሀ”ን ከ “ለ” የማላገናኝ ነበርኩ።”ትያትሩ መታየት እንደጀመረ አቶ አያ

ልነህ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ይደረጋል። ጸሀፌ ተውኔቱ ከዩኒቨርስቲው ቢወጡም “ድሃ አደግ”ን በግላቸው መስራት ቀጠሉ። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ በባህል ማዕከል ይሰሩ የነበሩትን ወጣት ተዋንያን ሰብስቦ ቀንዲል ቤተ ተውኔትን አቋቋሙ። በዚሁ ቤተ ተውኔት ስር ሆና ውርስ ትርጉም በሆነው “ጥበበኛዋ ጋለሞታ” ላይ እና “ከድጃ” ላይ ተጫውታለች። “ፕሮ ፕራይድ” እየሰራች ያጠናችው የአቶ አያልነህ ሌላ ፖለቲካ ቀመስ ትያትርም ነበር። “ሾተላይ” ይሰኛል። “የአቶ አያልነህ ትያትሮች ፖለቲካ አያጡም። ዳሰስ እያደረገ ነው የሚያልፈው” ትላለች። ላምሮት “ሾተላይ” ላይ አልተወነችም። ዘነበች ታደሰ (ጭራ ቀረሽ) እንድትሰራው ሲደረግ “ላለመሻማት” በሚል ተወችው።

ከዚህ በኋላ ከመድረክ ትያትሮች ራቀች። ሆኖም ከጥበቡ አለም አልወጣችም። ለሰባት ዓመታት ያህል በ“ፕሮፕራይድ” የባህል ማዕከል በሚዘጋጁ ድራማዎች ላይ ስትሰራ ቆይታለች። “ብዙ ስፖንሰሮች ስለነበሩን በየክፍላተ ሀገሩ ሁሉ እየሄድን ህብረተሰቡን በድራማ እናስተማር ነበር” ትላለች። “ፕሮ ፕራይድ” በኤፍ ኤም ሬድዬ ያስተላልፈው በነበረው “ይበቃል” በተሰኘ ፕሮግራም ላይም አጫጭር የሬድዬ ድራማዎች ትሰራ ነበር።

“ህይወት ለየቅል ነው” “ፕሮ ፕራይድ” እየሰራች በጎን ትምህር

ቷንም ትማር ነበር። ማርኬቲንግ ለመማር በገባችበት ዩኒቲ ኮሌጅ ሶስት ዓመት ከተማረች በኋላ ወደ እንግሊዝ የምትሄድበት ዕድል ስላገኘች አቋረጠችው። ለንደን ከሚገኙ ቤተሰቦቿ ጋር ለሶስት ዓመት ያህል ብትቆይም እንግሊዝ ብዙም አልተመቻትም። ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች። ባለቤቷ ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ ለስራ ጉዳይ ሲመጣ ሸገር እንደገና ደህና ሰንብች አለች። የልጅ እናት ለመሆን ቀናት እየቆጠረች የምትገኘው ላምሮት ወንድ ይሁን ሴት ገና አላወቀችም። “እሱ ያመጣውን…” ባይ ነች።ወደ ካምፓላ የመጣች ሰሞን ወደ ትም

ህርቱ አለም መግባት ፈልጋ የነበረ ቢሆንም በባለቤቷ የስራ ጸባይ ምክንያት ተረጋግታ ተቀምጣ መማር እንዳልቻለች ትናገራለች። “የባለቤቴ ስራ አንድ ቦታ ላይ አይደለም። የተለያየ ቦታዎች ያስኬደዋል። በቅርቡ ኬንያ እንሄዳለን። አንድ ነገር ለመስራት፤ አንድ ቦታ ላይ መርጋት አለብህ” ትላለች። ከእናትነት በኋላ ወደ ጥበብ ትመለስ እ

ንደሆን ስትጠየቅ “ከጥበብ ጋር መለያየት አልፈልግም” ስትል ትመልሳለች። ግን ደግሞ “ሌላም ስራ መጨመር እፈልጋለሁ” ስትል ምናልባት ወደ ንግድ አለም ልትገባ እንደምትችል ጥቆማ ትሰጣለች።

ህሪይ በሚፈልግበት ወቅት ጓደኞቹ ላምሮትን ያመጡለታል። የድራማው መቼት የሚካሄድበትን ቦታ እንኳ የማታውቀው ላምሮት “ትሰራው” ይባልና ቃለ ተውኔቱ ይሰጣታል። መስፍን ላምሮት ድራማውን እርሱ እንደሚፈልገው ትጫወተው እንደሆነ ጥርጣሬ ገብቶታል። ዝግጅቱ አልቆ፣ ድራማው ተቀርጾ፣ በእሁድ ጠዋት የመዝናኛ ፕሮግራም አማካኝነት አየር ላይ ዋለ። ምላሹ ደግሞ ያልተጠበቀ እና አስገራሚ ነበር። ድራማው የአንዲት ሴተኛ አዳሪን ህይ

ወት የሚያሳይ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነች ጓደኛዋ ህይወት እንዳይበላሽ ስለመትከፍላቸው መስዋዕትነቶች የሚተርክ ነው። የድራማው መቼት ደግሞ ሐረ

ር አቅራቢያ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች። ጉርሱም ትባላለች። ላምሮት ድራማውን ስትስራ ያንን ቦታ አታውቀውም። እስካሁንም ድረስ አላየችውም። “ፍላጎት ካለህ ቦታውን ትሰለዋለህ። ስለ ጎርሱም ሳስብ ጭል ጭል የሚል ወንዝ ለራሴ ይታየኛል”ትላለች በምናብ ርቃ ሄዳ። “በትያትር ስራዬ ብዙ ክፍለ ሀገር ሄጃለሁ። እስከድሬዳዋ ድረስ ሁሉ። እንደ እድል ሆኖ ግን ሐረር (ጉርሱምን) አላየሁም።”

ራስን መፍጠርእንደ “ሶስቱ ወፎች” እና የ“ልደት ጧ

ፍ” ሁሉ “ድሃ አደግ” የተሰኘውን ትያትር እንድትሰራ የተመረጠችውም በአጋጣሚ ነው። ላምሮት “ራሴን የፈጠርኩበት” እያለች የምትጠራው “ድሃ አደግ” መጀ

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

በአጋጣሚ ተመርጦ ዋና ተዋናይ የመሆን ነገር በላምሮት ላይ ተደጋግሞ ተከስቷል

Page 14: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና14

ሆላንድ እንደገባሁ በሁለተኛ ወሬ የቋንቋ ትምህርት ጀመርኩ። የኢኮኖሚ ችግር

አልነበረብንም። እኔና መቅደስ እየተላመድን ወደ ድሮው ፍቅራችን ተመለስን። ደንሀግ መልካም ከተማ ናት። አንዳንዱ እዚህ የማየው ሀበሻ ከሰፈሬ ትቼው የመጣሁት ልጅ እየመሰለኝ ሆዴ እየተረበሸ ሰላምታ እሰጣለሁ። ሁሉን ወደ ቤቴ እንዲመጣ እጋብዛለሁ። ስልክ እለወዋወጣለሁ። አምስተርዳም ድረስ እየሄድኩ ወደ ኢትዮጵያ ማሕበር ጎራ እያልኩ፣ በኢትዮጵያ ስለሚሆነው ነገር ለመስማት እሞክራለሁ። የምበሳጨው ቴሌቪዥን ሳይ ነው።

ቋንቋው ገና ባይገባኝም መቅደስ እየተረጎመችልኝ እከታተላለሁ። አንዳንዱ ፕሮግራም ወደ ስድብ የተጠጋ ነው። ኢትዮጵያን የሚመለከት ፕሮግራም ከተላለፈ፣ የሚተላለፈው ስለኢትዮጵያ ድህነት ነው። የሚደግፉትን መንግስት እንኳን አይምሩም። ሁልጊዜ የሚራብ አበሻ አያለሁ። ቀስ ብዬ ቲቪ ከማየት ወደ አለማየት ዞርኩ። አንዳንዴም ኢትዮጵያን በጣም ከመውደዳቸው የተነሳ ሊረዷት ቆርጠው የተነሱ ይመስላል። ከስራ መባረሬን አልሰሙም? ልመና ልወድቅ ትንሽ እንደቀረኝ አልሰሙም?ኋላ ግራ ይገባኝ ጀመር። በየቦታው የሚሰበስቡን ሺህ ዓይነት

የሀበሻ ፖለቲከኞች ጥያቄውን ኢትዮጵያን ሰበብ እንጂ ማዕከል አድርገው አንስተዋት አያውቁም። ማለት ስለኢትዮጵያ ያወራሉ ግን በልባቸው ያለው በማን እንደሚተዳደር የማይታወቅ ድርጅታቸው ነው። ሁሉም ‘እኔ አሪፍ ነኝ’ ሲሉ እሰማለሁ፣ ግን ለምን እንዲያ እንደሚሉ አልገባኝ አለ። በዕድሜዬ ማነስ ያልሰረስኩባቸው ድሮ የማደንቃቸው ፖለቲከኞች አስገረሙኝ። አንዳንዴ ምናልባት ልፎአቸው በስነስርዓት መሬት ተቀብሮ ዛፍ ስላልተተከለበት ነው ብዬ ለራሴ ነግሬው እስቃለሁ። አሾፍባችው ጀመርኩ። ለስብሰባ የምሄደው አንዳንድ በቅርብ ያወቅሁዋቸውን ሰዎች ለማግኘትና ለማውራት ብቻ ነበር። ከሰው ጋር በተገናኘሁ ቁጥር ግን ‘ይኼ ሰው ማነው?’ የሚባል ጥያቄ ተነሳ መሰል። አለነገር ያ ሰው አለምዘውድ የሚባል፣ ሄልቨርሱም የተባለ ከተማ የሚኖረው፣ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት አባል እንዲህ አላለኝም፡“ማነህ አንተ ለመሆኑ?”የፍልስፍና ጥያቄ አልነበረም። “ስወለድ እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች አል

ነበሩም። ለአንድ አገርና ለአንድ ችግር ይሄ ሁሉ ፓርቲ ምን ያስፈልጋል?” አልኩት። በየዋሕነት ነበር እንዲህ ያልኩት። አዲስአባ ድራፍት እየለጠጡ የሚተዋወቁት ሰው አካባቢ መንጌን እንደ መተረብ ቀላል መስሎኝ ነበር። እንዲህ ማለቴ ቀላል ሀሳብ መስሎኝ ነበር። የመሃይም ነገር። መቅደስ ላይ የሚነዛው አሉባልታ የ

መጣው ይሄን ከተናገርኩ በኋላ ነው። ምናልባት ሲወራ ኖሮ ወደ እኔ የመጣልኝ። ደሞም እላለሁ። ስለ እኔ የሚያወሩት ነገር መጥፎ ነገር ስላጡ መቅደስን መውረር የጀመሩ። * * *አንድ ቀን አምስተርዳም የእንቁጣጣ

ሽን በዓል ምክንያት በማድረግ የመዝናኛ ፓርቲ ተደርጎ፣ ከሶስት ከማውቃቸው ልጆች (አንዱን አዲስአባ አውቀዋለሁ) ጋር ቆመን ቢራ እየጠጣን በሞቅታ መሃል (ወይስ ይሄ ማሳሰቢያ ሊሆን እንጃ) አንዱ፡“መቅደስ ደህና ናት?” አለኝ። ደህና

መሆኗን እንደነገርኩት “አንተ ባህሬይን ነበረች እንዴ?”“እንጃ አይመስለኝም”

“እርግጠኛ አይደለህም? እንዴት አታውቅም?” ሌላው ቀጠለ። ተማክረው ይመስላል። አለማወቄ አላሳፈረኝም። አረብ አረብ

ነው ለእኔ። “ባህሬይን የአገራችንን ሴቶች የሚሰሯ

ቸው ተንኮል የሚደርስባቸው ጣጣ”ከዚህ በላይ አልሄዱም። የማውቀው አ

ጠቃላይ ነገር ተወራ። የሰማሁትን ደግሜ መስማቱ ጥቅም አልታየኝም። እነሱም የጀመሩትን ወሬ ያቋረጡት ምንም እንዳልተሰማኝ ገምተው መሰለኝ። ከወር ምናምን በኋላ አንድ ሰው ታሞ

ልጠይቅ ደንሀግ ሆስፒታል ስሄድ ነው ዝርዝሩ እንዲገባኝ ያህል ሰፋ ተደርጎ በአሽሙር የተነገረኝ። በሽተኛው እዚህ ነው። በጀርባው ተን

ጋሎ ያምጣል፣ እና ከአገሩ ተደብቆ የመጣ ተስቦ ተከስቶበት ያመዋል። እኔ በግራ በኩል ጤንነቱን ጠይቄ ወደ ቤቴ ለመሄድ አኮበኩቤአለሁ። ታች በግርጌ በኩል ሁለት ሰዎች ወንበር ስበው ተቀምጠዋል። “ኸረ ባክህ?” አለ አንዱ ድምጹን ከፍ

አድርጎ“እዛ ነበረች”“አረብ ኤሚሬትስ ሴተኛ አዳሪ ምናም

ን ነበረች?” ከዛ ቀና ብለው አዩኝና እንደፈሩኝ፣ ል

ክ ለስእኔ ሃፍረት ያወሩ እንደነበሩ ሁሉ፣ እና እንዳልቃወማቸው የፈሩ ዓይነት አስመስለው ተያይተው በፍጥነት ዝም አሉ። ልናገር አልናገር እያልኩ ሳመነታ በሽተ

ኛው በድንገት ዳነ መሰለኝ፡ “አንተ ባለቤትህ መቅደስ አቅለያስን ታውቃት ይሆን?” አለ“ማን ናት አቅለያስ?” አልኩ“እንዴት አታውቃትም?” አለ አንዱማለቴ መቅደስ ባህሬይን ሴተኛ አዳሪ

እንደነበረች እንድጠራጠርላቸው ነበር? እኔን በኢትዮጵያዊነቴ ከመውደድ ይልቅ ለፖለቲካ ድርጅቱ ስላቃጠርኩ ሲያጣጥለኝ ነው? በየስብሰባው አሰልቺ ጥሩንባቸው ‘መንግስት እህቶቻችንን ወደ ዓረብ አገር እየሰደደ አስጠቃቸው’ ይላሉ። ለመንግስቱ ሐይለማርያም ጊዜ ‘ጁንታው የመጓጓዝ ነጻነት ዜጋውን ነፈገ’ ሲሉ የነበሩ ይሆናሉ። የመዘባረቅ ከያኒያን። የተበወዙ። በማን አፍ እንደሚናገሩ አልገባኝም። በአንድ ራስ አስራ ሰባት ምላስ። የመቅደስ ውርደት የእሱ ውርደት አይደለም? በየመግለጫቸው ስለእህቶቻችን እዬዬ ይሉና፣ እዚህ ቂጣችን ስር መውደቃቸውን መንግስት ማብሸቂያ ሊያደርጉት ይለፋሉ። ደቻሳ ምን አለ?ምን አለ ያ የአራተኛ ክፍለጦር ሰካራም? ኢልም ሃጠራው። እዚህ አንዱ የምወዳት ሚስቴ እንድትቀፈኝ ይለፋል። ምናልባትም እኔ ከመምጣቴ በፊት በዚህ ድክመቷ እያስፈራራ አውጥቷት ይሆናል። ብዙ አሰብኩ። መናገር አልቻልኩም። ብዙ ብዙ አይነት እርግማን ነገር አእምሮዬን ደፈነው። እንዲህ የመሳሰለ፡‘እዚህ አልጋህ ላይ በበሽታው ተጣብ

ቀህ ቅር’‘እናንተ ያልረባ ፖለቲከኛ ሆናችሁ አር

ጅታችሁ ሙቱ’‘ቀድሞ የሸረሞጠ፣ ሚስቴን ሸርሙጣ

ያለ የበሰበሰ ተልካሻ’‘ጥሩንባ ሁሉ’መከራከሪያ ፍልስፍና ሳይሆን በአእም

ሮዬ አስፋልቶች ላይ የሚመላለሰው የስድብ ዚታዎ ነበር። ስድብን በስድብ መቃወም ደንብ አይደለም? አንገቴን ደፍቼ እቆምኩበት በቁጭት ወለል በእግሬ እየመታሁ ዓመታት ለመሰሉ ደቂቃዎች ያህል ቆምኩ። ቀና ብዬ ሳያቸው በእርግጥ ሊያሳምሙኝ እንደፈለጉ ገባኝ። ታላቅ ዕውቀትም አገኘሁ። ማታ ቤት እንደገባሁ መቅደስ ወደ ተኛ

ችበት ሄጄ የሆንኩትን ነገርኳት። “አቅለስያን አውቃታለሁ” አለችኝ“ለምን ባህሬይን እንደነበርሽ አልነገር

ሽኝም?”“ምን ያደርግልሃል? ብነግርህ ባልነግር

ህ ምን ትለውጣለህ? ባልሄድስ ኖሮ? ምኑ ደስ የሚል ነገር አለው? ላስታውሰውም አልፈልግም”“ምን አለበት ብትነግሪኝ?”“ምነው ያለጸባይህ ምርመራ አደረግህ

ብኝ?”“እንዴት ያለ ጸባይህ?”“ቸልተኛ ነበርክ፣ ወሬ አትወድም ነበ

ር”“እወዳለሁ፤ ግድ የለም”“ደስ አይልም በእግዚአብሔር”“ንገሪኝ። ሰው ስላሽሟጠጠኝ ነው”“ሰው? መጣባት እንደፈራችው? እሷ ክ

ሮኒንገን አይደለ ያለችው?”“ምን መጣባት?”“ምን አወሩህ?”“አላወሩኝም። አሽሟጠጡኝ”“የዞረበት ሕዝብ እኮ ነው። ፍቅር ልታ

መጣ ሄደህ ደበሩህ” አለችና ሳቀች“ስለ አንቺ”“ምን?”“ስለ አንቺ። ስለ እኔ ምን ያውቃሉ? ቢ

ያሙኝ ጠጪ ዱርዬ ነበር ነው፣ ካልፈጠሩ”“ምን አሉህ?”“አንቺ ንገሪኝ”“ይደብረኛል ልረሳው እፈልጋለሁ። በ

እናትህ”“ሴተኛ አዳሪ ነበርሽ አሉ”“ምን”አለች ከተጋደመችበት ቀና ብላ።“በቀጥታ አላሉኝም። አቅለስያ ስለም

ትባል ልጅ አንስተው……ሴተኛ ኣሪ እንደነበረች…….ከዛ በሆነ አስተያየት አዩኝ……አለ አይደለ ሚስትህም ነበረች ለማለት…….”“ጉድ! ገረድ ነበርኩ። በቃ”“ሸርሙጣን ከየት አመጡት?”“ቃሉ እኮ በየቦታው አለ። አንዱ ጋ መ

ለጠፍ ነው። እኔ ገረድ መሆኔ እስከዛሬ ቁስል ነው። በአገሬ አነጅቤ መማር ስችል ዕድሌን ሁሉ አበላሽቼ……ለአረብ ገረድ መሆን ቀላል አይደለም። አረብ ፈረንጅ አይደለም። ብዙ አለ። ተወኝ። እኔ ነኝ የኖርኩት። እዚህ ሆላንድ ሰላም አገር ተቀምጠው ይነጅሱናል። ምን ፈለጉ? ከሰው መግጠም የማልፈልገው ለዚህ ነው። በመጀመሪያ ቆንጆም አይደለሁም ለሸርሙጣነት ማን ይፈልገኛል። ሂሂሂ። ሁለተኛ ለተሻለ ኑሮ ነው ከአገሬ የወጣሁት። ግን ባርነት አጋጠመኝ። ተምረናል ተሻሽለናል ብለው፣ ውድ ውድ መኪና ይነዳሉ ግን ይገርማል፣ አንጎላቸው ገና ነው። ለመጀመሪያ የእቃ ስልጣኔና የመንፈስ ስልጣኔ እንደሚለያይ የገባኝ አረብ አገር ነው። ያገሬ ልጅ ዝተት ለብሶ አልደፈረኝም። በአፍ ብለከፍ፣ መልሼ የምለክፈው የምስድበው ያገሬ ወንድ ናፈቀኝ። ወንድ መስደብ ናፈቀኝ። ከወንድ መሰዳደብ ናፈቀኝ። አንዳንዴ 12 ጂ ይናፍቀኛል። የማታ ሽፍት። ጥቁር አንበሳ ፣ መንገድ እያቋረጥን ከክላስሜቴ ወንዶች ጋር ስሰዳደብ። ሌላ ነገር ሳይሆን በቃ አፋቸውና ተረባቸው ናፈቀኝ። አረብ አገር አንዲህ አይታሰብም። አንገትህን ደፍተህ ነው። ስንት ልጆች ራሳቸውን እን

ደገደሉ ታውቃለህ? ቤት ይቁጠረው ልበልህ። እንዳንሰማ አድርገው ስለሚቆጥሩት ነው እንጂ ይደፈራሉ። አልለመድንም። ተድፍሬ አላውቅም አገሬ። የአበሻ ሴቶች ለሚያውቃቸው ሂያጅ ናቸው ግን መደፈር አይወዱም። ደግ ወንድ አቀራረብ ሳይገባው ቢደፍር ይቅር ይባላል። በጥላቻ አይደለም። እኛ አገር ያለው መድፈር ያ ነው። የሚንቀኝ የሚጠላኝ ሲደፍረኝ እሱ ሌላ ነው” አለችና አተኩራ በዝምታ አየችኝ። ‘ተደፍሬአለሁ’ ልትል መሰለኝ። “ሸርሙጣ አልነበርኩም። እመነኝ። ተ

ገርጄአለሁ። ገርድ መሆኔ ሳይሆን አብሮት መአት መከራ ይመጣል። ምን ብዬ ልንገርህ?” በሃዘን ቀና ብላ አየችኝ። ልቤ ላይ ውጋት ተሰማኝ። የእውነት።

የአራዳ ልጅ ነኝና ተንኮል የሰራሁባቸው ጊዜያት ነበሩ። የሰው ሕልውና ግን አጥቁሬ አላውቅም። አላስፎግርም። ከማብሸቅ አያልፍም። እኔም ጓደኞቼም ‘ደባሪ’ መባልን እንጠላ ነበር። ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና ለማሰብ ሞከርኩ። ይሄ ግድግዳ ነበር። ለማሰብ እንቅፋቶች መነሳት አለባቸው። ይሄ እንቅፋት ነው። የስደት ስነ ልቡና የት ጋ እንደሚጠመዘዝ አላውቅም። ሰንጋ ተራ የማውቀው አራዳ የመሰለኝ የእኔ ቢጤ ጠጪ ድንገት ‘ኢ-አራዳ’ ይሆናል ብዬ አልጠበቅሁም። መቅደስ እንዳልዋሸችኝ ይገባኛል። ምክንያቱም አይኖቿ ውስጥ ሳትደፈር እንዳልቀረች ነገሩን ተናግራ ካሳየችኝ እንግዳ ትኩረት መገንዘብ አልከበደኝም። ይሄ ነገር ለእኔ ውርደት መሰለኝ። የውርደቱ ጽንሰ ሀሳብ የመጣው ባልገባኝ ምክንያት ከውስጤ ኃላፊነቱ የእኔ ስለመሰለኝ ነው። ለምን እንደሆነ አለማወቄ ደሞ የባሰ ረበሸኝ። ማሰብ አለመቻሌ። ሲጋራ ጠማኝ። ልክ እንደ ውሃ። “አመንከኝ”“አዎ”“እውነቱ ይሄ ነው”“ለምን ይሄን አለኝ? ለምን ዝም አልኩ

ት?”“ምን ልታደርገው? ምን ልትል?”“ምን እለዋለሁ?”“እንዲህ አድነው ሊያሳፍሩህ ሲፈልጉ

ለምን ይመስልሃል?”“እሱ እኮ ነው። እሱን እያሰብኩ ነው።

ለምን ወደ እኔ አመጡት?”“ስራ ሊያስፈቱህ ነዋ። ስንት ዓመቱ ነ

ው ሆላንድ ሲኖር። በዳች ቋንቋ የልጆች ፕሮግራም በቲቪ ማየት እንኳን አይችልም። አይገባውም። ቀንቶ ነው። አርፈህ መቀመጥህ ሊያበሳጨውና ሊቀና ይችላል። የተለየ ፖለቲካ ያስብ ይሆናል። የማይፈልጉትን ሃሳብ እየዞርክ እንዳታወራ ስም በማጥፋት ያገሉሃል። ሌላ ምንድነው ታዲያ። ፈሪዎች ናቸው። ናቃቸው።”አልጋ ላይ እንደተቀመጠች ትቼአት በ

ረንዳ ላይ ወጣሁ። ቀዝቃዛው ማታ ውስጥ የፖታት (በዘይት የተጠበሰ ድንች) ጠረን አለ። ግራና ቀኝ ጀርባዬ ላይ ሁለት እጆቿን አስቀመጠች። ገና ያልወረደ እርግዝናዋ ሲቀርበኝ ይሰማኛል። ልክ ማታ አዲስአባ በቅሎ ቤት ከቤተሰቤ ስሰናበት የሆነውን ነገር ይመስላል። ጭንቀት ሲመጣ፤ ሰዓትና የአየር ጸባይ አይቶ መሰለኝ። የደንሀግ ሰማይ ላይ በብርሃን የተተኮሰ ጉም ምናምን የመሰለ ቢጫ ውጋጋን አለ። ለስ ያለ አየር ከባህር ይመጣል። “ስልክ ተደወለ” አለችና ትታኝ ወደ ቤ

ት ገባች። ዞር ብዬ ላቅፋት ነበር። ያሳሰበኝ እሷ የተናገረችው ነገር አልነበ

ረም። ያሳሰበኝ በዚህ የጣጣ ካርታ መሃል የሚፈሰው ስም ያልተሰጠው አንዱ ወንዝ። አንዳንዴ ሲቸግረኝና ከአሁኑ ወጣ ገባ ጋር ስፋጠጥ መንግስት የነጠቀኝ ቸልተኛነት ይናፍቀኛል። ሲጋራ ለኮስኩና ባንኮኒ ተደግፌ ልረሳ እየሞከርኩ ቆምኩ። ከምኖርበት ሕንጻ ስር የማይታይ

ልፎበአዳም ረታ

*

ትረካ

ወደ ገጽ 22 ዞሯል

(ክፍል ሁለት)

ሰው የወረወረው የቸኮላታ ከረሜላ ልባስ በነፋስ እየተገፋ፣ በለስላሳው አስፋልት ላይ ያልፋል። ብዙ ጊዜ ግን አረፍ ብሎ በጸጥታ እስኪጠረግ ነገን የሚጠብቅ ይመስላል። ባለጌ ሰው መሆን አለበት ንጹህ ደንግሀግ መሃል ቆሻሻ እንዲህ የሚጥል። በስልክ ስታወራ እሰማታለሁ። ምን

እንደምትል ግን ግልጽ አይደለም። ይሄን አገር እወደዋለሁ። ግን ሰላም እ

ንዳለገኝ የሚፈልግ ሰው አለ። ይሄ ማለት አሁን ሰላም አለኝ ማለት ነው። ስትስቅ እሰማታለሁ። ውበቷ የሚወጣው ስትስቅ ነበር። ሌላ ነገሯ ሳይሆን ስትስቅ ‘ደስ አትልም?’ ነበር የሚባለው። ይከፋኝ ነበር። ለምን ሌላ አልተባለችም? ለእሷ ቆንጆ መሆን አለመሆን አስቤ ሳይሆን በብዙ አቅጣጫ ያልተሞካሸች ልጅ ገርል ፍሬንዴ በመሆኗ። ሰላም እንደነበረኝ የማውቀው ስለከፍ ነው? ‘ምቀኛ አታሳጣኝ’ ምናምን የሚሉት ለዚህ ይሆን? ከአገር ውጭ ከአገሬ ጋር የምሆነው እንዲህ ነው? እነዚህ አገራቸውን የዕውነት የሚወዱ ናቸው?ስልክ ዘግታ መጣችና ከኋላዬ አቀፈ

ችኝ። እንድትናገር እጠብቃታለሁ። አልተ

ናገረችም። “ለምንድነው አንድ ሰው ሌላ ሰውን

ለመደበር የሚነሳው?”“እግዜር ያውቃል። የተፈጥሮ ስጦ

ታ? ልክ እንደ ድምጻዊ”“ቆንጆ ነኝ?”“ምን?”“ቆንጆ ነኝ ወይ? ያልሰማህ አትምሰ

ል”“ሰምቼአለሁ። ምን አመጣው ብዬ ግ

ራ ገብቶኝ ነው”“አሁን አንዷ ስትደውልልኝ ምን አለ

ችኝ መሰለህ? ‘እከሌ ታች ዳውን ታውን አይታሽ ‘ኢትዮጵያዊ ነች ወይ?’ ብላ አለች’ አለችኝ”“ምን ማለቷ ነው?”“‘ባርያ ነሽ ምናምን’ ልትለኝ ነዋ። ‘አ

ትመስልም? ምናምን’ የሚሉት ነገር አላቸው”“አዲስአባ አላጋጠመሽም?”“እዚህ ግን ተስተካከልን። አይገርም

ም? ይሄኔ እናቶቻቸውና አባቶቻቸው እኩለ ሌሊት የሚመስሉ ናቸው። እነዚህ ጥቃቅን ነገሮች ናቸው። ቢያንስ ለእኛ ጥቃቅን ነገሮች መሆን ነበረባቸው። አለ አይደለ”“በቃ አየሽ ለወሬ የሚሆን መልካም

ነገር ጠፋ”“አንተስ?”“ምኑን?”“አልመለስክልኝም”ትንፋሿ ጀርባዬ ላይ ለአፍታ ጸጥ አ

ለ። መልስ እየጠበቀች፡፡ ዞር ብዬ ግዙፍነቷን አቀፍኩት። አይኖቿ ጮልጯና ደካማ ናቸው። ትልቅ አፏ ላይ ሳምኳት። የሚጣፍጥ ጠረን አለው። መልሴን ትጠብቃለች። “ስትስቂ አንጀት ታርሺያለሽ”እጇን ከትከሻዬ ላይ አንስታ እንደመ

ሽኮርመም አፏን ያዘች። “እውነት ነው? ይበቃኛል”“እውነት ነው” የእሷ እንዳልሆኑ ሁሉ ወንድ የሚመ

ስሉ የቆረፈዱ ትንንሽ እጆቿን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየቻቸው አይነት ለአፍታ ስታጠናቸው ቆየችና በማፈር ቀና ብላ አየችኝ። እንዳልገባኝ ትቼአት ለመሄድ፡“ሻይ ላፍላ?” አልኳት“ውሃ አምጣልኝ”“ልጁ እንዴት ነው። ብዙ ይፈራገጣ

ል?”ፈገግ ብላ አየችኝ። ሚስቴ ናት። በማ

ንም የማልለውጣት ሚስቴ ናት። ‘በእናት አገርና በሚስት የለም ዋዛ’ ይላ

Page 15: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 15

መጽሐፍ

“ተደርጎ ያውቃል ወይ እንግዳ ሥርዓት፣እግር አዲስ አባ ልቡና መቄት።”አስገራሚ የልጅነት ቀዬ ናፍቆት፤ መናፈቅማ ሁ

ሉም ይናፍቅ የለ ግን አንዳንድ ሰው ናፍቆቱን ሲጽፈውም ሲናገረውም ውበት አለው። “ተሰጥዎ ነው!” ይሉን ይኾን የግጥሙ ባለቤት አለቃ ለማ በትዝታቸው ውስጥ ስለ ቅኔ በምሳሌ እንደተናገሩት? “ዳቦው በሴትዮዋ ያምራል ይከፋል እንጂ፤ አንድ ስንዴ አደለም? ልባም ሴት ብትይዘው ያምራል፤ ሰነፍ ሴት ብትይዘው ይጨማለቃል… ተሰጥዎ ነው፤ ከግዜሃር የተሰጠው ነው ዋናው…” የመጽሐፈ ትዝታቸው መዝጊያ በኾነው የግዕዝ ቅኔም እንዲሁ አስገራሚ ናፍቆታቸውን ገልጸዋል።“አነ ወዝናም እንዘ ንጹሐን እምነውር ወእንዘ በ

ቀል አልብነአሮን እምበዊአ ቤቱ በከንቱ ከልዓነ።እስመ እመ ዐረግነ ላዕለ ወእመ ታሕተ ወረድነዘምስለ አቡነ አሮን ያስተሳልመነአረጋዊ ኢተረከብነ ለነ”በራሳቸው አንደበት ቅኔው ሲተረጎምም እንዲሁ የሚያስደስት ለዛ አለው የአቡነ አሮን ገዳምን ዝና ለሚያውቅ ሰው፤“እኔና ዝናብኸነውር ንጹሐን ስንሆን፤ ቂም በቀል ሳይኖርብን፤አሮን ወደቤቱ ከመግባት በከንቱ ከለከለን።ወደላይ ብንወጣ ወደታችም ብንወርድካባታችን ካሮን ጋር የሚያስታርቀንሽማግሌ አልተገኘልንምና።”አለቃ ለማ ስለ ልጅነት አገራቸው ታቦት ስለ አ

ቡነ አሮን ገዳም ያለውን እምነት በገለጹበት ስፍራ “ይህ ያቡነ አሮን እንዲያ ው ዋሻ ነው። ውስጡ ነው የተጠረበ እንጂ፤ ላዩ ዋሻ ነው። አቡነ አሮን በእጃቸው ነው የጠረቡት። … ገደል ሲናድ የተቀደደው ቀዳዳ ኸመንበሩ አጠገብ ኸቅኔ ማኅሌቱ ላይ ነው ጣራው ላይ። ጠሐይ ብልጭ ሲል ብርሃኑ ገብቶ ወለል ይላል። ዝናብ ጠብ አ

ይልም፣ ምን በረዶ ቢወርድ ጠብ አይልም።” ይህ እንግዲህ “ነገር ሲመጣ” አንዳንድ ቀን ከሚዘንበው ውጪ መኾኑ ነው። ነገር መጣ የሚባለውም ረሀብ፣ ጦርነት፣ መቅሰፍት እና የመሳሰለው ሲመጣ ነው።አለቃ ለማ እንግዲህ ራሳቸውን በዚህ የአቡነ አ

ሮን ዋሻ እንዳይገባ በተከለከለው ውኀ መስለውታል። ያውም ንጹህ እና ነውር በሌለበት የዝናም ውኀ። እራሳቸውንም እንዲሁ ነውር የሌለባቸው እንደኾኑ ይናገራሉ “ቂም በቀል የሌለባቸው” ንጹህ። ነገር ግን እንደዝናሙ ውኀ ሁሉ እርሳቸውም ተመልሰው ያገራቸውን ታቦት ለመሳለም ወደ አጥቢያቸው መሔድ አልቻሉም፤ መቄትን እንደናፈቋት ቀርተዋል። ያውም “በከንቱ”!እንዲያው አወጣጣቸው እና አኪያሔዳቸው በ

ልጅነታቸው አንድ አዋቂ ስለ እርሳቸው የተናገረውን ንግር በጣሙን ይመስላል። ስለ ቤተሰቡ ሁሉ መጻኢ እድል ፈንታ ሲተነብይ የነበረው እንግዳ ነብይ አለቃ ለማን ዘነጋቸው። በድጋሚ ከተለመነ እና ተጨማሪ ስጦታን ከተቀበለ በኋላ ግን ሰ

ውየው ለመናገር የከበደውን ያንን ትንቢት ተነፈሰው ምሬት ከሚመስል ጭማሪ ጋር “ምን አድርግ ትሉኛሉችሁ ወደ ፀሐይ መውጫ ብቻ ሲሔድ አየዋለሁ፤ የሚያርፍበትን አላወቅሁትም፤ ሲያርፍ አይታየኝም። እንዲያው ክንፍ አውጥቶ እንዳሞራ ወደ ምሥራቅ ሲሄድ አየዋለሁ።” አለቃም ራሳቸው ይህን የመሰለ ህልም ደጋግመው እንዳዩ ይናገራሉ። ፍቺውንም ያወቁት ይመስላሉ፤ “አረርጌ አይደለም? አረርጌ ነው” በስተመጨረሻ መኖሪያቸው የነበረችዋን ሐረርጌን የሚያመለክት ትንቢት እንደነበረ ያምናሉ።አለቃ ለማ የደራሲው መንግሥቱ ለማ አባት ና

ቸው። ምናልባትም የመንግሥቱ አባት መኾናቸው ከሌሎች እሳቸውን መሰል ሊቃውንት በተለየ ትዝታቸው በዚህ መልክ እንዲጻፍ ምክንያት ሰይኾን አልቀረም። ከእርሳቸውም በፊት ከእርሳቸውም በኋላ እንዲህ ቃል በቃል የተጻፈ ታሪክ ያላቸው ኢትዮጵያውን ያሉ አይመስሉም። ምሥጋና ለልጃቸው ለደማሙ ብእረኛ! የአዲስ አበባው ዩኒቨርሲቲ ፕሬስም የሦስት ምሁራንን መ

ዊው የሥነጽሁፍ እና የታሪክ ትምህርት ተሞክሮ ትረካውን ጣፋጭ አድርጎታል። ተራኪው አዛውንት በየመሀሉ የሚጠቅሷቸው የግዕዝ ቅኔዎች እና የአማርኛ ግጥሞች ትረካውን ሙዚቃዊ ቃና አድሎታል። መንግሥቱ ለማን ከሎንዶን የኢኮኖሚ ትምህርት ቤት ወደ ቅኔ እና የጥበብ ዓለም ያስሸፈታቸውም ቆሌ ለካንስ ድንገት የተከሰተ አልነበረም የኖረ የአያት የቅድመ አያት እንጂ። ተራኪው አለቃ ለማ ስለ እናታቸው (ስለ መንግሥቱ አያት) በሚናገሩ ጊዜም ይህ የቅኔ ውርስ በግልጽ የሚታይ ነው። እኚህ ሴት በእድሜ ከገፉ በኋላ የገጠሙትን ግጥም አለቃ ለማ እንደሚሉት “መቄት ውስጥ ያላጠናው የለም”። ቢጠናም አይደንቅም የሚገርም የጥበብ ልቡና ተንጸባርቆበታልና።“ጆሮ ቀለቡን ተሰፈረዐይን እንደራበው ቀረ”ተራኪው አለቃ ለማ የሚያጫውቱን ወግ አንዳ

ንድ ጊዜ ተረት ብቻ የሚመስሉንን ግለሰቦችም በቅርበት እና ባላየንበት ማንነታቸው የሚያሳየን ነው። አፄ ቴዎድሮስን ስናውቃቸው ቁጡ እና በየአቅጣጫው የሚሸፍተውን ግዛታቸውን ለማስገበር ፋታ የሌላቸው ባተሌ ነበሩ። በአለቃ ለማ ትረካ ውስጥ ግን ቴዎድሮስ በቆሎ ትምህርት ቤት የሚዘምር አንድ ድምፀ መልካም ተማሪ ለማዳመጥ ሲሉ ድንኳናቸውን በቆሎ ትምህርት ቤቱ አጠገብ አስተክለው ሦስት ቀን በዚያው ሲከርሙ ይታያሉ። የፍቅር እስከ መቃብሩ ጉዱ ካሣ እዚያው ዲማ ጊዮርጊስ አድራጊ ፈጣሪ ኾኖ አለቃ ለማ ቅኔ እንዲቀኙ ሲያደርግ ይታያል፤ በቅኔ ላይ ባሳየው ድክመቱ ምክንያትም የተዘረፈበትንም ቅኔ ያስታውሱታል። በዚቀኝነታቸው ብቻ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቁትም አለቃ ገብረሃና የታወቁ የዝማሜ እና የአቋቋም ሊቅ ኾነው ነገር ግን በብብታቸው የትምባሆ ቅል ደብቀው ቤተ መቅደስ ውስጥ እንደተገኙ ያሳዩናል። አፄ ዮሐንስ፣ አፄ ምኒልክ፣ ንጉሥ ሚካኤል ሁሉንም እንደገና በአዲስ ማንነታቸው እና በተራኪው ዕይታ እንድናያቸው ያደርጉናል። በዚህ ግሩም መጽሐፍ!

ሐበሻዊ ቃናhabeshawi

kana ብላችሁ

ፈልጉን

“ላይክ” () የሚለውን ምልክት

ተጫኑ

ወቅታዊ ዘገባዎች፣ “ሊንኮች”ን እና ፎቶዎች ያገኛሉ

ባለፉ የጋዜጣው እትሞች ላይ የወጡ ጽሁፎችን ያገኛሉ

የአለቃ ለማ ትዝታ በደማሙ ብእረኛ

ግቢያ በመጨመር በድጋሚ እንዲታተም አድርጎታል። ዩኒቨርስቲ ፕሬሱ እንዲህ አይነት ድንቅ መጽሐፎችን እያሳተመ የአንባብያንን የንባብ ጥም ለመቁረጥ የተነሳ ይመስላል። ምሥጋና ለዩኒቨርስቲ ፕሬስ!መንግሥቱ ለማ የአባታቸውን ትዝታ እንዲህ ባ

ለ ኹኔታ በማሳተማቸው የራሳቸውን ታሪክ ጨምሮ ስንት የአገሪቱን ታሪክ እንዳዳኑ ለመረዳት አይቸግርም። ተራኪው አዛውንት ከልጅነት ቀዬአቸው ከመቄት አንስተው እስከ አዲስ አበባ እና ሐረር ያደረጉት ጉዞ ከግለሰቡ ታሪክ ባሻገር የአገሪቱንም፣ የጥንታዊቱን ቤተክርስቲያንም ታሪክ ይተርካሉ። የጊዜውም ርዝመት የሚደንቅ ነው፤ ከአፄ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ አፄ ኀይለሥላሴ ድረስ የነበረውን የታሪክ ዘመን አንዳንዶቹን ከዐይን ምስክሮች እንደሰሟቸው አንዳንዶቹንም ራሳቸው እንዳለፉባቸው ታሪኮች ስለሚያስታውሷቸው ይህን ትረካ መከተል እንዴት ያለ ደስታ እንደሚፈጥር አንባቢው ብቻ ነው የሚረዳው።በዚህም ላይ ተራኪው ራሳቸው ያላቸው ባህላ

የመጽሐፍ ዳሰሳመዝገቡ ኃይሉ- አዲስ ነገር ኦንላይን

ተራኪ፦ አለቃ ለማ ኃይሉ

ጸሀፊ፦ መንግስቱ ለማ

አሳታሚ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ

የታተመበት ዓመት፦ 2003 ዓ.ም

Page 16: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና16

የከተማ ቧልት

ፊልም

ዩጋንዳ

የት ሄደን እንዝናና?

መቼ፦ ከሰኞ እስከ እሁድ የት፦ ሲኒፕሌክስ - ጋርደን ሲቲ- ከኡቹሚ ሞል በላይ ሶስተኛ ፎቅሰዓት፦ ከቀኑ አምስት፣ ስምንት፣ አስር ሰዓት እንደዚሁም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል፣ ሶስት ሰዓት ተኩል የመግቢያ ዋጋ፦ 16ሺህ ሽልንግ ( ዘወትር ማክሰኞ ስምንት ሺህ)

በሶስት የተለያዩ አዳራሾቹ የአሜሪካ እና የህንድ ፊልሞችን ሳምንቱን ሙሉ ለተመልካች የሚያቀርበው ሲኒፕሌክስ በሚቀጥሉት ሳምንታት ለዕይታ የሚያበቃቸው ፊልሞች የ“ሀሪ ፖተር” ተከታታይ ፊልም የመጨረሻ ክፍል፣ የ“ትራንስፎርመር” ተከታይ ፊልም እና “ብራይድስ ሜይድን” ነው።

ስኳር + ዘይት + ቤንዚን = ቦምብ ሰሞኑን በተለያዩ የቴክኒክ እና የሙያ

ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ወጣቶች የየራሳቸውን የፈጠራ ውጤቶች በኤግዚቢሽን ማዕከል አቅርበው ነበር፡፡ ይህንን የወጣቶችን ፈጠራ ያስተዋለ አንድ የሠፈሬ ወጣት ቀልብ የሚስብ የፈጠራ ሥራውን ለእኛ መንደር ሰዎች ይዞ ቀርቦ ነበር፡፡ ወጣቱ ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ ቤንዚን፣ ውሃ እና የተለያዩ ነገሮችን ከፊት ለፊቱ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ወጣት ጋር ያደረግኩትን ቆይታ እነሆ፤“ስምህ ማን ይባላል?”ወጣቱ ተናገረ፡፡“ለመንደራችን ነዋሪዎች ይዘህ የቀረብ

“የቴሊቪዥን የአገልግሎት ክፍያ ክፈሉ! ክፈሉ! ክፈሉ!” የሚለው የኢቲቪ የዘወትር ውትወታ እቤት በተገኘሁበት ሰዓት ሁሉ ቴሌቪዥኔ ላይ እንድጣድ ምክንያት ሆኖኛል፡፡ “ኢቲቪ እንዲህ ማለቱ ረብ ያለው መረጃ እና ቀልብ የሚስ

መንግሥታችን ለተፈጥሮ ሳይንስ፣ ለቴክኖሎጂ እና ለሒሳብ የትምህርት ዘርፍ ትኩረት መስጠቱ ሰሞኑን በየሚዲያው እንደ ጉድ እየተዘገበ ነው፡፡ እንደውም ለዘርፉ መምህራንና ተማሪዎች እንዲ

ሁም አዳዲስ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ላቀረቡ ግለሰቦች ሽልማቶችን በመስጠት ምን ያህል ትኩረት እንደሰጠ አሳይቶበታል፡፡በተለይ የሒሳቡ ነገር ከየትኛውም ዘርፍ በላይ መንግሥታችን ትኩረት እንደተ

ሰጠው ውስጠ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ለምን ቢሉ መንግሥት እና የሒሳብ እውቀት ባሌ እና ቦሌ ናቸውና፡፡ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ታዲያ፣ “የሒሳብ ሊቃውንት ሆይ ወዲህ ኑ!” እያለ ነው አሉ መንግሥት፡፡ሒሳብ የቁጥር ጉዳይ ነው፡፡ የቁጥር ጉዳይ ደግሞ መንግስትን እና ተቃዋሚ ኃ

ይሎችን፣ መንግሥትን እና የውጪ ኃይሎችን፣ መንግስትን እና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችን፣ መንግስትን እና የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን ያወዛገበ፣ አሁንም እያወዛገበ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ እስኪ ባለፉት ሃያ አመታት መንግሥታችንን ካወዛገቡት ቁጥር ነክ ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹን እንመልከት፤ሀ. የራሷ የኢትዮጵያ ዕድሜ የታሪክ ምሁራንንና መንግስትን አወዛገበ፤ለ. የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት አወዛገበ፤ሐ. ባለፉት ምርጫዎች /በተለይ 1997 ዓ.ም/ የተገኙት የድምፅ ቆጠራዎች ው

ጤት መንግሥትንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አወዛገበ፤መ. “እንደ ሾላ ሕገ መንግሥቱን በድንጋይ ለማውረድ ግርግር የፈጠሩ ፀረ ዴ

ሞክራሲ ኃይሎችን ለማስቆም ወደ ሰማይ በተተኮሰ ጥይት የሞቱ ሰዎች” ቁጥር አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ተቋማትንና መንግሥትን አወዛገበ፤ሠ. በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በተከፈለው መስዋዕትነት ያጣነው የሰው

ሕይወትና የገንዘብ መጠን ሲሰላ መንግሥትን እና ተቆርቋሪ ወገኖችን አወዛገበ፤ረ. በየዓመቱ የምናስመዘግበውና እያስመዘገብን ያለነው “ፈጣን የኢኮኖሚ ዕ

ድገት” በመቶኛ ተሰልቶ ሲቀመጥ የኢኮኖሚ ባለሞያዎችን እና መንግሥትን አወዛገበ፤ሰ. በየጊዜው በሚነሳው ረሃብ የሚጎዳውና እያለቀ ያለው ህዝባችን ቁጥር መን

ግሥታችንን እና የውጪ መገናኛ ብዙኃንን አወዛገበ፤ አሁንም እያወዛገበ ነው፡፡

ሌላው ሰሞነኛ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተው ጉዳይ በእግር ኳሱ፣ የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ስፖርት ክለብ የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ነው፡፡ ሊጉ ከመጠናቀቁ በፊት ባሉት አራት እና አምስት ጨዋታዎች ስቴዲየሙ የተለየ ድባብ ነበረው፡፡ በተለይ ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ካለው፡፡በስቴዲየም ውስጥም ሆነ ከስቴዲየም

ውጪ “ጨምሯል ቡና ጨምሯል፤ ቡና ገበያ አደገኛ!” ዓይነት የኑሮ ውድነትን የመቃወሚያ የሚመስሉ መዝሙሮችን መስማት ለከተማችን ነዋሪ እንግዳ አልነበረም፡፡ በተለይ ለስፖርቱ እንግዳ የሆኑ አንዳንድ ነዋሪዎች፣ “ጨምሯል ቡና ጨምሯል፤ ቡና ገበያ አደገኛ!” የሚለውን መዝሙር ሲሰሙ፣ “እናውቀዋለን፤ ቡና ተረት በሆነበት ጊዜ ሱሳችንን አትቀስቅሱብን!” በማለት ሲቀልዱ ተደምጠዋል፡፡

ብ ፕሮግራም ቢኖረው ነው” የሚል ተስፋ በመሰነቅ፡፡ ታዲያ በባለፈው ሳምንት ባንዱ ቀን ክፉና ደጉን ለመስማት የከፈትኩት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲህ የሚል ዜና ጆሮዬ ድረስ ይዞልኝ መጣ፡፡ “የደስታ በሽታ ከዓለም ላይ መጥፋቱ ተገለፀ፡፡” ዜናው ራሱ ደስታ የሚፈጥር ነበርና ደስ ተሰኘሁ፡፡በተለይ ይህ በሽታ ወደ አፍሪካ የገባው

በ19ኛው ክ/ዘመን መሆኑን ስሰማማ ለጠቅላላ እውቀት የሚሆን ጥሩ መረጃ በማግኘቴ ደስታዬ ወደር አጣ፡፡ አይታወቅም እኮ በየኤፍኤሙ በገፍ የአየር ሰዓት ከተሰጣቸው ከ”ቶክ ፉት ቦል” ፕሮግራም አዘጋጆች መካከል አንዱ የሚከተለውን የሞባይል ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ ይጠይቅ ይሆናል፡፡ /ዘንድሮ በአገራችን ከፍተኛውን ሚዲያ ሽፋን የያዘው የቦንዱ ሽያጭ እና የእግር ኳስ ስፖርት ጉዳይ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ ሌላ ብርቱ ጉዳይ አለብን እንዴ!? እኔ እንጃ! የሚያቀርቡልኝን ከመስማት እና ከማንበብ በስተቀር እኔ ምን አውቃለሁ!?/“የደስታ በሽታ ወደ አፍሪካ የገባው መ

ቼ ነው?” እኔ ሆዬ ሚስድ ኮል ለማድረጊያ ከቆጠብኳት ሣንቲም ላይ ቀንሼ ቁጥሮቹን ጠቅ፣ ጠቅ አድርጌ፣ “ሃሎ የቶክ ፉትቦል አዘጋጆች!?” ማለ

ት ብቻ፡፡“አዎ! ማን እንበል?”“እኔ ኤስ ነኝ፤ ከአዲሱ ሰፈር፤ የቅድሙ

ን ጥያቄ ለመመለስ ነበር፡፡”“እሺ ይቀጥሉ!”“የደስታ በሽታ ወደ አፍሪካ የገባው

በ19ኛው ክፍለ ዘመን ነው!” እላለኋ! የከሳቴ ብርሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት

“ደስታ” የሚለውን ቃል ሲፈታው፣ “የልቡና መደሰት፣ ኀዘን በሌለው ስሜት መሆን፣ የፊት መፍካት” ይለዋል፡፡ የደስታ በሽታን የሚያውቀው ደስታን የሚያውቅ ሕዝብ ነው ብዬ አጉረምርሜ ሳልጨርስ ግን የደስታ በሽታ የከብቶች በሽታ መሆኑን ማብራሪያ ተሰጠበት፡፡ አዎ! ጠንቁ ለሰዎችም የሚተርፍ በሽታ ሆነ እንጂ “የደስታ በሽታ” እንኳን የከብቶች በሽታ ሆነ አልኩ፡፡

ከው የፈጠራ ውጤት ምንድነው?”“በእነዚህ ንጥረ ነገሮች ቦምብ መሥራ

ት!”“እሺ ከስኳር፣ ከምግብ ዘይት፣ ከቤንዚ

ን፣ ከውሃ እና ኅብረተሰቡ በጥብቅ ከሚፈልጋቸው ከእነዚህ ነገሮች የሠራኸው ቦምብ አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ማለቴ ተግባራዊ የሚደረገው?”“እነዚህ ንጥረ ነገሮች ውህደት ፈጥረው

አይደለም ቦምብ የሚሆኑት፡፡” “እና?” “ራሳቸውን ከአገሪቱ በማጥፋት እንደ

ቦምብ መጠቀም ብቻ ነው፡፡”እግዚኦ! የምቀኛ ጆሮ ይደፈን!

ሌሎች ደግሞ “ቡና ገበያ አደገኛ!” የሚለውን መዝሙር ሲሰሙ “እንዴ! ምን ቡናው ብቻ የስኳሩ ገበያስ ቢሆን! ኧረ የየዘይቱ፣ የጤፉ፣ የሽሮውም ቢሆን መች ይቀመስና…!” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ለማንኛውም፣ “የሕዝብ ብሶት የወለደው ጀግናው የኢትዮጵያ ቡና ሠራዊት ቅ/ጊዮርጊስ ሲጠቀምበት የነበረውን ዋንጫ ተቆጣጥሮታል!” ቅ/ጊዮርጊስ ከአሥራ ሦስቱ የሊጉ ዕድሜ ዘጠኝ ጊዜ ሻምፒዮን መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ቡና ለዋንጫው እየቀረበ ሲመጣ

እንዲህ የሚል ልማታዊ መዝሙር መጣ፤ “አባይ ይገደባል፤ ቡና ዋንጫ ይበላል!” ዋንጫው ተበላ፡፡ እነሆ የሚከተለው

ዜማ ደግሞ ተከተለ፤“መሰናበቻ መሰናበቻ!ያሆ! መሰናበቻ፤አሁን የቀረው ግድቡ ብቻ!”

“ቡና ገበያ አደገኛ!”

ሒሳብ የቁጥር ጉዳይ ነው

የደስታ በሽታ እና “ቶክ ፉትቦል”

የ“ፌስ ቡክ” ስላቅ

ከላይ የቀረቡትን አራቱንም ጽሁፎች ከአዲስ አበባ ያደረሰን አምደኛችን

የአራት ኪሎው በእግዜር ነው

ኬንያ

እ.ኤ.አ በ2002 የኦስካርን ሽልማት በምርጥ የውጭ ሀገር ፊልም ዘርፍ ያሸነፈ ነው። “ኖ ዌር ኢን አፍሪካ” ስቴፈን ዝዌግ የተሰኘ ደራሲ በራሱ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ከጻፈው ልቦለድ መጽሐፍ ወደ ፊልም የተቀየረ ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከናዚዎች በመሸሽ ወደ ኬንያ ስለተሰደደ ቤተሰብ የሚተርክ ነው።

የጀርመን ፊልም በ4 ሺህ ሽልንግ መቼ፦ ሐምሌ 6 ቀን 2003 ዓ.ም የት፦ ሲኒፕሌክስ - ጋርደን ሲቲ- ከኡቹሚ ሞል በላይ ሶስተኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከምሽቱ አንድ ሰዓት የመግቢያ ዋጋ፦ አራት ሺህ ሽልንግ ብቻ

በሲኒማ ቤትፊልም

የጣፋጭ ኬክፌስቲቫል

የኬክ አፍቃሪ ለሆኑ እና ልጆቻቸውን ለማስደሰት ለሚፈልጉ ወላጆች ሁነኛ አጋጣሚ ነው። ብዙ ሀበሾች የኡጋንዳውያን ኬክ እንደ አገር ቤት አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ። በፌስቲቫል ደረጃ የሚዘጋጁት ኬኮች ግን ለየት እንደሚሉ ይገመታል። በቦታው ሄዶ ማረጋገጥ ነው።

መቼ፦ ቅዳሜ ሐምሌ 9 ቀን 2003 ዓ.ም የት፦ ኤሚን ፓሻ ሆቴል ሰዓት፦ ከቀኑ አራትሰዓት ጀምሮ ዋጋ፦ 20ሺህ ሽልንግ ለአዋቂዎች (ለህጻናት አምስት ሺህ)

የበጎ ፍቃደኞች ስብስብ የሆነ ፓታማንጎ የተባለ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት የአርጀንቲናንን ታንጎ ዳንስ ወደ ናይሮቢ አምጥቷል። ድርጅቱ ለጀማሪዎች የዳንስ ትምህርት ይሰጣል።

የአርጀንቲና ታንጎዳንስ መቼ፦ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የት፦ ኢጣሊያ ባህል ማዕከል- ዌስትላንድ- ከጃካራንዳ ሆቴል በተቃራኒ- ግሬንዳየር ታወር- አምስተኛ ፎቅሰዓት፦ ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል ዋጋ፦ በእያንዳንዱ የመማሪያ ቀን 500 ሽልንግ

Page 17: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 17

ፀጥ ረጭ ያለ ሰፈር፤ በግራ እና በቀኝ የተሰደሩት ቪላ ቤቶች ግዙፍ የጋራ በር አላቸው ፤ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ። አንድ የጥበቃ አባል በእነዚሁ የ

ቪላ ቤቶች የወል በር ላይ ቆሞ ገቢ ወጪ መኪናዎችን ይቃኛል። ፀጉረ ልውጥ መኪና እንዳይገባ በንቃት የሚከታተል ይመስላል። የጥበቃው ነገር በዚህ አያበቃም። ይባስ ብሎ እያንዳንዱ ቪላ ቤት በተናጥል የራሱ በርና በረኛ ተመድቦለታል። “የተሳካላቸው” ብቻ የሚኖሩበት መንደር መኾኑን ከአካባቢው የሚተነው ዝምታ የዋጠው አየር ያሳብቃል።በስተግራ አራተኛዋ ቪላ ቤት ግን የተለ

የ ባሕርይ ይታይበታል። የቪላ ቤቱ በር ገርበብ ተደርጎ የተተወ ነው። ደጅ ላይ ጥቂት መኪናዎች ተኮልኩለዋል። ይህ ቤት የሚታይ፣ የሚዳሰስ በረኛ የለውም። በውስጡ ግን ብዙ ዳሳሽ መዳፎች አሉበት። ለምሳሌ የጀሚላ ተዐምረኛ መዳፍ አንዱ ነው!

ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት . . .ወደ ውስጥ ሲዘለቅ ከሳሎኑ በራፍ ላይ የ

ተሰቀለው የእንግሊዝኛ ማስታወቅያ በደብዛዛ የአምፖል ብርሃን ውስጥ እንዲህ ይነበባል። “Close the door please! It is cold these days!” ሰሞኑን ይበርዳል! እባክዎ በሩን ይዝጉት! እንደማለት። በትንሹ ገርበብ ያለው የሳሎን በር ሲከፈት ቀጭኗ ኮሪደር “ሪሰፕሽን” የሚል ጽሑፍ ከአናቷ ወደተሰቀለባት ጠባብ ክፍል ታደርሳለች። በዚች ቀጭን ክፍል ደግሞ ሸንቀጥ ዘለግ ያለች ቆንጆ ተሰይማለች፤ ሕይወት ባለው ፈገግታ ተቀበለችን።“ምን ልታዘዝ?”ለደንቡ ነው እንጂ የምንፈልገውን ጠንቅ

ቃ ታውቀዋለች። አጠያየቋ በመረጃ እንደመጣን ለማረጋገጥ ያህል ነው። በዚህ ውድቅት መቼስ ማኅሌት ለመቆም እንዳልመጣን እኛም፤ እርሷም፤ ሰይጣንም እናውቃለን። ሻወር አስቀድመን መውሰድ እንደምንፈልግ ከጠየቀችን በኋላ ክፍሎቻችንን አመላከተችን። በቂ ፎጣዎች፣ የሻወር ጋውን እና ሌሎች የንጽሕና መጠብቂያ ቁሳቁሶችን የተሟሉ መኾናቸውን ዐሳየችን።“ሻወር ወስዳችሁ ስትጨርሱ አስተናጋጆ

ቻችሁ በየክፍላችሁ ይጠብቋችኋል! መልካም ምሽት!”የበረራ አስተናጋጆችን ዐይነት ቅልጥፍና

ይታይባታል። የሚዘናፈለው ፀጉሯ ወደፊት እየመጣ ሲያስቸግራት አንገቷን ወዝወዝ አድርጋ ትመልሰዋለች። ሌላ ጊዜ ደግሞ በጣቶቿ ሰብሰብ አድርጋ በጆሮዎቿ የኋሊት ትሰበስበዋለች። ከአፍታ በኋላ ፀጉሯ መልሶ ወደፊት ብትን ይልባታል። ዳግም ከአንገቷ ወዝወዝ ትልና ጆሮዎቿን ለሚበተነው ፀጉሯ እንደ ታኮ ትጠቀምበታለች፤ ዘንፋላው ፀጉሯ በጄ አይላትም። ዳግም አደብ ልታሲዘው ትሞክራለች።እንግዶችን በአንደበቷ ብቻ ሳይኾን በጥር

ሷ፣ በዐይኗ እንዲሁም በፀጉሯ መንከባከብን ታውቅበታለች። ሥራ የሚፈታ የሰውነት ክፍል የላትም፤ ዳሌዋን ጨምሮ።“ይቅርታ ሂሳብ ቅድሚያ ነው! በሰው

250 ብር!” የማሳረጊያ ንግግሯ ነበር።በሻማ ብርሃን “ማይም ተውኔት”

ሻወር በቅጡ መውሰዴ ትዝ አይለኝም። ኾኖም ቀጥሎ ለሚኾነው ነገር ጉጉት ያደረብኝ እንዳይመስል በሻወር ቤት ጥቂት ፀናሁ። ያውም ሥራ ፈትቼ።ወደ ተመደበልኝ ክፍል ስመለስ ጭልጭ

ል የሚል የሻማ ብርሃን፣ በጭልጭል የሻማ ብርሃን ውስጥ ደግሞ ለግላጋ ሴት፣ ከርሷ ሥር በአየር የተወጠረ እና ያበጠ የላስቲክ ፍራሽ ጠበቀኝ። መደናገጤን ዐይታ ነው መሰለኝ በከፊል ፈገግ አለች። ወይም ፈገግ ያለች መሰለኝ።“ሃይ! ጀሚላ እባላለሁ። ለምሽቱ አስተናጋ

ጅህ ነኝ” ቄንጠኛ ናት።“አመሰግናለሁ!” እያልኩ በነበረበት ቅጽበ

ት የሻወር ጋውኔን ገፈፈችው” በምትኩ መለመላዬን እንዳልቀር የማጣፋው ስስ ፎጣ ሰጠችኝ። ከሰከንዶች በኋላ “ፎጣውን ካልወደድከው መተው ትችላለህ” ስትል አበሰረችኝ። ኾኖም ፎጣው እንዲቆየኝ መረጥኩ።በሆዴ በአየር በተወጠረው የላስቲክ ፍራ

ሽ ላይ እንድጋደም ካዘዘችኝ በኋላ የተወሰኑ ሻማዎችን በማክሰም የክፍሉን ስልምልም ብርሃን ይበልጥ አደበዘዘችው። አሁን በዐይን ቋንቋ መግባባት ችግር ውስጥ ወድቋ

ል፤ የመግባቢያ ቋንቋው ወደ መዳፍ ተቀየረ። ጀሚላ በመዳፎቿ ታናግረኝ ጀመር። የማይም ድራማው ፊሽካ ተነፋ።እጅግ በስሱ የሚንቆረቆረው በመሣርያ ብ

ቻ የተቀነባበረ የሩቅ ምሥራቅ ሙዚቃ በምታቃስት የሴት ድምፅ ታጅቦ ከክፍሉ አንድ ጥግ ላይ በተገጠመ አነስተኛ “ስፒከር” እየተሞዘቀ ነው። ደብቅ ካሜራ በክፍሉ ውስጥ እንዳልተገጠመ በምን ርግጠኛ መዀን ይቻላል? የዚህ ቀስቃሽ ሙዚቃ የድምፅ ምጣኔ እውነትም ከሩቅ ምሥራቅ ከተከፈተ ቴፕ የሚሰማ ነው የሚመስለው። እጅግ ዝቅ ተደርጎ የተከፈተ ሙዚቃ!ልዩ መዓዛ ባለው የክሬም ቅባት በስሱ ት

ዳብሰኝ ጀመር። አስተሸሸቷ መታሸት ከሚለው ቃል ይልቅ መነካካት፣ መፈታተን እና መዳራት ለሚሉት ቃላት በጣሙን ይቀርባል። ቀጥላ የውስጥ እግሬን በረዣዥም ጥፍሮቿ መጠነቋቆል ጀመረች። በባለ መዐ

ዛው ክሬም ጀርባዬን ካሸችኝ በኋላ ከማጅራቴ ጀምሮ ቁልቁል በጥፍሮቿ እንደመቧጨር፣ እንደመቧጠጥ አደረገችኝ። ሰውነቴ ምላሽ ሰጠ።ትዕይንቱ በጀርባ ወደ መጋደም ተዛወረ።

የመሀል ጣቷን ጆሮዬ ውስጥ በመጨመር የተለየ ትርጉም ያለው መልእክት ልታስተላልፍልኝ ሞከረች። አንገቴ አካባቢ ጥሩ ስሜት የፈጠረብኝን አንዳች ነገር አድርጋ ወደ ደረቴ ተንደረደረች። ተመልሳ ደግሞ የመሀል ጣቷን በጆሮዎቼ በመጨመር ቀድሞ እንዳደረገችው ስሜቴን ለማናር ጣረች። የደረቴን ጡንቻዎች በስሜት ታሻቸው ጀመር። ከክሬሙ በቄንጥ በጣቷ ትጠነቁልና የደረቴ ጡቶች ላይ በማሳረፍ በጥፍሮቿ ጫፉን ብቻ እየነካካች ንዝረት ለመፍጠር ታተረች፤ ተሳካላት። ከዚህ በኋላ እኔን ፍፁም ረስታ ከደረቴ ጡቶች ጋር ጨዋታዋን አደራችው። ይህን ረዘም ላለ ደቂቃ ከቆየች

የአገር ቤት ጨዋታ

ቋንቋ በየፈርጁምራቂ

(ቦናሲ-Bonasi)

Vielezi vya wakati ቪኤሌዚ ቪያ- ዋካቲ -

የጊዜ ገላጮችHivi punde ሂቪ ፑንዴ - በጣም በቅርቡ (ወደፊት ጊዜን አመልካች ነው)Sasa hivi ሳሳ ሂቪ - ልክ አሁንLeo ሌኦ - ዛሬJana ጃና - ትናንትJuzi ጁዚ - ከትናንት ወዲያJuzi juzi ጁዚ ጁዚ - በቅርቡ (የአለፈ ጊዜን አመልካች ነው)Kesho ኬሾ - ነገKesho kutwa ኬሾ ኩቱዋ - ከነገ ወዲያMtondo ndogo ሙቶንዶ ንዶጎ - ከሶስት ቀናት በኋላMtondo ሙቶንዶ - ከአራት ቀናት በኋላZamani ዛማኒ - ከረጅም ጊዜ በፊት (የቆየ ጊዜን ለማመልከት)

የስዋሂሊ ቋንቋ ዳሰሳችንን ቀጥለናል። በመጀመሪያው እትማችን የመግባቢያ እና የሰላምታ ቋንቋዎችን ተመልክተናል። በሁለተኛው እትማችን ደግሞ የቁጥሮችን አጠቃቀም አይተናል። ለዛሬ ደግሞ ስዋሂሊ ተናጋሪዎች ጊዜን እንዴት እንሚቆጥሩ እን መለከትና እረፍት እናደርጋለን። ከሚቀጥለው እትም ጀምሮ በማዕከላዊ ኡጋንዳ በስፋት ስለሚነገረው የሉጋንዳ ቋንቋ ያጠናቀርነውን እናቀርባለን።

በስዋሂሊ ተናጋሪዎች ዘንድ የሰዓት አቆጣጠሩ ከአማርኛው ጋር ተመሳሳይ

ነው፡፡ ለምሳሌ ማለዳ ላይ እነሱም የሚጀምሩት አንድ ሰዓት ብለው ነው፡፡ የሳምንቱ ቀን ግን አንድ ተብሎ የሚጀምረው ከቅዳሜ ነው፡፡ ወሩ ደግሞ ከፈረንጆቹ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ከጥር ነው የሚጀምረው፡፡ በመሆኑም አዲስ ዓመታቸው ከጥር ይጀምራል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የጊዜ አቆጣጠሩን ከመመልከታችን በፊት ለቆጠራው የሚያገለግሉትን ቃላትና ትርጉማቸውን እናስቀድም፡፡

Asubuhi አሱቡሂ -ማለዳMchana ሙቻና - ቀን (ጊዜው ቀን መሆኑን ለማመልከት)Adhuhuri አዙሁሪ - እኩለ ቀን (ቀትር)Alasiri አላሲሪ - ከሰዓት በኋላ (ከስምንት እስከ ዘጠኝ ሰዓት)Jioni ጂኦኒ - ምሽትUsiku ኡሲኩ - ማታUsiku wa manane ኡሲኩ ዋ ማናኔ - ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ጊዜ Alfajiri አልፋጂሪ -ንጋት (አጠባብ)Mapambuzuko ማፓሙቡዙኮ - ንጋት

የሳምንቱ ቀናትJumamosi ጁማሞሲ- ቅዳሜJumapili ጁማፒሊ - እሁድJumatatu ጁማታቱ - ሰኞ

የዓመቱ ወራትJanuari ጃኑአሪ - ጥርFebruari ፌብሩአሪ - የካቲትMachi ማቺ - መጋቢትAprili አፕሪሊ - ሚያዝያMei ሜኢ - ግንቦትJuni ጁኒ - ሰኔJulai ጁላኢ - ሐምሌAgosti አጎስቲ - ነሐሴSeptemba ሴፕቴምባ - መስከረምOktoba ኦክቶባ - ጥቅምትNovemba ኖቬምባ - ህዳርDesemba ዲሴምባ - ታህሳስ

q Sikukuu likizo ሲኩኡ ሊኪዞ- የእረፍት ቀን q Krismasi ክሪስማሲ-ገናq Pasaka ፓሳካ- ፋሲካ q Mwaka Mpaya ሙዋካ ሙፓያ- አዲስ ዓመትq Siku ya kazi ሲኩ ያ ካዚ - የስራ ቀን q Liochelewa ሊኦቼልዋ- ማርፈድq Wakati upasao/siochelewa ዋካቲ ኡፓሳኦ/ሲኦቼሌዋ- ቀጠሮ ማክበር(አለማርፈድ)q Kutokuwako ኩቶኩዋኮ - መቅረትq kuja ኩጃ - መምጣት

Dakika ዳኪካ - ደቂቃSaa ሳአ - ሰዓትKasoro ካሶሮ - ሩብ ለሰዓት(ሩብ ጉዳይ፣ ከሩብ ለማለት)Siku ሲኩ - ቀንJuma /wiki ጁማ/ ዊኪ - ሳምንትMwezi ሙዌዚ - ወርMiezi ሚኤዚ - ወራትMwaka ሙዋካ- ዓመትSiku za wiki ሲኩ ዛ ዊኪ -

Jumanne ጁማኢኔ - ማክሰኞJumatano ጁማታኖ - ረቡዕAlhamisi አልሃሚሲ - ሐሙስIjumaa ኢጁማአ - አርብ Miezi za Mwaka ሚኤዚ ዛ ሙዋካ

n n n

n n n

በት በኋላ ድንገት ቁልቁል ተንደረደረች።ስሷ ፎጣዬ ደጀንነቷ አከተመ። በፈቃዷ

ተንሸራተተች። ሽምቅቅ አልኩኝ።“ታፍራለህ እንዴ!”እ . .!?“ታፍራለህ? የመጀመርያህ ነው?”“ኖ! ኖ !” ሽምጥጥ አድርጌ ዋሸኋት“ሻማ ትፈልጋለህ?”“አይ ይቅርብኝ!”በልቤ ግን የሻማውን ጥቅም ሳላውቀው ለ

ምን ተግደረደርሁ እያልሁ ነበር።ሻማ በዚህ ምስጢረኛ ቤት ሳሙና ኾኖ

እንደሚያገለግል አጫወተችኝ። “እየቀለጠ ያለ ሻማ የወንድ ሰውነት ላይ ሲፈስ መልካም ስሜት ይፈጥራል እኮ” አለችኝ። በቅላጩ የሻማ ጠብታ ስቃይ ውስጥ መልካም ስሜትን ለመፍጠር የሚደረግ ጥበብ ነው፡፡ እንደ ጀሚላ ማብራሪያ ብዙዎቹ የውጭ ዜጎች “የሻማ ስቃይ” ነፍሳቸው ነው። እነዚህ ደንበኞቿ፣ ላያቸው ላይ በሚቀልጠው የሻማ ስቃይ ውስጥ ደስታቸውን ያበራሉ። የውጭ ዜጎች ብቻ አይደሉም የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች፤ በስም ልትጠራቸው ያልፈቀደቻቸው ጥቂት ታዋቂ ሰዎችም የጀሚላ እና የሻማዋ ቋሚ ደንበኞች ናቸው።“አንዴ ከለመድከው ሻማ ሱስ ይኾናል”“እውነትሽን ነው?”ጭንቅላቷን በመነቅነቅ አዎንታዋን ገለ

ጸችከተሰጠኝ አጭር የሻማ ገለጻ በኋላ ነገሩ

ን መሞከር ፈለግኩ፤ ኾኖም አንዴ ይቅርብኝ ስላልኳት ዳግም ለመጠየቅ ኩራት ተናነቀኝ።

የተውኔቱ ጡዘት እና ፍጻሜጀሚላ በመዳፎቿ ካልኾነ ብዙ አታወራ

ም። ለጥያቄዎቼ ግን በሹክሹክታ አጠር ያሉ ምላሾችን ትሰጠኛለች። ብዙ ከማውራት ብዙ መሥራት ትመርጣለች። ለብር ሳይኾን ለሞያ ፍቅር የምትሥራ ነው የምትመስለው። ትኩረቷ ሰውነቴን ማናዘዙ ላይ ነው። ሥራውን ተክናበታለች፤ ዱባይ አንድ ዓመት ተኩል በግሏ ይህን አገልግሎት ትሰጥ እንደነበር ነገረችኝ። ከዚህ በላይ ስለራሷ ከመናገር ተቆጠበች። የእግሮቼን ጡንቻዎች በክሬም በማሸት እና በማሳሳብ ዘና ካደረገቻቸው በኋላ የእግር ጣቶቼ መሀል በመሀል ጣቷ እየገባች መልእክት ለማስተላለፍ ሞከረች። ዐይኖቼን በመጨፈን ምላሽ ለመስጠት ሞከርኩ።“መሳዥ ታደርገኛለህ?”“ማንን?”“እኔን!”‘እ!’ቤቱን ከጠቆሙኝ ሰዎች ይህ እንዳለ አል

ተነገረኝም ነበር፡፡“አልችልበትም ግን … ልሞክር?”“ሂሳብ ያስጨምርኻል”“ኸረ? ስንት?”“200 ብር…ለኔ ነው የምትሰጠኝ! ድርጅ

ቱ አያገባውም”ተስማማሁ። በነበርኹበት ኹኔታ አለመ

ስማማት አማራጭ አልነበረም። ሻሽ ላይነን ከመሰለ ጨርቅ የተሰራውን ስስ ጋውኗ

ን ጨምሮ ልብሶቿን አንድ በአንድ እያወለቀች በቄንጥ መስቀያው ላይ አንጠለጠለቻቸው። ጡት ማስያዣዋ እና የውስጥ ሱሪዋ እኔ እንዳወልቃቸው የተተው ናቸው።በዮጋ ዐይነት አቀማመጥ እግሮቿን አነባ

ብራ ተቀመጠች። በተራዬ ክሬሙን በስሱ እየጠነቆልኩ ከጀርባዋ ጀመርኋት። ጡት መያዣዋን እንድፈታላት ቀጠን ያለ ትዕዛዝ ሰጠችኝ። በጀርባዋም ኾነ በሆዷ ፍራሹ ላይ እንድትጋደም ያቀረብኩላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገችው። በሌላ አገላለጽ እርሷን ማሳጅ ማድረግ የምችለው ከወገቧ በታች ያለውን የሰውነቷን ክፍል ብቻ ነው። የውስጥ ሱሪዋም የማይደፈር ግዛቷን የሚያስከብር ዘብ እንደኾነ ተረዳኹ። ከዚያ ዉጭ ባለው ሰውነቷ መዳፌ እንደልቡ ጋለበበት። በተጣደፍኩ ቁጥር ዝግ እንድል ታስጠነቅቀኛለች። ኾኖም መዳፎቼ የተቀዳጁት ጊዜያዊ ሐሴት እጅግ ለአጭር ጊዜ የቆየ ነበር። ተስፈንጥራ በመነሳት የጡት መያዣዋን ትታ ጋውኗን ብቻ በመልበስ ከወገቡ አካባቢ ባለው መቀነት ሸብ አድርጋ አሰረችው።“ከዚህ በላይ መቆየት አይፈቀድም፡፡”ለአንድ ሰዓት ያህል የቆየው ጫዎታችን እ

የተጠናቀቀ መኾኑን አረዳችኝ።ኾኖም አንድ የማሳረግያ ትዕይንት እንደ

ቀረ ገብቶኛል። እየናረ ለነበረው ወንድነቴ መፍትሄ እንድትሰጠኝ ተማፀንዃት።“ያስጨምርኻል!”“ኸረ! ስንት!”“መቶ ብር! ድርጅቱ አያገባውም ለኔ ነው

የምትሰጠኝ፡፡”ለድርድር የሚበቃ አቅም አልነበረኝም።የጀሚላ መዳፎቿ የደረሱበትን የመጨረሻ

ው የዳሰሳ ጥበብ ተጠቅመው ለስሜቴ ጊዜያዊ ምላሽ ሰጡ።ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አልን!ሻወር ቤት ስገባ ቆሻሻ ውስጥ የምጥላቸ

ውን የሶፍት ወረቀቶች ሰብስባ የሻወር ጋውኔ ኪስ ውስጥ ሞጀረቻቸው። የሶፍት ወረቀቶቹን መታጠብያ ቤት መጣል እንዳልረሳ ባልጠበቅኹት ኹኔታ አጥብቃ አስጠነቀቀችኝ። ለምን ይህን ያህል አሳሰባት!?ልብሶቿን ከመስቀያው አውርዳ በጥድፊ

ያ ከለባበሰች በኋላ ድርጅቱ አይመለከታቸውም ያለችኝን ለእርሷ የሚገቡ ክፍያዎች እንድፈጽም የኪስ ቦርሳዬን አቀበለችኝ። ሦስት የመቶ ብር ኖቶችን ሰጠኋት።“ደንበኛ እንኾናለን! ሌላ ጊዜ ስትመጣ ለ

ሪሴፕሽኖቹ ጀሚላ ብለህ ንገራቸው።”በሩን ከፍታ ከመውጣቷ በፊት ልብሶቿ እ

ንዳልተዛነፉ ለመጨረሻ ጊዜ ርግጠኛ ለመኾን ሞከረች።“እኔ ምልሽ?”“አቤት!”“ጀሚላ ምን ማለት ነው?”“ቆንጆ ወይዘሪት . . .”ክፍሉ ውስጥ ብቻዬን ቀረሁ። ስሜት ቀስ

ቃሹ ሙዚቃ አልተቋረጠም። ክፉኛ የጥፋተኝነት ስሜት ኅሊናዬን ሲበረቅሰው ተሰማኝ። ክፍሉን ለባለተረኛ ዳሳሽና ተዳሳሽ መልቀቅ ነበረብኝ . . .

የጀሚላ መዳፎች

ፎቶ

- ከድ

ርጅቱ

ድረገ

አሮን ፀሐዬ

አዲስ ነገር ኦንላይን

ፎቶ

- ኢ

ዚ ላ

ይፍ

ድረ

ገጽበአዲስ አበባ እንዲህ 24 ሰዓት የማሳጅ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እየተስፋፉ ነው

Page 18: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና18

ካምፓላ ሜንጎ የሚገኘው የባጋንዳ ብሔር ንጉስ (ካባካ) ነጭ ቤተመንግስት በተለምዶ የሚያረብበት ጸጥታ ዛሬ የለም። ን

ጉሳቸውን የወንዶች ሁሉ የበላይ (ሳባሳጃ) ብለው ለሚጠሩት ባጋንዳዎች ዛሬ የሀዘን ቀን ነው። ሜይ 24። በዚህ ቀን ነበር የቀድሞው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚልተን ኦቦቴ በባጋንዳ ታሪክ መዝገብ ላይ በሀዘን የሰፈረ ጭፍጨፋ ያከናወኑት። ከልጅ ልጅ ለሚወራረሰው የባጋንዳ ንጉሳዊ ስርዓት ወደ ሃይማኖታዊ አምልኮ የሚጠጋ አመለካከት ያላቸው ባጋንዳውያን ከ45 ዓመት በፊት ያኔ ዙፋን ላይ የነበሩትን የአሁኑን ካባካ አባት ከሞት ለማዳን መስዋዕትነት የከፈሉበት ቀን ነው። አንድ ሺህ የሚጠጉ ባጋንዳውያን የተገደ

ሉበትን ያን ቀን ለማሰብ የባጋንዳ ብሔር አባላት በባለ ግርማ ሞገሱ ነጭ ቤተመንግስት ተሰባስበዋል። በሀዘን ጊዜ እንደሚያደርጉት ሁሉ ከዛፍ ቅርፊት የተሰራ (ባርክ ክሎዝ) ልብስ ለብሰዋል። ቀኑን ለመዘከር በቤተመንግሥቱ ደጃፍ የተሰባሰቡት ሰልፈኞች የኀዘን ሙዚቃ በሚያሰሙ አዳጊዎች አጃቢነት በካምፓላ ጎዳናዎች ለመዘዋወር እስኪነሱ ድረስ ወደ ቤተመንግሥቱ ለመግባት የማይሞከር ነበር። ባጋንዳዎች “ኦሉቢሪ ዋካባካ” እያሉ የሚጠሩት ቤተመንግስት በር በሰዎች ታጥሯል። ከቤተመንግስቱ ቀጠሮ አለኝ። ቀጠሮዬ

ጭፍጨፋው ሲካሄድ በቦታው ከነበሩ እና ካባካውን በህይወት ከአገር እንዲሸሹ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱ ሰው ጋር ነው። ሻለቃ አብርሃም ሳንኮማ ይባላሉ። የ

ካባካው የክብር ዘብ አባል እንደነበሩ ተነግሮኛል። ታሪክ ለመስማት ጓጉቼያለሁ። በስተመጨረሻ ወደባለግርማው ግቢ ዘለቅሁ። ሻለቃ አብርሃም ወዳሉበት ክፍል ጠቆሙኝ። ከውጭ ቆሜ በር ስቆረቁር በባሕላችን እንግዳን ወደ ቤታችን እንዲገባ የምንጋብዝበት አስደሳች ቃል ወደ እኔ ሲወረወር ሰማሁ። “ይግቡ! እንኳን ደኅና መጣህ”። ‘የሰማሁት የአማርኛ አረፍተ ነገር ነው አይደል?’ ራሴን ጠየቅሁ። በእርግጥም አማርኛ ነበር። የሻለቃ አብ

ርሃም ጥርት ያለ አማርኛ ከቤተመንግሥቱ ላይ አልነቀል ላለው ቀልቤ ጥሩ ማባነኛ ነበር። ወደቢሯቸው ስገባ አንድ ሙዚቃ ይሰማኝ ነበር። ግን በቅጡ አላደመጥኩትም ነበር። ሻለቃ አብርሃም በመቀመጫቸው ላይ ራሳቸው ካመቻቹ በኋላ ወደሚወዘውዙበት ሙዚቃ አመላከቱኝ። “ምነው ፊትህን አዙረህ ተቀመጥክ?” አሉኝ። ወይ ጉዴ! ለካንስ የሚያስደንቁ ነገሮች አላለቁም። የሻለቃ አብርሃም ኮምፒውተር የሚያጫ

ውተውን ሙዚቃ አውቀዋለሁ። አረ! ማወቅም ብቻ አይደል። ስሰማው ተብረከረኩ። “አለምዬ ሶራ፤ ሶራ ሶራ!”። ‘የት ነው ያለሁት?’ ጥያቄዬ ቀጥሏል። ምንም አስገራሚ ነገር እንዳልተፈጠረ ሁላ ሻለቃ አብርሃም ያናግሩኝ ይዘዋል። አማርኛቸውን ስላላመኑት ይመስላል እንግሊዝኛ ጀምረዋል። የኮምፒዩተሩን ስክሪን የሞሉት ትከሻቸው እስክስታ የሚመታ ሳይሆን የሚርገብገብ የሚመስል ሰዎች በጣታቸው እያሳዩኝ “Look at this! This takes me back to Addis!” አሉኝ። አንገቴን በመስማማት ነቀነቅኩ። በስንቱ ተደንቄ እች

ልበስ እንኳ የሚችልባት ብቸኛዋ የአፍሪካ አገር ኢትዮጵያ ነበረች። ልቡ ተሸነፈ።ናይሮቢ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባ

ሲ አቀና። በወቅቱ በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን አቶ ጌታቸው መካሻን አግኝቶ ያለውን ፍላጎት ገለጸ። በተመሳሳይ ኹኔታ ጥሪውን ተቀብለው የመጡ አፍሪካውያን ወጣቶች በዚያ ነበሩ። ወጣቶቹ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከጋና፣ ከናይጄሪያ እና ከኡጋንዳ የተውጣጡ ነበሩ። የመግቢያ ፈተና ወስደው ካለፉ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንዲሔዱ ተነገራቸው። እ.ኤ.አ ጥር 1960 አዲስ አበባ እንደደረ

ሱም በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በአቶ ከተማ ይፍሩ የሚመራ አንድ ቡድን ቃለመጠይቅ አደረገላቸው። በኢትዮጵያ ሊያገኟቸው የሚችሏቸውንም የትምህርት እድሎች ጨምረው ነገሯቸው። “ምን መማር ትፈልጋለህ?” የሚለው ጥያቄ አንዱ ነበር። አብረዋቸው የነበሩትን ወጣቶች ምኞት እውን ያደረገችው ኢትዮጵያ አብርሃምንም ምኞቱን አልነፈገችውም። ከሁሉ በላይ ወጣቱን አብርሃም ያስደነቀው የምላሹ ፍጥነት ነበር። አብረዋቸው ከነበሩት የእድሉ አሸናፊዎ

ች መካከል አንዱ ሕክምና አንዱ አውሮፕላን አብራሪነት እንደመረጡ ወዲያው ወደሚመለከታቸው ትምህርት ቤቶች ተላኩ። “እኔ ወታደራዊ ሳይንስ መማር እንደምፈልግ ስናገር ይህን ትምህርት ለምን እንደመረጥኩ ተጠይቄ ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም ለጥያቄው የሰጡትንም ምላሽ ያስታውሳሉ። “አፍሪካን ነፃ ለማውጣት!” ነበረ ምላሻቸው። “ብዙም ሳይቆይ ያለንበት ድረስ በወታደራዊ አለባበስ የተንቆጠቆጡት

ከሐረር ጦር አካዳሚጄኔራል ገብረሥላሴ ያሉበት የወታደር ጂፕ መኪና መጣ” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም መጀመሪያ የተፈጠረባቸውን ስሜትም ያስታውሳሉ። “ምን ተፈጠረ ታሰርኩ እንዴ!” የሚል ድንጋጤ እንደተሰማቸውም ሲያስታውሱ ፈገግ ይላሉ።

እነኛ የአደሬ ሴቶች…ሻለቃ አብርሃም እንደ እርሳቸው ሁሉ ከ

ተመለመሉ 49 ተማሪዎች ጋር በመኾን ወደ ሐረር ለመጓዝ የ60 የኢትዮጵያ ዶላር ተቀበሉ። ያኔ የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዳሁኑ ብር ሳይሆን ዶላር ነበር። ወደ ሐረር አብረዋቸው ይጓዙ የነበሩት ተማሪዎች ምን ሲሉዋቸው እንደነበረም ያስታውሳሉ። “ከየት ነው ደግሞ አንተ የመጣኸው? ለምን አገርህ አትማርም ነበር? እዚህ አገር ወታደር ኾነህ መሞት ትፈልጋለህ?” ከየአቅጣጫው የሚወረወሩ ጥያቄዎች ነበሩ። የአብርሃም ኹኔታ ለሌሎቹ የሐረር የጦር አካዳሚ ምልምሎችም ጥያቄ የፈጠረ ነበር። በጦር አካዳሚ ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ከሚሄዱ ምልምሎች መካከል ከእናቶቻቸው ተላቅሰው የተለያዩ ነበሩ። ይህ ሁኔታ አሁንም ድረስ ለሻለቃ አብርሃም ግርምትን እንደፈጠረባቸው አለ። እርሳቸው የገቡበት ኮርስ ሶስተኛው ዙር

ቢሆንም ሐረር የጦር አካዳሚ በነበሩ ጊዜ ግን ቀድመዋቸው ከገቡት የአንደኛ እና የሁለተኛ ኮርስ ተማሪዎች ጋር አብሮ የመቆየት እድል ገጥሟቸው ነበር። በወቅቱ አስተማሪ የነበሩት ደግሞ ህንዳውያን እና የሆለታ ገነት ምሩቅ ኢትዮጵያውያን መኮንኖች ነበሩ። “ስልጠናው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም ትምህርቱ በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎ

ች ይሰጥ ስለነበር አስቸጋሪ እንዳልሆነባቸው ያስረዳሉ። ምንም እንኳን አብረዋቸው የቆዩት ስድ

ስት ወር ብቻ ቢኾንም ከመካከላቸው ጄኔራል አበበን እና ጄኔራል ሙሉጌታን ያስታውሳሉ። በሁለተኛው ምድብ ከገቡት እጩ መኮንኖች መካከል በኋላ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ከነበሩት መካከል፤ ጎሹ ወልዴን፣ ፍሰሐ ደስታን ከነበራቸው ቅርርብ ጭምር ያስታውሷቸዋል። “ጎሹ የቅርብ ጓደኛዬ ነበር፣ ፍሰሐን የማስታውሰው ባስተማረኝ ጥቂት የትግርኛ ቃላት ነው” ይሉና ቃላቱን ያስታውሳሉ “ከመይለኻ፣ ጽቡቅ…”። ብርሃኑ ባየህንም “በመጠኑ ኩሩ ጎንደሬ ነበረ” እያሉ ትዝታቸውን ያካፍላሉ። ሻለቃ አብርሃም የተማሩባትን ሐረርን በ

ጣም እንደወደዷት ይናገራሉ። ሐረርን ለምን እንደወደዷት ሲናገሩ የድምፃቸው ከፍታ ይጨምራል። “አየሩ ተስማሚ ነው፣ የሴቶቹ ውበት!። እነኛ የአደሬ ሴቶች በጣም ውብ ነበሩ። ቋንቋ ባያግደኝ ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር! በዚያ ላይ ጥሩ የፍራፍሬ አገር ነበር” እያሉ ምክንያቶችን ይደረድራሉ።

ኡጋንዳዊው በጎጃምስልጠናቸውን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ

ያጠናቀቁት ሻለቃ አብርሃም ከምረቃው በኋላ ፈተና ገጠማቸው። በወቅቱ ኡጋንዳ ገና ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ያልወጣች በመኾኗ ወደ አገራቸው መመለስ እንደማይችሉ ታወቃቸው። ይህንን የሚያውቁት ብዙዎቹ ጓደኞቻቸውም እዚያው በኢትዮጵያ እንዲቀሩ መከሯቸው። “ዩጋንዳ በቅርቡ ነፃ ትወጣለች። እስከዚያው ድረስ እዚህ ቆይ” የወዳጆቻቸው ምክር ነበር። ምክሩን ሰምተው ኢትዮጵያ ቀሩ። እንደሌሎቹ ምሩቃ

ላለሁ!ስለ ባጋንዳ ንጉስ የነበሩኝን ጥያቄዎች ለ

ጊዜው ወደ ጎን አድርጌ ሻለቃ አብርሃም አንዴት እንዲህ ከኢትዮጵያ ጋር እንደተቆራኙ እንዲያጫውቱኝ ጠየቅኋቸው። ፊታቸው ላይ ደስታ እየተነበበ አመታት ወደ ኋላ ተመለሱ። ወደ ወጣትነታቸው ዘመን። ነገርን ከስሩ…..

ታሰርኩ እንዴ!”የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው

ወጣቱ አብርሃም በሁለት ምርጫዎች መካከል ልቡ ተከፍሏል። በአንድ በኩል እንደማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ወጣት ማኬሬሬ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን መቀጠል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የንክሩማህን የአንዲት አፍሪካ (pan Africa) ሐሳብ በመቀበል አፍሪካን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ መሳተፍ እንደምርጫ ቀርበውለታል። አብርሃም የወጣትነት ልቡ ወደ ሁለተኛው አማራጭ አዘነበለ። የተባበረች አንዲት አፍሪካን እውን ለማድረግ እንደሚያስችል ባመነበት ትግል ለመሳተፍ ወሰነ። እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገው ደ

ግሞ ናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወጣ ማስታወቂያ ነበር። እ.ኤ.አ በ1959 የተላለፈው ይህ ማስታወቂያ በመላው አፍሪካ ለሚገኙ ወጣቶች የተሰጠ “የቀዳማዊ “ኃይለሥላሴ ስኮላርሺፕ” እድል ነበር። ከዚህ በፊት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የተነሱትን ፎቶግራፍ ያየው አብርሃም ይህን የመሰለ እድል በቅኝ አገዛዝ በተያዙት ሌሎች የአፍሪካ አገሮች እንደማይሞከር ያውቅ ነበር። አንድ ጥቁር ወታደራዊ የማዕረግ ልብስ መ

ፎቶ

- መዝ

ገቡ ኃ

ይሉ

ፎቶ

- መዝ

ገቡ ኃ

ይሉ

አንድ ሺህ የሚጠጉ ባጋንዳውያን የተገደሉበትን ቀን ሜይ 24 ለማሰብ የባጋንዳ ብሔር አባላት በሀዘን ጊዜ እንደሚያደርጉት ሁሉ ከዛፍ ቅርፊት የተሰራ ልብስ ጭምር ለብሰው በካባካ ቤተመንግስት ተሰባስበው ነበር

ሐረር የተማሩት ሻለቃ አብርሃም ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ጊዜ ጀምሮ የካባካ የክብር ዘብ ሆነው በቤተመንግስት ውስጥ ይሰራሉ

ባጋንዳዎች “ኦሉቢሪ ዋካባካ” እያሉ የሚጠሩት ነጩ የካባካ ቤተመንግስት ከእነ ግርማ ሞገስ በካምፓላ ሜንጎ ተንጣሎ ይገኛል

በመዝገቡ ኃይሉ

በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

ትዝታ

Page 19: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 19

አተረፈላቸው። ካባካውን ካስመለጡበት ኬንያ ታስረው በኡጋንዳውያን ፖሊሶች ተመረመሩ። ለካባካው ታማኝ የነበሩት ሻለቃ አብርሃም ግን ምንም ትንፍሽ አላሉም።

“ጆሮ ጠቢ ኾንኩ!”ከእስር እንደተፈቱ በወቅቱ ለደህንነታቸ

ው አስጊ ከነበረችው ከአገራቸው ከኡጋንዳ ይልቅ ወደ ሁለተኛ ቤታቸው ወደ ኢትዮጵያ ፊታቸውን አዞሩ። “ወደጃንሆይም ቀርቤ ወደ እናት ክፍሌ እንዲመልሱኝ ጥያቄ አቀረብኩ” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። ጥያቄአቸው ግን አዎንታዊ ምላሽ አላገኘም። ምክንያቱም ከሻለቃ አብርሃም የተሰወረ አልነበረም። “ፋይሌ ተዘግቶ አልተሰናበትኩም” እያሉ መከራከሪያ ቢያቀርቡም ጉዳዩ ለጃንሆይ ቀላል አልነበረም። “ጃንሆይ በእኔ ምክንያት ከኡጋንዳ መንግ

ሥት ጋር መቃረን አልፈለጉም ነበር” ይላሉ አብርሃም። ግን ጃንሆይ ጥለው አልጣሏቸውም። “ይህ የእኛ ሰው ነው በማለት በተባበሩት መንግስታት ጽሕፈት ቤት ውስጥ በደህንነት ሰራተኝነት እንድቀጠር አደረጉኝ” ሲሉ የጃንሆይን ገለታ ያወሳሉ። “በእርግጥም አማርኛ ማወቄ ሥራውን በቀላሉ እንድሰራው ረድቶኛል” ይላሉ አብርሃም አስቂኙን የአማርኛ የደህንነት ስም እያስታወሱ። “ጆሮ ጠቢ ኾንኩ!”። በዚህ ዙር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵ

ያ ቤት ንብረት እንዲያፈሩ አድርጋቸዋለች። ከዚያም ከፍ ባለ ኢትዮጵያዊት ሚስትም አግኝተዋል። የሻለቃ አብርሃም ባለቤት ወይዘሮ መሠረት ገብረጻድቅ ይባላሉ። እ.ኤ.አ ከ1978 ጀምሮ ተጋብተው እስካሁንም በትዳር ዓለም አብረው አሉ። ይህም ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ያጠናከ

ትዝታ

እስከ ካባካ ቤተመንግሥትን ሁሉ እርሳቸውም ምድብ ክፍል እና ደሞዝ ተቆረጠላቸው። ያስተማረቻቸውን ኢትዮጵያን በውትድርና ለማገልገል ጎጃም ሁለተኛ ክፍለ ጦር ውስጥ በአሰልጣኝ መኮንንነት ተመደቡ።“ብዙም አማርኛ ስለማልችል የማሰለጥነ

ው ሰልፍ ነበር” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። “ለሰልፍ እና ለስፖርት ስልጠና የሚኾኑትን የአማርኛ ቃላት በደምብ ስለማውቃቸው በቀላሉ ነበር ሥራውን የለመድኩት” ይላሉ። አሁንም እነዚህኑ የትእዛዝ ቃላት ከነቅላፄያቸው በደምብ ያስታውሷቸዋል። “አሳርፍ! ተጠንቀቅ! ወደፊት ሒድ!”። እዚያው ጎጃም እያሉ ነበር የህይወታቸውን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን መልዕክት የደረሳቸው። “በዚሁ ምድብ ሥራዬ ላይ እንዳለሁ አን

ድ ቀን በሄሊኮፕተር የመጡ ክቡር ዘበኞች በአስቸኳይ አስጠሩኝ” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም፤ በአስቸኳይ ጃንሆይ ቤተ መንግሥት እንዲደርሱ የተጠሩበትን ሁኔታ ይተርካሉ። “የማእረግ ልብሴን እንደለበስኩ ወደ ሄሊኮፕተር ስጣደፍ አንዳንዶቹ ጓደኞቼ ለሹመት ልጠራ ለፍርድ ስላልገባቸው በጥያቄ ያጣድፉኝ ጀመር። አንዳንዶቹ ‘ምን አድርገህ ነው?’ ሲሉኝ ሌሎቹ ደግሞ ‘ከተሾምክ እንዳትረሳን’ ይሉኝ ነበር።” አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ሲደርሱ ያልጠረጠሩት ነገር ገጠማቸው። ጃንሆይ ብቻቸውን አልነበሩም። የባጋንዳ

ው ሥርወ መንግሥት የወቅቱ ንጉሥ ካባካ ሙቴሳም አብረዋቸው ተቀምጠው ነበር። “ካባካው በሉጋንዳ ስሜን እና ጎሳዬን ጠየቁኝ” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። በኋላ እንደሰሙት የእርሳቸውን እዚያ መኖር አን

ድ ሰው ተናግሮ ስለነበረ ይህን ለማጣራት ነበር የተጠሩት። “ካባካው ከመደነቃቸው በላይ ጥርጣሬም የነበራቸው ይመስላል” ይላሉ ሻለቃ። “ምክንያቱም ካባካው እኔ በእንግሊዝ የተላኩ ሰላይ አለመኾኔንም ለማጣራት ጥያቄዎች ይጠየቁኝ ነበር።” ካባካው ሻለቃ አብርሃምን ጥቂት የፈተ

ነ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር። ጥያቄው “ተመልሰህ አገርህን ለማገልገል ፈቃደኛ ነህ ወይ?” የሚል ነበር። “ደሞዝ ሳልቀበል፣ እንዲያው ሳልዘጋጅ ይዘውኝ ሊሄዱ ነው?” ብለው ሀሳብ ቢገባቸውም ያለማቅማማት መልስ ሰጡ። “እንዴታ ካባካ ምን ገዶኝ!”። የውስጣቸውን በውስጣቸው እንደያዙ የሰጡት መልስ ነበር። የያኔው የመቶ አለቃ የአሁኑ ሻለቃ አብ

ርሃም እንደፈሩት ያኔውኑ ወደ ኡጋንዳ አልተመለሱም። በአንድ ቀጭን ትእዛዝ ወደመጡበት ክፍላቸው እንዲመለሱ ተደረገ። “የመቶ አለቃ አብርሃምን ወደክፍላቸው መልሷቸው!”። ነገር ግን አንድ ተስፋ ከካባካው ተሰጥቷቸው ነበር። “ከነፃነት በኋላ እንጠራህና ወደአገርህ ትመጣለህ”። የማይታጠፈው የካባካ ሙቴሳ ቃል ነበር፤ ከባለ ግርማው የአራት ኪሎው ቤተ መንግሥት።

የጃንሆይ “አጃቢ”እ.ኤ.አ በጥቅምት 1962 ዩጋንዳም ቀን ወ

ጣላት። በገዛ ልጇ በካባካ ሙቴሳ ፕሬዚዳንትነት እንድትመራ ተደርጋ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ወጣች። በንጉሡም በዓለ ሲመት ላይ እንዲገኙ በክብር እንግድነት የተጠሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴም በባለሥልጣኖቻቸው አጃቢነት ወደ ኡጋንዳ ሊሄዱ ተነሱ። ጃንሆይ ወደ ኡጋንዳ ሲመጡ

ሄድ እና ተዘጋጅቼ እንድመጣ ይፈቀድልኝ” አሉ። ተፈቀደላቸው። የመልስ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ፤ ለማይቀረው የእናት አገር ጥሪ ዝግጅት!

የቁርጥ ቀንኢትዮጵያን ተሰናብተው ወደ ኡጋንዳ የ

መጡት ሻለቃ አብርሃም በካባካው የክብር ዘብ ውስጥ ተመደቡ። ለአራት ዓመት ካባካውን በታማኝነት እንዳገለገሉ ፈታኙ የቁርጥ ቀን መጣ። የካባካውን እውነተኛ ሰው ማንነት የሚፈትነው ችግር! አብርሃም ሳንኮማም ፈተናውን በቆራጥነት ለማለፍ ወደ ኋላ አላሉም። ህይወታቸውን እስከ መሥዋዕትነት በመሥጠት ፕሬዚዳንታቸው እና ንጉሣቸው የጣሉባቸው እምነት ትክክለኛ መኾኑን አስመሰከሩ።ነገሩ እንዲህ ነው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒ

ስትር የነበሩት ሚልተን ኦቦቴ ከፕሬዚዳንቱ ካባካ ሙቴሳ ጋር የነበራቸው አለመግባባት ጦዞ ወደ መበጠሱ ደረሰ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን በኃይል ለመፍታት ሞከሩ። እ.ኤ.አ ሜይ 24 ቀን 1966ም ወታደሮችን ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት በመላክ ድንገተኛ ጥቃት ከፈቱ። የንጉሡ የክብር ዘቦች ጥቃቱን በመከላከል ንጉሡን ለማትረፍ የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ። ሻለቃ አብርሃም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነበሩ። ሻለቃ አብርሃም በወቅቱ የነበራቸው ሚ

ና ንጉሡን በስውር በር በማስወጣት በ“ናሚሬምቤ” የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መደበቅ ድረስ ይሄዳል። በኋላም በጀልባ ወደ ሞምባሳ እንዲያመልጡ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ይህ ጀብዱ በህይወታቸው ከሚኮሩባቸው ተልዕኮዎች ቁንጮው ሳይሆን አይቀርም። ሆኖም ጀብዷቸው እስርን

ሩበት ሌላው ማሰሪያ ነበር። ከባለቤታቸውም ሁለት ልጆች የወለዱ ሲ

ኾን የመጀመሪያ ልጃቸው የዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነች። ልጆቻቸው አማርኛን አቀላጥፈው እንደሚናገሩ የሚገልጹት ሻለቃ አብርሃም በዚህም ምክንአት አንዳንድ ጊዜ ሚስጥር እንደሚያልፋቸው ይናገራሉ። “ ‘እናንተ ቅድም ምንድነው ለእናታችሁ የነገራችኋት’ እያልኩ ስቆጣ ሁሉም ይስቁብኛል” እያሉ እርሳቸውም ይስቃሉ። ሻለቃ አብርሃም አዲስ አበባ ገርጂ አካባ

ቢ ቤት እንዳላቸው ይናገራሉ። “አቤት አሁንኮ ሰፈሩ ሁሉ ተቀይሯል!” እያሉ ያፏጫሉ የትውልድ ቀዬአቸውን እንደሚያስታውሱ ሁሉ። ቤት የሰሩበትን ቦታ የገዙበትን ገንዘብ ትንሽነት ያደንቃሉ። “45 ሺህ ብር! አሁን በዚህ ዋጋ መሬት ማግኘት የማይታሰብ ነው።”ሻለቃ አብርሃም የሁለተኛ አገራቸው ትዝ

ታ የሚወዘውዛቸው ዓይነት ናቸው። “አብረውኝ የሰለጠኑት ጓደኞቼም አዛዦቼም ወደ ኡጋንዳ ስመጣ ደጋግመው የነገሩኝ አንድ ነገር ነበር ‘ኢትዮጵያ አገርህ ናት። ኢትዮጵያን እንዳትረሳ‘ ብለውኝ ነበር” ይላሉ። ሻለቃ አብርሃም ምላሻቸው ጥያቄም መልስም ነበር። “ኢትዮጵያን እንዴት እረሳታለሁ?!”።በእርግጥም አልረሷትም። ከሶስት ዓመት

በፊት ገበያ ላይ የዋለው የገጠሪቱ ኢትዮጵያን ዘፈን እያደመጡ በሀሳብ ይነጉዳሉ። ሻለቃውን ተሰናብቼያቸው ወጣሁ። “አለምዬ ሶራ!” እየሸኘኝ ነበር። በ“ባሲማ ኡጌንዜ” ፋንታ “አለምየ ሶራ”! ለዚያውም በካባካው ቤተ መንግሥት!

የመቶ አለቃ አብርሃንም አልረሷቸውም። “ከንጉሡ ባለሥልጣኖች ጋር በአንድ አ

ውሮፕላን በርረን ኡጋንዳ ደረስን” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም በኩራት። የዚያን ጊዜው ደስታቸው ከፊታቸው ላይ ይታያል። ኃይለሥላሴን አጅበው መምጣታቸውን እስካሁንም በኩራት ይናገሩታል። “እንደመጣን ያረፍነው አሁን ፓርክ ሆቴል ተብሎ በሚታወቀው የያኔው ሮያል ሆቴል ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም እንዴት ቤተሰቦቻቸውን እንዳገኙ ሲተርኩም በተመስጦ ነው።“ቀዳማዊ ኀይለሥላሴን አጅቤ በበዓለ ሲ

መቱ ላይ ስገኝ የብዙ ኡጋንዳውያን ቀልብ በእኔ ላይ አርፎ ነበር” ይላሉ አብርሃም። በቦታው ከነበሩት ሰዎች መካከልም አንድ ሰው ወደ እርሳቸው መጥቶ “አንተ ሳንኮማ አይደለህም እንዴ?” ሲል እንዳስታወሳቸው ይገልጽላቸዋል። “ያም ሰው የእኔን መምጣት ለመንደሬ ሰዎች ሁሉ አዳረሰው” ይላሉ ሻለቃ። ብዙም ሳይቆዩ ከካባካው ፈቃድ ተቀብለው ለረጅም ጊዜ የተለዩዋቸውን ቤተሰቦቻቸውን የማየት እድል አገኙ:፡ “ካባካው ቀድመው የጠየቁኝን ጥያቄ በድጋሚ ያቀረቡልኝም ከዚያ በኋላ ነበር” ሲሉ የእናት አገራቸው ጥሪ እንዴት እንደደረሳቸው ያስታውሳሉ። ካባካው “እኛ አሁን የምታገኘውን ያህ

ል ደሞዝ ልንከፍልህ አንችልም። መጥተህ ግን አገርህን እንድታገለግል እንፈልጋለን” ይሏቸዋል። አብርሃም በካባካው ንግግር ስሜታቸው ተነካ። እምቢ ሊሉት የማይችሉት ጥያቄ ነበር። ነገር ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ አቀረቡ። “አሁን ድንገት ነው ተጠርቼ የመጣሁት። ተመልሼ እንድ

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በካባካ ሙቴሳ በዓለ ሲመት ላይ በክብር እንግድነት ሲገኙ የመቶ አለቃ አብርሃንም አስከትለው ነበር

ሻለቃ አብርሃም ከአገራቸው ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ በተመለሱ ወቅት በጃንሆይ አማካኝነት በተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት የደህንነት ሰራተኛ ሆነው ተቀጥረው ነበር

ወጣቱ አብርሃም የሐረር ጦር አካዳሚ ካፈራቸው ወታደራዊ መኮንኖች አንዱ ነው ከሻለቃ አብርሃም ጋር በሐረር ጦር አካዳሚ ከተማሩት መካከል እንደ ብርሃኑ ባየህ ያሉት (በፎቶው መነጽር ያደረጉት) በስተኋላ ላይ የመንግስት ባለስልጣን ሆነዋል

ፎቶ

ዎች

- ከሻለ

ቃ አ

ብርሃ

ም ስ

ብስቦ

ፎቶ

- መዝ

ገቡ ኃ

ይሉ

Page 20: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና20

ሐበሻ በምስራቅ አፍሪካውያን ዓይንጋታንጋ አሌክስ በጎ ፈቃደኛ የማህበራዊ

አገልግሎት ሰራተኛ ነው፡፡ የዛሬ መኖሪያው ካምፓላ ይሁን እንጂ ትውልዱ ምዕራብ ኡጋንዳ ከሚገኝውና ኪሶሮ ከሚባለው ስፍራ ነው፡፡ ይህም ቢሆን አሌክስና እናት አባቶቹ የተወለዱበት እንጂ የአያት ቅደመ አያቶቹ እትብት የተቀበረበት ቦታ እንዳልሆነ አሌክስ ይናገራል፡፡ አሌክስ የአያት ቅደመ አያቶቹን መነሻ ሲያስብ ትዝ የምትለው ኢትዮጵያ ነች፡፡ እርሱ ሩዋንዳውያንም ሆኑ ኡጋንዳውያን (በተለይ ዛሬ በምዕራቡ ክፍል የሚገኙት) ምንጫቸው ኢትዮጵያ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ‹‹እንደሚባለው ቅድመ አያቶቼ የመጡት

ከሁለት ሀገር ነው፡፡ ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ፡፡ ከዚያም ወደታች ወረዱና ሩዋንዳ ገቡ፡፡ ሩዋንዳ ከገቡ በኋላ ደግሞ ወደ ኡጋንዳ ቀጠሉ›› ይላል፡፡ እንደ አሌክስ ግምት ይህ ፍልሰት የተከሰተው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡አሌክስ እንደ ብዙዎች የዛሬ ምስራቅ አ

ፍሪካ ኑዋሪዎች ሁሉ የመጣሁት ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ምድር ነው ለሚለው ታሪክ እውነትነት የሚጠቅሳቸው ምክንያቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በተለይ ቱትሲ በሚባሉት የሩዋንዳ ጎሳ አባላት፤ በምዕራብ ኡጋንዳ በሚገኙት በተለይ ባንኛኮሌ እና በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን የመልክና የአኗኗር ዘይቤ መመሳሰል ነው፡፡ ‹‹በታሪኩ እውነትነት አምናለሁ ምክንያቱ

ም የአኗኗር ሁኔታቸውንም ሆነ የሚያደርጉትንና መልካቸውን ስትመለከት እኔ የመጣሁበት እና ኢትዮጵያውያን በእጅጉ ይመሳሰላሉ፡፡ ለምሳሌ ከሶማሊያ የሚዋሰኑት ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን በብዛት የሚተዳደሩት በከብት እርባታ ነው፡፡ ሩዋንዳዎችንና ምዕራብ ኡጋንዳዎችን ስትመልከት በብዛት የሚተዳደሩት በዚሁ በከብት እርባታ ነው፡፡ ሁለቱም እንስሳት ያረባሉ፡፡ ይህ ሁሉ አንድነት የመጣው ከደማቸው መመሳሰል ጋር ተያይዞ ነው›› ብሏል የሀሳቡን እውነትነት ለማስደገፍ በጠቀሰው ምሳሌ፡፡

ደማችን አንድ ነውእንደ አሌክስ ሁሉ ትውልዴ ከፕሬዚዳን

ት ሙሴቬኒ የትውልድ መንደር ምዕራብ ኡጋንዳ ምባራራ ነው የሚለው ፕሪንስ ሪቻርድ “የዛሬዎቹ የምስራቅ አፍሪካ ነዋሪዎች የዘር ሀረጋቸው የሚመዘዘው ከቀድሞዋ ኢትዮጵያ ነው” ባይ ነው፡፡ ‹‹ከኢትዮጵያ ተነስተው በቱርካና ሀይቅ አቋርጠው ምዕራብ ኡጋንዳ ከዚያም ሩዋንዳና ብሩንዲ ተበትነዋል›› ይላል የዛሬዎቹን የሶስቱ ሀገራት (ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ) መነሻ ሲያብራራ፡፡ ‹‹እኔ ኡጋንዳውያን የመጡት ከኢትዮጵያ

መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ለዚህም ነው የኡጋንዳ መንግስት ለእነሱ አብዝቶ የሚጨነቀው፡፡ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያንም ደማቸው አንድ ነው፡፡ መጽሃፍትን ብታገላብጥ ኡጋንዳ ለሶማሊያውያንም ሆነ ለኢትዮጵያውያን ብዙ ነገር እንዳደረገች ትመለከታለህ፡፡ በጥቅሉ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ሀገራት ያለነው ህዝቦች እንዲህ የምንተባበረው የሁላችንም ደም አንድ በመሆኑ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ምንጩ ደግሞ ኢትዮጵያ ናት›› ሲል የዛሬው የአካባቢው ሀገራት ትብብር ከፖለቲካ ይልቅ በደም የተሳሰ

ረ ነው የሚለውን መከራከሪያ ያቀርባል፡፡ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ወደ ኢትዮጵ

ያ በመሄድ እውነታውን በአይኔ ተመልክቼ አረጋግጫለሁ የሚለው ሪቻርድ በመልክና በቁመናም ቢሆን እነዚህ ህዝቦች ተመሳሳይነት እንዳላቸው ይገልጻል፡፡ ‹‹ዝም ብለህ ከምዕራብ ኡጋንዳ አንድ ሰው ከሩዋንዳ ኪጋሊ ሌላ አንድ ሰው ውሰድና ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር አወዳድረው፡፡ ምን ያህል ተመሳሳይነት እንዳላቸው ታረጋግጣለህ›› ብሏል፡፡የታሪክ ምሁራን ግን ምስራቅ አፍሪካውያ

ን የዘር ግንዳቸው ከኢትዮጵያ ነው በሚለው እንደ አሌክስና ሪቻርድ በአንድ ወገን አይሰለፉም፡፡ ገሚሶቹ በሀሳቡ ሲስማሙ ሌሎች ደግሞ መሰረተ ቢስ መላምት ነው እስከማለት ይደርሳሉ፡፡

ቱትሲዎች ማናቸው? የእንግሊዙ አለም አቀፍ የዜና ማሰራጫ

ቢቢሲ በአንድ ወቅት የሩዋንዳን ጅምላ ጭፍጨፋ በተመለከተ ዜና ሲጽፍ የሚከተለውን አስፍሮ ነበር፡፡‹‹ …በእርግጥ ሁለቱ ጎሳዎች (ሁቱና ቱት

ሲ) በጣም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አንድ አይነት ቋንቋ ይናገራሉ፡፡ በአንድ አካባቢ ይኖራሉ፡፡ ተመሳሳይ ባህል ይከተላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ቱትሲዎች ከሁቱዎች ይልቅ ቀጠን እና ረዘም ያሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት የእነዚህ (ቱትሲዎች) የዘር ግንዳቸው የሚመዘዘው ከኢትዮጵያ ነው፡፡ በጅምላ ጭፍጨፋው ወቅት የቱትሲዎች አስከሬን በገዳዮቻቸው ወደ ወንዝ ይጣል ነበር፡፡ ገዳዮች ይህን በሚያደርጉበት ወቅት ወንዙ ቱትሲዎችን ወደመጡበት ኢትዮጵያ መልሶ ይውሰዳቸው እያሉ ነበር..››የተወሰኑ የታሪክ ምሁራን ያሰፈሩት መረ

ጃ እንደሚጠቁመው የዚህ የቢቢሲ ጽሁፍ መነሻ ታሪክ ዓመታትን ወደኋላ የሚያሻግር ነው፡፡ ኢሪዊን ኤም በርግ የተባለ በኒው

ዮርክ የህግ ባለሙያ ፕሮፌሰር ዮቻናን ብዌጄሪ ነገሩኝ ብሎ እንደጻፈው የቱትሲ ህዝቦች መገኛቸው ኢትዮጵያ ነው፡፡ ራሳቸው ፕሮፌሰር ብዌጄሪ የሩዋንዳው ቱትሲ ህዝቦች “ቤኔ ግዌ” ጎሳ አባል መሆናቸውን የህግ ባለሙያው ጽፏል፡፡ በትውልድም አይሁድ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ እሳቸው እንደሚሉት እ.ኤ.አ በ1270 የአይሁድ አገዛዝ ሲፈረካከስ “ቤኔ ዛግዌ”ን ጨምሮ በርካታ ጎሳዎች ተፈጠሩ፡፡ እነዚህም ብዌጄሪ “ሀቪላ” ብለው ወደሚጠሯቸው ወደ ታላላቅ ሀይቆች አካባቢ ማለትም ወደ ብሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ የኡጋንዳ የተወሰኑ አካባቢዎች፣ ታንዛኒያ እና ኮንጎ ተጓዙ፡፡ እነዚህ ጎሳዎች ከ 1270 እስከ 1527 የዘለ

ቀና የደቡብ ኩሸቲክ የተባለ ግዛት እንደገና አቋቁመው ነበር፡፡ በ1880 መጀመሪያ አካባቢ የካቶሊክ ሚሲዮኖች ወደዚህ አካባቢ መጡ፡፡ በዚህ ወቅት ከቱትሲ እምነት በስተቀር በሌላ አናምንም ባሉ ቱትሲ ህዝቦችና በካቶሊክ ሚሲዮኖች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ፡፡ ይህም እስከ ሃያኛው ክፍለዘመን የዘለቀ ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎ የጀርመን ሀይል ግዛቱን ሲቆጣጠር በወቅቱ የነበረው ወታደራዊ ኃይል ድጋፉን ለሚሲዮኖች አደረገ፡፡ ሚሲዮኖችም የካቶሊክን እምነት ለማስፋፋት ከቱትሲዎች እምቢተኝነት የገጠማቸውን ያህል በሁቱዎች ተቀባይነት በማግኘታቸው በሁቱዎች ላይ ብቻ ድልን ተቀዳጁ ይላሉ ፕሮፌሰር ብዌጄሪ፡፡ ይህንን ተከትሎም የቱትሲዎች መሬት እየተቀማ ለሁቱዎች ተሰጣቸው፡፡ እንደጸሐፊው አባባል በዚህ የተጀመረው ግጭት ነው በኋላ ላይ ወደ ጅምላ ጭፍጨፋ የተሸጋገረው፡፡

እውነት የነበረ ቅዠት ወይስ..? እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ በኡጋንዳ ማ

ኬሬሬ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ክፍለ ትምህርት ኃላፊውና የታሪክ ሊቁ ዶክተር አሲምዌ ጎ

ድፍሬይ ግን ኡጋንዳውያንም ሆኑ ምስራቅ አፍሪካውያን የዘር ግንዳቸው ኢትዮጵያ ነው የሚለውን ሀሳብ ‹‹የነጮች ጭንቅላት የወለደው መሰረት የለሽ መላምት›› ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ ቱትሲዎች የመጡት ከኢትዮጵያ ነው የ

ሚለውን የጸሀፊዎችን መከራከሪያም አውሮፓውያን አፍሪካውያንን ለመከፋፈል ከተጠቀሙበት ስልት እንደ አንዱ የሚወሰድ እንጂ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ክስተት አለመሆኑን ይገልጻሉ፡፡ እንደ ዶክተር ጎድፍሬይ የመከራከሪያ ሀሳብ ቤልጂየሞች በእምነት ሰበብ ወደ ሩዋንዳ በመጡ ጊዜ ህዝቦችን ለመከፋፈል ቀጥ ያለ አፍንጫ እና ረጅም ቁመት ያላቸውን መርጠው ለብቻ በማድረግ ይሄኛው የመጣው ከዚህ ነው ያኛው ደግሞ ከሌላ ነው በማለት ሁቱና ቱትሲን ለመከፋፈል የተጠቀሙበትና በኋላም ወደማያባራ የእርስ በእርስ እልቂት የተሸጋገረ ሴራ ነው፡፡ ዶክተር ጎድፍሬይ የምስራቅ አፍሪካውያ

ን ጎሳዎች ከኢትዮጵያ የመምጣት ታሪክ አሁን ላይ መሰረት የለሽ ይበሉት እንጂ እርሳቸውም ጉዳዩ ለዓመታት ምሁራንን ሲያፋጭ እንደቆየ ይመሰክራሉ፡፡ መመሳሰሉ የመጣው ከአካባቢ ነው የሚሉት ምሁሩ የኬንያው ማሳይ፣ የኡጋንዳዎቹ ቴሶ፣ ካራሞጆንግና ባንኛኮሌ እንዲሁም የሩዋንዳው ቱትሲ አርብቶአደሮች ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ እንዳላቸው ይመሰክራሉ፡፡ ይህ ግን ድንበር ስለሚዋሰኑ በዘመናት ሂደት የተወረሰ እንጂ ደማቸው አንድ ስለሆነ አይደለም ባይ ናቸው፡፡ ይህ ታሪክ የተበረዘው የአውሮፓውያን ርዕዮተ አለም ተጽዕኖ ባለባቸው አንዳንድ የቀድሞ ስነ-ሰው ተመራማሪዎች ነው፡፡ ከዘመናት በፊት ለረጅም ጊዜ ሲያከራክር የቆየ በአሁኑ ወቅት ግን ምንም የታሪክ ማረጋገጫ ያልተገኘለት መላምት ስለመሆኑ ከስምምነት የተደ

የዘር ግንድ ሲቆጠር

ረሰበት ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ምሁሩ ምስራቅ አፍሪካውያን በተለይ ም

ዕራብ ኡጋንዳውያን የባንቱ ፍልሰት አካል ናቸው ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ መነሻው በመሆኑ የዛሬዎቹ ምስራቅ አፍሪካውያን የዘር ምንጫቸው አፍሪካ እንጂ አውሮፓውያን እንደሚሉት መካከለኛው ምስራቅ ወይም አውሮፓ አይደለም፡፡ ነጮች ቅኝ መግዛት ስለፈለጉ “አፍሪካ ኋ

ላ ቀር ናት። ህዝቡም መሃይም፣ እምነት የለሽ ነው። ስለዚህ እኛ ሄደን ልናሰለጥነው ይገባል” ብለው መጡ፡፡ በዚህ መሀል እነሱ ለሽፋን ከሚጠቀሙበት በተቃራኒ የሆነ ነገር በተገኘ ጊዜ መቀበል ይከብዳቸው ነበር፡፡ “ይህም የእዚህ አንድ አካል ነው” ሲሉ የነጮች ርዕዮተ ዓለም ያስከተለው የታሪክ ብዥታ ያሉትን ሀሳብ ይቃወማሉ፡፡ “እንደ ቅኝ ገዥዎቹ ማንኛውም ጥሩ ነገር ከአፍሪካ ምድር ሊመጣ ወይም ሊገኝ አይችልም፡፡ ለዚህም ነው ኡጋንዳውያንንም ሆነ ሩዋንዳዎችን የመጣችሁት ከኢትዮጵያ ነው የሚል ጽሁፍ ማስነበብ የጀመሩት” ይላሉ፡፡ “ማንኛውም ሰልካካ አፍንጫና ለግላጋ

ቁመና ያለው ሁሉ ከአፍሪካውያን ወይም እንደነሱ አጠራር ከኔግሮ (ጥቁር አፍሪካውያን) ሊገኝ አይችልም፡፡ በመሆኑም መልካሞችን የመጣችሁት ከኢትዮጵያ ነው ይሏቸዋል። ንጉስ ሰሎሞንንና ንግስተ ሳባን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር ግንኙነት አድርጋ ስለነበር ዞሮ ዞሮ የኢትዮጵያም ከመካከለኛው ምስራቅ ነው በማለት ቆንጆ መገኛው አውሮፓ ወይም አካባቢው እንጂ አፍሪካ እንዳልሆነ ለመስበክ የተፈጠረ መላምት ነው›› ሲሉ ዶክተር ጎድፍሬይ አጥብቀው ይከራከራሉ።

ፊቴን ተመልከውየታሪክ ምሁሩ ዛሬ ላይ መሰረት የለሽ መ

ላምት ስለመሆኑ ስምምነት ተደርሶበታል ብለው ቢቋጩትም ለአብነት የኡጋንዳ የ

ጎብኝዎች መጠቆሚያ ድረ ገጽ ግን አሁንም ድረስ ከእርሳቸው በተቃራኒ መቆሙን የሚያመላክት ጽሁፍ ነው የሚያስነብው፡፡ ድረ ገጹ ላይ የኡጋንዳን ታሪክና የህዝብ አሰፋፈር በተመለከተ የሰፈረው ጽሁፍ በሰሜን፣ በምስራቅ እና በሰሜን ምስራቅ የሚገኙ ኡጋንዳውያን ምንጫቸው ከኢትዮጵያ መሆኑን ያብራራል፡፡ጽሁፉ እንደሚለው የአሁኗ ኡጋንዳ

እ.ኤ.አ ከ1880 እስከ 1926 ባለው ጊዜ በእንግሊዞች የተፈጠረች ናት፡፡ ከሁሉም ቀድመው በኡጋንዳ ይኖሩ የነበሩት የድንጋይ ዘመን ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቀሰ በቀስ በአንደኛው ምዕተ ዓመት አካባቢ ወደ ኡጋንዳ ይገቡ በነበሩ አርሶአደሮችና አርብቶአደሮች መተካት ጀመሩ፡፡ እንግሊዞች ኡጋንዳ በመጡበት ጊዜ ከ30 በላይ የተለያዩ ብሄርና ጎሳዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ጎሳዎች ሰፋ ባለ አራት መደብ ሊከፈሉ እንደሚችሉ የድረ ገጹ ጽሁፍ ያትታል፡፡ እነሱም ባንቱ፣ ሉኦ፣ አቴከሪን እና ሱዳኒክ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል አቴከሪን በሚባለው ሁ

ለተኛው ቡድን ውስጥ የሚገኙትና በተለይም በሰሜን፣ በምስራቅ እና በሰሜን ምስራቅ ኡጋንዳ የሚገኙ ሰፋሪዎች የመጡት ከኢትዮጵያ መሆኑን ጽሁፉ ያስረዳል፡፡ ይህ ቡድን ላንጊን፣ ካራሞጃውያን፣ ቴሶ፣ ካክዋ እና ኩማምን የሚያካትት ሲሆን የእነዚህ ብሔር አባላትም ራሳቸውን እንደ አንድ ህዝብ የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ በጊዜ ሂደት በፍልሰትና ተያያዥ ምክንያቶች በተለያየ የኡጋንዳ አካባቢ ቢሰፍሩም የራሳቸውን ሰዎች ከሌላው ለይተው ማወቅ ይችሉ እንደነበር ይነገራል፡፡በኡጋንዳ ጦር ውስጥ የሐላፊነት ቦታ ያላ

ቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ባለስልጣን የሚናገሩትም በድረ ገጹ የተጠቀሱትን ነጥቦች የሚያጠናክር ነው፡፡ “ታውቃለህ የእኛ አያት ቅድመ አያቶቻችን ከኢትዮጵያ ነው የመጡት፡፡ እኔ ከቱትሲዎች ወገን ነኝ፡፡ ፊቴን ተመልከው ከአንተና ከመሰሎችህ ጋር ይቀራረባል፡፡ ያኛውን ወጣት ተመልከተው፡፡ ኢትዮጵያዊ አይመስልም? ግን ኡጋንዳዊ ነው፡፡ እኔ ከመጣሁበት ጎሳ ነው” ሲሉ ማን ከኢትዮጵያ እንደሆነና እንዳልሆነ ከሰው መካከል እንኳን መለየት እስኪችሉ ድረስ ርግጠኛ መሆናቸውን ይናገራሉ ፡፡ “የምነግርህ ዛሬ ወይም ትላንት ስለሆነ ነገር አይደለም፡፡ እኔ እዚሁ ነው የተወለድኩት አባቴም እንዲሁ፡፡ የእኛን አባቶች የወለዱት ወይም ከዚያ በፊት ያሉት ግን የዘር ግንዳቸው ከኢትዮጵያ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከመልካችን ጀምሮ ብዙ ማሳያዎች አሉ።”ይህ ሁሉ ሆኖ አሁንም ድረስ ሁለቱን ጎራ

የሚያስታርቅ ጠርቶ የወጣ እውነት የለም፡፡ ገሚሶቹ ሀረጋችን ከኢትዮጵያ ነው ሲሉ ገሚሶች ደግሞ እኛ ከኢትዮጵያ አይደለንም ክርክሩ ቀጥሏል፡፡ ምን አልባት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛና ሰፊ ጥናት ተደርጎ ዳግም ወደ አዲስ እውነት መድረስ ይቻል እንደሆን ለአጥኚዎቹ የሚሰጥ የቤት ስራ ይሆናል፡፡

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ፎቶ

ዎች

- በኡ

ጋንዳ

የሐበሻ

ዊ ቃ

ና ዘጋ

ጋታንጋ አሌክስ እንደ ብዙዎች የዛሬ ምስራቅ አፍሪካ ኑዋሪዎች ሁሉ የመጣሁት ከኢትዮጵያ ነው የሚል እምነት አለው

የማኬሬሬ ዩኒቨርስቲው ዶክተር ጎድፍሬይ ግን ኡጋንዳውያንም ሆኑ ምስራቅ አፍሪካውያን የዘር ግንዳቸው ኢትዮጵያ ነው የሚለውን ሀሳብ ‹‹የነጮች ጭንቅላት የወለደው›› ሲሉ ያጣጥሉታል

Page 21: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 21

ከጓደኞቹ

ሰኔ 18 ቀን 2003 ዓ.ም የጋብቻ በዓላችሁን ላከበራችሁት

መስፍን ገብረስላሴ እና ሀና ተሾመ መልካም የትዳር ጊዜ

እንዲሆንላችሁ እንመኛለን

ምጥን ማስታወቂያዎች

የልደት፣ የሰርግ፣ የመልካም ምኞት መልዕክቶችን በምጥን ማስታወቂያ

ማውጣት ከፈለጉ በ+256-778-693669

አድራሻ፦ ካሳንጋ/ ጋባ መንገድ ከጆን ሱፐር ማርኬት ገባ ብሎ

ከምርጥ የኢትዮጵያ ቡና እና

ማኪያቶ ጋር

በዚህ መልኩ ያ አሰቃቂና ረጅሙ ሌሊት አለፈና ወደየቤታችን ሄድን፡፡ እኔ ወደ ቤቴ የሄድኩት ሌሊት አስራ አንድ ሰዓት ነው፡፡ እንደደነዘዝኩ መኝታ ቤቴ ገብቼ ጠዋት ልጄ ትምህርት ቤት ለመሄድ ስትነሳ ልብሴን ስታየው “ኡኡ” ብላ ጮኽች፡፡ ለካስ አስከሬንኑም የተጎዳውንም ስናነሳ ለብሴ በሙሉ ደም በደም ሆኗል፡፡ ልጄ የሆነውን አላወቀችም። “ከማን ጋር ተደባድበህ ነው የመጣኽው” እያለች ታለቅሳለች፡፡ ከአደጋው ማግስት ጀምሮ ባሉት ቀናትም አስከሬን መሸኘት ለቅሶ መድረስ ወዳጅ ዘመድ የሞተባቸውን ማጽናናት ሆነ፡፡ ምንም በህይወት እያለን ብናወራ ብን

ጣላ ወይም ብንሳሳቅ ብንጫወት በቅጽበት ወዳለመኖር እንቀየራለን፡፡ ህይወታችን ካለፈ ደግሞ ሁሉም ነገር ወዲያው ያበቃል፡፡ የነበረን ተክለሰውነት እንኳ የእኛ መሆኑ እስከማይታወቅ ድረስ ይሆናል፡፡ የሰው ልጅ ፈራሽ ነው የሚባለው እውነት ነው፡፡ ከአደጋው አንድ ቀን በኋላ አስከሬን የማን ይሁን የማን መለየት ተስኖን ነበር፡፡ በጋዜጣም እንዳነበባችሁት አንዳንዶች የራሳቸውን ወገን ሳይሆን የሌላ ሰው አስከሬን ይዘው እስከመሄድ ደርሰዋል፡፡ለተከታዮቹ ዘጠኝ አስር ቀናት በድኔ ነ

በር የሚንቀሳቀሰው፡፡ ድርጊቱ በህልም ወይም በእውን ስለመሰከቱ ሁሉ እርግጠኛ አልነበርኩም፡፡ እንቅልፍ ሁሉ ሊወስደኝ ስላልቻለ በመድሃኒት ኃይል ነበር የምተኛው፡፡ ከዚያ በኋላም ቢሆን ቅዠት ሁሉ ያስቸግረኝ ነበር፡፡ ሌሊቱ የረዘመውን ያክል ከአደጋው በኋላ ያለው ጊዜ ግን አጥሮ እንጂ ረዝሞ አልተሰማኝም፡፡ ምክንያቱም አደጋው መቼም ከጭንቅላት የሚወጣና የሚረሳ ባለመሆኑ ነው፡፡ አሁን አንድ ዓመት ሞላው ሲባል

ገርሞኛል። ትናንትና፣ ከወር ሁለት ወር በፊት የተከሰተ ያህል ነው የሚሰማኝ፡፡

የቦነስ ህይወትከዚያ በኋላ ደጋግሜ እንደተናገርኩት

በ“ቦነስ ህይወት” ነው የምኖረው፡፡ ያንን አይነት መጥፎ ገጠመኝ አልፈህ ከኖርክ በ“ቦነስ ህይወት” ነው የምትኖረው ማለት ነው፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ ኑሮዬ ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ነው፡፡ በዚህ አደጋ ህይወታቸው ካለፈው መካከል ብዙዎቹ በዚህ አይነት ህይወት ወስጥ ያለፉ ናቸው፡፡ ምንም በማያውቁት በዛ መልኩ ህይወታቸው ማለፉ ያሳዝነኛል፡፡ ብዙዎቹ ታላላቆቻቸውን አክባሪዎች ሳቅ ጨዋታንም የሚወዱ ነበሩ፡፡ እነዚህን ሁሉ ካጣህ በኋላ የምትኖረ

ው ህይወት ታዲያ እንዴት ነው ምታስናግደው የሚለው ጥያቄ የራሱ መልስ ይፈልጋል፡፡ በተለይ እንዲህ አይነት ገጠመኝ ውስጥ ተካፍለህ በህይወት ስትተር

የሚመስል ግን በአንድ ምሽት የዘላለም ጠባሳን ያተረፈ ዘግናኝ እውነት ነው፡፡ከዚያ በኋላ በተወሰነ መልኩም ቢሆን

ከሰው ሀገር ሰው ጋር በተለይ ከሶማሊያውያንና ከነጮች ጋር መቅረብን መጥላት ጀምሬአለሁ፡፡ ምክንያቱም እኔ እንደማስበው ፍንዳታው ኢላማ ያደረገው ነጮችን ነበር፡፡ እነሱ በተቀመጡበት አካባቢ ነበር፡፡ ቀደም ሲል እንዳልኩት የቦምብ ፍንዳታው ነጮችን ኢላማ ያደረገ ነበር፡፡ በመሆኑም ለእኛም ወገኖች መሞት ምክንያቶቹ እነሱ ናቸው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ በዚህም ምክንያት ነጮች የተሰበሰቡበት አካባቢ መቅረብ ጠልቻለሁ፡፡ እንዲያውም አደጋው ከተከሰተ በኋላ ባሉት የመጀመሪያ ቀናት ሐበሻ የተሰበሰበበት አካባቢም መቅረብን ጠልቼ ነበር፡፡ ራሴን ለማረጋጋት በሚልም ኡጋንዳን ለአንድ ወር ያህል ለቅቄ እስከመውጣት ደርሻለሁ፡፡

ወይኔ!በእለቱ ህይወታቸው ካለፈው መካከል

አራቱ ከእኛ ጋር ኳስ የሚጫወቱ ሲሆኑ ሶስቱ በእለቱ ጠዋት አብረውን የተጫወቱ ነበሩ፡፡ እኔ እንዲያውም መሸኛ አድርገልናቸዋል ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ቀደም ሲል እንዳልኩት አንዱ (ዘላለም) ከናይሮቢ በእንግድነት መጥቶ ነው ኳስም የተጫወተው፡፡ ከኳስ መልስም ከሁላችን ጋር በአንድ ማዕድ እየበላን እንጫወትና እንሳሳቅ የነበረው፡፡ ካሌብም ቢሆን ከሌላው ጊዜ በተለየ ጥሩ ጨዋታ ነበር የተጫወተው፡፡ በዚህ መልኩ ከቆየን በኋላ ማታ ኳስ ለማየት ተቀጣጥረን ነበር የተለያየነው፡፡ ማታ ታዲያ ካሌብ ከጓደኞቹ ጋር ሲገባ አንድ መቀመጫ ነው በሚል ሳልጠራው በመቅረቴ ዛሬም ድረስ ጸጸቱ ከአእምሮዬ ሊወጣ አልቻለም፡፡ ብዙ ጊዜ ካሌብን እኔ የገደልኩት ያክል ይሰማኛል፡፡ ካሌብ ከአፌ ነው ያመለጠኝ፡፡ ምናልባት ብቻውን ቢሆን ኖሮ እጠራው ነበር ፡፡ ሶስት ስለሆኑ ግን ይህንን ሳላደርገው ቀረሁ፡፡ አሁንም ድረስ ምነው ጠርቼ ባስቀመጥኩት ኖሮ እላለሁ፡፡

ፍ መቼም እንደምትሄድ ታውቀዋለህ፡፡ እነዚህ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ሩቅ ያስቡ የነበሩ ሰዎች በ45 ወይም በ50 ደቂቃ ብልጭታ ውስጥ በዚያ መልኩ ካለፉ እኛስ ብለን ማሰብ አለብን፡፡ በመሆኑም እኔ በግሌ ከዚያ በኋላ የኖርኩትና እየኖርኩ ያለሁት በቦነስ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ አንድ ነገር እንኳ ቢመጣ

ብዙ እንደማልረበሽ አውቀዋለሁ:: ምክንያቱም ከምንም በላይ ልምድ አግኝቸበታለሁ፡፡ የሰው ልጅ እንደ በዓል የቅርጫ ስጋ እየተከፋፈለ ከማንሳት በላይ ምን አለ? እኔ ሞቼ ቢሆን እንደዚያው ነበር እኮ ነው፡፡ በአንድ በኩል ወገኖቼን በመርዳቴ እርካታ ይሰማኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለነገም እንዳላስብ፣ አንድ ነገር ቢገጥመኝም ብዙ እንዳልገረም አድርጎኛል፡፡ ፍንዳታውን በተመለከተ በወቅቱ ላልነበሩት ሰዎች ስነግራቸው ህልም ነበር የሚመስላቸው፡፡ እውነትም ህልም

አዝኛለሁ። አንድ መታሰቢያ ማድረግ እንጂ ሌላ አቅም የለኝም። መታሰቢያው ሲከፈት አምባሳደሮች፣

የውጭ ሀገር ዜጎች እና የሞቱባቸው ቤተሰቦችን ጠርቼያለሁ። ብዙዎቹ ደስ ነው ያላቸው። አልፎ አልፎ ደግሞ የተለየ አስተያየት ትሰማለህ። ሆኖም ቀረ መሆን ያለበት ነገር ስለሆነ ነው እንጂ ይሄ ነገር ባይመጣ ኖሮ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ እንዲህ ዓይነት መታሰቢያ አይኖርም ነበር። እኔ ራሴን እንደ ደንበኛ አስበኝ። እዚህ

“ቪሌጅ” መጥቼ፣ አንድ የሆነ ሰው አጥቼ፣ ምግብ ቤቱ የሆነ መታሰቢያ ቢሰራ በጣም ነው ደስ የሚለኝ። አሁን አንዳንዴ ከሞቱባቸው ቤተሰቦች እየመጡ አበባ የሚያኖሩ አሉ። የውጭ ሀገር ዜጎች ደግሞ አበባ አምጥተው አስቀምጠው ፎቶግራፍ ያነሳሉ። የተለያዩ ሀገር ጋዜጠኞችም ይመጣሉ።

እዚህ ሀገር ወደ ሃያ ዓመት ገደማ ቆይተሻል። የካምፓላን ክፉ እና ደግ አይተሻል። ከብዙ ሐበሾች ጋር ትተዋወቂያለሽ። ይህ ቤትም የኢትዮጵያ ባህል ማሳያ ተብሎ የሚጠቀስ ነው። ለሐበሾች ምንድነው የምትያቸው? እኔ መቼም በእውነት ነው የምለው ከ

አደጋው በኋላ በተለምዶ እንደምናደርገው ቄጤማ ጎዝጉዘን፣ መሶባችን ወጥቶ፣ ፈንዲሻ አፈንድተን፣ ቡና ተፈልቶ፣ እጣኑ እየጤሰ እንግዶች እየገቡ እያለ ሰው ከቤተከርስቲያን ግልብጥ ብሎ መጥቶ ግቢውን ሲያጥለቀልቀው እኔ ወደ በረን

ዳ መጥቼ ስመለከት ፊቴን በእንባ ነው የራሰው። የምኮራባቸው ደንበኞቼ ቤቱን ግጥም አድርገው፣ ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ በየጠረጴዛው እየሄድን ቡና እያደልን፣ ሙዚቃ ተከፍቶ ሲጨፈር፣በቦታው ላይ ምንም የተፈጠረ አይመስልም። ወገንህ አለሁ ሲል ከዚህ የበለጠ ምን

የሚያስደስት ነገር አለ። ሰርተህ የሚበላልህ ሰው ከሌለ ምንም ዋጋ የለውም። ስለዚህ እጅግ በጣም የሚያኮራ ነው። የሀገራችንን ባህል እነሱ በመኖራቸው ያደመቁት እንጂ የእኔ ብቻ ስራ አይሆንም። በጠቅላላ የ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ደንበኞች ባሉበት በካምፓላም ይሁን በአሜሪካ፣ በካናዳም ይሁን በታንዛንያ፣ በኬንያም ይሁን በዓለም ላይ ላሉት ደንበኞቼ ልናገር የምፈልገው ከስራዬ በበለጠ ሁኔታ እጅግ በጣም ትልቅ ደንበኞች እንዳሉኝ ይሰማኛል። እኮራባቸዋለሁ።

ቤቱ ከታደሰ በኋላ ምን የተለወጠ ነገር አለ?በተቻለ መጠን ከእንግዲህ ደንበኛው

ንም ሆነ ራሳችንን ለመጠበቅ ጥብቅ ፍተሻ አለ። ሁለተኛ የሚከሰት ዓይነት ነገር አይደለም። የመፈተሻ መሳሪያዎች ተገዝተዋል። አሁን ኑሮ እየተወደደ በመሆኑ የምን

ገዛቸው ዕቃዎች ውድ ናቸው። ባለው ደረጃ የምግቦችን ጥራት ጨምረን አንዳንድ አዳዲስ ምግቦች ጀምረናል። ጠጅ፣ ጠላ ጀምረናል። ወደፊት ግን የፈረንጅ ምግቦችን፣ ባህላችንን ይበልጥ የሚያስተዋውቁ ነገሮች ለመጀመር ዕቅድ አለኝ። ። ለዚህ ሁሉ ላስደሰቱኝ ደንበኛቼ ከዚህ በበለጠ ሁኔታ አድርጌ ባልተወደደ ዋጋ ለማስተናገድ፣ የተሻሻለ ነገር ለማቅረብ ዕቅድ አለኝ።

ከገጽ 5 የዞረ

ማሜ እና…

ሐበሻዊ በየቀኑ

15ቃና

ማን ይናገር የነበረ…

ከገጽ 7 የዞረ

በአደጋው ወቅት አምቡላንስ እንኳን ባለመምጣቱ ፖሊሶች በራሳቸው መኪና ወዲያው ወዲያው እየተቀበሉ ወደ ሆስፒታል እየያዙ ይሄዱ ነበር

ፎቶ

- ሮይ

ተርስ

Page 22: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና22

ሉ፤ የመጀመሪያውን ባልችልበት የሁለተኛውን ማን ይከለክለኛል? ያ ሰው ወይም እነዛ ሰዎች ስሟን ሊያጠፉ ሲለፉ ነው የእኔ ሃላፊነት የገባኝ። አብሮ መብላት መጠጣትማ ዋና ነገር መሆኑ አቆመ። እሱ ተፈትሾ ወድቋል። በእርግጥ ልብን የመስጠት እንጂ። አብሬ ቂጣ የተጓተትኳቸውእንደ ቂል ልብን የመስጠት እንጂ። አብሬ ቂጣ የተጓተትኳቸው እንደ ቂል ቆጥረውኛል። ለወዳጄ የውርደት ስጦታ ‘ዲሞክራሲ’ በሚባል ክርታስ ጠቅለው ሰጥተዋታል። እኔንም ‘በታድለሃል’ ጋርደው ከለመድኳትና ካሳደገችኝ ለገሃር አባረውኛል። ፍቅር እንዳይደርስእሱ

የተሰራባቸውን ንጥረ ነገሮችን ማፍረስ ነው ልፋታቸው። አፍታ እድል አልሰጣቸውም። ለማንም ዝም ብዬ በር አልከፍትም። ውሃ እየቀዳሁ አስባለሁ። ሻይ ስጥድም አስባለሁ። ማንንም ሰው……ድርጊቱና አንደበቱን አወዳድሬ ነው የማምነው….ውሃ ቀድቼ እየሰጠኋት አስባለሁ። የሻይ ቅጠል ፓኮዎች እየመረጥኩ (ሶስት አይነት አሉኝ) አስባለሁ። በመስኮት ወደ ውጭ ታያለች። አልጋ ዳር ተቀምጣ። እርግዝናዋ የከፈላቸው እግሮቿ ግራና ቀኝ ወዲያ ወዲያ። ትልቅ አእምሮ አላት ትዕግስት አላት። ውሃ ስትጠጣ እያየሁዋት አስባለሁ። ጥበብም መልመድ ነበረብኝ። ‘የሰው

ልጅን፣ ዜጋውን ሳትወድ እንዴት አገርህን ትወዳለህ?’ አይነት ጥበብ። አስቸጋሪ ነበር። እሱን ከመቅደስ ተማርኩ።

መጋረጃ ዘግቼ አጠገቧ ተቀመጥኩ። ፊቷን ቀና አድርጌ ውሃ ያቀዘቀዛቸው ከ

ንፈሮቿን ሳምኳቸው። አስባለሁ …..ከእንግዲህ የበለጠ ቁም ነ

ገረኛ እንድሆን። ግን ጠባብ የሆነ። የእህቴን ቁስል ለማባበል። ለማዳን።እጄን ወደ ጣፋጭነቷ እልካለሁ። ወደ

ማሯ። ዳጥ እየሳበኝ። መውደድ ደግ ነው። ጀርባዬን ይበርደኛል። የሰሜን ባሕር አየር በባንኮኒ በር በኩል ይገባል። “በሩን አልዘጋሽም?”“መጋረጃውን ብቻ ነው”“ሰው በዚህ ቢመጣስ?”“አራተኛ ፎቅ ድረስ ማን በመሰላል እኛ

ን ለማየት ይመጣል ሂሂሂ”አንቺስ አራተኛ ፎቅ የምትኖሪ የተገለ

ልሽ ሴት አልነበርሽ? ምንሽ ሲሰለል ነው የተሰለልሽው ? የተሰደብሽው? የታማሽ

ው? ሕይወትሽ እንደ ማብሸቂያ የተቀመረው ? መጋረጃው በነፋስ ሲገለብ ባንኮኒው መደገፊአ ላይ አንድ ነገር ተቀምጦ አየሁ። ወይም ተቀምጦ ያየሁ መሰለኝ። የሞቀ እጄን ከጭኖቿ መሃል ሳላወጣ፣ እነበረበት ወደ ተመለሰው፣ ምንም ወደ ማያሳየኝ ውጭውን አለም ወደጋረደኝ መጋረጃ ላይ አፈጠጥኩ። አንድ እጅዋን ጭኔ ላይ ደረበች። መዘንጋትና መሰቃየት የማያፈርሳቸው

ሁነቶች አሉ። ሁነቶች። ከየት መጣ ይሄ ቃል? በቀትር ሰክሬ ብሔራዊ ትያትር ጀርባ አሮጌ መጻሕፍት ተራ፣ አጥፊው ጓደኛዬ ማሙሽ ቢራቱ መጽሐፍ ልግዛ ብሎ፣ ከገዛ በኋላ እኔን ለማሳቅ ሲያነብ የያዝኩት ቃል? መጋረጃው በቀላል ነፋስ ተነሳና ቀድሜ ያየሁትን ፍጡር ነገር ባንኮኒው መደገፊያ ላይ ተቀምጦ አየሁ። የ

ሆነ አሞራ ነገር ነው። ከእርግብ የሚተልቅ ዱጭጭ ያለ ነገር። ከጨለማው የበለጠ የጨለመ። “እንዴ ምንድነው?” አልኩና እጄን ከ

ጭኖቿ መሃል አውጥቼ ከተጋደምኩበት ቀና ብዬ ቁጭ አልኩ። መቅደስ ከተጋደመችበት አልተነሳች

ም። ትስለመለማለች። ፈገግ ብላለች። ገጽዋ ብዙ ነገር የተገነዘበ፤ ማንም ያልደረሰበት ዕውነት ላይ የደረሰች ሳቤላ አይነት ሆኖ። “ሰማሽ መቅዲ…..” አልኩና ባትሰማኝ

ም የበረንዳውን መብራት አብርቼ መጋረጃውን በፍጥነት ገለጥኩት። ባንኮኒው መደገፊያ ላይ ያየሁት የመሰ

ለኝ አሞራ የለም። ባንኮኒ ላይ ወጣሁና ወደ ሰማይ አየሁ። ተሳስቼ ይሆናል ወይም አይኖቼ። ወዲያው ክንፎቹ የሚያብ

ለጨልጩ የከተማው መብራት ለአፍታ የፈለቀበት የመሰለ በራሪ ነገር ወደ ወደቡ አቅጣጫ ሲበር አየሁ”” ‘ዝናብ ያረጠበው አሞራ ይሆናል፣ ወይም አይኔ ነው’ እያልኩ እየተገረምኩ ሳስብ መቅደስ መጣችና ራሴን ዳበሰችኝ። “ብጠራሽ ምን ሆንሽ፤ አትሰሚም?”“ጠራኸኝ?”

በቀጣዩ እትም የዚህን ትረካ የመጨረሻ ክፍል እናቀርባለን።

* ልፎ ማለት ወንዶች ሲገረዙ ከብልታቸው ተቆርጦ የሚቀበረው (የሚጣለው) ቁራጭ ነው። ይህ አጭር ልቦለድ የተወሰደው አዳም

ረታ በቅርቡ ካሳተመው አምስተኛ መጽሀፉ “ያመጣል መንገድ፣ ይወስዳል

መንገድ” ነው

ከገጽ 14 የዞረ

ልፎ ...

ከሌለህ ቋንቋ ስላወቅህ ብቻ የምትናገረው ነገር የለም። እንደዚህ አድርገን ነገሮችን ማየት አለብን። ትልቁ ነገር የአቅምህን መሞከር ነው። ደፍረው የገቡ ኢትዮጵያውያን ውጤታማ እና ስኬታማ ሆነው እንደውም የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ ሆነው ሲወጡ ነው ያየኋቸው። ስለዚህ ቋንቋ ችግር መሆን የለበትም። መተጋገዝ ይቻላል። ቀድሞ የገባ ካለ

“ምንድነው ያለው ነገር? እንዴት ልዘጋጅ? በምን መልኩ ባጠና ነው የተሻለ ውጤት ማግኘት የምችለው” ብሎ መጠየቅ ነው። አሁንም እንዲህ ነው የምንመካከረው። ከእኔ ቀድመው የገቡት መክረውኛል። ከእኔ ቀጥሎ የሚመጡ ካሉ ደግሞ እንዲሁ ይቀጥላል። አንዳችን ለአንዳችን አለኝታ መሆን አለብን። አንዳችን ለሌላችን መንገድ የምናሳይ መሆን አለብን። ፉክክር አለ። የተሻለ የምዘጋጅ ከሆነ ግ

ን አይከብድም። ብዙዎቹ ወጣቶች ናቸው። በዕድሜ ከእኔ ያነሱ ሊሆኑ ይችላሉ። ለትምህርት ያለን ስሜት ግን እኩል አይደለም። ምክንያቱም እኔ የምማረው በዓላማ ነው። ለአስር ዓመት ያህል ፈልጌ ያጣሁትን አግኝቼ አሁን በጉጉት ነው የምማረው። እነሱ ደግሞ በእድሜያቸው መማር ስላለባቸው ወይም በቤተሰብ ጎትጎታ ይሆናል የሚማሩት። ይህ ሁሉ ስላለ ተጠቃሚ እሆናለሁ። ጊዜዬን በአግባቡ እጠቀማለሁ። አነባለሁ። እኔም ሆንኩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን

ጥሩ ውጤቶች አሉን። ምናልባት እኔ ካሁን ቀደም ዩኒቨርስቲ ስለነበርኩ የጀርባ ታሪክ ስላለኝ ነው ሊባል ይችላል። ተመሳሳይ የትምህርት ዓይነት እየተማርኩ መሆኔ ጠቅሞኝ ሊሆን ይችላል። ከእኔ ጋር ከሚማሩት ኢትዮጵያውያን መካከል ግን ሁለተኛ ደረጃ ብቻ የጨረሱ አሉ። ጥሩ ውጤቶች እያስመዘገቡ ናቸው። ከተማሩ በኋላ ጥሩ ቦታ ደርሰው በአይኔ ያየኋቸው አሉ። እኔ ያለሁበት ትምህርት ቤት ተምረው በአሁኑ ሰዓት ወደ ስራው ገብተው ጥሩ ህይወት የሚኖሩ አሉ። ለዚህ ግን የአእምሮ ዝግጅት ያስፈል

ጋል። የትምህርት ስርዓቱ እንደእኛ አገር አይደለም። ፈተና ሲደርስ አይደለም የምታጠናው። ትምህርት በገባህ በመጀመሪያው ቀን በዓመት ውስጥ የምትማራቸው ነገሮች በሙሉ በቀኖች ተከፋፍሎ ይሰጠሃል። ትምህርት ተጀመረ ማለት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ታጠናለህ ማለት ነው። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጊዜው የአንተ አይደለም። የትምህርቱ ነው። እያንዳንዱን የቤት ስራ ተከታትለህ ካልሰራ እንደእኛ አገር ፈተና ሲደርስ ተዘጋጅቼ ውጤታማ እሆናለሁ ማለት የማይታሰብ ነው። ደግነቱ “ክሪስማስ መጣ ትባረራለህ” የሚባል ነገር የለም። ከወደቅህ ወይ ጊዜ አልነበረህም አሊያም

ስርዓቱ ሳይገባው አስቀድሞ አልተዘጋጀም ተብሎ ድጋሚ እድሉ ይሰጠሃል። እንደእኛ አገር ተባረረ ተብለው የምትሳቀቅበት፣ የምታፍርበት አይደለም።

ኢትዮጵያውያን በአውስትራልያ እንዴት ነው የሚኖሩት? ህይወታቸው ምን ይመስላል? ኢትዮጵያውያን በተለያየ መስክ ውስ

ጥ አሉ። ዩኒቨርስቲ አስተማሪ የሆኑ አሉ። የራሳቸውን ስራ የሚሰሩ አሉ። ከፍራፍሬ ለቃሚነት እስከ “ኮርፖሬት” ድርጅቶች ዋና ስራ አስኪያጅ ድረስ አሉ። የፋብሪካ ሰራተኞች አሉ። ለአረጋውያን እንክብካቤ የሚሰጥባቸው ቦታዎች ውስጥ የሚሰሩ አሉ። ታክሲ የሚሾፍሩ አሉ። በምድር ባቡር ውስጥ ባቡር ነጂነትን ጨምሮ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን አሉ። ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን የአገሩ ዜጋም እንደዚያው ነው። የስራ ባህሉ አለ። በትምህርት ያልገፋ አንድ አውስትራሊያዊ ምን ሊሰራ እንደሚችል ያውቃል። የኢትዮጵያውያንን ህይወትን ስትመለ

ከት ተማርክም አልተማርክ ሰርተው የሚያገኙት ነገር በቂ ነው። ቤት ገዝተው የሚኖሩ አሉ። ቤቱን የራሳቸው ለማድረግ እየከፈሉ የሚኖሩ አሉ። ምንም የማይሰራው እንኳ በመንግስት ድጋፍ ያለው መሰረታዊ ነገር አጥቶ አይኖርም። ብዙ ኢትዮጵያውያን ጥሩ ህይወት ነው የሚኖሩት። ራሳቸውን የጣሉ በጣም ጥቂቶች አሉ። ከመንግስት የሚያገኟትን ድጋፍ እንኳ በአግባቡ ሳይጠቀሙ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሚኖሩ አሉ። እንደእኔ አይነቱ የሚማረው መጠለያ

አለው፣ ከመንግስት በሚያገኘው ድጋፍ የሚበላውን፣ የሚጠጣውን፣ የትራንስፖርት እና የመሳሰሉትን መሰረታዊ ነገሮቹን፣ የመጽሐፍ መግዢያውን ሸፍኖ ይኖራል። የመጨረሻው ህይወት ሊባል የሚችለው እኔ የምኖረው ህይወት ነው። በእኔም ህይወት ግን ለመሰረታዊ ነገሮችን ምንም ሳላስብ ነው የምኖረው። ሙሉ ጊዜዬን ትምህርት ላይ ስላዋልኩ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እሰራለሁ። አውስትራልያ አንድ ስራ ሰርተህ መማር የምትችልበት አገር ነው። በትርፍ ጊዜህ መማር ትችላለህ። ሙሉ ሰዓት እየተማርክ በትርፍህ ጊዜ ብትሰራ እንኳ በቂ እና የተደላደለ የሚባል ህይወት መኖር ትችላለህ። አንዲህ ስልህ ግን እዚያ እስኪደረስ ፈ

ተናዎች የሉም ማለት አይደለም። ብዙ ፈተናዎች አሉ። ከዚህ ስትሄድ መጀመሪያ የምትጠብቀው ነገር ይኖራል። እንደሄድክ ስራ ላታገኝ ትችላለህ። አንዳንድ ቦታ ስራ ልታገኝ ትችላለህ። ነገር ግን ከመቀጠረህ በፊት ቢያንስ ቋንቋ በትክክል እንደምታውቅ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ። ቋንቋ እንድታሻሽል ደግሞ መንግስት ስርዓት ዘርግቷል። እንደሄድክ ይቀበሉሃል እስከፈለግከው ጊዜ በነጻ ቋንቋ እንድትማር ያደርጉሃል። መጀመሪያ ነገር መግባባት መቻልህ ነው ወደ ስራህ የሚወ

ትቆርጥ ትችላለህ። ያችን ወቅት አልፈህ ስርዓቱ ውስጥ ከገባህ በኋላ ነገሮች በጣም የተስተካከሉ ይሆናሉ። የምትፈልገውን ያህል ባይሆንም የተሻለ ህይወት ትኖራለህ። ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ ሀገራቸውን መልሰው በትንሹ ለመፍጠር ይሞክራሉ። በውጭው ዓለም “ሊትል ኢትዮጵያ” ተብሎ የተሰየሙ ቦታዎች ሁሉ አሉ። አማርኛ የስራ ቋንቋ የሆነበት ከተማም አለ። አውስትራልያ ያለው ሁኔታስ እንዴት ነው?እኛ መቼም ባህሪያችን የታወቀ ነው።

ከእነ ምጣዳችን፣ ከእነእንጀራችን፣ ከእነሽሮ በርበሬያችን ነው የምንሄደው። ካ

ራሞች አሉ። እያንዳንዱ ዓመት በዓል ተሰባስበን ድምቅ አድርገን ነው የምናከብረው። ጊዜው ስላለ በዓል መጠራራት አለ። አንድ ስራ ሰርቶ መኖር የሚቻልበት ሀገር ስለሆነ ያ ዕድሉን ፈጥሮታል። በዚያ ምክንያት የመገናኘቱ ደግሶ የመጠራራቱ ነገር አለ። ክርስትና ማስነሳት፣ ሰርግ መደገስ አለ። እንደውም ደስ የሚለው ልጆች ተምረው ሲመረቁ ኢትዮጵያኖች በጣም ደስተኛ ከመሆናቸው የተነሳ ፕሮግራም አዘጋጅተው እየተሰባሰቡ ያስመርቃሉ። ለማበረታታት የሚደረጉ ጥረቶች ትመለከታለህ። እከሌ ይማራል ሲባል እንኳ የሚሰጡት ክብር የተለየ ነው።

የኢትዮጵያውያን ማህብረሰብ በዓል ከማክበር በዘለለ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አሉ? ወደ አውስትራልያ ለሚመጡ ኢትዮጵያኖች የተዘጋጀ መረጃ ያቀርባሉ? ቢታመሙ ይረዳሉ? ትምህርት ቤት እንዲገቡ ስራዎች እንዲያገኙ መረጃ ይሰጣሉ? የኢትዮጵያውያን ማህብረሰብ በ “ኒው

ሳውዝ ዌልስ” በቅርቡ ቢሮ ከፍቷል። ለሚያስፈልገው ሰው በሚፈለገው መልኩ ትብብር ያደርጋሉ። እገዛ ለሚያስፈልገው ሰው ኢትዮጵያውያንን አሰባስበው እገዛ ይጠይቃሉ። በአጋጣሚ መጥቶ እዚያው መቆየት ለሚፈልግ ሰው ለኢሚግሬሽን ደብዳቤ ከመጻፍ አንስቶ ጉዳያቸውን አስተካክለው መጻፍ ለማይችሉ ሰዎች እገዛ እስከመስጠት ድረስ የተለያየ እርዳታ ያደርጋሉ። አንድ ስደተኛ ወደ አውስትራልያ ሲመ

ጣ አገር የሚያሳየው፣ የሚመዘገብበትንቦታ ፣ የሚወጣ የሚገባበትን መንገድ፣ ትራንስፖርት አጠቃቀሙን ሁሉ የሚያሳየው አለ። የአውስትራልያ መንግስት ይህንን ስርዓት አመቻችቷል። በማህበረሰቡ ደረጃ ግን ይህ በቂ አይደለም የሚል እምነት አለ። ማህበረሰቡ አዲስ የሚመጡ ስደተኞችን ተቀብሎ፣ አገር ለማላመድ፣ ከስርዓቱ ጋር እንዲዋህዱ ለማድረግ፣ ማድረግ የሚገባቸውን የሚጠቆም የምክር አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው እንደገና ተዋቅሯል። ለስደተኛው አስፈላጊውን መረጃ አዘጋጅቶ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እየተሰሩ ናቸው። በእርግጠኝነት የምነግርህ ከዚህ በኋላ ወደ ሲድኒ የሚመጡ ስደተኞችን ማህብረሰቡ ይቀበላቸዋል። የተለያየ መረጃ አዘጋጅቶ ይቆያቸዋል። የሚፈልጉት መስመር ላይ እንዴት መሄድ እንዳለባቸው፣ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ሀሳብ የሚሰጣቸው ይኖራል።

የአውስትራሊያ ስም ከስደተኞች እስር ጋር በተደጋጋሚ ሰነሳ ይሰማል። በርካታ ስደተኞች በታጠረ ቦታ ለረጅም ጊዜ እንደሚቆዩ የሚያሳዩ የብዙሃን መገናኛ ዘገባዎች በየጊዜው ይደመጣሉ። የአውስትራሊያ መንግስት ወደ አገ

ሩ ለሚመጡ ስደተኞች ያለው አቀባበል ምን ይመስላል? የኢሚግሬሽን ፖሊሲውስ? አውስትራልያ ያደገች ሀገር እንደመሆ

ኗ የሰው ኃይል ትፈልጋለች። በዚያ ሰፊ መሬት ላይ ከ25 ሚሊዮን የማይበልጥ ህዝብ ነው ያላት። ገና ብዙ ህዝብ የሚሰፈርባት ነች። አሰፋፈሩ ግን ያለውን ሁኔታ እና የኑሮ ደረጃ ሳይለወጥ መሆን አለበት። ለእንያንዳንዱ ነገር በፖሊሲ ደረጃ ያስቀመጡት ነገር አለ። ለምሳሌ የዋጋ ግሽበት እና የስራ አጥ ብዛት የት ድረስ ተቀባይነት እንዳለው ያስቀመጡት ነገር አለ። በዚህ ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ ያለው ምንም አይነት የአሰፋፈር ሁኔታ አይቀበሉም። እዚያ ለመስፈር የሚፈልገው ሰው ቁጥር ደግሞ ከፍተኛ ነው። አውስትራልያ በዩ.ኤን.ኤች. ሲ. አር የ

ሚመሩላትን ስደተኞች ትቀበላለች፡፡ ችግሩ ያለው በግል “ስፖንሰር” ተድርገው የሚመጡት ጋር ነው። እንደ ፊጂ እና ፖለኔዥያን ደሴቶች ካሉ ጎረቤት ሀገሮች፣ ከኤንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣ ቬትናም፣ጃፓን፣ ኮሪያ፣ ቻይና ፍልሰቱ በጣም ከፍተኛ ነው። ከእነዚህ ሀገራት በጀልባ የሚመጣው ስደተኛ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ካምፖች መስርተዋል። ካምፖቹ የተከፈቱት የአውስትራልያ ዋናው መሬት ላይ ሳይሆን ደሴቶች ላይ ነው። በእነዚህ ካምፕ ውስጥ ያሉትን እያጣሩ የሚገባቸውን ሰዎች እየመረጡ ነው የሚያስገቡት። በቅርቡ ከጎረቤት ሀገሮች የአሁኗ ጠቅ

ላይ ሚኒስቴሯ ጎረቤት ሀገሮች ከአንዱ ጋር ስምምነት ተፈራርመው ካምፕ ውስጥ የሞነሩ ስደተኞችን ወስደው ስምምነት የተፈራረመው ሀገር ወስደው አስፍረዋቸዋል። ይህ የተደረገው በአውስትራልያ ፖለቲከኞች ላይ ግፊቱ ከመጨመሩ የተነሳ ነው። የስደተኛ ጉዳይ ትልቅ የፖለቲካ አጀንዳ ነው። አዲሲቷ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከመመረ

ጧ በፊት አንዱ የምርጫ ቅስቀሳ አጀንዳዋ የነበረው “አዲስ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ አመጣለሁ” የሚል እንደነበር አስታውሳለሁ። ትክክል ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚ

ኒስቴር ኬቨን ራድ በተመረጠ ጊዜ እስከ 180 ሺህ ስደተኛ ለማስገባት ቃል ገብተው ነበር። እርሷ ስትመረጥ ግን በዓመት ከ145ሺህ ስደተኛ በላይ አይገባም ብላ ነበር። ምክንያቷ ደግሞ አሁን ያለንበት ኢኮኖሚያችን ከዚህ በላይ አይሸከምም በሚል ነበር። አንዱ የምርጫ መወዳዳሪያ አጀንዳዋ ይሄ ነበር። የተቃዋሚው መሪ ቶኒ አቦት እኛ የተሻለ “ኢሚግሬሽን ፖሊሲ” እናጠብቃለን እያለ ይሞግታት ነበር። እርሷ ግን “አንተ ኢሚግሬሽን ፖሊሲ አጠብቃለሁ የምትለው በዓመት 170 ሺህ ስደተኛ እቀበላለሁ ብለህ ነው። እኔ ተሰርቶ በተጠናቀቀ ፖሊሲዬ 145 ሺህ ስደተኛ ለመቀበል ነው ያቀድኩት። እንዴት አድርጎ ነው ያንተ ከእኔ የተሻለ ፖሊሲ ሊሆን የሚችለው” ብላ በክርክራቸው ወቅት ስትናገር አዳምጫለሁ።

q አውስትራልያውያን ራሳቸውን “ኦዚ” ብለው ነው የሚጠሩትq አብዛኞቹ አውስትራልያውያን ከሌላ ሀገር መጥተው የሰፈሩ ናቸው።

የመጀመሪያዎቹ የአገሬው ተወላጆች “አቦርጂኒ” ይባላሉ። q ከ179 አገሮች የተውጣጡ ማህበረሰቦች በአውስትራልያ ውስጥ

ይገኛሉ። q እንደ ሲድኒ ዓይነት ከተሞችን የሚጎበኝ ሰው እስያ ያለው

ሊመስለው ይችላል። በርካታ እስያውያን በሲድኒ ይኖራሉ። q ቱርኮች እና ኢጣሊያውያን እንደ “ኦዚዎች” ሁሉ ለረጅም ዓመታት

በአውስትራልያ በመኖራቸውበአገሩ ላይ የሚሰማቸው የባለቤትነት ስሜት ከፍተኛ ነው። q ቀድሞ 100 የአውስትራልያ ዶላር በ60 አሜሪካ ዶላር ይመነዘር

ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ተመሳሳይ መጠን ያለው አውስትራሊያ ገንዘብ 110 የአሜሪካን ዶላር ድረስ እየተመነዘረ ይገኛልq የአውስትራልያ አነስተኛ የደመወዝ መጠን ተብሎ የሚጠቀሰው 15

ዶላር ነው። ዝቅተኛ የሚባለውን ክፍያ የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን በሰዓት 18 ዶላር ያገኛሉ። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በሰዓት ከ20 እስከ 25 ዶላር የሚከፈልባቸውን ስራዎች ይሰራሉ። q አውስትራልያ በዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በኩል ከሚመጡላት ስደተኞች

መካከል በዓመት ስድስት ሺህ ያህሉን ለመቀበል ቃል የገባች ሲሆን “ስፔሻል ሂዩማንቴሪያን ፕሮግራም” በተሰኘው የመንግስቷ የድጋፍ እቅድ በዓመት 7750 ስደተኞች ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

ምፓላ የምታየውን። የሽሮ በርበሬ መደብር ሜልበርን ውስጥ ታገኘዋለህ። አምስት ስድስት ተከታታይ የሐበሻ ሆቴሎች ያሉበት አለ። እንደ ዋሽንግተን 18ኛው ስትሪት ሜልበርን ላይ የሐበሻ ሰፈር እየተፈጠረ ነው። ሲድኒም እንደዚያ ነው። አሰፋፈራችን አንዱ ቀድሞ የሄደውን ተከትለህ ነውና የምትገባው ሲድኒ ላይም ሶስት አራት ቦታዎች ላይ ሐበሻ በብዛት ያለባቸው አካባቢዎች አሉ። እንጀራውም፣ ከትፎውም፣ ሽሮውም፣ በየዓይነቱውም ሁሉም ነገር አለ። ተሰባስባችሁ በዓላት ታከብራላችሁ? የኢትዮጵያ ማህብረሰብ (ኮሚዩኒቲ) አ

ለ። በኮሚዩኒቲ ደረጃ የሚዘጋጁ ፕሮግ

ስድህ። ሁለተኛ እያንዳንዷን ስራ ለመስራት “ሰርተፍኬት” ሊኖርህ ይገባል። የጥበቃ ስራ ወይም የአረጋውያን እንክብካቤ ሊሆን ይችላል። ስራ መያዝ በምትፈልግበት ሙያ ተምረህ “ሰርተፍኬት” ይዘህ ነው ስራ የምትጀምረው። እንዲህ አልጋ በአልጋ የሆነ ምንም ነገር የለም። ታሽተህ ታሽተህ በአውስትራልያ ስርዓ

ት ውስጥ መግባት የምትችለው ከአንድ ወይም ከሁለት ዓመት በኋላ ነው። ለዕድለኞች ስራ ሊገኝ ይችላል። በሄደ ማግስት ስራ ያገኘ አለ። ሁለት ዓመት ተቀምጦ ስራ ያላገኘም አለ። ለምሳሌ እኛ የሄድንበት ጊዜ በዓለም የፋይናንስ ቀውስ ምክንያት ብዙ ሰዎች ከስራ የወጡበት ነበር። ብዙዎቻችን ስራ ብንፈልግም አላገኘንም። ከስራ የተፈናቀለው ወደሌ

ላ ስራ የሚገባበት ስለነበር እዚያ ሀገር ልምድ ያለው እያለ እኛን ማንም አይቀጥረንም ነበር። ስራ ለማግኘት ብቃት ያለው መሆን አ

ለብህ። በዚህ በጣም ያምናሉ። የሚፈለገውን ወረቀት እስክትይዝ፣ ከዚያ ደግሞ የመጀመሪያውን አይን መግለጫ ስራ ይዘህ የአገሬውን እውቀት እስክታገኝ ድረስ ትታሻለህ። በመንግስት ድጋፍ ነው የምትኖረው። በዚህ ጊዜ ቤተሰብህን፣ ወንድምህን፣ ጓደኛህን ላትረዳ ትችላለህ። ከዚህ ስትሄድ የምታስበው ሌላ ነው። በዚህም ምክንያት ብዙዎች ጭንቀት ላይ ይወድቃሉ። በተለይ ከሶስት ወር በኋላ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ በጣም ተደብረህ፣ ሁሉ ነገር አስጠልቶህ፣ ተስፋ ል

የእኛ ሰው ... ከገጽ 9 የዞረ

ጥቂት ስለ አውስትራልያ

Page 23: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011) ሐበሻዊ ቃና 23

ስፖርት

ከ40ሺህ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ የተሻለ ክፍያ እንዲቀርብለት ወኪሉ መወትወቱ የሚገርም አይሆንም:: የኤምሬትስ ዓመታዊ የትኬት ሽያጭ በ6.5 በመቶ ማሻቀቡ ደጋፊውን እንዳያሸሸው እና ገቢ እንዳይቀንስ ተፈርቷል:: ቬንገር በእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ው

ስጥ ተከበውም ቢሆን ከአናታቸው ካሉት ማንዩናይትድ፣ ማን ሲቲ እና ቸልሲ ጋራ መፎካከር እንደ ክር የቀጠነውን የአርሰናል ሕይወታቸውን ይወስናል:: የቀድሞ ክብሩን ለመመለስ የሚተጋው ሊቨርፑል እና ቶተንሐም ተጨማሪዎቹ ተቀናቃኞች ናቸው :: የክፍያ መጠኑን ከግምት በማስገባት የአርሰናል የግዢ ዝርዝር ውስጥ ሊካተቱ የሚ

ጠዋል። “ባለፈው ጥርም ይሄዳል ሲባል ነበር:: አሁንም ይወጣል የሚሉ ዜናዎች ከመሰማታቸው በስተቀር አርሰናልም ሆነ ሌላ ክለብ በራችንን አላንኳኳም” ሲሉ ገልፀዋል:: ሌላው እንቆቅልሽ የአንድሬ አርሻቪ

ን ጉዳይ እልባት አለማግኘቱ ነው:: የባለፈው ዓመት እንቅስቃሴው ደካማነት ቆይታውን አጠያያቂ አድርጎታል:: አምና ተከላካዮቹን ኮስቼንሊ እና ስኪላቺ በማስፈረም የተፈጠረው ስሕተት እንዳይደገም የፕሪምየር ሊጉ ልምድ ያላቸው የቦልተኑ ጋሪ ካሂል፣ የብላክበርኑ ክሪስቶፈር ሳምባ እና የኤቨርተኑ ሲልቪያን ዲስታን ላይ አነጣጥረዋል:: የክሊሺን ቦታ ኬራን ጂብስ ወይም ቶማስ ቨርማለንን ወደ ግራ መስመር በመግፋት መተካት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል::የቡድኑ አስተዳደር አሰራሩን የማይቀ

ይር እና የቬንገር ፍልስፍና ባለበት የ

1. የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ፡-የዘንድሮው ሊግ በቡና አሸናፊነት መጠናቀቁ በቀጣይ የውድድር ዘመን ለሌ

ሎች ክለቦቸም የሞራል ስንቅ ይሆናቸዋል፤ “ዋንጫ ማንሳት እንችላለን” የሚል ተስፋም ያስጨብጣቸዋል፡፡ ዋንጫ የለመደው ጊዮርጊስም ቢሆን በባላንጣው ትልቁን ዋንጫ መነጠቁ ከፍተኛ ቁጭት ውስጥ ይከተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የ2004 ፕሪምየር ሊግ ጥልቅ ፉክክር የሚታይበት ይሆናል፡፡ ደደቢት፣ ቡና እና ጊዮርጊስ ሊጉን የሶስት ፈረሶች ፉክክር ያደርጉታል፡፡ የመጀመሪያው የቡና ፈተና እዚህ ጋር ይሆናል፡፡

2. የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ፡- ከ1990 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡና ወደ ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድ

ር ተመልሷል፡፡ የኢትዮጵያ ክለቦች ብቃት በዚህ መድረክ ደከም ያለ በመሆኑ ቡድኑ የማጣሪያ ማጣሪያ ውስጥ ለመግባት ይገደዳል፡፡ በዚህ መድረክ መካፈል አዲስ የበጀት ርዕስ ይዞ ይመጣል፡፡ ቢያንስ አንድ የውጪ ጉዞ፤ በለስ ከቀናቸው ደግሞ ሁለት እና ሶስት ጊዜ በአየር መብረራቸው አይቀርም፡፡ በአህጉራዊው መድረክ ላይ ብቁ ሆኖ ለመቅረብ ደግሞ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበት በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ የሥራ አመራር ቦርዱ እና አዲሱ የደጋፊ ማህበር በዚህ በኩል ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡

3. የዝውውር ገበያው፡-ክለቡ ከዋንጫው በኋላ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባደረገው ስብሰባ የአሁ

ኑን ድል ተንተርሶ በቀጣይ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ዕቅድ ነድፏል፡፡ ይህ ዕቅድ መሬት ወርዶ ፍሬው የማይታይ ከሆነ ግን በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ትልቅ ፈተና ይፈጥርባቸዋል፡፡ ያሉትን ተጫዋቾች ለማሰንበትና አዳዲሶችን ለማስፈረም ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ በዝውውር ገበያው የክለቦች ጡንቻ ከዓመት ወደ ዓመት እየፈረጠመ መጥቷል፡፡ ቡና ዋንጫ ስላነሳ ብቻ የሚፈልገውን ተጫዋች የራሱ ማድረግ አይችልም፡፡ በድጋሚ በዝውውር ገበያው ከተፎካካሪዎች አጠገብ ለመቆም ፋይናንስ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡

4. የደጋፊዎች ሚና፡-አሁን በኃላፊነት ላይ ያለው የደጋፊዎች ማህበር ጠንክሮ በመስራቱ ብዙ ነገሮ

ችን ተከላክሎ ከውጤት ማማ ላይ ለመውጣት በቅቷል፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደታየው በቡና ጓዳ ረጃጅም እጆች ይበዛሉ፤ አዛዡ ብዙ ነው፡፡ እነዚህ እጆች መረማመጃ የሚያደርጉት ደግሞ የራሱን ደጋፊዎች ነው፡፡ የደጋፊዎች መብትና እና ግዴታ ብሎም ሚናቸው ወሰን እና ልክ ካልተበጀለት በድል ማግስት ሌላ ችግር ይዞ ይመጣል፡፡

5. አስተዳዳሪዎቹ፡-የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ

ልደ ጊዮርጊስ ግንቦት 8 ቀን 2001 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል የስንብት ንግግር ሲያደርጉ “ለአንድ ክለብ እየሠራን ነበር” የሚል ማስተባበያ ቢያቀርቡም ቤቱ ሊሰማቸው አልፈቀደም፡፡ ጊዜው በመርፈዱ ያቀረቡት “ውንጀላ” አላተረፋቸውም፡፡ የቡና ኃላፊዎችም ጣታቸውን ወደ ውጪ እየቀሰሩ የውስጥ ችግራቸውን ለመሸፈን የሚያደርጉት ሩጫ ከአሁን በኋላ ውሃ የማንሳት አቅሙ የወረደ ይሆናል፡፡ አመራሩ ራዕይ እና ግብ ይዞ ካልተነሳ አወዳደቁ የከፋ ይሆናል፡፡ በተለይ በጽህፈት ቤት አስተዳደር፣ በባለሙያ ቅጥር፣ በገበያ ማስፋፋት እና በክለብ አወቃቀር ዙሪያ ያለው ግዙፍ ጉድፍ ለውይይት የሚቀርብበትና መሠረት የሚጣልለት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡

“በዋናዎቹ የሀገር ውስጥ እና ሻምፕዮንስ ሊግ ውድድሮች ለታላቅ ስኬት ይመራናል” ይላል የቼልሲ ድረ ገፅ ከአዲስ ተቀጣሪው አሰልጣኝ የሚጠብቀውን በግልፅ ሲያውጅ:: ቼልሲ በአብራሞቪች አገዛዝ ዘመን ስምንት የሀገር ውስጥ ዋንጫዎች ሲያገኝ፣ አራት ጊዜ የሻምፕዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ እና አንድ የዋንጫ ተፋላሚ መሆኑ ሲታይ ግን የአሰልጣኙን የቤት ስራ ከባድ ያደርገዋል:: የ33 ዓመቱ አንድሬ ቪላስ ቦአስ የፕሪምየር ሊጉ ወጣት አሰልጣኝ ሲሆን ቢሊየነሩ አብራሞቪች ሰማያዊዎቹን ከተቆጣጠሩ ካለፉት ስምንት ዓመት ወዲህ የተቀጠረ ሰባተኛው አለቃ ነው::ከአንድሬ መሾም ዕለት ጀምሮ ከሀገሩ ል

ጅ ዦዜ ሞሪንሆ ጋራ ማነፃፀር የእንግሊዝ ብዙሃን መገናኛ ስራ ሆኗል:: ነገር ግን አሰልጣኙ በቅጥራቸው ማግስት ራሳቸውን “ስፔሻል ዋን” ብለው ከሰየሙት ሞሪንሆ ተቃራኒ አቀራረብን መርጧል:: በመጀመርያ ዕለት በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይም ለደጋፊው ያስተላለፈው መልዕክት ውጤት የሚገኘው በቡድኑ እንጂ በአንድ ግለሰብ እንዳልሆነ ነው:: “ከአንድ ሰው ምንም አትጠብቁ” ብሏል ለክለቡ ቲቪ:: “በጋራ ስራ በሚገኝ ጥምረት የቡድን ጥንካሬ እንድንፈጥር ጠብቁ:: ይህም ለአዲሱ አመራር ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው:: የእኔ መምጣት ሳይሆን ዋናው ቁም ነገር የክለቡ ውጤታማነት ቀጣይ መሆኑ ነው” ያለው ፖርቱጋላዊ ከኃላፊነቱ ብዙ እንደሚፈለግ አልሸሸገም:: “የእኔ ፈተና በማሸነፍ መቀጠል እንደሆን ምንም ጥርጥር የለውም:: አንድ ሰው ብሆንም የስኬት ጥማቱ አለኝ:” ብሏል ቪላስ ቦአስ::ቼልሲ ለአሰልጣኙ 4.4 ሚልዮን ፓው

ንድ ዓመታዊ ደመወዝ ለመክፈል ሲስማማ ከፖርቶ ጋራ የነበረውን ውል ለማፍረስ የወጣው ወጪ ግን ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏል:: እግረ መንገዱንም በወጣቱ መሪ ላይ ያለውን አመኔታም አረጋግጧል:: 13.3 ሚልዮን ፓውንድ ለፖርቶ ካሳ ሲከፍል ያላቅማማው የአብራሞቪች አመራር እ.ኤ.አ ከ2004 ወዲህ አሰልጣኝ ለመቅጠር እና ለማባረር 64 ሚልዮን ፓውንድ አውጥቷል::ቀጣዩ ስራ ደግሞ አሰልጣኙ የሚፈልገ

ውን ተጨዋቾች ለመግዛት የማይጎድለውን የሩሲያዊውን ሳምሶናይት ይዞ መንቀሳቀስ ነው:: አንድሬ የአሰልጣኝ ቡድኑን ከፖርቶ በማምጣት ሲያጠናክር የቀድሞ የቸልሲ ኮከብ እና አምና ዌስትብሮምዊችን የመራውን ሮቤርቶ ዲማቴዮን ረዳቱ አድርጎ ሾሟል:: ከዚህ ቀደም ለሞሪንሆ በፖርቶ፣ ቼልሲ እና ኢንተር ሚላን ለሰባ

ት ዓመታት የተጨዋች መልማይ ሆኖ ማገልገሉ ለአሁኑ ስራው የሚሆኑ ተሰላፊዎችን ለማግኘት እንዳይቸገር ይረዳዋል:: ባለፈው ዓመት ፖርቶን ለአራት ዋንጫ

ዎች ካበቃ ጀምሮ ከሞሪንሆ ጋራ ንግግር ማቆሙ ኮሎምብያዊውን አጥቂ ራዳሜል ፋላካኦን ለመግዛት የሚያደርጉትን ፍጥጫ አጓጊ አድርጎታል:: “ምርጥ ተጨዋቾች ቢኖሩንም ቡድኑን ለማጠናከር ሌሎችን ማስፈረም ያስፈልጋል” ያለው ቦአስ ከሞሪንሆ መልማይነት በሁለት ዓመታት ልዩነት ውስጥ የቼልሲ አሰልጣኝ መሆኑ እንደደነቀው ገልፅዋል:: “የሆነ እብደት ቢመስልም ከእውነታው መደበቅ አልችልም:: ወጣት ብሆንም ልምዱን ለማግኘት እድሉን መጠቀም አለብኝ:: ፖርቶንም ሆነ ቼልሲን የዦዜን ፈለግ ለመከተል ብዬ አልተቀበልኩም:: ሁለቱም ክለቦች በዓለም የሚፈለጉ ናቸው:: የእኔና የሞሪንሆ

የሰባት ዓመት ግንኙነት ሞያዊ እና በጥሩ ጓደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው:: ከእንደእርሱ ያለ አሰልጣኝ ጋራ ስትነፃፀር የበለጠ ኃላፊነት ይሰማሃል::”በእግር ኳስ ውስጥ ውስጣዊ ተነሳሽነት

ቁልፍ ሚና ስለመጫወቱ ፍፁም እምነት እንዳለው የሚናገርው አንድሬ ከሞሪንሆ ጥላ ለመውጣት የቼልሲን የረዥም ጊዜ ጥማት የሆነውን የሻምፕዮንስ ሊግ ዋንጫን ለአብራሞሺች ማበርከት ያስፈልገዋል:: ይህንንም ከግብ ለማድረስ ስታምፎርድ ብሪጅን ጥራት ባላቸው ተጨዋቾች ለመገንባት ወጥኗል:: ለዚህም ፋልካኦ፣ ሉካ ሞድሪች፣ ሳሚር ናስሪ እና ዦአኦ ሙቲንሆን በግዢ እቅዱ ውስጥ አስገብቷል:: “ስፔሻል ዋንን” ወደ “ግሩፕ ዋን” ቀይሮታል “እግር ኳስ የአንድ ሰው ትርኢት አይደለም” በማለት:: “እኔ” ሳይሆን “እኛ!”

አንድሬ-የቼልሲ አዲሱ ሞሪንሆ?

አዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ አንድሬ “እግር ኳስ የአንድ ሰው ትርኢት አይደለም” በማለት የሞሪንሆን “ስፔሻል ዋን” ፍልስፍና ወደ “ግሩፕ ዋን” ቀይሮታል

ላን ከተማ ቢጓዙ ምናልባት ሰበር ዜና ይዘው ሊመጡ ይችላሉ:: ይህም ካልተሳካ ዋንጫ በታሪኬ ውስጥ እንዲካተት ስለምፈልግ ኋይት ኅርት ሌን በቃኝ የሚለው ጥበበኛው ሉካ ሞድሪች አማራጭ አላቸው:: ክሮሽያዊው ለአሰልጣኙ ሀሪ ሬድናፕ አሰናብቱኝ ማለቱ አሰፍስፈው ለሚጠብቁት ቼልሲ እና ዩናይትድ የምስራች ነው:: ስለዚህ የገንዘብ ችግር የሌለባቸው ፈርጉሰን ተቀናቃኛቸውን ቼልሲን መቅደም ይጠበቅባቸዋል::ፈርጉሰን ከግዢ ዘመቻቸው ጎን ለጎን አ

ላስፈላጊ ተጨዋቾችን በሽያጭ እያሰናበቱ ነው። በሻምዮንስ ሊግ ፍፃሜ ከተጠባባቂ አሰላለፍ ውጪ የሆነው አጥቂው ቤ

ርባቶቭ ቀዳሚው ተጠቃሽ ነው። ተከላካዩ ጆን ኦሼ የኦልድ ትራፎርድ ትዝታ ለመሆን ክለብ ሲያፈላልግ ዌስ ብራውን ሰንደርላንድን ተቀላቅሏል:: ቤርባቶቭ መድረሻው ቫሌንሲያ ወይም ጁቬንቱስ ይሆናል ተብሎ እየተወራ ነው:: የቀድሞው የቀኝ መስመር ተከላካይ ጋ

ሪ ኔቭል የዩናይትድ አካሄድን በማየት መጪውን የኦልድ ትራፎርድ ብሩኅ ጊዜ ተንብይዋል:: “ውጤት የተጠሙ ተጨዋቾች ስላሉ የ1999ኙን የአውሮፓ ድል የመድገም ተስፋ አላቸው:: ምክንያቱም እኛም ዋንጫ ከማግኘታችን በፊት ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ከጫፍ እየደረስን ተሸንፈናል:: ስለዚህ ተራራውን ለመውጣት ከባድ ቢሆንም ማንችስተር እና ሪያል ማድሪድ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የባርሳን ዝና ይነጥቁታል” ብሏል::

በኤርሚያስ አማረ- ቤልጅየም

ነጥቦች ለኢትዮጵያ ቡና 5የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንደተጠናቀቀ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሰ

ለሞን ክፍሌ ጋር አጭር የስልክ ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ መሥራችና የሥራ አመራር ቦርድ አባል መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ “ፕሪምየር ሊጉ በአዲስ ፎርማት ከተጀመረ አንስቶ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደሎችን ስናስተናግድ ቆይተን ለዚህ ድል በመብቃታችን ተደስተናል” ብለዋል፡፡ የተገኘውን ድል ማጣጣም ራሱን የቻለ ቦታ ቢኖረውም በቀጣይ ስለ ወደፊቱ ማሰብ ግን ቡናን ወደኋላ ሲጎትቱት ከነበሩት ውስጣዊ ጣጣዎች ለመላቀቅ መንደርደሪያ ሊሆን ይገባል፡፡ ለዛሬ አምስት ነጥብ ነጥቦች ይታዩኛል፡፡

ይህ ጹሁፍ ከኤርሚያስ “ፌስ ቡክ” ገጽ የተወሰደ ነው

ችሉ ተጨዋቾች ወጣት እና የግል ችሎታቸው ላቅ ያሉ ነገርግን ለመሻሻል የተጠሙእንደሚሆኑ እርግጥ ነው::አስራ አንድ ሚልዮን ፓውንድ የወጣ

በት የቡድኑ የመጀመርያ ፈራሚ አይቮሪኮስታዊው አጥቂ ጀርቪንሆ ከላይ የተባለውን መስፈርት የሚያሟላ ሲሆን ሌላኛው እጩ አርጀንቲናዊው ሪኪ አልቫሬዝ የመሐል ሜዳ አቀናባሪነት ሚናን ከፋብሪጋስ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል:: የ24 ዓመቱን አማካይ ዝውውር ለማሳካት ከኢንተር ሚላን ጋራ መፎካከር ያስፈልጋል:: የሳውዝሃምፕተኑ የ17 ዓመት የመስመር ተሰላፊ አሌክስ ቻምበርሊን የዋልኮትን ፈለግ ተከትሎ ወደ ኤምሬትስ ይመጣል ተብሎ ቢታሰብም እስካሁን ከወሬ የዘለለ ነገር አልታየም:: የክለቡ አሰልጣኝ ኒጀል አድኪንስም “ተጨባጭ የዝውውር ጥያቄ ከአርሰናል እንዳልቀረበላቸው” አረጋግ

ሚፀና ከሆነ አርሰናል በአዲሱ ውድድር ዘመን የሚቀርበው በእነዚህ ተጨዋቾች ነው:: የቡድኑን ተጨዋቾች ሊነጥቁ የመሚመጡ ቱጃር እና ባላንጣ ክለቦችን ከበር ለመመለስ የሚያስችል ዘዴ ያስፈልጋቸዋል:: አለበለዝያ የናስሪ እና የፍላሚኒ ዓይነት ክስተቶች በመጪዎቹ ዓመታትም ከመድፈኞቹ ጋራ ተያይዘው የሚነሱ ዜናዎች ይሆናሉ:: አርሰናሎች አምና ሜዳ ላይ ነጥብ ለማግኘት ተፎካክረው ሊሆን ይቸላል:: የግዢ ገበያው ላይም ጥረት ያደርጉ ይሆናል:: ይሁን እንጂ ስብስቡ የብዙኃኑን ደጋፊ ፍላጎት በበቂ ሁኔታ ይመልሳል ወይ የሚለው ጥያቄ እንዳወያየ ይቀጥላል:: ታዋቂው ተንታኝ ማርቲን ሳሙኤልም ይህን ከግምት አስገብቶ ይመስላል “ተቀበሉት፣ አርሰናል ከእንግዲህ ኮከቦችን የሚስብ ሊሆን አይችልም” ያለው::

ማንዩናይትድን...ከገጽ 24 የዞረ

“አርሰናል...ከገጽ 24 የዞረ

በካሳሁን ይልማ

በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

ስ ዘጠኝ ጊዜ ዋንጫውን ሲያነሳ ፣ መብራትና ሀዋሳ ከነማ እኩል ሁለት ጊዜ አግኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን ቡና አሁን አራተኛ ሆኖ ተመዘግቧል፡፡ ቡና የዘንድሮውን ዋንጫ በማሸነፉ

100 ሺ ብር ሲሸለም፣ ሁለተኛ የወጣው ጊዮርጊስ 50ሺ፣ ሶስተኛ የወጣው ደደቢት ደግሞ 25 ሺ ብር ተቀብለዋል፡፡ ቡና እና ጊዮርጊስን ከዋንጫ ያለያየው 1 ነጥብ ነው፡፡ ቡና 61፣ ጊዮርጊስ በበኩሉ 60 ነጥብ አስመዝግበው ነው ውድድሩን የጨረሱት፡፡ ለቡና ወሳኝ በነበረው የመጨረሻው የሙገር ጨዋታ ቡድኑ ሶስት ሙሉ ነጥብ ቋጥሮ እንዲወጣ ያስቻለ

ውን ሁለተኛውን እና የመዝጊያውን ጎል ያስቆጠረው 17 ቁጥር ለባሹ አጥቂ መድሀኔ ታደሰ ነበር። ይህ ተጨዋች ቡና የዚህ ዓመት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሲዳማ ቡና ጋር ይርጋለም ላይ ሲያደርግ የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረ ነበር፡፡ የቡና መጀመሪያውም፣ የመጨረሻውም ግቦች የእርሱ ሆነዋል፡፡እንደ መድሀኔ ሁሉ የቡናው አምበል ግ

ጥምጥሞሽም ያስገርማል። የአምበሉ ስም እድሉ ደረጀ ነው። እውነትም እንደስሙ እድለኛ ነው፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ለቡና የመጀመሪያውን ዋንጫ አንስቷል፡፡ እድሉ ቡና ውስጥ ረጅም አመት የቆየ ተጨዋች ነው፡፡ የመጨረሻው ጨዋታ አንዳለቀ በለማመን ስሜት ራሱን ይዞ ሜዳ ላይ ቁጭ ብሎ ነበር፡፡ የ32 ዓመቱ እድሉ ደረጀ በሰው ኃይል አመራር ማኔጅ

መንት ዘንድሮ ይመረቃል፡፡ እንደ እድሉ ሁሉ ሌላው የቡና ተጫዋች አራዶምም በዚህ ዓመት ነው የሚመረቀው። የቡና ሌሎች ተጫዋቾች የትምህርት ደረጃም ከፍ ያለ ነው፡፡ በረኛው ወንድወሰን ዲግሪ አለው፣ ተስፋዬ ቢያቋርጥም የሕክምና ተማሪ ነበር። “እየተማርን ዋንጫ እንበላለን”፤ “እየተጫወትንም እንማራለን” ነው ነገሩ። ለቡና የዘንድሮ ውጤት ማማር ከፍተ

ኛ አስተዋጾኦ ያደረጉት መሀል ሜዳ ያሉ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ በተለይ ዳዊት፣ መሱድና ምንያህል ይጠቀሳሉ፡፡ በፕሪሚየር ሊግ ታሪክ የመጀመሪያ ዋንጫ በማምጣታቸው ተጫዋቾቹ ሪከርድ ሽልማት አንደሚሰጣቸው እየተነገረ ነው፡፡ ደጋፊ ማህበሩ ለአሰልጣኙ መኪና ሊገዛ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ሰኔ 28 ቀን 2003 አዲ

ስ አበባ ስታዲየም አጠገብ ባለ ሆት ስፖት ሆቴል ውስጥ የቡና ደጋፊዎች ግብዣ አዘጋጅተው ነበር፡፡ ጭፈራውና ግብዣው የደመቀ ነበር፡፡ ሁሉም ቢጫ ማሊያ አድርገው የዋንጫውን ድል በደስታ አጣጥመውታል። ደጋፊው ለቡድናችን ውጤት ለአስገኙ

ት ሽልማት ይገባቸዋል በሚል በየቦታው የተለያየ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ አዲሱ የደጋፊ ማህበር ብዙ የአሰራር ለውጥ በማድረግ፣ በደጋፊው ውስጥ ንቅናቄ በመፍጠር፣ ለተጫዋቾቹ ትጥቅ በማቅረብ እና ሞራል በመስጠት ለዋንጫው መገኘት ትልቅ ምክንያት ሆኗል፡፡

ይህ ጹሁፍ የተወሰደው ገነነ መኩሪያ ቀድሞ ያዘጋጀው በነበረው ጋዜጣው ስም ከከፈተው

እና ሊብሮ ዶት ኮም ከተሰኘው ድረ ገጽ ሲሆን መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል

ከገጽ 24 የዞረ

“ቡና ገበያ...

Page 24: Habeshawi Kana 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)ሐበሻዊ ቃና24

ስፖርት

በሮቢን ቫን ፐርሲ አዕምሮ ውስጥ አንድ ጥያቄ ይመሳሰላል:: የቡድን አጋሮቹ በኤምሬትስ የመውጫ በር ላይ መሆን ግርታ ቢፈጥርብትም እውነታውን በሚገባ ተርድቶታል:: ፋብሪጋስን እና ናስሪን ለመተቸት ከመጣደፍ ይልቅ ምክንያታዊነትን ማየት መርጧል::“ አርሰናል ከተጫዋች ጋራ የደመወዝን ሁኔታ ሲደራደር ከተወሰነ ጣራ በላይ ፈቀቅ አይልም” ይላል ሆላንዳዊው ሲያስረዳ:: “ ክለቡ የተትረፈረፈ ገንዘብ አይከፍልም:: ችግሩን ለመቅረፍ ይህን ማሻሻል እና ወደ ከፍተኛ ክፍያ ማሳደግ አለባቸው :: 27 እና 28 ዓመት ዕድሜ ላይ ከደረስክ ሶስት እና አራት እጥፍ ወደ ምታገኝበት ሌላ ቦታ የመሄድ ውሳኔን እረዳለሁ:: ያን የሚያህል ክፍያ ደግሞ አርሰናል የሚያቀርብ ከሆነ ተጨዋቹ የመልቀቅ ፍላጎት አይኖረውም::”እንደዚህ ያለ ቀውስ ለመድፈኞቹ አዲ

ስ አይደለም:: በ2008 የውድድር ዓመት መጨረሻ ላይ ማቲዩ ፍላሚኒ በቦስማን ሕግ (ነፃ ዝውውር) ወደ ኤሲ ሚላን መጓዝ እና የአሌክሳንደር ህሌብ በባርሴሎና እይታ ውስጥ መውደቅ ከዘንድሮው ክስተት ጋራ ያመሳስለዋል:: በወቅቱ የቁልፍ ተጨዋቾች ክለቡን ለመልቀቅ መወሰን በሌሎች ተጨዋቾች ላይ የሚፈጠረው ስነ ልቡናዊ ተፅእኖ ስጋት ቢፈጥርም “ፕሮፌሰሩ” ቬንገር ስምንት ጊዜ ብቻ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ወደተሰለፈው ሳሚር ናስሪ ፊታቸውን ለማዞር ጊዜ አልወሰደባቸውም::ሶስት ዓመት ወደፊት ስንመጣ ታሪክ

ራሱን ሊደግም ተቃርቧል:: በራሪው ሴስክ ፋብሪጋስ ወደ እናት ክለቡ ባርሴሎና፣ ናስሪ ሊቀራመቱት ካሰፈሰፉት የተ

“አርሰናል ኮከቦችን አይስብም”መቸውን ለመምረጥ ሲዘጋጅ፣ ጋኤል ክሊሺ ገንዘብ “ለሚበትነው” ማን ሲቲ ፊርማውን አኑሯል:: ናስሪ የኤምሬትስ የደሞዝ ጫፍ የሆነው 90 ሺህ ፓውንድ ቀረቦለት አሻፈረኝ ማለት ግርምትን ፈጥሯል:: እምቢታው ፈላጊ ክለቦቹ ምንያህል የላቀ ክፍያ እንዳላቸው ያሳያል:: እናም የአርሰናል የደመወዝ እርከን ባጣ ቆየኝ አድርጎ እየጠለፈው ነው::የአዲሱ ውድድር ዓመት ዝግጅት በተ

ጀመረበት በዚህ ሳምንት የቬንገር ቡድን መረጋጋት ውስጥ አይደለም:: ሰውዬው የቡድናችውን አምበል ፋብሪጋስን እና ናስሪን ለማሳመን ፈታኝ ድርድር ሲጠብቃቸው ብቁ ማጠናከርያ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ጊዜአቸውን በአግባቡ መጠቀም አለባቸው:: በሁለቱም ሩጫዎች ለአሰልጣኙ ወሳኝ ሚና የሚጫወተው ፓውንድ ነው:: ከለንደኑ ክለብ ልውጣ ለሚሉት በቂ ክፍያ ከማቅረበ ባሻገር እነርሱን ሐሳብ ለማስለወጥ ምርጥ ተጨዋቾችን መግዛት እንዲሁም አሳማኝ ፕሮጀክት መንደፍ ይጠበቅባቸዋል:: ኮከቦችን ለማስፈረም ደግሞ የክለቡን ካዝና መነቅነቅ ግድ ይላል::በእርግጥ ቬንገር የበቁ ኢኮኖሚስት ና

ቸው:: የአርሴናል “ራስን በአስተማማኝ ሁኔታ የመቻል ሞዴል” ጥሩ ፍሬ አሳይቷል:: በዋናው የክለቡ ባለቤት ስታን ክሮኤንክ የተወደደውም ይኸው አሰራር ነው :: ከደመወዝ ወጪ 50 በመቶ አትራፊ ሆነዋል :: ይሁን እንጂ አካሄዱ እያደር ከተፎካካሪነት ሐዲድ ውጪ እያደረጋቸው ነው:: እ.ኤ.አ በ2008 ማንችስተር ሲቲ የገንዘብ ጡንቻው እንደዛሬው አልፈረጠመም:: ቶተንሐሞችም ቢሆን የላይኛውን የደረጃ ሰንጠረዥ አያውቁትም ነበር:: ልብ የሚያሸፍት የደመወዝ ክፍያ ከሚከፍሉ ክለቦች አንፃር ሲታይ አርሰናል አምስተኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ ለ

እነዚህ መጤ ባላንጣዎች ክፍተት እየሰጣችው ነው::አዲስ ተጨዋቾችን ለመመልመል ቬን

ገር ገንዘብ አላጡም:: ከአምና ብቻ ያልተጠቀሙበት 30 ሚልዮን ፓውንድ አላቸው። ከክሊሺ ሽያጭ የተገኘው ሰባት ሚሊዮን ፓውንድ እና ከፋብሪጋስ እና ከቤንድትነር ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ጋራ ሲደማመር የደጋፊውን አንገት ቀና የሚያስደርግ ተጨዋች ማምጣት ይቻላል::

ምናልባት አሰልጣኙ ለሁዋን ማታ ዝውውር 20ሚሊዮን ፓውንድ ቫሌንሲያ ጠረጴዛ ላይ ሊያስቀምጡ ይችላሉ:: ነገር ግን ለተጨዋቹ አሳማኝ ሳምንታዊ ክፍያ ለመክፈል የመድፈራቸው ሁኔታ አጠያያቂ ነው:: ናስሪን ሊገዙ ያሰቡት ማን ዩናይትድ እ

ና ቸልሲ በሳምንት 150 ሺህ ፓውንድ ሊከፍሉት ፈቃደኛ ናቸው:: ተጨዋቾች ደግሞ በሞያቸው ላይ የሚቆዩት እስከ

30ዎቹ አጋማሽ እድሜ ስለሆነ የገንዝብ ፍቅር ሰለባ መሆናቸው አይቀሬ ነው:: የአርሰናል የደመወዝ እርከን አቋም በአሁኑ የእግር ኳስ ገበያ የማያዛልቅ ነው:: ናስሪን ለማቆየት 120ሺህ ፓውንድ ቢቀርብ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሌሎች ቡድኖች የደመወዙን ሒሳብ ሰቅለውት ይመጣሉ:: ከዚህ የክፍያ ቀውስ በተጨማሪ የዋንጫ ድርቅ የተጨዋቹን ፍልሰት አፍጥኖታል:: ናስሪም ምክንያቱ የዋንጫ

ጥማት እንደሆነ በግልፅ ተናግሯል:: “ጡረታ ስትወጣ ምን አገኘሁ ብለህ ትጠይቃለህ” ይላል። ቫን ፐርሲ እና ዋልኮትም የቀራቸው

የሁለት ዓመት ኮንትራት ጊዜ ነው:: ታዳጊው ጃክ ዊልሸር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተሰላፊ መሆኑ እና ፋብሪጋስ ከለቀቀ እርሱ የቡድኑ ዋልታ ስለሚሆን

“ቡና ገበያ አደገኛ!”ማንችስተር ዩናይትዶች የፕሪምየር ሊ

ግ ንግስናቸውን ካረጋገጡ በኋላ በፌሽታ ሻምፓኝ ከመክፈት ይልቅ የጭፈራ ስነስርዓታቸውን ለድርብ ድል ፈንጠዚያ ከሻምፕዮንስ ሊግ ፍፃሜ መልስ እንዲሆን ቀጠሮ አስይዘዋል:: በሁለትዮሽ ድል የሚገኝን ደስታ ለማጣጣም በደንብ የሚያውቁትን ባርሳ በሀገራቸው ዌምብሌይ ሜዳ ለመደምሰስ ዝግጅታቸውን አጡፈዋል:: የዋንጫን መንገድ መቀየስ የሚያውቁበት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን “ሜሲን ለማቆም ልጆቼ ስራቸውን አጠናቀዋል ”ሲሉ፣ ልበ ሙሉው ሪዮ ፈርዲናንድ “በ2008 ሮም ላይ የሰራነውን ስኅተት አንደግምም” በማለት ፎከረ:: ሩኒም በጨዋታው ላይ ሊገኝ እንደሚችል የእንግሊዝ ብዙሃን መገናኛዎች ተነበዩ::ከሜይ 28ቱ የፍፃሜ ጨዋታ 90 ደቂ

ቃ በኋላ ፊሽካ ሲሰማ ሜሲንም፣ ባርሳንም የሚያቆም አንዳች ልዩ ኃይል አልተገኘም:: ከዩናይትድ ካምፕ የሚወጡ አስተያየቶች “እጅ ሰጥተናል” የሚሉ ሆኑ:: አዎ! ባርሳን ለመቋቋም የታክቲክ ጋጋታ እና ኳስ የሚያጨናግፉ ተጨዋቾችን መደርደር ብቻ ሳይሆን ያለእንከን ጨዋታን መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ ለፈርጊ ነጋሪ አላሻቸውም:: “በአሰልጣኝነት ዘመኔ እንደዚህ ያለ ብልጫ ያሳየብኝ እና ኳስ የደበቀብን ቡድን አላየሁም” ሲሉ የጨዋ ምስክርነት ሰጥተዋል::

ማንዩናይትድን ከባርሳ በላይ

ከጎምዛዛው ሽንፈት በኋላ የታሰበው የጥንድ ዋንጫ ሕልም ባይሳካም የፕሪምየር ሊጉን ጣፋጭ ድል በበረዷማ ዝናብ ታጅበው አጣጥመዋል:: በሆታው መካከል አሰልጣኙ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ ጆሮ የሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል:: “መላው የብሪታንያ ቡድኖች የባርሳን የአሰለጣጠን እና የአጨዋወት ዘይቤ መከትል አለብን” ሲሉ ቀጣይ እቅዳቸውን በግልፅ አስቀምጠዋል:: “እንደ ባርሳ አሳማኝ እግር ኳስን ማሳየት::”እቅዳቸውን ለማሳካት እና ቃላቸውን

ለማክበር የእረፍቱ ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመዋል:: በዌምብሌይ እጃቸው በንዴት ሲንቀጠቀጥ በገሃድ የታዩት ስኮትላንዳዊ የሐሳባቸውን የሚያደርሱላቸው ተጨዋቾች ፍለጋ የጀመሩት በጊዜ ነበር:: አሽሊ ያንግን ከአስቶንቪላ፣ አስተማማኝ እና ለረዥም ጊዜ የጎል በሮችን የሚጠብቅ ወጣት በረኛ ፍለጋ ደግሞ ወደ

ስፔን ተጉዘው ደሄያን ገዝተዋል:: የ19 ዓመቱን የብላክበርን ተከላካይ ፊል ጆንስን በ16.5 ሚልዮን ፓውንድ አስፈርመዋል:: ፈርጊ ፈጣሪ ተጨዋች ለማግኘት ሲሉ የጠላታቸውን አርሰናልን በር ለማንኳኳትም ፈራ ተባ አላሉም:: ልቡ የሸፈተውን ናስሪን ጠይቀዋል:: ቬንገር “በፍፁም የማይታስብ” ቢሉ

ም የተጨዋቹ ኮንትራት ተጠናቆ በነፃ እንዳይሄድ በማሰብ ጥሩ ዋጋ ከቀረበላቸው ሳይዋጥላቸውም ቢሆን መስማማታቸው አይቀርም:: ሌላው የቀያይ ሰይጣኖቹ እቅድ የኢንተሩ ሽናይደር ነው:: ሆላንዳዊው በኔራዙሪ ደስተኛ እንደሆነ መናገሩ እና የሞራቲ የማይነካ ልጅ ቢመስልም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጫወት ናፍቆቱ እንደሆነ መግለፁ ዩናይትዶች የግሌዘርን ገንዘብ ተሸክመው ወደሚ

በካሳሁን ይልማ

በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

በካሳሁን ይልማ

በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

የ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የኢትዮጵያ ቡና ክለብ

ቀኑ ሰኔ 20 ቀን 2003 ዓ.ም ነው። ሙገር እና ቡና የፕሪሚየር ሊጉን የመዝጊያ ጨዋታ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን ይህን ጨዋታ ካሸነፈ ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያነሳ በመሆኑ ይህንን ታሪክ ለመመልከት በርካታ ተመልካች ለገሀር የሚገኘውን የአዲስ አበባ ስታዲየም አጨናንቆታል፡፡ ወደ ስታዲየም ለመግባት የነበረው ግፊያ የተነሳ የአንድ ሰው ህይወት ያሳጣ ነበር።

እንዲህ ለገሃር ከሚገኘው የአዲስ አበባ ስታዲያም አንስቶ እስከ ዋሸንግተን ዲሲ ባሉ የቡና ደጋፊና የቀድሞ ተጨዋቾች በጉጉት የተጠበቀው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል። ጨዋታውን የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በሳተላይት አማካኝንት በቀጥታ በማስተላለፉ በየሀገራቱ ያሉ ደጋፊዎች ድሉን አጣጥመውታል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ 13 ዓ

መት ሲጀመር ከመሰረቱት ከለቦች አን

ዱ የሆነው ቡና የሊጉን ዋንጫ አግኝቶ አያውቅም። ከፕሪሚየር ሊግ መስራቾች ዘንድሮ ያሉት ሶስት ሲሆኑ ሁለቱ ከዚህ ቀደም ዋንጫውን ወስደዋል፡፡ ቡና ነበር የቀረው፡፡ ቡናም ቢሆን በ1990ና 1996 ሁለት ጊዜ ዋንጫው ጋር ደርሶ በመጨረሻው ሰዓት ነው ያጣው፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ የ13 ዓመት ታሪክ ሶስት ቡድኖች ብቻ ነበሩ ዋንጫ ያገኙት፡፡ ጊዮርጊ

(ከላይ በስተግራ) ፋብሪጋስን እና ናስሪ

በኤምሬትስ የመውጫ በር ላይ ናቸው (ከላይ መሃል)

አይቮሪኮስታዊው አጥቂ ጀርቪንሆ

(ከላይ በስተቀኝ) አርጀንቲናዊው ሪኪ

አልቫሬዝ የመሐል ሜዳ አቀናባሪነት ሚናን

ከፋብሪጋስ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል

ጋኤል ክሊሺ ገንዘብ “ለሚበትነው” ማን ማንችስተር ሲቲ ፊርማውን አኑሯልየሳውዝሃምፕተኑ የ17 ዓመት የመስመር ተሰላፊ አሌክስ ቻምበርሊን የዋልኮትን ፈለግ

ተከትሎ ወደ ኤምሬትስ ይመጣል ተብሎ ተገምቷል

የአስቶንቪላው አሽሊ ያንግ