Top Banner
CBE CBE Informer ቅፅ 5 ቁጥር 4 ሐምሌ 2007 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ
20

CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Feb 10, 2020

Download

Documents

dariahiddleston
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

CBEኢ ን ፎ ር መ ር

CBE Informer ቅፅ 5 ቁጥር 4 ሐምሌ 2007

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ

Page 2: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክራዕይ

� በ2025 (እ.ኤ.አ) ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባንክ መሆን፡፡

ተልዕኮ � ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ ሙያዊ ብቃትና ጥሩ ሥነምግባር ያላቸውን ሠራተኞችንና ዘመናዊ

የባንክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት፤ እንዲሁም ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ብሔራዊ የልማት ሥራዎች በመደገፍ የባለድርሻ አካላትን ፍላጐቶች ለማርካት በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡ የሕብረተሰቡን ያልተገደበ አመኔታ ማትረፍ ለስኬታማነታችን መሠረት መሆኑን በጽኑ እናምናለን፡፡

እሴቶች1. ተቋማዊ ኃላፊነት

� በብሔራዊ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የምንጫወተውን ሚና ከፍተኛ ዋጋ የምንሰጠው በመሆኑ ልናሳድገው እንጥራለን፡፡

� የኢትዮጵያንና ሌሎች የቢዝነስ ግንኙነት የመሠረትንባቸውን ሀገሮች ህጐች እናከብራን፡፡ � ለሕብረተሰቡና ለአካባቢ ደህንነት እንሠራለን፡፡

2. የደንበኞች እርካታ � በአገልግሎታችን ልቀን በመገኘት ደንበኞቻችንን ለማርካት እንጥራለን፡፡

3. የአገልግሎት ጥራት � ጥራት ያለው አገልግሎት ለደንበኞቻችን ለመስጠት በቁርጠኝነት የተነሳን ሲሆን፣

መለያችን ጥራት እንዲሆን በትጋት እንሠራለን፡፡

4. ፈጠራ � የደንበኞቻችንን ፍላጐት የሚያረኩና የባንካችንን እንቅስቃሴ የሚያጐለብቱ አዳዲስ

ሃሣቦችን እናበረታታለን፡፡

5. የቡድን ሥራ � የቡድን ሥራ ለስኬታማነታችን ያለውን ጠቀሜታ እንገነዘባለን፡፡ � የአመለካከቶች ብዝሃነት እናከብራለን፡፡

6. መልካም ስብዕና � ለላቁቱ የአክብሮትና የመልካም ስብዕና መርሆዎች ለመተግበር በፅናት ጥረት እናደርጋለን፡፡

7. ሠራተኞች � ሠራተኞቻችን ወደር የሌላቸው የድርጅቱ ትልቅ ሃብት መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡

8. የህዝብ አመኔታ � የሥራችን ቀጣይነት በሕብረተሰቡ አመኔታ የሚወሰን በመሆኑ ይህንን መጠበቅና

ማጠናከር እንዳለብን እንገነዘባለን፡፡

Page 3: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 1

ማውጫርዕስ

አጫጭር ዜናዎች......................

ልዩ ዘገባ...................................

ቅምሻ.......................................

አዲስ የተከፈቱ ቅርንጫፎች ዝርዝር.......................................

ገፅ

2

11

13

15

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ኮሙዩኒኬሽንስ ንዑስ

የሥራ ሂደት በየሁለት ወሩ

የሚዘጋጅ

CBEኢ ን ፎ ር መ ር

CBE Informer ቅፅ 5 ቁጥር 4 ሐምሌ 2007

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ

አድራሻ :-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክኮሙዩኒኬሽንስ ንዑስ የሥራ ሂደትስልክ ቁጥር - 011 122 8755ፋክስ ቁጥር - 011 123 7958ኢሜል- [email protected]

Page 4: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia2

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ቅዳሜ ሀምሌ 18 ቀን 2007 ዓ.ም

በእንጦጦ ተራራ ላይ በሚገኘውና የኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ማህበር ባዘጋጀው ቦታ ላይ የዛፍ ችግኝ ተከላ

አከናወኑ፡፡ በችግኝ ተከላው ላይ ከባንኩ

ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ 150

ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

የሀገር በቀል ዛፍ ችግኞች ተከላ ላይ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ

አጫጭር ዜናዎች

Page 5: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 3

የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ፍቅሩ ደቅሲሳ የሀገራችን የደን ሽፋን እጅጉን እየተመናመነ በመምጣቱ ሀገራችን ለአየር ንብረት መዛባትና ተያያዥ ችግሮች መዳረጓን አስታውሰዋል፡፡ ይህን ሁኔታ ለመቀየር የድርሻውን ለመወጣት የኢትዮጵያ የቅርስ ባላደራ ማህበር በእንጦጦ ተራራ ላይ 1300 ሄክታር ቦታ ወስዶ ልዩ ልዩ የደን ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ የተቀደሰ አላማ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመሩ ተቋማት መካከል አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ አያይዘውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደአንጋፋ የባንክ አገልግሎት ሰጪነቱ የሚመጠን ምላሽ በመስጠቱ በማህበሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ይህንኑ ተግባር ለማበረታታትና እውቅና ለመስጠትም የባንኩን ሥም የያዘ ታፔላ በፓርኩ ውስጥ በቅርብ እንደሚተከል ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

በ ች ግ ኝ ተ ከ ላ ፕ ሮ ግ ራ ም ላ ይ ባንኩን በመወከል የተገኙት የባንኩ የኮሚዩኒኬሽንስ ንዑስ የሥራ ሂደት ሥራ - አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በበኩላቸው በዚህ ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ መርሃ ግብር ላይ ባንኩ በመሳተፉ ደስታ እንደሚሰማው ገልጸዋል፡፡ ዛፉቹ በሚገባ ጸድቀው የታለመላቸውን ዓላማ እንዲያሳኩ ችግኞቹን በዘላቂነት የመንከባከቡ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡

በዕለቱ የተለያየ ዝርያ ያላቸው በርካታ ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞች ተተክለዋል፡፡

Page 6: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia4

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ኢንባ) አዲስ ለሚያስገነባው ዋናው መስሪያ

ቤት ህንፃ ክቡር አቶ በረከት ስምኦን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ

አዲስ ለሚገነባው ዋና መስሪያ ቤት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ በተገኙበት ሰኔ 20፣ 2007 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ስነ

Page 7: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 5

ሥርዓቱ ላይ ክቡር አቶ በረከት ባደረጉት ንግግር አንጋፋው ባንክ ባለፉት አመታት ባደረገው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ገና ያልተነካ የፋይናንስ ገበያ ያላትና በመስኩ ሰፊ የማደግ እድል እየተፈጠረ መምጣቱን ገልፀው፤ ቀጣዩን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በአስተማማኝ ስኬት ተግባራዊ የማድረግ ጉዳይ ከሌሎች ስራዎች በተጨማሪ የፋይናንስ ተቋማት መጠነ ሰፊ ገንዘብ በቁጠባ መልክ አሰባስበው በሚሰጡት የብድር አገልግሎት እንደሚወሰን ገልፀዋል።

ኢንባ በ2025 ዓ.ም ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ አገልግሎት የመስጠት ብቃት ያለው ባንክ ለመሆን አልሞ የሚንቀሳቀስ የልማት ተቋም እንደመሆኑ ከአገራችን ፈጣን እድገት ጋር በሚጣጣም አኳኋን የተገነባ ዘመናዊ ህንጻ ባለቤት ለመሆን በወሰነው መሠረት የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት ህንፃ ባንኩን ለማጠናከር ከሚወሰዱት በርካታ እርምጃዎች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

በሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ባደረጉት ንግግር ባንኩ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተከትሎ የአምስት አመት ስትራቴጂ በመንደፍና ዝርዝር የአፈፃፀም እቅድ በማውጣት፣ እንዲሁም እቅድና ስትራቴጂውን በየጊዜው በመፈተሽና በመተግበር ባለፉት አምስት አመታት በባንኩ ታሪክ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል በማለት አብራርተዋል።

በተጨማሪም ባንኩ የዋና መሥሪያ

ቤት ህንፃ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው፣ ዓለም አቀፍ ባንኮች ያሏቸውን ህንፃዎችና ፋሲሊቲ መነሻ በማድረግ ደረጃውን የጠበቀ መመዘኛ ተዘጋጅቶ ወደ ዓለም አቀፍ ጨረታ የተገባ መሆኑን ገልፀዋል። በጨረታውም አምስት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መሳተፋቸውን አስታውሰዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ሚስተር ላ ዪፋን በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገሪቱ ካሉት ባንኮች ትልቁ ባንክ እንደመሆኑ የባንኩ አመራር ይህንን ትልቅ ህንፃ ለማሰራት መነሳሳቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። ህንፃውን የሚገነባው ቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ብቻ የአፍሪካ ኅብረት እና የመሳሰሉትን ህንፃዎች ሠርቶ ማስረከቡን አውስተው፤ ለዚህ ስኬት መብቃቱም የተገባ መሆኑን አብራርተዋል። በመሆኑም የኮንስትራክሽን ኩባንያው ለዚህ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ መገንባት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባው አሳስበዋል።

በሥነ ስርዓቱ ማጠቃለያ ለእንግዶች የምሳ ግብዣ የተደረገ ሲሆን፤ በስፍራውም ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ደንበኞች፣ ታዋቂ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Page 8: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia6

Page 9: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 7

በ መዲናችን መገናኛ አካባቢ የተገነባው ባለ አስራ ሰባት ደረጃ

የ”ልህቀት ማዕከል ህንፃ” ክቡር አቶ በረከት ስምኦን በሚኒስትር ማዕረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ በተገኙበት ሰኔ 13፣ 2007 ዓ.ም ተመርቋል።

በሥነ ስርዓቱ ላይ አቶ በቃሉ ዘለቀ ባደረጉት ንግግር ባንኩ አገራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ጎን ለጎን በ2025 ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ ባንክ ለመሆን የሚያስችል ራዕይ ሰንቆ

”የልህቀት ማዕከል“ ተመረቀበከፍተኛ ደረጃ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በሥራ ላይ በዋሉት የሀብት ማሰባሰብ ስትራቴጂ ፣የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትግበራ ስትራቴጂ እና የሰው ሃይል ልማት ስትራቴጂ አማካይነት ኢንባ በ2003 የነበረውን ብር 55 ቢሊዮን ተቀማጭ ገንዘብ በአሁኑ ወቅት ወደ ብር 240 ቢሊዮን ማሳደግ መቻሉን አስታውቀዋል።

የባንኩ ቅርንጫፎች ብዛት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 220 ወደ 956 ከፍ ያለ ሲሆን፣ የደንበኞች ቁጥርም ከአንድ ሚሊዮን ወደ 10.1 ሚሊዮን

Page 10: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia8

አድጓል። የኢንባ አገልግሎት ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂ የተደገፈ በመሆኑ በቅርንጫፎች በአማካይ በየቀኑ 700,000 የፋይናንስ ልውውጥ እየተካሄደና በካርድ፣ በሞባይል እና በኢንተርኔትም 80,000 ያህል የፋይናንስ ልውውጥ መፈፀም መቻሉን ገልፀዋል።

አቶ በቃሉ በንግግራቸው ማጠቃለያ ለተመረቀው ዘመናዊ ህንፃ ግንባታ በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ ላደረጉት፣ በተለይም ሕንፃውን በጥራትና በውበት ለሠራው ተክለብርሃን አምባዬ የህንፃ ተቋራጭ ድርጅትና ለአዲስ መብራቱ አማካሪ ድርጅት እንዲሁም በባንኩ በኩል የክትትልና የድጋፍ ተግባሩን ሲያከናውኑ ለነበሩት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተጨማሪም የባንኩን የሰው ኃብት ልማት ስትራቴጂ በመቀየስ ሂደት ከፍተኛ የማማከር አገልግሎት ለሰጠው የፍራንክፈርት ስኩል ኦፍ ፋይናንስ ተቋም ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ገልፀዋል።

በክብር እንግድነት የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ እንዲሁም የኢንባ የቦርድ ሰብሳቢ

ክቡር አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው፤ አገራችን በፈጣን የእድገት ለውጥ ውስጥ እንደምትገኝና ለውጡም መላው የአገራችን ህዝቦች ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውን እና ገንዘባቸውን በማረባረባቸው የተገኘ ለውጥ መሆኑን አስገንዝበዋል። መላው የአገራችን ህዝቦች በልማታዊ አቅጣጫ እየተመሩ የሚያደርጉትን ለውጥ ለመደገፍ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም አውስተዋል።

በተጨማሪም የልህቀት ማዕከሉ ተገንብቶ ለሥራ ዝግጁ መሆን ባንኩ ለሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዘመን ተልዕኮ ተፈላጊውን ብቃት ለመገንባት የሚያስችለው ወሳኝ መነሻ ይሆነዋል ተብሎ እንደሚታመን አስታውቀዋል።

የህዳሴ ህንፃ ተቋራጭ አቶ ተክለብርሃን አምባዬ በበኩላቸው ለህንፃው ተጀምሮ መጨረስ የባንኩ አስተዳደር የበኩሉን አ ስ ተ ዋ ፅ ኦ እ ን ዳ በ ረ ከ ተ ገ ል ፀ ው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም ለማዕከሉ ግንባታ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋሞች የቦርድ ሰብሳቢው ሽልማት አበርክተዋል።

Page 11: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 9

Page 12: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia10

ተተኪ አመራር ሠልጣኞች ተመረቁከባንኩ የተተኪ ቡድን (Succes-

sion team) የተመረጡ አንድ መቶ የደረጃ አንድ እና የደረጃ ሁለት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ለአንድ ወር የተሰጣቸውን ስልጠና አጠናቀው ግንቦት 28፣ 2007 ተመርቀዋል።

ለተመራቂዎቹ የተሠጣቸው የሥራ ላይ ሥልጠና የደንበኞች አገልግሎት እና ትራንዛክሽን፣ የህግ አገልግሎት ፣ የካሽ ማኔጅመንት እና የውስጥ ቁጥጥር እና ዶክመንት ቼኪንግን ያካተተ ነበር።

የሥልጠናው ዓላማ ተተኪዎችን

ለማብቃት ሲሆን፣ የደረጃ አንድና ሁለት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆቹ ከተተኪ ቡድኑ ተመርጠው ስልጠና እንደተሰጣቸውና ስልጠናው ወደፊትም የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል።

በግዮን ሆቴል በመገኘት ሠልጣኞቹን የመረቁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ባደረጉት ንግግር ባንኩ ተተኪዎችን ለማፍራት ፕሮግራም ቀርፆ በመንቀሳቀስ የሰው ሃይል ልማቱን እያጎለበተ መሆኑን ገልፀዋል።

Page 13: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 11

የህዳሴ ህንፃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የህንፃ ግንባታ ባህል ተከትሎ የተገነባ ሲሆን፣ በጠቅላላው 17 ወለሎች አሉት። ሁለቱ ወለሎች ለመኪና ማቆሚያ የሚያገለግሉ ናቸው። የህንፃው ምድር ቤት ለባንኩ ሠራተኞችና ባንኩን አገልግለው ጡረታ ለወጡ ሠራተኞች የጅምናዚየም አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

የህንፃው መዳረሻ የተቀላጠፈ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ ሲሆን የቅርንጫፉ መጠሪያም የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ እድገት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ በሚይዙትና የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ አስኪያጅ በነበሩት እና በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት በክቡር ዶ/ር ተፈራ ደግፌ ስም የተሰየመና አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ነው።

1ኛ ፎቅ ላይ ያለው ወለል ለሠራተኞች እና ለሰልጣኞች የተሟላ የሬስቶራንት

ልዩ ዘገባ

አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ሁለተኛው ፎቅ ደግሞ ለባንኩ ሠራተኞች የቤተ መፃህፍት አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

ከሦስተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ያሉት ወለሎች ደረጃቸውን በጠበቁ የመገልገያ መሣሪያዎች የተሟሉ አንድ ለሥልጠና አገልግሎት የሚውል የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ 18 “ሲንዲኬት” ክፍሎች እና 27 የሥልጠና ክፍሎች አሏቸው።

የህዳሴ ህንፃ በአብዛኛው ለሰው ኃይል ልማት ስትራቴጂ ዋነኛ አጋዥ በመሆን አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል። ህንፃው በምድር ቤት ከሚኖረው ቅርንጫፍ ባንክ በስተቀር ሙሉ በሙሉ ለስልጠናና ተያያዥ የአእምሮ ማበልፀጊያ ተግባራት እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።

በዚህ ህንፃ የሚታቀፈው የልህቀት ማዕከል የባንኩን የሰው ኃይል ብቃት ከማበልፀግ በዘለለ በአገራችን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ው ስ ጥ በ ሞ ዴ ል ነ ት የ ሚ ያ ገ ለ ግ ል እንዲሁም አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰኔ 13፣ 2007 በደማቅ ሥነ ስርዓት የልህቀት ማዕከልን ያስመረቀ ሲሆን፤ በሳምንቱ ደግሞ ለዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።በዚህ ዕትም የሁለቱን ህንፃዎች ዲዛይን አጠቃላይ ገለፃ የሚመለከት አጭር ዘገባ እናቀርባለን።

የህዳሴ ህንጻ

Page 14: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia12

የዋናው መስሪያ ቤት ህንፃሰኔ 20፣ 2007 የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት የዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ በአራት አመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ አለም ዓቀፍ ባንኮች የሚከተሉትን ዲዛይን መነሻ በማድረግ ደረጃውን ጠብቆ የሚገነባ ነው።

የዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ የአፍሪካ መለያ የሆነው የአልማዝ ቅርጽ ያለው ሲሆን ፤ ዲዛይኑም አራት መሠረታዊ ሐሳቦችን ማለትም፤

� የቦታ አጠቃቀምን ያገናዘበ እና ተጠቃሚዎችን ያማከለ (People oriented and high efficient office space)

� ከፍተኛ ቴክኖሎጂ እና እውቀት የተካተተበት (High tech intelligent digital technology)

� ዘለቄታዊ የአረንጓዴ ህንፃ ዲዛይን መርሆችን የተከተለ (Sustainablity green architectural design)

� ባህላዊ ገፅታዎችን (Iconic cultural features ) አካቶ የተዘጋጀ ነው።

ዋናው መሥሪያ ቤት አንድ ትልቅ ህንፃ እና በግራና በቀኝ ሁለት አጠር ያሉ ህንፃዎች ያሉት ነው። ትልቁ ማማ መሰል ህንፃ ወደ መሬት 20 ሜትር ጠልቆ የሚገባ ሲሆን አራት የምድር ቤቶች አሉት። ቁመቱም ከመሬት በላይ 198 ሜትር ይሆናል።

ከመሬት በታች ያሉት አራት ምድር ቤቶች ሜካኒካል ኢኩፕመንት፣ የዳታ ማዕከል እና ካሽ ቮልት ማስቀመጫ የሚኖሩትና 1,500 መኪኖች ማስቆም እንዲችል ተደርጎ የሚታነፅ ነው።

ይህ ሕንፃ 46 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፣ መጨረሻ ላይ ከሚገኙት ሁለት ወለሎች ውጭ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ነው። ከሁለቱ የመጨረሻ ወለሎች አንዱ ሬስቶራንት (SKY Restaurant) ይሆናል። የፎቁ የመጨረሻ ወለል ከ198 ሜትር ከፍታ ላይ ከተማችንን ለማየት የሚያስችልና ለሕዝብ ክፍት የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

ከመሬት በላይ አምስት ወለሎች ያሉት አንደኛው ትንሽ ህንፃ ሙሉ በሙሉ ለገበያ ማዕከልነት አገልግሎት የሚውል ይሆናል። ሁለተኛው ተመሳሳይ ባለ አምስት ወለሎች ህንፃ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የስብሰባ ማዕከል ሲሆን አንድ 2,000 ሰው የመያዝ አቅም ያለው ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ፣ሁለት 300 ተሰብሳቢ ማስተናገድ የሚችሉ አዳራሾች፣ እንዲሁም አምስት 200 ተሳታፊዎች የሚይዙ አዳራሾች ይኖሩታል። በተጨማሪም ቤተ መፃሕፍት፣ የመረጃ ማዕከል፣ የመወያያ ክፍሎች እና ለባንኩ ሠራተኞች ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጡ ተጨማሪ ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን፣ ለአገራችን ኮንፍረንስ ቱሪዝም ጉልህ ድርሻ የሚያበረክት ይሆናል።

Page 15: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 13

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በድህነት እና በጦርነት ስትጠራ የቆየች

ብትሆንም በአሁኑ ወቅት ኢኮኖሚዋ እያደገና ወዳገሪቱ የሚገቡት የቱሪስቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በቱሪዝም ረገድ ከሌሎች በቱሪዝም ካደጉ የአፍሪካ አገሮች አልፎም ከነደቡብ ኮሪያ ጋር እየተነፃፀረች እንደምትገኝ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ነገር ግን ንፅፅሩ በታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሮአዊ ሀብት የተወሰነ አይደለም፡፡ ምናልባትም አገራችን ካላት የቱሪዝም ሀብት አንፃር ሲታይ አሉ ከሚባሉት የዓለም አገሮች ጋርም ተወዳዳሪ መሆን የምትችል ነች፡፡ ነገር ግን ሩቅ ሳንሄድ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ አሁን የኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ከሚባሉት የአፍሪካ አገሮች ምናልባትም ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ወዘተ ጋር ሲተያይ በመካከላችን ብዙ

ቅምሻ

የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ልዩነት እንዳለ ግምት ውስጥ ማስገባት እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ እነዚህ አገሮች የብዙ ተከታታይ ዓመት ያልተቆራረጠ የቱሪዝም ልምድና ዕውቀት ያላቸውና በየጊዜው የየቱሪስት ዓይነቶችን ፍላጎት መሠረት አድርገው ኢንዱስትሪውን ያሳደጉ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በአሁኑ ወቅት እነዚህ አገሮች ያሉዋቸውን የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ ማለትም የለሙና ዓይነተ ብዙ የቱሪዝም መስህቦች፣ የተለያዩ ቱሪስቶችን ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ ሰፊና ስታንዳርድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (አስጎብኚ ድርጅቶች፣ ሆቴል፣ ሪዞርት፣ ሬስቶራንት፣ ሎጅ፣ የኮንፈረንስ ማዕከላት፣ ወዘተ) በመስኩ የተሰማራው የሰው ኃይልና አጠቃላይ ሕ ዝ ቡ ስ ለ ቱ ሪ ዝ ም ፣ ስ ለ ቱ ሪ ስ ት አገልግሎት አሰጣጥና መስተንግዶ ያላቸው ዕውቀትና ግንዛቤ ቀደም ሲል ከነበራቸው መልካም አጋጣሚዎች አንፃር በጊዜ ሒደት ያደገ ነው፡፡ በእነዚህ አገሮች

Page 16: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia14

በኢንዱስትሪው ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ የሆነው የግሉ ዘርፍ ከፍተኛ አቅምን ፈጥሯል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአብዛኞቹ አገሮች ለምሳሌ ኬንያ፣ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካና ጋና የማርኬቲንግና የፕሮሞሽን ሥራዎች የሚከወኑት በቱሪዝም ቦርዱ ሲሆን፣ አብዛኛው ወጪ የሚሸፈነው ከግሉ ዘርፍ በተለያየ መልኩ ከሚሰበሰብ ገቢ ነው፡፡ በእነዚህ አገሮች የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ውስጥ የሚገኙ መስህቦች የለሙና የቱሪስቶችን ፍላጎት የሚያሟሉና የ ሚ ያ ረ ኩ በ መ ሆ ና ቸ ው ፣ በ መ ስ ኩ የተሰማሩ ባለሙያዎችም የቱሪዝም ዕውቀታቸው ያደገ በመሆኑ በቱሪስቶችና በቱሪስት ላኪ ድርጅቶች ተመራጭ አድርጓቸዋል፡፡ እነዚህ አገሮች ይህንን ሁሉ ስኬት ያስመዘገቡት ማለትም መስህቦችን በቱሪስት ስታንዳርድ ማልማት፣ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማስፋፋትና ማሳደግ፣ የሰው ኃይል ልማት ወዘተ በአንድ ጀምበር ወይም በጥቂት ዓመታት የለወጡት አይደለም፡፡ ምናልባትም የ60 ዓመት ተከታታይና ያልተቆራረጠ ለውጥ ዕድገት ውጤት ወይም ከቅኝ ግዛት ጊዜ ጀምሮ የተፈጠረ እንጂ፡፡ የእነዚህን አገሮች የግል ዘርፍ ብንመለከት በባለቤትነትና በሠራተኝነት እየተመራ ወይም የተያዘው በአብዛኛው በአውሮፓውያን የቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው በመጡ ዜጎች ነው፡፡ ይህ የራሱ በጎ የሆነና ያልሆነ ገጽታ ያለው ነው፡፡

ቀደም ሲል እንደተወሳው አገራችን ሰፊ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ተፈጥሮአዊ

የቱሪዝም ሀብቶች ባለቤት ከመሆኗ አንፃር ከማንኛውም የዓለማችን አገሮች ተወዳዳሪ የምትሆን ናት፡፡ እስካሁን ድረስ በአገራችን 22 ዓለም አቀፍ ቅርሶችን በ ተ ባ በ ሩ ት መ ን ግ ሥ ታ ት ድ ር ጅ ት የሳይንስ፣ ባህልና ትምህርት ድርጅት አስመዝግባለች፡፡ የ24 ብሔራዊ ፓርኮች፣ የአራት የዱር እንስሳት መጠለያዎች ፣ የ18 የዱር እንስሳት ቁጥጥር አደን ቀበሌዎች፣ የሰባት የዱር እንስሳት መኖሪያ ቀጠናዎች (Wildlife Reserve)፣ እንዲሁም ብዛት ያላቸው የማኅበረሰብ ተኮር ተፈጥሮአዊ አካባቢዎች (Community Based Conservation Areas) ባለቤት ናት፡፡ እንዲሁም የብዙ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መኖሪያ እንደመሆኗ የዓይነተ ብዙ የባህል እሴቶች ባለቤት በመሆኗ ለ ቀ ጣ ዩ የ ቱ ሪ ዝ ም ኢ ን ዱ ስ ት ሪ ው ዕድገት ተስፋ ናቸው፡፡ በተለይም አሁን መንግሥት ለዘርፉ ከሰጠው የትኩረት አቅጣጫ አንፃር የቱሪዝም መዳረሻዎችን ( መ ስ ህ ቦ ች ን ና አ ገ ል ግ ሎ ት ሰ ጪ ተቋማትን) ማልማትና ዘርፉን በሠለጠነ የሰው ኃይል ማጠናከር ዋነኛው ተግባሩ ሲሆን፣ በቀጣይም ውጤታማ የቱሪዝም ማስተዋወቅ ሥራዎችን በመሥራት ወደ አገራችን ብዙ ቱሪስቶች እንዲመጡ በማድረግ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ለአገሪቱ ኢኮኖሚና ለማኅበረሰቡ ዕድገት ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ ይችላል፡፡

: www.world-guides.com/Africa/east-africa/Ethiopia/

:የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገትና ተስፋ

ምንጮች

Page 17: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia 15

ቁጥር የዲስትሪክት ሥም የቅርንጫፍ ሥም የተከፈተበት ቀን (እ.ኤ.አ)

1 ምዕራብ አ.አ ጎማ ተራ ጃንዋሪ 23 ቀን 2015

2 ምዕራብ አ.አ ቡሳ አፕሪል 14 ቀን 2015

3 ምዕራብ አ.አ ሰፈረ እዮር አፕሪል 17 ቀን 2015

4 ምዕራብ አ.አ ጠሮ ትራፊክ አፕሪል 20 ቀን 2015

5 ምዕራብ አ.አ መሀል አምባ ሜይ 14 ቀን 2015

6 ምዕራብ አ.አ አገና ጁላይ 06 ቀን 2015

7 ምዕራብ አ.አ አራት መንታ ጁላይ 23 ቀን 2015

8 ሰሜን አ.አ ሰሜን ገበያ ሜይ 13 ቀን 2015

9 ምስራቅ አ.አ ሲኤምሲ ሚካኤል ሜይ 11 ቀን 2015

10 ምስራቅ አ.አ ተርሚናል ጁን 10 ቀን 2015

11 ምስራቅ አ.አ ተፈራ ደግፌ ጁን 12 ቀን 2015

12 ደቡብ አዲስ ጎተራ ኮንዶሚኒየም ሜይ 16 ቀን 2015

13 ነቀምቴ አገምሳ አፕሪል 08 ቀን 2015

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 31 ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ከፈተ ባንኩ ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት አገልግሎት ባልደረሰባቸው ከተሞችና አካባቢዎች ቅርንጫፎችን የመክፈት ጥረቱን

አዲስ የተከፈቱ ቅርንጫፎች ዝርዝርአጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም መሠረት ባለፈው እትም ከተዘረዘሩት ቅርንጫፎች በተጨማሪ የሚከተሉትን 31 ቅርንጫፎች በመክፈት የባንኩን የቅርጫፍ ቁጥር 968 አድርሷል፡፡

Page 18: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of Ethiopia16

14 ነቀምቴ ሶግ አፕሪል 14 ቀን 2015

15 ነቀምቴ ዋማ ጁን 12 ቀን 2015

16 ሐዋሳ ጋንቦ በር አፕሪል 07 ቀን 2015

17 መቀሌ ኩነቫ አፕሪል 09 ቀን 2015

18 መቀሌ ባዕኸር ጁን 13 ቀን 2015

19 መቀሌ አዳባይ ጁን 12 ቀን 2015

20 መቀሌ ወልዋሎ ጁን 15 ቀን 2015

21 መቀሌ ዛና ጁን 15 ቀን 2015

22 ደሴ ከለዋን አፕሪል 24 ቀን 2015

23 ደሴ ኩርባ ሜይ 10 ቀን 2015

24 ደሴ ጨፋ ሮቢት ጁን 29 ቀን 2015

25 ደሴ ሳልመኔ ጁን 29 ቀን 2015

26 ጐንደር ኮኪት ጁን 03 ቀን 2015

27 ድሬደዋ ገንደቆሬ አፕሪል 24 ቀን 2015

28 ድሬደዋ ኩርፋጨሌ ጁን 16 ቀን 2015

29 ሻሸመኔ ሐረሮ ጁላይ 03 ቀን 2015

30 ጅማ አምቡዬ ጁን 12 ቀን 2015

31 ወላይታ ሶዶ ዳሞት ወይዴ ጁን 28 ቀን 2015

ቁጥር የዲስትሪክት ሥም የቅርንጫፍ ሥም የተከፈተበት ቀን (እ.ኤ.አ)

Page 19: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

ውድ አንባብያን!የዜና መጽሄታችን /CBE-Informer/ በባንካችን ውስጥ የመረጃ ልውውጥን የተሳለጠ ለማድረግ ተግባር ላይ ከዋሉት መሳሪያዎች አንዷ ናት፡፡

ስለሆነም

በተለያዩ የባንኩ የስራ ክፍሎች የተከናወኑ አስተማሪና አርአያነት ያላቸው ጉዳዮች፣

በባንኩ የ70 አመት ታሪክ ውስጥ ሊታወሱ የሚገባቸው አበይት ቁምነገሮች፣

ከባንክ ጋር በተያያዘ ከንባብ የተገኙ ቁምነገሮችና ዕውቀቶች፣

ከሁለት ገጽ ያልበለጡ አዝናኝ ጽሁፎች (አጭር ልብ ወለድ፣ ግጥም፣ አስቂኝ ገጠመኞች)

ለዝግጅት ክፍሉ በመላክ የመጽሄታችንን ይዘት እናዳብር፣ ልምዳችንንም እናካፍል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፌስቡክ ገጻችን “ላይክ” በማድረግ፣ የቲውተር ገጻችንን በመጎብኘትና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የመረጃ ፍሰቱን ለማሳለጥ እንዲሁም የባንኩን አገልግሎት ለበርካቶች ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ያግዙ፡፡

የፌስ ቡክና የቲውተር ገጾቻችን አድራሻ የሚከተለው ነው፡፡

[email protected]@combanketh.com

Page 20: CBE - combanketh.et · የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ አድራሻ :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽንስ

Commercial Bank of EthiopiaThe bank you can always rely on