Top Banner
የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ FEDERAL DOCUMENTS AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY ዜና ሰነድ በውስጥ ገጾቻችን በፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ዋና መስሪያ ቤት የሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ተጨማሪ ሃላፊነት ተሰጠው ፡፡ . ጠቅላይ ሚኒስትር ሀ/ማርያም ደሳለኝ ለኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ፡፡ የኤጀንሲው ሰራተኞች ሁለተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ጉብኝት አደረጉ፡፡ • ወድቆ የተገኘ 80ሺህ ብር ለባለቤቱ ተሰጠ፡፡ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ልደታ በሚወስደው መንገድ ፊሊፕስ ህንጻ ፊት ለፊት ጨለለቅ አልሳም ታወር ስልክ ፡ 011-553 47 88 • ነጻ ስልክ መስመር 888/2 • ፋክስ ፡ 11-515 63 90/011–552 03 08 • E-mail : [email protected] • Website : www.dara.gov.et • www.facebook.com/Documents Authentication-Registration Agency ህዳር 2009 ዓ.ም
12

AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

Feb 19, 2020

Download

Documents

dariahiddleston
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ FEDERAL DOCUMENTS

AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY

ዜና ሰነድ

በውስጥ ገጾቻችን

በፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

ዋና መስሪያ ቤት

• የሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ተጨማሪ ሃላፊነት ተሰጠው ፡፡

. ጠቅላይ ሚኒስትር ሀ/ማርያም ደሳለኝ ለኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ፡፡

• የኤጀንሲው ሰራተኞች ሁለተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ጉብኝት አደረጉ፡፡

• ወድቆ የተገኘ 80ሺህ ብር ለባለቤቱ ተሰጠ፡፡

ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ልደታ በሚወስደው መንገድ

ፊሊፕስ ህንጻ ፊት ለፊት ጨለለቅ አልሳም ታወር

• ስልክ ፡ 011-553 47 88• ነጻ ስልክ መስመር 888/2• ፋክስ ፡ 11-515 63 90/011–552 03 08• E-mail : [email protected]• Website : www.dara.gov.et• www.facebook.com/Documents Authentication-Registration Agency

ህዳር 2009 ዓ.ም

Page 2: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

ተልዕኮ

ራዕይ

እሴቶች

Mission

Vision

Core Values

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ FEDERAL ATTORNY GENERAL FEDERALDOCUMENTS

AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY

የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ስራ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰዎችና በድርጅቶች የሚደረጉ የውልና ሌሎች ግንኙነቶችን የሚወስኑ ሰነዶች አግባብ ባላቸው ህጎች መሰረት በማጣራት ማረጋገጥና መመዝገብ ሲፈልጉ በቀላሉ ሊገኙ በሚችሉበት አስተማማኝ ሆኔታ በጥንቃቄና በዘመናዊ የመረጃ ስርዓት አደራጅቶ መያዝ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በሃገርና በአለም አቀፍ ደረጃ በግለሰቦችና በድርጅቶች መካከል የሚደረጉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ግንኙነቶችን ጤናማ በማድረግ ሂደት የፍትህ ስርአቱንና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለማገዝ የሚያስችል ግልጽ ተልእኮ በመያዝ ይህንኑ ተልእኮ ፣ ተደራሽ፣በቴክኖዎሎጂ የተደገፈ ግልጽነትና እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር በመዘርጋት የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ አገልግሎት አሰጣጡን ከዘመኑ የለውጥ እንቅስቃሴ እና ከተገልጋዩ ፍላጎት ጋር እንዲሄድ ለማስቻል የለዉጥ እንቅስቃሴውን በየጊዜው እያደሰ ለበለጠ ውጤታማነትና የደንበኞችን እርካታ ለማስገኘት ተግቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡በመሆኑም ኤጀንሲው ባለፉው በጀት ዓመት ባሉት 14 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በቀን በአማካኝ ከ4980 በላይ ተገልጋዮችን አስተናግዷል፡፡ይህም ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ አገልግሎቱን ያላገኙ እንዲሁም ጉዳያቸው በእንጥልጥል ላይ የሚገኙትን ተገልጋዮች ሳያካትት ነው፡፡ይህን አገልግሎት መስጠት የተቻለው ከጠቅላላው ሰራተኛ 67 ከመቶ በሆኑት የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ነው፡፡ በዝግጅት ክፍሉ መልእክት ይቺን ካልናችሁ ሌላውን ደግሞ ለንባብ አቅርበናል፡፡ ገንቢ አስተያየታችሁን ዋናው መ/ ቤት በሚገኝበት ሜክሲኮ በአካል በመምጣት ወይም በስልካችን 0115-58-73-77 ወይም በ888 ነጻ የስልክ መስመራችን በመደወል ወይም በፌስቡክ አድራሻችን ብታደርሱን ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡

መልካም ንባብ

የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ አገልግሎት በመስጠት በ2017 ዓ.ም ተገልጋዩን ያረካ ሞዴል ተቋም ሆኖ ማየት

ምንጊዜም ተገልጋዮቻችንን እናስቀድማለን!!

- ቅድሚያ ለተገልጋዮች- ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት- የህግ የበላይነት - የአገልግሎት ጥራት- ሚስጥር ጠባቂነት- በትብብር መስራት- ታማኝነት ፣ እና ግልፅነት- ቀጣይነት ያለው መሻሻል

The work of documents authentication and registration is to help contractual agreements and other relations between persons and organizations in both domestic and international level and it gives support to the justice system, thus, contemporary registered documents are placed in reliable, available and safe way.

To see the agency being a model institution by 2025 in satisfying customers through authenticated and registered documents service provision based on international standards.

- Customers focused- Quick and fair service- Rule of law- Quality service- Confidentiality- Team work- Integrity and transparency- Continuous Improvement

Whenever, we strive to satsify our custemers!!

የዝግጅት ክፍሉ መልእክት

Page 3: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

1

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ትጋት አገልግሎት በመስጠት በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ የልማት ተቋማት ዘንድ በርካታ ሽልማቶችንና የምስክር ወረቀቶችን ማግኘት ከመቻሉም በተጨማሪ በተገልጋዮችም ዘንድ ከበሬታንና ምስጋናን የተቸረ ሆኗል፡፡ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በሰዎች መካከል የሚደረጉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች መስተጋብሮችን በሚመለከት የሚፈፀሙ የውል እና ሌሎች ግንኙነቶችን በሕግ አግባብ በማረጋገጥ እምነት የሚጣልበት ሰነድ በማመንጨት እንዲሁም ሰነዶችን መዝግቦ በመያዝ በማናቸውም ጊዜ እንዲገኙ በማድረግ ለሕገ-መንግስታዊ መብቶች ዋስትና መስጠት በማስፈለጉ ፤ የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ተግባር በመላ አገሪቱ ወጥ የሆነ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ፣ አገር አቀፍና አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አሰራር እንዲኖረው የሚያስችል ሕግ በማስፈለጉ ፤ በሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ተቋማት መካከል ግልጽ ግንኙነት የሚፈጥር እና ያለአግባብ የሚረጋገጡ ሰነዶችን መቆጣጠር የሚያስችል የተሻሻለ ሥርዓት መኖሩ በሰዎች

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ተጨማሪ ሃላፊነት ተሰጠውመካከል የሚደረጉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶችን በማቀላጠፍ እንዲሁም አሰራሩን ተገማች በማድረግ በሀገሪቱ ውስጥ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር የበለጠ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ እና እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ በሥራ ላይ ያሉትን የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ ሕጎች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 922/2008 አውጥቶ ወደኤጀንሲነት እንዲሸጋገር በማድረግም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 379/2008 ተጨማሪ ሃላፊነቶችና ተግባራት ተሰጥተውታል፡፡

ኤጀንሲው በመንግስት የሚሾሙ አንድ ዋና ዳይሬክተርና ሁለት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና አስፈላጊው ሃላፊዎችና ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡ ስልጣንና ተግባራቱም በፊት ይሰጣቸው ከነበሩ አገልግሎቶችና ተግባራት በተጨማሪ ያላግባብ ተረጋግጠው የተመዘገቡ ሰነዶችን አግዶ የማቆየት ተግባር፣በክልሎች ለሚገኙ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ተቋማት የሙያ፣ የቴክኒክና ሌሎች መሰል ድጋፎች የመስጠት፣ አንዲሁም የምክር ፣ የልምድ ልውውጥ እና የስልጠና መድረኮችን የማዘጋጀት፣ በሀገሪቱ ተረጋግጠው የተመዘገቡ ሰነዶችን በአንድ የመረጃ ማዕከል የማደራጀት፣

ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመረጃ መረብ የማገናኘት፣በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ስርዓት እንዲኖር ያግዛሉ ተብለው በተመረጡ ጉዳዮች ላይ ሞዴል ሰነዶችንና ፎርማቶችን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው ሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ተቋማት የማሰራጨት፣ ዓላማውን ማሳካት የሚያስችሉ የፖሊሲ ሃሳቦችን በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል የማቅረብ ሲወሰንም በስራ ላይ የማዋል፣ እንዲሁም ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን የማከናወን የሚሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡

ኤጀንሲው አሰራሩን የበለጠ ዘመናዊ እና ተደራሽ በማድረግ ረገድም ጠንክሮ እየሰራ ነው፡፡የውክልና አገልግሎት በቀጥታ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን በተዘጋጀ ሞዴል ሰነዶች አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው፡፡

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመንም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹን ከሃያ(20) በላይ ለማድረስ ግብ ሰንቋል፡፡

Page 4: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

2

አቶ መረሳ ገ/ዮሃንስ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር

አቶ ሙሉቀን አማረ የኤጀንሲው የድጋፍ ስራዎች ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አቶ አሽማዊ ሰይፉ የኤጀንሲው የኦፕሬሽን ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በቁጥር መ60-3/830/3 24 በተጻፈ ደብዳቤ በፌደራል የሰነዶች

ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ የሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 379/2008 አንቀጽ 7(1) መሰረት

1) አቶ መረሳ ገ/ዮሃንስ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር

2 ) አቶ ሙሉቀን አማረ የኤጀንሲው የድጋፍ ስራዎች ምክትል ዋና ዳይሬክተር

3 )አቶ አሽማዊ ሰይፉ የኤጀንሲው የኦፕሬሽን ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር

በመሆን በኢ . ፌ. ዴ .ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከነሃሴ 24/2008 ዓ.ም ጀምሮ የተሾሙ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ፡፡

Page 5: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

3

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁን የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ አሁን ያለበትን የሥራ እንቅስቃሴ ግንቦት 20 ቀን 2008ዓ.ም ጉብኝት አደረጉ::ጉብኝቱንያደረጉት በመጀመሪያዉ ዙር ያልተካተቱት 85 የኤጀንሲዉ አመራሮችና ሠራተኞች ናቸዉ::

የዘንድሮዉን ጉብኝት ልዩ እና ታሪካዊ የሚያደረገዉ የግንቦት 20 የብር ኢዩበልዩ በአል በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ባለበት ጊዜ በዓሉን በዛው በግድቡ ስፍራ ማክበር መቻሉ ነዉ::›› ሲሉ በስፍራው የታደሙ የኤጀንሲው ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡

በእለቱም የግንቦት ሃያ ድል እንዲገኝ እና ለዚህ ግድብ ጉብኝት እንድንበቃ የህይወትና የአካል መስዋእትነት ለከፈሉ እንዲሁም በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት ለተለዩት የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ለአቶ አህመድ ናስር የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል:: የህዳሴዉ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘዉ በቀለ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ

የኤጀንሲው ሰራተኞች የታላቁን የህዳሴ ግድብ ለሁለተኛ ዙር ጉብኝት አደረጉኤጀንሲ በአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋና ዉጤታማ መሆኑን እንደሚያዉቁት ገልጸዉ ተቋሙ በሚሰጠዉ አገልግሎት ለፍትህ ስርአቱና ለኢንቨስትመንቱ መሳለጥ እንዲሁም ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሥራ በመስራት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ግድቡ የሀገሪቱን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦችን ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ኑሮን ያስተሳሰረ በመሆኑ ዋና አላማዉም የዜጎችን ህይወት ማሻሻል ነዉ ብለዋል::

እንደ ኢንጅነር ስመኘዉ ገለጻ ግድቡ ከሀይል ማመንጫነት ባሻገር ለሀገሪቱ የቱሪዝም ፍሰት፤ ለመዝናኛ እና ለዲፕሎማሲ ትስስር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለዉ አስረድተው ይህ የህዳሴ ግድብ ከአፍሪካ 1ኛ ከአለም ደግሞ 8ኛ ደረጃን የያዘ የኃይል ማመንጫ እንዳለዉ እና ዉኃዉም ወደ ላይ 246 ኪሎ ሜትር እርዝመት እና 1874 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለዉ ሰዉ ሰራሽ ኃይቅ እንደሚኖረዉ አብራርተዋል::

በገለጻዉ ስነስርአት ላይም ኤጀንሲዉን በመወከል የቅርንጫፍ ሰባትና ስምንት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ወ/ሮ ጌጤ ፈለቀ እና ወ/ሮ እርግአት

ገ/የሱስ የተዘጋጀዉን ስጦታ ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ አበርክተዋል:: ኢንጅነር ስመኘዉ በቀለም በመጀመሪያዉ ዙር ግንቦት ወር 2007 ዓ.ም የኤጀንሲዉ አመራሮችና ሠራተኞች ጉብኝት ማድረጋቸዉን በማስታወስ ከኤጀንሲዉ አመራሮችና ሠራተኞች መካከል አብዛኞቹ ሴቶች መሆናቸዉን በማዉሳት ይህም በተቋሙ አሰራር ሊበረታታ እንደሚገባም በአጽንኦት አስገንዝበዋል::

በማጠቃለያዉ የህዳሴዉ ግድብ አሁን ያለበትን ደረጃ በተለያየ አቅጣጫ በተጨባጭ በመዘዋወር ጉብኝት ተደርጓል::

የኤጀንሲው አመራሮችና ሰራተኞች በህዳሴ ግድብ

Page 6: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

4

በኤጀንሲው ቅርንጫፍ አስራ አንድ ጽ/ቤት ሰኔ 7/ ቀን 2008 ዓ.ም ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ባለ ጉዳይ የተሽከርካሪ ሽያጭን አስመልክቶ መረጃ ለመጠየቅ በመጡበት ወቅት በእጃቸው ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበረውን በውስጡ 80,000.00 /ሰማንያ ሺህ/ የኢትዮጵያ ብርና 300 /ሶስት መቶ የአሜሪካን ዶላር/ እና ሌሎች መረጃዎችን የያዘ ቦርሳ በስምሪት ዴስክ ላይ ረስተውት በመሄዳቸው የጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ካሳዬ ንብረቱን የያዘውን ቦርሳ አግኝተው ለባለቤቱ በጥንቃቄ አስረክበዋል፡፡ በወቅቱ ንብረቱ እንደጠፋባቸው ያስታወሱት ግለሰብ በስራ መውጫ ሰዓት ወደ ቢሮው በመመለስ ቦርሳ ረስተው መሄዳቸውን ስለገለጹ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ እና ባልደረቦቻቸው በቂ ማጣራት አድርገው ገንዘቡ ተመልሶላቸዋል ፡፡ ከዚህ ቀደም በዚሁ ቅርንጫፍ መጋቢት ወር ላይ በተመሳሳይ የተለያዩ ሰነዶችና ግምቱ ከ25ሺ ብር በላይ የሆነ ሞባይል ረስተው ለሄዱ አንድ ተገልጋይ ንብረታቸው እንዲመለስላቸው የተደረገ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ በተመሳሳይም ጳጉሜ ወር 2008 ዓም አየር ጤና በሚገኘው ቅንጫፍ ስድስት ጽ/ቤት ወድቆ የተገኘ 25 ሺህ ብር ለባለቤቱ በመመለስ ታማኝነትን መርህ ያደረገ ተቋምነቱን አስመስክሯል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊው ወድቆ ያገኙትን ከ80 ሺህ ብር በላይ ለባለቤቱ አስረከቡ

አቶ መለስ ካሴ የቅርንጫፍ አስራ አንድ ስራ አስኪያጅ ቅርንጫፍ ስድስት ወድቆ የተገኘው ብር ለባለቤቱ ሲመለስ

Page 7: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የመጀመሪያው አምስት አመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (ከ2003-2007) አፈፃፀም ማጠቃለያ

በጀት ዓመት

ጉዳይ ተገልጋይ ገቢ ፈሰስ

ዕቅድ ክንውን ዕቅድ ክንውን ዕቅድ ክንውን ዕቅድ ክንውን 2003 300,000 326,318 570,350 618,121 90,ሚሊየን 97,035,151.00 70ሚሊየን .00 78,397,880.00

2004 350,000 387,730 653,620 731,592 114ሚሊዮን 116,666,785.00 85,ሚሊየን 87,896,158.00

2005 403,480 427,181 744,500 891,879 136ሚሊዮን 147,962,898.00 108ሚሊየን 113,975,657.00

2006 505,000 526,633 1,005,200 1,099,039 160ሚሊዮን 171,947,652.00 117ሚሊየን100 ሺህ 133,798,801.00

2007 684,623 605,186 1,428,753 1,215,386 200ሚሊዮን 226,578,332.00 133 ሚሊየን 225ሺህ 710 162,560,000.00 ድምር 2,243,103 2,273,048 4,402,423 4,556,017 7መቶ ሚሊዮን 760,190,818.00 513ሺህ325,ሚሊዮን710.00 576,628,496.00

የሁለተኛው አምስት አመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (ከ2008-2012) የመጀመሪያው የ2008 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም

በጀት ዓመት

ጉዳይ ተገልጋይ ገቢ ፈሰስ

ዕቅድ ክንውን ዕቅድ ክንውን ዕቅድ ክንውን ዕቅድ ክንውን 2008 679,872 638,714 1,369,583 1,334,329 283,100,000.00 272,601,660.78 185,000,000.00 197,160,556.28

Page 8: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

5

The office scores a progress Since the establishment of DARO it has been serving the customers with keen and enthusiastic manner, it has accumulated different trophy awards and certificates from governments and non-government organizations and also has appreciated and honored by the customers.

WHEREAS, authentication of documents provide reliable means of evidence and thus facilitate social, economic, contractual and other relations between persons both at domestic and international levels as well as registration of documents ensures availability of documents whenever required and provide guarantees for constitutional

rights;

WHEREAS, it has become necessary to put in place law and procedure that meets international standard to make the activities of authentication and registration of documents uniform, effective and efficient all over the country;

WHEREAS, it has become necessary to amend the existing laws of authentication and registration of documents to create transparent relations between authentication and registration institutions and supervising improperly certified documents and to enable to have efficient economic and social relations among persons as

well as to make the procedures predictable and thereby to create one economic community;

The parliament endorses proclamation No: 922/2008 and makes DARO to DARA. Additional responsibilities and tasks are given based on Council of Ministers Regulation No. 379/2016.

The Agency shall have: A Director General and as may be necessary, Deputy Director Generals to be appointed by the Government; and the necessary staff.

The Agency shall have the powers and duties to: execute provisions specified in the

Page 9: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

6

Proclamation with respect to document authentication and registration as well as suspend improperly authenticated and registered documents; provide professional, technical and other similar assistance for regional document authentication and registration institutions as well as prepare forums of training, discussion and experience sharing; organize national central data base for authenticated and registered documents and network with other institutions; prepare and disseminate selected model formats for relevant documents authentication and registration institutions which may help for the establishment of uniform documents authentication and registration system in a nationwide;

Prime minister H/Desalenge approved positions for higher officials of DARA.

According to the letter written on September 1st 2016 from office of EFDR Prime minister ,The Ethiopia Federal Democratic Republic prime minister , Ato H/ mariam Desalenge assigned the agency”s higher official 1) Ato Merssa G/yohannes the agency’s head . 2) Ato Muluken Amare 3) Ato ashemawi seifu the agency’s operation affairs vice director .

prepare and forward policy ideas to the relevant concerned bodies which may enable it to attain the objectives; and implement same upon approval; prepare and submit internal regulations and directives to the Ministry and implement same upon approval; work in collaboration with the relevant federal and regional states; perform such other activities are conducive to the attainment of its objectives.

The Agency is doing best to make its service contemporary and popularize. Thus, the online contract is given and houses and cars sale are given for the customersin model documents. In the next 2nd GTP the Agency also has a plan to expand its branch offices up to twenty in Addis Ababa City Administration.

Page 10: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

7

In addition to economical development of the country, the attraction of the country’s land escapes observed had big memorable.The 25th Colorfully celebration of the down fall of Durg in Ethiopia, could makes the day special and historical because the day is celebrated on the dam by the workers and the directors.

After we arrived at the dam praying was taken place to the martyr, who lost their life being working for their country, And Ato Ahmed Nasir, Benishangul- Gumuz president, who depart near in death.

Engineer Simegnew Bekele, the

manager of the dam, welcomed the attendants and he appreciated the Agency’s reliable work and document authentication system to support the justice system and the investment it takes its part in the development of the country.

According to Engineer Simegnew the dam is the manifestation of nation, nationality and people of Ethiopia. And it has own great political, economic and social value be one family and Improving their life standards mainly by providing electric power in addition to tourism, recreation and negotiation of diplomatic impact of the country.

The manager explained that the

DARA staff visit Great Renaissance Dam Documents Authentication and Registration Agency workers visited the great Ethiopian Renaissance dam in May 28, 2016.E.C.

The Agency’s 85 workers and directors who visited the Dam are who didn’t participate in the first Round session.

As the time schedule may 26/ 2016 the trip was began from Addis Ababa and arrived at Nekemet town after a day journey and arrived at Assosa the second day. Stood at 3:00 A.M begun journey 45km distance in boarder of Sudan and arrived at 9;15 A.M to the great Ethiopian Reissuance dam.

Page 11: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

8

Documents Authentication and Registration Agency, Branch 11 office Manager has got a wonderful admire and respect after returning a customer bag containing 80,000 ETB and 300 USD , June 7,2008 E.C

A father of three, medical doctor who doesn’t want to mention his name officially was running late for an office information desk, after a while he has got useful information from an officer and dropped his bag. Just a few hours after he realized that his bag was dropped in hectic office. he said ˝I had left the bag containing essential documents and cash on customers information desk. However on the moment I didn’t have a time to make a trip to the bank and deposit the cash after I

An honest office manager returns more than 80,000 ETB to the claimant

sold my old car”The Manager of the office Mr MELSE KASSIE, who has a tendency of checking the office regularly before he left out and found the bag on the desk. Lately, he waited a long time to return the bag to claimant in front of witnesses. “It’s not the first time “Mr MELSE KASSIE, who has been the branch manager has found many valuable documents and cell phone in office and returned to the owners back. Now following his latest find he urging fellow employees to do the same if they find themselves in a similar situation.

At last the doctor admires Mr MELSE including the whole honest employees for their ethical action and their co operation.

great Ethiopian Reissuance dam is the 1st Dam in Africa and the 8th largest Dam in the world. It will have 246km length and 1874 square km width man made dam.

Before the conclusion w/ro Gete Feleke and w/ro Ergat G/yesus represent the agency and gave memorable gift to engineer Simegnew Bekele which is prepared by the attendants .

Page 12: AUTHENTICATION AND REGISTRATION AGENCY Magazine.pdfተልዕኮ ራዕይ እሴቶች Mission Vision Core Values በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌዴራል የሰነዶች

የፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ FEDERAL DOCUMENTS AUTHENTICATION

AND REGISTRATION AGENCY

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲበኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

ስልክ 011-551-14-49 / 011-553-71-33 ፋክስ 011-515-63-90 ዌብሳይት www.daro.gov.et

Facebook/ Document-Authentication-and-Registration-Agencyነፃ የጥሪ ማዕከል 888/.2

የዋናው መስሪያ ቤትና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አድራሻዎች ዋና መስሪያ ቤትከሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ከፊሊፕስ ህንፃ ፊትለፊት ጨለለቅ አልሳም ታወር ስልክ ማዞሪያ 011-553-47-88 ፋክስ 011- 515-63-90 / 011- 552-03-08 e-mail [email protected] website www.dara.gov.et

www.facebook.com /Document-Authentication-and-Registration-Agency

ቅርንጫፍ አንድ ጽ/ቤት ደብረዘይት መንገድ አጐና ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ 1ኛ ፎቅ

ስልክ 011- 552 -36- 44ቅርንጫፍ ሁለት ጽ/ቤት

ኮልፌ ሰፈረ ሰላም ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል አጠገብ ስልክ 011- 275- 86 -11ቅርንጫፍ ሶስት ጽ/ቤት

መገናኛ ደራርቱ ቱሉ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ስልክ 011- 655 -19- 67ቅርንጫፍ አራት ጽ/ቤት

ስድስት ኪሎ ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ስልክ 011- 124 -02- 70 ወይም 0111541273 Fax 011-124- 94- 12

ቅርንጫፍ አምስት ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወረድ ብሎ በሚገኘው ዳሮሌ ህንጻ 3ኛ ፎቅ

ስልክ 011- 155- 12 -43 ወይም 011541274ቅርንጫፍ ስድስት ጽ/ቤት

አየር ጤና አደባባይ ከሳሚ ሬስቶራንት አጠገብ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛፎቅ ስልክ 011- 348 -91 -33 Fax 011- 348 -04- 47

ቅርንጫፍ ሰባት ጽ/ቤትቃሊቲ ከተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ወረድ ብሉ ሚሚ

ስቲል አጠገብ ተልካም ህንፃ 1ኛ ፎቅ ስልክ 011- 439- 06- 07 Fax 011- 434- 62- 03

ቅርንጫፍ ስምንት ጽ/ቤትካዛንቺዝ ዮርዳኖስ ሆቴል ፊት ለፊት እናት ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ስልክ 011- 515 -26- 33

ቅርንጫፍ ዘጠኝ ጽ/ቤትከቄራ አንበሳ ጫማ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ማሩ ብረታ ብረት ፊት ለፊት SD ህንፃ 2ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011- 470 -43- 64ቅርንጫፍ አስር ጽ/ቤት

ሜክሲኮ ጨለለቅ አልሳም ታወር 2ኛ ፎቅ ስስልክ ማዞሪያ 011-553-47-88 ፋክስ 011 515-63-90/ 011 552-03-08

ቅርንጫፍ አስራ አንድ ጽ/ቤትከ ሲኤም ሲ አደባባይ ወደ ሰሚት በሚወስደው መንገድ ከሰንሻይን ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 1ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 011-869-55-73ቅርንጫፍ አስራሁለት ጽ/ቤት

ቦሌ መድሃኒአለም መድሀኒአለም ቤ/ክ ፊት ለፊት ማፊ ሲቲ ሞል / ብርሃኔ አደሬ/ ታወር አጠገብ የሚገኘው ህንጻ 3ኛ ፎቅ

ቅርንጫፍ አስራ ሶስት ጽ/ቤት በጎጃም በረንዳ ዮሃንስ ቤ/ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ 500 ሜትር ርቀት

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በሚገኝበት ህንፃ ላይ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ድሬዳዋ አስተዳደር ካውንስል ሕንፃ ውስጥ ስልክ ቁጥር 025-111-87-26 / 025-111-28-20 ፋክስ 025-111-05-56

ምንጊዜም ተገልጋዮችን እናስቀድማለን !!