Top Banner
መጽሐፍ ቅዱስ 2015 0 www.tlcfan.org 66? 81? ወይስ ? በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል
38

መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

Feb 15, 2018

Download

Documents

trinhnhan
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

0 www.tlcfan.org

66?

81?

ወይስ?

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

1 www.tlcfan.org

አስተማሪ ሊዮን ኢማኒኤል

መጽሐፍ ቅዱስ

የመጀመሪያ እትም

Copyright ©2009

የሁለተኛ እትም

REVISED 2015

መብቱ የተጠበቀ ነው፦

All rights Reserved to:

Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

FOUNDER OF

THE LION S CALL FOR ALL NATION INTERNATIONAL MINISTRY

Permission is granted to copy and quote freely from this publication for non-commercial purposes.

Page 3: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

2 www.tlcfan.org

ማውጫ

1. መግቢያ ................................................................................... 3

2. የመጽሐፍ ቅዱስ እንቆቅልሽነት ............................................... 6

3. መጽሐፍ ቅዱስ ልዮ መጽሐፍ .................................................. 10

4. መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ............................... 12

5. 22 የብሉይ ኪዳን መጻፍቶች .................................................... 13

6. ወንጌሎችና መልዕክቶች ......................................................... 21

7. አዲስ ኪዳን ............................................................................. 25

8. ሐዋርያትና አዲስ ኪዳን .......................................................... 34

Copyright © 2009

All rights Reserved

Page 4: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

3 www.tlcfan.org

መግቢያ

ከሰው ወይም ከጓደኛችሁ ታላቅ የሆነ ስጦታን የተቀበላችሁበት ቀን ልታስታውሱ

ትችላላችሁን? ያ ቀን የተደሰትንበት ብቻ ሳይሆን በልባችንም ትልቅ ነገር ጥሎ ያለፈበት ቀን

እንደ ነበር አያጠራጥርም። ስጦታው የሰጪውን ለእናንተ ያለውን ዋጋ የሚያሳይና በሁለታችሁ

መካከል ያለውን ግኑኝነት የሚያጸባርቅ ነው።

ልክ እንደዚሁ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጆች ሁሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠ

ስጦታ ነው። እግዚአብሔር የሰጠን ቃል ከእርሱ ውጪ ሊገለጡልን ያማይችሉ በአካባቢያችን

ያለውን ነገር ሁሉ ያስተምረናል ይገልጥልናል። ስለተፈጠሩት ነገሮችና ሰው እንዴት

እንደተፈጠረ እንኳን የምናገኘው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ማንኛውን

በሕይወት የሚገጥመንን ችግሮች የሚፈታ መርህም የያዘ ነው። እግዚአብሔር እንዴት

እቅዱንና ዓላማውን በዘመናቶች ውስጥ በመፈጸም በምድር ላይ መልካም ነገርን እንዴትና መቼ

እንደሚያመጣ መመልከት እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱሳችን ምን አይነት ታላቅ ስጦታ ነው!

ቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰጠንም ስለ እግዚአብሔር በግልጽ ይናገራል። ይህም

እርሱን እንድናውቀው ስለሚፈልግ ነው። ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር

እንድንቀርብም የሚያደርግ ሃይል ያለው የእግዚአብሔር ድምፅ የያዘ መጽሐፍ ነው። ሰው

አንድ መጽሐፍ ቅዱስ በቤቱ ካለው ፈጽሞ ብቻውን አይደለም።

መጽሐፍ ቅዱስ በዓለ ዙሪያ 2,300 ቋንቋዎች ተተርጉሟል። መጽሐፍ ቅዱስ በ90%

ሰዎች ዘንድ ይገኛል። ቢያንስ ከሚሊየን የሚበልጥ መጽሐፍ ቅዱስ በሳምንት ውስጥ በዓለም

ዙሪያ ወደ ሰዎች እጅ እንደሚሰራጭ ይታመናል። ይህም በገበያ መዝገብ ላይ ብቻ ያለውን

በማሰባሰብ የተጠና ጥናት ያረጋገጠው ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በዚህ ምክንያት ብቻ ከመጽሐፎች

ሁሉ በላይ ያደርገዋ።

መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ነው። 2.ጢሞ.3፥16 እንዴትን እንደ ሆነ ራሱ

መጽሐፍ ቅዱስ መልስን በ2.ጴጥ.1፥21 ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ደብዳቤ

የእግዚአብሔርን መልዕክት ለሰው ልጆች ሁሉ ይዟል። መጽሐፍ ቅዱስ ዘርን ቋንቋንና

ሃይማኖትን በመምረጥ የሚደግፍና የሚያደላ መጽሐፍ አይደለም። የሰው ልጆች ሁሉ

በጠቅላላው ዓለም የሚገኙ ማንበብ ሆን ይህም መልዕክት በቀላሉ መረዳት እንዲችሉ ተደርጎ

የተጻፈ ነው።

Page 5: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

4 www.tlcfan.org

መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም ቃሉ በተለያዮ

ሰዎች መጥቶ የተሰባሰበበትን ዘመናት ቆጥረን ነው። ይህን መጽሐፍ በመንፈስ ተመርተው

የጻፉት ሰዎች በተለያየ ዘመን ሃገርና ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው። በሳይንስ እንኳን

ብንመለከተው መጽሐፍ ቅዱስ ሁሌ ትክክለኛ ነው። ሳይንቲስቶች ምድር ክብ መሆኗን ሳያውቁ

ስለ ምድር ክብነት የሚናገር መጽሐፍ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ብዙ ሳይንቲስቶስ አገኘን

የሚሉት አዲስ ነገር ሁሉ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ እናገኘዋለን። በታሪክ አጥኚዎች

መነጽር ብንመለከተውም መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ ትክክል ነው።

በምድር ላይ ያለፉ ነገስታትን ታሪክ የምድር አቀማመጥና የሃገሮች ስም ሁሉ ይዞ

ይገኛል። ይህ የሆነበት ምክንያት መጽሐፉ ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እንጂ ሌላ አይደለም። ገና

ሰዎች ያልደረሱበት ስንት ሚስጥራትን ይዞ ይሆን?

መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር በመሆኑ የተነሳ ሰውን ለማስተካከል፣ ለማረም ልክ

እንደ አንድ እቃ ማኑዋል የሚሰራ ነው። ለሰዎች እንደ ማኑዋል የሚሰራ ከፈጣሪያቸው የተሰጠ

መርህ ነው። ሰው ያለ እግዚአብሔር ማኑዋል ማንነቱ ሊታወቅ ሆነ ሊታረም ካለበት ችግር

ሊጠገን ፈጽሞ አይችልም። 2.ጢሞ.3፥16

መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ትንቢታዊ ነው። ይህም ማለት በመጪው ዘመን የሚሆነውን

መረጃ ይሰጠናል። ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት ብዙ ትንቢቶች እንዴት እንደ ተፈጸሙ

በማስረገጥ ይህ ትንቢት ተፈጸመ በማለት ብዙ ጊዜ ከቃሉ ሲናገር እንሰማዋለን። ልክ እንደዚሁ

ደግሞ በእኛም ዘመን ሆነ በሚመጣው ዘመን የሚፈጸም ነገርን ጠቅልሎ የያዘ የከበረ መጽሐፍ

ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ድንቅ መጽሐፍ ነው። ስለዚህ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ ሆነ

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የእኛ ሃላፊነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የመጣ ስጦታ

እንደ መሆኑ መጠን ለራሳችን ጥቅም እንጂ ማንበብ ግዴታ የለብንም። ስጦታን መቀበልና

በክብር ስፍራ ማስቀመጥ ወይም የሚገባው ስፍራ ላይ ማስቀመጥ ተቀባዮ ለሰጪው ያለውን

ክብር ያሳያል። ሰው ስለ ሰው መናገር አይችልም። ምክንያቱም ሰው ሰውን አልፈጠረውምና

ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ሰውን ስለ ፈጠረ ስለ ሰው ሁሉ ከ ሀ እስከ ፐ መናገር ይችላል።

Page 6: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

5 www.tlcfan.org

ስለራሳችን ከሰው ከመስማት ይልቅ ከእግዚአብሔር በመስማትና ስለ ራሳችን ወይም

ሰሌሎችም የሰው ልጆች ማወቅ እንችላለን። ይህ ብቻ አይደለም ይህን ታላቅ ስጦታ የሰጠንን

ፈጣሪያችንን እግዚአብሔር እናውቃለን።

ስንቶቻችን ራሳችንን ክርስቲያን ብለን የምንጠራ መጽሐፍ ቅዱስን በሙሉ አንብበት

እናውቃለን? ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ሳናነብ በእውነት ክርስቲያን ብለን ራሳችንን ስንጠራ

አናፍርም? ቃሉ የሌላቸውን ኢየሱስ ዲያቢሎስ ብሎ ጠርቷቸው ነበር። እኛ ዛሬ እግዚአብሔር

ማን ብሎ ይሆን የሚጠራን? ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እናውቃለን? ስንቶቻችን መጽሐፍ

ቅዱስን በማንበብ የሁለ ጊዜ ተጠቃሚዎች ነን?

ብዙዎቻችሁ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት አንድርጌ እንደማነብና ቃሉን እንዴት

እንደማጠና በተደጋጋሚ ጠይቃችሁኛል ይህ መጽሐፍ ለዚህ እና ለተለያዮ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ

ለጠየቃችኋቸው ጥያቄዎች መልሶችን ይሰጣል ብዬ አምናለሁ። ምንም እንኳን ጥልቀት ባለው

መልኩ ሁሉን ሃሳብ በዚህ መጽሐፍ በዝርዝር ባልጽፈውም ከሞላ ጎደል የብዙዎችን ጥያቄ

ይመልሳል። የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብ የሚያነቃቃንን ያህል ሃሳብ በዚህ መጽሐፍ ላይ

አስቀምጫለሁ። እንዴት መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ እንደምንችልም ትምሕርትንም እናገኛለን።

ደግሞም በመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር 66, 81 ወይስ 49 ስንት ናቸው? የሚለውን ጥያቄ መልስ

ይህን መጽሐፍ አንብበን ስንጨርስ እናገኘዋለን። እግዚአብሔር ቃሉን የምታነቡበትን ጸጋ

ያብዛላችሁ!!!

Page 7: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

6 www.tlcfan.org

የመጽሐፍ ቅዱስ እንቆቅልሽነት

መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲገጣጥሙት ከአባት የተሰጠ

ፓዝል ወይም እንቆቅልሽ ነው። ይህን ስንል በውስጡ ያለው እውነት የተደበቀ ነው ለማለት

አይደለም። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚናገረውን ሃሳብ ትክክለኛውን ምስል ያለ ምንም

ስህተት ለመረዳት የተለያዮ ቃሎችን ከሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገባው መልኩ

በማሰባሰብ ልናገጣጥምና ልንመለከት እንደሚገባን ለማሳየት ነው። የእግዚአብሔር ቃል እንደ

እንቆቅልሽ ፍቺ የሚያስፈልገው መተርጎም የሚያስፈልገው ነው። ለዚህ ነው ኢትዮጴያዊው

ጃንደረባ የሚተርጉምልኝ ሳይኖር ስለ ማንና ስለ ምን እንደሚናገር እንዴት መረዳት እችላለሁ

በማለት ፊሊጶስ እንዲተረጉምለት ወደ ሰረገላው ወጥቶ ከጎኑ እንዲቀመጥ ጋበዘው።

የእግዚአብሔር ጋር መተርጎም እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ በተለያዮ ክፍሎች

ላይ ይህን ሃሳብ በመደገፍ ይናገራል። ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኃላ ያደረገው ነገር ቢኖር

የደቀመዛሙርቱን አዕምሮ ቃሉን እንዲያስተውሉ በውጡ የተጻፈውን እንዲረዱ መክፈትና

በሕጉ በነብያትና በመዝሙራት የተጻፈውን መተርጎም ነው። ሉቃ.24

የእግዚአብሔርን ቃል እንቆቅልሽነት ለመፍታት በውስጡ የተጻፈውን እግዚአብሔር

እንደሚናገርበት ትክክለኛ ሃሳብ ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ የተለያዮ መርሆችን

ያስቀምጥልና፣ ከዚህ በኃላ ያሉት አራት መርሆች በመጠቀም ቃሉን በውስጡ የተጻፈውን

እውነት ወደ መረዳት ልንመጣና እያንዳዳችን በግላችን በውስጡ የተጻፈውን እግዚአብሔርንና

የእግዚአብሔርን ነገር ሁሉ መመልከት እንችላለን፣

መሰረት፦

ሁልጊዜ ልናደርገው የሚገባው የመጀመሪያው መርሃችን የሆነው መሰረትን መጣል

ነው። ማንኛውንም አይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለመረዳት መሰረቱንና ምንጩን መመልከት

የመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያነቡ አማኞች ተግባራችን ነው። መጀመሪያ

የሚታወቀውን የቃሉን እውነት መሰረት በማድረግ ወደ ማይታወቀው ወደ ተሰወረው ሚስጥር

እንመጣለን። ይህም እያንዳዳችን ራሳችንንም ስናስተምር ነው።

Page 8: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

7 www.tlcfan.org

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን መሰረታዊ እውነቶች በትክክል ሳንረዳ ከፍ

ወዳለው እውቀት ራሳችንን ብናመጣ የተስተካከለን መንፈሳዊ እድገትና መንፈሳዊነትን በላያችን

ላይ አናመጣም። ልጃችንን በህጻንነቱ አልጄብራ እንደማናስተምረው ሁሉ መንፈሳዊ ነገር

እንዲሁ ነው። ከመጀመሪያ ከመደመር መቀነስ ጀምረን ከፍ ወዳለው ነገር እንሄዳላን

እናድጋለን። ነገር ግን እንደ መሰረት የጣልናቸው ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ የመረዳት

እውነቶች ግን ከፍ ወዳለው ነገር ለመድረስ ወሳኝና ሊዘነጉ ያማይገባቸው ናቸው።

ስለዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን እንቆቅልሽነት ለመረዳት ከመጀመሪያው ከመሰረቱ

በመነሳት በመሰረት ላይ ያገኘነውን እውነት በማሳደግና በማስፋት የሚቀጥል እንጂ

የመጀመሪያውን የሚጥል አይደለም።

መስመር በመስመር መጓዝ፦

ሁለተኛ መርሃችን ቃሉን መስመር በመስመር በቅደም ተከተል ማገጣጠም ነው።

አንድ ታሪክ ስናነብ የምናነበውን ከመጀመሪያው ከታሪኩ መሰረት በመነሳት በቅደም ተከተል

ወደ ታሪኩ መደምደሚያ በመጓዝ ነው። ማንኛውንም ቃል እየቀነጫጨቡ ማንበብ ትክክል

አይደለም። የመጀመሪያውን መርህ ከሁለተኛው ጋር በማጣመር ቃሉን ልናጠና ይገባል።

ይህም መሰረታዊ እውነትን በሕይወታችንና በልባችን በመጣል። ቃሉን በሙሉ በጥቅሉ ማንበብ

መቻል አለበት። የእግዚአብሔር ቃል በሙሉ አንብቦ የማያውቅ አማኝ አማኝነቱ ምኑ ላይ

እንደ ሆነ እኔ አይገባኝም። ይህን ስል በተለያየ ነገር ቃሉን ማንበብ የማይችሉትን አልልም።

የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና አንዳንድ ጊዜ ታሪኩ ሲያልቅ መጨረሻው ራሱ

ታሪኩን በክፍት ሊያቆመው ይችላል። ነገር ግን እንዴትና ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ በደንብ

አንብቦ የተረዳ ሰው ታሪኩ በሌላው መጽሐፍ ላይ ሲቀጠል በቀላሉ መረዳትን ያገኛል።

ካቆመበትም በቀላሉ በመጀመር ወደ ቀጣዮ ክፍል ያለምንም ችግር ሊሻገር ይችላል። አለበለዚያ

ቃሉን ጥቅስ እየለቀምን ከቃሉ እየወሰድን የምናጠና የምንማር ከሆነ ለስህተት የተጋለጥን

ከመሆናችን ማሻገር ወጥ የሆነ መንፈሳዊ እድገትን በላያችን ላይ ማምጣት አንችልም።

Page 9: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

8 www.tlcfan.org

ሰለዚህ የቃሉን እንቆቅልሽነት ለመፍታት ቃሉን መስመር በመስመር በቅደም

ተከተል ማንበብ አለብን። ቃሉ በዚህ መልኩ ማጥናት ከዚህ ባሻገር የነገሮችን ጅማሬና ፍጻሜ

እንድንረዳ ያደርገናል። ያነበብነውን ነገር አቁመን ስንጀምር ሃሳቡ በጠላት ከአዕምሯችን

እንዳይወሰድ የሚያደርግን ሕይወት እንለማመዳለን። ስለዚህ ቃሉ ሲነበብ ቆንጠር ቆንጠር

እየተደረከ ሊሆን አይገባውም። ለምሳሌ ዘፍጥረትን ማንበብ ከጀመርን ሳንጨርስ ወደ ሌላ

መጽሐፍ ባንሄድ መልካም ነው። ሌላ ሃሳብ ቢመጣልን እንኳን በወረቀን በመጻፍ አንብበን

ስንጨርስ ቀጥለን ልንመለከተው እንችላለን። በጠቃላይ መደባለቅ አይገባንም። ይህ ሦስተኛ

መርሃችን ቢሆንም ከአንደኛና ከሁለተኛው መርህ ጋርም የሚሄድ የማይነጣጠል ነው።

አለመደባለቅ፦

ሦስተኛው መርሃችን አንድን ነገር ከመሰረቱ በመነሳት መስመር በመስመር ማጥናት

ስንጀምር ሌላ ሃሳብ እንኳን ከሌላ ስፍራ ቢመጣልን የምናነበውን ስፍራ አለመቀላቀል መቻል

ነው። ነገር ግን ይህ ቃል ምንም እንኳ ከዚያኛው ጋር ቢገናኝ እንኳ የራሱ የሆነ የተጻፈበት

ዘመንና መንፈስ ስላለው ትክክለኛው ሃሳብ ለመገነዘብ አለመደባለቅ በጣም ወሳኝ የሆነ

የእግዚአብሔር ቃል ጥናት መርህ ነው።

ለምሳሌ ልክ እንድ ፍላጎት፣ ፍቅር፣ ፍስሃ፣ ፍሬና ፍጽምና ሁሉም በ ``ፍ``

ስለሚጀምሩ ብለን ሃሳባቸውን በመደባለቅ አንድ ለማድረግ ብንሞክር የተደበላለቀ መረዳትን

እንቀበላለን። ስለዚህ የቃሉን ሚስጥር ወይም ፍቺ ለመረዳት አንችልም። ቃል መደበላለቅን

ልናስወግድና ቃልን ከቃል ጋር አገናኝተን ስናጠና ደግሞ የሚሄደውን ከማይሄደውም ጋር

የሚፈታውን ከማይፈታው መለየትን ማወቅን መቻል ይኖርብናል።

ዋነኛውን መያዝ፦

የመጨረሻውን አራተኛ መርሃችን የምናነበውን ክፍል ዋናኛ ሃሳብ ማግኘት ነው።

የቃሉን ልብ ማግኘት ነው። ከቃሉ ጀርባ ያለውን መንፈስ ማግኘት ነው። በሌላ አማርኛ ከቃሉ

ጀርባ ያለውን መንፈስ መስማት መረዳት ነው። በአንድ ንባብ ውስጥ የተለያዪ ሐሳቦች ሊካተቱ

ይችላሉ። ነገር ግን የመልዕክቱ መካከለኛ ግን ሁል ጊዜ አንድ ነው።

Page 10: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

9 www.tlcfan.org

ስለዚህም የቃሉን ዋንኛ ነገር ማስተዋል ይገባናል። በመጀመርያ ከመሰረት በመነሳት

በቅደም ተከተል መስመር በመስመር በመከተል ያለመደባለቅ ማንኛውን ሃሳብ ማግኘት የሚችል

ማንኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ማግኘትና ቃልን ከቃል

መገጣጠምና የመጀመሪያውን የመነሻውን ቃል በሙሉ ክብሩና ስፋቱና በጥልቀቱ መመልከት

ይችላል።

ዳንኤል በዘመኑ የእግዚአብሔርን ቃል በራዕይ ተረድቶ ሲናገር ያየውን ሁሉ

አልጻፈም። ነገር ግን ከእግዚአብሔር በራዕይ ሆነ በህልም የመጣለትን ቃል ዋንኛውን መርጦ

ይናገራል። ከዚህ በፊት ከተገለጠው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚሄደውን ሌላውን

የእግዚአብሔር ቃል የማይጻረረውን በመመልከት መርጦ ይናገር ነበር። ዳን.7፥1 ስለዚህ

ከተጻፈው አለማለፍና የቃሉን ዋንኛውን ሃሳብ መረዳት ትልቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት

መሰረት ነው። ይህ ማለት ግን ለመንፈስ ቅዱስ ለሚገልጥልን አዳዲስ መረዳቶች ራሳችንን

መቆለፍ የለብንም። ለሌላ ሰው የማይሆን ለእኛ የሚሆንና የሚሰማ ብዙ ሊያሳየን ይችላልና

ነው። ራእይ.10፥4-4, 1.ቆሮ.2፥9

Page 11: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

10 www.tlcfan.org

መጽሐፍ ቅዱስ ልዮ መጽሐፍ

መጽሐፍ ቅዱስ ልዮ መጽሐፍ ለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለውም። ምንም እንኳ

የተለያዪ ቅዱሳን መጽሐፍት ጥርቅም ቢሆንም ቃሉ በመላው ዓለም በእያንዳንዱ ቋንቋ

የተረጎበመ ነው። በምድር ላይ ከሚገኙ ማንኛውም አይነት ሐይማኖቶች መጽሐፍ በላይና

በዓለም ካሉ ማንኛውም አይነት መጽሐፎች በላይ የታተመ መጽሐፍ ነው። ልዪ የሚያደርጉት

የተላያዮ ማንነት አሉት። ከእነርሱም መካከል አንዳንድ ሃሳቦችን እንድንመለከት እወዳለሁ፦

የእግዚአብሔር የራሱ እስትንፋስ ያለበት ስለሆነ ነው።

በ1500 ዓመቶች ውስጥ የተፃፈ መጽሐፍ ነው።

ከ40 ትውልድ በላይ የሚበልጥ ታሪክን ይዟል።

ከ40 በላይ በሚሆኑ ጸሃፊዎች ተጽፏል። እነዚህም ከተለያያ የግል ሕይወት ጎዳና

የመጡ ናቸው።

ሙሴ / በግብፅ ለመሪነት የሰለጠነ ፓለቲካዊ መሪ ነበር።

ጴጥሮስ/ አሳ አጥማጅ ነበር።

አሞፅ/ እስሳት ጠባቂ ነበር።

ኢያሱ/ የመታደሮች ጀነራል ነበር።

ነህቢያ/ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበር።

ዳንኤል/ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነበር።

ሉቃስ/ ዶክተር ነበር።

ሰለሞን/ንጉስ ነበር።

ማቴዎስ/ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር።

ጳውሎስ/ አስተማሪ ነበር።

በተለያዮ ስፍራዎች የተጻፉ ናቸው።

ሙሴ በምድረበዳ ጻፈው

ኤርሚያስ በዋሻ ጻፈው

ዳንኤል በተራራ ላይና በቤተመንግስት ውስጥ ጻፈው

ጳውሎስ በእስር ቤት ውስጥ ጻፈው

ሉቃስ በጉዞ ሳላ ጻፈው......ወዘተ

Page 12: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

11 www.tlcfan.org

በተለያያ ዘመንና ጊዜ የተጻፈ ነው።

ዳዊት በጦርነት ጊዜ

ሰለሞን በሰላም ጊዜ

ጳውሎስ በመከራ ጊዜ

ሙሴና ሉቃስ በጉዞ ጊዜ

በተለያየ መልክ የተጻፈ ነው።

አንዳዶች በደስታ ሌሎች በሃዘን

በትንቢት መልክ፣ በታሪክ፣ በምስክርነት፣ በምክር፣ በዝማሬ፣ በምሳሌ፣

በጥበብ......ወዘተ።

በሦስት አህጉሮች የተጻፈ ነው።

በእስያ፣ በአፍሪካና በአውሮፓ

በሦስት ቋንቋ የተጻፈ ነው።

በዕብራይስጥ

በአረማዊ

በግሪክ

የመጨረሻውና የመደምደሚያ መጽሐፍ ቅዱስን ልዮ የሚያደርገው

ዋንኛው ነገር እነዚህ ሁሉ ከላይ የዘረዘርናቸው የሃገር የሰዎች ማንነት መላያየት

የዘመን መለያየት የተጻፈውን ጽሁፍ እርስ በእርሱ እንዲቃረን እንዲጋጭ

አለማድረጉ ነው።

እነዚህ ጽሁፎች በተለያየ ዘመን ሥፍራና ሁኔታና በተለያየ የሕይወትና የስልጣን ደረጃ

ባላቸው ሰዎች ቢጻፍ እንኳ ቃላቸው ሁሉ የሚናገረው ስለ አንድ ነገር ነው። ስለ ኢየሱስ

ክርስቶስና አካሉ። ኢየሱስና ፍጥረቱ ስለዚህም ቃሉ መንፈሳዊ መኮታዊ እንደ ሆነ ልዮ እንደ

ሆነ በዚህ እናረጋግጣለን።

Page 13: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

12 www.tlcfan.org

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ

ቃሉ የእግዚአብሔር እስትንፋስ አለው። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ቃሉ

ከእግዚአብሔር ልብ የወጣ ስለሆነ ነው። 2.ጢሞ.3፥16 ይህን ለመረዳት ያህል እግዚአብሔር

ሲተነፍስ እንዚህ ሰዎች የተነፈሰውን አየር ስበው ያኑኑ አየር በወረቀት ወይም በዘመናቸው

በነበረው የእንስሳትም ቆዳ ሆነ በቅጠሎች ላይ በጹፍ አስቀመጡት። ይህ ማለት ምንም እንኳን

ቃሉ የእግዚአብሔር ቢሆንም የሰው ቃል ፈጽሞ አልተቀላቀለበትም ማለት ነው።

ከእግዚአብሔር ወደ ውስጣቸው የሳቡት እስትንፋስ ያንኑ በቀለም በዘመኑ በነበረው ነገር ላይ

አስቀመጡት። ቃሉ ስናጠና በቃሉ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን እስትንፋስ ለማግኘት ነው።

እግዚአብሔርና ቃሉ ፈጽሞ አይለያዮም። ቃሉ እግዚአብሔር ነው። ቃሉ

እግዚአብሔር ራሱ በጹሁፍ ሲገለጥ ማለት ነው። ከእያንዳንዱ የእግዚአብሔር እስትንፋስ

ካለባቸው ከእነዚህ ቃሎች ጀርባ የሚገለጠውና የሚታየው እግዚአብሔርና ሕይወት የሆነው

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

ኢየሱስ ከትንሳኤው በኃላ ከኢየሩሳሌም ወደ ኤማውስ እየተጓዙ ያሉትን ሉቃስንና

ቄሊዮጳስን በሕጉና በነብያት ጀምሮ አብራራላቸው ተረጎመላቸው። ሉቃ.24፥44 ከኢየሱስ

ንግግር ትምህርት ተነስተን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት በሶስት ዋና ክፍሎች እንደሚከፈል

መመልከት እንችላለን። እነርሱም ሕጉ፣ ነብያትና መዝሙራት ናቸው።

Page 14: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

13 www.tlcfan.org

22 የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ዝርዝር

በድሮ ወቅት ዕዝራ ከባቢሎን ባርነት በኃላ እንዳስተካከለው ብሉይ ኪዳን 22

መጽሐፍትን ብቻ የያዘ ነበር። 22 መሆኑ ደግሞ የራሱ የሆነ ሚስጥር አለው። ነገር ግን ከጥቂት

ዓመታት በፊት 22 መጽሐፍ ሆነው በዕዝራ ቅደም ተከተላቸውን የያዙ የዕዝራ መጽሐፎች ወደ

39 መጽሐፍቶች ተሰነጣጥቀዋል። ዕዝራ እንዳስቀመጣቸው ከዚህ በታች አስቀምጬዋለሁ፦

1. ሕጉ ዘፍጥረት

ዘጸአት

ዘሌዋውያን

ዘሁልቁ

ዘዳግም

2. ነብያት ኢያሱና መሳፍንት

የመንግስት መጽሐፎች (ሳሙኤልና ነገስት)

ኢሳያስ

ኤርሚያስ

ሕዝቅኤል

አስራ ሁለቱ (ታናኖሾቹ ነብያት/ ከሆሴ እስከ ሚልክያስ)

3. መዝሙራትና ቅዱስ ጽሁፎች

መዝሙር

ምሳሌ

ኢዮብ

መሃልይ መሃልይ

ሩት

ስቆቃው ኤርሚያ

መክብብ

አስቴር

ዳንኤል

ዕዝራና ነህሚያ

ዜና

Page 15: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

14 www.tlcfan.org

ኢየሱስ በማቴ.23፥35 የብሉ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ቅደም ተከተል የሚያሳይ ቃል

ጥሎልን አልፏል። ይህም ከአቤል እስከ ዘካርያስ በማለት ነው። 2.ዜና.24፥20,21 ከ391 ኤ.ዲ

በኃላ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት 39 መጽሐፍ ሆኖ ተከፋፈለ። ይህም የተከናወነው በጄሮም

በሚባል ሰው ሲሆን 22ቱን በሰላሳ ዘጠኝ ከፋፍሎ አስቀመጠው። ያስቀመጠውም በላቲን

በተተረጎመው “ቩልጌት” ተብሎ በሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው።

ከዚያን ጊዜ በኃላ የተተረጎሙ ማንኛውም አይነት የዚህን ሰው ፈለግ በመከተል

የተተረጎሙ መጽሐፍ ቅዱሶች ናቸው። እርሱም ሆነ ከእርሱ በኃላ የተረጎሙ ሰዎች ከ22

መጽሐፎች አላጎደሉም ወይም አልጨመሩም። ነገር ግን 22 የነበሩትን በ39 ከፋፍለው አሁን

በእጃችን በሚገኘው መልኩ መጽሐፍ ቅዱስን ለእኛ አሰተላለፉልን። ስለዚህም በ22 ቁጥር

አባቶቻችን በድሮ ዘመን ያስቀመጡበትን ዋንኛ ሃሳብ መንፈስና የልብ ሃሳብ ፈጽሞ አጠፏት።

22 ቁጥር የልጅነት ቁጥር ነው። የእግዚአብሔር ቃልና የእግዚአብሔር ልጆች

ግኑኝነት ከትውልድ ተደበቀ። ትውልድ በቁጥር ውስጥ ይመለከተው የነበረው የእግዚአብሔርና

የሰው ሕብረት ተለወጠ። ብርሃን የሆነው ቃሉና ዳግም የተወለዱ ልጆች ግንኙነት በጣም ወሳኝ

የሆነ ነገር ነው።

ልጆቹ በሚገለጡበት ወቅት ቃሉ የብርሃን አካልንም የሰጣቸዋል። በቃሉ ውስጥም

22,000 ሌዋውያን ከበኩር የተዋጁ ቤዛነትን የተቀበሉ እንደነበሩ እንመልከታለን። ይህ

በመጨረሻው ዘመን በልጆች ላይ የሚሆነው የሚያመለክት ትንቢታዊ ጥላ ነው። ዘሁ.3፥39

ዕዝራ 22 መጽሐፍ አድርጎ ብሉይን ሲከፋፍል የሚያውቀውና የሚረዳው ብዙ መለኮታዊ ይሆነ

መረዳ ስለ 22 ቁጥር ከእግዚአብሔር ዘንድ ለብሉይ ኪዳን መጽሐፎች የተቀበለው ቁጥር እንደ

ነበረ ማወቅ እንችላለን።

ሰለሞን የሰላም ንጉስ መቅደሱን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያስመርቅ 22,000 በጎችን

በስምንተኛው ቀን የዳስ በዓል ላይ ለመስዋዕትነት አቀረበ። 2.ዜና.7፥5 ይህ ስምንተኛ ቀን

የእግዚአብሔር ልጆች የሚገለጡበት ቀን የሚያሳይ ትንቢታዊ ጥላ ነው። 22 ቁጥር በተለያየ

መልኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲቀመጥ ታላቅ መልዕክት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር

የሚያያዝን ሚስጥር ይዞ ይገኛል። ሃያ ሁለት ቁጥርና የእግዚአብሔር ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ

ውስጥ ተነጣጥለው አናገኛቸውም። (‘’000’’ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቁጥር ሶስት ጊዜ ሲጻፍ

የሚያጸናው ራሱን ቁጥር ወይም ከፊቱ ያለውን ቁጥር በሶስት ምስክርነት ነው።)

Page 16: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

15 www.tlcfan.org

ጳውሎስ ተብሎ ከመጠራቱ በፊት የድሮ ስሙ ሳዖል የሚለው ስሙ 22 ጊዜ

በሐዋርያት ስራ ላይ ተጠቅሷል። ለመጨረሻ ጊዜ ሳዖል የተጠቀሰው በሐዋ.26፥14 ሲሆን

በአንድ ስፍራ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል። “ሳዖል ሳዖል ለምን ታሳድደኛለህ?” ይህ ቃል የተጠቀሰው

በ22 ቀን በ7ኛው ወር በስምንተኛው በዳስ በዓል ቀን ነበር። ይህም የሚያሳየው በርስታችን

የምንቀበለውን ሁለት እጥፍ በረከት ነው።

የአብርሃም ስም በዘፍጥረት 25፥5 ላይ ለ22ኛ ጊዜ ተጠቅሷል። ይህም አብርሃም

ያለውን ሃብት ሁሉ ለይሳቅ ሲያወርሰው ነው። ይህም ስምንተኛው የዳስ በዓል ቀን

የእግዚአብሔር ልጆች እርስታቸው የሆነውን የክርስቶስ አይነት የትንሳኤ አካል የሚቀበሉበት

ቀን አባታቸው የሚያወርሳቸው የሚያሳይ ነው።

እንዲሁ ደግሞ የእያሱ ስም በዘዳ.31፥7 ላይ ለ22ኛ ጊዜ ተጠቅሷል። ይህም ሙሴ

ስልጣኑን ለኢያሱ ሲያስተላልፍ ነው። ይህም ኢያሱ የቀረውን ሕዝብ ወደ ከንዓን ያስገባ ዘንድ

ነው። የዮሴፍ ስም በዘፍጥረት.39፥4 ላይ ለ22ኛ ጊዜ ተጠቅሷል። ይህሞ ጲጥፋራ በቤቱ ላይ

ሁሉ ጌታ አድርጎ ሲሾመውና ያለውን ሁሉ በእጁ ሲሰጠው ነው።

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገር የታመኑ የእግዚአብሔር ልጆች በቤቱ ሹመትና

ስልጣን እንደሚሰጣቸው እግዚአብሔር ተናግሯል። ሉቃ.12፥44 የከበረው አካላችን ከብርሃን

ጋር ተያይዞ ተገልጿል። በመቅረዙ ላይ 22 እንቡጥና በዮሐንስ ወንጌል ብርሃን 22 ጊዜ ተጠቅሶ

እናገኛለን። ይህ ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን 22 ቁጥር ምሳሌነት በመፍታት ብንነጋገር

ከሃሳባችን እንወጣለን ነገር ግን 22 ቁጥር ታላቅ ቁጥር እንደ ሆነ ካወቅን ይበቃናል። ከላይ

የጠቀስኳቸው ለምሳሌ ነው።

ይህም ሁሉ ዕዝራ ብሉይ ኪዳንን በ22 በመከፋፈል ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር

ያለውን ግኑኝነት አጥብቆት ነበር። የብሉይ ኪዳንን መጽሐፍት ከ22 ወደ 39 መጽሐፍት

ሲከፋፋል ትውልድ ያጣው 22 ከጀርባው የሰወረውን ታላቅ ሚስጥርን ነው። ነገር ግን

እግዚአብሔርን ትዕዛዝ አሜን ብሎ የሚቀበል ጌታን የሚወድና የሚመረምር ሰው የሚያገኘው

ሚስጥር ነው።

Page 17: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

16 www.tlcfan.org

39 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለመጽናት የመከራ ምሳሌ ቁጥር ነው። ብዙዎች

ይህን ቁጥር ብሉይ ያለ አዲስ ኪዳን የማይጸና ነውና 39 ቁጥር መከፋፈሉ መለኮታዊ ነው

ብለው የሚያምኑ አሉ። እኔ ግን የአባታችን ዕዝራ ያስቀመጠውን ቅደም ተከጠል እመርጣለሁ።

በአጠናን ደረጃ እንኳ ሳይቀር ታላቅ ሚና እንዳለው ተመልክቻለሁ። ብሉይ ኪዳን በራሱ ደግሞ

ሊጸና የማይችል ነው ብሎ የሚቀበል ልብ የለኝም። የእግዚአብሔር ቃል በቆመበት ስፍራ ሁሉ

ሙሉና ጽኑ ነው። ኢየሱስ በነበረበት ዘመን አዲስ ኪዳን መጽሐፍ የለም ነበር እንዴት ነው

ታዲያ ብሉይ ያለ አዲስ ማለት የምንችለው። ብሉይ ብቻውን ራሱ ኢየሱስን መግለጥ

እንደሚችል ማወቅ አለብን። ኢየሱስ ስለ እርሱ ደቀመዛሙርቱን ሆነ ሕዝቡ ያስተማረው ዕዝራ

ካሰባሰባቸው መጽሐፍቶች በመነሳት ነው።

ብሉይ ኪዳንን በሳዖል ልንመስለው አዲስ ኪዳን ደግሞ በጳውሎስ እንችላለን። ሳዖል

22 ጊዜ ስሙ ተጠቅሷልና ነው። ሁለቱ ማንነቶቹ ወሳኝ ሲሆኑ ነገር ግን የተላያዮ የእድገት

ደረጃዎችና ያሳያል። የዕብራይስጡ ቃል 22 ፊደሎች አሉት። በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ቃል

ብርሃን ያመለክታሉ። መዝሙር 119 ለ22 ክፍል ተከፋፍሏል። ይህም በእያንዳንዱ ከ1-22

ባሉት በዕብራይስጥ ቃሎች በሰየም ነው። እያንዳዱ ክፍል 8 ቁጥሮች አሉት። እያንዳንዱም

ክፍል የዕብራይስጡን ፊደል ይዟል።

ይህ ረጅምና 176 ቁጥር ያለው ምዕራፍ ነው። እያንዳንዱ ክፍል ስለ እግዚአብሔር

ቃል፣ ስለ ሕግ፣ ትዕዛዛት...ወዘተ ይናገራል። ይህም የእግዚአብሔር ቃል በ22 ፊደሎች

እንደተቀመጠ በግልጽ ያሳያል። ዕዝራ ይህንንም መሰረት በማድግ ብሉይ ኪዳንን በ22

እንደከፋፈለው ልንመለከት እንችላለን። በብሉይ ኪዳን ለነበሩ ቅዱሳን 22 ቁጥር የፍጽምና

የሙላት ቁጥር ነበር። ብሉይ ኪዳንን ዕዝራ 22 ቁጥር ሲከፍለው ሙሉነቱንም ለማሳየት ነው።

በመጨረሻም በአዲስ ኪዳን ዘመን መጨረሻ የቀረው ሐዋርያ ከሽማግሌዎች ጋር

በኢየሩሳሌም ተነገግሮ ከአዲስ ኪዳን ብዙ መጽሐፎች መካከል 27 መጽሐፍት በብሉይ ኪዳን

ላይ እንዲጨመሩ መክሯል። ይህም መጽሐፍ ቅዱስን በዕዝራና በዮሐንስና በጳውሎስ

የተጨመሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ድምር 49 እንዲሆን አድርጎታል።

ይህም ቁጥር ሙሉ ኢዮቤልዮን የሚያሳይ ቁጥር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ኢዮቤልዮ

መጽሐፍ የሚል ውስጣዊ ስም እንደሚይዝ ያሳይ ነበር ማለት ነው። 27 ዮሐንስ የመረጠው

ቁጥር የደህንነት አገልግሎት ቁጥር ሰለሆነ ነው ብዮ አምናለሁ።

Page 18: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

17 www.tlcfan.org

ሰለ መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ ‘’የቁጥሮች ትርጉም’’ የሚለውን

መጽሐፌን ያንብቡ። 27 የአዲስ ኪዳንን የወንጌል አገልግሎት ምስክርነት መዝግቦ የያዘ

የመጽሐፍት ቁጥር ነው። ይህ ዮሐንስ እንዳስቀመጠው 27 ሆኖ እስካሁን በዚህ ቁጥር ጸንቶ

ይገኛል። ዮሐንስ ራዕይን 22 ምዕራፍ ማስቀመጡ ስለ ብሉይ ኪዳንን በአንድ ጨምቆ

ማስቀመጡ ይሆንን?

ጄሮም መጽሐፍ ቅዱስን በ39 ክፍል ነጣጥሎ ከመከፋፈሉ በፊት 22 እንደነበረ

እውቅናን ይሰጣል። ይሁንና በ391 ኤ.ዲ ጄሮም ለሳሙኤልና ለነገስት መግቢያ ድፏል። በዚያ

ላይ ይህንን እውቅና እንደ ሰጠ እንመለከታለን። ምክንያቱም ከ22 መጽሐፎች ወደ 39

የነጣጠላቸው እርሱ ነውና ነው።

In 391 A.D. Jerome wrote in his Preface to Samuel and Kings,

"As, then, there are twenty-two elementary characters by means of which we write in Hebrew

all we say, and the compass of the human voice is contained within their limits, so we reckon

twenty-two books, by which, as by the alphabet of the doctrine of God, a righteous man is

instructed in tender infancy, and, as it were, while still at the breast."

http://www.ccel.org/ccel/schaff/npnf206.vii.iii.iv.html (See end of second paragraph)

ይህን ያስቀመጥኩ ጀሮም ራሱ ብሉይ ኪዳን 22 መጽሐፍ እንደነበሩ እውቅና

እንደሰጠ ራሳችን እንድንመልከት ነው። የሰጠሁትን ድረ ግጽ በመመልከት ይህን ራሳችን

ማረጋገጥ እንችላለን። የሚያሳዝነው ግን ምንም እንኳን 22 እንደሆኑ ቢያምንም ለ39

ሰነጣጥቆታል። ዶክተር ቡሊንጀርም ይህንን እውነት ተረድቶ ነበር። በኮንፓንየን መጽሐፍ

ቅዱስ ትርጉም ላይ ይህን ጠቅሶ አልፋል።

Dr. Bullinger he wrote in Appendix 95 of The Companion Bible,

"Our English Bibles follow the order as given in the Latin Vulgate. This order, therefore, depends

on the arbitrary judgment of one man, Jerome (A.D. 382-405). All theories based on this order

rest on human authority and are thus without any true foundation."

Page 19: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

18 www.tlcfan.org

ጆሲፈስ የአይሁድ ካህን የሆነ በመጨረሻም የታሪክ ጸሃፊ የሆነ ታላቅ የእግዚአብሔር

ሰው ነው። ብሉይ ኪዳን 22 መጽሐፍ እንደሆኑ ይናገራል። ይህንን ምስክረነቱን “አጌኔስት

አፒዮን” መጽሐፉ ላይ አስቀምጦታል።

Josephus, the first-century Jewish priest-turned-historian, for he says in his book, Against

Apion, I, viii,

"For we have not an innumerable multitude of books among us, disagreeing from and

contradicting one another [as the Greeks have] but only twenty-two books, which contain the

records of all the past times; which are justly believed to be divine; and of them, five belong to

Moses, which contain his laws, and the traditions of the origin of mankind till his death."

እንግዲህ በእነዚህን በድሮ ዘመን በነበሩ ምስክሮች ላይ የሌሎችንም ምስክሮች

መጨመር እንችላለን። ሁሉ የብሉይ ኪዳን መጽሐፎች ዕዝራ እንዳስቀመጠው ከላይ እንዳያነው

22 እንደሆኑ ይመሰክራሉ። ብዙ በአሁን ዘመን ያሉ መጽሐፍ ቅዱሶች የአማረኛውን ጨምሮ

የተተረጎሙት ከግሪኩ ነው። ቁጥራቸው ጄሮም እንዳስቀመጠው 39 ናቸው። በእርግጥ የሰው

ልጆች ከክርታስ ጥቅልል መጽሐፍ ወደ ሚገለጠው መጽሐፍ መለወጣቸው በጣም አስፈለጊና

ተገቢ ነው ብዮ አምናለሁ። ምክንያቱም በአሁን ዘመንም የመጽሐፍ ጥቅልሎች ብንጠቀም

ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስን ተሸክሞ ለመሄድና በጉባሔ መካከልም ገልጦ ለማንበብ በጣም አስቸጋሪ

ይሆን ነበር። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ለመጀመሪያ ጊዜ በመግዛት መጠቀም የጀመሩ ጊዜ ይህ

አቀማመጥ ለእነርሱ በቀላሉ ለማንበብ የሚመች ነበር። ሌላ ለማንበብም ቢፈልጉ 22 መጽሐፍ

ሆኖ የተዘጋጀ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ አልነበረም። ንጉስ ጀምስ (kjv)ን የተረጎመው ከዚሁ ሰው

ትርጉም በመነሳት ከግሪኩ ወደ እንግሊዘኛው ተረጎመው።

ይህ ሁሉ ይሁን እንጂ እያንዳዳችን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ በድሮ አባቶቻችን

ዘመን በ22 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተከፋፈለ እንደነበረ ሁላችን ልናውቀው የሚገባ ነው፣

ወደ እዚህ ወደ ድሮ ጥቅል መጽሐፍ መመለስ አለብን እያልኩ አይደለም። ነገር ግን

እግዚአብሔር ባሪያዎቹን ተጠቅሞ ያስቀመጠው ለትምህርታችን ፈጽሞ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ

ለግል ጥቅም ወይም ዝም ብሎ መጽሐፉን መበታተን ወይም ቅደም ተከተላቸውን ማበላሸት

አይገባም ብዬ አምናለሁ።

Page 20: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

19 www.tlcfan.org

የጀሮምን በ39 የተከፋፈለ መጽሐፍ ማንበብ ግን ሃጢያት ነው ብዬም አላምንም።

ነገር ግን በድሮ ዘመን አቀማመጥ የተቀመጡ መጽሐፍ ቅዱሶች አሁን በገበያ ላይ ይገኛሉ።

ይህ ማለት በውጣቸው የያዘው ቃል ይለያል ማለት ሳይሆን አቀማመጣቸው 39 ሆኖ

ከመከፋፈል ይልቅ 22 ሆኖ ምንም ቃል ሳያጎድልና ሳይጨምር በዕዝራ በድሮ ዘመን በነበረው

መልኩ ተደርድሮ ተቀምጧል። በአደራደር የዕዝራና የጀሮም ስብስብ የለያያሉ። ነገር ግን

ምንም ቃል አልጨመረም አልቀነሰም። ይህን መግዛት ለምትፈልጉ በዚህ አድራሻ ሄዳችሁ

ድረ-ገጽ ላይ ልታገኙት ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ በድሮ ወይም በመጀመሪያ

መልኩ በሚል ርዕስ ስር ብትፈልጉም ታገኙታላችሁ፦

http://www.amazon.com/Holy-Bible-Its-Original-

Order/dp/0967547997/ref=sr_1_3?ie=UTF8&s=books&qid=1233391020&sr=1-3

እግዚአብሔር ቃል ትክክለኛ ቅጂውና በድሮ ዘመን በነበረው ቁጥሩ ማንበብ

የሚጨምረው እንጂ የሚያጎድለው ነገር የለውም። ሮም ኢየሩሳሌምን በወረረችና መቅደሱ

በፈረሰ ጊዜ በማደሪያው ድንኳን የነበረውን የወርቅ ገበታውንና መቅረዙን ጨምረው ሮማውያን

በ70ኛው ኤ.ዴ ወደ ሮም ወስደውታል። ይህንን አይሁዳዊው ካህን የነበረው ጆሲፈስ የተባለው

ጸሐፊ የአይሁዶች ጦርነት በሚለው መጽሐፉ ላይ በዝርዝር አስቀምጦታል።

Wars of the Jews, VII, v, 5 (end of par. 5),

". . . for the other spoils, they were carried in great plenty. But for those that were taken in the

temple of Jerusalem, they made the greatest figure of them all; that is the golden table, of the

weight of many talents; the candlestick also, that was made of gold . . . and last of all the spoils

was carried the Law of the Jews."

አባቶቻችን ያስቀመጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ቅደም ተከተል በቸልተኝነት ይሁን

መልካም በማሰብ የመጀመሪያውን መልኩን አጥቷል። በታሪክ አዲስ ኪዳን የሚሆኑትን

መጽሐፎች ደግሞ ለመምረጥ ዮሐንስ ጴጥሮስና ጳውሎስ ለውሳኔ ተጠርተው እንደነበር በታሪክ

ተዘግቦ ይገኛል። ይህ በ27 የተከፋፈለውን የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጠናቀቀው ጳውሎስ

በሮም ታስሮ በነበረበት ወቅት ነው።

Page 21: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

20 www.tlcfan.org

ጄሮም ከብሉይ ኪዳን በኃላ አዲስ ኪዳንንም አስተካክሏል ነገር ግን የአዲስ ኪዳኑ

ቅደም ተከተል ከሃይማኖታዊ ፓለቲካ ጋር በተያያዘ መልኩ ነበር የደረደራቸው። የአዲስ ኪዳን

መድሐፍ አደራደር በአራቱ ወንጌል ይጀምርና አምስተኛውን ወንጌል ሐዋርያትን ሰራ

ያደርጋል። ይህም አቀማመጥ የብሉይ ኪዳኑን የ5ቱን የሙሴም መጽሐፎች የሚያንጸባርቅ

ለማድረግ ነው።

In Appendix 2 of Chapter 1, Restoring the Original Bible, by Dr. Ernest Martin, he quotes from

Professor R. Gregory in A.D. 1907, who wrote a book called Canon and Text of the New

Testament. The quotation is from page 467-469 of Gregory's book:

"The order in which we place the books of the New Testament is not a matter of indifference.

Every Christian should be familiar with these books, and should know precisely where to find

each book. Every New Testament should have the books in precisely the same order, the order

of the Greek Church, which in this case is of right the guardian of this ancient literature [see

Romans 3:1, 21]."

ከዛም ይህን ሃሳብ ካስቀመጠ በኃላ ይህ ሰው እነዚህን የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅደም

ተከተሎች ያስቀምጣል። በሚቀጥለው እርዕስ ላይ በዝርዝር እንመለከተዋለን፦

Page 22: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

21 www.tlcfan.org

ወንጌሎችና መልዕክቶች

ይህ ቅደም ተክተል ዶክተር ኢቫን ፔኒ በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ትርጉሙ ላይ

በ1914 በታተመው ህትመት ላይ ይህን የቀደመ የአዲስ ኪዳን ዝርዝር በመከተል

አስቀምጦታል። ይህ ዶክተር ይህን ዘርዝር የተጠቀመበት እያንዳንዱ ቃል ቁጥር ስላለው

በቁጥር አቀማመጡ ትክክለኛው ይህ መሆኑን በብዙ መረጃዎች በማስረገጥ ይህ የአዲስ ኪዳን

የሚለውን ለሕዝብ አቅርቧል።

ይህ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ የቁጥር መልዕክቱ ትክክለኛ ግቡን እንዲመታ ከላይ

ባየነው መልኩ መቀመጥ እንዳለበት ትክክለኛውም የአዲስ ኪዳን አቀማመጥ ይህ እንደሆነ

አስረግጦ አልፏል። የሰውየውን ሃሳብና በዘመኑ ያቀረበውን መረጃ ካነበብኩ በኃላ ይህ ሰው

ትክክለኛ ሐዋርያቶች ያሰቀመጡትን ቅደም ተከተል ተከትሎ አሰቀምጦታል ብዬ ለማመን

በቅቻለሁ።

ማቴዎስ

ማርቆስ

ሉቃስ

ዮሐንስ

የሐዋርያት ሥራ

ያቆብ

1ጴጥሮስ

2ጴጥሮስ

1ዮሐንስ

2ዮሐንስ

3ዮሐንስ

ይሁዳ

ሮሜ

1ቆሮንጦስ

2ቆሮንጦስ

ገላትያ

ኤፌሶን

ፊሊጵስዮስ

ቆላስያስ

1ተሰሎንቄ

2ተሰሎንቄ

ዕብራውያን

1ጢሞቴዎስ

2ጢሞቴዎስ

ቲቶ

ፊልሞን

ራዕይ

Page 23: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

22 www.tlcfan.org

ጄሮም የጳውሎስን ጽሁፎች መጀመሪያ በማድረግ በሐዋርያት የተቀመጠውን

የአዲስ ኪዳን አቀማመጥ አጥፍቶታል። በእርግጥ በመጽሐፉ ላይ ምንም የጨመረውም ሆነ

አያጎደለው ነገር የለም። የጳውሎስን ትምህርት ከቀደሙት ሐዋርያት መልዕክቶች ያስቀደመው

ለጳውሎስ ሰለ ሰራው ሥራ የከበሬታን ስፍራ ለመስጠት እንደሆነ ራሱ ተናግሯል።

ይህም የሮማን ጳጳሳት ጳውሎስ ሮማዊ እንደሆነ በመታመን ለሃይማኖታቸው

መመኪያ እንደሆነ ስለሚያውቅ እነርሱን ለማስደሰትና የተረጎመው መጽሐፍም ለገበያ ከዚህ

የተነሳ እንዲበቃ እንዲቀለው ለማድረግ ነው። ይህም ሃሳቡ ተሳክቶለት አዲስ ኪዳን አሁን

በእጃችን በሚገኘው መልኩ እንዲቀመጥ አድርጎታል። ይህ የሮማን ጳጳሳት በዘመናቸው

ያስደሰተና ያኮራ ለእነርሱ የሃይማኖት ፓለቲካ ታሪካዊ የሆነ ትልቅ ስፍራና ትርጉም ያለው

ነው።

በመጀመሪው በአዲስ ኪዳን ዘመን የኢየሱስ የሥጋ ወንድም ያቆብ በኢሩሳሌም

ከነበሩ የእምነት አዕማድ መካከል አንዱ ነበር። ያኔ በዚያን ዘመን ኢየሩሳሌም የክርስትና

ሃይማኖት እንብርት ነበረች። ጳውሎስ በወንጌሉ ተቃውሞ በደረሰበት ጊዜ ጥያቄውን

ለማስፈታት የሚሄደው ኢየሩሳሌም ነበር። ሐዋ.15 ላይ ይህንን እንመለከታለን። ትምህርቱ

ትክክል እንደነበረ ከረታ በኃላ በያቆብ የተጻፈ በሚያገለግልበት ቦታ ሁሉ የሚያቀርበው ደብዳቤ

ተጽፎለት ለአገልግሎት ከኢየሩሳሌም ተላከ።

ያቆብም ሆን የእርሱ ሌላ ወንድም ይሁዳ በኢየሱስ አገልግሎት ጊዜ አማኝ

አልነበሩም። ይህን እውነት በዮሐ.7፥5 ላይ መመልከት እንችላለን። ነገር ግን ከትንሳኤው በኃላ

ወደ እምነት መጥተዋል። ይህ ከክርስቶስ ጋር ያለውን መንፈሳዊ ህብረት ለማድረግ ብዙ

እንደሚያዳግታቸው መገመት እንችላለን። በሥጋ ወንድም የሆነን ሰው አምላክና ጌታ አድርጎ

መቀበል ታላቅ እምነትን የሚጠይቅ ነው። መንፈሳዊ ሕብረቱ ደግሞ ከዚህ የሚቀጥል ነው።

ያቆብ የኢየሩሳሌም ቤተክርሲያ አዕማድ የተደረገው በ44ኛው ኤ.ዲ ላይ ነው።

ይህም ሄሮድስ ሌላኛውን ያቆብ ከገደለው በኃላ ነው። የሞተው ያቆብ የዘበዴዎስ አንደኛ ልጁ

ነበር። ያቆብ ሲገደል የተገደለው በእስፔን የወንጌል አገልግሎቱን ጨርሶ እንደተመለሰ ነው።

ሄሮድስ በሰይፍ ገደለው። ሐዋ.12፥3 ሐይማኖተኞችን እንዳስደሰተ ሲያውቅ ጴጥሮችንም

ጨምሮ አሰረው። የፋሲካ በዓል ሰለ ነበር ሊገለው አልቻለም፣። ነገር ግን በዓሉ እስከሚያልፍ

ጠበቀ። ሐዋ.12

Page 24: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

23 www.tlcfan.org

ከፋሲካ በኃላ ጴጥሮስን እንዳይገድለው መልአክ ከእስር ቤት አስወጣው። ጴጥሮስም

ወደ ቂሳሪያ አመለጠ። እርሷም ሮም ከሚቆጣጠራት ከተማ አንዷ ናት። በዚያ ፊሊጶስ

መኖርያውን ከጴጥሮስ ስደት በፊት እዛ አድርጎ ነበር። ጴጥሮስ እርሱ ጋር እንዳረፈ ግልጽ

ነው። ሐዋ.8፥40,21፥8,9 ወደ ሃሳባችን እንመለስና ሐዋርያት የተውጣጣን ደንብ በኢየሩሳሌም

ለምትገኘው ቤተክርሲያን አውጥተው ነበር። እነዚህም ደንቦች ከሃገር ሃገር ለወንጌል ሥራ

በተመላለሱ ወቅት ለሌሎቹም ይህን ደንብ ይሰጡ ነበር። ነገር ግን ኢየሩሳሌም የሁሉ ነገር

መነሻና ከበድ ያሉ ችግሮች የሚፈቱባት ቤተክርሲያን ነበረች። ጴጥሮስ ወደ ቂሳሪያ ከዛም ወደ

አንጶቅያ ከሸሸ በኃላ ከሄሮድስ ሽሽት ለብዙ ርቆ አልቆየም ወዲያው ተመለሰ። ምክንያቱን

ሄሮድስ ስለሞተ ነው።

ከዚያም ከተመለሰ በኃላ የኢየሱስን ወንድም ያቆብን በኢየሩሳሌም ጳጳስ አድርገው

ቀቡት። ያቆብ በኢየሩሳሌም ለነበረችው ቤተክርሲያን አዕማድ ነበር። ጴጥሮስም የቤተክርሲያን

ከያቆብና ዮሐንስ ጋር አዕማድ ነበር። እንግዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጳጳሳት የነበሩት በኢየሩሳሌም

እንጂ በሮም አልነበረም። ያቆብ 62 ኤ.ዲ ሰማዕት እስከሚሆንበት ቀን ድረስ ሁለተኛ ጳጳስ

ነበር። ከእርሱ በኃላ የአጎቱ ልጅ ስምዖን ጳጳስ ሆኖ ተቀብቷል።

በዚያን ወቅት ለቤተክርሲያን ሽማግሌዎች መገዛትና ማክበር በጣም አስፈላጊና

ሁሉም ደግሞ በደስታ የምያደርጉት ነበር። ሐዋርያትም ሆነ ሌሎች አገልጋዮች የሚጠሩት

በስልጣናቸውና በክብር ስማቸው ነበር። በኢየሱስ አገልግሎት ወቅት በብዛት ከክርስቶስ ጋር

በአገልግሎትና በጉዞ ጎልተው የሚታዮት ሦስቱ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያቆብ ናቸው። ማቴ.17፥1

በዚያን ወቅት ጴጥሮስ እንደ መሪ ይታይ ነበር። ነገር ግን በኃላ ጳውሎስ ያቆብ መሪ እንደነበር

ተናግሯል። ቀያፋ ደግሞ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንደ ነበሩ ተናግሯል። ገላ.2፥9

ጳውሎስ 14 መጽሐፍን ጽፏል 10ኛው የዕብራዊያን መጽሐፍ ነው። ጄሮም ከሌሎቹ

መጽሐፎች በመለየት ከያቆብ በፊት አስቀመጠው። ይህም ያቆብን መጽሐፍ ለማራቅ ለገበያና

የሮማውያንን ልብ ለመሳብ የተደረገ የሰው ሃሳብ ነበር። ጳውሎስ በዚያን ወቅት በሮማ

ሃይማኖተኞች ሰዎችም ጭምር ይኮራበት የነበረ ሮማዊ ነው። ከሃዋርያቶች ሁሉ በደረጃ

የሚያንሰውን ማነሱንም ራሱ ጳውሎስ የተናገረውን ባለማስተዋል ከያቆብ በፊት አደረገው።

ይህ በደረጃ ማስቀመጥ ከፈለገ ነው።

Page 25: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

24 www.tlcfan.org

1ቆሮ.15፥9, ገላ.2፥7 የጀሮም ሃሳብ የጳውሎስን መጽሐፎች ከጴጥሮስና ከያቆብ

የበለጠ ነገር እንዳላቸው ለማሳየት መሆኑን በዘመኑ የነበሩ በተለያየ የትችት መጽሐፋቸው

አስቀምጠውታል። ዛሬም ለዶክትሪንና ለሃይማኖት ተብሎ የሚተረጎሙ መጽሐፍ እውነተኛ

ሃሳባቸውን እንደሚለቁ ማለት ነው። ይህ ሰው ግን ሃሳባቸውን ሳይሆን አደራደራቸውን

አቀያየረው። ለአሁን ላለንበት ዘመን ምንም አይጠቅምም ብንልም ይህ መሆኑ ግን በዘመኑ

የራሱ የሆንን ታሪክና ሥራን ሰርቶ ያለፈ አከራካሪ የነበረ ጉዳይ ነው።

ይህ የአዲስ ኪዳን መጽሐፎች አደራደር በአራተኛው ክፍለ ዘመን የኢየሩሳሌም

ቤተክርሲያንን ሕጋዊነት ለማሳጣት ለተጀመረው የሃይማኖታዊ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ታላቅ

ቁልፍ ነበር። ይህም ተሳክቶ በኢየሩሳሌም ፋንታ ሮም የክርስቲያን መዓከል እንድትሆን

አድርጓታል። ይህ አይሁዶችም የሚፈልጉት ጉዳይ ነበር። ምክንያቱም አዲስ ኪዳንን

አይቀበሉም በኢየሱስም መሲህነት አያምኑም ነበርና ነው። ሐዋ.15፥25 ኢየሩሳሌም ትልቅ

ታስተዳድር የነበረች በጳጳስ ያቆብ የምትመራ ቤተክርሲያን እንደዚህ ባለና በተመሳሳይ ጉዳዮች

ክብሯን አጥታለች። ሐዋርያት በዚያን ዘመን የነበረውን የባሕል ልዮነት ተገንዝበው ነበር።

የተለያዮ ባሕሎችንም በሚገባ መልኩ በማቅናት ተቀብለው በትክክለኛ መልኩ አስተናግደው

ነበር። ነገር ግን ሐዋርያት በዚህ ዘመን እውነተኛይቱ ቤተክርሲያን ነን ብለው ሌላ የጽድቅ

መንገድን እንዳበጁ ሌላ የጽድቅ መንገድን ባሕላቸው ልዮ ለሆነ ፈጽመው አላበጁም።

የጽድቅ መንገድ አንድ ነው። አሁን ግን እውነተኛ ቤተክርሲያን ነን የሚሉ ብዙ

የጽድቅ መንገዶችን በሰው አዕምሮ አበጅተዋል። ይህን ለምን እንዳደረጉ ቢጠየቁ ከሐዋርያት

በጥበባቸው የነጠቁትን ስልጣን ተሰጥቶናል በማለት ብዙ የታሪክ መጽሐፎችንን ይደረድራሉ።

ይህ ሁሉ ግን ከእውነት የራቀ ነው። ከፍ ባለ በእግዚአብሔር ሃሳብና ቃል ላይ የሚነሳውን

ማንኛውም ሃሳብ እንደነ ጳውሎስ እኛም በዚህ ዘመን እናፈርሳለን።

ሙሴ ሕጉን ከጻፈ በኃላ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥቶታል። ዘዳ.31፥9 ይህም

በታማኝነት የሰጠው በዘመኑ ለነበሩ ታቦቱ ይሸከሙ ለነበሩ ለሌዊ ልጆች ለካህናቱና ለእስራኤል

ሽማግሌዎች ነበር። ያኔ ለመንግስቱ ታማኝ ሆነው የተገኙ እነርሱ ነበሩ። ከ1000 ዓመት በኃላ

ዕዝራ የሚባለው ካህን የብሉይ ኪዳንን መጽሐፍ አደራደርና ደረጃ አስተካክሎ ጨረሰ። ዕዝራ

በትውልዱ ከአሮን ዘር ግንድ ነው። ዕዝ.7፥1-5 ይሁንና በዕዝራ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ዝርዝር

ውስጥ ያልገቡ ከዚያ በኃላም ሆነ በፊት የተጻፉ መጽሐፎች ነበሩ።

Page 26: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

25 www.tlcfan.org

ዕዝራ በ22 የብሉይ ኪዳን መጽሐፎች ላይ ዕዝራ ያስተካከላቸውና የጨመራቸው

የቀሩ ጥቃቅን እውነቶች አሉ። እነዚህም ሰለ ኤዶማውያን ንጉስ በዘፍጥረት 36 ላይ ያለውን

ታሪክ፤ ይህ በዚህ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የስም ዝርዝር 300 ዓመት ከሙሴ ሞት በኃላ የሆነ

ነው ስለዚህ ሙሴ ሊጽፈው አይችልም። ምክንያቱም ይህ የስም ዝርዝር ከሙሴ ጀምሮ እስከ

ንጉስ ሳዖል ድረስ ያለውን የስም ዝርዝር ይይዛልና ነው። ቁጥር 31 ይህን በደንብ ያስረዳል።

ሌላውም በዕዝራ የተስተካከለ በዘዳግም.34፥5-12 የሕጉ መጨረሻ በሆነው መጽሐፍ

ላይ የሙሴ የመጨረሻ ሕይወት የሰራው ሥራ ተዘግቦ እናያለን ይህ ሙሴ መጽሐፉን ጽፎ

ሲያስረክበው በመጽሐፉ ላይ አልነበረው ይህ በዕዝራ የተጻፈ ነው።

30 ቀን እስራኤላዊና ለሙሴ ማልቀሳቸውና በቁጥር 6 ላይ ያለው ቃልም በትክክል

ይህ ቃል በሌላ ዘመን እንደተጨመረ ያስረግጣል። “እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩም ማንም

አላወቀም” ይህ በእርግጥ ሙሴ ከሞተ ከብዙ ዓመታት በኃላ እንደተጻፈ ያስረዳል።

ሊቃውንቶች ሁለቱን የዜና መጽሐፎችን ዕዝራ እንደጻፋቸው ይናገራሉ። ይህም

በ70 የባቢሎን ግዛት የተጠናቀቀ ሲሆን ይህ ጽሁፍ የተጻፈው ሰው በንጉስ ቂሮስ በነበረበት

ዘመን ወይም ከእርሱ በኃላ የነበረ ጻሐፊ እንደሆነ ይታመናል። በዚያን ዘመን የነበረ ታዋቂ

ጸሐፊ ደግሞ ዕዝራ እንደ ነበር ታሪክ ይዘግባል። ሰለዚህ የዜና መጽሐፍ የተጻፈው በዕዝራ ነው

ማለት እንችላለን።

ዕዝራ ቅዱሳን መጽሐፎችን ጠንቅቆ የሚያውቅ ነበር። በዜና መጽሐፉም ላይ በ22

መጽሐፍ ውስጥ ያልገቡትን ሰባት መጽሐፎች ጠቅሶልናል። ይህ ማለት እነርሱን እንደ በአሁን

ዘመን መቀበል አለብን ወይም የለብንም ለማለት አይደለም።

ነገር ግን ዕዝራ ያልጨመረበት የራሱ የሆነ ግንዛቤ አለው ብዮ አምናለሁ።

መጀመሪያው 22 ቁጥርን ጠብቆ ብሉይ ኪዳን እንዲኖር ሲሆን ሌሎቹን ያልጨመረው ደግሞ

እንደ ሪፈራንስ ማጣቀሻ እንደ ሆነ አውቃለሁ። ምክንያቱም ሰላልተጨመሩት መጽሐፎች

ምንም መጥፎ ነገር አልተናገረም። እዲሁም የተናገረውን የሚያጸና ማብራሪያ እንዳለባቸው

አመልክቷል አልፏል።

Page 27: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

26 www.tlcfan.org

ስለዚህ እነርሱን ማንበብ ችግር ያመጣል ብዮ አላምንም። ነገር ግን በተጻፉት በ22

ብሉይ ኪዳን እንዲታዮ እንጂ ከ22 ጋር ገብተው እንዲቆጠሩ ዕዝራ አልፈለገም። ይህን

እግዚአብሔርን ሳይጠይቅ እንዳላደረገ አምናለሁ። ስለዚህ እኛም እንደ ደረስንበት

እግዚአብሔርን ጠይቀን እንመላለስ፦

የነብዮ ናታን መጽሐፍ 1.ዜና.29፥29, 2.ዜና.9፥29

የባለ ራዕዮ ሳሙኤል መጽሐፍ. 1.ዜና.29፥29, 2.ዜና.33፥19

የባለ ራዕዮ ጋድ መጽሐፍ 1.ዜና.29፥29

የሴሎናዊው የአሒያ ትንቢት መጽሐፍ 2.ዜና.9፥29

የባለ ራዕዮ አዶ መጽሐፍ. 2.ዜና.9፥29,12፥29

የነብዮ ሸማያ መጽሐፍ. 2.ዜና.12፥15

የአናኒ ልጅ የኢዮ መጽሐፍ. 2.ዜና.20፥34

እነዚህ የጠፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አይደሉም። በዚያን ዘመን

ከመንፈሳዊነታቸው ታሪካዊነታቸው የታመኑ መጽሐፎች እንደነበሩ ማየት እንችላለን። በዚህ

ዘመንም ብዙ መንፈሳዊ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሊገቡ የማይችሉ መጽሐፎች እንዳሉ

ማለት ነው።

Page 28: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

27 www.tlcfan.org

አዲስ ኪዳን

ጴጥሮስና ያቆብ የክርስቶስ በተራራ ላይ መለወጥ ምስክሮች ነበሩ። ማቴ.17፥1

ጳውሎስና ጴጥሮስ በሮም እስር ላይ በነበሩ ወቅት የአዲስ ኪዳንን መጽሐፍ ቁጥርና የትኞቹ

በአዲስ ኪዳን ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ከዮሐንስ ጋር መመስማማት ወሰኑ። 2.ጴጥ.1፥16-

18 ጳውሎስ ከጴጥሮስ አስቀድሞ በሮም እስር ላይ ነበር። ይህን ከጴጥሮስ ጋር ከሰሩ በኃላ በ62-

63 ኤ.ዲ ላይ ከሁለት ዓመት በኃላ ተፈቷል። ከዛም በእስያ ወደሚገኙት 7ቱ ቤተክርሲያኖች

63-64 ኤ.ዲ ከመምጣቱ በፊት ወደ ስፔንና ቢሪቴን በመሄድ ወንጌል ሰብኳል።

ከዛም በኃላ እንደገና ታስሮ ሰማዕት ወደሚሆንበት ወደ ሮም መጥቷል። ይህ የሆነው

በ64ና በ66 ኤ.ዲ መካከል ነው። ጳውሎስ የተሰቀለው ክርስቲያኖች ሰለ ታላቁ የሮም እሳት

ከተረፉ በኃላ ነው። ይህም በ1.ጴጥ.4፥12 ላይ የእሳት ፈተና ተብሎ ተቀምጧል። ይህ በዚያን

ዘመን ጴጥሮስ ስለሚመጣው የሮም የእሳት ፈተና የተነገረው ትንቢት ወይም ቅዱሳን ሊሆን

የሚገባቸውን ማስጠንቀቂያም ነበር።

ጳውሎስ የታሰረው ከኤፌሶን በ64-65 ባለው ዘመን ውስጥ ነው። ይህ ለጳውሎስ

ስድስተኛው እስሩ ነበር። ይህን ጳውሎስ ራሱ በመጨረሻውና በሰባተኛው በሮም እስሩ ላይ

ገልጾታል። የሮም ክሌመንት ይህን ይናገራል፦

1 Clement 5:5, 6 "(5) By reason of jealousy and strife, Paul by his example pointed out the prize

of patient endurance. After that he had been SEVEN TIMES IN BONDS, had been driven into

exile, had been stoned, had preached in the East and in the West, he won the noble renown

which was the reward of his faith, (6) having taught righteousness unto the whole world and

having reached the farthest bounds of the West [i.e., Britain]; and when he had borne his

testimony before the rulers, so he departed from the world and went unto the holy place,

having been found a notable pattern of patient endurance."

በመጨረሻውም ጳውሎስ ሊሰቀል ባለበት ሰዓት ለጢሞቴዎስ በጻፈው ላይ ለሄኔሲፎሩ

ቤተ ስዎች ምሕረትን ጌታ እንዲስጥ በመለመን ያመሰግናቸዋል። በኤፌሶን ለስድሰተኛ ጊዜ

በታሰረበት ወቅትና በሰባተኛውና በመጨረሻው እስሩ በጳውሎስ እንዳላፈረበትና እንዳገለገለው

ይመሰክራል። 2.ጢሞ.1፥16,18 ጳውሎስ በኤፌሶን እስር በነበረበት ወቅት ቆላስያስን፣

ፊሊጲሲዮስንና ኤፌሶንን ጽፏል።

Page 29: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

28 www.tlcfan.org

አንዳዶች ኤፌሶንን የጻፈው በመጨረሻው በሮም እስር ላይ በነበረበት ወቅት ነው

ብለው ያምናሉ። ዶር ኤርኔስት ማርቲን ኤፌሶን የተፃፈው በኤፌሶን እስር ላይ ሆኖ እንደሆነ

ያምናሉ። (See Restoring the Original Bible, p. 238-240.)

ዶክተር ኢቫን ፔኒ በአዲስ ኪዳን የቁጥር መጽሐፉ ላይ ለኤፌሶን የሚለውን

ኤፌ.1፥1 ላይ ያለውን ያወጣዋል። ወይ የጻፈው ወይ ዶክተር ሲተረጉሙት ኤፌሶን የሚለውን

ዘንግተውታል ማለት ነው። ነገር ግን በ1935 የተሻሻለውን የቁጥር አዲስ ኪዳን ላይ ቁጥር

መሟላትና ጳውሎስ የት ሆኖ መጻፉ ከተጻፈው የበለጠ ነገር የለውም። ለኤፌሶን የሚለውን

ለናንተ የፈለጋችሁትን እንድተወስኑ ትቼዋላሁ ብለዋል።

በእውኑ ጳውሎስ የት ሆኖ መጻፉ ለእኛ መልዕክት የለውምን? የኤፌሶን መጽሐፍ

ለሎዶቂያውያን እንደ ሆነ ይታመናል። ጳውሎስ በኤፌሶን እስር በነበረ ወቅት ቆላስያስን

እንደጻፈ አይተናል። በቆላስያስ ላይ ለሎዶቂያም እንደጻፈ ይናገራል። ይህ ለሎዶቂያ

ጽፌውለሁ ብሎ ጳውሎስ የተናገረው መጽሐፍ የኤፌሶን መጽሐፍ ነው ተብሎ በብዙዋኑ

መርማሪዎች ይታመናል። ቆላ.4፥16

በሌላ መልኩም ጳውሎስ በየቤተክርሲያኑ የተላከው ኮፒ ለእያንዳዱ ቤተክርሲያን

እንዲሄድ ይፈልጋል። ቆላስያስና ሎዶቂያ በጣም የተራራቁ ከተሞች አይደሉም። በኤፌ.3፥1ና

6፥20 ላይ ጳውሎስ ከእስር ለመፈታት እየተጠባበቀ እንደነበር እናያለን። ይህ ጥበቃው

ከቆላስያስ.4፥3,4 ጋር ይመሳሰላል። ይህም ሁለቱ ደብዳቤዎች ከአንድ ቦታ እንደተጻፉ

ያመለክታል። በሮም የጻፈው ግን ጢሞቴዎስን ብቻ ነው። ይህም ሰባተኛውና የመጨረሻው

እስሩ ሲሆን ይህም ስቅለቱን በመጠባበቅ ላይ የነበረበት ጊዜ ነው።

2.ጢሞ.4፥6-8 የጳውሎስ ጥበቃ በኤፌሶን ከነበረው ጥበቃ ፈጽሞ የተለየ ነበር።

ኤፌሶን በሮም ሊጻፍ አይችልም። ምክንያቱም እንዲፈታ እንዲለመንለት ጸሎትን በሮም ሆኖ

አልጠየቀምና ነው። ወንጌልን ለመስበክ መፈታትን እንዲያገኝ ጸሎትን የፈለገው በኤፌሶን

እስር ላይ ባለበት ወቅት ነው። ጳውሎስ ወደ ሮም በመጨረሻው እስሩ በመጣ ወቅት በብዙ

ክርስቲያኖች ዘንድ የተገፋ መሆኑን ለጢሞቴዎስ ገልጾለታል። ይህም የደረሰበት በኤፌሶን ነው

ተብሎ ታመናል። 2.ጢሞ.2፥9 ጳውሎስ በዚያን ወቅት ለቄሳር በመሰዋት በመሰዋት ሕይወቱን

ማትረፍ ይችል ነበር። ነገር ግን ለወንጌል መስፋፋት ሲልና ላመነበት እውነት ጸንቶ በመቆሙ

ሰማዕት ሊሆን በቅቷል።

Page 30: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

29 www.tlcfan.org

በምዕራፍ ሦስት ላይ በመጨረሻው ሰዓት የሚያስጨንቅ ዘመን እንደሚመጣ

አሳታውቆታል። 3፥8, ዘጸ.7፥11 ልክ በሙሴ እንደ ሆነው ጳውሎስም ልክ እንደዛው ስለገጠመው

ይህን ቃል በመጠቀም ሁኔታውን በግልጽ ያስረዳዋል። ይህን የደረሰበትን ተቃውሞ በምዕራፍ

አራት ላይ ይዘረዝረዋል። 4፥9-11 ይህ ደግሞ ጳውሎስ በዚህን ወቅት እንደተተወ ብዙዎች

ነፍሳቸውን ለማዳን ጥለውት እንደሄዱ መመልከት እንችላለን።

ጴጥሮስና ዮሐንስም ስለዚህ ስለ ክርስቲያኖች ወደ ኃላ መመለስ ጽፈዋል ይህም

የጌታ መምጣት መዘግየት ጋር የተያያዘም ነበር። በዚያን ዘመን ያሉ ክርስቶስ ኢየሱስ በ70-

73 ኤ.ዲ ይመለሳል ብለው ጠብቀው ነበር።

በጳውሎስ በመጀመሪያ ጽሁፎች ላይ ይህን የክርስቶስን ቶሎ መመለስ የሚደግፉ

ሃሳቦችን እንመለከታለን። ነገር ግን በኃላ ለጳውሎስም ሆነ ለጴጥሮስ የክርስቶስ መምጣት ቶሎ

እንደማይሆን ተገልጦላቸዋል። ጴጥሮስ አንድ ቀን እንደ አንድ ሺ ዓመት ነው በማለት

አስረድቷል። 2.ጴጥ.3፥3-8 ጴጥሮስ በመቀጠልም የኢየሱስ ዳግም መምጣት እንደ ኖህ ውሃና

እንደ ሌባ እንደ ሆነ ያስረዳል። 3፥5-7,10 ይህም የሚያሳየው ከመምጣቱ በፊት ጥፋትና

መፍረስ እንደሚሆን ነው።

ዮሐንስም ብዙዎች አሳቹ ክርስቶስ እንደሆኑ ተገልጿል በማለት የጴጥሮስን ቃል

ያጸናል። ደግሞ መጀመሪያ አማኞች እንደነበሩ ይናገራል። ነገር ግን ከእነርሱ በመለየት ወደ

አይሁድነት እንደተመለሱ ይመሰክራል። ይህም ከሮም ጋር እንዲመሳጠሩ አድጓቸዋል።

1.ዮሐ.2፥18-23 እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ አልነበረም ብለው እንደ አይሁዶች ይክዳሉና ነው።

ይህ ደግሞ ለሮም ካቶሊክ ቤተክርሲያን ታላቅ ሃይማኖታዊ ፖለቲካዋን እንድታስፋፋ

አድርጓታል።

ጴጥሮስ ደግሞ በመጨመር ብዙዎች እንደ በለዓም አይነት ሃሰተኛ ነብያትን

ተከትለዋል ብሎ ይናገራል። 2.ጴጥ.2፥15 አንዳዶቹን ነብያት ሲነቅፍ እንዲህ ይላል፦ ራሳቸው

በእስራት ታስረው ሌሎችን ነጻ እናወጣለን ይላሉ ብሏል። 2፥19,22 ውሻ ወደ ትፋቱ

እንደሚመለስ ወደ ቆሻሻና አስጸያፊ ወደ ሆነ ነገር እንደተመለሱ ያስረዳል። ይህም እነዚህ

ሰዎች ሌላ መልካም የሆነ ነገር ተምረውና አምነው እንደ ነበርና በኃላ ግን ተመልሰው ወደ

ድሮው መንገድ ሃሳብ፣ ኑሮና ሃይማኖት እንደተመለሱ ያሳያል።

Page 31: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

30 www.tlcfan.org

ጴጥሮስ ይህን ሁሉ የጻፈው 66 ኤ.ዲ ከመሞቱ አስቀድሞ ነው በ66 ኤ.ዴ አይሁዶች

በፍልስጤም ላይ ያመጹበት ዘመን ነው። ይህም በኢየሩሳሌም መፍረስ በ70 ኤ.ዲ ተጠናቋል።

ብዙ የአይሁድ አማኝ የነበሩ ክርስቲያኖችም ለሮም ከመገዛት ይልቅ አብረው አምጸው ነበር።

ይህም ኤርሚያስም ሆነ ኢየሱስ የተነበዮት ትንቢት ተፈጻሚ እንዲሆን አድርጎታል።

በ64 ኤ.ዲ የኢየሩሳሌም መቅደስ ፈጽሞ ታድሶ ነበር። ይህም ሥራ ከክርስቶስ ሞት

በፊት ከ20 ዓመት በፊት በሄሮድስ መታደስ የጀመረው ነው። ጆሲፈስ የሚባለው ካህን አይሁድ

የታሪክ ጸሐፊ ሁሉን በዝርዝር ያስቀምጠዋል። Antiquities of the Jews, XX, ix, 7, "And now it

was that the temple was finished." ይህም በዚያን ወቅት መሆኑ ሁሉ በመታደሱ ኢየሱስ

ይመጣል ብለው ጠብቀው ነበር። ይህም ሃሳብ እስካሁን አለ። አሁንም መቅደሱ ታድሶ ሲያልቅ

ይመጣል ብለው ክርስቲያኖች ሳይቀሩ ያምናሉ። ይህ ዕብደት ነው።

ይህም ለሕዝብ የውሸት ተስፋ መስጠት እንጂ ከእውነት ጋር ምንም የተያያዘ ነገር

መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም። ያኔ መቅደሱን በመጨረሳቸው ኢየሱስ ጀነራል ሆኖ በመምጣት

ከሮማ ነጻ እንዲያወጣቸው ጠበቁ። ዛሬም በዓለም ላይ ያሉ የተላያዮ ሃይማኖቶች ከዚህ ያልተለየ

እምነት ይዘው መመልከት የጎላ ሆኗል። አልፎ ተርፎ ታላላቅ የጌታ ጸጋ ያለባቸው ባሪያዎች

ለኢየሩሳሌም መቅደስ መታደስ መዋጮን ከምዕመናን ሲያሰባስቡ ማየት የተለመደ ሆኗል።

በእውኑ ኢየሱስ የሚመጣው ፍጥረታዊ መቅደስ ወይስ መንፈሳዊው መቅደስ ተዘጋጅቶ ሲያበቃ

ነውን?

በዚያን ወቅት ነጻነትን አውጀው ለአመጽ ያነሳሱ ነብያት ሁሉ ሕዝቡን ለጥፋት

ዳረጉት። ብዙዎችም ለባርነትና ለግዞት ተሸጡ። ነብያቶቹ የኢየሱስን ትንቢት የሚቃረን ነገር

ይዘው እንደወጡ አሰተውለው የነበሩ ደቀመዛሙርቱን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ነበሩ። በኢየሱስ

ትንቢት መሰረት ከጥፋት በፊት ያመለጡም ደግሞ ብዙዎች ነበሩ። ማቴ.24 በመጨረሻው ግን

ከነብያቶቹ ውሽት ይልቅ የኢየሱስ ትንቢትና ቃል ትክክል እንደነበረ ተረጋገጠ። ነብያቶቹ

ሕዝቡን ከምንም አላዳኗቸውም እነርሱም ሳይቀር ከሕዝቡ ጋር ባሪያ ሆኑ።

ጳውሎስ እንደዚህ አይነት ነገር በክርስቲያኖች ዘንድ እንዳይደገም ይህን ጻፈልን።

2.ተሰ.2፥3-4 ጳውሎስ በዚያ መቅደስ ቢመጣም የሚመጣው የጥፋት ልጅ እንደሆነ ተናገረ።

ዮሐ.17፥12 ይህም አሳች ክርስቶስ ነው። ይህም የአይሁዶች የተሳሳተ ጥበቃ የሚያመጣው

የሚፈጥረው ሰው ነው።

Page 32: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

31 www.tlcfan.org

ይሁዳ የሚያመለክተው ክርስቲያን የነበረውን ክርስቶስን አሳልፎ የሸጠውን

ወሸተኛውን መሲ መጠበቅ የሚደግፈውን ሰው ማንነት ነው። ይህ ታሪክ በዚህ ዘመን ራሱን

ደግሟል። አይሁድ ሆኑ ክርስቲያን ሳያውቁት ትንቢቱ የሚደግምባቸው ሃያሌዎች ናቸው።

የአሁዶች አመጽ የጀመረው ልክ እንደ ጳውሎስና ጴጥሮስ አገልግሎት ሲሆን ያለቀውም

በእልቂት ነው።

የተላያዮ ሰዎች በሃሳባቸው የፈጠሩትን መሲ እንዲጠባበቁ እንዲሁ በደመ ነፍስ

አስከትለዋቸው ለእልቂት አብቅተዋቸዋል። ይህ ሁሉ ከመሆኑ የተነሳ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ

ቅዱስ መጠንና አቀማመጥ በውስጡ ሊይዛቸው የሚገባ መጽሐፎች መወሰን ነበረበት።

በሐዋርያትም ይህ ተወስኖ አሁን ያለበትን ቁጥር ይዟል። ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው

ሁለተኛ ደብዳቤውን እንዲህ በማለት ይዘጋዋል፦ 9-21

“9 በቶሎ ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ 10 ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ

ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ

ድልማጥያ ሄደዋል፤ 11 ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ። ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ

ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው። 12 ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን

ላክሁት። 3 ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና

መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ። 14 የናስ አንጥረኛው

እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል። 15 አንተም

ደግሞ ከእርሱ ተጠበቅ፥ የምንናገረውን እጅግ ተቃውሞአልና። 16 በፊተኛው

ሙግቴ አንድ ስንኳ አልደረሰልኝም፥ ሁሉም ተዉኝ እንጂ፤ ይህንም

አይቍጠርባቸው፤ 17 ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ

እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ። 18

ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤

ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። 19 ለጵርስቅላና ለአቂላ

ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ። 20 ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፥

ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውሁት። 21 ከክረምት በፊት እንድትመጣ

ትጋ። ኤውግሎስና ጱዴስ ሊኖስም ቅላውዲያም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ

ያቀርቡልሃል። 22 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ

ጋር ይሁን፤ አሜን።”

Page 33: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

32 www.tlcfan.org

ጳውሎስ ማርቆስና ጢሞቴዎስ የመጀመሪያውን ቅጂ መጽሐፍ ይዘውለት እንዲመጡ

ይናገራል። በርኖሱ ሊለብሰው ሳይሆን መጽሐፍቱን ለመሸፈኛና ለመደበቂያ ይጠቀምሙበት

የነበረ የመጽሐፍ ሽፋን ስለነበር ነው። ይህም መጽሐፍ በተለያየ ሁኔታ እንዳይበላሽ ለመጠበቅ

ጭምር ነው።

Dr. Martin quotes Vincent's Word Studies in the New Testament, "Phelonen was a wrapper of

parchments, and was translated figuratively in Latin by toga or paenula, 'a cloak', sometimes of

leather." (See p. 385)

ጳውሎስ መጽሐፍቱ ወደ እርሱ እንዲመጡ የፈለገው ከመሞቱ በፊት የመጨረሻውን

እርማት ሊያደርግለትና በቅደም ተከተል ሊያስቀምጣቸው እንደ ሆነ ይታመናል። ይህንን

ስራውን ከጴጥሮስ ጋር እንደሰሩትም ይታመናል። ጴጥሮስ በተራራው ላይ ከክርስቶስ ጋር

ከነበሩት ሐዋርያት አንዱ ነው። ከዚያም ከተጠናቀቀ በኃላ በጢሞቴዎስና በማርቆስ ወደ ኤፌሶን

ወደ ዮሐንስ እንደተላከ ይታመናል። ከዚያም ዮሐንስ የአዲስ ኪዳንን ቅደም ተከተል መልክ

የመጨረሻውን ጹፉን ራዕይን በማስቀመጥ ጠቅልሎታል። ይህንን በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን

አጠናቆታል።

ለብዙ ጊዜያት የቤተክርሲያን ሽማግሌዎችና አዋቂዎች አዲስ ኪዳንን ቅደም ተከተል

ያስተካከሉ አድረጌ አምን ነበር። ታሪክን በመርመሬ ግን እውነቱን አውቄ በጣም ስለ ተደነኩና

ስለተባረኩ ለአንባቢዎች ከማስረጃው ጋር ለማስቀመጥ ወስኛለሁ። ጳውሎስና ጴጥሮስ በሮም

እስር ቤት የሰሩት ታላቅ መንፈሳዊ ስራ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚጠቃለለውንና

የማይጠቃለለውን መጽሐፍ ለመለየትና ጽሁፋቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ለማረም ነው።

ዕዝራም ብሉይ ኪዳንን ሲያሰባስብ በዘመኑ ብዙ መጽሃፎች እንደነበሩ ራሱ

ተናግሯል። ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አላካተታቸውም። ጳውሎስና ጴጥሮስም

ተመሳሳይ ነገር እንደገጠማቸው መገመት እንችላለን። የቀሩት ያልተጠቃለሉት መጽሐፎች

በሮማውያን እጅ ገብተዋል የሚባልም እምነት አለ። የሮም ካቶሊክ ቤተክርሲያንም ይህን ሃሳብ

ከመደገፏ ባሻገር ብዙዎቹን መጽሐፎን ትጠቀማቸዋለች ተብሎ ይታመናል። ቃል ሁሉ ግን

በእግዚአብሔር ቃል ምስክር መቆሙ ወሳኝ ነበር። በእግዚአብሔር ባሪያዎችና በቀደመው ቃሉ

በምስክሮች የጸኑትን ለአዲስ ኪዳንም ሆነ ለብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ለመሆን

አብቅተዋቸዋል።

Page 34: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

33 www.tlcfan.org

አዲስ ኪዳን ወንጌሎች በመጀመሪያ የተጻፉት በጥንቱ አርማይክ ሲጻፍ የቀሩት

ደግሞ በግሪክ እንደተጻፉ ይታመናል። ማንኛውም ከእነዚህ ውጪ የተረጎሙት በቃላት

እጥረትና ተመሳሳይ ቃል በሚተረጎምበት ቃል ስለማይገኝ ትርጉሙ ትክክለኛ ሃሳብን በአንዳንድ

ስፍራ ላይ አይሰጥም። ይህም ለተለያዮ ሃይማኖት መፈጠር ወይም የቃል ስሕተት ውስጥ የሰው

ልጆችን ጥሏን። ስለዚህ ቃሉን ስናጠና በተቻለን መጠን በዋና ቅጂ ዲክሽነሪ መዝገበ ቃላት

በመያዝ እንድናጠና አበረታታለሁ። የሚደንቀውና ሳልጠቁም ለማለፍ የማልፈልገው ነገር

ቢኖር አማርኛችን ከብዙ ካጠናኋቸው ትርጉሞች ወደ ዋናው ቅጂ ያደላ መሆኑን እመሰክራለሁ።

Page 35: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

34 www.tlcfan.org

ሐዋርያትና አዲስ ኪዳን

ለሐዋርያት መጽሐፎቹን መምረጡ ብቻ ሳይሆን መጽሐፎቹን ቅደም ተከተል

ማስያዙ ሌላው ዋነኛ ሥራ ነበር። እንዲህ ብለው እንዳስቀመጧቸው የነገራል፦

ሀ. መሰረታዊ የሕጻናት ትምህርት፦

ሮሜ

1.ቆሮንጦስ

2ቆሮንጦስ

ገላትያ

1.ቆሮ.3፥1,2, 2.ቆሮ.6፥13, ገላ.3፥24-29, 4፥1-10

ለ. ትዕዛዝና እርማት ለጎልማሳ ልጅ፦

ኤፌሶን

ፊሊጲሲዮስ

ቆላስያስ

ኤፌ.4፥12-14

ሐ. ለበሰለ ልጅ አጥንትና ሥጋ፦

1.ተሰሎንቄ

2.ተሰሎንቄ

ዕብራውያን

1.ቆሮ.13፥13 የፍቅር ምዕራፍ በመባል ይታወቃል። ነገር ግን ሦስት የከበሩ ነገሮች

እንዳሉና የመጨረሻው ግን ፍቅር እንደሆነ ይናገራል። የመጀመሪያው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ

ይህን መልክ የያዘ ነበር።

Page 36: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

35 www.tlcfan.org

ያቆብ ፦ እምነት ላይ ያተኮረና በሥራ እንዴት ውጤቱ እንደሚታይ ያሳያል።

ያቆብ.2፥17 ያቆብ እምነትን 19 ጊዜ ይጠቀመዋል። ከዚህም የተነሳ የእምነት

ቁጥር 19 ተብሎ ተሰይሟል።

ጴጥሮስ፦ በተሰፋ የሆነን መከራ ያስተምራል (1.ጴጥ.1፥3,13,21, 3፥15)

ዮሐንስ፦ ሰለ ወንድማማች መዋደደ ያተኩራል። ሁሉን መጽሐፍ በደንብ

አድርገን ስናጠና ይህን እንረዳለን።

ጳውሎስ፦ የእምነት መሰረት የሆኑትን ክርስቶስም ቀድሞ የሚናገራቸውን

መሰረታዊ ትምህርቶች አስተምሯል። ዕብ.6፥1-2

ንስሃ

እምነት

ጥምቀቶች

እጆችን መጫን

የሙታን ትንሳኤ

የዘመናት ፍርድ

ብስለት (ይህም የመጨረሻው የመሰረቱ መደምደሚያ ነው)

የጳውሎስን መልዕክቶች ጠጋ ብለን ብንመለከት በሮሜ ለብሪትሽ ሮያል ቤተሰብ

በጦርንርት እስር ላይ በሮም ለነበሩ በተጻፈው የሮሜ መልዕክቱ ላይ ይህን ትምህርቱን

እናገኛለን።

ንስሃ. ሮሜ.2፥4

እምነት. ሮሜ. 3 – 4

ጥምቀት. ሮሜ.6

እጆችን መጫን(ጥሪ) ሮሜ.9 – 11

ሙታን ትንሳኤ. ሮሜ.12፥2

የዘመን ፍርድ. ሮሜ.14፦9-13

ብስለት. ሮሜ.15፥14-16

Page 37: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

36 www.tlcfan.org

አንደኛና ሁለተኛ ቆሮንጦስና በገላትያ መሰረታዊ የሕጻናት ትምህርትን የያዙ ሲሆኑ

ከዓለም ለመጡ ለአዲስ ክርስቲያን በእምነት ስር እንዲሰዱ ለማድረግ የተጻፉ ናቸው። ገላትያ

በመጀመሪያ የተጻፈው አይሁዳዊ ክርስቲያን ለሆኑ ገና ኢየሱስ የሃጢያታቸው መስዋዕት

እንደሆነ በደንብ ላልገባቸው እውነቱን በእርግጥ ለማስያዝ የተጻፈ ነው። በዚያን ወቅት ይህ

ሲጻፍላቸው አዲስ ኪዳን ምን እንደ ሆነ የጠለቀ መረዳት የላቸውም ነበር። ከዚህም የተነሳ

ኢየሱስን የአሮጌው ኪዳን ራስ አድርገው ያስቡ ነበር።

ገላትያ ጽድቅ በሕግ ወይም በሕግ በሆነ ቃል ኪዳን እንጠብቃለን፣ እናደርጋለን፣

እንገዛልን፣ እንቀበላለን በማለት እንደማይመጣ ለማስረዳት የተጻፈ ነው። ዘጸ.19፥8 ሁሉ

ጠፍተዋል ሁሉ ሃጢያትን ሰርተዋል። ገላትያ መጽሐፍ አንዳዶች እንደሚሉት ሕጉን አልሻረም

ወይም አያናንቅም። ነገር ግን ሕጉን የታቀደበትን ሥፍራ ይሰጣል። ሕጉ ጽድቅና ቅድስና

ምን መሆኑና ለማስረዳት የተሰጠ ነው። ነገር ግን ይህን ጽድቅ ሆነ ቅድስና እንድንይዝ

ለማድረግ ምንም ብቃት አይሰጠንም። ምክንያቱም ሕጉን ለመፈጸም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ

በእኛ ውስጥ በቀዳሚነት ሊኖር አስፈላጊ ነው።

ይህም በየ እድገት መጠናችን በመጠን በመጠን እየተመጠነ የሚሰጠን ነው። በፋሲካ

በበዓለ አምሳና በዳስ በዓል ነው። ሕጉን በሙላት የምንጠብቅበትን መንፈስ ለመቀበል የመንፈስን

ሙላት ወደ የዳስ በዓል ደርሰን መሞላትን ይጠይቃል።

እያንዳንዱ የጳውሎስ መጽሐፍት ልዮ ናቸው። በሁሉ መጽሐፉ ላይ በዕብራውያንና

በሮሜ እንዳየነው 7ቱን መሰረታዊ ትምሕርቶች አይደጋግምም። በሁለተኛው የጽሁፍ ክፍሉ

በብስለት መንገድ ላይ ያሉትን ያዛል ያርማል። ለዚህ ቁልፍ የሆነው ጥቅስ በኤፌ.4፥12-14

የሚገኘው ነው።

በጨረሻውም የጽሁፍ ክፍሉ የክርስቶስን ሁለተኛ መምጣት ይተነብያል። ይህም

አጥንትና ሥጋ የበሰሉ አማኞች መብል በመባል ይታወቃል። ራዕይንም መጨረሻ ያደረጉበት

ምክንያትም ይሄ ነው። የበሰለ መሰረታዊ ትምህርት ያለው ሰው በመጨረሻ ሁሉን በመጨረስ

ወደዚያ እውቀት እና እምነት እንዲደርስ ለማድረግ ነው ተብሎ ይታመናል። እኔም ይህን

እምነት እደግፋለሁ።

Page 38: መጽሐፍ ቅዱስ - T.L.C.F.A.N. Holy Bible.pdf · መጽሐፍ 2015ቅዱስ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ለመጻፍ በጥቅሉ1,600 ዓመታትን ፈጅቷል። ይህም

መጽሐፍ ቅዱስ 2015

37 www.tlcfan.org

በሐዋርያት ዘመን አንድ አማኝ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ እንደ እምነቱ ደረጃ

ቅደም ተከተል በመከተል እንጂ እንደ አሁኑ ዘመን እንደ ፈለጉ ማንበብ ወይም መሰበክ ፈጽሞ

የለም ነበር። ይህ በኢየሱስ አገልግሎትም የታየ እውነት ነው።

የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ አደረደርና አመዳደብ ትክክለኛ የክርስቲያንን ዕድገት ደረጃ

የጠበቀ እንዲሆን የሚያደርግ ነው። ይህም በትክክል ሲጠና ነው። ይህ በጴጥሮስና በጳውሎስ

ብሎም በዮሐንስ ታቅዶ የተደረገ መሆኑን ለማመን የሚያዳግት አይደለም። በዚያ ሰላልነበርን

እውነት ነው ብለን መከራከር አንችልም። ከክርክር ይርቅ ዘንድ ደግሞ ለሰው ክብሩ ነው።

ነገር ግን እውነትን ተመልክተን እናምናለን። ያየነውን እንመሰክራለን።

ከላይ ካለው መረጃ በመነሳት መጽሐፍ ቅዱስ 66 ወይም 81 እንዳልሆነ እንረዳለን።

በትክክለኛ ትርጉሙ እንዳየነው 49 ሆነው የተሰበሰቡት ትክክል ናቸው። ነገር ግን ምንም

እንኳን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይገቡም ሊነበቡ የሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱስም

የሚያጣቅሳቸው ሌሎች መጽሐፎች እንዳሉ አምናለሁ። ለምሳሌ ያህልም የጃሻር መጽሐፍ

የሄኖክ መጽሐፍ ይገኙባቸዋል። የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነው። ቃሉን ማጥናት ደግሞ ይህን

የእግዚአብሔርን የእውነት ክብር እንድንካፈል ይረዳናል።

ጴጥሮስ በ2.ጴጥ.1፥15 የተናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንቶች ሰለ አዲስ ኪዳን

መጽሐፎች ቅደም ተከተልና ዝርዝር ነው ብለው ያምናሉ። ይህን ሁሉ ዋጋ በመክፈል ቃሉን

ስላደረሱልን ደስ ሊለንና በሁሉ ነገር ፍለጋቸውን ልንከተል ይገባናል ብዮ አምናለሁ። እውነቱ

የበራለት ሰዎች ደግም ይህን እውነት ላልሰማው እናድርስ። እኔም እውነቱን እመሰክራለሁ።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብኖር በቀሪው ዘመኔ በዕብራይስጥና ግሪኩ ቀጥተኛ ትርጉም በድሮው

መጽሐፍ ቅዱስ አደያደርና ቁጥር 49ኙን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፎች በአማርኛ ለማዘጋጀት

ፈልጋለሁ። በዚህ በጸሎት ደግፉኝ።

ይህ ለጠየቃችሁት ጥያቄ ለመመልስ የተዛገጀ መጽሐፍ ነው። ብዙዎች መልሳችሁ እንደተመለሰ

እገምታለሁ። ያለነሳሁት ሃሳብ ካለና ጥያቄ መጠየቅ ከለጋችሁ በፌስ ቡክ ገጽ ወይም ሜሴጅ

ማድረግ ይችላሉ። የጌታ ሰላምና ጸጋ ይብዛሎት።የጌታ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። ማራናታ

……………………………ተፈጸም………………………………