Top Banner
addismaleda.com Nurturing Like the River ከመሪው የግል ባንክ ጋር አብረው ይስሩ! ቅጽ 2 ቁጥር 100 መስከረም 23 2013 10 ብር 0114 655 656 / 0111 263 434 www.unicportal.com.et እራሳችንን እና ማህበረሰባችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!! እርቀታችንን እንጠብቅ እጃችንን እንታጠብ ለአነስተኛ የዳቦ ጋጋሪዎች ዱቄት ማቅረብ ቆመ 800 ብር ይሸጥ የነበረው ዱቄት 2650 ብር እየተሸጠ ነው በረድኤት ገበየሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ ኩንታል የዳቦ ዱቄት በ 800 ብር ሲያቀርብላቸው የነበረው ሂደት ባልታወቀ ምክንያት እንዳቋረጠባቸው ዳቦ ጋጋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡ አንድ ኩንታል ዱቄት በ 800 ብር ማቅረብ በመቆሙም ምክንት ዳቦ ጋጋሪዎቹም ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸውን እና አሁን በሶስት እጥፍ አድጎ አንዱን ኩንታል በ2 ሺህ 650 ብር በኩንታል ከፋብሪካዎች እየገዙ እየተጠቀሙ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የዳቦ ቤቶች ባለንብረቶች እንደሚሉት፣ መንግሥት የሚያቀርብላቸው የዳቦ ዱቄት ዋጋ በአንድ ኩንታል በ 800 ብር ሲሆን፣ ገፅ 22 ኤጀንሲው በ1.6 ቢሊዮን ብር ባለ 26 ወለል ህንፃ ሊገነባ ነው ወደ ገፅ 22 ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› መርሻ ጥሩነህ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ደረጃ ወደ ሪጅዎፖሊታንት ለማሳደግ ጥናት አድርጎ ለአማራ ክልል ማቅቡን አስታወቀ፡፡ የከተማዋን የመዋቅር እድገት ለማሳደግ የደብረ ብርሃን ከተማ ነባራዊ ሁኔታን በከተማ አስተዳደሩ የተቋቋመ ኮሚቴ ጥናት አድርጎ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡ ደብረ ብርሃን አሁን ከምትገኝበት ፈርጅ አንድ የከተማ አስተዳደር ደረጃ ወደ ሪጅዎፖሊታንት የደብረ ብርሃን ከተማን ወደ ‹ሪጅዎፖሊታንት› ለማሳደግ ጥናት ቀረበ ፎቶ ሳሙኤል ሀብተአብ
24

‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

Mar 22, 2023

Download

Documents

Khang Minh
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

addismaleda.com

Nurturing Like the River

ከመሪው የግል ባንክ ጋር አብረው ይስሩ!

ቅጽ 2 ቁጥር 100 መስከረም 23 2013 10ብር 0114 655 656 / 0111 263 434

www.unicportal.com.et

እራሳችንን እና ማህበረሰባችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!!

እርቀታችንን እንጠብቅ

እጃችንን እንታጠብ

ለአነስተኛየዳቦጋጋሪዎችዱቄትማቅረብቆመ

800 ብር ይሸጥ የነበረው ዱቄት 2650 ብር እየተሸጠ ነው

በረድኤት ገበየሁ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ ኩንታል የዳቦ ዱቄት በ 800 ብር ሲያቀርብላቸው የነበረው ሂደት ባልታወቀ ምክንያት እንዳቋረጠባቸው ዳቦ ጋጋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡

አንድ ኩንታል ዱቄት በ 800 ብር ማቅረብ በመቆሙም ምክንት ዳቦ ጋጋሪዎቹም ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸውን እና አሁን በሶስት እጥፍ አድጎ አንዱን ኩንታል በ2 ሺህ 650 ብር በኩንታል ከፋብሪካዎች እየገዙ እየተጠቀሙ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የዳቦ ቤቶች ባለንብረቶች እንደሚሉት፣ መንግሥት የሚያቀርብላቸው የዳቦ ዱቄት ዋጋ በአንድ ኩንታል በ 800 ብር ሲሆን፣

ገፅ 22

ኤጀንሲውበ1.6ቢሊዮንብርባለ26ወለልህንፃሊገነባነው

ወደ ገፅ 22

‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር››

መርሻ ጥሩነህ

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ደረጃ ወደ ሪጅዎፖሊታንት ለማሳደግ ጥናት አድርጎ ለአማራ ክልል ማቅቡን አስታወቀ፡፡

የከተማዋን የመዋቅር እድገት ለማሳደግ የደብረ ብርሃን ከተማ ነባራዊ ሁኔታን በከተማ አስተዳደሩ የተቋቋመ ኮሚቴ ጥናት አድርጎ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ደብረ ብርሃን አሁን ከምትገኝበት ፈርጅ አንድ የከተማ አስተዳደር ደረጃ ወደ ሪጅዎፖሊታንት

የደብረብርሃንከተማንወደ

‹ሪጅዎፖሊታንት›ለማሳደግጥናትቀረበ

ፎቶ

ሳሙ

ኤል

ሀብ

ተአ

Page 2: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 2

ኦፕሬሽንስ ማኔጀር

ታምራት አስታጥቄ

መራሔ አሰናጅተወዳጅ ስንታየሁ

ዋና አዘጋጅ

ኤርሚያስ ሙሉጌታ

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 10

የቤት ቁጥር አዲስ

ምክትል ዋና አዘጋጅ

ሊድያ ተስፋዬ

ረዳት አዘጋጅዳዊት አስታጥቄ

ዘጋቢረድኤት ገበየሁ

መርሻ ጥሩነህ

እዮብ ውብነህ

ማኅበራዊ ሚድያ አዘጋጅ

እየሩስ ተስፋዬ

ምስልና ገጽ ቅንብር

አሸናፊ ፀጋዬ

እዮብ ተፈራ

ቋሚ አምደኞችቤተልሔም ነጋሽ

በፍቃዱ ኃይሉ

ፎቶግራፈርሳሙኤል ሀብተአብ

አሸናፊ ፀጋዬ

ድረገጽብዙአየሁ ተከስተ

የሽያጭና ግብይት ሥራ አስኪያጅሙሉጌታ ተሰማ

የደንበኞች አገልግሎትተፈስሂ ጌትዬ

ህትመት ክትትልዮናስ ሸንቁጥ

ስርጭት

ሄኖክ እንግዳወርቅ

ናኦል ለገሰ

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 228

ጆሞ ኬኒያታ መንግድ

ከእስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ባንቢስ ሱፐርማርኬት

በሚወስደው መንገድ ከመካነ ኢየሱስ ሕንፃ ጎን ፀሐይ መሳይ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ

የዝግጅት ክፍሉ ስልክ፡ 0911253767

ኢ-ሜል፡ [email protected]

መካነ ድር፡ www.addismaleda.com

ፌስቡክ፡ facebook.com/addismaleda

የሽያጭ ክፍል፡ +251961414141

አታሚ

ማስተር ማተሚያ ቤት

አዲስ ማለዳ በቻምፒየን ኮሚኒኬሽንስ አሳታሚነት ለአንባቢያን የምትደርስ ሳምንታዊ የቅ\ዳሜ ጋዜጣ ስትሆን በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የምዝገባ ፈቃድ ቁጥር 441/210 ተመዝግባለች።ቻምፒየን ኮሚኒኬሽንስ በንግድ ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባ ቁጥር MT/AA/2/0011632/2004 እና በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መዝገብ ቁጥር 14/670/9329/2005 የተመዘገበ የንግድ ተቋም ነው።

ርዕሰ አንቀፅ

የአዲስማለዳየአንድመቶሳምንታትጉዞ!

ማስታወቂያ

የዛሬዋ አዲስ ማለዳ ለአንድ መቶኛ ዕትም መድረስ ያን ያክል ባያኩራራም ያስደስታል! ደስታው ለምን ቢሉ ያለማቋረጥ እዚህ መድረስ በቀላሉ አይቻልምና ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አብረዋት፣ ወይም ቀደም ብለው አሊያም ዘግየት ብለው የጀመሩ ጋዜጦች በሚያሳዝን መልኩ መንገድ ላይ መቅረታቸውም ተጠቃሽ ነው። ላለመኩራራት ደግሞ በአገራችን በግል ዘርፍ ከኹለት ዐሥርታት በላይ የቆዩ ጋዜጦች በመኖራቸው ነው።

የሆነው ሆኖ አዲስ ማለዳ ከየት ወዴት የሚለውን በዚህ ርዕሰ አንቀጽ ላይ ለመጻፍ መነሳታችን የኋላ ከሌለ የለም የፊቱ የሚለው መርኅ መሰረት አደርገን ጋዜጣዋ የመጣችበትን መንገድ ዓይታ የጎደላትን ለመሙላት ይረዳታል ከሚል እሳቤ መሆኑ ይሰመርበት።

ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባት መሰረት ነው። የኅትመት መገናኛ ብዙኀን ደግሞ ይህንን ዕሴት ዕውን ለማድረግ እና ዜጎች በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚጠብቃቸውን የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ አማራጭ መድረክ ናቸው። በመረጃ ያልበለጸገ ማኅበረሰብ መንግሥትን ተጠያቂ የማድረቅ አቅሙ ውስን ነው። የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ሊዳብር የሚችለውም የሐሳብ ሙግትና ምክንያታዊነት እየጎለበተና ባህል እየሆነ ሲመጣ ነው። እነዚህን ዐቢይ ተልዕኮዎች ለማሳካት ከግለሰብ፣ ከቡድንና መንግሥት ተጽዕኖ የተላቀቁና በስርዓት የተደራጁ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት ያስፈልጋል።

የመገናኛ ብዙኀን ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። አንዳንዶች እንዲያውም ዘርፉ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ከጀርባ አጥትነት ሚና ጋር ያመሳስሉታል።

አዲስ ማለዳ ዜጎች ማወቅ የሚገባቸውን ወቅታዊ መረጃዎች ታደርሳለች፤ ትምህርት አዘል ሥልጡን የውይይት መድረክ በመፍጠር የሠለጠነ ማኅበረ-ለፖለቲካዊ ተዋስዖ ከነውስንነቱ እንዲዳብር የበኩሏን ተወጥታለች፤ እየተወጣችም ትገኛለች። በተጨማሪም የምርመራ ጋዜጠኝነትን በመተግበር የአገር ሀብት እንዳይባክን፣ የተደራጀ ወንጀል እንዳይስፋፋና በሥልጣን መባለግና ያለአግባብ መጠቀምን በማጋለጥ ዴሞክራሲያዊነት እንዲያብብ፣ የመብት ተጠያቂነት እንዲጎለብት ብሎም ኀላፊነትና ተጠያቂነት በግለሰብ፣ በማኅበረሰብ እና በመንግሥት ደረጃ እንዲዳብር በመጠኑም ቢሆን የበኩሏን ሚና እየተወጣች ትገኛለች። አዲስ ማለዳ በዚህ ረገድ ከሠራቻቸው ጥቂት ማሳያ አብነቶችን ወረድ ብለን እንጠቅሳለን።

አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገለልተኛና ነፃ መድረክ ነች። ታማኝነታችን እና ወገንተኝነታችን ለሙያችን፣ ለእሴቶችን እና ለዲሞክራሲያዊ መርሆቻችን መሆኑን በተግባር እስካሁን አስመስክረናል ብለን በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን።

በርዕይዋ በኢትዮጵያ የአራተኛነት መንግሥት ሚናዋና ለመውጣት እና ዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ነጻ፣ ገለልጸኛና ተዓማኒ መገናኛ ብዙኀን መሆንን የሰነቀችው አዲስ ማለዳ፣ በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆኑንን ዓላማ አድርጋ እየሠራች ብትገኝም የምኞቷን ያክል አሳክታለች የሚል ቅዠት ግን የላትም፤ ገና ብዙ ይቀራታልና።

አዲስ ማለዳ ዕሴቶቼ ናቸው ብላ ያነገበቻቸውን ሐቀኝነት፣ ምክንያታዊነት፣ ብዝኀነት፣ ስልጡንነት፣ ጨዋነት እና ሙያተኝነት ጋር የማይፃረሩ ሐሳቦችን እና አስተያየቶችን ሁሉ እያስተናገደች ከርማለች፤ ወደፊትም ታስተናግዳለች። ከዚህ ባሻገር ዝርዝር ዓላማዬ ብላ የለየቻቸው ለተደራሲያን ወቅታዊ መረጃዎችን ማቅረብ፣ ትምህርት አዘል ሥልጡን ውይይት ማስተናገድ፤ ዴሞክራሲያዊነት እንዲያብብ፣ የመብት ጠያቂነት እንዲጎለብት እንዲሁም ዜጎች፣ በተለይም ደግሞ ድምጽ አልባ ለሆኑት ልሳን መሆንን ያካትታል። እነዚህን ዓላማዎችን እያሳካች መሆን አለመሆኑን መፍረድ የተደራሲያንም ቢሆን፣ ለማታወስ ያክል አንዳንዶቹን በመጠቃቀስ ለአንባብያን እናስታውሳል።

በአንድ መቶ ሳምንታት ቀይታዋ፥ አዲስ ማለዳ ብዙ ዘገባዎችን ያስተናገደች ሲሆን አንዳንዶቹ ዘገባዎች ወይም ጽሑፎች ተደራሲያኖቿን እንዲሁም የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ትኩረት እንዲሁም ሌሎች መደበኛ መገናኛ ብዙኀንን የሳቡ፣ ያወያዩ ጉዳዮች ሆነው አልፈዋል። ይህም አዲስ ማለዳን ለማስተወወቅ የራሱን አስተዋጽዖ አድርጓል።

አዲስ ማለዳ በተለይ በብዙዎች ዘንድ የምትታወቀው በየትኛውም መገናኛ ብዙኀን ያልተሰሙ ዘገባዎችን መሥራቷ ነው፡፡ አልፎ አልፎም በጥቆማ የምታገኛቸውን አንዳንዶች ‘ጮማ’ የሚሉት ቀልብ ሳቢ ዜና ለመጀመሪያ ጊዜ ተሠርተው ሌሎች መደበኛ መገናኛ ብዙኀን በፍጥነት

የተቀባሏቸው፤ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በከፍተኛ ደረጃ የተሰራጩ ዘገባዎች ለመሥራትም ታድላለች።

ከበርካታዎቹ ኹለቱን ለአብነት መጥቀስ ደራሲዎቿን እናስታውስ፤ አንደኛው መስከረም 17/2012 በፊት ገጽ ላይ ያስነበበችው “የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ በሚል ሥያሜ ኢሕአዴግ ውሕድ ፓርቲ ሊሆን ነው” የሚለው አቦል ዜናዋ በዚህ ረገድ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ሰበር ዜናዋ ነበር። የዜናውን ፍንጭ ረቡዕ አግኝታ፣ ኀሙስና አርብን ለማረጋገጥ ላይ ታች ስትል ቆይታ ዓርብ ምሽቱን ተጽፎና ተዘጋጅቶ ወደ ኅትመት ገብቶ እስኪወጣ ድረስ በመደበኛ ብዙኀንም ይሁን በማኅበራዊ ገፆች ምንም ሳይባል ነው ዜናውን ለአንባብያን ያደረሰችው። ይህ አጋጣሚ ለአዲስ ማለዳ መታወቅ ከፍተኛውን አስተዋፅዖ አደርጓል።

በሌላ ቀን ደግሞ ፓስፖርት ለማደስም ይሁን አዲስ ለማውጣት ዜጎች በተቸገሩበት ወቅት፥ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ውስጥ የሚሠሩ አንዳንድ ሠራተኞች ይህንን ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚውን በመጠቀም ከጉዞ ወኪል ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር የሙስና አሠራር ሰንሰለቶችን በመዘርጋት ዜጎችን ሲያጉላሉ በተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፋ የምርመራ ዘገባ ማቅረቧን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን የሚያጣራና ለችግሩ መፍትሔ የሚሰጥ ግብረ ኀይል ወዲያውኑ በማቋቋም ወደ ሥራ መግባቱና በአጭር ጊዜ ውስጥ ላጋጠመው ችግር መፍትሔ ለመስጠት መሞከሩ አዲስ ማለዳን ካኮሯት ሥራዎቿ ተርታ ይመደባል።

አሁን አሁን በአገራችን መገናኛ ብዙኀን እምብዛም የማይሠራውን የምርመራ ዘገባ እና ትንታኔ አዲስ ማለዳ አቅም በፈቀደ መጠን ለመሥራት ታትራለች። በዚህም ከፍተኛ ትኩረትን መሳብ ከመቻሏም ባሻገር አበረታች የሞራል ድጋፍን አትርፋበታለች። ከእነዚህ የምርመራ ዘገባዎች እና ሰፊ ትንታኔዎች መካከል ስለ አንዳንድ የፕሮቴስታንት አጭበርባሪ የሃይማኖት አስተማሪዎች፣ በአዲስ አበባ በዘመነ ኮሮና የከተማዋ ከበርቴዎች የራቁት እና የግብረሰዶም ምሽት ቤቶች ክራሞት እንዲሁም የአደንዛዥ ዝውውርና ተጠቃሚነት ዙሪያ የተሠሩት የሚገኙባቸው ሲሆን የብዙዎችን ቀልብም ስበዋል፤ በአስተማሪነታቸውም ተወድሰዋል። በተጨማሪም በወንጀል መከላከል ላይ ለተሠማሩ የመንግሥት አካላትም መነሻ ፍንጭ ሰጥቷቸዋል የሚል እምንት አዲስ ማለዳ አላት።

ይሁንና እነዚህ የምርመራ ዘገባዎች በሚሠሩበት ወቅት እንዲሁም ከተሠሩም በኋላ ከፍተኛ ጫና ከተለያዩ ወገኖች የነበሩ ቢሆንም ከማስፈራሪና ዛቻነት ግን የዘለሉ አልነበሩም።

የአዲስ ማለዳ የአንድ መቶ ሳምንታት ጉዞዋ አልጋ በአልጋ ነበር ማለት አይቻልም። ሌሎች መደበኛ መገናኛ ብዙኀን በተለይ የኅትመቶቹ የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች ሁሉ አዲስ ማለዳም ተጋፍጣለች።

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ ማለዳ በሥርጭት በኩል ያጋጠሟትን ተግዳሮት እስካሁን ድረስ የተከተላት ዘልቋል። በተጨማሪም በቅርቡ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና (የኦቪድ 19) ወረርሺኝ ምክንያት በከፍተኛ ችግር ቢያጋጥማትም ችግሩን በመቋቋም ለአንድም ቀን ኅትመቱ ሳይቋረጥ ማስቀጠል መቻሏ እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው።

አዲስ ማለዳ በተጓዘችባቸው አንድ መቶ ሳምንታት ብዙም ባይባልመ የዘገባ ዝንፈቶች ፈጽማ ታውቃለች፤ ወዲያውኑ የማስተካከያ እርምጃዎችን ወስዳለችም።

የአዲስ ማለዳ ከኅትመት ጎን ለጎን ዘመኑ የሚጠይቀውን የዲጅታል አማራጭ መድረኮችን በደንብ መጠቀም ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ እየሠራች ትገኛለች። በተለይ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ ያላትን አማራጭ ተዓማኒ የዜና ምንጭነቷን በመጠቀም እየሠራች ትገኛለች። በፌስቡክ፣ በቲውተር፣ በቴሌራም፣ በዩቲዩብ እንዲሁም በይፋዊ ድረገጿ ተደራሽነቷን እያሰፋች ትገኛለች፤ በተጠናከረ መንገድ ለመውጣት ብዙ ጥረቶችን እንዲሁም መሬት የወረዱ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ትገኛለች።

በዚህ አጋጣሚ ሳይጠቀስ የሚያልፈው ጉዳይ፥ አዲስ ማለዳ በአንድ መቶ ሳምንታት ቆይታዋ በአዲሱ ዓመት 2013 መጀመሪያ ላይ ራሱን የቻለ ወርሃዊ “አዲስ ማለዳ መጽሔትን” በገጸ በረከትነት ማቅረብ መቻሏ ነው።

በመጨረሻም መጀመሪያ ላይ እንደተጠቀሰው አዲስ ማለዳ በእስካሁን ጉዞዋ የምትኩራራ ሳይሆን ከድክመቷ እየተማረች፣ ጥንካሬዋን ይበልጥ እያጎለበተች የምትቀጥል እንዲሁም እስካሁን ለሄደችበትም ሆነ ለምትቀጥለው ጉዞ የአንባቢዎቿ ድጋፍ፣ አስተያየትና ትችት አሁንም ይቀጥል ስትል ላለፈው ምስጋና ለወደፊቱ ደግሞ ጥሪዋን ታቀርባለች።

Page 3: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 3አቦል ዜና

በመርሻ ጥሩነህ

አዲስ የጸደቀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ደንብ ቁጥር 474/2012 ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የኢንቨስትመንት መስኮችን ከስምንት ወደ 30 ከፍ አድረጓል።

አዲስ የጸደቀው የኢንቨስትመንት ደንብ ቀድሞ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ተከልለው የነበሩ የኢንቨስትመንት መስኮች ከስምነት ወደ 30 ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች የቅንጅት ኢንቨስትመንት የተከለሉ ኢንቨስትመንት መስኮችን እንዲሁም ከመንግሰት ጋር በቅንጅት የሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶችን በአዲስ መልክ አካቷል።

በደንቡ አዲስ የተካተቱት ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የኢንቨስትመንት መስኮች በተለያዩ የብሔራዊ ዋና ዋና መስመሮች የኤሌክተሪክ ኃይል ማሰተላለፍ፣ ነዳጅ እና የነዳጅ ምርቶችን ማቅረብ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመረተን የራስ ምርት በጅምላ መሽጥ እና ኤሌክትሪክ ንግድን ሳይጨምር የችርቻሮ ንግድ፣ ጥሬ ቡና፣ ጫት፣ የቅባት እህል፣ ጥራጥሬ፣ ማዕድናት፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የተፈጥሮ ደን ውጤቶች፣ ዶሮ፣ እና ጋማ ከብቶችን ጨምሮ ከብቶችን ከገበያ በመግዛት በመላክ የሚሰራ የውጭ ንግድ፣ ቡታጋዝና ቢቱመንን ሳይጨምር የገቢ ንግድ፣ የኮከብ ደረጃ ያላቸው ሳይጨምር የሆቴል፣ የሎጅ፣ የሪዞርት፣ የሞቴል፣ የእንግዳ ማረፊያ እና የፔንሲዮን

እና የሰፖርት ውርርድ ሥራዎች፣ በኢዱስትሪ መጠን የሚካሄዱትን ሳይጨምር የልብስ ንጽህና መስጫ አገልግሎት፣ የጥበቃ አገልግሎት፣ የድለላ ሥራዎች እና ከፍተኛ የዘርፍ ዕውቀት እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ልምድ እና የሥራ ትስስር የሚጠይቁ መርከቦችን እና ሌሎች ተመሳሳየው ሙያተኞችን ከሥራ ጋር የማገናኘት አገልግሎትን ሳይጨምር የግል ሥራ እነ ሠራተኛ የማገናኘት አገልግሎት መሆናቸው በደንቡ ላይ ተቀምጧል።

ደንቡ ላይ አዲስ ከተካተቱት ኢንቨስትመንት መስኮች ውስጥ የባቡር ትራንስፖርት፣ የኬብል መኪና ትራንስፖርት፣ የኮልድ ቼይን ትራንስፖርትን ሳይጨምር የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት

አዲሱየኢንቨስትመንትደንብለአገረውስጥባለሀብቶችየተከለሉዘርፎችንአሰፋአገልግሎት፣ የወጭ አገር ብሔራዊ ምግብ የሚቀርብ የኮከብ ደረጃ ያለው የሬስቶራንተ አገልግሎትን ሳይጨምር የሬስቶራንት፣ የሻይ ቤት፣ የቡና ቤት፣ የመጠጥ ቤት፣ የምሽት ክለብ እና ምግብ የማቅረብ አገልግሎት፣ ከደረጃ አንድ በታች የሆኑ የኮንስትራክሽን እና የቁፋሮ አገልግሎት እንደሆኑ በአዲሱ ደምብ ላይ ተገልጿል።

እንዱሁም የጉዞ ወኪል፣ ጉዞ ትኬት ሽያጭ እና የንግድ ደጋፊ አገልግሎት፣ የማስጎብኘት አገልግሎት፣ ለተወሰኑ ኢንዱስትሪ የሚገለግሉ ከባድ መሣሪያዎችን እና ልዩ ተሸከርካራችን ሳይጨምር መሣሪያዎች፣ ማሽኖች እና ተሽከርካሪዎችን ማከራየት፣ ለአገር ውስጥ ገበያ የሚቀርቡ የዳቦ እና የኬክ ምርቶች ማዘጋጀት፣ የወፍጮ ቤት አገልግሎት፣ የጸጉር ማስተካከል እና የቁንጅና ሳሎን አገልግሎት፣ የአንጥረኝነት ሥራ እና በአፍሪካ ደረጃ የማይካሄድ የልብስ ስፌት፣ የአውሮፕላኖች ጥገና እና ዕድሳትን ጨምሮ የጥገና እና የዕድሳት አገለግሎት ሆኖም የከፍተኛ ኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች እና የህክምና መሳሪያዎች ጥገና እና ዕድሳት ሳይጨምር፣ በአውሮፕላን ማረፊያ ቦታ ለሚቆሙ አውሮፕላኖች የሚሰጡ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች፣ እንጨት የመሰንጠቅ ሥራ፣ የጣውላ ሥራ እና ያልተጠናቀቁ የእንጨት ውጤቶችን የመገጣጠም ሥራ፣ የግምሩክ አስተላላፊ አገልግሎት፣ ብሎኬት እና ጡብ ማምረት፣ የከባ ድንጋይ ማውጣት፣ የሎተሪ

ረድኤት ገበየሁ

በ2012 አገር ዐቀፍ የኹለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ በኢትዮጲያ ያለውን የኢንተርኔት አስተማማኝነት እና የተማርንበትን ጊዜ ያላማከለ ነው ሲሉ የ12 ክፍል ተፈታኞች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

ተማሪዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ነን በማለት ከገለፁት ምክንቶች መካከል አንደኛው የኢንተርኔት አገልግሎቱ ሲሆን፤ ሁሉን ተቋቁመን እንፈተን እንኳ ብለን ብንወስን ከዚህ በፊት ከቴክኖሎጂ ጋር ያለን ቅርበት ግምት ውስጥ አለመግባቱ ዋናው ተግዳሮት ነው ብለዋል።

ከዛም ባሻገር ‹‹ትምህርት ሚኒስቴር እንዴት አስቦት እንደሆነ ባላውቅም የአገር ዐቀፍ የኹለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ለክልልም ለከተሞችም በእኩል ሰዓት የሚሰጥ እንደመሆኑ አንዳንድ ቦታ የመቋረጥ ችግር ቢያጋጥም ትምህርት ሚኒስቴር እንዴት ሊፈታው ነው›› በማለት የገለፀልን ለደኅንነቱ ሲባል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተፈታኝ ተማሪ ‹‹ የኛን ህይወት እንደማበላሸት ነው የምቆጥረው››ሲል ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

በተጨማሪም የ 11ኛ ከፍል ሙሉ ትምህርቱ እና የ 12ኛ ክፍል ደግሞ የስድስት ወር ትምህርት በቀረው አጭር ጊዜ ውስጥ እንዴት ድጋሚ ተሸፍኖ ሊያልቅ ነው ሙሉውን በፈተናው የሚካተተው በማለት ያነሱ ሲሆን ፤ ለአምስት ሳምንታት እንዲሰጥ የተወሰነው ከፈተና በፊት የክለሳ ትምህርትም እስከአሁን አለመጀመሩ ሌላኛው ግርታን እየፈጠረብን ያለ ነገር ነው በማለት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ይሁን እና እስከአሁን ስጋት ውስጥ በመሆናችን ምክንያት ደግሞ በየትምህርት ቤቶቻችን የትምህርት ክለሳ እና መሰረታዊው ኮምፒውተር ስልጠናው መቼ እንደሚጀመር ደጋግመን በስልክም በአካልም እየጠየቅን ቢሆንም ትምህርት ቤቶቻችን ግን ‹‹መቼ እንደሚሰጥ ለኛም የተረጋገጠልን ነገር የለም ›› በማለት እንደሚመልሱላቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር መረጃ በመፈለግ ደጋግመን ብንደውልም መልዕክት ብንልክም ማግኘት አልቻልም። ከዛም በተጨማሪ ለሳምንታት የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት ሃረጓ ማሞ ወልደ ሚካኤል ጋር በእጅ ስልካቸው ደውለን

መልዕክት ልክን የነበረ ቢሆንም ‹‹አሁን ስብሰባ ላይ ነኝ ምላሽ መስጠት አልችልም›› በማለታቸው ሳይሳካልን ቀርቷል።

ነገር ግን የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ህዳር 22 እና 23፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና ደግሞ ከህዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 እንዲሰጥ የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡ እና ለዚያም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጾ ነበር።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት

‹‹የሁለተኛደረጃመልቀቂያፈተናየሚሰጥበትሂደትእኛእንድንጎዳያደርገናል››ተማሪዎች

ረድኤት ገበየሁ

የመኪና አስመጪዎች ማኅበር ራሱን የቻለ የመኪና መገጣጠሚያ ተቋም አንድ ላይ በመሆን ሊከፍቱ እንደሆነ እና ይህንንም ሀሳባቸውን ለትራንስፖርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

ከሶስት ሺህ በላይ የመኪና አስመጪዎች አለን የሚሉት የመኪና አስመጪዎች ማኅበር ዋና ስራ አስኪያጅ መሃመድ አህመዴ የማኅበሩ አባላት አንድ ላይ በመሆን መኪና በአገር ውስጥ መገጣጠም እንዲችል ብለን በተደጋጋሚ ጥያቄ ለሚኒስቴር መስርያ ቤቱ አቅርበናል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ጨምረው ተናግረዋል።

መሃመድ እንዳሉት ከሆነ የማህበሩ አባላት ከሆኑ አስመጪዎች ይሄ ሃሳብ የመጣውም መንግስት ባወጣው ህግ መሰረት አዳዲስ መኪኖች እንጂ ጥቅም ላይ የዋሉ መኪኖች ወደ ኢትዮጲያ መግባት የለበትም የሚለውን ሕግ መሰረት አድርጎ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በዚህም ጥቅም ላይ የዋሉ መኪኖችን ማስገባት ስለማይቻል የታሰበው ነገር ወደ መኪና ስራ ብንገባና መኪና መገጣጠሚያ ኩባንያ ብንከፍት ብለን እንቅስቃሴ ጀምረናል ብለዋል ። በመስከረም 19 /2013 የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሰብስበውን ነበር የሚሉት መሃመድ የመኪና መገጣጠሚያ ለማቋቋም ፍላጎቱ እንዳለን እና ነገር ግን የትራንስፖርት ሚኒስቴርም መንግስትም ጣልቃ ቢገባ ቁጥራችን ከ 3 ሺህ በላይ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ከፍተኛም መነሻ ስለሚኖረን ወደ መገጣጠሚያ ፋብሪካ እንድንለወጥ በአክሲዮን መደራጀት ይቻላል ብለን በእለቱ በሸራተን በነበረው ስብሰባ ላይ ጥያቄ አቅርበናል ብለዋል። ይሄን ጥያቄ ስናቀርብ የመጀመርያችን አይደለም የሚሉት የመሃበሩ ሃላፊ ለኢንቨስትምንት ኮሚሽን ከሶስት ወር በፊት ቅድሚያ አቅርበን ነበር ‹‹ ነገር ግን ገና ሂደት ላይ ያለ ነገር በመሆኑ ጥናት እና ምን ያህል የገንዘብ አቅም እንደሚያስፈልገን ግን አልታወቀም›› ብለዋል።

አሁን ላይ መሰረተ ሃሳብ ላይ ነን ያሉት የመሃበሩ ሃላፊ ፍቃዱ ሲሰጠን ደግሞ ወደ ጥናት እንገባለን ብለዋል። ነገር ግን ከመንግስት ከፍተኛ እርዳታ ያስፈልገናል የሚሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ቁጥራቸው በዛ ያለ መሆኑን ጠቅሰው በማህበሩ ያሉት አስመጪዎች ‹‹የገንዘብ ችግር ላይኖርብን ይችላል። ከ ሶስት ሺህ በላይ የሆነው አስመጪዎች እያንዳንዳችን አንድ ሚሊዮን ብናወጣ እንኳ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ይችላል›› ይሄ አነድ ትልቅ መገጣጠሚያ መክፈት ያስችላል ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል።

ይህ መሆኑ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው እና አብዛኛው አስመጪ የግሉ የሆነ መሸጫ ቦታ አለው የሚሉት ስራ አስኪያጁ አባል የሆኑት እራሳችን ከገጣጠምነው ላይ በመውሰድ መቸርቸር ይችላሉ ይሄም ይበልጥ አዋጭ ይሆናል ብለዋል።

በተያያዘም ትራንስፖርት ሚኒስቴር በበኩሉ የቀረበው ጥያቄ ተገቢነት ያለው እና ታይቶ እንደሚወሰን በመድረኩ ተናግረዋል። በተያያዘም

በመድረኩ ላይ ከተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች መካከል የኤሌክትሮኒክስ መኪና ጉዳይ ዋናው ሲሆን መኪናው እንደሚያስፈልገው መጠን ‹‹ በነዳጅ ማደያዎች አካባቢ ቻርጅ ማድረጊያ መኖር አለበት ተብሏል።

ከዛም ባለፈ በስፋት ከተነሱት ሃሳቦች የአገር ውስጥ መገጣጠሚያዎች እንዲበዙ የማድረግ እና ከዛም ባለፈ ወደ አገር ውስጥ( import) የሚደረገውን መኪና ለመቀነስ ታስቦ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተነስተዋል። በውይይቱ ላይ የፌደራል ትራንስፖርት ባለ ስልጣን ዋና ዳይሬክትር የሆኑት አብዲሳ ያደታ እና የትራስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ዳግማይት ሞገስ ጥያቄዎች እንደቀረበላቸው ተጠቁሟል ። ማህበሩ አያይዞም በአገር ውስጥ መኪናዎችን መገጣጠም ተሸከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚወጣውን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የመኪናአስመጪዎችመገጣጠሚያኢትዮጲያውስጥለማስጀመርጥያቄአቀረቡ

አንዱ ነው።

ከዚህ በፊት “የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የሥራ መስኮች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 270/2004” በሚለው ደንብ ላይ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የሥራ ዘርፎች የመገናኛ ብዙሀን ሥራዎች፣ የብሮድካስት ሥራዎች፣ የጥብቅናና የህግ አገልግሎት፣ አገር በቀል የባህል መድኃኒቶች ማዘጋጀት፣ የባንክ፣ ኢንሹራንስና አነስተኛ ብድርና ቁጠባ፣ እቃዎችን የማሸግ፣ የማስተላለፍና የመርከብ ውክልና አገልግሎት፣የማስታወቂያ እና የፕሮሞሽንና የትርጉም ሠራዎች ናቸው።

የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 እንደሚሰጥም በምክረ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል።

ነገር ግን እነዚህ ምክረ ሃሳቦችም እንደ ሁኔታው ተፈፃሚ ላይሆኑ የሚችሉበት አማራጭ ተቀምጠዋል። ትምህርት ሚኒስቴር ከቀናት በፊት እንደገለፀው የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት ጊዜ ለመስጠት ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከል መሰረት ያደረጉ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን እንደሚካሄድ እና ተማሪዎች የ45 ቀን የማካካሻ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም እንደሚሰጣቸው የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሃረጓ ማሞ ተናግረው ነበር።

ስለዚህም ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት እና ፈተናም የሚሰጠው አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ ብቻ መሆኑም ተገልጿል። ይህ መሆኑ እና የተረጋገጠ ነገር አለመነገሩ ደግሞ ተፈታኝ ተማሪዎቹ ከፍተኛ ጥርጣሬ እና መጨናነቅን እንደፈጠረባቸው ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።

Page 4: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 4ትንታኔ

ረድኤት ገበየሁ

የሰሞነኛው የአገራችን የፍርድ ቤት ውሎን በተመለከተ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው እንግዳ መሳይ ክስተቶች መካከል ዳኞች ግራ ቀኙን ተመልክተው ተከሳሽ ተጠርጥሮ የተያዘበትን ጉዳይ ካመዛዘኑ በኋላ የሚሰጧቸው የዋስትና መብቶች ተፈፃሚነት በፖሊስ መደነቃቀፉ ነው።

ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የሰጣቸውን የዋስትና መብት ተጠቅመው የተጠየቁትን የዋስትና ማስያዣ ቢያሟሉም ፖሊስ ግን የፍርድ ቤትን ትእዛዝ መፈጸም አለመቻሉ የፍርድ ቤትን ነጻነትን እና ህግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ ጥሏል።

ለዚህ ማሳያ ከሆኑት የፍርድ ቤት ውሎዎች መካከል የኢትዮጵያውን ዴሞክራሲያው ፓርቲ (ኢዴፓ)አባል የሆኑት ልደቱ አያሌው ዋነኛው ናቸው።ልደቱ መስከረም 12 2013 ላይ ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ተመልክቶ የክስ ሂደታቸውን በውጪ ሆነው መከታተል ይችላሉ ሲል የ100 ሺህ ብር ዋስትና ተጠይቆባቸው ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር ።

በትዕዛዙም መሰረትም ልደቱ አያሌው የተጠየቁትን የ100 ሺህ ብር የዋስትና ትዕዛዝ ቢያሟሉም ፖሊስ ሊፈታቸው ፍቃደኛ ካለመሆኑ በላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ ዋስትናቸው እንዲታገድ አድርጓል። ይህምበ ለሁለት ጊዜ ችሎትከመሆኑም በላይ ህጉን የተከተለ ነው? ወይንስ አይደለም በሚል ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ አና የሃሳብ ምልልስ እየተደረገበት ይገኛል።

ከዚህ በፊትም በአራት አስራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ላይ ከሀጫሉ ግድያ በኋላ ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ንብረት እንዲወድም፣ የሰው ህይወት እንዲጠፋ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለቱ አራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ እንደከፈተባቸው ይታወቃል።

በቀረበባቸው ክስም ፍርድ ቤቱ በዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች ተይዘው እንደነበር የአስራት ቴሌቪዥን ዘግቦ ነበር።

ታዲያ በፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው የተረጋጋጠላቸው ተከሳሾችን ፖሊስ አለቅም ማለቱ በህግ ባለሙያዎች እና በዘርፉ በርካታ አመታትን በዘርፉ ከሰሩ ምሁራንን ዘንድ ምን አንድምታ አለው በማለት አዲስ ማለዳ አነጋግራለች።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ብዙሃኑ የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ አሁን እየሆነ ያለው እና በፍርድ ቤቶች ውሎ ተደጋግሞ የሚሰማው አካሄድ በፍፁም ትክክል ያልሆን እና የህግ ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚሳድር ፤ ከእዛም ሲከፋ የሰዎችን ህገ -መንግስታዊ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊ መብትን የሚጋፋ ነው ሲሉ ተችተዋል።

በየነ ይርጉ ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ስማቸው የተቀየረ የህግ ባለሙያ እንደተናገሩት ከሆነ ‹‹አቃቤ ህግ ይግባኝ ለመጠየቅ የህግ መሰረት

እንደሌለው እና እንዲያውም ጉዳዩ የህገ መንግስት ጉዳይ ብቻም ሳይሆን የሰብዓዊ መብትም ጨምር እንደሆነ አንስተዋል። የዋስትን ጉዳይ ከምንም ምክንያት በጣም ጥበቃ ከሚደረግላቸው መብቶች መካከል ዋስትና መብት አንዱ መሆኑን አንስተዋል።

ስለዚህም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ያ መብት ግን በሌላ ኃይል ሲገደብ ሰብዓዊ መብታቸው ፤ ወይንም ነፃነታቸው እንደተገደበ ስለሚቆጠር ትልቅ ስህተት መሆኑን ያነሳሉ። በእርግጥ የዋስትና መብት የሚከለከልባቸው ልዩ ጉዳዮች መኖራቸው እና ይኸውም አንዱ የወንጀሉ ክብደት መሆኑ ሌላኛው ደግሞ በህዝብ እና በግለሰብ ላይ የደረሰው ወንጀል ታይቶ፣ በዋስ እንዲወጡ ቢደረግ በሕዝብ ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ ታይቶ (ተገምቶ) የዋስትና መብት ሊከለከል እንደሚቻል ይናገራሉ።

አሁን ያለው ግን ፍርድ ቤት ከግራ እና ከቀኝ ያለውን ጉዳይ አመዛዝኖ የዋስትና መብት ከፈቀደልህ በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ማለት ይችላል ወይ ነው ጥያቄው ? እንደ ባለሙያው ከሆነ ተጠርጣሪው ያን የዋስትና መብት ተከልክሎ ቢሆን ይግባኝ ማለት እንደሚችል ጠቅሰው ይህም የተፈቀደበት ምክንያት ዋስትና ለተከለከለው ተጠርጣሪ የነፃነት መብቱን በመሆኑ ሁለተኛ እድል እንዲሰጠው ማድረግ ስለተፈለገ እንደሆነ አንስተዋል።

መንግስት ግን ፍርድ ቤት ላይ ባለው እምነት የተነሳ ሁኔታዎችን አመዛዝኖ የዋስትና መብት ከፈቀደ አቃቤ ህግ የተሰጠው የዋስትና መብት ላይ ይግባኝ እንዲጠይቁ የሚያደርግ መብት በግልፅ አለመኖሩ፣ ሁለት አይነት አተረጓጎም እንዲይዝ እንዳደረገው የሚያነሱት ባለሙያው እንደሚያነሱት በግልፅ ካለተፈቀደ እንደ ተከለከለ ይቆጠራል የሚሉ ባለያዎች አሉ። ስለዚህም እንደዚህ አይነት መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ላይ መብትን ለመገደብ በግልፅ የተቀመጠ ስልጣን ሊኖር እንደሚገባም ያነሳሉ።

በሂደቱም ፍርድ ቤቱ ሊያይ የሚገባው ይግባኝ ማለት የሚችል መብት ባለው ላይ ነው እንጂ በግልፅ ያልተቀመጠ ስልጣን አለኝ በሚለው ላይ አለመሆኑ ይጨምራሉ። በተጨማሪ እንደ ማጠቃለያ የህግ ባለሙያው የተናገሩት ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ቀድሞውንም ሲፈቅድ ካመዛዘነ በኋላ ስለሚሆን እስክ ጭራሹም ከዛ ሂደት በኋላ የዋስትና መብት ለምን ተፈቀደ ብሎ አቃቤ ህግ ይግባኝ የሚጠይቅበት የህግ አግባብ የለም ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ሃሳብ የሰጡ የህግ ባለሙያዎች እንዳሉን ደግሞ እንደዚህ ሊያስደርግ የሚያስችል ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ተናግረዋል ይህም ፍርድ ቤት የዋስትና መብት የሰጠው ሰው ከእስር ቤት የመውጣት ጉዳይ እድል ሳይሆን መብት መሆኑን ጨምረው አንስተዋል። ከዚህ ቀደም ‹‹እኔም እንደዚህ አይነት ችግር አጋጥሞኝ ነበር› የሚሉት የህግ ባለሙያው ይሄ ህገወጥ ድርጊት ነው ሲሉም አክለዋል።

ህገ ወጥነቱም በፖሊስ እና በአቃቤ ህግ

መካከል የሚደረግ ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን እና የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አክብሮ ተጠርጣሪን ለቆ አቃቢ ህግ ይግባኝ ከጠየቀበት ግን በይግባኙ መሰረት የተፈቀደው ዋስትና መብት አክብሮ፣ ትክክል አይደለም ከተባለ ግን ተጠርጣሪን ዳግም መያዝ ይችላል እንጂ ፤ እጁ ላይ አቆይቶ መጠየቅ አይችልም ብለዋል ።

ከዚህም በተጨማሪ ፖሊስ በበኩሉ የአቃቤ ህግ ይግባኝ ማለት አለማለት አይመለከተውም ይልቁንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝን ማክበር ብቻ ከፖሊስ እንደሚጠበቅ ያስረዳሉ። ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱ እንዲከበር የመታወቂያ ዋስም ይሁን የገንዘብ ዋስ እነዚያን አሟልቶ ሲገኝ ፖሊስ መልቀቅ ብቻ እንደሚጠበቅበት አንስተዋል ። ይህንንም ጥያቄ ቢሆን ተጠርጣሪው የሚያቀርበው ለፖሊስም እናለአቃቤ ህግ ሳይሆን ለፍርድ ቤቱ መሆኑን ገልጸዋል ከዚያም ፍርድ ቤቱ በተራው ትዕዛዝ ሊሰጣል እንደሚችል ያነሳሉ። ይህንን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተቀበለ ማንኛውም የሕግ አካል በእጁ ላይ የሚገኝን የትኛውም ተጠርጣሪ የመልቀቅ ግዴታ አለበት ይላሉ።

ይሄ ሊሆን የማይችልበት ሁኔታ ግን ሊኖር እንደሚችል በመደበኛው ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ውስጥ መኖሩን እና አቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቅ እንዲችል የሚፈቅድለት ዋስትናውን ሊያስከለክል የሚችል አዲስ ነገር ያገኘ ከሆነ የዋስትናው መብት እንዲሻሻል መጠየቅ እንደሚችል ሌላናው የህግ ባለሙያ ለአዲስ ማለዳ ስለ ጉዳዩ አብራርተዋል።

ይህን ክፍተት በማየት እየተዘጋጀ ያለው ረቂቅ ህግ ሊያየው እንደሚችል ይገመታል።ለ60 ዓመታት ገደማ በሥራ ላይ የቆየው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ እንዲሻሻል ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ የሚንስትሮች ምክር ቤት መስከረም 16/2013 ባካሄደው ስብሰባ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም ምናልባትም ክፍተቱን ሊሞላ እንደሚችል ከሰሞኑ ሕጉን በማርቀቅ ሂደት ለረጅም ጊዜ የተሳተፉት ሙሉወርቅ ሚደቅሳ እንስተዋል።

“በአጠቃለይ ረቂቅ ሕጉ ሲተገበር አብዛኛውን ሥራ ለፖሊስ እና ለዐቃቤ ሕግ በመስጠት ፍርድ ቤት ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ ተጠርጣሪዎች እና ተከሳሾች ረዥም ጊዜ ፍትሕ ሳያገኙ የሚቆዩበትን ጊዜ ያስጥራል፣ በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን አስሮ ከመመርመር ይልቅ ምርመራ አከናውኖ ወደ መያዝ እንደሚገባው ስለሚያደርግ ትልቅ እፎይታ ሊሰጥ እንደሚችል ያነሳሉ።

ከእነዚህም መካከል የዋስትና መብት፣ የጊዜ ቀጠሮ እና የቅጣት አፈጻጸሞች ላይ ለውጦች እንደሚኖር ጠቁመዋል።

• የዋስትና መብት

ብዙ ጊዜ ጠበቆች ደንበኛዬ ተጠርጥሮ የታሰረበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል አይለደም’ ሲሉ ዐቃቤ ሕግ በተቃራኒው ‘የዋስትና መብት መሰጠት የለበትም’ የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ መስማት የተለመደ ነገር ነው።

የሕግ ባለሙያው ቀለምወርቅ ሚደቅሳም የዋስትና መብት ብዙ አጨቃጫቂ ነገሮች እንደሉት ይናገራሉ። ይህ ረቂቅ አዋጅም አጨቃጫቂ የሚባሉ የዋስትና መብት ጉዳዮችን ግልጽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ይጠቅሳሉ።

በኢትዮጵያ እስካሁን የተለመደው የገንዘብ ዋትስና መሆኑን በማስታወስም፤ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጠርጣሪው በየቀኑ ወይም በየሳምንቱ ወደ መንግሥት ተቋም እየቀረበ ሪፖርት እያደረገ ከዚያ ውጪ ሥራውን እንዲሰራ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ይናገራሉ።

• የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ

መርማሪ ፖሊስ በያዘው ተጠርጣሪ ላይ ምርመራ ለማድረግ ፍርድ ቤትን በተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ ሲጠይቅ ይስተዋላል።

ነባሩ የሥነ ሥርዓት ሕግ መደበኛው በሚባለው ወንጀል የ14 ቀን በጸረ-ሽብር ደግሞ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ሊፈቀድ እንሚችል ያስቀምጣል። ይሁን እንጂ ነባሩ ሕግ፣ ገደብ አያስቀምጥም። “ለምን ያክል ጊዜ ነው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የሚያስቀምጠው የሚለው ላይ ገደብ የለም” ይላሉ።

አዲሱ ሕግ ግን ለወንጀሎቹ ዝቅተኛ ወንጀል፣ መካከለኛ ወንጀል እና ከፍተኛ ወንጀል የሚል ደረጃ በማውጣት የምርመራ ቀን ብዛት እና ገደብ ላይ ጣራ ማውጣቱን ይናገራሉ ሙሉወርቅ ይናገራሉ።

“ይሄ ከተከሳሾች መብት አንጻር ጠቃሚ ድንጋጌ ነው። ለምሳሌ መካከለኛ ለሚባሉ ወንጀሎች መርማሪ ፖሊስ ከሁለት ጊዜ በላይ የምረመራ ጊዜ መጠየቅ አይችልም።”

በተቻለ መጠን አንድ ተጠርጣሪ ከመያዙ በፊት ፖሊስ ማስረጃ እንዲሰበሰብ ጥረት የሚያደርግ ሕግ ነው ይላሉ ሙሉወርቅ።

“ተጠርጣሪው ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ አውቆ እራሱን ለመሰወር እና ማስረጃ ለማጥፋት የሚሞክርበት ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ ፖሊስ የምረመራ ስራውን ጨርሶ መያዝ እንዳለበት ያስቀምጣል። ተጠርጣሪን ይዞ ማስረጃ የመፈለግ ሂደት መቀየር እንዳለበትም ያስቀምጣል።

• የቅጣት አፈጻጸም

ነባሩ የሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ የቅጣት አፈጻጸም ዝርዝር ነገሮች የሉትም። ለምሳሌ ብዙ ጊዜ ተፈጻሚ ባይሆንም የሞት ቅጣትን ፍርድ ቤቶች እንደሚያስተላልፉ የሕግ ባለሙያው ይናገራሉ።

ይህ የሞት ቅጣት በምን መንገድ ነው መፈጸም ያለበት? የሞት ቅጣት የተበየነበት ሰው የሞት ፍርዱ ወደ የእድሜ ልክ እስራት ሳይቀየርለት ወይም የሞት ቅጣቱ ተፈጻሚ ሳይሆንበት ለምን ያህለ ጊዜ ይቆያል? በሚሉት ጉዳዮች ላይ አዲሱ ሕግ ዝርዝር የአፈጻጸም ድንጋጌዎች ይዟል።

ከሞት ቅጣት በተጨማሪ ዝርዝር የሆነ የገንዘብ ቅጣት እና የእስራት ቅጣት ላይ ዝርዝር የአፈጻጸም ድንጋጌዎችን መያዙን ብዙወርቅ ከቢቢሲ ጋር ከነበራችው ቆይታ አንስተዋል።

ሰሞናዊው የዋስትና መብት መንፈግ በህግ ባለሙያዎች እይታ

Page 5: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 5

ከብርለውጡጋርበተያያዘበኢትዮ-ጅቡቲድንበርላይየዋጋንረትአጋጠመ

በራያቆቦወረዳየተከሰተውንየበርሃአንበጣለመከላከልበቂአልባሳትናኬሚካልእየቀረበአይደለም

አቦል ዜና

የአዲስአበባዩኒቨርሲቲበተማሪዎችለይተጨማሪክፍያጠየቀ

በእየሩስ ተስፋዬ

በኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየሩ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ድንበር ላይ በሚደረገው ግብይት ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።

ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚመላለሱ ምንጮቻችን እንደገለጹት ከሆነም የዋጋ ጭማሪው ከብር ለውጡ ጋር ተያይዞ መታየቱንም ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም አንድ ነጥብ አምስት ሊትር ውሃ እስከ 20 ብር ይሸጥ የነበረ ሲሆን በአሁን ወቅት ደግሞ በእጥፍ ጭማሪ በማድረግ እስከ 40 ብር እየተሸጠ እንደሆነ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል።

ውሃ ብቻ ሳይሆን የለስላሳ መጠጦችም ቢሆን የመቶ በመቶ ጭማሪ እንደተደረገባቸው ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል።

ባለ አምስት ሊትር ፈሳሽ ዘይትም ቢሆን ከዚህ ቀደም እስከ 280 ሲሸጡ የነበረ ሲሆን በአሁን ወቅት ደግሞ በ380 ብር ከመሸጣቸው ጋር ተያይዞም የምግብ ዋጋዎችም መናራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ለስራ ከኢትዮጵያ ወደ ጅብቲ የሚያቀኑ ሹፌሮችም ወደ ጅቡቲ ሲገቡ ለኮቴ ተብለው ከዚህ ቀደም ከ400 ብር እስከ 600 ብር እንደሚቀበሏቸው የገለጹ ሲሆን በአሁን ወቅት ደግሞ እስከ 1200 ብር እንደሚቀበሏቸውም ጠቁመዋል።

ከላይ የተጠቀሱት የዋጋ ጭማሪዎች ከሰሞኑን ቅናሽ ተደርጎባቸው የተሻሻሉ መሆናቸውን ምንጮቻቸን ገልጸዋል።

በመርሻ ጥሩነህ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ ከፍተኛ መንጋ ያለው የበርሃ አንበጣ በዘጠን ቀበሌዎች ተከስቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም በቂ የኬሚካል አቅርቦት፣ የኬሚካል ርጭት መከላከያ አልባሳት እና ለርጭት የሚገለግሉ የሄሊኮፕተር አቅርቦት ማግኘት እየተቻለ አለመሆኑን የራያ ቆቦ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

ከአፋር ክልል ከአማራ ክልል አዋሳኝ አቅራቢያ መነሻውን አድርጎ በራያ ቆቦ ወረዳ ከተከሰተ ከ15 ቀን በላይ ያስቆጠረው የበርሃ አንበጣ አሁን ላይ የዕድገት ደረጃውን እየጨረሰ በአየር ላይ እየበረረ በደረሱ ስብል እና አዝዕርቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም መንጋው የተከሰተበት መጠንና የተሠራው የመከላከል ሥራ በእጅጉ አናሳ መሆኑን

በዚሁ ሳምንት ለሥራ ጉዳይ ጅቡቲ ደርሰው የተመለሱት ምንጫችን እንደሚሉት ከሆነ ‹‹በኢትዮጵያ የብር ኖት ላይ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ነጋዴዎቹ የዋጋ ጭማሪ ከማድረጋቸው በተጨማሪም በአሮጌው ብር መገበያየት የለብንም፤ ከዚህ በኋላም በአዲሶቹ የብር ኖቶች ብቻ ነው የምንገበያየው እስከማለት ደርሰዋል›› ብለዋል።

ምንጮቻችን እንደሚሉት ከሆነም ይህም ሆነ ተብሎ የሚሠራ ነገር ነው ፤በተለይ በጅቡቲ የሚገኙ አንዳንድ ነጋዴዎች ከዚህ በፊት የነበረውን የኢትዮጵያን ብር በማከማቸታቸው ምክንያት አሁን ላይ ብሩን እንዴት ለመቀየር ግራ ስለገባቸው አንዱ መንገድ ይህ ይሆናል ብለው እንዳደረጉት እንገምታለን ነው ያሉት።

አዲስ ማለዳም የዛሬ ሳምንት ባወጣችው በ99 እትሟ ላይ የብር ለውጡን ተከትሎ በአንዳንድ የአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች በሕገወጥ መንገድ ገንዘብን በአይነት የመቀየር እንቅስቃሴዎች እየተስዋሉ መሆኑ የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ማስታወቃቸውንም ዘግባ ነበር።

የራያ ቆቦ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ተስፋየ ታረቀኝ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

ምክትል ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ እንደሚገልጹት የበርሃ አንበጣ መንጋው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ሌት ከቀን በመከላከል ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የዘጠኝ ቀበሌ አርሶ አደር አሁን ላይ የድካምና

በእየሩስ ተስፋዬ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማታ መርሀ -ግብር የህዝብ ግንኙነትና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመነት የኹለተኛ ድግሪ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ለመመረቂያ ጽሁፍ የሚውል የመቶ በመቶ ጭማሪ ክፍያ መጠየቁን ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።

ባለፈው 2012 ዓመት ዩኒቨርስቲው ይቀበል የነበረው 6120 ብር እንደነበረ እና በዚህ ዓመት ግን 13 ሺህ 620 ብር እንዲከፈል መወሰኑ አግባብ አለመሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል ።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ አክለው በአሁን ወቅት ‹‹የግል ትምህርት ቤቶች ቅናሽ ያደረጉ እንዳሉም እናውቃለን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግን አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተገቢ አይደለም ሲሉ አስታውቀዋል።

በዚህም ምክንያት የተደረገው ጭማሪ ከሞራልም ይሁን ከህግ አንጻር ተገቢ አይደለም በማለት ለዩኒቨርሰቲው ያሳወቅን ቢሆንም

እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት መፍትሔ ማግኘት አልቻልንም ሲሉ ገልጸዋል።

ችግራችንን ለማሳወቅም የአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ጋዜጠንኝት እና ኮሙዩኒኬሽን ዲፓርትመንት፣ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ብናስገባም እስካሁን ምንም ዓይት ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡

ምዝገባው በፈረንጆቹ መስከረም 23 እና 24 እንዲከናወን ዩኒቨርስቲው ቢያሳውቀንም ማንም ተማሪ ሊመዘገብ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተመራቂ ተማሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡

አብዛኛው ተማሪ ሲጠብቅ የነበረው ከዚህ ቀደም ሲከፈል በነበው ዋጋ እንጂ በፍጹም ከመቶ በመቶ በላይ ጭማሪ አለመሆኑን እና ይህም ችግር በተለይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋዜጠኝነት እና ኮሙዩኒኬሽን ፋኩሊቲ ላይ እንደሚበረታም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ- 19 ከተከሰተ በኋላ ከመምህራኖች ጋር የምንገናኘው በኦንላይን

ብቻ ነበር የሚሉት ምንጮቻችን ውሳኔው ከዚህ ቀደም የተላለፈ ነው ቢባል እንኳን አሳማኝ እንዳልሆነ እንደ ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል ገቢ የቀነሰብን በመሆኑ ዩንቨርሲቲው በድንገት እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ማሳለፉ ‹‹መመረቂያ ጊዜያቸው ስለደረሰ ይከፍላሉ ምንም አያመጡም›› የሚል አስተሳሰብ በዩኒቨርስቲው በኩል እንዳለ የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡

ካለአግባብ የተጨመረብን ክፍያ እንዲስተካከለንም ይመለከታቸዋል የተባሉትን ሰዎች ለማናገር ብንሞክርም በኮቪድ ምክንያት ወደ ውስጥ ገብታችሁ ማናገር አትችሉም ተብለናልም ሲሉም አክለዋል።

በአጠቃላይ ቁጥራቸው 43 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና ስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ተምህርት ክፍል የኹለተኛ ድግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ክፍያው ይስተካከለን በማለት የተማሪዎች ስምና ፊርማ ያለበት ጥያቄያቸውን ለዩኒቨረስቲው፣ለሳይንስና ክፍተኛ ትምርት ተቋማት ሚኒስቴር ማስገባታቸውን የአዲስ ማለዳ

ምንጮች ጠቁመዋለ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ስለጉዳዩ የሚመለከተው ነገር እንደሌለው አስታውቋል።

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት ደቻሳ ጉርሙ ‹‹እኛ ዩኒቨርስቲዎች ለሚመድቡት ዋጋ ተመን የማውጣት ኃላፊነት የለብንም ነገሩም እኛን አይመከለትም ብለዋል።

ዩኒቨርስቲዎች በግል በሚያስተምሩበት ጊዜ ለክፍያ የሚያስቀምጡት የራሳቸው ዋጋ ይኖራቸዋል እንጂ በእኛ በኩል ይህን ማስከፈል አለባችሁ ብለን ያስቀመጥነው መሥፈርት የለም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ተማሪዎቹ ላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ የሰጠ ሲሆን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) በዚህ ዓመት ያደረግነው ምንም ዓይነት ጭማሪ የለም በማለት አጠር ያለ ምላሻቸውን ለአዲስ ማለዳ ሰጥተዋል።

በዚህም ‹‹አንዳንድ ግለሰቦች ነባሩን ገንዘብ በርከት አድርገው ከሚገባው በላይ ይዘው ስለነበረ አዳዲሶቹ የብር ኖቶች ይፋ ሲደረጉ በነባሩ ብር ንብረቶችን በውድ ዋጋ የመግዛት እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ተስተውለዋል›› ያሉት ኃላፊው፣ አንድ በግ እስከ 10 ሺሕ እና 15 ሺሕ ብር ድረስ እገዛለው ብሎ ለማጭበርበር መሞከር እና ይህን መሰል እንቅስቃሴዎች በተለያዩ አካባቢዎች መስተዋላቸውን ለአዲስ ማለዳ መግለጻቸውም አይዘነጋም።

ኃላፊው እንዳስታወቁት ነባሩን ገንዘብን በአይነት የመለወጥ እንቅስቃሴዎቹ እየተስተዋሉ ያሉት በወሰን አካባቢዎች ሲሆን፣ ክልሉ ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው በሰሜን ወሎ፣ ራያና ቆቦ አካባቢዎች እና በሌሎች የክልሉ ጫፍ አዋሳኝ አካባቢዎች መሆኑንም አንስተዋል።

እንደ ክልል የአዳዲስ ብር ኖቶቹ ስርጭት ዘግየት ብሎ መጀመሩን የሚገልጹት ግዛቸው፣ ካሳለፍነው ሰኞ መስከረም 10/2013 ጀምሮ እንደ ክልል ከሁሉም የከተማ ባንኮች ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ስርጭቱ እንዲከናወን ይፋዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯልም ብለዋል።

ነዋሪዎች በተሳሳቱ የብር ኖቶች እንዳይጭበረበሩ የማሳወቅ እንቅስቃሴ የክልሉ ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ለማድረግ ተሞክሯል የሚሉት ኃላፊው፣ የብር ኖቶቹን በተመሳሳይ መልኩ ሠርቶ በማምጣት ደረጃ እስካሁን የተገለፀ ነገር አለመኖሩን ጠቅሰዋል።

በአገር ዐቀፍ ደረጃ ከመስከረም 5/2013 ጀምሮ የአዳዲስ የብር ኖቶችን ይፋ መደረጉም ይታወሳል።

የመሰልቸት ስሜት ውሰጥ መገባቱን ጠቁመዋል። በመሆኑም ሌሎች መንጋው ያልተከሰተባቸው አካባቢዎች የመከላከል ሥራውን አንዲያግዙ ጥሪ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።

እስከ መሰከረም 20/2013 ድረስ የበርሃ አንበጣው የእድገት ጊዜውን ሙሉ በሙሉ ባለመጨረሱ እንቅስቃሴው ከመሬት በላይ ብዙ የራቀ ባለመሆኑ በሰው ሀይል የመከላከል ሥራ ሲሰራ አንደነበር የጠቆሙት ተስፋየ አሁን ላይ ግን እድገቱ በአየር ከፍታ ላይ መብረር የሚችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ በሰው ኃይል መደረስ የማይችሉ ዛፎች ላይ እየሰፈረ መሆኑን ተናግረዋል።

በቦታው ላይ ከተከሰተው የበርሃ አንበጣ መንጋ አደገኝነት አንጻር ከፍተኛ ትብብርና ርብርብ ተደርጎ ባለበት መከላከል ካልተቻለ አንደ አገር

ከፍተኛ ጉዳት ሊስከትልና ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚዛመትበት ሁኔታ ሰፊ እንደሚሆን ምክትል ኃላፊው አሳስበዋል።

መንጋውን ባለበት ለመከላከል ከሚያስልጉት የኬሚካልና አልባሳት በተጨማሪ የመከላከል ሥራ ለመስራት የበጀት ድጋፍ አንደሚስፈልግ ተስፋየ ጠቁመዋል። በአካባቢው መንጋውን ለመከላከል እዚያው እየዋሉና እያደሩ ተሰማርተው የሚገኙ ባለሙያዎች ቢያንስ የምግብ ወጭ እንኳን መሸፈን የሚቻልበት ሁኔታ አስፈላጊ መሆኑን ምክትል ኃላፊው ጠቁመዋል።

የበርሃ አንበጣ መንጋው አቅሙ እየጎለበተ መምጣቱን ተከትሎ የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ለፌደራል ግብርና ቢሮ የሂልኮፕተር ድጋፍ ጠይቆ መስከረም 20/2013 ምሽት ላይ እልካለሁ ቢልም አለመላኩን ተስፋየ ተናግረዋል። ያልተላከበትን ምክንያት ደውለው ሲጠይቁ በአካባቢው ያለው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምቹ ባለመሆኑ እንደቀረ እንደተነገራቸውና መስከረም 21/2013 ከጥዋቱ 1፡30 ይደርሳል የተባሉ ቢሆንም በተባለው ስዓት ሂልኮፕተር አለመላኩን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ተስፋሁን መንግስቴ በበኩላቸው በቂ የኬሚካል አቅርቦት መኖሩን እና የአልባሳት አቅርቦት እጥረት ቢኖርም 400 የባለሙያዎች አልባሳት አቅርበናል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የሄሊኮብተር አለመቅረብን በተመለከተ በነበረው የአየር ሁኔታ ደመስከረም 20/2013 ደርሶ መመለሱንና መስከረም 21/2013 በቦታው ደርሶ አሰሳ እያደረገ መሆኑን ተስፋሁን ተናግረዋል። ነገር ግን የፌደራል መንግስት ለክልሉ ያቀረበው ሄሊኮፕተር አንድ ብቻ በመሆኑ እጠረቱ መኖሩን የገለጹት ተስፋሁን ለፌደራል መንግስት ተጨማሪ ሄሊኮፕተር ለክልሉ እንዲቀርብ መጠየቃቸውን ጠቁመዋል።

የበርሃ አንበጣው አስካሁን የተከሰተባቸው ቀበሌዎች በራያ ቆቦ ወረዳ ሥር ከሚገኙ 42 ቀበሌዎች በዘጠኝ ቀበሌዎች ይሁን አንጅ በአየር ከፍታ ላይ መብረር የሚችለው መንጋ ወደ ሌሎች ቀበሌዎች መዛመት መጀመሩም ተጠቁሟል። እስካሁን መንጋው ከተከሰተባቸው ቀበሌዎች ውስጥ 09፣ 05፣ 10፣ 35፣ 44፣ 23፣ 24 እና 22 ይገኙበታል።

በዘጠኙ ቀበሌዎች የበርሃ አንበጣው በደረሱ ሰብሎች ላይ ያደረሰው ጉዳት እስከ መስከረም 20/2013 ድረስ ብቻ 632 ሄክታር ሰብል ማወደሙን ተስፋየ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። የደረሰው ጉዳት ጤፍ 137 ሄክታር፣ ማሽላ 469 ሄክታር፣ ሰሊጥ 10 ሄክታር አንዱሁም በበቆሎ ሰብል ላይ 15 ኬክታር ሰብል ማውደሙን ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል። የደረሰው ጉዳት በጤፍ እና በሰሊጥ ሰብል ላይ መቶ በመቶ ሲሆን በበቆሎ ስብል ላይ 80 በመቶ እና በማሽላ ሰብል ላይ 75 በመቶ መሆኑን ተስፋየ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

• 1ነጥብ 5 ሊትር የታሸገ ውሃ እስከ 40 ብር እየተሸጠ ነው

• በዚህ ዓመት የተጨመረ ምንም ዓይነት ክፍያ የለም - የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

Page 6: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 6ማኅበረ ፖለቲካ

አዲስ ማለዳ እነሆ አንድ መቶኛ እትሟን አድርሳለች። ሊደርሱ ካሰቡበት ስፍራ በሚወስደው ረጅም ጉዞ መካከል ላይ አረፍ ማለት ደንብ ነውና፣ መቶኛዋ ላይ ሆናም መለስ ብላ በዘገባ፣ መረጃና ሐሳብ በማካፈል ያለፈቻቸውን ጊዜያት ልትቃኝ ወደደች።

‹ሲቄ› የኦሮሞ ሴት የምትይዛት በትር ወይም ቀጭን ዱላ ናት። ግን በላይዋ ላይ ብዙ ኃይል አለ። ይህም በሚቀበለውና በሚያምነው ማኅበረሰብ ዘንድ ዋጋው ከምንም በላይ የላቀ ነው። አንድ ከአወሮፓ የመጣ ሰው የሲቄን ምንነት ካልተነገረው በቀር ሊያውቅ አይችልም። ሲቄን ከልጅነት እስከ እውቀቱ በሚያውቅ ማኅበረሰብ ግን በአንጻሩ ሰላም፣ መታዘዝና መከባበር በሲቄዋ ላይ ይታየዋል።

በአዲስ ማለዳ የሲቄ አምድም እንዲህ ባለ መንገድ፣ ለሚቀበል፣ ተረድቶ ሊተረጉም ለሚችለው ሁሉ ሐሳቦች ሲተላለፉ ነበር። ምን ያህል ተጽእኖ መፍጠር እንደተቻለ፣ ምን ያህል ጥያቄን በልቦና ፈጥሮ ወደ መመራመር የሚያቀርብ ሐሳብ ተገኝቶ እንደሆነ ለማወቅ ጥናት ሳያስፈልግ አይቀርም። ከዛ ባለፈ ግን በወፍ በረር ልንቃኘው የምንችል ገሀድ መልክ አለው።

በእርግጥ የተለያዩና በርካታ፣ ወቅታዊና የኖሩ ሐሳቦች ተነስተዋል፤ በሲቄ አምድ። ግን ሐሳብ አቅራቢዎች በብዝኀነት አልታዩም። ስለሴቶች ጉዳይ መገናኛ ብዙኀን በቂ ሽፋን አይሰጡም ወይስ ይሰጣሉ የሚለው በሙግት ላይ ሆኖ እያለ፣ ያለውን አውድ መጠቀም ግን በብዛት አይታይም።

ነገሩን ከዚህ አምድ አንጻረ ብቻ በማየት አይደለም ይህ ነጥብ የተነሳው። በበርካታ መገናኛ ብዙኀን ያሉ በጉዳዩ የሚሠሩ ባለሞያዎችም ‹አስተያየት ስጡን› ብለው ሲጠይቁ የሚሰጣቸው ደጅ እንደሚያስጠናቸው፣ ‹ሐሳባችሁን በጽሑፍ አካፍሉን› ብለው ሲጠይቁም እንካችሁ የሚል እንደሌለ ይናገራሉ። በአንጻሩ ግን ለውጥ እንዲመጣ ይፈልጋሉ፣ ድምጽ የሚሆነን አጣን የሚሉ ይሰማሉ።

እንዲህ በማለት ሁሉንም መውቀስ እንደማይቻል ግልጽ ነው። ብዙ ሥራ አጥ ባለበት አገር ሠራተኛ አጣሁ የሚል አሠሪ እንደሚገኝ ሁሉ፣ ምንአልባት ሐሳቡን ሊያስተላልፍ፣ ሊናገር ወይም ሊጽፍ የሚፈልግ ሰው እና አውዱን የፈጠረው አካል አልገናኝ ብለው ይሆናል።

የውሃ ጠብታ በዘመናት ሂደት ድንጋይን ትሰብራለች። ዓለም ዛሬ ያላትን መልክ የያዘችው በአንድ ጀንበር አይደለም፣ በብዙ እልፍ ዓመታት ነው። ዛሬ ያለንበት ጥሩም ሆነ አስከፊ ኹነት በጊዜ ውስጥ፣ በአዝጋሚ ሂደት አልፎ የደረሰ ነው። እናም በሴቶች ጉዳይ እውነት ለውጥ ለማምጣት የሚፈልጉ ሰዎችም የትኛውንም አምድ ሊንቁ፣ ቸል ሊሉ አይገባም።

በብዙ ቁምነገር የሚጠበቁ ሰዎች በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የሆነ ያልሆነውን በመጻፍ፣ በመነቋቆር፣ የእልህ መልስ በመሰጣጠት፣ በመሰዳደብ ሲባክኑ እያየን ነው። በዛ መልክ በየሳምንቱ በሚፈጠርለት አዲስ አጀንዳ ያለፈውን አጀንዳ እርግፍ አድርጎ በሚረሳ ትውልድ መካከል ላለመረሳት ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል። በትክክል ለውጥ ማምጣት ግን የሚቻል አይመስለኝም።

ደግሞም ያንንም አውድ በአግባቡ የሚጠቀሙ እንዳሉ ግልጽ ነው። በተለይ በሴቶች ሥም የሚሠሩ፣ ስለሴቶች ቆመናል የሚሉና ስለሴቶች እንደሚሟገቱ የሚናገሩ ሰዎች፣ ጥቂት ጊዜ ወስደውና ሰጥተው ሐሳባቸውን ለማካፈል ፈቃደኛ ካልሆኑ መልካም አይደለም። በፖለቲካው ካሉ ሰዎች ወኔ ቅንጣቱን የሚያህል የጽናት ምልክት ካልታየባቸውም እንደዛው።

አዲስ ማለዳ ሌላ ብዙ መቶ እትሞችን ወደፊት ልትገሰግስ አልማለች፤ ጥሪዋም አብረን እንጓዝ የሚል ነው። እናም አብረን እንጓዝ!

“ሲቄ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል ‹አለንጋ› የሚል ትርጉም አለው። በገዳ ትውፊታዊ አስተዳደር ውስጥ በባሏ ጥቃት የደረሰባት ሚስት፣ ከሌሎች ሴቶች ጋር በመሆን ባሏ ላይ የካሣ ውሳኔ የምታሳልፍበት ስርዓት ሲቄ ይባላል።

እንደ አገርኛው አባባል ከሆነ ‹ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም!› አዎ የመልካም የማጀት ባለሞያ (የኩሽና) ሙያዋ የሚለካው ቡዙውን ጊዜ በውጤቷ ነው - ክሽን አድርጋ በምትሠራው ወጥ። ታዲያ ለዚህ ጣፋጭ ሙያዋ ውጤት ይህች እንደ እንዝርት የምትሾር ባለሞያ ብዙውን ጊዜ የምትሻው ግብአቶችን ነው እንጂ ሙያዋን ለማሳየት ኩሽናን እንኳ የግድ አትልም። ሜዳ ላይ ቢሆን እንኳ ተአምሯን ትተገብረዋለች። ሙያው በእጇ ነውና። ግና ሜዳ ላይም ሆነ ጓዳ፣ እንደባሕሉ ወጥ ሠሪዋ አስቀድሞ ጉልቻዎቿን ትመርጣለች። ምክንያቱም ለድስቷ የሚቀመጥበት የመርጋቱ ሕልውናዎች በመሆናቸው ነው። አገርም እንደ ድስቱ…።

ባለፉት ኹለት ዓመታት በኢትዮጵያ እፁብ ሊሰኝ ይቀርብ የነበረ ለውጥ እንዲሁም ከዚህም ፍጹም ተፃራሪ የሆነ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የሞላበትን አውሬያዊ ነውጥም ዐይተናል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አገር የቆመችባቸው ጉልቻዎቿ የማርጋት ግብራቸውን ስተው ድስቱን ለመገልበጥ መነዋወጣቸው ነው።

ጉልቻ ሲመረጥ አይነተኛው መስፈርት ድስቱን ማስመቸቱ ብቻ አይደለም፤ እሳትን መቋቋሙም ጭምር እንጂ። የእሳቱን ሙቀት የማይቋቋም ከሆነ ይፈነዳል፤ በፍንዳታውም ድስቱ አደጋ ያጋጥመዋል፤ አጋድሎ ወጡን ይደፋል አልያም ዘጭ ብሎ (ውስጡ የያዘውን በመጠኑ ወደላይ በትኖ) በስሩ እሳቱ ላይ ያርፋል። የተፈነገለው ጉልቻ ግብሩን ስቷልና ለዝናብ ወጥቶ የሚጣል ደንጊያ ብቻ ይሆናል።

የድስቱ ተፍፃሜት ይህ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም እሳት የሆነው ድንጋይ ፍንጥርጣሪም የባለሙያዋን (የወጥዋጯን) ሕላዌ ሊያከትመው ይችላል። በመሆኑም ይህች ባለሙያ ወጧን ልትሠራ ስትሰናዳ ድስቱን የሚያረጉላትን ድንጋዮች መልክ (ቅርፅ) ብቻ ሳይሆን የድንጋዮችን አስተማማኝ አለትነት ለራሷ ሕላዌ ስትል በጥንቃቄ መምረጥ ይኖርባታል። ባለሙያዋ በየጊዜው እሳቱን ትቆሰቁሳለች፥ ትመጥናለች፣ ያለመታከት ድስቷን ታማስላለች። ውስጡ ያለው እኩል ሆኖ እንዲበስል፥ እንዲስማማ በቅደም ተከተል መጨመር ያለባትን ማጣፈጫ ቅመማት እያከለች (በዚህ ሁሉ ጊዜ ታዲያ የድስቷን ነውር ትርክርክ ዙሪያውን እያጠራች) በትዕግስት ታበስላለች። በዚህ ጊዜ ግን ጉልቻ ፈጽሞ ስጋቷ እንዲሆን አታደርግም።

በሥልጣን ግብር፣ ጉልቻነት ጀርባን ወይ ገጽን በእሳት እያስመቱ አገርን ያክል ታላቅ ድስት የመሸከምና የማረጋጋት ትልቅ ኃላፊነት ነው። እነዚህን ብርቱ ጉልቻዎች በመልክ ብቻ ሳይሆን በጽናታቸውና በግልጋሎት አስተማማኝነታቸው መምረጡ ደግሞ በድስት የተመሰለች አገርን እነዚህ ጉልቻዎች ላይ የሚያሸክመው መሪ (ባለሙያ) ኃላፊነት ነው። ምንግዜም ቢሆን ግብዓቱ ቢኖርም እዚህና እዛ ተበታትኖ መሸከፋና ማምጣቱ አንድ ሥራ በሆነበት ጊዜ አይደለም፣ በተትረፈረፈ ግብዓትም ቢሆን እንኳ የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት ተፈላጊውን ነገር መለየት ግድ ይላልና።

ይኼ ግዜ ደግሞ የዘመን ንጋት የሚበሰርበት፣ የመልካም አዲስ ዓመት አውዱ የሚታይበት፥ የሚሸ’ትበት ብሎም የሚቀመስበት በዓል ነው። እናም ብዙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያ የከሸነችውን መቋደስ ልማዳችን ነው። ግን ባለሙያዋ እዚህ ደረጃ አድርሳ ለውጤት ከማብቃቷ በፊት በመሠራት ላይ እያለ ጉልቻው ቢወላውል እና ቢደፋ፥ አልያም ድስቱን መልሳ መላልሳ በማንሳት ጉልቻዎችን በመቀያየር ብትጠመድ ሙያዋ

የወንድሙን ነፍስ እንዲያጠፋበት የዋለ የደም ማፍሰሻ መሣሪያ የሆነ ነው - ደንጊያነት። ስለዚህ ለጉልቻነት ሲመረጥ ከመካከላቸው ስለተገኘና እጅ ስላነሳው ሳይሆን የተፈለገዉን የማርጋት ዓላማ የሚያሳካ መሆኑን በቅርጹን ዐይቶ፥ የመቋቋምና በእሳት ዋዕይ ውሎው ፈንድቶ በመፈረካከስ፡ ድስቱን ፈንግሎ ራሱም ከነዲድነቱ ለመብረድ ጊዜን የማይፈጅ፥ ሌሎችንም አደጋ ላይ የማይጥል መሆኑን መለየት ያሻል።

እነሆ ጉልቻዎቻችን አንዳንዶቹ በተነዋወጡበትና ድስቱን ባንቀጠቀጡበት ስፍራ ዛሬም እዛው ተጎልተው በነበሩበቱ ተትተዋል። ባለሙያው ላያቸው ላይ የሰየመውን ድስት ብድግ አድርጎ ቅርፃቸውን ‹በፍትሕ መዶሻ› ጠረብ ጠረብ በማድረግ መልሶ ሲሰይመው አላየንምና ደግመው አለማነዋወጣቸውን መናገር አይቻልም። ምናልባትም ዝዋዥዌ እያጫወቱት መስሏቸው ይሆናል። ቀሪዎቹ ደግሞ ሲያነዋውጡ ከነበሩበቱ ታላቅ የጉልቻነት ስርፋ ተነስተው፥ ሌላ ቦታ ተወስደው፥ ሌላ ድስት ተጥዶባቸዋል።

ወዳጄ የፍትሕ መዶሻ ያላረፈበትና ለማስተካከል ያልቀረጸውን፥ ጉርብጥብጥነቱንም ወቅሮ ያላመቻቸው ደንጊያ ላይ አሁንም ሌላ ድስት እንዲሰየምበት መፍቀድ፤ በተቀየረውም ስፍራ የተተካው ጉልቻ ቀድሞ ተጎልቶበት ከነበረበት (መጎለቻ) ቦታው የነበረው ግብሩ ተመዝኖ ካልመጣ ‹ሰላም ለምከሽንበት ድስት ማረፊያ ጉልቻ አለኝ› ለማለት ብቻ ያስመስልበታል። ይሕ ደግሞ ባለሙያውን ያቃልለዋል፤ ሙያውን መተግበር ሳይጀምር ከአጀማመሩ ከአሰነዳዱ ይፈርዱታል። ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል አይደል ኗሪው ብሂል?!

መሪ ባለሙያ ስትሆን፣ ለዛውም በእሳት ላይ የተጣደችን እንደ ድስት ሁሉን ዐቅፋ በእኩል መጠን አብስላ ለመመገብ የምትተጋ አገርን አስተዳዳሪነትን ስትወስድ፣ ቅድሚያ የዐይን ሽፋሽፍት ርግብግቢት ቅጽበትን ያሕል ጊዜን እንኳ ወስደህ ደግመህ እንዳታስበው የሚያደርግህ ‹የሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችል ይሆን አይሆን?› ስትል የምትጠራጠርበትን ደንጊያ ለጉልቻነት አለመሰየም ነው። እነዚህ አገር የተጣደባቸው ጉልቻዎች (ከታች እቶኑ እየለበለበው የተሰየመበትን ሰላምን በውስጡ ከትቶ የመከ’ሸን ግብሩን) በእሳት ላይ ለመጽናት በሐላፊነት በመርጋት የሚቆሙና የተሰየመባቸውንም አገር በሰላም እርጋታ የሚያቆሙ ሊሆኑ ግድ ነው።

ባለሙያ ተሰኝተህ ያስመዘገብከው ውጤት ሊኖር ግድ ይላል። የአንድ ስፍራ ግሩም ውጤትህ ከሌላው ቦታ ካስመዘገብከው ዝቅተኛ ውጤት አልያም ምንም ሲከፋም አሉታዊ (negative) ውጤት ጋር ተደማምሮና ተካፍሎ እጅግ ቢያንስ ባዶ (zero) ሊሆን ቢችል እንጂ አሉታዊ (neg-ative) ሊሆን ፈጽሞ አይ’ገባውም። ምንም ደግ ነገር ሥራ፣ የማደግ አብነት የተሰኙትን ግንባታንና የመሰረተ ልማት አውታሮች ማስጀመር ብቻ ሳይሆን ማስጨረስም ላይ ድረስ እንኳን በመቶዎች የሚቆጠር የሰው ሕይወት ቀርቶ አንዲት ነፍስ እንኳ ለዛውም በሰየምከው ጉልቻ የነውጥ አጋፋሪነት ከጠፋ ልትወቀስ ልትገሰጽስ አይገባህምን?

በሙያህ ታምኖብህ ሰው ሁሉ ታበስለውን ደግ ሰላም ሲጠብቅ ጉልቻህ ተንሸራቶ ሲቀሽብብህና ይህ ነገር ሲደጋገም፣ ጉልቻህንም ለሌላ ጉልቻነት እንዳይመረጥና እንዳያሳስት ፍትሐዊነት በሞላው መዶሻ ፈረካክሰህ ለሌላ የጠጠርነት ሕላዌ ካላዋልከው እውነት ሙያህ በምክንያት ይታይልህ ሳይሆን በሰበብ ይታይብህ እንዳይሆን ሰግተህ ነው ተብሎ ቢታሰብስ ‹እኮ እንዴት?!› ስትል ትጠይቅ ይሆን? እንጃ!።

ዛሬም ቢሆን በአንዳንድ ከፍታ ስፍራ የሚገኙቱ ለማርጋት የተመረጡቱ ራሳቸው ተነዋዋጭ በመሆናቸው የተሰየመባቸው ድስት መርጋት አቅቶት ስንቱ ሙያህን አማኝ ተስፈኛ ተሠርቶ የሚበስለውን ሰላም መብላት ሳይችል ኃላፊነታቸውን ያጎደሉቱ እነዚህ ደንጊያዎች በሚወነጭፉትና በሚያስወነጭፉት እሳት ሕይወቱ እየተበላ በሰቆቃ እንዲኖር ሆኗል። ይህንንም የሚያደርጉ ገዳይ ጉልቻዎችህን አስወግድ። ይብቃን!

ድስቱእናጉልቻዎቹየጉልቻና የድስትን ግንኙነት ከአገርና ከመሪዎች ጋር የሚያነጻጽሩት በኃይሉ፣ በሥልጣን ግብር፣ ጉልቻነት ማለት ገጽን በእሳት

እያስመቱ አገርን ያክል ታላቅ ድስት የመሸከምና የማረጋጋት ትልቅ ኃላፊነት ነው ይላሉ። ለጉልቻ የሚመረጠው ድንጋይም ለድስቱ መረጋጋት ወሳኝ እንደሆነ አገር በቀሉን ሙያ በማንጸሪያነት አብራርተዋል። ባለፉት ኹለት ዓመታትም ጉልቻው

ባለመርጋቱ የተነሳ በኢትዮጵያ የደረሰውን ጥፋትና ወደፊት ምን ሊደረግ ይገባል በሚሉት ሐሳቦች ላይ ነጥቦችን አንስተዋል።

በመቶውሳምንታት

አገራችን የተቆመችባቸው ጉልቻዎች በተለይ በእነዚህ ኹለት ዓመታት ግዜ ውስጥ

ከማርጋት ግብራቸው ወጥተው ሲነዋወጡና ድስቱን

ከወዲያ ወዲህ ሲንጡት አላየን ይሆን?!

ጥራቱም ጣዕሙም ይጓደላል። አበሳሰሉም ያረረና ያልበሰለ ድብልቅ ሆኖ ተመጋቢውን ያውካል። ስለዚህ የድስቱ መቀመጫዎችን መምረጥ ሙያን ከማስመስከር ይቀድማል፤ እንዲያውም የማስመስከሪያ አንዱ ጅማሮ ይሆናል።

አገራችን የተቆመችባቸው ጉልቻዎች በተለይ በእነዚህ ኹለት ዓመታት ግዜ ውስጥ ከማርጋት ግብራቸው ወጥተው ሲነዋወጡና ድስቱን ከወዲያ ወዲህ ሲንጡት አላየን ይሆን?! ነዲድ እሳትን ተቋቁመው የተሰየሙበት ኃላፊነት ላይ ከመርጋት ይልቅ ራሳቸው ፍም እሳት ሆነው ለግብዓትነት የታሰበውን ሁሉ ነድደው እንደ ማገዶ አመድ ሲያደርጉት አላስተዋልን ይሆን? ባለሙያውስ የእነዚህን ጉልቻዎች ‹አውቆ አጥፊነት› ለይቶ ከቀየራቸው በኋላ ሌላ ቦታ ላይ መጎለቱ አለበለዚያም የፈረደበትን መከረኛ ድስት እያመላለሰ በማንሳት አመዱ ላይ ሲያስተካክልና ድስቱን መልሶ እየሰየመባቸው ሲርመጠመጥ አልታዘብንና አላዘንንምን?! አንዳንድ ቦታ ላይ ሙሉ ለሙሉ ጉልቻዎቹ በግብራቸው እንዲቆዩ እንደማይጠበቅና መቀየራቸው ግድ እንደሆነ በባለሙያ ቋንቋ ሲነገር አልሰማንምን?!

‹ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፤ ካልሆነ ደንጊያ ነው ብለው ወደውጭ አውጥተው ይጥሉሀል።› የሚለው ከቅዱስ ቃሉ መዝዘን በቀን ተቀን ውሏችን የምናወሳው ‹ብሂል› ለእነዚህ ግብራቸውን ስተው ከደንጊያዎች ግልጋሎትም ተርታ እንኳ ዘቅጠው ለተገኙቱ ጉልቻነትን የመሰለ ኃላፊነት አውቀው በማፍረስ ለተለዩቱ ወደ ዉጭ መ’ጣል ብቻ ቅጣት እንዴት ሊሆን ይችላል?!

ተገቢ ፍርድስ እንዲሆን ዳግምም ሌላ ባለሙያ በስሕተት ሆነ በዳተኝነት መልሶ እንዳይሰይማቸውና መሰል ስሕተትን እንዳይፈጽሙ፥ ከደንጊያ ተራ ተመርጠው የጉልቻነት ኃላፊነትን ለሚሸከሙና ለተሸከሙቱ ቀሪዎቹም ሆነ አዲስ ተጎላች ደንጊያዎች ትምሕርት ይሆናቸው ዘንድ እነዚህ የማርጋት ዕምነትን ዕሳት ሆነው የበሉቱን፥ ድስቱን አነዋውጸው ለደፉቱ በፍትሕ መዶሻ ትዕቢት ጥፋታቸው ከላያቸው ላይ መቀረፅ፥ መወቀር አልያም መድቀቅስ አይገባውምን?!

ፍትሕ ቀሪውን ከማስተማር፥ ሁሉን በእኩልነት ከመዳኘት ባለፈና ሰላምን ከማስፈን ሌላ ስንት ገጽታ አለው?! ባለሙያስ በሚያስቀመጠው መልካም ጉልቻዎች ላይ የሚሰየመው ድስት ውስጥ ሰላምን ለመከሸን አስቦ ሲነሳ አመራረጡ ደንጊያነት ብቻ እንዴት ሊሆን ይቻላል?! እርግጥ ነው ደንጊያን እንደ ደንጊያ አይነቱ ሊመርጡት ግድ ይላል፤ አንዳንዱ ማዕዘን ነው፤ የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች ከተሰኙቱ አንዱን - ፅኑዕ ቤትን ያህል ለማነጽ የሚውል ግብአት ነው።

ሌላው ግብሩ ደግሞ የጥፋት ነው። ሞትን ያስጀመረ መግደያ። ቃየል በንጹህ ወንድሙ አቤል ላይ እጁን ቢያነሳ በመዳፉ መሐል ነግሶ

Page 7: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 7ትንታኔ

በመረጃየመጥለቅለቅአደጋንበኃላፊነትናበተዓማኒነትመጋፈጥ

ከመንግሥትና ከሕዝብ መካከል ሆኖ እንደ ዐይን ደግሞም እንደ ጆሮ የሚያገለግለው የብዙኀን መገናኛ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ተገኝቷል። እንደውም የሚፈተንበት ጊዜ ሳይሆን አይቀርም። ምክንያቱ ደግሞ ሁሉም ያሻውን

በአጭር ፍጥነት ለብዙዎች ማድረስ የሚችልበት አውድ በተፈጠረበት ዘመን፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ የሆነውን ነገር አጥርቶ ማቅረብ ወሳኙ ሥራ ነውና። ይህንን ነጥብ አጥብቀው ያነሱት አብርሐም ፀሐዬ፣ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ግዴታን መወጣት

ከመቼውም በላይ የሚያስፈልግበት ጊዜ አሁን ነው ይላሉ።

የሰው ልጆች አግባብ ባለው የአኗኗር ስርዓት የሚኖሩ ሥልጡን እንሰሳት ይባላሉ። በተነጻጻሪነት ነጻና ግብረ ገብ ያላቸው ፍጡራንም ናቸው። የሰዎች ነጻነት ሌላውን ሰው ለጉዳት እስካልዳረገ ድረስ የተዘረጋ ኬላ አልባ ተጓዥ ነው። ሰዎች ለሚሠሩትና ለሚናገሩት ነጻ ናቸው። አስተሳሰባቸውን መሬት የማውረድ ነጻነትን የተጎናጸፉ በመሆናቸው የቱንም የማድረግና የማሰብ ፍላጎታቸው የተጠበቀ ነው።

በዚህም የተነሳ ዓለም በጊዜው ሂደት ውስጥ በመሻሻል ወይም በለውጥ ውስጥ እንድታልፍ ምክንያት ሆኗል። ሰዎች የአፈጣጠር ነጻነታቸውን ተጠቅመው የተሻለ አኗኗር ለማግኘት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አድካሚ ሥራዎችን የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎችን በመፈልሰፍና በእነርሱ በመጠቀም ከቀደሙት ዘመናት አንጻር ይኸኛው ጊዜ ተመራጭ እንዲሆን አስችለዋል፤ የወደፊቱም የበለጠ ይሆናል። በዚህ ሂደት ውስጥ ግኝቶችን ለማሰራጨት፣ በተቃራኒው ደግሞ ለሰው ልጆች ስጋት የሆኑትን ለማሳወቅ እንዲቻል መረጃዎችን የማስተላለፍ ሥራ እንደዋና ተግባር በመታየቱ በሰዎች መካከል ተግባቦት ሊያድግ ችሏል።

ይህም አንዱ ጋር ያለው ሌላው ጋር እንዲገኝ ጠቅሟል፤ የአንዱ ሃብት ለሌኛው ግብዓት ሆኗል። ቋንቋ፣ ርዕዮተ ዓለም፣ ባህል፣ ሐይማኖት ተወራርሰዋል። ግንኙነት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ መረጃ እንደ ትልቅ ሀብት በመቆጠሩ የመረጃ ዘመን (Information Era) ተብሎ እስከመሰየም ተደርሷል። በዚህም ምክንያት የብዙኀን መገናኛዎች ተወልደዋል።

እነዚህ ተቋማት የማኅበረሰቡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዋና የጀርባ አጥንት ሆነው ብቅ ብለዋል። ጋዜጠኝነቱም ዋና ዘዋሪ በመሆን እንደሌሎቹ ሙያዎች ሁሉ መደብ አግኝቶ እያገለገለ ነው። ጋዜጠኝነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጽእኖ በመፍጠር ሕዝብና መንግሥት መካከል የቆመ ከፍተኛ ባለድርሻ አካል ሆኖ እየታየ ያለ ነው። ኃይል ያላቸው መንግሥታት ከተቻላቸው እንዲጠቅማቸው ሲሉ ይቀርቡታል፤ በቻሉት ሁሉ ሊጠቀሙበት የሚሹት ዘርፍ ነው። በገንዘብ የተጠናከሩት ደግሞ አጥብቀው ይፈልጉታል፤ እስከተቻላቸው ድረስ ግን ይሸሹታል። ጉልበተኞች አስፈራርተው ያስቆሙታል።

ጋዜጠኝነት በመፈራትና በመከበር እንደየ አገሩ የፖለቲካ ባህል ሲሳደድ፣ ሲከበርና ሲፈራ እየኖረ ያለ ግዙፍ ዘርፍ ሲሆን፣ የገዳዮችን ዱካ በማጥፋት ጋዜጠኞችን መግደል በየጊዜው እየታየ ያለ ጥሬ ሐቅ ነው። ዓለም ነገሯ ውስብስብ እየሆነ በመጣ ቁጥር የኃይል ተቀናቃኝና ተወዳዳሪ ኃይላት በየቦታው ይታያሉ። እነዚህ አካላት ያለመገናኛ ብዙኀን ድጋፍ የትም እንደማይደርሱ በማመን በጥቅምና በማስፈራራት የብዙኀን መገናኛውን ለመጠቀም ይፈልጋሉ። ሐሰትና ሐሰተኞች በበዙባት ዓለም ተዓማኒነትን፣ ኃላፊነትንና ሰብዓዊነትን ግድ የሚለው የብዙኀን መገናኛ ለመኖር ይቸገራል። ጋዜጠኝነት እስከዛሬም ፈተና ላይ ነው።

ሰዎች በነጻነት እንዲኖሩ ማድረግ የሚቻለው የተሻለ አስተሳሰብና ተግባቦት (communi-cation) መፍጠር ሲቻል ነው። ጋዜጠኝነቱ ይህንን ጉዳይ በግልና በተቋም ደረጃ ይከውናል። የአስተዳደር ብልሹነትን በመጠቆምና በማጋለጥ የተሻሉ ስፍራዎች ሰፊ ቦታ እንዲያገኙ ማድረግ የጋዜጠኝነት ዓላማ ነው። አንድ ጋዜጠኛ ለሚያቀርበው መረጃ የአቅራቢውን ፍላጎት ተንተርሶ አይደለም። ሚዛኑን እስካልሳተ ድረስ ዜናዎች ይሠራሉ፤ የሕዝቡን ፍላጎት ባማከለ ከሥልጣንና ከገንዘብ ጫና ውጪ ሆኖ ተዓማኒ ዜና መሥራት ግዴታ ነው። ጋዜጠኝነት እውነት የሆኑትን ክስተቶች ትክክለኛነታቸውን በማጣራት ይፋ የማድረግ ሙያዊ ግዴታ አለበት። ለዚህም ነው ፈተናው የሚበዛው!

ጋዜጠኝነት ከኃላፊነትና ከተዓማኒነት አንጻር

ጋዜጠኝነት ኃላፊነት ነው። በአንድ አገር ዴሞክራሲን ለማስፈን ከተፈለገ ገለልተኛ (inde-pendent) ሙያውን የጠበቀና (professional) ኃላፊነት የሚሰማው (responsible) ጋዜጠኛና ጋዜጠኝነት ሊኖር ግድ ነው።

ጋዜጠኝነት መረጃ መስጠት፣ ተፈላጊ ጉዳዮችን በመምረጥ መወያያ እንዲሆኑ ማኅበረሰብ ላይ ንቃት የመፍጠርና ክፍተቶች ሲኖሩ ትችቶችን በማቅረብ የሚሠራ ሙያ ነው።

በአንድ አገር ላይ እንደወሲባዊ ጥቃቶች፣ የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ፣ ለሥራ ተብለው በሚቀርቡ ኬሚካሎች የሚጎዱ ሰዎችን የመሳሰሉ ጉዳቶችን መፈተሽና ይፋ ማድረግ ጋዜጠኝነት መሥራት ከሚገባው ሥራዎች መካከል ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚመደቡ ናቸው። ጋዜጠኝነት የተነገረውን ወይም የቀረበለትን ብቻ ለማስተላለፍ የሚሠራ ሙያ አይደለም።

ማርክ ትዌይን እንደሚለው ‹የሕዝብ ትልቁ ችግርና ቅሽምና ጋዜጣ ላይ የወጣን ጉዳይ ሁሉ ማመኑ ላይ ነው።› ይላል። ጋዜጠኝነት ከተሳሳተ ሕዝብ ይሳሳታል። የስህተቱ ውጤት ደግሞ መጨረሻ ላይ የሚያመጣው ጉዳት ይኖራል። የተሸፋፈነ ወይም የተደበቀ ነገር ደግሞ ቀርቶ አይቀርምና ነገሮችን በይፋ በማውጣት የሕዝቡን የማወቅ፣ የመወያየትና መፍትሄው ላይ ተሳታፊ የማድረግ ሥራ እንዲተገበር ማድረግ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው። ይህ ዓይነት አሰራር እንዲበረታታ በማድረግ በአንድ አገር ላይ ከላይ እስከታች ግልጽ አሰራር እንዲሰፍን ማገዝ ይቻላል። የጋዜጠኝነትም ዋንኛው ኃላፊነት ይህ ነው።

ጋዜጠኝነት ተዓማኒነት በእጅጉ የሚጠበቅበት ዘርፍ ነው። የተከሰተን ማንኛውም ጥሬ ሃቅ እንደወረደ ከማቅረብ ወይም ከማስተላለፍ ይልቅ እውነትነቱንና አግባብነቱን ግራና ቀኝ የመፈተሽ፣ ጠለቅ ብሎ በማየትና ዙሪያ ገባውን በመበርበር መነሻና መድረሻውን የማየትና የመገመት ላቅ ያለ ሥራና ዕይታን የሚሻ ሙያ ነው።

ሕዝብ ነገሮችን ወይም ክስተቶችን ከተለያየ አቅጣጫ ማየት እንዲችል መረጃዎችን የመስጠት ብቃት ይጠበቃል። ዓለም እጅግ ውስብስብ ክዋኔዎች የበዙባት ሆናለች። ለሕዝቡ ደግሞ በዚህ ልክ የሚከታተል ጋዜጠኝነት ወይም ብዙኀን መገናኛዎች በኃላፊነትና በተዓማኒነት ካልተሰማሩ በስተቀር ሕዝብ አስተማማኝ መረጃ የማግኘትና በዚህ ላይ ተመስርቶ ትክክለኛ ድምዳሜ ላይ መድረስ ያዳግተዋል።

ተዓማኒነት ሲባልም ነገሮችን በአሉባልታ ሰምቶ ያለማረጋገጫ ለመረጃነት በማብቃትና ከሚገባው በላይ በማጦዝ የጋዜጣ ማሻሻጫ ማድረግ አይደለም። መገናኛ ብዙኀን ተዓማኒነት መፍጠር ይገባቸዋል ሲባል እውነተኛ መረጃዎች

የመረጃ መጥለቅለቅ

የዚህ የጊዜያችን ተግዳሮት ማኅበረሰብ በመረጃ መጥለቅለቅ እየተጎዳ መምጣቱ ነው። የቱ ትክክል የትኛው የተሳሳተ መሆኑን ለመለየት በማይችልበት አደጋ ውስጥ ይገኛል። መረጃዎች የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት አሻጥር ተሸክመው ከእውነተኛው መረጃ ጋር ተደባልቀው ወደ ሕዝቡ ይረጫሉ። ጥቅምን ለማስጠበቅና ሥልጣንን ለማረጋገጥ ሲባል የተሸራረፉ መረጃዎች በብዙኀን መገናኛ በኩል ከላይ ወደታች ይፈሳሉ።

ለዚህ ነው ጋዜጠኝነት በጥቅም ፈላጊዎች ምክንያት ለሕዝብ ሐቅን የማስተላለፍ ተግባሩ አጣብቂኝ ውስጥ እየወደቀ ያለው። የግለሰቦችና የአገራት ሀብት የማፍራት ገደብ የለሽ ፍላጎት የተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል እንዳይኖር አድርጎታል። ተናጥቀህ ብላ በዓለማችን ሰፍኗል። በዚህ መካከል ሰብዓዊነትና የማኅበረሰብ እሴቶች እየተሸረሸሩ ነው።

ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታችሁን እናስከብርላችኋለን በሚል የቡድን መሪዎች እየተፈለፈሉ ነው። ዘረኛ፣ አክራሪና ዋሾ መንግሥታት ቦታ እያገኙ መጥተዋል። እውነቱ ግን ሌላ ነውና ይህ ዓይነት አስተሳሰብ አገር አፍርሷል፤ ለእልቂት ዳርጓል። የተለያየ ፍላጎትና መልክን ይዞ አንድ የመሆን ብዝኀነት (Diver-sity) እየቀጨጨ በመሆኑ በተለይም አፍሪካ የመለያየትና የመነቋቆር እንዲሁም የመገዳደል አደጋ ውስጥ ሆናለች። በዚህም ብዙ ንጹሃንን አጥታለች፤ እያጣችም ነው። ዓለም በቀለም፣ በዘር፣ በአካባቢና በቋንቋ መከፋፈል ውስጥ እየገባች በሄደች ቁጥር የተፈጥሮ ሀብትን የመቀራመት፣ በዚህም ስግብግብነት የሚፈጥረው ግጭት ለአደጋ ይዳርጋል።

ከመረጃና መገናኛ ብዙኀን ሥራ ጋር ተያይዞ በርካታ ምሁራን ጋዜጠኞችንና ሕዝብን ይመክራሉ። በአብዛኛው በመረጃ ደረጃ የሚሰሙ የአናሳ ቡድን መሪዎች፣ የየአገራት መሪዎች፣ እንዲሁም ከነዚህ ጋር የጎንዮሽ ጥቅም ያላቸው ታዋቂና አዋቂ ሰዎች ትርክት ፖለቲካዊ ተዓማኒነትን በመፍጠር ላይ የተመሠረተ ነው። በጊዜያዊነት የሥልጣን መንበራቸውን ለማጠናከር፤ ያቀዱትን የጥቂት ቡድኖችን ተጠቃሚነት ለማስፈን፣ እንደ እቅድ የያዙትን የጥቂት ቡድኖችን የበላይነት ለማስጠበቅ፣ በአብሮ መሆን ውስጥ ያጡትን ጥቅም በመነጠል ለማግኘት ሲሉ የታላቅነት ትርክትን ያነግሳሉ።

ቡድኖቻቸው የተለየና ያልተፈጠረ ዶሴ እንዳለ አድርገው በመግለጥ ያልተጻፈ ያነባሉ። ያልተከሰተ እንደተከሰተ በማድረግ ፍርሃትን ይወልዳሉ ወይም በተቃራኒ የተሻለ ነገ አለ በሚል ቀቢጸ ተስፋ መረጃ በማንሸራሸር ተከታዮቻቸውን ያቅፉበታል። ይህ የመረጃ መጥለቅለቅ አደጋ በወቅታዊ የፖለቲካ ትርክቶች የተሞላ ነው።

የሕዝብን ታሪክ፣ ባህላዊ እሴትና እምነት በመሸርሸር ጥርጣሬን የሚፈጥሩ አደገኛ መረጃዎች እየተፈበረኩ ነው። አሁን ላይ ጋዜጠኝነት ከምንግዜውም በላይ ያስፈልጋል። ያየውን እውነት መሳይ ንግግርና ኹነት ዙሪያ ገባውን ተመልክቶ ካልፈተሸ በስተቀር ራሱም የመረጃ መጥለቅለቁን አደጋ በማባባስ ሕዝብን አቅጣጫ ያስታል። በስተመጨረሻም ማንም የማይጠቀምበት አደጋ ተከስቶ ለፈራጅም ለተፈራጅም አለመብቃት አለና በኃላፊነትና በተዓማኒነት መሥራት ሙያዊ ግዴታ ነው።

አብርሐም ፀሐዬ የተግባቦት ባለሞያና የቢዝነስ አማካሪ ሲሆኑ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ላይ ይገኛሉ።

ተዓማኒነት ሲባል

ነገሮችን በአሉባልታ

ሰምቶ ያለማረጋገጫ

ለመረጃነት በማብቃትና

ከሚገባው በላይ

በማጦዝ የጋዜጣ

ማሻሻጫ ማድረግ

አይደለም

ቢሆኑ እንኳን ከሕግ አንጻር ባለማየት ወይም የሚመጣውን አሉታዊ ውጤት ባለመገንዘብ የተሰማና የታየን ጉዳይ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ በማዋል ተጨማሪ ስህተት ላለመፍጠር መጠንቀቅም ነው።

መረጃዎች የግለሰቦችን ሰብዓዊ መብት በመጣስ የሚሰበሰቡም አይደሉም። ከዚህ በፊት እንግሊዝ ውስጥ ከ168 ዓመታት ቆይታ በኋላ የተዘጋ ጋዜጣን ካስታወስን የታዋቂ ሰዎችና የባለሥልጣናትን ስልኮች በመጥለፍ መረጃዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ጥሶ እየመነተፈ ይፋ ሲያደርግ ሊደረስበት በመቻሉ ነው። በአጠቃላይ ጋዜጠኝነት ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን ተሸክሞ የሚጓዝ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ዘርፈ ብዙ ሙያ ነው። ለዚህ ዓይነት ጥልቅ ዕይታና የማመዛዘን ብቃት ለሚጠይቅ ሥራ ደግሞ ትልቅ አቅም ያለው ጋዜጠኛና ብቃት ያለው በሙያ የተደራጀ የመገናኛ ብዙኀን ያስፈልጋል።

ለመደምደም ያህል ቀደም ባለ ጊዜ አንድ የእንግሊዝ ፖለቲከኛ ያሉትን ጠቅሰን እንለፍ። ‹ፖለቲከኞች ወይም ባለሥልጣናት በብዙኀን መገናኛ ላይ ፍራቻ ካላቸው፣ አንድ የመርከብ ካፒቴንም የገዛ መጓጓዣ ባህሩን እንደፈራው ይቆጠራል።› (“…for a politician to com-plain about the press is like a ship’s cap-tain complaining about the sea.”) ይህም ሲባል ካፒቴኑ የሆነ በራሱ ያልተማመነው ነገር አለ ማለት ነው። በትክክል እየሠራሁ ነው የሚል ሰውም የብዙኀን መገናኛን አይፈራም።

Page 8: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 8

አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ኪሳራ የሚያደርስበት ጉዳይ ነው የሚሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ምሑራኖች ለአዲስ ማለዳ ይናገራሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የመንግስትን አካሔድ በመደገፍ አስተያየት የሚሰጡ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እንደሚሉት በእርግጥ እንዲህ አይነት ነገር በቅርብ አመታት ተደርገው አለመታወቃቸው ግርታን የሚፈጥር ጉዳይ ቢሆንም ቅሉ የተደረገው ግን ፖሊስ ለሕዝብ ዘብ እንደመሚቆም እና የትኛውንም አገር እና ሕዝብ ጠላትን ለመመከት እንዲሁም አጥፊዎችን ላለመታገስ አቋም የሚግልጽበት እንጂ ሌሎች እንደሚሉት አይነት አንደምታ የለውም ሲሉ ይናገራሉ። በትርዒቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድም ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የተወጣጣው እና ስብጥሩ አገርን ለመጠበቅ ጠንካራ ዘብ የሚያደርገው ይኸው ፖሊስ ስብስብ የተጀመረውን ለውጥ ከዳር ለማድረስ አገርን እና ሕዝብን በመጠበቅ ዜጎች ነግደው ሚያተርፉበት፣ ስለነገ የሚያልሙባትን አገር እንዲፈጥሩ እንደሚያደርጉ አውስተዋል።

ከየትኛው የፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ እና አገርን እና ሕዝብ ለመጠበቅ ብቻ የቆመ ኃይል መሆኑንም ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረው፤ ዝናብ እና ቁር ፣ ሐሩር ሳይበግራቸው አገርን ለመጠበቅ ለሚተጉ የፖሊስ አባላትም የፌደራል መንግስት ምስጋና እንደሚያቀርብም ተናግረዋል።

የትርዒቱን አላማ በተመለከተ ለአዲስ ማለዳ አስተያየታቸውን የሰጡ ግለሰቦች እንደሚናገሩት ፌደራል መንግስት በክልሎች ላይ እየተካሔደ ያለውን የልዩ ኃይል ፖሊስ ስልጠና እና በብዛትም በጥራትም ከመጨመር ጋር ተያይዞ ስጋት ቢጤ ሳይገባው እንዳልቀረ ይናገራሉ። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከሰልፉ አንድ ቀን አስቀድሞ በመስከረም 18/2012 በሸራተን አዲስ በተካሔደው ውይይት ላይ የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሐት ካሚል በአጽንኦት የክልል መንግስታት ውስጥ የሚገኙ ልዩ ኃይል አባላት ከፌደራል ፖሊስ ጋር በትጥቅ እና በሌሎች ተያያዥ ትጥቆች ያነሰ እንደሚሆን እና ይህም የማያከራክር ጉዳይ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

በአጭር ጊዜ ልዩነት ውስጥ ከፍተኛ ሆነ ወታደራዊ ትርዒት ማካሔዱ ግርምትን የሚያጭር እና መንግስት ምን አይነት መልዕክት ወደ ሕዝብ ሊያስተላልፍ እንደፈለገ ማወቅ እንዳልተቻለም አስተያየት ሰጪዎች ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሰላም እና ደኅንነት ባለሙያዎች ለአዲስ ማለዳ ሲናገሩ እንደገለጹት ‹‹ሰላምን ለማምጣት እና ለማስከበር በሚል በመንግስት በኩል እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ለመገምገም ወይም ለማድነቅ ያለንበት ሁኔታ የሚፈቅድ አይደለም። በበርካታ አካባቢዎች ያለውን መፈናቀል እና ግድያ እየተመለከትን ባለንበት ሁኔታ አሁን ላይ የፖሊስ ጠንካራ አቋም ለማሳየት ትርኢት

ባሳለፍነው ሳምንት መስከረም 19/2013 ማለዳ ላይ ከአንድ ትውልድ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ነበር መስቀል አደባባይ አሸብርቆ የዋለው። ምናልባትም አፍ አውጥቶ ቢናገር ስፍራው ራሱ አብዮት አደባባይ ነኝ የሚል ምላሽም የሚሰጥ ይመስላል በቀድሞው ስያሜው ለመጠራት እየዳዳው።

በዓይነቱ ልዩ ሆነው ዝግጅት ደግሞ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት የተለያዩ ትርዒቶችን ማሳየታቸው ደግሞ በእርግጥም ከብቃታቸው እና ከአስደማሚ ልምምድ ብቃታቸው ባለፈ ምንድነው ሊተላለፍ የፈለገው መልዕክት ከመንግስት ወገን የሚሉ ጥያቄዎችን በስፋት ሲያስነሳ እና ይህንንም ተከትሎ በመገናኛ ብዙኃንም ሲተላለፉ ነበሩ ጉዳዮች ተሰምተዋል። ይሁን እንጂ ከወታደራዊው መንግስት ከስልጣን መወገድ ወዲህ እንዲህ የተደራጀ እና ሰፊ ሽፋን የተሰጠው የአገሪቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የተገኙበት የፖሊስ የሰልፍ እና ልዩ ልዩ እንቅስቃሴ ትርኢት ሲካሔድ ይህ የመጀመሪያው ነው።

‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› በሚል መሪ ቃል የተካሔደው ይኸው ትርዒት የፌደራል ፖሊስ በተለያዩ ምድቦቹ እና የኃይል ክፍሎች ያለውን ኃላፊነት እና ስራ በተግባር ያሳየበት ትዕይንት ነበር። ብሎኬትን በጭንቅላት ከመስበር እስከ ከ12ኛ ፎቅ እስከ መዝለል፤ ከኮማንዶ ትርዒት እሳት ላይ እስከመገለባበጥ የመሳሰሉት ጉዳዮች የታዩበት ደማቅ ክብረ በኣልም ነበር።

ይሁን እንጂ ለዛሬ ጽሑፋችን መነሻ ያደረግነው በርካታ መልኮችን የያዘው ይኸው የፖሊስ ወታደራዊ ትዕይነት እንዴት በአሁኑ ወቅት ያውም ምርጫ ደርሷል በሚባልበት ወቅት መደረጉ ጉዳዩን ከድጡ ወደ ማጡ የሚያስገባ ጉዳይ አይሆንም ወይ የሚሉ የፖለቲካ ምሁራኖች እዚህም እዛም እየተከሰቱ ነው። በተለይም ደግሞ የፖለቲካ ምህዳሩን አስፍተናል በሚል ሰፊ ስራ እና የፖሮፖጋንዳ ጭዋታዎችን ሲያቀነቅን ለነበረው የለውጡ ኃይል በዚህ ወቅት ይህን ጉዳይ ማድረጉ እጅግ የፖለቲካ ኪሳራ የሚያደርስበት እና በዓለም

‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር››

Page 9: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 9

ወደ ገፅ 15 ዞሯል››ወደ ገፅ 14 ዞሯል››

ከማድረግ ይልቅ በተግባር የተወሰዱ እርምጃዎች እየተገመገሙ ሕዝብም ቢያያቸው መልካም ይን ነበር ›› ሲሉ ይናገራሉ። አያይዘውም ይህን አይነት ድንገተኛ የወታደራዊ ትርዒት ማካሔድም በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥን እንደሚፈጥርም አልሸሸጉም።

ዓለም አቀፋዊ ትርጉሙ የወታደራዊ ትርኢት ጽንሰ ሀሳብ እንደሚተነተነው ሴቶች እና ወንዶች የወታደራዊ አባላትን በአንድ ደምብ ልብስ በማልበስ እና በሕዝብ ፊት በማሰለፍ ከሕዝብ ድጋፍን እና ከበሬታን በመልካም ጎን የሚሰጥንም አመለካከት ለመግኘት ያለመ ሀሳብ እንዳለው ባለሙያዎች ይተነትናሉ። ሚሊታሪ ቤኔፊተሰ ኢንፎርሜሽን ተሰነው ድረ ገጽ እንደሚያመለክተው በቀደሙት ጊዜያት በአገረ አሜሪካ እንዲህ አይነት ወታደራዊ ትርኢቶች ይደረጉ እንደነበር እና ይህም የተለመደ ጉዳይ እንደሆነም ያትታል። ይሁን እንጂ በአገራችን ኢትዮጵያ ይህን አይነት ውታደራዊ ትርኢት ስንመለከት ለአብዛኞቻችን በተለይም ደግሞ ወጣት የዕድሜ ክልል ውስጥ ላለው አዲስ እና እንግዳ ነገር እንደሚሆንበት አይጠረጠርም። በእርግጥ በወታደራዊ ትርኢት ወቅት በኢትዮጵያ ቀደም ባሉ ጊዜያት ከሚታየው የወታደራዊው ሰልፍ ባሻገር ለሕዝብ እና ለአገር ሚታየው ከቀላል ሩሲያ ስሪት ክላሽንኮቭ መሳሪያ እስከ ከባባድ መሳሪያዎች ድረስም ለዕይታ የሚቀርቡበት ሁኔታም ነበር።

በካፒታሊስቶች ምድር አሜሪካ ይህን አይነት ሰልፍ እና ትርኢት በማካሔድ ተቀናቃኝ እንዳልነበራት እና በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኮሪያ እና ሌሎች ጥቂት አገራት ላይ የሚታየውን እና አምባገነኖች መለያ ነው እስከ መባል የደረሰውን የወታደራዊ ሰልፍ እና ትርኢት በሚገባ ይካሔድባት ነበረ ግንባር ቀደም አገርም እንደሆነች ይነገራል። አንድን ክብረ በዓል መሰረት አድርጎ እንደሚካሄድ ታሪክ ድርሳናት እንዲሁም የወታደራዊ ትርኢትን በሚገባ የሚተነትኑ ዓለም አቀፋዊ ሰዎች ቢናገሩም በኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በመስከረም 19/2013 የተካሔደው ይኸው በፌደራል ፖሊስ በኩል የተካሔደው ይኸው ሰልፍ ግን ምንን መሰረት ያደረገ እንደነበር አለመታወቁም በርካታ ሰዎች ዘንድ ቅሬታን ሲያቀርቡ ነበር። አዲስ ማለዳ ከትርኢቱ አንድ ቀን አስቀድማ ባደረገችው ምልከታ ለኹነቱ የሚደረጉ ጥበቃዎችን እና ጥንቃቄዎችን በሚገባ ተመልክታለች በዚህም እጅግ አድናቆትን የሚስቸር ጉዳይ እንደሆነ ለማየት ተችሏል። ይሁን እንጂ በአንጻሩ የድንገተኛ ሕመምተኞች ማመላለሻ አሙቡላንሶች ግን እንዳያልፉ ሲከለከሉ እና ወደ መጡበት አቅጣጫ ሲመለሱም ለመታዘብ ችላለች። ይህ ደግሞ የሰልፉ አላማ እና መሪ ቃል ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› በሚል የተሰናዳውን ዝግጅት ጋር በጠና የታመመን እና ታማሚውን ይዞ ሚከንፈውን አምቡላንስ ማስመለስ ጋር የተደረገውን ውሳኔ እንዴት ማስታረቅ እንደሚቻል ምላሽ የሚያሻው

ጉዳይ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ ማለዳ በድንገት ጥያቄ ካቀረበችላቸው ግለሰቦች መሰብሰብ እንደቻለችው አስተያየት ሰጪዎች ረቡዕ መስከረም 20/2013 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሔደው የፖሊስ ትርኢት በትግራይ ክልል በክልሉ ልዩ ኃይል በተደጋጋሚ የተደረገውን ሰልፍ ምላሽ ለመስጠት ይመስላል የሚል ምላሽ የሰጡም አልታጡም። አስተያየት ሰጪዎች በአንድ በኩልም የፌደራል መንግስት እያደረገ ያለውን የፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላትን የማደራጀት እና የመገንባት ሒደቱን አድንቀው ነገር ግን ከክልሎች ጋር እልህ መጋባትንም ቢያቆም መልካም እንደሆነ ምክረ ሀሳባቸውን ገልጸዋል። ‹‹እኔ በግሌ ፈርቼ ነበር›› የምትለን አስተያየት ሰጪያችን እንደ እኔ አይነት በርካታ ሰዎችም እንደሚኖሩ እና በተደረገው ሰልፍ ፍርሀት እንደተሰማትም አልደበቀችም። ሕዝብን ደኅንነቱ የተረጋገጠ እንዲመስለው እና በእርግጥም ጠንካራ ፖሊስ ኃይል መገንባቱን ለማሳየት የተደረገውን ሰልፍ እና ትርኢት በአደባባይ ባይደረግ እና ለሕዝብ የደኅንነት መረጋገጥ ተብሎ ሕዝብን ስጋት ውስጥ መክተት ተገቢ እንዳልሆንም ይናገራሉ።

አዲስ ማለዳ ካነጋገረቻቸው መንገደኞች እና አስተያየት ሰጪዎችም አንደምታው ምን ይመስላል በሚል ለመለሱት ጥያቄ በበቅርቡ በቀድሞው ምክር ቤት አባል አስመላሽ ወልደስላሴ አማካኝነት የትግራይ ክልል ከመስከረም 25/2013 ጀምሮ ከፌደራል መንግስት የሚወጡ ትዕዛዛትን እንደማይቀበሉ ይፋ መደረጉን ተከትሎ የተላለፈ መልዕክትም ይሆናል ሲሉም መላ ምታቸውን ያስቀምጣሉ።

በርካታ መልኮችን የያዘው የፌደራል ፖሊስ የሰልፍ ትርኢት በርካታ መላ ምቶች የተስተናገዱበት ቢሆንም በመንግስት በኩል ግን በተለይም ደግሞ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው የተላለፈው መልዕክት በመንግስት በኩል ያለው አቋም እና ሁሉን አቀፍ ለውጥ እያካሔደ የሚገኘውን የፌደራል ፖሊስ አባላትን እና ተቋም የሚያሞካሽ ነበር።

እና ለአገር››

Page 10: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 10

Page 11: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 11

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ቸርችል ጎዳና አካባቢ በሚገኙ ባለቤታቸው በውል የማይታወቁ ሁለት ሕንፃዎች በካሬ ከ300 እስከ 400 ብር እየከፈለ ለዐሥር ዓመታት መከራየቱ ታወቀ።

አዲስ ማለዳ ሕንፃዎቹ በሚገኙበት አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በአካል በመገኘት ሁለቱ ባለ አራትና ስምንት ፎቅ ሕንፃዎች በአንድ ግለሰብ ባለቤትነት ሥር እንደሆኑና ባለቤቱም በውል እንደማይታወቁ አረጋግጣለች።

ኢትዮ ቴሌኮም ባለ አራት ፎቁን ሕንፃ ከዛሬ ዐሥር ዓመት በፊት በጊዜው ለነበረው “ትርንስፎርሜሽን ፕሮግራም ኦፊስ” እንዲሁም ባለ ስምንት ፎቅ ሕንፃውን ደግሞ ከአምስት ዓመት በፊት ለጥሪ ማዕከልነት እንደተከራየው ለማወቅ ተችሏል።

የሕንፃዎቹን ባለቤት ኃይለሥላሴ እንደሚባሉ እና ከሥማቸው ውጭ በፎቶም ሆነ በአካል አይተዋቸው እንደማያውቁ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ሕንፃዎቹን ኢትዮ ቴሌኮም ከተከራያቸው ረጅም ጊዜ ስለሆነው እና ሕንፃዎቹንም የሚያስተዳድረው ኢትዮ ቴሌኮም ስለሆነ ኢትዩ ቴሌኮም ገዝቷቸዋል እስከማለትም ደርሰው እንደነበር አክለዋል።(1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011)

በ10 ዓመታት ውስጥ 261 ጋዜጣና መጽሔቶች ከኅትመት ውጭ ሆነዋል

ከየካቲት ወር 2001 እስከ ኅዳር 2011 ባሉት አሥር ዓመታት ውስጥ 288 ጋዜጣና መጽሔቶች ፍቃድ ቢወስዱም 27 ብቻ ኅትመት ላይ እንዳሉ ታወቀ። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለአዲስ ማለዳ እንደገለጸው ከ2001 ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ውስጥ 87 ጋዜጦች እና 174 መጽሔቶች በተለያዩ ምክንያቶች ከኅትመት ውጭ ሆነዋል።

የባለሥልጣኑ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ገብረ ጊዮርጊስ አብርሃ የኅዳር ወር መረጃን መሠረት በማድረግ ‹‹ቁጥራቸው በየወሩ ልዩነት ቢያሳይም በኅዳር ወር 27 የተለያየ ይዘት ያላቸው የኅትመት ሚዲያዎች ብቻ ናቸው ገበያ ላይ የዋሉት›› ብለዋል።

አያይዘውም የተጠቀሰው አኀዝ የሚያመለክተው የብሮድካስት ባለሥልጣን ቁጥጥር በሚያደርግባቸው አዲስ አበባ እና ክልሎች ላይ የስርጭት አድማስ ያላቸውን የኅትመት ሚዲያዎች እንጂ ክልላዊ ጋዜጦችና መጽሔቶን አይጨምርም ብለዋል።

ለኅትመት መገናኛዎቹ መክሰም በባለሥልጣኑ እንደ ምክንያት የተዘረዘሩት የኅትመት ዋጋ መጨመር፣ የመረጃ እጥረት፣ የቤት ኪራይ መጨመር እና ማስታወቂያዎች በጥቂት የመገናኛ ኅትመቶች ቁጥጥር ሥር መውደቅ ናቸው።

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደኅንነት መረጃ ማዕከል በተደጋጋሚ ቁጥራቸው የበረከቱ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን እና ግብይቶችን በመረጃ አስደግፌ ለሚመለከተው አካል ባቀርብም እርምጃ አልተወሰደልንም ሲል ወቀሰ።

ማዕከሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በሥልጣን ላይ እያሉ በተደጋጋሚ ‹‹የሕገ ወጥ ዝውውሩን እና ግብይቱን ምንጮች በተጨባጭ መረጃ አስደግፌ ሪፖርት ባደርግም ምላሽ ሳይሰጠኝ ቀርቷል›› ብሏል። በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን ሕገ ወጥ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገራት ገንዘቦች ዝውውር አስቀድሞ መከላከል ይቻል ነበር ሲሉ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኪዳነማሪያም ገብረፃዲቅ መግለፃቸውን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተስፋየ ዳባ ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል። አሁንም ቢሆን የተደራጁ መረጃዎችን ወደ እርምጃ የመቀየር ክፍተት መኖሩን ዋና ዳይሬክተሩ ለቋሚ ኮሚቴው አሳውቀዋል።(ቅጽ 1 ቁጥር 13 የካቲት 2 ቀን 2011

የአዲስ አበባ አስተዳደር በሰንዳፋው ቆሻሻ ማስወገጃ ላይ ፍላጎት የለውም ተባለከአዲስ አበባ አስተዳደር በ37 ኪሎ ሜትር

ርቀት ሰንዳፋ ላይ ተገንቶ የነበረውና በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ገጥሞት ሥራ ያቆመው ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ላይ ብዙም ፍላጎት እንደሌለው ታወቀ፡፡

አዲስ ማለዳ ከአንድ የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እንደሰማችው አስተዳደሩ በተቃውሞ የተቋረጠውን ማስወገጃ ወደ አገልግሎት የመመለስ ፍላጎት የለውም፡፡

የአዲስ ማለዳ ምንጭ እንዳሉት አንድ የአሜሪካ ኩባንያ በስፍራው ጥናት እያደረገ ይገኛል። በጥናቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴርም እየተሳተፈ ስለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ጥናቱም ከዚህ ቀደም የተደፋው ቆሻሻ በአካባቢው ላይ ተፅዕኖ ይሩረው፣ አይሩረው ለማወቅ እና መፍትሔውስ ምንድን ነው የሚሉትን ለመለየት የሚካሄድ ነው ተብሏል፡፡

አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ የወጣበት ‹‹የሰንዳፋ ዘመናዊ የቆሻሻ ላንድ ፊል›› ከፈረንሳይ መንግሥት በተገኘ ገንዘብ የተገነባ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡ ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011

በጋምቤላ በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የወሊድ መቆጣጠሪያ ተጠቃሚዎች

ቁጥር በ13 በመቶ ቀነሰበጋምቤላ ክልል ባለፉት ኹለት ዓመታት

ሲከሰቱ በነበሩ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት የጤና አገልግሎቶችን ባግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ባላመቻሉ ከኹለት ዓመት በፊት 33 በመቶ ደርሶ የነበረው የወሊድ መቆጣጠሪያ ሽፋን በ13 በመቶ በማሽቆልቆል 20 በመቶ ደረሰ።

በፀጥታ መደፍረስ አማካኝነት በከተሞች እና በወረዳዎች መሠራት የነበረባቸው የሥነ ተዋልዶ ሥራዎችን እንደልብ ተንቀሳቅሶ ለማከናወን አለመቻሉ መሰረታዊ ምክንያት ይሁን እንጂ፣ የተለያዩ ችግሮች ለሽፋኑ መቀነስ ምክንያት እንደሆኑ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ካን ጋልዋክ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።(ቅጽ 1 ቁጥር 48 መስከረም 24 2012

አዲስ ማለዳ እስከ መቶኛ እትም ስትጓዝ ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን ቀደማ ለኢትዮጵያውያን ካስነበበቻቸው እና ምርመራ በማድረግ ካቀረበቻቸው አቦል ዜናዎች መኸል ደግሞ ለትውስታ እንዲሆን ከበርካታዎቹ መኸል የሚከተሉትን አቀርበንላችኋል፡፡

“ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ”በሚል

ስያሜ ውሕድ ፓርቲ ሊሆን ነው

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕዴን) በትጥቅ ትግል ላይ እያሉ በትግራይ በረሃ በ1981 የመሰረቱት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ (ኢብፓ)/ Ethio-pian Prosperity Party (EPP) ሊባል እንደሆነ አዲስ ማለዳ ከታማኝ ምንጮች ሰማች።

በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ፍልስፍና ሲመራ የቆየው ኢሕአዴግ የአፋር፣ የጋምቤላ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የሶማሌና የሐረሪ ክልል ገዢ ፓርቲዎችን በማቀፍ አንድ ወጥ ፓርቲ ሆነው ለመውጣት የፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብና ለኢትዮጵያ ብልጽግናን ያመጣሉ ተብለው ተስፋ የሚጣልባቸውን የፓርቲውን ፖሊሲና ስትራቴጂዎች በወጣት ምሁራን በማስረቀቅ ሒደት ላይ መሆኑን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ያረጋግጣሉ።

ከመስከረም 8 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በጉባዔው አብዮታዊ ዴሞክራሲን በመተካት የአዲሱ ፓርቲ የፖለቲካ ፍልስፍና ይሆናል በተባለው የመደመር የፖለቲካ ቀመር ላይ ውይይት እየተደረገ እንደሆነም አዲስ ማለዳ ማረጋገጥ ችላለች። የመደመር ፍልስፍና ላይ በባህር ዳር፣ በአዳማ እና ሐዋሳ ከተሞች ላይ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ወጣቶችንና ምሁራንን ያሳተፈ ዝግ ስብሳባ እየተደረገ ይገኛል።(ቅጽ 1 ቁጥር 46 መስከረም 10 2012)

በወለጋ የንግድ ባንክ ዝርፊያ ጋር በተያያዘ ቅጣት ተጥሎባቸው የነበሩ ግለሰብ

ሹመት ተሰጣቸውየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታኅሣሥ 18/2011

በጊምቢ ቅርንጫፍ ከተፈጸመው የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ዝርፊያ ጋር በተያያዘ ያልተገባ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሎ ቅጣት ተጥሎባቸው የነበሩትን ካሳሁን ሽፈራው የኦፕሬቲቭ ሪሌሺንሺፕ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙ ጥያቄ አስነሳ።

በተለይም ያለ ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት እውቅና እንዲሁም ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ዘረፋው በተፈፀመበት ዕለት ጠዋት ላይ የጊምቢ ቅርንጫፍ እንደ ʻኢሹʼ ቅርንጫፍ - ማለትም በአካባቢው ከሚገኙ ቅርንጫፎች ብር ለማሳደር - እንዲያገለግል ትዕዛዝ መስጠታቸው ተረጋግጦ እያለ ሹመት መሰጠቱ ውዝግብን ፈጥሯል።

በተጨማሪ በታጣቂዎች ገንዘቡ በተዘረፈበት ቀን 9 ሰዓት ከ45 ላይ ያለበቂ አጀብ ገንዘቡን አልሰጥም ያሉትን የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን ደሳለኝ ረጋሳን በስልክ ገንዘቡን ለዳሌ ቅርንጫፍ እንዲሰጡ ማዘዛቸውን ካሳሁን አምነው ቢቀጡም ተጨማሪ ሹመት መሰጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ ከባንኩ የሰው ሀብት ክፍል ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ገልፀዋል።(ቅጽ 1 ቁጥር 23 ሚያዚያ 5 ቀን 2011

Page 12: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 12

Page 13: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 13

Page 14: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 14አንደበት

አዲስ ማለዳ ላለፉት 100 ሳምንታት ያለማቋረጥ በየሳምንቱ ቅዳሜ ማልዳ ለአንባቢያን ስትቀርብ ቆይታለች፤ እነሆ ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2013 100ኛ እትሟ ሆነ። አሐዱ ብላ ስትጀምር በገባችው ቃል መሠረትም ሙያዊ ሥነ ምግባር ሳይጎድልባት፣ የተለያዩ ሐሳቦችን እያስተናገደች፣ ቃሏን ጠብቃ እዚህ ደርሳለች። ዛሬ ካደረሳት መንገድ ይልቅ የሚቀራት ብዙ መሆኑ እሙን ነው። አሁን ግን መቶኛ ሳምንቷን፣ መቶኛ እትሟን ምክንያት በማድረግ አረፍ ብላ በትውስታ የቀደመውን ልታስቃኛችሁ ወድዳለች።

‹‹ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መፍጠር የነዐቢይ ብቻ ኀላፊነት ሳይሆን የእኛም

ጭምር መሆኑን እንዲረዱም፣ እንዲያምኑም እንፈልጋለን።››

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ

(ኢዜማ) መሪ

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላችሁ ብዙ ጊዜ ይወራል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ አጋጣሚ በሕዝብ በቀጥታ የሚመረጥ መሪ እንዲኖር እንደሚፈልጉ የተናገሩበት አጋጣሚም አለ። በዚህ ዓይነት አብሮ በአንድ ፓርቲ ውስጥ የመሥራት አጋጣሚው ይኖረናል ብለው ያስባሉ?

የእኛ ፍላጎት ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊ አገር እንዲኖር ነው። ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ አገር በአንድ ፓርቲ ላይ ተመስርቶ አይሆንም። ኹለት ሦስት ጠንካራ፣ መወዳደር የሚችሉ፣ የተለያየ አመለካከት ያላቸው፣ አማራጭ ማቅረብ የሚችሉ ፓርቲዎች መኖር አለባቸው ብለን እናምናለን። ጠንካራ የተቃዋቀሚ ድርጅቶች ያስፈልጋሉ።

ከነዐቢይ ጋር ለዘለቄታው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ አብረን እንሰራለን። ምክንያቱም የጋራ አገር ነው ያለን፣ አገር በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ከተበጠበጠ ሁላችንም ነው የሚጎድልብን። ይህንን የለውጥ ሒደት ትክክለኛው ቦታ ላይ አድርሶ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መፍጠር ካልቻልን አማራጩ ሌላ አንባገነን ማምጣት ሳይሆን የአገር መፍረስ ሊያጋጥም ይችላል፤ ጉዳዩ ቀላል አይደለም።

እኛ የምናየው በረጅም ጊዜ ጠንካራ መደላድል ላይ የሚቆም ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዴት እንፍጠር የሚለውን ነው። ይሄን ከሚያስቡ ኃይሎች ጋር በመመካከር የጋራ ስርዓት የማቆም ኀላፊነት አለብን።

አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መፍጠር የነዐቢይ ብቻ ኀላፊነት ሳይሆን የእኛም ጭምር መሆኑን እንዲረዱም፣ እንዲያምኑም እንፈልጋለን።

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

‹‹አፋር ከኢትዮጵያዊነት ውጪ ሌላ ማንነት የለውም።››

ዶ/ር ኮንቴ ሞሳ

የአፋር ሕዝቦች ፓርቲ ሊቀመንበር

የብሔርተኝነት ማቆጥቆጥ አፋር እምብዛም አይታይም። የዚህ መሠረቱ ምንድን ነው?

አፋር “ግብዝ” ነው። ያለእኛ ኢትዮጵያ የለችም፤ እኛም ያለኢትዮጵያ የለንም ይላል። ስለዚህም እኛ ጋር የሚኖረው ሕዝብ ወገናችን ነው ብሎ ያምናል። በአፋር ባሕል ውስጥ እሴቶች አሉ። ለምሳሌ በአፋር ነፍሰ ገዳይ አይገደልም፣ እስር ቤትም የለም። ምክንያቱም “ነፍስ ከሁሉ በላይ ክቡር ናት፤ ከፈጣሪ በቀር ነፍስ የማጥፋት መብት ያለው ሰው የለም” ብለው ያምናሉ። ይህ ለአፋር ሕዝብ መሠረታዊ ፍልስፍና ነው። አብሮ የመኖሩ ነገር ለየት ያለው ከዚህ የተነሳ ነው።

በተጨማሪም የአፋር ሕዝብ አብሮ እንጂ እንደ ግለሰብ መኖር የሚችል አይደለም። አካባቢው አደገኛ ነው፤ በረሃ ነው፤ ሀብትንም መጋራት አለ። ሕዝቡ እንጂ ክልሉ ለየት ያለ ስርዓትና አስተዳደር ኖሮት አይደለም።

በሙዚቃችንም “አገር ብርሃን የላትም፤ ምድር ብርሃን የላትም፤ ብርሃኗ ሕዝቧ ነው” የሚባል ነገር አለ። ይህ ከትውልድ ትውልድ ሕጻናት ሲዘምሩት የሚያድጉት ነው።

ሌላው ለኢትዮጵያ ብዙ የተከፈለ መስዋዕትነት አለ። ቱርክ፣ ግብጽን፣ ፖርቱጋልና አረቦችንም ከመመለስ ታሪክ አንጻር ብዙ ያልተዘመረላቸው ናቸው። ለእኛ ኢትጵያዊነትን የሚሰጥ ሰው የለም ይላሉ። አንድ ግመል እየነዳ የሚሔድ ሰው የኢትዮጵያን ባንዲራ አድርጎ በረሃ ሲያቋርጥ፤ አንዳንድ ሰዎች እንዴት ክብር ያለውን ባንዲራ አንገቱ ላይ እንደጨርቅ አንጠልጥሎ ይሔዳል ይሉታል። አፋሮች የሚሉት “አገራችን እኛን መስላ የምትኖር ናት” ነው። እኛ ተንቀሳቃሽ ነን፤ አንድ ቦታ የሚኖር ሰው ይኖራል፤ እኛ ግን ስለምንሔድና ተጓዥ ስለሆንን በሔድንበት አብራን ታድራለች የሚል እሴት አላቸው።

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

‹‹በማዕከላዊ ጥፊ፣ ድብደባና ማስፈራራት ይካሔድብኝ ነበር።››

ኦኬሎ አኳይ ኦቻላ

የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር

በማዕከላዊ ያለፉበት ሁኔታ ምን ይመስል ነበር፤ የክስ ሂደቱስ?በማዕከላዊ ጥፊ፣ ድብደባና ማስፈራራት ይካሔድብኝ ነበር። በመጀመሪያ በአገር ክህደት ሊከሱኝ አስበው ነበር በኋላ ላይ ግን ሽብርተኛ ብለውኝ ቂሊንጦ እስር ቤት ወረወሩኝ። መቀመጫዬ ላይ በርግጫ የተመታሁት ለበሸታ (Perianal Festula) ዳርጎኛል። ኖርዌይ ከተመለስኩ በኋላ ዶክትር ለማግኘት አንድ ዓመት ፈጅቶብኝ ኹለት ጊዜ ኦፕራሲዮን አድርጌያለሁ።ቂሊንጦ ክስ የተመሠረተብኝ በሽብርተኝነት ነው። ራሳቸው የሠሩት ሥራ እና የፈጸሙትን ግድያ ነው ወደ እኔ ያስተላለፉት። ብዙ ክስ ነበረብኝ። የሽብር ክሱ ከግንቦት 7 ሊቀ መንበር ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ከኦነጉ ሊቀመንበር ከዳዉድ ኢብሳ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን) ሊቀ መንበር በሬ አግድ እና የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋዴን) ሊቀመንበር አፒ ኡጁሉ ጋር አሲረሃል በሚል ነው። በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን መሪ ዴቪድ ያውያው ጋርም ግንኙነት በመፍጠር መንግሥት ለመገልበጥ በማቀድ ተከስሻለሁ።በክስ ሒደቱ ጠበቃ አልፈልግም አልኩኝ፤ መንግሥት የሾመው ጠበቃ መከሰስ የለባቸውም አለ። ደቡብ ሱዳን ነው የተያዙትና ወደዚያው መልሷቸው አለ። ይህን በማለቱም ጠበቃው ከሥራው ተባረረ።ከዛ በኋላ አምሃ መኮንን ጠበቃ ሆነልኝ፤ ኖርዌይ ኤምባሲ እየሔደ ሥራው ተጀመረ።ከኹለት ዓመት ክርክር በኋላ በ2008 የሽብር ክሱ ውድቅ ተደረገ። ከዛ ደግሞ ጋምቤላን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል አሲረሃል በሚል በወንጀለኛ አዋጅ ቁጥር 241 መሰረት ዘጠኝ ዓመት ተፈረደብኝ፤ ወደ ቃሊቲ ገባሁ።የእስር ቆይታዬ በድምሩ ሦስት ዓመት ከ11 ወር ነው።[ጠቅላይ ሚኒስትር] ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሥልጣናቸው በፈቃዳቸው ከመልቀቃቸው አንድ ቀን በፊት ተፈታሁ። ፓስፖርቴ እስር ቤት ስለጠፋ ጊዜያዊ ፓስፖርት የኖርዌ ኤምባሲ ሰጥቶኝ ወዲያውኑ ወደ ኖርዌይ መልሶኛል።

ቅጽ 1 ቁጥር 51 ጥቅምት 15 2012

‹‹ፖለቲከኛው ሊያብድ ይችላል፤ ሕዝብ ግን ሕዝብ ነው።››

አባ ዱላ ገመዳ

በአብዛኛው ባለሥልጣናት የትምህርት ሚኒስትር ሆነውም፣ ልጆቻቸው አገር ውስጥ ከሚያስተምሩት የማያስተምሩት ይበልጣል ይባላል፤ እርስዎ እንዴት አገር ውስጥ ለማስተማር ወስኑ?ልጆች ወደ ውጭ ሲሔዱ ኹለት ነገር ይጎድላቸዋል ብዬ አምናለሁ። ይሄን ሌላው ላያምንበት ይችላል። ልጆችን ልጅ የሚያደርገው የቤተሰብ ፍቅር ነው። ማንነታቸውን የሚገልጸው ቤተሰባቸው ነው። ማንም ሰው ለትምህርት በሔደበት አገር በሙያ የሚጨምረው ትንሽ ነው፤ ይዞት የሚያድገው ዋናው ባህሪ ቤተሰቡ ጋር የፈጠረው ነው።ስለዚህ ከአገር በተለዩ ቁጥር ከቤተሰብ ፍቅራቸውና ከቤተሰብ ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ ከሰውም ጋር ያላቸው አጠቃላይ ነገር ይዘበራረቃል። ይሄን በጽኑ አምንበታለው። ብዙ ዕድል ነበር፣ ትንሽ ደግሞ በራሴ አይቻለሁ። የመጀመሪያ ልጄን ልኬ አይቼዋለሁ፤ መልሼዋለሁ። በትንሹ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አገር ውስጥ መጨረስ አለባቸው።ኹለተኛው አገርን ይረሳሉ። የኔ ልጆች አገርን ዕወቅ ፕሮግራም ነበራቸው። አሁን ትንሽ የጸጥታ ችግር ስለሆነ ነው ያቆሙት። አንድ ክረምት ጎጃም፣ ጎንደር ሔደዋል፤ አይተዋል። ማንም የሚቀበላቸው የለም። እናታቸው ናት ይዛቸው የምትሔደው። በራሳቸው ሆቴል ይይዛሉ፣ ታክሲ ይዘው ይንቀሳቀሳሉ፤ ይመጣሉ፣ ይሔዳሉ፣ ያያሉ። ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢም ብዙ አይተዋል፤ ሐዋሳም ሌሎችንም። ለመዝናኛ አይደለም፤ ማወቅ ስላለባቸው ነው። ትግራይ ሔደዋል፤ በደንብም አይተውታል። አሁን መጨረሻ ጅግጅጋ ሊሔዱ ሲሉ ነው የጸጥታ ችግር የተፈጠረው።ይሄ ለምንድነው፤ አገር ውስጥ ስለኖርሽ ብቻ አገርን አታውቂም። እዚህ ሆኖ ሰዉ በጣም ያወቀው ስለአሜሪካ ነው። ይሄ ጥሩ ነው፤ ስለአሜሪካም ስለጃፓንም ማወቅ አለብን። ከሁሉ በፊት ግን አገራችንን ማወቅ አለብን። እኔ ደግሞ በጣም አምንበታለሁ። መጽሐፌን አይተሸ ከሆነ ስለእኔ ከሚገልጸው በላይ ስለ አገሪቱ ይገልጻል። ስለዚህ አገርን ሕዝብን እንደማወቅ ትልቅ ነገር የለም።

ቅጽ 2 ቁጥር 55 ኅዳር 13 2012

Page 15: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 15አንደበት

በዚህ በአንደበት አምድ የፖለቲካ ሰዎችን ጨምሮ ምሁራንና መምህራን፣ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች፣ የጥበብ ሰዎች፣ በጎ አድጊዎች፣ አሸናፊዎችና ብርቱዎች፣ ከአንጋፎች እስከ ወጣኒ ወጣቶች ድረስ በእንግድነት በየሳምንቱ ቀርበዋል።

ከእነዚህ መካከል በዚህ እትም የተወሰኑትን በማንሳት በሰጡት ቃለመጠይቅ ካነሱት ሐሳብ መካከል የተወሰነውን በመምረጥ የአዲስ ማለዳው ዳዊት አስታጥቄ ተከታዩን አሰናድቷል።

‹‹እዚህ አገር መንግሥት በጣም ተዳክሟል፤ እንደኔ ያሉ ሰዎች ከገፋነው

ፍርክስክሱ ሊወጣ ይችላል።››

ጃዋር መሐመድየኦፌኮ አማራር አባል››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ከውጪ ለመጡት ፖለቲከኞችና ተሟጋቾ የሰጡትን ትኩረት ያክል ላንተ አልሰጡም ይባላል። በዚህ ምክንያት የጃዋር የፖለቲካ ተሳትፎና ተጽዕኖ ፈጣሪነት አገር ውስጥ ከገባ ጀምሮ እየቀነሰ ነው የሚል ዕይታ አለ። እዚህ ላይ ምን ትላለህ?አልስማማም! እዛ [አሜሪካ] ሲመጡ ተወያይተናል፤ እዚህም ስመጣ በተደጋጋሚ ተወያይተናል። መንግሥትን ሆነ ተቃዋሚውን የመቀላቀል ፍላጎት የለኝም፤ በመብት ተሟጋችነቴ ነው መቀጠል የምፈልገው። እንደተሟጋች ከመንግሥት በመጠነኛ ርቀት መራቅ አለብህ። ምክንያቱም ሕዝብ ከመንግሥት ጋር ነህ ብሎ ካሰበ ላንተ የሚኖረው ቀረቤታ የዛኑ ያክል ይሆናል። መንግሥትንም በጣም ከቀረብክና ትችት የምትሰጣቸው ከሆነ ‹እንዴት ጉያዬ ሥር ሆኖ ይተቸኛል› የሚል ነገር ይመጣል። ስለዚህ ተከባብረህ በመጠነኛ ርቀት ላይ መገኘቱ አስፈላጊ ነው።ተፅዕኖና ተሳትፎን በተመለከተም ቀንሷል። ለምን?ምክንያቱም በጣም ተፅዕኖ ሲፈጠር የነበረው የአንባገነን ሥርዓት ስለነበረ ነው። አሁን ለውጡን እየመሩት ወደ ዴሞክራሲ እያሸጋገሩን ነው የሚል እምነት አለኝ።ኹለተኛ እዚህ አገር መንግሥት በጣም ተዳክሟል፤ እንደኔ ያሉ ሰዎች ከገፋነው ፍርክስክሱ ሊወጣ ይችላል። ስለዚህ መጠንቀቅ አለብን። ተቃዋሚቹም የሚንቀሳቀሱት በጣም በጥንቃቄ ነው። እኛም ቢሆን መንግሥትን የመደገፍ ሥራ ነው እየሠራን ያለነው። ይሁንና ‹እንደዚሁ እንቀጥላለን ወይ› ለሚለው መልሴ እንደሁኔታው የሚል ነው። እነዐቢይ ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር የሚሔዱ ከሆነ ድጋፋችንን እንቀጥላለን፤ ወደ መቀልበስ ከሔዱ ተፅዕኗችን እየጨመረ ይሔዳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 3 ኅዳር 22 ቀን 2011

‹‹በብሔራዊ መግባባት እነዚህን ለብዙ ዘመናት ተከማችተው የመጡ ችግሮች ሁሉ በአንዴ እንፍታ ማለት

አይቻልም።››መረራ ጉዲና (ዶ/ር)

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር

የአገሪቱን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ መሠረታዊ የምንላቸው ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?ኢትዮጵያ ወዴት ትሂድ፣ አንድ አገረ አለን የለንም የሚለው ላይ መስማማት ያስፈልጋል። እየታገልን ያለነው የተለያዩ አገሮችን ለመፍጠር ነው ወይስ የተሻለ አንድ አገርን ለመገንባት ነው? የአገሪቱ አንድነት ላይ አቅጣጫ ማስያዝ የግድ ያስፈልጋል።አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት መገንባት ላይ መስማማት አለብን። የኢትዮጵያ ሕዝቦች ይሁንታን ያገኘው ፓርቲ በነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ወደ ሥልጣን የሚወጣበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሕዝብ ይሁንታን ያላገኘው የሚወርድበትና ትግሉን የሕዝብ ይሁንታ እስኪያገኝ የሚቀጥልበት ሥርዓት ማለት ነው።ከዚህ ውጪ ያሉ ጉዳዮችን የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ፖሊሲያቸው ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ለምሳሌ የቋንቋ ጥያቄን፣ ምን ዓይነት ፌዴራሊዝም እንከተል የሚለውን፣ የግለሰብ መብቶችንና የማኅበረሰብ መብቶችን እና የመሬት ጥያቄን የመሳሰሉትን ማለቴ ነው። የኢትዮጵያ ችግር ኢሕአዴግ 27 ዓመታት የከፋፍለህ ግዛ ሴራ እንጂ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም አላመጣም። የመድረክ አቋም ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም እስከተገነባ ድረስ የግለሰብ መብትና የቡድን መብቶች አንድ ላይ መስተናገድ ይችላሉ የሚል ነው።በብሔራዊ መግባባት እነዚህን ለብዙ ዘመናት ተከማችተው የመጡ ችግሮች ሁሉ በአንዴ እንፍታ ማለት አይቻልም። ችግሮች መፈታት ያለባቸው ደረጃ በደረጃ ነው። አለበለዚያ ችግሩ ተቃዋሚውን በመከፋፈልና አገሪቱን ሌላ ዙር ቀውስ ውስጥ ይከታታል።እንዴት አብረን እንኑር፣ ምን ዓይነት የመንግሥት ቅርጽ ይኑረን፣ ሁላችንንም በእኩልንት የሚያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዴት እንፍጠር በሚሉት ዙሪያ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እየተነጋገሩና እየተደራደሩ መፍታት ላይ መድረስ ይሻላል።

ኅዳር 10፣2011

‹‹አገሪቷ ውስጥ ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ያካተተ የሥልጣን ክፍፍል በማድረግ ኢትዮጵያ ውስጥ

ያሉትን ችግሮች መፍታት አይቻልም።››

ከአንዳርጋቸው ጽጌ

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ችግር ለማቃለል አንዳንዶች የሽግግር መንግሥት ወይም የሽግግር ምክር ቤት መቋቋም አለበት በሚል ይሞግታሉ። በዚህስ ላይ የእናንተ አቋም ምንድን ነው?አገሪቷ ውስጥ ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ያካተተ የሥልጣን ክፍፍል በማድረግ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ችግሮች መፍታት አይቻልም። አሁን ዐቢይ እየሠራ ያለው ተቋማትን ነፃ ማድረግ፣ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፣ ሽብርተኛ የተባሉ ድርጅቶችን በሙሉ በአገር ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ የሽግግር መንግሥት ከሚሠራው በላይ በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ ነው ብዬ አስባለሁ። የሽግግር መንግሥት ቢመጣ በአገሪቷ ውስጥ የበለጠ ቀውስ ይፈጥራል። መጀመሪያም ቢሆን ከ80 በላይ ፓርቲዎች ባሉበት አገር የሽግግር መንግሥት ማድረግ የሚታሰብ አይደለም። ወሳኝ በመሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማት እና የሕግ ጉዳዮች ላይ መምከር ይገባል። እሱም ላይ ቢሆን ከፓርቲዎች ብዛት አንጻር መንግሥት የሆነ ነገር ማድረግ አለበት።በፌዴራል መንግሥቱና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት ይገልጹታል?በመጀመሪያ ፌደራላዊ ስርዓቱ ሲዋቀር እያንዳንዱ ክልል ራሱን የቻለ ማዕከላዊ መንግሥት መገዳደር የሚችል ጉልበት በሚኖረው ደረጃ ሠራዊትና ሌላ ነገር እንዲያቋቁሙ የተደረገበት መንገድ ውሎ አድሮ አሁን ያለው ሊፈጠር እንደሚችል ተነጋግረን ነበር። በ1985 ባቀረብኩት ክርክር የብሔር መብት ማስከበር ቋንቋን፣ ባሕልን ማሳደግ፣ መጠቀምና ማስጠበቅ ጥሩ ሆኖ ሳለ ዞሮ ዞሮ ዘር ወደሚወልደው የብሔር አደረጃጀት መግባት አደገኛ መሆኑን አመላክቻለሁ። እያንዳንዱን አካባቢ ሥም እየጠራሁ ድርጅት መኖር የለበትም እስከማለት ድረስ ሔጃለ። አሁን የምናየው ፌደራሊዝሙ የተደራጀበት ውጤት ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 5 ታኅሣሥ 6 ቀን 2011

“ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ በጣም አስደምመውኝ ነበር። እጅግ የተሻለች

ኢትዮጵያ ለመፍጠር ህልም አላቸው።”

ፈራንሲስ ፉኩያማ (ፕሮፌሰር) በሃርቫርድ ዩኒቨሪቲ ፖለቲካል ሳይንስ መምህር

አስቀድሞ የማንነት ፖለቲካን ሲያነሱ፤ በጣም መከፋፈል ባለባቸው አገራት የሚታዩ የመፍረስ ምልክቶችን ለይተው ነበር። ከዛ አንጻር አሁን ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ እንዴት ያዩታል?ኢትዮጵያ በርግጥም አደጋ ውስጥ ናት፣ አደጋው ምናልባትም የመፈራረስ ሊሆን ይችላል። ይህም የሆነው የብሔራዊ አንድነት ስሜት ያልተሰማቸውና በኢትዮጵያ ውስጥ ራሳቸውን ማየት ያልቻሉ ብዙ የብሔር ቡድኖች ስላሉ ነው። ይህ በጣም አደገኛ ሁኔታ ነው። ሶርያ፣ ኢራቅና ሶማሊያን አይተናል። ሁሉን የሚያስማማ አንድ ብሔራዊ ማንነት መፍጠር ባለመቻላቸው የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል በቅርቡም የፈረሱ አገራትን ተመልክተናል። ኢትዮጵያ በዚህ መንገድና አቅጣጫ ልትሔድ አይገባም።ችግሩን እዛ ደረጃ ሳይደርስ ለመፍታት ምን ቢደረግ ይላሉ?መፍትሔው የሚመሰረተው እንዳልኩት ብሔራዊ አንድነትን በመፍጠር ላይ ነው። ይህም በተለይም በአገር መሪዎች ላይ የሚጣል ኀላፊነት ነው። ሰዎች ከብሔር ማንነት ጋር ሚዛናዊ የሆነ የኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብን ሊፈጥሩ ይገባል። ለምሳሌ ሶሪያን ብትወስጂ ሁሉም ስለራሱ ሃይማኖት እና ጎሳ ላይ ያተኩራል እንጂ ስለ ሶሪያ የሚያስብ አልነበረም። ይህም በመጨረሻ ወደ እርስ በርስ ጦርነት አምርቷል።ከዚህ ቀደም በነበሮት ጉብኝት ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይን የማግኘት ዕድል ነበረዎት። በእሳቸው እና በመንግሥታቸው ላይ ያሎት አሰተያየትስ ምንድን ነው?ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ በጣም አስደምመውኝ ነበር። እጅግ የተሻለች ኢትዮጵያ ለመፍጠር ህልም አላቸው። የአገሪቱን አንድነት ማስጠበቅ የሚችል ፕሮጀክት ይዘው መጥተዋል ብዬ አምናለሁ።

(ቅጽ 1 ቁጥር 42 ነሐሴ 18 2011)

Page 16: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 16ትንታኔ

አገር በዜጎች ይገነባል። ዜጎቿ በየትኛውም አስተሳሰብ ደረጃ እና ንቃተ ሕሊና ቢሆኑ ለአገር ግንባታ እና ለአገር ማቆም ሁሉም እኩል ባለቤትነት እና ደርሻ

ይኖራቸዋል። በዜጎች መፈቃቀድ እና መደጋገፍ ላቅ ሲልም መወቃቀስ አገር ከዘመመችበት ትቃናለች፤ ከወደቀችበት ትነሳለች፤ በከፍታም ላይ ከሆነች ከፍ ብላ ልዕልናዋን አስጠብቃ ትበራለች አገርም ትሆናለች።

የኢትዮጵያ ጉዳይም ከዚህ የሚለይ አይደለም የ3 ሽሕ ዘመን ታሪክን ወደ ኋላ ሔደን ባየንበት እና በምንዳስስበት ጊዜም አገረ መንግስት በዜጎች ቆሞ ነገስታት በጠቢባን ተመክረው እና ተነቅፈው የወንበራቸውን ዓይን ከሸወራራነት መልሰዋል። ‹‹አነዋሪ›› እና ‹‹አደጓሪ›› የተለያየ ገቢር ያላቸውን ሰዎች ቀጥረውም ከሚያሞካሿቸው አደግዳጊ በዙሪያቸው ከሚገኙ ግለሰቦች ባለፈ ወደ አሸሟሪዎች እና ህጸጽን ነቅሰው ወደ

ስፍራዎች እና ስማቸው በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ስፍራዎች ላይ በኃላፊነት እና በከፍተኛ የሙያ ደረጃ ላይ ተሰድረው የሚገኙ ዜጎቿ ምስክር ናቸው። በተጓዳኝም ነገስታትን በሰላ ትችታቸው እየሸነቆጡ የሚቆጠቁጥ ቀን መጥቶ ነገስታት ቁጣቸው ሲጠነክርም ወደ ዘብጥያ እየተወረወሩ ትችታቸውን እና አደባባይ ነቀፌታቸውን የማይተው ጥቂት ጠቢባንም ኢትዮጵያ አፍርታለች።

ዘጠና ዓመታትን በአልበገር ባይነት ያሳለፉት እና የአገር አድባር፣ የአገር ዋርካ፣ መምህር፣ የስነ መልክዓ ምድር ሊቅ፣ ጸሐፊ፣ የሰው ቁስል የሚጠዘጥዛቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ አምባገነኖችን የሚጋፈጥ ሰፊ ደረት ባለቤት እና ጭቆናን የማይሸከም ስስ ትከሻ ባለቤት መስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) ወይም ደግሞ በወዳጆቻቸው አንደበት ‹‹የኔታ››። መስፍን ወልደማሪያም አዲስ አበባ ተወልደው አዲስ አበባ ያደጉ የመሐል አገር ሰው ይሁኑ እንጂ ልባቸው

ምጽዋን ተሸግሮ ዳህላክ ደሴት ላይ የሚሰፍፍ በመልክዓ ምድር የማይገደቡ ብርቱ ፍጡር፤ መሐል ፒያሳ ተቀምጠው ደቡብ ኦሞ ኛንጋቶም እና ዳሰነች የጓዳ ጩኸት የሚያደነቁራቸው ሰብኣዊነትን ኖረው ያለፉ የምርጥ ነብስ ባለቤት፤ ሸገር ላይ ከትመው ቶጎ ጫሌን በንስር ኣይናቸው የሚያስሱ ድንቅ ሰው። በዘመናቸው ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ ሦስት መንግስታትን በሰላ ብዕራቸው ዕረፍት የነሱ ለምንዱባን ቆመው ለግፉዓን የተዋደቁ የጭቁኖች የቁርጥ ቀን ልጅ የወጣትነት ዘመን ብስጩ፣ የጎልማሳነት ዘመን ተጋፋጭ፣ እርጅና ዘመን መካሪው መስፍን ወልደማሪያም ።

መጽሐፍት

እንጉርጉሮ (ግጥምና ቅኔ)፣ መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ (ታሪክ)፣ ኢትዮጵያ ከየት ወዴት? (ታሪክ)፣ ዛሬም እንጉርጉሮ (ግጥምና ቅኔ)፣ ልማት ኢትዮጵያዊነት በኅብረት (ታሪክ)፣ አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ (ታሪክ)፣ እንዘጭ! እምቦጭ! የኢትዮጵያ ጉዞ (ፖለቲካ) Rural Vulnerability to Famine

90ዓመታትየአልበገር ባይነት ጉዞ

ሚያወጡ አነዋሪዎች በማዘንበል ምን ተባለ? ምንስ ጎደለ በሚል ከተቺዎች ጠንካራ ምክርን በማውጣት የመንግስታቸውን ካስማ እና የዘመነ መንግስታቸውን ዕድሜ አርዝመው ፤ አገርን አስቀጥለዋል። አገርን ከትውልድ ወደ ትውልድ እያሸጋገሩ በዘመናት መካከልም የሚያጋጥመውንም ችግር ከጠቢባን ጋር እየፈቱ የተሸገሩ መንግስታት ጥቂት አይደሉም አሁንም እንደዛው ይቀጥላሉ። ይሁን እንጂ ከነገስታት እና ከገዢዎች ባሻገር ጠቢባን ሲነሱ፤ ሲወሱ እና ሲወደሱ የሚገኙበት መድረክ እጅግ ጥቂት ነው። ለየት ብለው ወጥተው ታሪክ የመዘገባቸው እና ዘመን ያገነናቸው ካልሆኑ በስተቀር በየቤተ መንግስቱ ጓዳ ተሸሽገው የዕለት ተዕለት የንግስና ጉዞን ያቃኑ እና ነገስታትን የገሰጹ ሲወደሱ እምበዛም አይታይም።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በጠቢባን እና በሊቆቿ የጠበብትነት ደረጃ እና ዕውቀት ልክ ከዓለማት ተርታ ለመመደብ እና ተመድባም አስጠብቃ ለመሔድ የቻለች አገር ለመሆኗ በዓለም ቁልፍ

የአዲስ ማለዳ ዝግጅት ክፍል በመስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልጻለን

Page 17: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 17

xxx

ትንታኔ

in Ethiopia, 1958-1977 የኔታ በግሩም የቋንቋ ችሎታ ለንባብ ያበቋቸው ዘመን ተሸጋሪ የመጽሐፍ መደርደሪያ አድማቂ እና ሁሉ በሁሉ የሆነ የአዕምሮ

ምግብ የሆኑ መጽሐፍት ናቸው። በመጽሐፍት ታትመው መጽሐፍ በሚል ስም ወደ ሕዝብ ደረሱ እንጂ መስፍን ወልደማሪያም በተለያዩ መጽሔቶች እና ጋዜጦች ላይም ሳምንታዊ አምደኛ በመሆን በሰላ ብዕራቸው

ያልበረበሩት የዓለም ምስጢር እና አሰናስለው ያላነሱት የኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣

እና ኢኮኖሚያዊ ቋጠሮ የለም የማለት ድፍረቱን የሚሰጡን ደጋፊዎቻችን ናቸው።

መስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) እጅግ ለበዛው የአጼው ዘመነ መንግስት የዜጎች በደል ግንባር ቀደም ተሟጋች በመሆን እና የመንግስትን ሕጸጽ አይቶ እንዳላየ ሳያልፍ ‹‹ንጉሥ አይከሰስ፤

ሰማይ አይታረስ›› የሚለውን ብሒል ገና በማለዳው አሽንቀጥረው ጥለው ‹‹እንዴት

ተብሎ መንግስት ይህን ያደርጋል›› የሚሉ ሞጋች ሀሳቦችን ሰንዝረው ንጉሡን የነካ

ከፈጣሪ ተጣላ የሚለውን የአገሬውን ሀሳብ በአደባባይ የሰበረ የጭቆናን ቀንበር ከሕዝብ

ላይ ያላላ የያኔው ወጣት በሰውነት ማጎልመሻ የፈረጠመው የዕኩልነት ጠበቃው መስፍን

ወልደማሪያም ነበር። ተናዳጅ እና ጠበኛነትን ከሩህሩህ እና አዛኝነት፣ ለተበደለ

ከመቆም ጋር አጣጥመው የልጅነት ሕይወታቸውን ያለፉ ግለሰብ ናቸው።

‹‹ሰው›› የሚለውን ክቡር ፍጡር በትክክል

በስብዕናቸው የገለጹ ጠበኛነት እና ቁጡነታቸውን በጊዜ

ሂደት ጥለው ለተበደለ መቆምን ግን በሕይወት ዘመናቸው መርህ

እስኪያደርጉት ድረስ አቅፈው የሔዱ የመርህ ሰው ናቸው። በሚያዚያ 2008

ለንባብ በበቃው ውይይት መጽሔት ላይ ግለ ታሪካቸውን 86ኛ ዓመታቸውን ተመርኩዞ ባዘጋጀው ጽሑፍ ልጅነታቸውን እንዲህ ይገልጸዋል። ‹‹ፕሮፌሰር መስፍን ፈረንጆች (for-mative age) የሚሉት ወይም አፍላ ዕድሜያቸው ላይ ጣልያን ኢትዮያን የወረረችበት ጊዜ ነበር። አርበኝነት የሚያደንቀው እና ‹ባንዳነት›ን የሚጠየፈውማንነታቸው የተቀረጸው ምናልባትም የዛን ጊዜ በልጅነት ልቦና ደጋግመው ይሰሟቸው ከነበሩ ትርክቶች በመነሳት እንደሆነ ይገመታል። ከልጅነት ጊዜዎቻቸው በአንዱ አንድ ጣልያናዊ አንድ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ እግሩን አነባብሮ ሲያነብ ተመልክተው ምን እንዳነሳሳቸው ሳይታወቃቸው ድንጋይ አንስተው በመወርወርቅልጥሙን ብለውት ሲሮጡ ጣልያኑ ተከትሎ አባርሮ ይዞ በእርግጫ የደበደባቸው ከልጅነት ትዝታቸው አንዱ ነው›› ሲል መጽሔቱ ያስነብባል።

በእርግጥ ፕሮፌሰሩ በመጽሐፋቸው እንደገለጹ የነጭን በላይነት ከልጅነታቸው ጀምረው

እንደጠሉ በኋላም ወደ ኬንያ ለጉዳይ ሔደው ያጋጠማቸውን

ጉዳይም እንዲህ ከትበውታል

‹‹ . .ኬንያ

ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ። በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ። በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ ወለሉ አመራሁ።

እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር ፦ “ኢትዮጵያዊ ነህ?›› የጀብድ እና እምቢ ባይነት አቋም አብሯቸው ያረጀ መገለጫቸው ነበር።

ከየካቲት 12ቱ የግራዚያኒ ጭፍጨፋ የተረፉ፣ በደርግ የቀይ እና ኢህአፓ የነጭ ሽብርን የተጋፈጡ ፣ ከመንግስቱ ኃይለማሪያም ቁጣ እስከ መለስ ዜናዊ አህአዴግ ዘመን የአንገት ለአንገት ትንቅንቅ ተጋፍጠው መንገህስት ሔዶ መንግስት ተተክቷል። ስልጣንን አባላጊነት አበክረው የሚናገሩት እና ስልጣንን አምርረው ሚጠየፉት የኔታ ገና በለጋነታቸው ጭቆናን መታገል ምለው ነበር ነበርና ወታደራዊው መንግስት በትጥቅ ትግል ተገርስሶ አብዮታዊ ዲሞክራሲ አቀንቃኙ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት የመጀመሪያዎቹ ለጋነት ዕድሜ ጨምሮ ሙግታቸውን ጀምረው ነበር። በኤርትራ መገንጠል እና ኤርትራዊያን ናችሁ ተብለው ከኢትዮጵያ አራቱም ማዕዘን ተፈልቅቀው ወደ ማያውቁት ቀየ የተጋዙትን ቀን የከፈላቸውን የአንድ አገር ዜጎችን ጉዳይ በተመለከተ በዓለም አደባባይ ጮኸዋል።

በክህደት ቁልቁለት መጽሐፋቸው ላይ ለንደን ላይ የኤርትራ መገንጠል ዕውን ሆኖ ድርድሩም በአገረ እንግሊዝ በሚካሔድበት ወቅት ከኤርትራ ወገን ፕሬዘዳንት ኢሳያስን በአጋጣሚ አግኝተው ያናገሩትን በእርግጥም ወቀሱትን ቢባል የሚቀል ንግግር እንዲህ ያስቀምጡታል ‹‹ኢሳያስን አንተ የአሉላ አባነጋ ልጅ፣ የዘርዓይ ድረስ ልጅ ሆነህ እንዴት ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ትላለህ? ሌሎች ሌሎች ቢሉስ ይሁን አልኩት እርሱም አላሳፈረኝም በትኩረት አዳመጠኝ ›› ይላሉ። የኤርትራ አገርነት አሁንም ለፕሮፌሰር መስፍን የማይዋጥ እና ሳይዋጥላቸውም ይህቺን ዓለም ጥለው የሔዱ ለእምነታቸው የቆሙ አንጋፋ ሙሑር ነበሩ።

በዘመነ ኢህአዴግ በ1997 በሦስተኛው አገራዊ ምርጫ ላይ ከፍተኛ ፖለቲካ ተሳትፎ ከነበራቸው ግለሰቦች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሱ የነበሩት መስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) የምርጫ 97 የቅድመ ምርጫ ሽር ጉዶች፣ የምረጡኝ ቅስቀሳዎች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ገዢው ፓርቲ ያደርጉት ነበረው የገጽለገጽ ክርክር እንዴት ያለ የፍሰሀ ዘመን ላይ ደረስን ተባለበት ድንቅ ጊዜ ነበር። አገር አድባሩ፤ የዕውቀት ጉልላት፤ የሰውነት ጥግ መስፍን ወልደማሪያም (የኔታ) ይህን ወቅት በአስደማሚ የንግግር ችሎታ እና መካች ባጣ ጠንካራ ሙግት ተቀናቃኞችን ድባቅ የሚመቱ ቀልብን የሚገዙ ተከራካሪ እንደነበሩ ሕያዋን ምስክሮች ነን። ይሁን እንጂ ሲያልቅ አያምርምና በሦስተኛው ዓለም የምርጫ ታሪክ አኩሪ አይደለም እና ድህረ ምርጫ ወቅት በቅድመ ምርጫ ታዩት ፈርጦች በሙሉ ወደ ዕስር ተጋዙ። ድሮም የፊት ለፊት ሰው የነበሩት መስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) በእርጅና ዘመናቸው ወደ ዘብጥያ አምርተው ነበር።

ዓለም ትኩረቱን በያኔዎቹ ታሳሪዎች ዘድርጎ በጊዜው የነበረውን መንግስት እንዲፈታቸው ጫና ለማሳደር ቢሞክርም ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ ያለው የመለስ ዜናዊ መንግስት የኔታን ጨምሮ በኋላ ላይ ወደ ትጥቅ ትግል ያመሩትን ዜጎች ዘለግ ላሉ ጊዜያት ማቆት ችሎ በኋላ ላይም በይቅርታ እንዲፈቱ ሆኗል። ‹‹ኢህአዴግ ሕገ አራዊት ነው›› በሚል ትችታቸው ለረዥም ጊዜያት ሲሞግቱ የነበሩት መስፍን ወልደማሪያም ከግንባሩ ጋር ሆድ እና ጀርባ እንደሆኑ የ27 ዓመት ወጣቱ ግንባር ኢህአዴግ በለውጡ ማግስት ፍርስርሱ ወጥቶ ከአራት ድርጅቶች ግንባር አንዱ ሲቀር ቀድሞ አጋር ያላቸው ተጨምረውበት ወደ ብልጽግና ፓርቲ ራሱን ለውጧል፤ በዚህም ውስጥ የኔታ የሚሉት ነበራቸው።

1922 ይህቺን ዓለም የተቀላቀሉት መስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) በያኔው አንድ ለእናቱ በነበረው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማስተማር የጀመሩ እና ረጅሙን የሕይወት ጉዟቸውንም በዛው ያጋመሱ አንጋፋ ሙሑር እንደሆኑም ታሪክ ድርሳናቸው ያወሳል። የጥልቅ ዕውቀት ባለቤት እና የግሩም ስብዕና ጥቅል መኖቸውን የሚናገሩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ናቸው። ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጋር አጭር ቆይታ ያደረጉት በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ዕውቀት አባታቸው እንደነበሩ ተናግረው ነብይነታቸውን እና ትንቢታቸውም ጠብ እንዳላለ በ88ኛ ዓመታቸው ላይ ሆነው በአንድ አጋጣሚ በተገናኙበት ወቅት ‹‹ከእንግዲህ አንድ ወይ ኹለት ዓመት ብቆይ ነው›› የሚል የሕይወታቸውንም ኡደት የተነበዩ ሰው እንደነበሩም ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር እና ቀድሞው የየኔታ የትግል አጋር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታም ‹‹በግሌ ትልቅ ነገር ነው ያጣሁት›› ሲሉ ይጀምራሉ መስፍን ወልደማሪያምን (ፕ/ር) ዜና ዕረፍት በሰሙበት ሰዓት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻሉ። ‹‹በግሌ ከእርሱ ጋር የማደርጋቸው

ውይይቶች እና ክርክሮች ብዙ ትምህርት የሚሰጡ እና ከፍተኛ ዕውቀትን ሚያሲዙ ነበሩ›› ሲሉም በነበር የቀረውን የኹለቱን ግንኙነት አውስተው ይናገራሉ።

ከሁሉም ግን በእኔ እምነት ፕሮፍን (የኔታ ብለው ከሚጠሯቸው ወዳጆቻቸው የተረፉት እንዲህ ነው ሚጠሯቸው) እንደገለጸ ተሰማኝነት የጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እንዲህ ሲል ትውውቃቸውን እና መጀመሪያ የነበረውን የርቀት ግምት እና ምልከታ በፕሮፍ ላይ እና በኋላ ላይ ካገኘው ጋር አሰናስሎ መስክርነቱን በድምቀት እንዲህ ይገልጸል ‹‹በርዕዮተ ዓለም ምክንያት አፍንጫዬን ይዤ የተጠጋኋቸው ፕሮፌሰር መስፍን ግን ፈጽሞ እንደገመትኳቸው ኾነው አላገኘኋቸውም፡፡

አንደኛ፦ በጣም! በጣም! በጣም! ወጣት ይወዳሉ፡፡ የሐሳብ ድግግሞሻቸውን እና ሌክቸራቸውን ታግሶ የሚሰማቸው ከተገኘማ በጣም ደስታቸው ነው፡፡ ዝም ብለው ለሰሟቸው ወይንም ካርታ ከሚያጫውቷቸው እኩዮቻቸው ጋር ከመዋል ይልቅ ከሚጣላቸው ወጣት ጋራ ሲጨቃጨቁ መዋልን ይመርጣሉ እላለሁኝ፡፡ የእኛ ቢጤ እብሪተኛ የኾነን ወጣትን ማልመድን ደግሞ ልክ ፈረስ እንደመግራት ተክነውበታል፡፡ ለምን አይችሉበት!? ስንት ትውልድ በስራቸው አለፈ? እንዲያው ሳናውቅ፣ ዐይናችን ሳያየው፤ ግንኙነታችን ከፕሮፌሰር መስፍንነት ወደ “ፕሮፍነት” ተለወጠ፤ ከእኛ ጋር ተቀላቅለው ቡና መጠጣትና የቆጥ የባጡን ማውራት ተጀመረ፡፡

ሁለተኛ፦ በጤንነት እና በዕድሜ ምክንያት እንደ ዔሊ ለማዝገም ቢገደደዱም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እና ሳይታክቱ በእጅጉ ይሠራሉ፡፡ መጽሐፎቻቸውን ሙሉ በሙሉ አሊያም የመጀመሪያውን ድራፍት ራሳቸው ይተይባሉ፡፡

ሦስተኛ፦ በአደባባይ መናገርም ኾነ መጻፍ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ፈፅሞ ያልለወጧቸው ዋና ዋና አቋሞች አሏቸው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ስለ ሰላማዊ ትግል፤ ስለ ስደት፤ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፤ ስለ ሕግ የበላይነት፤ ስለ መሬት ፖሊሲ፤ ስለ ኢትዮጵያ ዳር ድንበር ያሏቸውን አቋሞች ከፈለጋችኹ 50 ዓመት ወደኋላ ተመልሳችኹ ሂዱና አጥኑ፤ አሁንም ያኔም ፕሮፌሰር መስፍን ያው ናቸው››፡፡

በእርግጥም ፒያሳ የስመ ጥር ኬክ መገኛ ኤንሪኮ ያለበትን ዘመን ጠገብ ሕንጻ እንደታጠፉ ቁልቁል ሲንደረደሩ በሚገኘው ሌላ ዘመን ተሸጋሪ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ ይኖሩ የነበረው የኔታ በራቸው ተቆልፎ እንደማያውቅ እግር ጥሎት የገባ ሁሉ ለሕይወት ዘመኑ የሚበቃውን ምክር ተሸክሞ እንደሚወጣ አሳባቂም ነው።

ከዓመታት በፊት በመኖሪያ ቤታቸው በተገኘሁበት ወቅት በዛ ባተሌነት በሚገንበት አዲስ አበባ እምብርት ላይ እንዲህ ያለ የጸጥታ ድባብ ይገኛል ብየ ማሰብ የተሳነኝ ጊዜ ነበር። በቅርበት ያውቃቸው ከነበረ እና ቀጠሮ ይዞ ለመጠየቅ ካቀና ወዳጄ ጋር ተደርቤ ነበር እና ያቀናሁት ልብ ድረስ ዘልቆ በሚገባ አባታዊ አስተያየት እየተመለከቱ ‹‹እንግዲህ ሽማግሌ ቤት ረዳት በሌለኝ ሰዓት መጥታችሁ ከእኔ ሻይ እንዳትጠብቁ፤ ነገር ግን ማንቆርቆሪያውም እሳቱም እዚሁ ነው ገብታችሁ መንጎዳጎድ ትችላላችሁ›› ብለው በአብረሐማዊ መንፈስ ተቀብለው አስተናግደውናል።

ቤት እንደ አገር ነው በነዋሪው ይሟሻል፣ በባለቤቱም ይቀረጻል። የመስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) ቤትም እንዲሁ ነው። አብዛኛውን የቤታቸውን ክፍል ከፍተኛ ሆነ የመጽሐፍ ክምር ኹለተኛ ግድግዳ እስኪመስል ድረስ የተቆለለ ነበር። በአንድ አነድናቂያቸው እና አክባሪያቸው እንደተሰጣቸው የነገሩን እና በርካታ በትንሿ አንጎሌ ልመረምረው ያልቻልኳቸውን ጥልቅ ምክሮችን አሸክመው ሰደዱን ። ቆይታው እውነት ለመናገር የሽራፊ ሰክዶች ያህል ያጠረ ቢመስልም ሳይታወቀን አራት ሰዓታትን በመጽሐፍት ታጅበን ተንቀሳቃሽ መጽሐፍ እያናገረን ቆይተን ነበር።

90ኛ ዓመታቸውን ባከበሩ ዕለት ከአዲስ ማለዳ ጋር አችር ቆይታ አድርገው ነበሩት መስፍን ወልደማሪያም (ፕ/ር) በእድሜ ብዛት ለማይዛነፈው የአዕምሯቸው ቅልጥፍና ትልቅ ምስክር መሆን ይቻላል። ቆይታቸው ለካንስ ስንብታቸውም ነበር። የአገር ዋርካ እና አድባር፣ መካሪው ምሑር የሰብዓዊ መብት ታጋዩ ፕሮፌሰር 90ኛ ዓመታቸውን አክብረው እንደተወደዱ ዘልቀው ዓለምን በናጣት ወረርሽኝ ኮሮና ቫይረስ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ማክሰኞ መስከረም 19/2013 ሌሊት አምስት ሰዓት ላይ ይህቺን ዓለም ተሰናብተው ረጅሙን የዘለዓለም ጉዞ ጀምረዋል።

Page 18: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 18

አወል ቃሲም አሎ (ዶ/ር)

በዩናይትድ ኪንግደም ኪል ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር

የትርክት ልዩነቶች ጫፍ ደርሰው ለአገር ሕልውና አደጋ ሊሆኑ አይችሉም?

ሊሆኑ ይችላሉ። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ የማንነት ፖለቲካ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና ባገኘበት አገር ይህ የማንነት ፖለቲካ በጣም ጫፍ ደርሶ የጋራ ርዕይ በሌለበት፣ ሁሉም ወደ ሥልጣን ሊያደርሰኝ የሚችለው ይሄ ነው ብሎ የረጅም ጊዜ ግብ ሳይያዝ ጉዞ የሚደረግ ከሆነ ትልቅ ስጋት ሊሆን ይችላል።

አንድ ዓይነት የትግል ዘዴን የተወሰነ የትግል ምዕራፍን ለማለፍ ከተጠቀምክ ያንን ምዕራፍ ደግሞ አገር ለመገንባት የሚያስፈልገው ስትራቴጂ እንድንጠቀም ማተኮር ይኖርብናል። ከዛሬ 10 ወራት በፊት የመታገያ ዘዴዎች ዛሬም የምንጠቀምባቸው ከሆነ ትግል ላይ አይደለንም፤ በግብታዊነት እየተንቀሳቀስን ነው ማለት ነው።

ኅብረተሰባዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዲመጣ የምንፈልግ ከሆነ የተለያዩ የትግል ደረጃዎችና ስልቶችን መጠቀም ያስፈልጋል።አምባገነን ሥርዓትን ለማፍረስ የተጠቀምክበትን ስልት ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመገንባት ልትጠቀምበት አትችልም። አሁን ትርክቶች ገንቢ መሆን መቻል አለባቸው። ተዋስኦው መልሶ ገንቢ መሆን መቻል አለበት። ዝም ብሎ አፍራሽ መሆን አይደለም። እንደ ግለሰብም እንደተቋምም መለወጥ ያስፈልጋል። አተያያችን ከድሮው አቅጣጫ ትንሽ ዞር ማለት አለበት።

አሁን ትልቁ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ከዚህ በፊት ተጎዳሁ የሚለው አካል ያስብ የነበረው ስለጉዳቱ ስለነበረ፣ ከዛ አመለካከት መውጣት አልቻለም። አሁን ቅርብ ጊዜም ሥልጣን አጣሁ የሚለው አካል ደግሞ ተመልሶ እዛው ተጎዳሁ የሚለው አመለካከት ውስጥ ገብቷል። በሄድክበት አቅጣጫ ሁሉ የምታገኘው የተጎዳ ሕዝብን ነው። ሁሉም ተጎጂ ነኝ በሚልበት ወቅት አጓጊ፣ ቆራጥ የሆነ መጪውን አመልካች የሆነ ርዕይ ለማየት ያስቸግራል።

ቅጽ 1 ቁጥር 10 ጥር 11 ቀን 2011

‹‹ሕወሓት ያለው አንድ አማራጭ ሥልጣን ለሕዝብ አስረክቦ ተቃዋሚ

ሆኖ መቀጠል ነው››አብረሃ ደስታ

የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና) ሊቀመንበር

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ክልል መንግሥት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል ግልጽ የሆነ የአቋም ልዩነቶች እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። አሁን ባለው አካሔድ የሕወሓት ዕጣ ፈንታ ምንድነው?ሕወሓት አሁን ካለው የፌደራል መንግሥት ጋር ተስማምቶ ለመኖር ጥረት ማድረግ የሚችል ይመስለኛል። ቢሆንም ሕወሓት በጣም የተጠላ ድርጅት ነው። በጣም ብዙ ችግር፣ ግፍ ሲፈጽም ነበረ። ማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ አይቀበለውም፤ የትግራይ ሕዝብም አይቀበለውም። በመሆኑም በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ይቀበሉታል ብለን አናስብም። በዚህ ሁኔታ ሕወሓት ያለው አንድ አማራጭ ሥልጣን ለሕዝብ አስረክቦ ተቃዋሚ ሆኖ መቀጠል ነው። በትግራይ ክልል ከተመረጠ ግን ሊያስተዳደር ይችላል። ስለዚህ የግድ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ስላልተስማማ ይጠፋል ማለት አይደለም።ለውጡ በሕወሓት ብዙም ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም ይባላል። በሕዝቡና በእናንተ በኩል ያለውን እውነት ቢገልጹልን?እኛ ለውጥ መደረግ እንዳለበት እናምናለን፤ ለውጡንም እንደግፋለን። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ የለውጡ ሒደት በትክክል እየተመራ አይደለም ብለን እናምናለን፤ ምክንያቱም መጀመሪያ ትኩረት ማግኘት ያለበት የፀጥታ፣ ሠላም እና መረጋጋት መኖር ላይ ነው። መንግሥት በእያንዳንዱ አካባቢ ቁጥጥር ሊኖረው ይገባል።[ሁኔታዎች] ወዳልተፈለገ [መንገድ] እንዳያመሩ፣ ሕዝቡ እንዳይጋጭ ሕግ መከበር አለበት፣ ስርዓት ማስያዝ ያስፈልጋል። በድምሩ የለውጡ ሒደት በትክክል እየተካሔደ ነው ብለን አናስብም። ስለዚህ ወደ ዴሞክራሲ የምናደርገው ሽግግር የተሳካ እንዲሆን መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ ብለን እናምናለን።በነገራችን ላይ የትግራይ ሕዝብ እውነታውን ያውቀዋል። ነገር ግን ሕወሓት አሁን እየተካሔደ ያለውን ለውጥ ‹‹ፀረ ትግራይ የሆነ፣ የትግራይን ሕዝብ ለመምታት የተቃጣ እንጂ የትግራይን ሕዝብ ለመጥቀም አይደለም›› በሚል ነው እየሰበከ ያለው። የትግራይ ሕዝብም ‹‹ለውጡ ሕዝብን ለማጥቃት ወይስ ሕዝብን ለመጥቀም ነው እየተደረገ ያለው›› በሚል ጥርጣሬ ውስጥ ገብቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011

‹‹በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ታግሎ የሚያውቅ ድርጅት ኖሮ

አያውቅም››ዓለማየሁ አረዳ (ዶ/ር)

ፖለቲከኛና የ‹ምሁሩ› መጽሐፍ አዘጋጅ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካቶች የኢትዮጵያ ትልቁ ተግዳሮት የዘውግ ብሔርተኝነት እንደሆነ በስፋት ሲናገሩ ይሰማል። መፍትሔው ምንድን ነው ይላሉ?

ዐቢይ አሕመድ ማለት የኦዴፓና የኢሕአዴግ ሊቀ መንበር ናቸው። እርሳቸው ራሳቸው ዛሬ ትልቁ ተግዳሮታችን ብሔርተኛነት ነው ብለው ነው የሚያስተምሩን። ልብ አድርግ! ራሳቸው የአንድ ብሔርተኛ ፓርቲ ሊቀ መንበር መሆናቸውን።

በመጀመሪያ እርምጃ ነገዳዊ ብሔርተኝነት ወይም በአጠቃላይ ብሔርተኝነት ከታሪክ የተፈጠረ ክስተት እንጂ እንደው ከሰማይ ዱብ ያለ መጥፎ ነገር አይደለም። የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ፣ የተለያየ እምነት የሚያራምዱ፣ የተለያየ ሐሳብ፣ የተለያየ ማኅበረ ሥነ ልቦና ያላቸው ሕዝቦች ከመኖራቸው ጋር የተያያዘ ነው።

ነገድ በጣም ለስላሳ አስተሳሰብ ነው። ያንን ለስላሳ ሐሳብ ወስደው ተበድያለሁ ማለት ሲጀመርና የፖለቲካ ልሂቁ ሲገባበት ወደ ርዕዮት ይቀየራል። ስለዚህ የመጀመሪያ ነገር የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ትልቁ ተግዳሮት ብሔርተኝነት መሆኑን መቀበል ነው። በትምክህተኝነትም በጠባብነት በሚሉት ማለት ነው።

ችግሩ መፈታት አለበት። ለመፍታት ደግሞ ምን መደረግ አለበት የሚለው ቀጣይ ጥያቄ ነው የሚሆነው። መልሱ ደግሞ ከዓለም ታሪክ መማር ነው። በመጽሐፌ ውስጥ ኢትዮጵያ ልትማር የምትችልባቸውን ስምንት አገራት ጠቅሻለሁ። ብሔርተኝነትን በመፍታት ረገድ ሊብራል ዴሞክራሲ ነው የሚያዋጣው። ሶሻሊዝም ብሔርተኝነትን አልፈታም፤ እንዲያውም የበለጠ ወደ ከረረ ሁኔታ ውስጥ ነው የከተተው። መሰመር ያለበት ብሔርተኝነት የሕዝቡ ርዕዮት አይደለም፤ የልሂቁ እንጂ።

ታኅሳስ 9 ቀን 2011

‹‹የምርጫ ሥራ አስቸጋሪ ነው። የፈለግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብሆን እንኳን ነገ ጠዋት ተነስቼ እንደ አዲስ

ቀን እቀጥላለሁ።›› ብርቱካን ሚዴቅሳ

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

የምርጫ ቦርድ ሥራ ከባድ እንደሆነ ይታወቃል። ቢሮውን ከመያዞት በፊት የነበረዎት ግምትና ቢሮውን ተረክበው በተግባር ያገኙት ሲነጻጸር ምን ይመስላል?

የዚህ ቤት [ምርጫ ቦርድ] የረጅም ጊዜ ደንበኛ ነኝ። በተለያየ መልኩ አንዱ ምርጫ አልፎ ሌላው ሲመጣ እንደተወዳዳሪ፣ የፓርቲ ጠበቃ፣ ከምርጫ መዛባት ጋር በተያያዘ፣ እንደ ፓርቲ መሪ ወዘተ ስለዚህ ችግሮቹን በደንብ አውቃቸዋለሁ።

በእርግጥ አሁን ቦርዱ ውስጥ ገብቼ ሳየው እንደጠበቅኩት ነው ያገኘሁት። ከግምቴ በጣም የራቀ፣ አስደነገጠኝ የምለው ነገር የለም። [ችግሮቹም] አዲስ ሆኖብኛል ለማለት አልችልም። ምክንያቱም የለመድኳቸውም የማውቃቸውም ስለሆኑ ነው።

አሁን አዳዲስ የፖለቲካ ተዋናዮች አሉ፤ የመገናኛ ብዙኀን በጣም ሊያግዙ ይችላሉ። ለውጡን የሚመጥን ሥራ ካልሠራን አስቸጋሪ እንደሚሆን በደንብ እረዳለሁ። ሥራው ከባድ ነው፤ ከገመትኩት በላይ ግን ከባድ ነው ብዬ እስካሁን አንገቴን አልደፋሁም።

ስለዚህ በብቃት እወጣዋለሁ ብለው ያምናሉ?

እንደሱ ለማድረግ እምነት ባይኖረኝ እዚህ ለምን እቀመጣለው? እንደአገርም እንደግለሰብም ዕድሉ በጣም ዋጋ የሚሰጠው ነው ብዬ አምናለሁ። ያን ዕድል በጣም ወደ ተሻለ ውጤት ለማምጣት የምችለውን በሙሉ አደርጋለሁ። ‹ይሆናል አይሆንም› ብዬ ብዙም አላመነታም፤ እንዲሆን መሥራት ነው ያለብኝ። አዕምሮዬ ውስጥም ያለው ይኸው ነው።

በተለይ ውጪ አገር ቆይቶ ለመጣ ሰው ተስፋ የሚያስቆርጡ ብዙ ነገሮች አሉ። ፍጥነት እና ነገሮች ቀልጠፍጠፍ ብለው እንዲሠሩ ትፈልጋለህ፤ የቴክኖሌጂውም፣ የሰው ኃይል አቅሙም በምትፈልገው መንገድ አይሔድልህም። የፈለገ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብሆን እንኳን ነገ ጠዋት ተነስቼ እንደ አዲስ ቀን እቀጥላለሁ።

ቅጽ 1 ቁጥር 12 ጥር 25 ቀን 2011

Page 19: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 19

የቅርብ ወዳጆቻቸው እንደገለጹት የሥመ ጥሩው፣ በአንዳንዶች ደግሞ የአወዛጋቢው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ሕይወት ያለፈው ማክሰኞ፣ መስከረም 19 ከምሽቱ 4 አካባቢ ነው። ረበዕ፣ ከማለዳው ጅመሮ ህልፈታቸው በማኅበራዊ ትስስር መድረክ እንደ ሰደድ እሳት መሰራጨት ጀመረ፤ መደበኛ መገናኛ ብዙኀንም የሞታቸውን ዜና አሰሙ።

በሚያስገርም ፍጥነት መርዶው ከተነገረ በሰዓታት ውስጥ የሃዘን መግለጫ ዶፍ ከየአቅጣጫው ይዘንብ ጀመረ። ረፋድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስቡክ ላይ “የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከመጨረሻው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል።” ሲሉ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተከትሎም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመሳሳይ ይዘት ያለው የኀዘን መግለጫዎችን በተከታታይ ገለጹ።

ከባለሥልጣናቱ በተጨማሪ ተርታው ሕዝብም ባገኘው አጋጣሚና መድረክ ኀዝኑን ገልጿል፤ ኢትዮጵያ አንደኛና ብቸኛውን የአገር ዋርካ፣ የአገር ሽማግሌ፣ የአገር አድባር አጣች ብለዋል። ቤተ መጽሐፍቱ ተቃጠለ በሚል አገላለጽ የኀዘናቸውን ከባድነት ለማሳየት የተጠቀሙም ነበሩ።

የሆነው ሆኖ ብዙዎች ፕሮፌሰር መስፍን ለአገራቸው ኢትዮጵያ የነበራቸው የማይናወጽ ፍቅር፣ በማይነጥፈው ብዕራቸው በርካታ ጠቃሚ መጻሕፍት ማበርከታቸውን፣ ለምንም እና ለማንም አይበገሬነታቸውን፣ ለይሉንታና ሰው ምን አለኝ ኬረዳሽነታቸውን፣ ሐባቸውን ሳያሽሞነሙኑ እንደወረደ ማቅረባቸውን፣ ለማንም ያለማጎብደድ ባህሪያቸውን፣ በማንም ላይ (ቀደም ብለው እንኳን ያወደሱት ቢሆን) ያለ ፍርሃት የሚሰነዝሩት የሰላ ትችታቸውን፣ እስከመጨረሻው (እድሜ እንኳን ተጭኗቸው) ጥርት ያለ ሐሳባቸውን ጥርት ብሎ በሚወርድ አነጋገቸውን እንዲሁም እስከ እስትንፋሳቸው መጨረሻ ድረስ በጽሑፍ ሐሳባቸውን ማጋራታቸውን በመጥቀስ ትውስታቸው ሆኖ እንደሚቀጠል ማስታወሻ ጽፈዋል። በአጠቃላይ ለዕድሜ ልክ አበርክቷቸው ምስጋና ቸረዋቸዋል።

አንዳንዶች ለመንግሥት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። መንግሥት ኀዘኑ ከምር ከሆነ በተግባር የተገለጠ ማስታወሻ በሥማቸው ይሰይምላቸው

ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ሌሎች ጥያቄው ገፋ አድርገው እስቲ ለዕድሜ ልክ አገልግሎታቸው ሃውልት ያሳንጽላቸው አሊያም መንገድ ወይም አደባባይ በሥማቸው ይሰይም ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። በሸገር ፓርክ ውስጥ ከሚገነቡት ቤተ መጻሕፍቶች ውስጥ አንዱን በሥማቸው ይሰየም ሲሉ ምክረ ሐሳባቸውንም ያቀረቡ አሉ።

ይህንን ጥያቄ ሰምቶ ይሁን በራስ ተነሳሽነት ኢዜማ ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል። በዋና ጽሕፈት ቤቱ የሚገኘውን ትልቁን የስብሰባ አዳራሽ “መስፍን ወልደማሪያም የስብሰባ አዳራሽ” ብሎ ሰይሞታል። የኢዜማ ተግባር በብዙዎች መወደስን አስገኝቶለታል።

ይሁንና በቅርብ ወዳጆቻቸው የኔታ ተብለው የሚጠሩት የፕሮፌሰር መስፍን ህልፈት ያልሞቃቸውም ያልበረዳቸው ሰዎች አልታጡም። ከዚህም አለፍ ሲል በቀደመው ጊዜ ፕሮፌሰሩ ያነሷቸውን ሐሳቦችና አመለካከታቸውን እንደ መከራከሪያ በማንሳት ቅሬታቸውን ለመግለጽ አጋጣሚውን የተጠቀሙበትም አሉ።

አብነት ለመጥቀስም ፕሮፌሰር መስፍን “አማራ የሚባል ማንነትም ብሔርም የለም፤ አማራን እወክለዋለሁ የሚል ሰው ባገኝ አዕምሮው በሽተኛ ነው እላለሁ” ብለዋል በሚል ኀዘናቸውን የገለጹ ሳይሆን ወቀሳ የሰነዘሩም አሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘም አማራን ለማጥፋት የተነሱ ሁሉ ታሪክ ሆነው ድራሽ አባታቸው ጠፍቶ እንደ ጉምተነው፣ እንደ ጢስ በነው አልፈዋል ሲሉ ጠንከር ያለ ነቀፌታም የሰነዘሩ ይገኛሉ።

የፕሮፌሰር መስፍን የቀብር ሥነ ስርዓትን በተመለከተ በይፋ ባይነገርም ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ ማክሰኞ፣ መስከረም 26 ይፈጸማል ሲሉ አንድ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ የሚሳተፉ ሰው ለአንድ ሚዲያ መናገራቸው ተሰምቷል።

ከኹለት ሳምንት በፊት ከቤት ሠራተኛቸው ተጋባባቸው በተባለው የኮሮና ቫይረስ ሰበብ ተመርምረው እሳቸውም የኮረና ቫይረስ እንዳለባቸው የተነገራቸው ፕሮፌሰር መስፍን፥ ሕክምና ይከታተሉበት በነበረው ጳውሎስ ሆስፒታል ለቀናት በጥሩ ጤንነት ላይ የነበሩ ሲሆን በድንገት በሞቱበት ቀን መደካከም ማሳያታቸውን የቅርብ ሰው ነኝ የሚሉ አንድ ግለሰብ ለአንድ ሚዲያ አስታውቀዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን የኹለት ሴት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን ኹቱም ልጆቻቸው በዶክትሬት የትምህርት ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል።

ከተናጋሪው አንደበት

ሰሞነኛየየኔታመስፍንስንብት!

አምሀ ዳኘውበአሐዱ ቴሌቭዥን ኬላ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ

ከተናገሩት።

1 ቻይና 12.8

2 አሜሪካ 8.6

3 ጀርመን 8

4 ጃፓን 3.8

5 ኔዘርላንድ 3.7

6 ኮሪያ 3.1

7 ፈረንሳይ 3

8 ጣልያን 2.8

9 እንግሊዝ 2.5

10 ቤልጂየም 2.4

አይስላንድ 46,074

ደረጃ አገራት በመላክ የሚሸፍኑት አገር (በመቶኛ)

ቱ ምርታቸውን ወደ ተቀሩት አገራት የሚልኩ አገራቶች

አፍሪካ በ15 ዓመታት ውስጥ (ከፈረንጆቹ 2000 እስከ 2015)

በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ያጣችው በንዘብ፤

የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት

ትእይንተ ዜና

በአለም ላይ ከፍተኛ ከራሳቸው አልፈው ወደ ተቀሩት አገራት ምርቶቻቸውን በከፍተኛ መጠን የሚልኩ አገራት አሉ። በዚህም መሰረት ቪዡዋል ካፒታሊስት ኮም የተሰኘ ድህረ ገፅ በዚህ ምርቶቻቸውን ከራሳቸው አልፈው ወደ ተቀሩት አገራት የሚልኩ አገራት በማለት አስርቱን ለይቶ አውጥቷል። በዝርዝሩ መሠረት ቻይና በምርቶቿ

በምታካልላቸው አገራት ብዛት አንደኛ ላይ የተቀመጠች ሲሆን አሜሪካ እና ጀርመን ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ተቀምጠዋል። በመቀጠል ጃፓን፣ ኔዘርላንድ፣ ኮሪያ ከአራት አስከ ስድስት ያለው ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ፤ ፈረንሳይ ጣልያን ፣ እንግሊዝ ከሰባት አስከ ዘጠኝ ያለው ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በመጨረሻም ቤልጂየም አስረኛ ደረጃን በመያዝ በዝርዝሩ ላይ ተካታለች።

ፎቶ ሳሙኤል ሀብተአብ

ማረፊያ

ቢሊዮን ዶላር836

ምንጭ፡ -ቪዡዋል ካፒታሊስት ኮም (2018)

Page 20: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 20

ሕይወት እና ጥበብ

የመጥፎዎች ሩጫ ነፍስ እንዲኖረው

ያገዘው የሊቃውንቱ ዝምታ ነው

ትኩረቱን በዛ ላይ አድርጎ ነው። በትህትናም ከራሱ ሥም ይልቅ የመጽሐፉን ሐሳብ ገንኖ እንዲወጣ በመሻቱ ነው፤ ለአዲስ ማለዳ እንደነገራት።

ነገር ግን ያንን ማድረጉ ትክክል እንዳልነበር ከመረዳት ላይ መድረሱን አንስቷል። ለዛም ነው ‹ሰባት ቁጥር› መጽሐፉን በሦስተኛ እትሙ በሥሙ ያደረገው።

የይባቤ ዕይታ

አገራት ዘመናዊ ቀለምን መላበስ ሲጀምሩ እንደ ብልሃት መጠናቸው የራሳቸውን የኖረ እውቀትና ባህል ሳይዘነጉ ነው። አንዳንዶች ደግሞ የቀደመውን ቀለም ይተዋሉ፤ ይረሳሉ። በኢትዮጵያም በብዙ መልክ የተተወ፣ የተዘነጋ አገር በቀል እውቀት አለ። ይህም ክፍተቱ ምኑ ጋር ይሆን የተፈጠረው የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

ይባቤ በበኩሉ የሆነ ቦታ ላይ የተሰበረም ባይሆን የተጣመመ ድልድይ አለ ይላል። ‹‹ችግሩ የአንድ የሆነ አካል ጥፋት አይደለም። ሁላችን በቀጥታም በተዘዋወሪም አጥፍተናል። ፖሊሲና ዐለማቀፍ ተጽእኖም አለ።›› ሲል ዘመናዊነት ከአገር በቀል እውቀት ጋር ተሰናስሎ ያልቀጠለበትን ምክንያት ያስረዳል።

ያም ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ዝምታም ለዚህ አስተዋጽኦ አድርጓል ባይ ነው። ሊቃውንቱ ዘመኑን የሚመጥን ሥራ እየሠሩ አይደለም። መናገር ባለባቸው ደረጃ አለመናገራቸው፣ እንደ ጥንቱ አራቱ ኃያላን እስከሞትና መሰየፍ ድረስ መንግሥታትን የሚታገሉ በብዛት አለመታየታቸው ለዚህ ሰበብ ሆኗል። የእምነት አባቶችና አዋቂ የተባሉት ሳይቀር ከፖለቲካው መገናኘታቸው ደግሞ ዝምታቸውን አጠንክሮታል።

‹‹የመጥፎዎች ሩጫ ነፍስ እንዲኖረው ያገዘው የእነርሱም ዝምታ ነው።›› ሲል በአንድ መንገድ ይጠቀልለዋል። ከእነዚህም በተጓዳኝ በስርዓተ ትምህርት ሆነ ተብሎ የጎደፈም አለ የሚለው ይባቤ፣ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ለዚህ ትውልድ ሊታዘን እንደሚገባ ይላል።

በሊድያ ተስፋዬ

አሜሪካዊው ደራሲና የተውኔት ጸሐፊ ሬይ ብራድበሪ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹የአንድ አገር ባህል ለማጥፋት መጻሕፍትን ማቃጠል አይጠበቅም። ሰዎች እንዳያነቡ ማድረግ ብቻ ነው።››

መጻሕፍት የእውቀት፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የማንነትና መሰል አገር የሚያክል መረጃ ተሸካሚዎች ናቸው። በአገራችንም ምንም እንኳ የንባብ ባህሉ የሚታማ ቢሆንም፣ የተሰጣቸውን መክሊት ሳያተርፉበት ላለመመለስ የሚተጉ፣ የሚጽፉ ደራስያን ብዙ ናቸው። ከዘመናዊት ዓለም የተገኘውን ክህሎት ከነባር እውቀት ጋር አዋህደው ዘመንን የዋጀ ሥራም የሚያቀርቡ ጥቂት አይደሉም።

እንዲህ ባለ መንገድ ስድስት መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃው ይባቤ አዳነ የአዲስ ማለዳ እንግዳ ነበር። ብዙዎች ‹አክሳሳፎስ› በተሰኘ የመጀመሪያ የመጽሐፍ ሥራው የሚያወሱት ሲሆን፣ በቅርቡ ለንባብ ያበቃው ‹ሰባት ቁጥር› መጽሐፍም እንደዛው ለንባብ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ቀልብ ገዝቷል። በኹለቱ መካከልም አምስት መጻሕፍትን አድርሷል።

ይባቤ ከአዲስ ማለዳ ጋር ባደረገው ቆይታ ስለሕይወት ጉዞው፣ ስለመጽሐፍቱ እንዲሁም በአገር በቀል እውቀት ላይ ስላሉ አመለካከቶች ዕይታውን አካፍሏል።

ስለ ‹ሰባት ቁጥር›

ሰባት ቁጥር መጽሐፍ ለንባብ የበቃ ሰሞን በማኅበራዊ ድረ ገጾች የተለያዩ ሐሳቦች ሲነሱ ነበር። ይልቁንም በተመሳሳይ ርዕስ ከወጣውና በመስፍን ሰለሞን ሙሀባ ከተጻፈው መጽሐፍ ጋር በተገናኘ የተነሳ ውዝግብ ነው። ጉዳዩንም የተለያዩ መገናኛ ብዙኀን በትኩረት የቃኙት ሲሆን፣ ኹለቱን ደራስያን በአንድ መድረክ በማገናኘት እንዲነጋገሩም ሆኗል። መጽሐፍቱ በርዕስ ይመሳሰሉ እንጂ በይዘት ግን ልዩነት እንዳላቸው ልብ ይሏል!

ይህ ይቆየንና ወደተነሳንበት ጉዳይ እንመለስ። ይባቤ በዚህ መጽሐፉ ‹ሰው

‹‹ለሥነ ጽሑፍ ያገዘኝና ብርታት የተሰጠኝ የቤተክርስትያን ትምህርት ነው። ጅማ ተጓዳኝ መጻሕፍትን እያነበብኩኝ ስሄድ ራሴን መፈለግ ጀመርኩ። እንዴት ከተደራሲ ጋር መግባባት እንዳልብኝ የገባኝና መንገዱን ያገኘሁት ደግሞ ከዘመናዊው ትምህርት ነው።›› ይላል ይባቤ፤ የመጽሐፍ ሥራዎቹ ቅኝት ከየት የተወረሰ እንደሆነ ሲያስረዳ።

መደበኛ ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ ነበር፣ የኹለተኛ ዓመት ትምህርቱን ሲጀምር ነው አክሳሳፎስ የተሰኘ የመጀመሪያ መጽሐፉን የጀመረው። መጽሐፉን እያዳበረው ሄዶ፣ ሐሳብ በሐሳብ ላይ እየታከለ፣ በንባብ የጎደለውን እየሞላ፤ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ጨርሶ አዲስ አበባ ገባ። ያኔ ነው አክሳሳፎስ የሕትመት ብርሃን ያየው።

ይባቤና የብዕር ሥም

ይባቤ የመጽሐፍ ሥራዎቹን ‹ሰባት ቁጥር›ን ጨምሮ በብዕር ሥም ነው ያወጣቸው። ይህንንም የሚያደርገው ዋናው ጉዳይ ሊያስተላልፍ የፈለገው ሐሳብ መሆኑን በማመን

የደራሲው ዕይታዎች - ከ‹ሰባት ቁጥር› መጽሐፍ

ባሻገር

ማለት ሰባት ቁጥር ነው።› ይላል። በኢትዮጵያ ሰባት ቁጥር የተለየ ትኩረት የተሰጠው ይሁን እንጂ በውጪ አገር ሁሉንም ቁጥር ከሰው ጋር ያገናኛሉ። ዓለም ራሱ ቁጥር ነው ብለው ስለሚያምኑም ነው ሲል ያስረዳል።

ሰባት ቁጥርን በሚመለከት ታድያ በባህርማዶም የተጻፉ እንዳሉ የሚያነሳው ይባቤ፣ እነዛም ግን በሰባት ቁጥር ላይ ልዩ ትኩረት አድርገው ሳይሆን ሰባትን እንደሌሎች ቁጥሮች አንድ አካል አድርገው ነው። በኢትዮጵያ ግን ስለ ሰባት ቁጥር፣ ከሰውና ከተፈጥሮ ጋር ያለው ግንኙነትና በዚህም ውስጥ የሚነበበው ምስጢር ዙሪያ የተጻፈ ብዙ እንዳለ ይጠቅሳል። ‹‹የበለጠ ማጥናት ግን ሊጠይቅ ይችላል›› ይባቤ እንዳለው ነው።

ይህ መጽሐፉ ታድያ ስለሰባት ቁጥር ብቻ አይደለም። ይልቁንም ሕይወትን በሰባት ቁጥር ውስጥ የሚያሳይ ነው። ከዛም ተሻግሮ ደግሞ ግብጽና ኢትዮጵያን በሚመለከት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮችንም ያነሳል።

እንዴት ወደ መጽሐፍ?

‹‹ለሕይወት መንገዴ ትልቁ አስተዋጽኦ ቤተክርስትያን ናት።›› ይላል መለስ ብሎ ጉዞውን ሲያስታውስ። በቤተክርስትያን ትምህርት ዘልቆ እስከ ቅኔ ቤት መማሩም ዕይታውን እንዲያሰፋ እንደረዳው፣ ቅኔ ፈጠራን ለማዳበር ምን ያህል እንደሚያግዝም አያይዞ ያወሳል።

ሌላው ወደ መጽሐፍ ሥራ እንዲዘልቅ ያደረገው ምክንያት ደግሞ በመደበኛ ትምህርት ላይ ሳለ ተጓዳኝ መጻሕፍትን ማንበቡ ነው። ‹‹የመጀመሪያና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ጅማ ነው የተማርኩት። በዛም ተጓዳኝ መጽሐፍ ማንበብ ጀመርኩኝ።›› ይላል። ታድያ አንድ ቀን በሥም ብቻ ያውቀው የነበረውን የአቤ ጉበኛን መጽሐፍ አነበበ። የአቤ ጉበኛን የትውልድ ስፍራ ያውቅ ነበርና፤ ‹ከዚህ አካባቢ ይህን የሚያህል ታላቅ ደራሲ ወጥቷል!› የሚለው ጉዳይ በርትቶ ተሰማው። ምንአልባት ያ ቅጽበት ዛሬ የደረሰበት ጉዞ ውጥን ሳይሆን አልቀረም።

Page 21: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 21

ሕይወት እና ጥበብ

ታድያ ትውልድም ጋር እንከን ሳይኖር ቀርቶ አይደለም። የሥልጣኔን ምንነት በሚገባ አለመረዳት፣ ቆም ብሎ አለማየትና ከውጪ የቀረበውን ሁሉ ጥሩ ነው ብሎ መቀበል በትውልዱ ላይ የሚታይ ግድፈት ነው ሲል ይገልጸዋል። ‹‹ለዓለማቀፍ ተጽእኖ ሰለባ መሆንም ድክመት ነው። በዚህ ወጣት ላይ ብዙ ተጽእኖና ፈተና አለ። በገዛ ሞባይልና ቲቪው የሚቀርብለት ብዙ ነገር አለ። የሚመራው መንግሥትም ሲዋሽ ያያል። ከላይ ደፍርሶ ከታች ሊጠራ አይችልም።›› ሲል በሁሉም መልኩ ለውጥ እንደሚያሻ ያሳስባል።

ኢትዮጵያዊ ሰው - ከ‹ሰባት ቁጥር› ባሻገር

ሰባት ቁጥር ከሰው ጋር ያለው ትስስርና ተጓዳኝ ምስጢር አንባብያን ከመጽሐፉ ያገኙት ዘንድ እናቆየው። ወዲህ ግን ስለ ሰውነት ብሎም ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ይባቤ አንድ ክስተትን ያወሳል። ደርግ ከሥልጣን ወርዶ ኢሕአዴግ ወደ አገር መምራት ሊመጣ በነበረው ወቅት አገር ለሰባት ቀናት ያለመንግሥት ቆይታለች። ግን ሰላም ነው። ያ ክስተት ዛሬ ቢሆንስ ኖሮ?

አጭር በሚመስል የዓመታት ልዩነት ውስጥ ያለው በግብረገብነት እንዲሁም ሰብአዊነት ላይ ያለው ልዩነት የደረስንበትን ደረጃ ያሳያል ብሎ ያምናል፤ ይባቤ። ‹‹አሁን መንግሥት ባይኖርስ?› ሲል ይጠይቃል። ‹‹መከላከያ/ወታደር እንኳ እያለ ሰው ይሞታል። ደረጃችን እንዴት እንደወደቀ ዐይተናል።›› ሲል ይገልጸዋል።

አያይዞ ያነሳውና እንደ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን እንደ አፍሪካም ያለው ችግር፣ ፈታኝ ነገር ካልገጠመ በቀር ለመፍትሄ አለመዘጋጀትን ነው። ‹‹ትምህርት ቤት ስንማር እንኳ ፈተና ሲደርስ ነው የምናጠናው። ብዙ ነገር ተገደን ነው የምናደርገው። ይህ የሆነው ግብረገብነት ስለጎደለን ነው።›› ሲል ያለውን ስህተት ያነሳል።

የውጪውን ተጽእኖ አውስቶ፣ ሰው ሊገደብ አልያም ተጽዕኖ ሊያርፍበት የሚችለው በሚፈቅደውና በሚቀበለው መጠን ነው ይላል። በአንጻሩ ግን በተለይም በከፍተኛ የትምህርት

ተቋመት ከውጪ እንደወረደ የሚመጣውን በመቀበል ባህር ማዶ ያሉ ባለጸጋ አገራት ያሻቸውን ተጽእኖ እንዲያሳርፉ አስችሏቸዋል።

‹‹ዩኒቨርስቲ የሰው በረት ሆኗል/ነው። እንደውም አሁን ይመጥነዋል። በረት የእንስሳ ነው፣ እኛ ከዛም አንሰናል። እንስሳ ዱላ ይዞ አይዞርም።›› ሲል በትምህርት ተቋማት ይታይ የነበረውን ጥፋት አብዝቶ ይኮንናል። በዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን ዝም ብሎ እንዲውጥ የተደረገ ወጣት፣ የተሰጠውን ሳያመነዥግ ይውጣል። ይህም ለአገሩም ለራሱም አጥፊ እንዲሆን ያደርገዋል።

‹‹መጀመሪያ ሰው በራሱ ማንነት ራሱን ችሎ መቆም አለበት። ክፉና ደጉን የሚለይ አእምሮ ተሰጥቶናል። ሁሉም ሰው እያንዳንዱ የጎደለውን የሚሞላበት የተለያየ የተሰጠው ጸጋ አለ። ሁሉንም አንድ የሚያደርገው ደግሞ አእምሮው ነው። መጀመሪያ ለትልቅ ዓላማ የተፈጠረ ሰው መሆኑን መቀበል አለበት። ቀጥሎም በአገሩ እውቀት መመካት፣ ለማስተካከል እንዲቻልም የተበላሸውን ማወቅ ያስፈልጋል።›› ይላል ይባቤ።

ያም ሆነ ይህ አሁንም ተስፋ አለ ባይ ነው። ይልቁንም ትውልድ ወደ ቀደመው የአገሩ እውቀት መጥቶ ለማወቅና ለመመራመር የሚተጋበት ጊዜ መምጣቱ እንደማይቀር ያምናል። እንዴት የተባለ እንደሆነ መልሱ እንዲህ ነው፤ ‹‹ምክንያቱም የውጪውን ቃርመን የሚጨበጥ እናጣለን። ፈረንጅ የሚሰጠን ገለባውን ነውና።›› ነው መልሱ።

የሕይወት ጉዞ

ይባቤ በሕይወቱ በብዙ ፈተና አልፏል። ወላጅ እናቱን በልጅነት እድሜ ያጣ ሲሆን፣ ያደገው ከአያቱ ጋር ነው። እህት ስለሌለው ቅር ቢሰኝም ኹለት ወንድሞች ግን አሉት። አያቶች አንደላቀው እንደሚያሳድጉ ይታወቃልና፣ እርሱም በተመሳሳይ ደስተኛ ሆኖ ልጅነቱን እንዳሳለፈ ያወሳል።

ያም ቢሆን እንደ ልጅ መጫወትና መቦረቅን

የመረጠ አልነበረም። እንደውም ለትምህርት ልዩ ፍቅር ነበረውና ትኩረቱ ለዛው ነበር።

በቤተክርስትያን ትምህርት ነው ትምህርቱንም የጀመረው። አንድ ብሎ ከንባብ ቤት ጀምሮ እስከ ቅኔ ቤትም ዘልቋል። ይህንን ትምህርት እንዲማርም አያቱ ምክንያት እንደነበሩ ያስታውሳል። ‹‹የመጀመሪውን መስመር የዘረጋችልኝ አያቴ ናት። የእህል ጉዳይ ችግር የለም፤ ትምህርት ነበር ችግሩ። እንደ አሁን አይደለም።›› ሲልም ከቤተክህነት ትምህርት ውጪ ዘመናዊ የቀለም ትምህርት በቶሎ እንዳልጀመረ ያወሳል።

እድሜው ከፍ እያለ ሲሄድ ታድያ የራሱን መንገድ የሚያወጣ፣ የሌሎች ፍላጎት እንዲጫንበት የማይሻ ሆነ። ‹ነገስ?› ብሎ የወደፊቱንም ማሰብ የጀመረው በለጋ እድሜው ነው። የቤተክህነቱን ትምህርት ከገፋበት ወደ መሪጌታ ማዕረግ እንደሚያደርሰው ተረዳ። ያ ግን ጥጉ እንዲሆን አልፈለገም። እናም ዘመናዊ የቀለም ትምህርትን አብዝቶ ፈለገ። አደረገውም።

‹‹ቤተሰቤ በዚህ ደስተኛ አልነበረም። ብዙም ተቀጥቻለሁ። ጅማ ድረስ የሄድኩትም ለዛ ነው። ካሰብኩት ዓላማ ዝንፍ ላለማለት ብዬ።›› ሲል የትምህርት አሃዱውን ለአዲስ ማለዳ አጫውቷታል።

ትምህርትን ፍለጋ ወደ ጅማ አቀና። ወንድሙ በዛ ቢኖርም ከእርሱ ጋር ለመኖር አልሆነለትም። የዚህም ምክንያቱ ቤተሰቦቹ ወደ ዘመናዊ ትምህርት መግባቱን ስላልወደዱ ወንድሙም ከቤተሰብ መቀያየምን ባለመፈለጉ ነው።

ይባቤ በዚህም ጉዞው አልተገታም። ‹‹ዓላማዬ መማር ብቻ ስለሆነ ብዙ ውጣ ውረድ አሳለፍኩኝ።›› ይለል፤ ከብዙ በጥቂቱ እያነሳ። ያኔ ነው ፓታክ ከሚባል በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና መምህር ከሆነ አንድ ሕንዳዊ ጋር የተገናኙት።

ይህ ሰውም ሊያስተምረው ፈቀደ። በቤቱም

እንደ ጥበቃ እያገለገለው፣ በር በመክፈትና በመዝጋት እንዲሁም የተባለውን በመታዘዝ፣ ትምህርቱን እየተማረ ኑሮውን ከፓታክ ጋር አደረገ።

በዘመናዊ የቀለም ትምህርት ጎበዝ የነበረው ይባቤ፣ ይማርበት በነበረው ‹ጅሬን› በሚባል ትምህርት ቤት፣ መምህራኑ ሳይቀር ተሟግተው ክፍል እንዲዘል መደረጉንም በፈገግታ ያነሳል። እርሱ ዝም ብሎ ሳለ መምህራኑ ስለእርሱ ያደረጉትን ሙግት እንደማይረሳውም ጭምር።

ሕንዳዊው ፓታክም ያንን ሲሰማና የተማሪው ይባቤን ውጤት ሲያይ በእጅጉ ደስተኛ ይሆን ነበር። ‹‹ቀናነትን፣ ለሰዎች መኖርን የተማርኩት ከእርሱ (ከፓታክ) ነው። ማህበራዊ ሕይወት የሚባለው ለሰዎች መኖርና መስጠት መሆኑን ያወቅኩት ከውጪ ከመጣ ፈረንጅ ነው።›› ይላል።

ታድያ ፓታክ ይባቤን ምን ላድርግልህ ሲል ይጠይቀዋል፤ ለጎበዝ ተማሪ እንዲህ ማለት የተገባ ነውና። ይባቤም በጊዜው ትምህርቱ ብቻ ነበርና ቁምነገሩ ‹‹ነገ ድንገት ባትኖር ትምህርቴ ሊታጎል ይችላል። እናም ሥራ ፈልግልኝ›› ሲል ሥራ ማግኘትና እየሠራ መማር እንደሚፈልግ ይገልጻል። ፓታክም ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ደብዳቤ ጻፈ። ያኔ ይባቤ ጅማ ዩኒቨርሲቲ አትክልተኛ ሆኖ እየሠራ ከሚወደው ትምህርት ጋር ቆይታውን ቀጠለ።

‹‹በዛ እየሠራሁ አንደኛና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ጨረስኩኝ። አሥራ ኹለተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሲቀረኝ ግን ወደ ጎጃም ሄድኩኝ።›› ይላል። ይህ የሆነው ደግሞ በጅማ ኦሮምኛ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ፈተና ይሰጥ ስለነበር፣ እርሱ ደግሞ ለፈተና በሚያደርስ መጠን ቋንቋውን አውቀዋለሁ ብሎ ስላላመነ ነው።

‹‹ጊዜአዊ ምቾት ለዘላቂው ሕይወት ጉዳት ሊሆን አይገባም ብዬ አምናለሁ። መሠረት ላይ መሥራት ያስፈልጋል። አሁን ተመችቶ በኋላ ከመቸገር አሁን ተቸግሮ በኋላ መደሰት ይሻላል። ቀጣዩን ነበር የማስበውም።›› ሲል በጅማ ዩኒቨርስቲ ከነበረው ምቾት ይልቅ ትምህርቱን አስቀደመ። 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተነ በኋላ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ደረሰው። የቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርቱንም በጎንደር ዩኒቨርስቲ አጠናቀቀ።

በቅርቡና ወደፊት

ይባቤ ሰባት ቁጥር የተሰኘው መጽሐፍ ኹለተኛ ቅጽ እንደሚኖረው ተናግሯል። ይህ መጽሐፍ የሚወጣበትን ጊዜ በእርግጥ መናገር ባይቻልም፣ ይህን ዓመት ማለትም 2013ን እንደማይዘል ግን ያረጋግጣል። ‹‹ሐሳብ ስለሚጨምር፣ የሚያጠናክሩ መጻሕፍትም የማገኝ ስለመሰለኝ ትንሽ ማቆየቴ አይቀርም።›› ሲል ተናግሯል።

በሌላ በኩል አቤ ጉበኛን ደጋግሞ የሚያነሳው ይባቤ፣ ብዙ አልተነገረለትምና አቤ ጉበኛ በቋሚነት የሚወሳበትን አንዳች ሥራ የመሥራት ሐሳብ አለው። በጊዜው በእድሜው ከሚጠበቀው በላይ ሠርቷል ሲል የሚያወሳውን አቤ ጉበኛን፣ ለሞተለት ዓላማ እስከሞት የሄደ መሆኑ ደግሞ ምን ያህል ትልቅ ዋጋ እንዳለው ለመጥቀስ ይሞክራል። እና ‹‹አቤ ጉበኛ ለእኔ ጉልበቴ ነው።›› ይላል።

‹‹ለወደፊት ብዙ ሐሳብ አለኝ። በተለይ ከንባብ ጋር በተገናኘ ልሠራ የማስበው አለ። እንደ አቤ ጉበኛ ያሉ ሰዎችም የሚዘከሩበት ቋሚ መድረክ፣ ትምህርት ቤት ከመክፈት ጀምሮ ወይም ሲምፖዝየም ማዘጋጀት እፈልጋለሁ። በሕይወት ያሉ ጉልበት የሚሆኑ ሰዎችንም ወደፊት የማምጣት ሐሳብ አለኝ። እነዚህ ሊቃውንት ዝምታቸው አንድም መድረኩ ባለመፈጠሩ ሊሆን ይችላልና።›› ብሏል።

በዚህ እናጠቃል፤ ይባቤ ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበረው ቆይታ ከንግግሩ መካከል ይህን አለ፤ ‹‹እውቀትና ችሎታ ብሔር የለውም። ከትጋት የሚመጣ ነው እንጂ።››

Page 22: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 22

የደብረብርሃንከተማንወደ‹ሪጅዎፖሊታንት›...

ኤጀንሲውበ1.6ቢሊዮንብርባለ26ወለልህንፃሊገነባነው

ለአነስተኛየዳቦጋጋሪዎችዱቄትማቅረብ...

ከገፅ 1 የዞረ

ከገፅ 1 የዞረ

በእዮብ ውብነህ

የፌደራል ሰነዶች ምዝገባና ማረጋጋጫ ኤጀንሲ በ1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ለዋና መስሪያ ቤትነት የሚያገለግል ባለ 26 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ መሆኑ ተገለፀ።

የኤጀንሲውን ህንፃ ለመገንባትም በፌዴራል መንግስት ህንፃዎች ግንባታ ጽ/ቤት እና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን መካከል ሀሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 የኮንትራት ስምምነት ፊርማ ተከናውኗል።

በስምምነቱም መሠረት የሚገነባውን ባለ 26 ወለል (4B+G +21) ህንፃ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ዋጋ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሰርቶ እንዲያስረክብ መስማማቱን የፌዴራል ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ግንባታው በአዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አደባባይ በሚባለው አካባቢ 2 ሺህ 758 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ላይ እንደሚከናወንም ታውቋል፡፡

ኤጀንሲው በአዲስ አበባ 14 ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች እንዳሉት የገለፁት ሙሉቀን ዋና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ 14ቱም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡባቸው ህንፃዎች የኪራይ እንደሆኑ ገልፀው ለሁሉም የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መስሪያ ቤቶች በአጠቃላይ በየአመቱ ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ የኪራይ ወጪ እየከፈሉ እንደሆነ ኃላፊው ገልፀዋል።

የኤጀንሲው የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በጣም እያደገ መጥቷል የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከዚህ አንፃር የሚሰጠውን አገልግሎት በተቀላጠፈ መንገድ መስጠት እንዲቻል አመቺ የሆነ ህንፃ አስፈላጊ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ህንፃ ማስገንባት ባይቻል እንኳን ኤጀንሲው በዋና መስሪያ ቤትነት የሚገለገልበት የራሱ የሆነ ህንፃ እንዲኖረው በመታሰቡ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦታ እንዲሰጠው በመጠየቅ ሲጠባበቅ መቆየቱን ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት ኤጀንሲው ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የሚያስፈልገው ቦታ መሃል ከተማና ለተገልጋዩ ምቹ መሆን ስለሚገባው ቦታ ሲፈለግ ቆይቶ 2009 መጨረሻ አካባቢ ይኸው ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኘው ቦታ ለግንባታ እንደተሰጠው የሚገልፁት ሙሉቀን ከፍቃድ እና ከጨረታ ሂደት ጋር የተያያዙ ስራዎች እየተሰሩ እስካሁን መቆየቱን ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።

በሚገነባው አዲስ ህንፃ ላይ በዋናው መስሪያ ቤት በአንድ ህንጻ ስር ተሰባስበው የሌሉና ከቦታ ጥበት አንፃር በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተበታተኑ አገልግሎቶችን በአንድ ማእከል እንዲሰጡ

15 ኩንታል በ 12000 ብር በወር ኹለት ጊዜ ይረከቡ እንደነበር ይናገራሉ። ነገር ግን ከትስስር (መንግሥት የዳቦ ዱቄትን በቅናሽ የሚያስረክባቸው አባላት መደብ) እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ፣ ከግል ነጋዴዎች ላይ አንድ ኩንታል የስንዴ ዱቄት በ 1 ሺሕ 800ብር ለመግዛት እየተገደዱ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት የዳቦ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጋቸውን ይናገራሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ዳቦ ጋጋሪዎቹ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነ በምን ምክንያት ዱቄት መሰጠት እንዳቆመ ተደጋጋሚ ጥያቄ ብንጠይቅም ምክንያቱ እንኳን ሳይነገረን ‹‹ እስከ መስከረም ግማሽ ወይንም ጥቅምት መጀመርያ ላይ ይመጣል ጠብቁ›› የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እና በዚህ ምክንያት ከባድ ኪሳራ ውስጥ ከመግባት ባለፈ አሁን ላይ መንግስት እያደረገ ያለው ሸገር ዳቦ ስለተከፈተ አነስተኛ ዳቦ ጋጋሪዎችን ከገበያ የማስወጣት ስራ

እየተሰራ ነው በማለት ይናገራሉ፡፡ ‹‹ብንናገርም የሚሰማን አካል የለም›› አሁን ካለው አንፃራዊ ሁኔታ ጋር ስናየው ‹‹ ስንዴው ሸገር ዳቦ ጋር እና በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሰዎች ወደ እዛ እየሄደ ነው›› የሚል ሃሳብ ነው ያለን፡፡ በሕጋዊ አካሔዱ መሰረት ቅድሚያ ወረዳ ሄደን ከዛ ደብዳቤ ከተፃፈልን በኋላ ክፍለ ከተማ እንሄድና ክፍለ ከተማው ደግሞ ድጋሚ ደብዳቤ ይሰጠን እና እሱን ይዘን ፋብሪካ እንሄዳለን ከዛ አንድ ኩንታል 800 ብር እንረከብ ነበር አሁን ግን አንድ ኩንታል በብዙ ዕጥፍ ጨምሮብን 2650 ብር ነው ምንገዛው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ማንን ማናገር እንደምንችልም አናውቅም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ንግድ እና ኦንዱስትሪ ሚኒስቴር ሳይቀር ጥያቄ አቅርበን ነበር ታገሱ ከማለት ውጪ ምንም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም በማለት ዳቦ ጋጋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የንግድ እና ኢንዱስትሪ የህዝብ

ግንኙነት ሃላፊ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ምንም አይነት ዱቄት እጥረት እንዳልተፈጠረ እና ከዚህ ቀደም እንደነበረው ነው ያለው ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ስለተነሱት ቅሬታም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የንግድ እና ኢንዱስትሪ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ካለፈው አመት ጀምሮ መተግበር የጀመረው ይህ ዱቄት እያጠፉ እያመጡ ያለው አሰራር ተጠናክሮ መቀጠሉን እና በቀን ከሦስት ሺሕ ዳቦ በታች የሚያመርቱ ዳቦ ቤቶች አቅማቸውን ካላሳደጉ ዱቄቱን እንዳማያቀርብላቸው እንደተነገራቸው የዳቦ ቤት ባለቤቶች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እንደሚደረግም ገልፀዋል።

ኤጀንሲው በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂን መሰረት በማድረግ የሚሰራ ተቋም እንደመሆኑ ትልቅ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማእከል እንደሚኖረውም የጠቆሙት ዳይሬክተሩ በተጨማሪም የአንድ ማእከል አገልግሎት ከመስጠት አንፃር ከኤጀንሲው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች መሰል ተቋማትን ጭምር በአንድ አምጥቶ ተገልጋዮች የተሳለጠና ምቹ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ መታሰቡንም አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ኤጀንሲው ሁሉም አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶቹን ጨምሮ በአማካኝ በቀን 6100 ተገልጋይ የሚያስተናግድ መሆኑን የሚገልፁት ሙሉቀን የእነዚህን ተገልጋዮች ሰነድ በዘመናዊ መልኩ አደራጅቶ ለመያዝ እና ለማስተዳደር አሁን ሊገነባ የታሰበው ህንፃ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም ገልፀዋል።

የህንፃውም ግንባታ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና በስሩ የሚሰራው የፌደራል ተቋማት ህንፃዎች ግንባታ ጽ/ቤት በሚያደርጉት ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚሰራ የሚገልፁት ሙሉቀን በዚህ መሰረት የግንባታው ዲዛይን ካለቀ በኋላ ጽ/ቤቱ ለግንባታው ሙሉ አለማቀፋዊ ጨረታ ማውጣቱን በማስታወስ ጨረታውን የተወዳደሩት ሁሉም የቻይና ኩባንያዎች እንደነበሩና አሸናፊው ኩባንያ 2.5 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ዋጋ አቅርቦ እንደነበር ገልፀዋል።

ይህንን የዋጋ መጋነን በመመልከት ሌሎች አማራጮችንም ማየት አስፈላጊ ነው ተብሎ በመታመኑ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እንዲሁም የፌደራል ተቋማት ህንፃዎች ግንባታ ጽ/ቤት በአንድ ላይ ሆነው የመንግስት የግዢ ስርአቶችን በመከተል ህንፃው አገር በቀል በሆነ የኮንስትራክሽን ተቋም አስገንብቶ ወጪን ለመቀነስ በተጨማሪም በራስ ተቋም ትልልቅ ፕሮጀክቶችን መስራት እንደሚቻልም ጭምር እንደማሳም ሊሆን ይችላል በማለት ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግንባታው እንዲከናወን መወሰኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ሰነዶች ምዝገባና ማረጋጋጫ ኤጀንሲ የፌደራል ተቋም እንደመሆኑ አጠቃላይ የግንባታውን ፕሮጀክት በጀት የሚያዘው በገንዘብ ሚኒስቴር መሆኑንም ሙሉቀን ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ኤጀንሲው በ2012 በጀት አመት 530 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን አንስተው በ2011 ከሰበሰበው የ380 ሚሊዮን ብር ገቢ ጋር ሲነፃፀር በየአመቱ የኤጀንሲው በገቢው እያደገ መሄዱን እንደሚያሳይ ገልፀዋል። በያዝነው የ2013 በጀት አመት 600 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ኤጀንሲው እቅድ መያዙንም ዋና ዳይሪክተሩ ጨምረው ገልፀዋል።

ከተማ በማሳደግ ከተማዋን በክፍለ ከተማ ደረጃ ለማደራጀት የተጀመረ ሥራ መሆኑን የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢና የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ህንፃ ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አምሳሉ መኮንን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው እንደገለጹት ደብረ ብርሃን ከተማ አሁን ላይ ያላት መዋቅር በቀበሌ ደረጃ ብቻ የተዋቀረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከተማዋ አሁን ከደረሰችበት ስፋት አንፃር በቀበሌ ደረጃ የተዋቀረው አደረጃጀት ተመጣጣኝ አለመሆኑን የገለጹት ኃላፊው የከተማዋን አደረጃጀት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለማዋቀር ያለመ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም የከተማዋ አደረጃጀት ለተቀላጠፈ አሰራርና አገልግሎት ምቹ እንዳልሆነ የጠቆሙት ኃላፊው አዲስ መዋቅር ችግሩን ይፈታዋል ተብሎ ይታሰባል ብለዋል፡፡

ደብረ ብርሃን ከተማ አንድ ከተማ ሪጅዎፖሊታንት ደረጃ ለማግኘት ከ250 ሺሕ በላይ የህዝብ ቁጥር እንደሚስፈልግ ለአዲስ ማለዳ የገለጹት ኃላፊው ደብረ ብርሃን አሁን ላይ ከቀበሌዎች በተሰበሰበ መረጃ 350 ሺሕ በላይ የህዝብ ቁጥር እንዳላት ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት ከተማ አስተዳደሩ የደብረ ብርሃንን ነባራዊ ሁኔታ በማጥናት እንዲሁም የሌሎች ከተሞችን ተሞክሮ በማካተት መስከረም 22/2013 ለክልሉ መንግስት አዲሱን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር መዋቅር ጥናት እንደሚያቀርቡ አመላክተዋል፡፡ የክልሉ መንግስት የቀረበለትን አዲስ የመዋቅር ደረጃ እድገት ተቀብሎ ካጸደቀው ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ ደረጃ አንደምትዋቀር ኃላፊው ተቁመዋል፡፡

አዲስ የቀረበው የመዋቅር እድገት ጥናት በአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ ተቀባይነት አግኝቶ ከጸደቀ ደብረ ብርሃን

ከተማ ተጠሪነቷ ለክልሉ መንግስት እንድትሆን ያስችላታል ብለዋል አምሳሉ፡፡

የከተማዋን ደረጃ ማሳደግ ለከተማዋ እድገት ከፍኛ ጥቅም እንደሚኖረው የጠቆሙት ኃላፊው ወደ ከተማዋ የሚመጡ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳደግ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡ ወደ ከተማዋ የሚመጡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን በቀጥታ ከመቀበልና ከማሳደግ በተጨማሪም ከተማዋ የሚኖራት ስልጣን ከፍ ስለሚል ችግሮቿን በራሷመፍታት እንድትችልና ተጨማሪ የስራ ማስኬጅና የካፒታል በጀት እንድታገኝ ያስችላታል ተብሏል፡፡

ከተማዋን በአዲስ አደረጃጀት ለማዋቀር የመጨረሻ የክፍለ ከተሞችና የቀበሌዎችን ቁጥር መግለጽ አይቻልም ቢልም የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የከተማዋ መዋቅራዊ ጥናት መነሻ ሀሳብ በከተማ አስተዳደሩ የተቋቋመው ኮሚቴ ባስቀመጠው የመነሻ ሀሳብ 5 ክፍለ ከተሞች፣ በከተማዋ 17 ቀበሌዎች፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በጽሕፈት ቤት ደረጃ እንዲደራጁ እና የክፍለ ከተሞች ስያሜ ከከተማዋ ታሪካዊ ኩነቶች ጋር የተዛመዱ እንዲሆኑ ተደርገው ታጭተው ቀርበዋል፡፡

በቀረበው ምክረ ሀሳብ መሰረት የክፍለ ከተሞች ስያሜ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ፣ ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ፣ ልቼ ክፍለ ከተማ፣ አንሳስ ማሪያም ክፍለ ከተማ፣ ጠባሴ ክፍለ ከተማ፣ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ እና እሌኒ ክፍለ ከተማ የሚሉት በእጩነት የቀረቡ ስያሜዎች ናቸው፡፡

ደብረ ብርሃን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአካባቢው ባለው የሰላምና ምቱ የሥራ አሁኔታ በኢንቨስመንት ዘርፍ ከሌሎች አካባቢዎች በተሻለ ማረፊያ እየሆነች እና ጥሩ የሚባል የኢንቨስትመንት ስበት እያገኘች እንደምትገኝም በቅርቡ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲዘገብ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

Page 23: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 23ወፍ በረር

የመንግስት የልማት ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በየነ ገብረመስቀል የ2012 በጀት አፈፃፀምን አስመልክቶ በሰጡት መስከረም 20/2013 መግለጫ ላይ እንዳሉት ወደ ግል ይዞታ ከተዘዋወሩ ድርጅቶች አጠቃላይ የሽያጭ ገቢ መሰብሰብ የነበረበት 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ቢሆንም መሰብሰብ የነበረበትን 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ያህል ገቢ አለመሰብሰቡን አስታወቁ።

የተሰበሰበው የገንዘብ መጠንም በ2012 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ሲሆን በ2013 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ደግሞ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን በድምሩ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ነውም ብለዋል፡፡ ገቢው ላመሰብሰቡ እንደ ችግር ሆነ የተነሳውም ሂሳብ በመዝጋና በማስመርመር በኩል ወደ ኋላ የቀሩ ድርጅቶች መኖራቸው ተነስቷል፡፡

ኤጀንሲው በ2012 በጀት ዓመት 338 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 300 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከልማት ድርጅቶች በአጠቃላይ 55 ነጥብ 5 ቢሊየን ትርፍ መገኘቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ምርትና አገልግሎታቸውን በውጭ ምንዛሬ ከሚሸጡ ድርጅቶች 8 ነጥብ 67 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱንም የተናገሩት አቶ በየነ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ግሩፕ 3 ነጥብ 74 ቢሊየን ዶላር በማስገባት በአንደኝነት

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ 74,144 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ቁልፍ፣ ውልና ካርታ ለእድለኞችና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች አስረክበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ነዋሪ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ በእጣ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

በዛሬው ዕለትም የከተማው ምክትል ከንቲባ አዳነች ለ13ኛ ዙር 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች እና 22 ሺህ 915 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ካርታ፣ ቁልፍ እና ውል ርክክብ አስጀምረዋል።

በመድረኩ ላይ አዳነች ለተመረጡ 100 እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ቁልፍ፣ ካርታና ውል ያስረከቡ ሲሆን ቀሪዎቹ የቤት እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በየክፍለ ከተሞቻቸው እስከ ጥቅምት

የመንግስትየልማትይዞታናአስተዳደርኤጀንሲ1ነጥብ2ቢሊየንብርልሰበሰበም

የአዲስአበባከተማአስተዳደርከ74ሺሕበላይየጋራመኖሪያቤቶችንቁልፍአስተላለፈ

ከአፍሪካበዓመትበስውርየሚወጣውገንዘብከ50ወደ89ቢሊዮንዶላርአሻቀበ

ከአፍሪካ በስውር ወደ ሌሎች የዓለማችን አገራት የሚወጣው አመታዊ ገንዘብ ከ50 ቢሊዮን ወደ 89 ቢሊየን ዶላር ከፍ ማለቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

አህጉሪቷ በዋናነት ገንዘቡን የምታጣው በሙስና በታክስ ማጭበርበር እና በስርቆት እንደሆነ ነው የድርጅቱ ሪፖርት ያመላከተው፡፡

አፍሪካ ይህንን መጠን ያለው ገንዘብ የምታጣው ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ነው፡፡ ድርጅቱ ከአምስት አመታት በፊት በአዲስ አበባ በተደረገው ስብሰባ ላይ በተመሳሳይ መልኩ 50 ቢሊየን ዶላር በስወራ ታጣ እንደነበረ አስታውቆ ነበር፡፡ በመሆኑም በየአመቱ ከፍተኛ ገንዘብ በስወራ መልኩ እንደምታጣ ነው ሪፖርቱ የሚያሳየው፡፡

እንዲህ አይነት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሙስና የአፍሪካ ልማት እክል እየሆነ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ በከፍተኛ ሁኔታ አህጉሪቷ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲያጋጥማት ምክንያት መሆኑንም ነው በሪፖርቱ የተገለጸው፡፡

በአጠቃላይ የሀገራት ምጣኔ ኃብቱ እንዲጎዳና ድህነትና የኢኮኖሚ አለመጣጠን እንዲኖር ምክንያት ሆኗል ሲል በሪፖርቱ ላይ ማተቱን አልጀዚራ ዘግቧል።

ዓለምአቀፍየመረጃተደራሽነትቀን

በኢትዮጵያተከበረየመረጃ ተደራሽነት በኮረና ወረርሽኝ ወቅት

በሚል በኢትዮጰያ ዓለም አቀፍ የመረጃ ተደራሽነት ቀን ተከበረ። የኢትዮጵያ የሚዲያ ሰፖርት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህል፣ የትምህርትና የሳይንስ ድርጅት (ዩኒስኮ) ጋር በመተባበር ነው በኢትዮጵያ የተከበረው።

ዪኒስኮ በኢትዮጵያ የመረጃ ተደራሽነትን ለማጠናከር ከኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋር እየሰራ መሆኑን በቨርችዋል በተከናወነው ዊብናሪ ላይ አስታውቋል።

ዊብናሪው በኢትዮጵያ ሲከበር ለሦስትኛ ጊዜ ሲሆን በዓለም ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ ነው የተከበረው። በዊብናሪው ላይ አምስት ኢትዮጵያዊ የሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። የመረጃ ነፃነት ለመንግስታቱ ድርጅት አንዱ የትኩረት አጀንዳ መሆኑን በኢትዮጵያ የዩኒስኮ ቅርንጫፍ አስታውቋል። መረጃ በኮረና ወረርሽኝ ወቅት የመረጃ መዛባት ከቫይረሱ ባልተናነሰ ጉዳት አንደሚያደርስ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ በበኩሉ የመረጃ ነፃነትን ለማጠናከር በትኩረት አንደሚሰራ አስታውቋል። በዚሁ ዌብናር ላይ ከፍተኛ የሚዲያ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ባደረጉት ውይይትም ላይ ወቅቱ መረጃን ወደ ሚዲያ ተቋማት እና ከሚዲያ ተቋማትም ወደ ሕዝብ የሚደርሰውን ፍሰት በተመለከተ ከፍተኛ ተግዳሮት ፈጥሮ እንደነበር እና አሁንም በሚገባው መጠን እንዳልተቀረፈ ተነስቷል። በውይይቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) የተሳተፉ ሲሆን የተነሳው ጉዳይ በእርግጥም ባለስልጣኑ የሚረዳው ጉዳይ እንደሆነ እና ይህንንም ለመፍታት ጥረቶችን እንደሚያደርግም ዳይሬክተሩ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

12 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ርክክብ መፈፀም እንደሚችሉ ታውቋል።

አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የከተማ አስተዳደሩ አቅርቦቱና ፍላጎቱ ያልተጣጣመውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን እና የፋይናንስ አቅርቦቶችን በማመቻቸት የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት ይሰራል ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በተከናወኑ የልማት ስራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መጋለጣቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ በዙሪያዋ የሚገኙ አርሶ አደሮችን የምትገፋ ሳትሆን አብራ የምታድግ እንድትሆን የልማት ተፈናቃይ አርሶ አደሮችም የዚሁ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም አዳነች አክለው ገልጸዋል።

አልማ የተጀመሩ የትምህርት መሠረተ ልማቶችን ለማጠናቀቅ፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር፣ ለቴክኒክና ሙያ ፕሮጀክቶች እና ለጤናው ዘርፍ ልማት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት መድቧል። ከዚህ ውስጥ ወደ 2 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚሆነውን ለአዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ ወጪ እንደሚደረግ ማኅበሩ ገልጿል።

የአማራ ልማት ማኅበር በ2013 5 ሺሕ 20 መማሪያ ክፍሎች የሚኖራቸው 1 ሺህ 255 አዲስ ሕንጻዎችን ለመገንባት አቅዶ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ። ይህም በ2012 ተገንብተው ከተጠናቀቁት እና በተለያዩ የግንባታ ደረጃዎች ከሚገኙት በተጨማሪ የሚሠራ ነው ተብሏል። ማኅበሩ በትምህርቱ ዘርፍ በልዩ ትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ማኅበሩ እንዳስታወቀው በ2012 በጀት ዓመት 422 መማሪያ ክፍሎች ያሏቸው 97 የመጀመሪያ ደረጃ እና 114 ክፍሎች ያሏቸው 25 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ሕንጻዎች ተገንብተው ተጠናቅቀዋል። 1 ሺህ 60 የመማሪያ ክፍሎች ያሏቸው 265 የአንደኛ ደረጃ እና 122 የመማሪያ ክፍሎች ያሏቸው 29 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሕንጻዎች ደግሞ በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ወደ 80 በመቶ የሚሆኑት በመጠናቀቅ ሂደት ላይ መሆናቸውንና የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ከመጠናቀቁ በፊት ለመጨረስ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ለዚህም ወረዳዎች ተጨማሪ ሀብት ማፈላለግ በሚችሉበት ሁኔታ ጉባኤ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል። ጥሩ መግባባት ላይ እየተደረሰ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች የጥራት ደረጃቸው ዝቅተኛ ነው። የተማሪ እና የመማሪያ ክፍል ጥምርታውም ከደረጃ በታች ነው። አልማ በሦስት ዓመታት ውስጥ የጥራት ደረጃ ያሟሉ ትምህርት ቤቶችን ከ16 በመቶ ወደ 50 በመቶ ማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ እቅድ አውጥቶ እየሠራ ይገኛል። ለዚህም የነባር ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እና ምንም በሌለባቸው አካባቢዎች አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ማኅበረሰቡ የችግሩን መጠን በሚገባ በመረዳት የራሱን ችግር በራሱ አቅም ለመሸፈን በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ ቀርቧል።

ደረጃ ላይ ሲገኝ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ደግሞ 3ነጥብ 43 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ በማስገኘት የሁለተኝነት ደረጃን አግኝቷል ብለዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ከፕራይቬታይዜሽን ሽያጭ ቅድሚያ ክፍያ 1 ነጥብ 4 ቢየን ብር፣ ከፕራይቬታይዜሽን ውዝፍ ክፍያ ፣ 1 ነጥብ 8 ቢሊየንና ከፕራይቬታይዜሽን ሽያጭ በህግ ከተያዙ ውዝፍ ዕዳዎች 1 ቢሊየን ብር ገቢ ለማድረግ ለህግ የማቅረብና ውሳኔ ሲያገኙ የምስፈፀም እቅድ መያዙን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ወደ ግል ይዞታ ይዘዋወራሉ በሚል እቅድ ከተያዘላቸው የመንገስት ልማት ድርጅቶች መካከል በ2012 በጀት ዓመት አንድም ድርጅትን ወደ ግል ይዞታ አለመዘዋወሩን ከኤጀንሲው ገልጿል፡፡

የአማራልማትማኅበር3.5ቢሊዮንብርዓመታዊበጀትመያዙንአስታወቀ

ከዘንድሮጀምሮበየዓመቱበአገርአቀፍደረጃየመምህራንቀንመከበርሊጀምርነውከዘንድሮ ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የመምህራን

ቀን እንዲከበር መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ገረመው ሁሉቃ (ዶ/ር) እንደገለጹት መምህራን ትውልድን በመቅረፅ ውስጥ ትልቅ ሚና ስላላቸው ለመምህራን አስፈላጊውን እውቅና እና ክብር መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ አስታውቀዋል። መንግስትም ከዘንድሮ ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የመምህራን ቀን እንዲከበር መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

ቀኑን መምህራንን በማክበር፣ በማሰብ እንዲሁም የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፎችን በማቅረብ እና የፓናል ውይይት በማድረግ ታስቦ እንደሚውል ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ዮሃንስ በንቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው ቀኑን ከማክበር ባሻገር ቀድሞ የነበረውን የመምህራንን ክብር እና ጥያቄ ለመመለስ ይሰራል ነው ያሉት፡፡

የመምህራን ቀኑ ለአንድ ወር ያህል ወጥነት ባለው መልኩ ከትምህርት ቤት እስከ አገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Page 24: ‹‹ከራስ በላይ ለሕዝብ እና ለአገር›› - Addis Maleda

አዲስ ማለዳ መስከረም 23 ቀን 2013

addismaleda.com

ቅጽ 2 ቁጥር 100 ገፅ 24ማስታወቂያ