Top Banner
ዜና መፅሔት ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A [email protected] | www.etsugar.gov.et | www.facebook.com/etsugar ቅፅ 2. ቁጥር 2 -ታህሳስ 2006 የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት ሥራ ማህበራት ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጋር ለጋራ ጥቅም ለመስራት ተስማሙ www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተከበረ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በድምቀት አከበሩ ኮርፖሬሽኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከተቀመጠው የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ግብ 70 በመቶውን ማሣካት ይችላል ስኳር ኮርፖሬሽን በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመኑ ከሚገነባቸው የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ሰባቱን በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ምርት በማስጀመር የዕቅዱን 70 በመቶ ማሣካት የሚያስችለው ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት በዚህ ዓመት ተንዳሆ 1 እንዲሁም በ2007 ዓ.ም ተንዳሆ 2፣ ኩራዝ 1፣ ከሰም፣ በለስ 1 እና 2 እና አርጆ ዲዴሳ ተጠናቀው ምርት ይጀምራሉ፡፡ በሌላ በኩል ወልቃይት፣ በለስ 3 እና ኩራዝ 2 እና 3 በ2ኛው ምዕራፍ የዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ምርት ማምረት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 25 ኛው የዓለም ኤድስ ቀን “አንድም ሰው በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዳይያዝ ኃላፊነታችንን በመወጣት የአገራችንን ሕዳሴ እናሳካ!” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተከበረ፡፡ በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ ፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የስራ አመራሮችና ሠራተኞች ስምንተኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ህዳር 28 ቀን 2006 ዓ.ም በድምቀት አከበሩ፡፡ “ሕገ መንግስታችን ለሕዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚህ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ አቶ አደባባይ አባይ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከመበታተን አደጋ ወጥተው አንድ መሆን የቻሉት የቃል ኪዳን ሰነዳቸው በሆነው ሕገ መንግስት አማካይነት መሆኑን አስታውሰው ፣ ሕገ መንግስቱን በማወቅና በማሳወቅ እንዲሁም እሴቶቹን በመፈጸም ኃላፊነትን መወጣት ይገባል ብለዋል፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት የሕዝቦችን በጋራ አብሮ የመኖር በጎ ልምዶችን በማጠናከርና » ገጽ.3 » ገጽ.5 » ገጽ.4 የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበራት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከህዳር 7–14/2006ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ከህዳር 7-13/2006 ዓ.ም ድረስ በነበረው ጊዜ የውይይት መድረኮች የተካሄዱት » ገጽ.15 አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ አቶ አደባባይ አባይ በውስጥ ገፆች የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ... ገጽ. 15 ጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት .... ገጽ. 19 የሳቡሬ ከተማ ከስኳር ልማቱ ተጠቃሚ እየሆነች ነው...ገጽ. 8 • የእቅድ ዘመኑን የስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ግብ ተደራሽነት የሚያመለክት ፍኖተ ካርታ (Roadmap) ተዘጋጀ ጣፋጭ
20

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2 ታህሳስ 2006

Jul 14, 2015

Download

Business

meresaf
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በአለም ተወዳዳሪ የሆነ የስኳር ኢንዱስትሪ መፍጠር

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 [email protected] || www.etsugar.gov.et || www.facebook.com/etsugar

ቅፅ 2. ቁጥር 2 -ታህሳስ 2006

የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት ሥራ ማህበራት ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጋር ለጋራ ጥቅም ለመስራት ተስማሙ

www.etsugar.gov.et.com || www.facebook.com/etsugar

የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተከበረ

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በድምቀት አከበሩ

ኮርፖሬሽኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከተቀመጠው

የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ግብ 70 በመቶውን ማሣካት ይችላል

ስኳር ኮርፖሬሽን በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመኑ ከሚገነባቸው የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ሰባቱን በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ምርት በማስጀመር የዕቅዱን 70 በመቶ ማሣካት የሚያስችለው ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት በዚህ ዓመት ተንዳሆ 1 እንዲሁም በ2007 ዓ.ም ተንዳሆ 2፣ ኩራዝ 1፣ ከሰም፣ በለስ 1 እና 2 እና አርጆ ዲዴሳ ተጠናቀው ምርት ይጀምራሉ፡፡ በሌላ በኩል ወልቃይት፣ በለስ 3 እና ኩራዝ 2 እና 3 በ2ኛው ምዕራፍ የዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ምርት ማምረት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

25ኛው የዓለም ኤድስ ቀን “አንድም ሰው በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዳይያዝ ኃላፊነታችንን በመወጣት የአገራችንን ሕዳሴ እናሳካ!” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ

ደረጃ በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተከበረ፡፡በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ ፣

የስኳር ኮርፖሬሽን የስራ አመራሮችና ሠራተኞች ስምንተኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ህዳር 28 ቀን 2006 ዓ.ም በድምቀት አከበሩ፡፡

“ሕገ መንግስታችን ለሕዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚህ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር የኮርፖሬት ሪፎርምና አቅም ግንባታ አማካሪ አቶ አደባባይ

አባይ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከመበታተን አደጋ ወጥተው አንድ መሆን የቻሉት የቃል ኪዳን ሰነዳቸው በሆነው ሕገ መንግስት አማካይነት መሆኑን አስታውሰው ፣ ሕገ መንግስቱን በማወቅና በማሳወቅ እንዲሁም እሴቶቹን በመፈጸም ኃላፊነትን መወጣት ይገባል ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት የሕዝቦችን በጋራ አብሮ የመኖር በጎ ልምዶችን በማጠናከርና

» ገጽ.3

» ገጽ.5

» ገጽ.4

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበራት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከህዳር 7–14/2006ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ከህዳር 7-13/2006 ዓ.ም ድረስ በነበረው ጊዜ የውይይት መድረኮች የተካሄዱት

» ገጽ.15

አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

አቶ አደባባይ አባይበውስጥ ገፆችየስኳር ልማት በሚካሄድባቸው

አካባቢዎች የሚገኙ ... ገጽ. 15ጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት

ፕሮጀክት ....ገጽ. 19የሳቡሬ ከተማ ከስኳር ልማቱ ተጠቃሚ

እየሆነች ነው...ገጽ. 8

• የእቅድ ዘመኑን የስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ግብ ተደራሽነት የሚያመለክት ፍኖተ ካርታ (Roadmap) ተዘጋጀ

ጣፋጭ

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

2

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክትየአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የግብርና ምርቶችን በዓይነትና በጥራት የምናሣድግበት ብቻ ሣይሆን ከግብርና ወደ ኢንዱሰትሪ የምናደርገውን መዋቅራዊ ሽግግርም የምናሰፋበትና የምናፋጥንበት ጭምር ነው፡፡ ይህን መዋቅራዊ ሽግግር ተግባራዊ ለማድረግ ከተያዙ ዕቅዶች መካከል የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ዋንኛው ነው፡፡ ዘርፉ ግብርናን ከኢንዱስትሪው ጋር በማገናኘት ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ የግብርና ምርታማነትን ለማጎልበት የሚያስችል፣ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ለማሣደግ የሚያግዝ፣ የአገር ውስጥ

የስኳር ምርት ፍላጎት ከመሸፈን አልፎ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት የሚያስችል ነው፡፡ በተጓዳኝ በሚመረቱ ምርቶችም የአገሪቷን የኃይል አቅርቦት በመደገፍ፣ ኤታኖልን የመሳሰሉ ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶችን በመቀነስ እና ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በማምረት ዘርፉ ሊያበረክት የሚችለው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

በቅርቡ የስኳር ልማት ንዑስ ዘርፍ ያለፉትን ሦስት ዓመታት አፈፃፀም ለማየትና በቀሪዎቹ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ጊዜያት የት መድረስ እንደሚቻል ለመረዳት ባካሄድነው ግምገማ ለዕቅድ ዘመኑ ከተቀመጠው ግብ 70 በመቶውን ማሣካት እንደምንችል አይተናል፡፡ በዚሁ መሠረት አዳዲስ ከሚገነቡ ፋብሪካዎች ሰባቱን ማለትም ተንዳሆ አንድን በያዝነው ዓመት እንዲሁም ተንዳሆ ሁለት፣ ኩራዝ አንድ፣ ከሰም፣ በለስ አንድና ሁለት እና አርጆ ዲዴሣ፣ በ2007 ዓ.ም. ተጠናቀው ማምረት ይጀምራሉ፡፡ እነዚህ ወደ ማምረት የሚገቡ ፋብሪካዎች ከፍተኛ የማስፋፊያ ሥራ ከተሰራላቸው ነባር ሦስት ፋብሪካዎች ጋር በድምሩ በ2007 መጨረሻ ከ1.5 ሚሊዮን ቶን ያላነሰ ስኳር ማምረት የሚያስችሉን ይሆናሉ፡፡ በተመሣሣይ በተጓዳኝ የሚመረቱ ምርቶች መጠን፣ በልማት አካባቢዎቹ የሚካሄዱ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሠረተ ልማት ግንባታ፣ እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራና መሰል የልማት እንቅስቃሴዎች ጉልህ በሆነ ደረጃ ያድጋሉ፡፡

በቀጣዩ ዓመት መጨረሻ የምንደርስበት ግብም ሆነ ከዚያ ቀጥሎ ባሉ ቀጣይ ጊዜያት በስኳር ልማት ዘርፍ ልናስመዘግብ የምናስበው ውጤት ከምንም በላይ ምርታማነታችንን በማሣደግ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

ከዚህ አኳያ በሔክታር ከ1500 ኩንታል ያላነሰ የሸንኮራ ምርት ለማግኘት የሚያስችሉን የመሬት እንክብካቤና የግብዓት አቅርቦት እንዲሁም የጥናትና የምርምር ሥራዎች ላይ አተኩረን እንሰራለን፡፡

የቴክኖሎጂ ዕውቀትና አጠቃቀማችንን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻልም ትኩረት ሰጥተን እንንቀሳቀሳለን፡፡ ጤንነቱ የተጠበቀ፣ ምርታማነቱ የላቀ፣ ሥነ-ምግባሩ የጎለበተ አምራች የሰው ኃይል በኢንዱስትሪው ውስጥ በብዛት እንዲፈጠርም ልዩ ልዩ ተግባራትን እናከናውናለን፡፡ ኢንዱስትሪው ሠላማዊና የተረጋጋ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትም ይከናወናሉ፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ከፍተኛ የስኳርና የተጓዳኝ ምርቶች በማምረት የአገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ህዝባችንን እና የዚህ ውጤት ተዋናይ የሆነውን ሠራተኛ የእድገቱ ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ በእርግጥ ከፊታችን ያለው ትልቅ ኃላፊነት የሚጠይቅ ተልዕኮ ነው፡፡ የተቋሙ ሥራ አመራር አባላትና ሠራተኞች እንዲሁም በተለያዩ የኮንትራት ሥራዎች ውስጥ የሚሣተፉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ሁላችንም ልናሣካው የሚጠበቅብንን ትልቅ ተልዕኮ የሚመጥን ምላሽ ለመስጠት በጋራ እንድንረባረብ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

ክቡር አቶ ሽፈራው ጃርሶበሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን

ዋና ዳይሬክተር

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

3

ኮርፖሬሽኑ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን የሶስት ዓመታት (2003 - 2005 ዓ.ም ) አፈጻጸም በመፈተሽ በአምስት ዓመቱ የስኳር ልማት እቅድ የት መድረስ እንደሚቻል በትክክል ለማወቅ ባደረገው ግምገማ በአምስት አመቱ የእቅድ ዘመን በስኳር ልማት ዘርፍ ከተቀመጠው የከፍተኛ አማራጭ የግብ ስኬት 70 በመቶውን ማሣካት እንደሚችል አረጋግጧል፡፡

አገሪቱ በስኳር ልማት ዘርፍ ያላትን ከፍተኛ እምቅ አቅም በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አዳዲስ ፋብሪካዎችን የመገንባትና የነባሮቹን አቅም በከፍተኛ ደረጃ የማሣደግ ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት የመሠረተ ልማት አውታሮች ባልነበሩበት፣ ለዘርፉ ልማት የሚውል በቂ ፋይናንስ በሌለበትና የዘርፉ ልምድና የማስፈፀም አቅም ውስን በነበረበት ሁኔታ ሥራው የተጀመረ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ አሁን የተደረሰበት ውጤት እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡

በመሆኑም ሥራው ሲጀመር በነበረው በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ የከፍተኛውን የግብ ስኬት አማራጭ 70 በመቶ መድረስ ከተቻለ በቀጣይ አጭር ሊባል በሚችል ጊዜ ውስጥ በስኳር ልማት ከዓለም ግንባር ቀደም ስኳር አምራች አገሮች ተርታ መሰለፍ እንደሚቻል አሁን የተደረሰበት ውጤት አመላክቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ እያካሄዳቸው ካሉ የስኳር ፋብሪካ ግንባታዎች መካከል የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ በማጠናቀቂያ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህ የበጀት ዓመት ወደ ማምረት ይሸጋገራል፡፡ የበለስ 1 እና 2፣ የኩራዝ 1፣ የተንዳሆ 2፣ የከሰምና የአርጆ ዲዴሳ ፋብሪካዎች ደግሞ በ2007 ማምረት ይጀምራሉ፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቶችም በኩል ወንጂ ሸዋና ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች ተጠናቀው ተጨማሪ ምርት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

በእስካሁን የልማት ጥረት ዓመታዊ የሀገር ውስጥ የስኳር ምርት በ2005 መጨረሻ ከነበረበት 232 ሺህ ቶን ተከታታይ ዕድገት በማስመዝገብ በ2007 መጨረሻ ከ1 ሚሊዮን 585 ሺህ ቶን በላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ ይህም የአገር ውስጥ ፍጆታ ከመሸፈን አልፎ ምርቱን ወደ ውጭ መላክ

የሚቻልበት ደረጃ ላይ የሚያደርስ ይሆናል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ አገሪቱ ስኳር ከውጭ ለማስመጣት ታወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማዳን የሚችልበት ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን እንዲያውም በ2007 ዓ.ም ወደ 658,200 ቶን ስኳር ወደ ውጭ በመላክ ከ376 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዓመታዊ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

በቀሪዎቹ የትግበራ ጊዜያት የመስኖ ልማት ግንባታን አጠናክሮ በመቀጠልና በፕሮጀክቶች 149,790 ሔክታር አገዳ በመትከል በአጠቃላይ የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የአገዳ ሽፋንን ከ204,000 ሄክታር በላይ ለማድረስ ጥረት ይደረጋል፡፡ የማስፋፊያ ስራ በተጠናቀቀላቸው በነባር ስኳር ፋብሪካዎችና በአዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በ2006 እና በ2007 ዓ.ም ከ92 ሺህ በላይ ተጨማሪ የሥራ ዕድሎች ይፈጠራሉ፡፡ የልማቱ ሥራ በሚካሔድባቸው አካባቢዎች የሚገኘው ሕብረተሰብም በፕሮጀከቶቹ አማካኝነት ከሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆንበት አቅጣጫም ተቀምጧል፡፡

ከስኳር ምርት በተጓዳኝ በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ከስኳር ፋብሪካዎቹ 197 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ እንደሚደረስ ይገመታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በ2007 የኢታኖል ምርትን ከ134 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ በማድረስ አገሪቱ ለነዳጅ የምታወጣውን ወጪ ለመቀነስ ኮርፖሬሽኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በ2006 እና በ2007 በቁጥር 3,265 የመኖሪያ ቤት፣ የአገልግሎት መስጫና ተያያዥ ግንባታዎችን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃትም በመረባረብ ላይ ነው፡፡

በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ግብ ተደራሽነት ፍኖተ ካርታ (Road Map) በጥቅምት ወር ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ ውሏል፡፡ ፍኖተ ካርታው በስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ኢንዱስትሪ ልማት ንዑስ ዘርፍ ውስጥ በ2006 እና በ2007 ዓ.ም ተፈጻሚ የሚሆኑ ዋና ዋና ግቦችን አካቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን...

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

4

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በምስራቅ ሸዋና አርሲ ዞኖች በሚገኙና የሸንኮራ አገዳ ልማቱ በሚካሄድባቸው ወረዳዎችና ቀበሌዎች ከተውጣጡ በየደረጃው ከሚገኙ አመራር አካላት፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮችና ህብረት ሥራ ማህበራት ተወካዮች ጋር ነው፡፡

ህዳር 14 /2006 ዓ.ም. በአዳማ ገልማ አባገዳ የስብሰባ አዳራሽ ለስድስት ቀናት በተለያዩ ደረጃዎች ሲካሄድ የቆዩ ውይይቶች የማጠቃለያ መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፣ የክልሉ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት፣ የፌዴራል ህብረት ስራና ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የስራ ኃላፊዎች፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አመራሮች፣ ከየአካባቢዎቹ የመጡ አርሶ አደሮች፣ የምሥራቅ ሸዋና የአርሲ ዞኖች አስተዳዳሪዎችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአዳማ፣ የቦሰትና የዶዶታ ወረዳዎች አመራሮችና ሌሎች የሚመለከታቸው 581 ተሳታፊዎች በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ በውይይቱ ላይ “በወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና በሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት (አውትግሮወርስ) መካከል የሚታየው የልማት አፈጻጸም፣ ተግዳሮቶችና ኪራይ ሰብሳቢነት” በሚል ርእስ የመወያያ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

አቶ ዳመነ ባቀረቡት ጽሁፍ የአገዳ መሸጫ ዋጋ ሳይሻሻል መቆየቱ፣ የተሟላ የመሰረተ ልማት እጥረት፣ ለሸንኮራ አገዳ እድገት የሚበጁ እንክብካቤዎች ወቅታቸውንና ጥራታቸውን ጠብቀው ባለማከናወናቸው ምክንያት የሚከሰት የምርታማነት ማነስ፣ ከልማቱ ጋር የሚጣጣም የስራ ባህል አለመኖር፣ በአንዳንድ ማሳዎች ላይ ወቅቱን ጠብቆ መሬቱን አለማዘጋጀት፣ በቂ የሆነ የመስኖ ውኃ አለማቅረብ፣ የመድን ሽፋን

አለመኖርና ሌሎችንም ተያያዥ ችግሮች ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም በዩኒየን አመራር፣ በመሰረታዊ ማህበራት አመራርና በፋብሪካው በኩል የሚንጸባረቁ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራት እንዲሁም የአሰራርና የአደረጃጀት ክፍተትም እንደችግር ተነስተዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በጽሁፋቸው ማጠቃለያ በመፍትሔነት ከጠቀሱዋቸው ሐሳቦች መካከል የኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉን በቀጣይነት አጠናክሮ መቀጠልና ግልጽነት ያለው አሰራርና ድጋፍ አሰጣጥ ማስፈን፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር፣ አሰራርን ማሻሻል፣ የመድን ሽፋን እንዲኖር ማድረግ፣ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የሚሉትና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

በውይይቱ ወቅት የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አመራሮችና አባላት መፍትሔ ያሻቸዋል ያሉዋቸውን ጉዳዮች አንስተዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ለፋብሪካው ለሚያቀርቡት የሸንኮራ አገዳ ምርት ዋጋ ይሻሻል፣ ከመስኖና ከሌሎች የምርት ግብአቶች አቅርቦት ጋር በተያያዘ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጥበት መንገድ ይመቻች፣ በማቆያ የተያዙ መሬቶች ቶሎ ወደ ልማት ይግቡ የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ይገኙበታል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ተወካዮች የውይይት መድረኩ በሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደሮች ማህበራትና ፋብሪካው እንደ ችግር የሚያነሷቸውን ጉዳዮች በመለየት ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ አኳኋን ለማስተናገድ የተመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ስኳር ለማምረት ብዙ ግብዓቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ተወካዮች ይህንን ታሣቢ ያደረገ የዋጋ ድርድር ለማካሄድ ጭምር መድረኩ መመቻቸቱን አስረድተዋል፡፡

በአገልግሎት አቅርቦት ረገድ አሉ የተባሉ

ችግሮችን ለመፍታትም ፋብሪካው ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ አብራርተው በተመሣሣይ ከአርሶ አደሮች በኩል ከምርታማነትና ፋብሪካውን እንደ አገርና እንደራሣቸው ሐብት አድርጎ በመቁጠር ረገድ ያሉ የአመለካከት ችግሮች እንዲስተካከሉ አሳስበዋል፡፡ በቀጣይም ፋብሪካውና ማህበራቱ በመደበኛ ሁኔታ በመወያየት ሁለቱንም አካላት ተጠቃሚ የሚያደርግ አቅጣጫን መከተልና ለጋራ ልማት አብረው መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

መድረኩን የመሩት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት የማጠቃለያ ሐሣብ በአገሪቱ ልማት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ላለው የስኳር ልማት መሳካት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ ዞኖችና የየወረዳዎቹ አመራሮች እንዲሁም የፋብሪካውና የማህበራትና የዩኒየኖች አመራሮችና ሰራተኞች ተቀናጅተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ህብረተሰቡም ፋብሪካው እራሱንም ሆነ አገሪቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቅም መሆኑን ተረድቶ የባለቤትነት ስሜትን እንዲያዳብር በማሳሰብ የሁለቱ ግንኙነት በግልጽነትና በፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም ስኬት የውይይት መድረኮች በመደበኛነት ተጠናክረው እንደሚካሄዱ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የስራ ኃላፊዎች፣ የሸንኮራ አገዳ አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አመራርና አባላት፣ የዩኒየን አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የፋብሪካው አመራሮችና ሰራተኞች ተወካዮች ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ተቀናጅተው ለመስራት ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

በአቋም መግለጫቸውም የስኳር ልማቱ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለመለወጥና ለሀገር ልማትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመገንዘብ ለውጤታማነቱ እጅ ለእጅ ተያያይዘው ለመስራትና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በውይይት እየፈቱ ለመሄድ የየበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

በማህበራቱና በፋብሪካው መካከል ውይይት በተደረገበት ወቅት

የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት ሥራ ማህበራት ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጋር ...

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

5

የዓለም ኤድስ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ በመተሐራ...

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብድላዚዝ መሐመድና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሙላቱ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር በመላ አገሪቱ በተፈጠሩ በብዚ ሺ የሚቆጠሩ አምራች ኃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው ታላላቅ የልማትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትን መግታት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸው ወገኖች የጸረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መድኃኒት አግኝተው አምራች ኃይሎች እንዲሆኑና በአገራቸው የልማትና የእድገት ጉዞ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ማገዝና መርዳት አስፈላጊ ነውም ብለዋል ፕሬዚዳንት ሙላቱ፡፡

በዓሉ የተከበረበት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካን በመሳሰሉና በመገንባት ላይ ባሉት ታላላቅ ፕሮጀክቶችና በተለያዩ የልማት ተቋሞች በመስራት ላይ የሚገኙ ወጣቶች ከኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ራሳቸውን መጠበቅ ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ አሳስበዋል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበኩላቸው ከስራቸው ባሕሪ የተነሳ በርካታ የሰው ኃይል የሚሰማሩባቸውን

ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ለሚመሩ ስኳር ኮርፖሬሽንን ለመሳሰሉ ተቋማት ኤች.አይ.ቪ ኤድስን መከላከልና መቆጣጠር ተልዕኮን ከማሳካት ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው ብለዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸውን 2100 ሠራተኞችንና በበሽታው ወላጆቻቸውን ያጡ ሕጻናትን ከመደገፍና ከመንከባከብ በተጓዳኝ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ የመከላከል ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በመከላከልና በእንክብካቤ ስራው ውስጥ ጉልህ ሚና የሚጫወት የኤች.አይ.ቪ ግብረ ኃይል መቋቋሙንና ከተቋሙ አመታዊ በጀት ላይ ሁለት በመቶ የሚሆነው ለዚሁ ስራ እንዲውል መመደቡንም አብራርተዋል፡፡

በእስካሁኑ ጅምር የመከላከል፣ የመንከባከብና ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች አበረታች ውጤቶች ቢመዘገቡም የስኳር ልማት ዘርፉ ካለው ተጋላጭነትና የተያዘውን እቅድ በአጭር ጊዜ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ ከመሆኑ አንጻር ኮርፖሬሽኑ የበለጠ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑንም አቶ ሽፈራው ጠቁመዋል፡፡

የዓለም ኤድስ ቀን በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ መከበሩ ኮርፖሬሽኑ የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ረገድ የተለየ ኃላፊነት እንዲሸከም የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት

ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም በዋና መስሪያ ቤት ፣ በፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች የተሰማሩ ሰራተኞች የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል በስኳር ልማት ዘርፍ የተቀመጡ የልማት ግቦችን ለማሳካት በበለጠ ቁርጠኝነት እንዲነሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ./ኤድስን በመከላከል ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ ከሚገኙ 16 የአፍሪካ አገሮች መካከል ግንባር ቀደም መሆን መቻሏን አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይም ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው የታላላቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የተጠናከረ የመከላከል ስራ እንደሚሰራ ይፋ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ በኤች.አይ.ቪ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር በ90 በመቶ እንዲሁም በቫይረሱ ምክንያት ይደርስ የነበረውን ሞትና ጉዳት ከ54 በመቶ በላይ መቀነስ መቻሏ በበዓሉ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በዓሉ የተከበረበት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ባቋቋመው አንድ ሆስፒታል ፣ ሁለት ፖሊና አራት ሳተላይት ክሊኒኮች አማካይነት ለፋብሪካው ሰራተኞች ፣ ቤተሰቦቻቸውና ለአካባቢው ነዋሪ ሕብረተሰብ የኤች.አይ.ቪ. ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የዓለም ኤድስ ቀን በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ በተከበረበት ወቅት

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

6

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች በከፍተኛ የማምረት

አቅም ሥራ ጀመሩ የማስፋፊያ ሥራቸው የተጠናቀቀው የወንጂ ሸዋና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች ከጥቅምት ወር 2006ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በተሳካ ሁኔታ ሥራ ጀመሩ፡፡ የተካሄደው የማስፋፊያ ሥራ የፋብሪካዎቹን የማምረት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራው የተጠናቀቀው የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የማምረት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ከጥቅምት 10/2006 ዓ.ም ጀምሮ እያመረተ ነው፡፡ ፋብሪካው በ2006 በጀት ዓመት 2 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህ የምርት መጠን በ2005 በጀት ዓመት ከተገኘው ምርት ጋር ሲነጻጸር የ900 ሺህ ኩንታል ልዩነት ይኖረዋል፡፡

ፋብሪካው በሂደት በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በአመት ወደ 2 ሚሊዮን 700 ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ

ዕድሜ አገልግለው ስኳር ማምረት ባቆሙት ነባሮቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ምትክ በተከናወነ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታው የተጠናቀቀው አዲሱ ዘመናዊ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከጥቅምት 22/2006 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር ማምረት ጀምሯል፡፡

በ2005ዓ.ም መጨረሻ የሙከራ ምርት ያካሄደው ይህ ፋብሪካ በያዝነው በጀት ዓመት ከ950 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር እንዲያመርት የታቀደ ሲሆን፣ ለምርቱ የሚሆን በቂ የሸንኮራ አገዳና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች ዝግጁ ሆነዋል፡፡

አሮጌዎቹ የወንጂ እና የሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች በዓመት 750 ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርቱ የነበረ ሲሆን፣ በምትካቸው የተገነባው አዲሱ ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፉ ብቻ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር በዓመት ከ1 ሚሊዮን 460 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡

በሌላ በኩል በያዝነው በጀት ዓመት 1 ሚሊዮን 300 ሺህ ኩንታል ስኳር እንደሚያመርት የሚጠበቀው የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ስራ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካም በያዝነው በጀት ዓመት ምርት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጠቀሱት አራት የስኳር ፋብሪካዎች በበጀት ዓመቱ ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር ለማምረት የታቀደ ሲሆን፣ ይህም ከአምናው ምርት ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ይሆናል፡፡ በዘርፉ ዘንድሮ የሚገኘው ምርት የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላት ባለፈ ምርቱን ከውጭ ለማስገባት ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል፡፡

የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲያድግና የአመቱ የማምረት ተግባር ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲጀመር አመራሮችና ሠራተኞች ሰፊ ርብርብ አድርገዋል፡፡

አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብካ

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

7

የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች “ከስኳር ልማቱ ጎን ለጎን ለግድቡ ስኬት እንተጋለን!” የሚል መሪ ቃል አንግበው በሁለት ዙሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኙ፡፡

ሠራተኞቹ የኮርፖሬሽኑ የማህበራዊ ጉዳዮች በሚያስተባብረው የአገርህን እወቅ ክበብ አማካኝነት ግድቡ በሚገነባበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ተገኝተው ጉብኝት ያካሄዱት ጥቅምት 4 እና ህዳር 9 ቀን 2006 ዓ.ም ነው፡፡

በመጀመሪያው ዙር 41 የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ከጥቅምት 2 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ግንባታው በሚካሄድበት ስፍራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከህዳር 9 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው የሁለተኛው ዙር ጉብኝት ደግሞ 35 ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡

በሁለቱም ዙሮች ግድቡ ወደሚገነባበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ላመሩት የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ስለ ግድቡ ግንባታና ተያያዥ ጉዳዮች በከፍተኛ የፕሮጀክቱ ባለሙያዎች በአዳራሽ ውስጥና በመስክ ጉብኝት ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

በጉብኝቶቹ ወቅት በሥራ ምክንያት በግንባታው ስፍራ መገኘት ያልቻሉት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ለኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ባስተላለፉት የጽሁፍ መልዕክት “በቅድሚያ የራሳችሁን ፕሮጀክት ስለጎበኛችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፡፡ በተመለከታችሁት ሁሉ ደስተኛ እንደሆናችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በቀጣይ ሁላችንም በከፍተኛ የአገር ፍቅር እጅ ለእጅ በመያያዝና የተጀመረውን የልማት ጉዞ ይበልጥ በማስቀጠል በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በየተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ ጠንክረን

መስራት ይጠበቅብናል ” ብለዋል፡፡

የግድቡን ግንባታ አስመልክቶ አንዳንድ ያነጋገርናቸው ተጓዦች በሰጡን አስተያየት በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ ይመለከቱት የነበረውን የግድቡን ሥራ በአካል ተገኝተው መመልከታቸው የበለጠ የባለቤትነት ስሜትና በቁጭት የመስራት ተነሳሽነትን እንደፈጠረላቸው ገልጸው፣ ለግንባታው ስኬት የጀመሩትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ከግድቡ በተጨማሪ በአሶሳ ከተማ የሚገኙትን የሼህ ሆጀሌ አልሃሰን የችሎት አዳራሽና የመቃብር ስፍራ ጎብኝተዋል፡፡

በሦስት ዙሮች ተከፍሎ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የጉብኝት መርሐ ግብር ለሦስተኛው ዙር ጉዞ ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኙ

ሰራተኞቹ በግድቡ የግንባታ ሂደትና በተመለከቱት ነገር ደስተኛ ሆነዋል

» ገጽ.8

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

8

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች... ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የጉዞ መርሃ ግብሩን ያዘጋጀው የኮርፖሬሽኑ የአገርህን እወቅ ክበብ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ተቋቁሞ እስካሁን 117 አባላትን ያቀፈ ሲሆን፣ ዓላማው ሠራተኞችን ከማዝናናትና ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባለፈ መንግሥት በሚያካሂደው ዘላቂ ልማት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው፡፡

በተመሳሳይ ዜና የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ 39 ሠራተኞች፣ የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት 300 ሠራተኞች እንዲሁም

የወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ 42 ሠራተኞች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሥራ እቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ስለ ግድቡ ፕሮጀክት አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመረዳታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሠራተኞቹ ለፕሮጀክቱ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር በተሰማሩበት ዘርፍ ተልዕኮአቸውን በላቀ ሁኔታ በመፈጸም አገሪቱ ወዳለመችው የእድገት ደረጃ እንድትደርስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት

ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በአንድ ቀን ከ 74 ሄክታር በላይ የሸንኮራ አገዳ ዘር ተተከለ

የሳቡሬ ከተማ ከስኳር ልማቱ ተጠቃሚ እየሆነች ነው

ስያሜዋን ከአንድ ፈረንሳዊ ባለሀብት የወረሰችው የሳቡሬ ከተማ የስኳር ልማቱን ተከትሎ ከተዘረጉ መሠረተ ልማቶች ተጠቃሚ መሆኗ ተገለጸ፡፡ በ1904 ዓ.ም እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ይህች ከተማ የከሠም ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ተከትለው በተዘረጉ የመንገድ ፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የገመድ አልባ የብሮድባንድ ኢንተርኔትና የ24 ሰአት የመብራት አገልግሎቶች ተጠቃሚ መሆን ችላለች፡፡

ከተማዋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለከሰም ስኳር ልማት ተብለው በተዘረጉ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ መሆኗ ለእድገቷ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

የአትክልትና ፍራፍሬ ልማትን ተከትላ የተመሠረተችውና በኋላም የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሳቢያ የተስፋፋችው ሳቡሬ የገጠር ከተማ ስትሆን ለበርካታ አመታት በቂ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት አልነበሯትም፡፡

ከተማዋ የዘመናዊ የግንኙነት መረቦች ተጠቃሚ መሆኗ እንደ ዳግም ልደት እንደሚቆጠርና በቀጣይ በፍጥነት እድገት ለማስመዝገብ በምታደርገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል የላከልን ዘገባ አመልክቷል፡፡

በጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሰራተኞች በተደረገ የተቀናጀ ንቅናቄ በአንድ ቀን 74 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት በሸንኮራ አገዳ ዘር መሸፈኑ ተገለጸ፡፡

በአገዳ ተከላ የንቅናቄ እቅድ ዙሪያ የፕሮጀክቱ አመራር ከሰራተኛው ጋር ባደረገው እንቅስቃሴ “ሁሉም መንገዶች ወደ በለስ አገዳ ተከላ ያመራሉ!” በሚል መሪ ቃል ወደ ተግባር ተገብቶ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን መረጃ ያመለክታል ፡፡

የልማት ቡድኖችን በአራት የዞን ጽ/ቤቶች ከፋፍሎ ስራን ቆጥሮ በመስጠትና በቡድኖቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የሥራ ውድድር መንፈስ በመፍጠር ውጤቱ ሊገኝ መቻሉን ነው መረጃው የጠቆመው፡፡

የፕሮጀክቱ የአመራር ኮሚቴ ወረዳዎችን

በመከፋፈሉና ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረጉ ሰራተኛው በእለቱ በተከላ ስራው ላይ ብቻ እንዲያተኩር ተደርጎ ተፈላጊው ውጤት ሊገኝ ችሏል፡፡

ለስራው የሚያስፈልገውን ተጨማሪ የሰው ኃይል ከአማራና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከማቅረብ በተጨማሪ የአገዳ አቅርቦት ችግር እንዳይኖር ያሉትን የፕሮጀክቱንና በኪራይ የተገኙትን ተሽከርካሪዎች በአግባቡ መጠቀም በመቻሉ እቅዱ ከግብ ደርሷል፡፡ በሌላ በኩል ሁኔታውን በቅርብ ይከታተል የነበረው ከ3ዐዐዐ በላይ የሚሆን የጃዊ ወረዳ ህዝብ ፣ የንግዱ ማህበረሰብና የወረዳው የፖሊስ አባላት የሰራተኛውን ሞራልና መነሳሳት በመደገፍ የሁለት ቀናት የአገዳ ተከላ ዘመቻ ሥራ ማከናወናቸውን የፕሮጀክቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የላከው መረጃ ያመለክታል ፡፡

የፊንጫአ ሰራተኞች በጉዞ ላይ

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

9

ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለት ሲከናወን የቆየው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ የእድሳት ሥራ ከተቀመጠለት ዕቅድ አስቀድሞ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

የፋብሪካው ሠራተኞች ጥቅምት 29 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ባካሄዱት የሦስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ እደተመለከተው በስኳር ኮርፖሬሽን፣ በፋብሪካው አመራሮችና አጠቃላይ ሠራተኞች በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ ለ14 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ጥገና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ ስኳር ማምረት ተጀምሯል፡፡

ፋብሪካውን ለማደስ በተካሄዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችና ለሠራተኛው በአመለካከት፣ በመልካም ግንኙነትና በቡድን ግንባታ በተሰጡ ሥልጠናዎች በአመራሩ እንዲሁም በአጠቃላይ ሠራተኛው ዘንድ የባለቤትነት፣ የቁጭት፣ የተነሳሽነትና የቁርጠኝነት ስሜቶች በመፈጠራቸው በጥገናው ሂደት ላይ የታየው ርብርብ እጅግ ከፍተኛ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም በግምገማው ወቅት እንደገለጹት መንግስት ለፋብሪካው እድሳትና ጥገና በሰጠው ልዩ ትኩረት ከ4ዐዐ ሚሊዮን ብር

በላይ መድቦ እርጅና የተጫናቸው ማሽነሪዎች እንዲሻሻሉና ለጥገና የሚያስፈልጉ ግብዓቶችም በወቅቱ ከውጭ ሀገሮች እንዲገቡ በመደረጉ ለጥገናው መፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ ፋብሪካው ከቀድሞ በተለየ ሁኔታ እንዲጠገን መደረጉን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ በስራው ላይ በተለይም ሠራተኛው ለተጫወተው ከፍተኛ ሚና ታላቅ ክብር የሚገባው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጥገናው ላይ መላው ሰራተኛ ለ14 ሳምንታት ያህል ከመደበኛ ስራው ውጭ በየዕለቱ ተጨማሪ የአንድ ሰዓት ነጻ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን በዚህም ሰራተኛው 4.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ማዳኑ ታውቋል፡፤

በግምገማው ላይ የተሳተፉት ሠራተኞች በበኩላቸው በጥገና ሂደቱ ከመንግሥት ጀምሮ በተዋረድ እስከ ፋብሪካው ከፍተኛ አመራሮች ድረስ የተሰጠው የቅርብ ድጋፍና ክትትል ለስኬት እንዳበቃቸው ተናግረዋል፡፡

እንደ ተሳታፊዎቹ አስተያየት ቁርጠኛ የለውጥ አመራር በመኖሩና ቀደም ሲል የነበሩ የአመለካከት ክፍተቶች እየተለወጡ በመሆናቸው ውጤታማ ተቋማዊ ለውጦችን መመልከት ተችሏል፡፡

የለውጥ ንቅናቄው በፋብሪካ ብቻ ሳይወሰን በመኖሪያ አካባቢዎችም ጭምር በመሆኑ ከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት በመፈጠሩ በቀጣይም የተጀመረውን ተቋማዊ ለውጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተሳታፊዎቹ መግለጻቸውን የዘገበው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሕዝብ አደረጃጀት፣ ሕዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ጉዳዮች ክፍል ነው፡፡

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የ2006 የበጀት አመት እቅድ ትግበራ ዝግጅቱን ከቀሪ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ጋር የተጣጣመ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡

የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ አስራት እንደገለጹት የፕሮጀክቱ የፋብሪካ ግንባታ ስራ እየተጠናቀቀ የሚገኝ በመሆኑ ከዴዴሳ ወንዝ ውሃ በቀጥታ በመሳብ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ስድስት ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለመትከልና ፋብሪካውን በማሟሸት

ምርት ለመጀመር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ይህን እቅዱን ለማሳካት በሁለት ሺ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት የመስኖ ዝርጋታ ለማከናወን የሚያስችል ጨረታ አውጥቶ ጨረታው በሂደት ላይ የሚገኝ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በተያያዘም ለልማቱ ከሚፈለገው መሬት ላይ ተነሺ ለሆኑ ዜጎች የማሕበራዊ ተቋማት ግንባታ ለማስፈጸም ከአካባቢው አስተዳደር አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴ እየተደረገ

እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ አመልክተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አመታዊ እቅዱን ለማሳካት እየሰራ ነው

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ እድሳት በስኬት

ተጠናቀቀ

» ገጽ.12

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006
Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

11

የስኳር ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 ከተቋቋመ ጀምሮ ላለፉት ሦስት አመታት ኮርፖሬሽኑን በሚኒስትር ማዕረግ በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት የአቶ አባይ ጸሐዬ ሽኝትና ከጥቅምት 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት የአቶ ሽፈራው ጃርሶ አቀባበል ሥነ ስርአት

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

12

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በሞሪሽየስ ለአንድ ወር በኬን ፋርም ማኔጅመንት ፣ በኢሪጌሽን ፣ በሜካናይዜሽን፣ በኬሚካል ኮንትሮልና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስልጠና ወስደው የተመለሱ የኮፖሬሽኑ የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ባለሙያዎች ከስልጠናው ያገኙትን ልምድ ለተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ባልደረቦች አካፈሉ፡፡

ፋብሪካው ለዜና መጽሔት ዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ እንዳመለከተው ስልጠናው ኮርፖሬሽኑ የጀመራቸውን የስኳር ልማት ስራዎች በላቀ ደረጃ ለማከናወን የሚያስችል

የቴክኒክና የማኔጅመንት ክህሎት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት ያግዛል፡፡

ሰልጣኞቹ ለሌሎች ተመራማሪዎች ከስልጠናው ያገኙትን ልምድ ባካፈሉበት ወቅት ስልጠናውን በወሰዱበት አገር ምርምር የሚሰራው በግለሰቦች ፍላጎት ሳይሆን የደንበኞችን ፍላጎት በመለየትና ችግሮችን ለመፍታት ታስቦ በሚቀረጹ ፕሮጀክቶች አማካይነት ነው ብለዋል፡፡

የበጀት አመቱን እቅድ ለማሳካት ቁልፍ ሚና ከሚኖራቸው

ዝግጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የፕሮጀክቱን የሰው ሃይል

በአመለካካትና በክህሎት ማብቃት መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ

ጠቁመው 139 የፕሮጀክቱ ስራ አመራሮችና ሠራተኞች በውጪ

አገር፣ በኮርፖሬሽኑና በፕሮጀክት ደረጃ በተለያዩ ርዕሶች

ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

በፕሮጀክቱ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ልማት ለአካባቢውና

ለአገሪቱ ምጣኔ ሐብት እድገት ሊኖረው በሚችለው ጠቀሜታ

ዙሪያ ለአካባቢው ህብረተሰብ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ

መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው ስራውን ከዞን፣ ከወረዳና

ከቀበሌ አመራሮች ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች

መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም ለልማቱ ከሚፈለገው መሬት ላይ ተነሺ ለሆኑ ዜጎች

የማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለማስፈጸም ከአካባቢው

የአስተዳደር አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴ እየተደረገ

እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ አመልክተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አመታዊ እቅዱን ...

ስልጠና ተከታትለው የተመለሱ ባለሙያዎች ልምዳቸውን አካፈሉ

ስልጠናውን ተከታትለው የተመለሱ ባለሙያዎቸ በስኳር ኢንደስትሪ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ የሞሪሽየስ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ያላቸውን ዕውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ ወደአገራችን መጥተው የሚያካፍሉበት ሁኔታ ቢመቻች አገሪቱ ተጠቃሚ ልትሆን እንደምትችልም ገልጸዋል ፡፡ሰልጣኞቹ በስልጠናው ወቅት ላገኙት እውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ እውቅና የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ከምርምርና ስልጠና ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ዮሐንስ መኳንንት እጅ ተረክበዋል፡፡

በሌላ በኩል በሙከራ ማሳ ላይ የሚገኙትና የምርምር ስራቸው ተጠናቆ ለተጠቃሚ ለማድረስ የዘር ማባዛት ስራ እየተሰራላቸው የሚገኙት N52 219 እና N53 216 የተባሉት ዝርያዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ እንደሚገኙ የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

ምርምሩን በመሪነት እያካሄዱ የሚገኙት አቶ አብይ ጌታነህ ዝርያዎቹ በአገዳ ብዛት፣ በስኳር ይዘታቸውና በሄክታር በሚሰጡት የምርት መጠን በአሁኑ ወቅት በፋብሪካዎች ምርት ላይ ከሚገኘው B52 298 ከተባለው ጋር ሲነጻጸር የተሻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ዝርያዎቹን በሰፊው ወደ ተጠቃሚው ለማድረስ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናው ትኩረት ካደረገባቸው መስኮች አንዱ የኬን ፋርም ማኔጅመንት ይገኝበታል

Page 13: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

13የፋብሪካው ሰራተኞች ፈንዱን ለማቋቋም ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና ድጋፍ

ፈንድ አቋቋሙየወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝባቸውን ሠራተኞችና ወላጆቻቸውን በበሽታው ያጡ ህጻናትን በቋሚነት ለመርዳት የሚያስችል የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና ድጋፍ ፈንድ አቋቋሙ፡፡

የድጋፍ ፈንዱ የተቋቋመው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን ታህሳስ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በፋብሪካ ደረጃ በተከበረበት ወቅት የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ባደረጉት ውይይት ላይ በተደረሰ ስምምነት ነው፡፡

በስምምነቱ መሰረት ሰራተኞቹ በየወሩ በቋሚነት ከወር ደመወዛቸው ብር 0.5 በመቶ ለመከላከልና ድጋፍ ስራው እንዲውል ተስማምተዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አታክልቲ ተስፋይ የፋብሪካው ሰራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነት ቋሚ የኤች አይ ቪ ኤድስ ድጋፍና መከላከል ፈንድ ለማቋቋም በመቻላቸው ልባዊ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የስኳር ኮርፖሬሽን ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ አስተባባሪ ወ/ሮ ካሰች ሺበሺ በፋብሪካው ያለውን የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትና የመከላከል ስራውን በተመለከተ የዳሰሳ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

ፋብሪካው ዕለቱን ምክንያት በማድረግ በሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ባካሄደው ልዩ ዝግጅት በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ 46 ታዳጊ ህጻናት የ13 ሺ 8ዐዐ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የፋብሪካው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጨምሮ ሠራተኞች፣ የስኳር ኮርፖሬሽን ተወካዮችና የምሥራቅ ሸዋ ጤና ቢሮ ተወካይ ተገኝተዋል፡፡

በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ቀደም ሲል የተቋቋመው የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ፈንድ ለ20 በበሽታው ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት በየወሩ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የፈንዱ የገቢ ምንጭ የሰራተኛው መዋጮና ከፋብሪካው በየአመቱ የሚመደብ ገንዘብ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Page 14: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

14

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

የበዓሉ ታዳሚዎች

የሴት ሰራተኞቹ የጽዳት ዘመቻ ከ 8 ሺ ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ አድኗል

የፋብሪካው ሴት ሰራተኞች በለውጥ ንቅናቄ ግንባር ቀደም ሚና እንጫወታለን አሉ

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሴት ሠራተኞች በፋብሪካው በተጀመረው አጠቃላይ የለውጥ ንቅናቄ ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወቱ አስታወቁ፡፡

‹‹በሴቶች የነቃ ተሳትፎ ምርታማነታችንን እናሳድጋለን›› በሚል መሪ ቃል 220 የሚሆኑ የፋብሪካው ሴት ሠራተኞች ህዳር 1/2ዐዐ6 ዓ.ም በፋብሪካው የምርት ቦታ በመገኘት የጽዳት ዘመቻ ያካሄዱ ሲሆን፣ ያከናወኑት ተግባር በገንዘብ ሲተመን ከ 8 ሺህ ብር በላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን ሥርዓተ-ፆታ ዳይሬክተር ወ/ሮ እንጉዳይ አሰፋ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ የኤች.አይ.ቪ./ኤድስ መከላከያ አስተባባሪ ወ/ሮ ካሰች ሺበሺ በጽዳት

ዘመቻው ላይ በመሳተፍ የሰራተኞቹን ዓላማ አበረታተዋል፡፡

በጽዳት ዘመቻው ማጠቃለያ ሥነ-ስርዓት ላይ ሁለቱም የሥራ ኃላፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም የነበረውን የተዛባ የሥርዓተ-ፆታ አመለካከት በመለወጥ ሴቶችንና ወንዶችን በሁሉም ዘርፍ እኩል ተሣታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በአጭር ጊዜ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል ብለዋል፡፡

ሴቶች አካባቢንና ማህበረሰብን ወደ መልካምና ወደ ምርታማነት የመለወጥ አቅም ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ የፋብሪካው ሴት ሰራተኞች የጀመሩትን

አርዓያነት ያለው ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም በወቅቱ ባደረጉት ንግግር የፋብሪካውን ምርታማነት ለማሳደግ እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ የለውጥ ንቅናቄ ውስጥ ሴት ሠራተኞች የጀመሩትን ብርቱ ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉና ፋብሪካውም በዚህ አመት 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለማምረት የያዘው ዕቅድ እንደሚሳካ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሥርዓተ ፆታ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዓለሚቱ ጉልቴ በበኩላቸው የጽዳት መርሃ ግብሩ ዋና አላማ ሴት ሰራተኞች ለፋብሪካው ምርታማነትና እድገት ሊያከናውኗቸው ከሚችሉት በርካታ ተግባራት ውስጥ የፋብሪካውን የምርት ቦታ ጽዱ በማድረግ ለስራ አመቺና ማራኪ የሚሆንበትን ሁኔታ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

Page 15: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

15

የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የስኳር ልማቱን እንደሚፈልጉ ከመግለፅ ባለፈ የልማቱ ተዋናዮች እየሆኑ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ ከዜና መጽሔቱ ዝግጅት ክፍል ጋር ባደረጉት ቆይታ የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚፈልጉት ከመግለጽ ባለፈ ቀዳሚ ተዋናዮች እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

መንግስት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት እያከናወነ የሚገኘው የስኳር ልማት ልማቱ

የሚካሄድበትን አካባቢ ህብረተሰብ ይሁንታ ካላገኘ ዋጋ እንደማይኖረው ይገነዘባል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ረገድ በልማቱ አጠቃላይ ሂደት ላይ በመወያየትና በመተማመን እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ሕብረተሰቡ የስኳር ልማቱ የራሱ መሆኑን በመገንዘቡና በማመኑ በአንዳንድ ቦታዎች “በነጻ የሸንኮራ አገዳ ለምን አንተክልም?” በማለት ከመጠየቅ ባለፈ በበለስ የስኳር ልማት ፕጀክት የሸንኮራ አገዳ በመትከል የልማቱ አጋር መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል ብለዋል፡፡መንግስት የስኳር ልማቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አካል ሲያደርግ

በዋናነት ልማቱ የሚከናወንበት አካባቢ ሕብረተሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ስልት በመንደፍ ነው ያሉት አቶ ዳመነ ይህም እስካሁን በተከናወኑ ሥራዎች በተግባር መረጋገጡን አብራርተዋል፡፡

የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በ2005 ዓ.ም በነባር ስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጀክቶች ለ60 ሺህ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠራላቸው ገልፀው ይህ ጥረት ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ከአቶ ዳመነ ዳሮታ ጋር የተደረገው ሙሉ ቃለ ምልልስ በገጽ 16 ተስተናግዷል፡፡

የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የልማቱ ተዋናዮች እየሆኑ ነው

የተዛቡ ግኝኙነቶችን በማረም የሕገ መንግስታዊ ስርአቱ አደጋ የሆኑትን የሃይማኖት አክራሪነትንና ኪራይ ሰብሳቢነት መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አያይዘውም በስኳር ልማት ዘርፍ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተቀመጡትን ግቦች እውን ለማድረግ የዋናው መስሪያ ቤት፣ የፋብሪካዎችና የፕሮጀክቶች ሠራተኞች በህብረት በመስራት የሕገ መንግስቱን ዓላማዎች ማሳካት እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል፡፡

ሕገ መንግስቱ የፀደቀበትን ቀን ማክበር ሠራተኞች እርስ በርሳቸው እንዲተዋወቁ ያስችላል ያሉት አማካሪው ሕገ መንግስቱን ተከትለው ከወጡ የልማት እቅዶች መካከል አንዱ የሆነውን የስኳር ልማት ዘርፍ ስኬትን ለማረጋገጥ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኛ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይም አንድ ጠንካራ የፖለቲካና የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የዘርፉን እቅዶች ለማሳካት በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በእለቱ «የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስትና ሕብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት « በሚል ርእስ የመነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ሕገ መንግስቱን የተመለከቱ የጥያቄና መልስ ውድድሮችም ተካሂደዋል፡፡

ይህ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በስኳር ፋብሪካዎችና በፕሮጄክቶችም በድምቀት ተከብሯል፡፡

በተያያዘም የዓለም ኤድስ ቀንና የነጭ ሪቫን ቀን በዕለቱ በኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ታስቦ ውሏል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የብሔር ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ቀን...

የበዓሉ ታዳሚዎች

Page 16: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

16

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

አቶ ዳመነ ዳሮታበስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር

በኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየሦስት ወሩ እየታተመ የሚወጣው ጣፋጭ ዜና መጽሔት በዚህ ወር ዕትሙ የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚኖረው ህዝብ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተከናወኑ ስላሉ ሥራዎች እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳመነ ዳሮታ ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል ፡፡

ጣፋጭ- በያዝነው በጀት ዓመት የዘርፉ ዋነኛ የሥራ ትኩረት ምን እንደሆነ ቢገልጹልን?

አቶ ዳመነ - ኮርፖሬሽኑ የስኳር ምርት ከውጪ ማስገባትን በማስቀረት የአገር ውስጥ ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር ወደ ውጪ አገር ኤክስፖርት ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ያለውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ የኢንዱስትሪ አካባቢ ሠላም መሆን ወሳኝ ነው፡፡ ስለሆነም የዘርፉ የበጀት ዓመቱ የትኩረት አቅጣጫ የኮርፖሬሽኑ የልማት ዕቅድ ተፈፃሚ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣትና በሂደትም በልማት አካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ ከልማቱ ተጨባጭ ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ እንዲሄድ ከክልል መንግስታት ጋር በቅንጅት መሥራት ነው፡፡

ጣፋጭ- በስኳር ፋብሪካዎችና ኘሮጀክቶች አካባቢ የሚገኘው ህብረተሰብ የልማቱ ዋንኛ ተጠቃሚ እንዲሆን እስካሁን የተከናወኑ ሥራዎችን (ከማህበራዊ አገልግሎቶችና ከመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከሥልጠና ….. አኳያ ) ጠቅለል አድርገው ቢያብራሩልን?

አቶ ዳመነ - መንግስት የስኳር ልማትን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አካል ሲያደርግ በዋነኝነት ልማቱ የሚከናወንበት አካባቢ ህብረተሰብ ከልማቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ስልት

በመንደፍ ነው፡፡ በመሆኑም እስከ አሁን በበለስ ስኳር ልማት አካባቢ በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳ በሁለት ሠፈራ ጣቢያዎች (አሊኩራንድና ኩምብር)፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፓዌና ዳንጉር ወረዳዎች በሁለት ሠፈራ ጣቢያዎች (አባወሬኛና ባንባጅዋ) እና በወልቃይት በቆራሪት ሠፈራ ጣቢያ መልሰው ለሚቋቋሙ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ት/ቤቶች፣

የጤና ተቋማት፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ የቀበሌ ጽ/ቤቶች፣ የፖሊስ ጣቢያዎች፣ የውሃ ተቋማት፣ መዳረሻ መንገዶች እና መሰል ማህበራዊ ተቋማት እየተገነቡና የተጠናቀቁት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

እንዲሁም በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት አካባቢ በቦዲ ሦስት መንደሮች፣ በጉራ

Page 17: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

17 » ገጽ.18

አንድ መንደርና በሃይለ ውሃ ሁለት መንደሮች በአጠቃላይ በስድስት መንደሮች በእያንዳንዳቸው ከአስር በላይ ማህበራዊ ተቋማትና የመሠረተ ልማት አውታሮች እየተገነቡ ያለበት ሁኔታ ሲኖር የቦዲ ሦስት መንደሮች ተጠናቀው ለአርብቶ አደሮች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ሌላ በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ብ/ብ/ እና ሕዝቦች ክልል የጋራ በጀት በማኪ ወንዝ አካባቢ በአንድ መንደርና በሻርማ ወንዝ አካባቢ በሁለት መንደሮች አርብቶ አደሮች ቀደም ሲል በሚኖሩበት አካባቢ የውሃ አማራጭ በመገኘቱ ባሉበት አገልግሎት እንዲያገኙ የማህበራዊ ተቋማትና የመሠረተ ልማት አውታሮች እየተገነቡ ናቸው፡፡

በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ ውስጥ ህጋዊ መሠረት ሳይኖራቸው ለረጅም ጊዜ የቆዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከፋብሪካው አስተዳደር ወሰን ውጪ ለማስፈር በአዲሱ የሰፈራ ጣቢያ ከስምንት በላይ ማህበራዊ ተቋማት እየተገነቡ ሲሆን፤ በአርጆ ዲዴሳ፣ በወንጂ ሸዋ እና በመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራዊ ተቋማትን ለመገንባት እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፡፡

በሌላም በኩል በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤትነት በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ለሚገኙ አርብቶ አደሮች በዱብቲ ወረዳ በአስር መንደሮች በእያንዳንዳቸው የሰባት ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፣ ተቋማቱ በከፊል አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት አካባቢም ለሚገኙ አርብቶ አደሮች ተመሳሳይ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው፡፡

ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በነባር ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በ2005 ዓ.ም ወደ 60 ሺህ የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን መጨረሻ በዘርፉ ከ200 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጠራል፡፡ በተለይ በልማቱ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች በሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት

(TVET) ጋር በመቀናጀት በኮርፖሬሽኑ ሙሉ ወጪ የመለስተኛ ሙያ ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት በኩራዝ 232፣ በበለስ 79 እና በወልቃይት 204 ወጣቶች በተለያዩ የኮንስትራክሽን ሙያዎችና በትራክተር ኦፕሬተርነት ስልጠና አግኝተው በፕሮጀክቶቹ እንዲቀጠሩ ተደርጓል፡፡ ይህ ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ጣፋጭ- ከካሳ ክፍያ፣ ከመልሶ ማቋቋም (መንደር ማሰባሰብ፣ ሰፈራ) እና በመስኖ ከሚለማ መሬት ርክክብ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ተግባራትን ቢገልጹልን? በዚህ ረገድ አልፎ አልፎ ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በምን አግባብ እየተፈቱ ነው?

አቶ ዳመነ -የሀብት ቆጠራና ካሳ ክፍያም ሆነ ዜጎችን መልሶ ማቋቋም ስራዎችን የምናከናውነው ልማቱ ከሚገኝበት ክልል ጋር በመቀናጀት ነው፡፡ በመሆኑም እስከ አሁን ባለው ሂደት የጎላ ችግር አላጋጠመንም ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ በበለስና በወልቃይት ስኳር ልማቶች ምክንያት መልሰው የሚሰፍሩ ዜጎች በአዋጁ መሠረት ሀብትና ንብረት ተገምቶ ካሳ እንዲከፈላቸው እየተደረገ ነው፡፡

በኩራዝ አካባቢ የሚገኘው መሬት ቀደም ሲል በአርብቶ አደሮች ተይዞ በቋሚነት የለማ ንብረትና ሀብት የሌለ በመሆኑ እስከ አሁን ድረስ የካሳ ክፍያ ያልተፈፀመ ቢሆንም የአርብቶ አደሩን ኑሮ በዘላቂነት ለመለወጥ መንግስት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የመስኖ መሰረተ ልማት በመስራት አርብቶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተንዳሆና በከሰምም በመንግስት ከፍተኛ ወጪ የመስኖ መሰረተ ልማት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች እየተገነባ ይገኛል፡፡

ጣፋጭ- የስኳር ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ህዝቡ በባለቤትነት ስሜት ተነሳስቶ የልማቱ አጋዥ ኃይል እንዲሆን እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን ቢያብራሩልን ፡፡ ምንስ ውጤት ተገኝቷል?

አቶ ዳመነ - ምንም እንኳ መንግስት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለአገርና ልማቱ ለሚከናወንበት አካባቢ የጎላ ጠቀሜታ ያለው ልማት እያከናወነ ቢሆንም ህብረተሰቡ ሳያምንበት በጫና የሚፈፀም ልማት ዋጋ የማይኖረው መሆኑን ከማንም ይልቅ ይገነዘባል፡፡ በመሆኑም ወደ የትኛውም ስራ ከመግባታችን በፊት ስለልማቱ አጠቃላይ ሂደት ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየትና በመተማመን እየሄድን እንገኛለን፡፡ ውጤቱንም ስንመለከት በልማቱ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚፈልጉ ከመግለፅ ባለፈ የልማቱ ቀዳሚ ተዋናዮች እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በአንዳንድ ቦታዎችም የሸንኮራ አገዳ ተከላ ሳይቀር “ በነፃ ለምን አንተክልም” ከማለት ባለፈ በበለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት የሸንኮራ አገዳ በመትከል አጋርነታቸውን እየገለጹ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የገባኸውን ቃል ወደ ተግባር መለወጥ እስከ ቻልክ ድረስ ህብረተሰቡ ከልማት ፍላጎት ባለፈ የባለቤትነት ስሜት እያደረበት ይሄዳል፤ አሁንም እየታየ ያለው ይህ ነው፡፡

ጣፋጭ- የሸንኮራ አገዳ አብቃዮችን እና አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማትን በማደራጀት፣ በማስተባበርና በመከታተል ረገድ ምን ያህል ርቀት ተጉዛችኋል? የሥራችሁን መገለጫዎች ቢጠቅሱልን?

አቶ ዳመነ - እንደሚታወቀው የሸንኮራ አብቃይ አርሶ አደሮች የህብረት ስራ ማህበራት ልምድ ያለው በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ የማደራጀት ስራው የሚሰራው ከማህበራት ማደራጃ ጽ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት ሲሆን አርሶ አደሩ ከመሬት ይዞታው ሳይፈናቀል የልማቱ ቀኝ እጅ በመሆን ሸንኮራ እያመረተ ለፋብሪካው እንዲያቀርብ እና ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ ሂደት እስከ አሁን 31 መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት እና አንድ ዩኒየን የተቋቋሙ ሲሆን በልማቱ ዙሪያ ያሉ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ዝርዝር ጥናት በማጥናትና ከአርሶ አደሩ ጋር በመተማመን በየጊዜው

Page 18: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

18

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ ገብተናል፡፡

በሌላ በኩል በተለይ በአዳዲስ ፕሮጀክቶች አካባቢ የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ከሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት ጋር እየሰራን በመሆኑ ብዙ ወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

ጣፋጭ - ልማቱን ከማፋጠን አንጻር ከክልሎች ፣ ከዞኖች ከወረዳዎችና ከሌሎች የባለ ድርሻ አካላት ጋር ያላችሁ ግንንኙነት ምን ይመስላል?

አቶ ዳመነ - የእኛ ስራ ከህዝብ ጋር በቀጥታ የተገናኘ እንደመሆኑ መጠን ልማቱ ከሚገኝባቸው ክልሎች ጋር በቅርበት የምንሰራ ሲሆን ክልሎች የስኳር ልማት ስቲሪንግ ኮሚቴ በማዋቀር ለስራው ትኩረት በመስጠት በባለቤትነት እየመሩት ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁን ያለን ግንኙነት መልካም የሚባል ነው፡፡

ጣፋጭ- «በስኳር ልማት ሳቢያ ህዝብ ተፈናቀለ፣ ሰብዓዊ መብቱ ተጣሰ፣ ለዜጎች ተገቢው ካሳ አልተከፈለም፣ ደን ተመነጠረ፣ ቅርሶች አልተጠበቁም፣ የእምነት ቦታ ተደፈረ.» የሚሉ ተደጋጋሚ ስሞታዎች (በተለይም ደግሞ የኩራዝ ስኳር ልማት ኘሮጀክት በሚካሄድበት አካባቢ) የሰብዓዊ መብትና የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ነን በሚሉ ተቋማትና በአንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች ይናፈሳሉ፡፡ በዚህ ላይ የእርስዎ ምላሽ ምንድ ነው?

አቶ ዳመነ - በየጊዜው በተለያዩ ፍትሐዊነት በጎደላቸው ተቋማት የሚናፈሱ አሉባልታዎችና ተጨባጭ እውነታውን ስንመለከተው የማይገናኝበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እኛ የምንሰራው ለህዝብ ነው፤ ህዝቡ ያላመነበትና ተጠቃሚ የማይሆንበትን ልማት አንሰራም፡፡ በደቡብ ኦሞ መንግስት ህዝቡን በኃይል እያፈናቀለ መሆኑን የሚናገሩ አሉ ፡፡ ይህ ከእውነት የራቀ እና የአርብቶ አደሩን

መለወጥ የማይፈልጉ አካላት የሐሰት ውንጀላ ነው፡፡

ይልቁንም አርብቶ አደሩ በልማት ክልሉ ውስጥ የአኗኗር ባህሉና ወጉ ሳይዛባ በመንደር እየተሰባሰበ ውሃን ማዕከል ያደረገ የመስኖ መሠረተ ልማት የሚሰጠውና የማህበራዊ ተቋማት የሚገነቡለት በመሆኑ ሌሎች ይህንን ለውጥ እያዩ ለምን ፈጥናችሁ ወደ እኛም አትመጡም እያሉን ነው ፡፡

እንዲሁም በአርሶ አደር አካባቢዎች ተገቢው ካሳ የሚከፈልና መሟላት ያለበት ማህበራዊ ተቋምና የመሠረተ ልማት አውታሮች ከነበረው ተመጣጣኝና በተሻለ ሁኔታ እየተገነባ ነው፡፡ የተለያዩ የስራ ዕድሎች እየተፈጠሩ በመሆናቸው ተነሺው ህብረተሰብ በተጨባጭ ተጠቃሚ መሆኑን ስለተገነዘበ የልማቱ አጋር እየሆነ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል የሸንኮራ አገዳ ልማት የአረንጓዴ ልማት አካል እንደመሆኑ መጠን የአካባቢ አየር ንብረት በመጠበቅ አዎንታዊ የሆነ ሚናን ይጫወታል፡፡ ከእምነት ቦታ አንፃርም በአንዳንድ የውጪ ሚዲያ ሳይቀር ብዙ ሲባል የነበረው የዋልድባ ገዳም ተደፈረ የሚል ነበር፡፡ ልማቱ በገዳሙ ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ የሌለ ቢሆንም አንዳንድ የተለየ ፍላጎት ያላቸው አካላት አጀንዳ ለማድረግ በሰፊው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ሆኖም በአካባቢው ያለው ህብረተሰብ ሁኔታውን በቅርበት የሚያውቀውና የሚገነዘበው በመሆኑ ለልማቱ ያለውን አጋርነት እየገለፀ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተሳሳተ አቅጣጫ ሲጓዙ የነበሩ ጭምር ስህተት መሆኑን በማመን ከመንግሥትና ከሕዝብ ጎን በመቆም ልማቱን ለመደገፍ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በሁሉም አካባቢ ያለው ህዝባችን የልማቱን ፋይዳ በመገንዘብ የራሱን አስተዋፅዖ እያበረከተ የሚገኝ በመሆኑ የሰብዓዊ መብትና የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ነን የሚሉ አካላት ይህንኑ በማመን ከአፍራሽ ቅስቀሳቸው ቢቆጠቡ መልካም ነው እላለሁ፡፡

እኛ የምንሰራው ለህዝብ ነው፤ ህዝቡ ያላመነበትና ተጠቃሚ የማይሆንበትን ልማት አንሰራም ”

Page 19: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

19

የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክትጣና በለስ

እናስተዋውቃችሁ

ከአምስት አመታት በፊት በ2001 ዓ.ም ነበር በአማራ ብሔራዊ ክልል «ጣና የተቀናጀ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት» የተጀመረው፡፡ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተጠነሰሰበት በ2003 ዓ.ም የአካባቢውን እምቅ አቅም እንዲሁም አዋጭነቱን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በደንብ ቁጥር 192/2003 ፕሮጀክቱ «ጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር ልማት ፕሮጀክት» በሚል ስያሜ በስኳር ኮርፖሬሽን ስር እንዲሆን አደረገው፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በመተከል ዞን በፖዊና ዳንጉር ወረዳዎች ውስጥ የሚገኘው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት የጃዊ ፣ ፓዊና ዳንጉር ሜዳዎችን ተንተርሶ የሚፈሰውን የበለስ ወንዝን አቅጣጫ በማስቀየር 75 ሺ ሄክታር መሬት (50ሺህ ሄክታር በአማራ ክልል እንዲሁም 25ሺህ ሄክታር በቤኒሻንጉል ክልል) ላይ የሸንኮራ አገዳና ሌሎች ተፈላጊ ሰብሎችን እንዲያመርት ታስቦ የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በዳንግላ መስመር 558 ኪ.ሜ ወይም በሌላኛው አማራጭ መንገድ ከአዲስ አበባ በኮሶበር ቻግኒ 597 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ ዋና ጽ/ቤት «መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሰፈር» ከጃዊ ወረዳ ዋና ከተማ ፈንደቃ በአንድ ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኝ ቆላማ የአየር ንብረት ባለው አካባቢ የከተመ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ለመስኖ ስራ የሚጠቀምበትን የበለስ ወንዝን አቅጣጫ የማስቀየር ስራ ሙሉ ለሙሉ የተከናወነው

በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ነው፡፡ የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር የተሰራውና 13 ሜትር ቁመትና በሰከንድ 60 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ የመልቀቅ አቅም ያላቸው ስድስት በሮችን ያካተተው ዘመናዊ የውሃ መቀልበሻ አናት (ዊር) የሰሜን ጎንደሩ አለፋ ወረዳ ፣ የምዕራብ ጎጃሙ ደቡብ አቸነፈርና የአዊ ዞኑ ጃዊ ወረዳዎች በሚዋሰኑበት ስፍራ ላይ ይገኛል፡፡ ውሃው ወደ እርሻ ማሳዎች እንዲደርስ ለማድረግም 31 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ዋና ካናል ተገንብቷል፡፡

በፕሮጀክቱ የእስከአሁን እንቅስቃሴ ከ17,ዐዐዐ ሄክታር በላይ መሬት ከሦስተኛ ወገን ነፃ በማድረግ ለአገዳ እርሻ ዝግጁ ከመደረጉም በላይ ውሃ ወደ አገዳ እርሻ ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ እስከ ህዳር 2006 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ 2,724 ሔክታር መሬት ሙሉ በሙሉ በሸንኮራ አገዳ ዘር በመሸፈን ለሚገነቡ ፋብሪካዎች የሙከራ ተግባርና የዘር አቅርቦት በራሱ በፕሮጀክቱ እየተሸፈነ ይገኛል፡፡ የበለስ የተቀናጀ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ እያንዳንቸው በቀን 12 ሺ ቶን የሸንኮራ አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው ሦስት ፋብሪካዎች / በለስ ቁጥር 1፣ በለስ ቁጥር 2 እና አይማ ፋብሪካ/ ይኖሩታል፡፡ በ75 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግብአትነት የሚጠቀሙት እነዚህ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ በድምሩ በዓመት 726ሺህ ቶን ወይም 7 ሚሊዮን 260 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ይኖራቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከስኳር ተረፈ ምርት በአመት 62.4 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል እና 165 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመርቱም ይጠበቃል፡፡ ይህም አገራችን ተግባራዊ በማድረግ ከዓለም ግንባር ቀደም የሆነችበትን የአረንጓዴ

ልማት ስትራቴጂን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ዓላማዬ ብሎ ከያዛቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ ለዜጐች የሥራ እድል ፈጠራን ማመቻቸት ነው፡፡ በዚህም መሠረት በአሁኑ ጊዜ ለ1ዐ ሺ 6ዐ3 ወንዶችና ለ3ሺ742 ሴቶች በአጠቃላይ ለ14ሺ345 የአካባቢው ነዋሪዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ከ69 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

በ2ዐዐ4 ዓ.ም ፕሮጀክቱ በሚገነባበት አካባቢ ይኖሩ ለነበሩና እንዲሰፍሩ ለተደረጉ 1,909 የጃዊ ወረዳ የቤተሰብ ኃላፊዎች የመኖሪያና የእርሻ ቦታ ከመመቻቸቱም ባሻገር 53 ሚሊዮን ብር የካሣ ክፍያ ተሰጥቶ በአግባቡ በተመረጠላቸው ቦታ ሰፍረው የተረጋጋ ኑሮ በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ነዋሪዎቹ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች ፣ የሰውና የእንስሳት ጤና ኬላዎች ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ፣ ክረምትና በጋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መንገድ በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

ለስኳር ልማቱ መፋጠን አስተዋጽኦ ለማድረግ በፈቃዳቸው መኖሪያ አካባቢያቸውን እና የእርሻ መሬታቸውን ትተው ከተነሱ የአካባቢው ማሕበረሰብ ልጆች ውስጥ 1ዐኛ ክፍልን አጠናቀው ስራ አጥ የነበሩ 30 ወጣቶችን በመመልመል በጫንጮ ትራክተር ኦፕሬተር ማሰልጠኛ ለሦስት ወር እንዲሰለጥኑ ተደርጎ በፕሮጀክቱ በቋሚ ሠራተኛነት ተቀጥረዋል፡፡ በዚህም ፕሮጀክቱ ለህብረተሰቡ ያለውን አጋርነት በተግባር አስመስክሯል፡፡

Page 20: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 4 ቅፅ 2. ቁጥር 2  ታህሳስ 2006

:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A [email protected]

www.facebook.com/etsugar

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽኝ ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት

www.etsugar.gov.et

ጣፋጭ ዜና መጽሔት Food Lover Owned Since 2012