Top Banner
ዜና መፅሔት ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ! ቅፅ 3 ቁጥር 4- ሰኔ 2007 ዓ.ም www.etsugar.gov.et.com || facebook.com/etsugar ጣፋጭ በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት :+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ተመረቀ የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም ተመረቀ፡፡ በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ፋብሪካው ቀደም ሲል በፓኪስታን ባለሃብቶች የተጀመረ እንደነበር አስታውሰው፣ ይሁንና ባለቤቶቹ በራሳቸው ችግር ምክንያት የፋብሪካውን ግንባታ ማስቀጠል በማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ፋብሪካውን ተረክቦ እንዲሰራ ጥያቄ አቅርበው መንግሥት ፋብሪካውን ተረክቦ ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ የከሰም ስኳር ፋብሪካ 90 በመቶ የፋብሪካ ግንባታውን በማጠናቀቅ በግንቦት ወር መጨረሻ የሙከራ ምርት ጀምሯል፡፡ በቅርብ ቀናት ውስጥም ወደ መደበኛ የማምረት ሂደት ውስጥ ይገባል፡፡ የፋብሪካው ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ ቸኮል እንደገለጹት፣ ፋብሪካው መጀመሪያ ላይ ወደ ምርት ሲገባ በዕቅድ የከሰም ስኳር ፋብሪካ የሙከራ ምርት ጀመረ » ወደ ገጽ 2 ዞሯል በውስጥ ገጾች በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ኑሮ እየተሻሻለ መሆኑ ተገለጸ ››ገጽ 5 በኮርፖሬሽን ደረጃ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ተመሠረተ ››ገጽ 6 በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ተነስቶ የነበረውን እሳት ሲያጠፉ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምስጋና ዝግጅት ተካሄደ * ለመታሰቢያነት የመሰናዶ ትምህርት ቤት በፋብሪካው አካባቢ ይገነባል ስኳር ኮርፖሬሽን መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ተነስቶ የነበረውን እሳት ለማጥፋት የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የፋብሪካውን ሠራተኞች ለመዘከርና ለማመስገን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለማጽናናት የምስጋና ዝግጅት አካሄደ፡፡ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም በተካሄደው ዝግጅት ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር » ወደ ገጽ 3 ዞሯል » ወደ ገጽ 4 ዞሯል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፋብሪካውን ሲመርቁ የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት
16

ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

Feb 16, 2017

Download

Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ዜና መፅሔት

ራዕይ፡ ቀጣይነት ባለው ዕድገት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 የስኳር አምራች አገራት ተርታ መሰለፍ!

ቅፅ 3 ቁጥር 4- ሰኔ 2007 ዓ.ምwww.etsugar.gov.et.com || facebook.com/etsugar

ጣፋጭ

በስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ ዜና መጽሔት:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ተመረቀየአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም ተመረቀ፡፡

በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ፋብሪካው ቀደም ሲል በፓኪስታን ባለሃብቶች የተጀመረ እንደነበር

አስታውሰው፣ ይሁንና ባለቤቶቹ በራሳቸው ችግር ምክንያት የፋብሪካውን ግንባታ ማስቀጠል በማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ፋብሪካውን ተረክቦ እንዲሰራ ጥያቄ አቅርበው መንግሥት ፋብሪካውን ተረክቦ ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የከሰም ስኳር ፋብሪካ 90 በመቶ የፋብሪካ ግንባታውን በማጠናቀቅ በግንቦት ወር መጨረሻ የሙከራ ምርት ጀምሯል፡፡ በቅርብ ቀናት ውስጥም ወደ መደበኛ የማምረት ሂደት ውስጥ ይገባል፡፡

የፋብሪካው ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ ቸኮል እንደገለጹት፣ ፋብሪካው መጀመሪያ ላይ ወደ ምርት ሲገባ በዕቅድ

የከሰም ስኳር ፋብሪካ የሙከራ ምርት ጀመረ

» ወደ ገጽ 2 ዞሯል

በውስጥ ገጾች

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ኑሮ እየተሻሻለ መሆኑ ተገለጸ ››ገጽ 5

በኮርፖሬሽን ደረጃ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ተመሠረተ ››ገጽ 6

በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ተነስቶ የነበረውን እሳት ሲያጠፉ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የምስጋና ዝግጅት ተካሄደ

* ለመታሰቢያነት የመሰናዶ ትምህርት ቤት በፋብሪካው አካባቢ ይገነባል

ስኳር ኮርፖሬሽን መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ተነስቶ የነበረውን እሳት ለማጥፋት የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን የፋብሪካውን ሠራተኞች ለመዘከርና ለማመስገን እንዲሁም

ቤተሰቦቻቸውን ለማጽናናት የምስጋና ዝግጅት አካሄደ፡፡

በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ሚያዝያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም በተካሄደው ዝግጅት ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር

» ወደ ገጽ 3 ዞሯል

» ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፋብሪካውን ሲመርቁ

የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት

Page 2: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 3. ቁጥር 4 | ሰኔ 2007 | 2

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ...

መንግሥት ልማቱ በአካባቢው እንዲካሄድ ሲወስን በዋነኛነት የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን በማሰብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንንም ለማሳካት የአካባቢው አርሶ አደሮች ለፋብሪካው ግብዓት የሚውለውን ሸንኮራ አገዳ በማልማትና በማቅረብ ሥራ ውስጥ በስፋት እንዲሰማሩ የኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ወለጋ፣ የኢሉአባቦራ እና የጅማ ዞኖች አንድ ላይ በመሆንና አርሶ አደሮቹን በማስተባበር ወደ ልማቱ ውስጥ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው ወጣቶችም የትኛውንም ሥራ ሳይንቁ በፋብሪካው የተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ ተሰማርተው መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ለፋብሪካው ግብዓት የሚውለው የሸንኮራ አገዳ በ50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ መሆኑን አቶ ኃይለማርያም ጠቅሰው፣ ለዚሁ ሥራ የተጀመረው ግድብ ተጠናቆ የመስኖ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ማፋጠን እንዲቻል የግድቡን ሥራ የያዙት የኢትዮጵያ የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት እና የኦሮሚያ የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ከፍተኛ ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ኢንዱስትሪ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብለው ከተለዩት ንዑስ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ አንዱ የስኳር ልማት ዘርፍ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚሁ መሰረት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ከሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ የተንዳሆ 1 እና የከሰም ስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ተጠናቆ የሙከራ ምርት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ለፋብሪካው ሥራ መጀመር ያላሰለሰ ጥረት ላበረከቱ የፋብሪካው የማኔጅመንት አካላት እና ሠራተኞች እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ ላደረጉ የፓኪስታን ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በበኩላቸው የፋብሪካውን ምረቃ አስመልክተው እንደተናገሩት፣ መንግሥት ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ፋብሪካውን

በ2005ዓ.ም አል ሀበሽ ከተባለ የፓኪስታን ኩባንያ ወደ ራሱ በማዛወር ወደ ሥራ እንዲገባ አድርጓል ብለዋል፡፡

በተለይም ስኳር ኮርፖሬሽን ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ባካሄዳቸው መጠነ ሰፊ ሥራዎች የፋብሪካውን ቀሪ ሥራዎች በማጠናቀቅ ለምረቃ ማብቃቱን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት በቂ የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት የሌለው በመሆኑ ይህንን ችግር በፍጥነት ለመፍታት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡

በእለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አበራ ማሞ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ በዘንድሮ ዓመት ለፋብሪካው ግብዓት የሚውል እስካሁን ከ1ሺህ 600 ሄክታር መሬት በላይ በሸንኮራ አገዳ የለማ ሲሆን፣ ለ2007/2008 የምርት ዘመን ደግሞ 4ሺህ 369 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ በ2ሺህ 300 ሄክታር መሬት ላይ ተከላ ተጀምሯል፡፡

የመስኖ መሰረተ ልማት በሚፈለገው ደረጃ ባለመዘርጋቱ እና የአካባቢውን አርሶ አደር በተፈለገው ጊዜ በመንደር የማሰባሰብ ሥራ በመጓተቱ የተያዘውን የአገዳ ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ማሳካት አለመቻሉን ነው ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለው ያስረዱት፡፡

ፋብሪካው ከአካባቢው ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የተመረቁ በርካታ ወጣቶችን ወደ ሥራ ያስገባ መሆኑን ያመለከቱት አቶ

አበራ፣ በተጨማሪም በብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን የሰለጠኑ ባለሙያዎች ተመድበው እራሳቸውን እና ህብረተሰቡን መጥቀም ጀምረዋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት ከአካባቢው ማህበረሰብ የተውጣጡ ሥራ ፈላጊዎችን በ21 ማህበራት ተደራጅተው ለበርካታ አባላት የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን ከ2500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአርጆ ዲዴሳ ፋብሪካ ምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር ከድር፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪ እና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ እንዲሁም የፌደራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የፋብሪካው የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡

በምስራቅ ወለጋና በኢሉ አባቦራ ዞኖች መካከል ከአዲስ አበባ - ጅማ - በደሌ መንገድ 540 ኪ.ሜ እንዲሁም ከአዲስ አበባ - ነቀምት - አርጆ - በደሌ መስመር 395 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ አሁን በቀን 8ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፣ ወደፊት በቀን 12ሺህ ኩንታል ስኳር ማምረት እንዲችል ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡

» ከገጽ 1 የዞረ

Page 3: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

| 3

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የከሰም ስኳር ፋብሪካ የሙከራ ...

» ከገጽ 1 የዞረ

የተያዘው የማምረት አቅሙ 80 በመቶ ነው፡፡ በዚህም በመጀመሪያዎቹ የሙከራ ጊዚያት 3 ሺህ ቶን የሸንኮራ አገዳ በቀን በመፍጨት ወይም በቀን 3 ሺህ ኩንታል ስኳር በማምረት በቀጣይ ወደ 4ሺህ 800 ቶን (4ሺህ 800 ኩንታል ስኳር ) በቀን የሚያመርትበት ደረጃ ይደርሳል፡፡

አቶ ወርቁ አክለው እንዳብራሩት ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ወደሚችልበት ደረጃ ሲደርስ በቀን 6 ሺህ ቶን የሸንኮራ አገዳ በመፍጨት ዓመታዊ ስኳር የማምረት አቅሙ 1.53 ሚሊዮን ኩንታል ይሸጋገራል፡፡

የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከሚገኝበት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሳ ከሐምሌ አጋማሽ እስከ ነሐሴ መጨረሻ ብቻ በዝናም ምክንያት ካልቆመ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ ሊያመርት የሚያስችል የአየር ንብረት ያለው አካባቢ እንደሆነ ነው ጊዜያዊ ዋና ስራ አስኪያጁ የሚገልጹት፡፡

በአሁኑ ወቅት የፋብሪካው ሁለት ባለ 13 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ተሞክረው በጥሩ ሁኔታ በመስራት ላይ እንደሚገኙ አቶ ወርቁ ጠቁመው፣ የኃይል ማስተላለፊያ ሰብ ስቴሸን ግንባታም በመከናወን ላይ እንደሚገኝና በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ ይህ የሰብ ስቴሽን ግንባታ እንደተጠናቀቀ ፋብሪካው የራሱን የኃይል ፍላጎት በማሟላት ከ10 እስከ 12 ሜጋ ዋት የሚደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል ለብሔራዊ ቋት እንደሚያበረክትም አስረድተዋል፡፡

ፋብሪካው እስካሁን ለ5 ሺህ 294 ዜጎች የቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዚያዊ የስራ እድል እንደፈጠረ የሚገልጹት አቶ ወርቁ፣ በዚህም ከ490 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ተወላጅ አርብቶ አደሮች ቋሚ የስራ ዕድል አግኝተዋል ብለዋል፡፡

የማኅበረሰቡን ሁሉ አቀፍ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያም ቁጥራቸው እስከ 755 የሚደርስ የአካባቢውን አርብቶ አደሮች በሸንኮራ አገዳ አብቃይነት ለማሳተፍ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ፋብሪካው ለ463 አርብቶ አደሮች ለእያንዳንዳቸው

0.25 ሔክታር የጓሮ እርሻ መሬትና 0.75 ሔክታር በሸንኮራ የተሸፈነ ማሳ እንዲሰጣቸው አድርጓል ነው ያሉት፡፡ በአሁኑ ወቅትም 396.75 ሔክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት በአካባቢው አርብቶ አደሮች እየለማ እንደሚገኝ አያይዘው ገልጸዋል፡፡

አቶ መላኩ አለኸኝ በስኳር ኮርፖሬሽን የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው እንደገለጹት የከሰም ስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዲገባ በኮርፖሬሽኑ በኩል ከፍተኛ እገዛ ተደርጓል፡፡

የከሰም ስኳር ፋብሪካ በተለይ ከአካባቢው ህዝብ፣ ከፌዴራል እስከ ከአፋር ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የነበሩ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫ በጋራ አስቀምጦ ለተግባራዊነቱ በቅንጅት በመስራቱ ፋብሪካው ወደ ሙከራ ምርት ሊገባ መቻሉንም አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካው ከአካባቢው ሕዝብ፣ ከአስተዳደሩና ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በስኳር ልማቱ ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረሱ የተዘረፉ የፋብሪካው ማሽነሪዎች እና የመስኖ አውታር መሸፈኛ ጂኦሜምብሬኖች በሕዝቡ ትብብር እንዲመለሱ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡

የመንግሥት ስትራተጂ ማንኛውም ፕሮጀክት ሲከናወን የአካባቢውን ተወላጆች የመጀመሪያ ተጠቃሚ የማድረግ አቅጣጫን መከተል እንደሚገባው የሚያስቀምጥ መሆኑን ያወሱት አቶ መላኩ በከሰም ስኳር ፋብሪካ የአካባቢው ተወላጅ አርብቶ አደሮች በሸንኮራ አገዳ

ልማት እና በተለያዩ ማሽነሪዎች አስፈላጊውን ስልጠና አግኝተው እንዲሳተፉ እና በቀጣይም በተለይ የትምህርት ዝግጅቱ ያላቸው ወደ አመራርነት እንዲሸጋገሩ በመንግሥትም ሆነ በፋብሪካችን አቅጣጫ ተይዞ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ሀሰን ዳውድ ሀሰን በፋብሪካው የህዝብ አደረጃጀትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው እንደገለጹት ከፋብሪካው፣ ከፌዴራልና ከክልል አመራር አካላት ጋር በመቀናጀትና በጋራ የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የአካባቢው ተወላጅ አርብቶ አደሮች ጋር በልማቱ አስፈላጊነት ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል፡፡ ይህ በመሆኑም ዛሬ ላይ በፋብሪካው የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ይደርሱ የነበሩ አንዳንድ ችግሮች መወገድ ከመቻላቸው በላይ በአካባቢው አርብቶ አደር ዘንድ የባለቤትነት መንፈስ በመስረጹ የፋብሪካው የሥራ እንቅስቃሴ ያለምንም መስተጓጎል እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአካባቢው አርብቶ አደሮች ከልማቱ የመጀመሪያ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የአካባቢው ተወላጆች የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስደው በፋብሪካ፣ በሸንኮራ አገዳ ማሳ፣ በጥበቃ፣ በትራክተር ኦፕሬተርነት እና በተለያዩ ሙያዎች ተቀጥረው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ያብራሩት አቶ ሀሰን፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችም በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተደራጅተው እየሰሩ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

የፋብሪካው ጊዜያዊ ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ ቸኮል

Page 4: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 3. ቁጥር 4 | ሰኔ 2007 | 4

በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ተነስቶ የነበረውን.. » ከገጽ 1 የዞረ

አቶ ሽፈራው ጃርሶ በፋብሪካው ላይ ደርሶ የነበረውን የእሳት አደጋ በመከላከል ዘመቻ ለተሳተፉ የፋብሪካው መላ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት፣ ለአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ለኦሮሚያ ክልል የተለያዩ መ/ቤቶች፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን፣ ለፌደራል ፖሊስ እና እሳቱን በማጥፋት ድጋፍ ላደረጉ ሌሎች ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አክለውም “ጀግንነት በጦር ሜዳ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ የጀግንነት ተግባር አለ፡፡ ለዚህ ደግሞ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ፋብሪካቸውን ከጥፋት ለማዳን የሰሩት ጀብድ ማረጋገጫ ነው፡፡ ከአካል ጉዳት እስከ ምትክ የለሽ የህይወት መስዋዕትነት ከፍለው ፋብሪካውን ከውድመት በመታደግ ጀግኖች መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡ ፊንጫአ እንዲህና እንዲያ ነበር ተብሎ ሊወራለት ከነበረው የታሪክ አጋጣሚ በማዳን ምትክ የማይገኝለት ሀገራዊ ውለታ ፈጽመዋል፡፡ “የሀገር ሀብት የሆነው ፋብሪካ ከሚጠፋ

በማለት ራሳቸውን ግንባር ቀደም መስዋዕት በማድረግ እውነተኛ የሀገር ፍቅር ያላቸው ጀግኖች መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡ የፈጸሙት ተግባር ከቃል በላይ የሆነ፣ በእጅጉ ልብን የሚነካ፣ ምንጊዜም ከአእምሮ የማይጠፋ ህያው ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም በስኳር ኢንዱስትሪ ዘወትር ደምቀው የሚወደሱ ባለውለታዎች ናቸው” ብለዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የእነዚህን ጀግኖች ገድልና ታሪክ በክብር በማኖር ለትውልድ እንዲተላለፍ ከማድረግ ባሻገር ለሰማዕታቱ መታሰቢያ የሚሆን ደረጃውን የጠበቀ የመሰናዶ ትምህርት ቤት በፋብሪካው አካባቢ ለመገንባት መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የአባይ ጮመን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገለታ ቱሊ ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር የትምህርት ቤቱን የመሠረተ ድንጋይ ካስቀመጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር ስኳር ኮርፖሬሽን ፋብሪካውን ከከፍተኛ ጉዳት ለማዳን የህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች መታሰቢያ እንዲሆን የመሰናዶ ትምህርት

ቤት ለመገንባት መወሰኑ ተገቢና የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ መኮንን በበኩላቸው “ያጋጠመን ድንገተኛ አደጋ እጅግ አስደንጋጭ ቢሆንም በሁሉም ባለድርሻ አካላት መለኪያ የለሽ ርብርብ በተለይም በጀግኖች ሠራተኞቻችን የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ፋብሪካችንን ከጉዳት ለማዳን ችለናል” ብለዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ፋብሪካው በፍጥነት ወደ መደበኛ የምርት ሥራ መግባት መቻሉን አስታውሰዋል፡፡

በመጨረሻም መስዋዕትነት ለከፈሉት ሠራተኞችና በከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት ከፋብሪካው ጎን ለነበረው የአካባቢው ማህበረሰብ ያላቸውን ልዩ አድናቆትና ምስጋና የገለጹት ዋና ስራ አስኪያጁ፣ የጀግኖቹን ታሪክ ጠብቆ ለማቆየት የፋብሪካው ሠራተኞች ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ በኃላፊነት ስሜት ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ መኮንን

Page 5: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

| 5

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮች ኑሮ እየተሻሻለ መሆኑ ተገለጸ

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአካባቢው የሚገኙ አርብቶ አደሮች የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባከናወናቸው በርካታ ተግባራት ኑሮአቸው እየተሻሻለ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በግንቦት ወር መጨረሻ በፕሮጀክቱ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮች በተዘጋጀላቸው መስኖ ገብ መሬት ላይ የሚያለሙት በቆሎ ራሳቸውን በምግብ እልህ ከመቻል ባለፈ ሌሎች ወገኖቻቸውን እንዲረዱ አስችሏቸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ዋንኛ ዓላማ የአካባቢውን አርብቶ አደሮች የልማቱ ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ተግባር በቀጣይ ፕሮጀክቱ በሚደርስባቸው ሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

“የመስኖ መሠረተ ልማቱ በተዳረሰበት ቦታ ሁሉ የመጀመሪያ ስራችን የሚሆነው የአካባቢውን ሕብረተሰብ ተጠቃሚ ማድረግ

ነው፡፡ ለአርብቶ አደሮቹ የሚሆን ማሳ አስተካክለን ሳንሰጥ ፕሮጀክቱ ለራሱ የሚሆን አገዳ አይተክልም፡፡ ይህ በፖሊሲ ደረጃ የምንመራበት ነው፡፡ ይህም አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለፕሮጀክቱም ከፍተኛ ጠቀሜታ አስገኝቷል፡፡” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

በቀጣይም አርብቶ አደሮቹ በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ የሸንኮራ አገዳ አልምተው ለፋብሪካው በመሸጥ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል፡፡

አርብቶ አደሮቹ በመንደር በተሰባሰቡባቸው አካባቢዎች የተገነቡ የመሠረተ ልማትና የማህበራዊ ተቋማት ከአገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዳስቻላቸውም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡

የኦሞ ሸለቆ በኢትዮጵያ ትልቁ የሸንኮራ አገዳ የሚለማበት ሸለቆ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሽፈራው ወደ ሸለቆው የሚወስዱ ሦስት የአስፋል መንገዶች በግንባታ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው በቀጣይ የአካባቢው አርብቶ

አደር የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የአካባቢው አርብቶ አደር ከሸንኮራ አገዳ የሚገኘውን ተረፈ ምርት በመጠቀም በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ በስፋት ተሳታፊ እንዲሆን የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡

የአርብቶ አደሩን ልጆች ከፕሮጀክቱ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና እየሰጠ ወደ ስራ ማሰማራቱን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰው፣ ይህን ጥረቱን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

የአካባቢው ህብረተሰብ ከኦሞ ኩራዝ ስካር ልማት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ተጠቃሚ ቢሆንም በስራ እድል ፈጠራና በሌሎች ተያያዥ ስራዎች ለመላ አገሪቱ ዜጎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እየሰጠ ያለ ፕሮጀክት መሆኑንም አቶ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

የኦሞ ኩራዝ ስካር ልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ

» ወደ ገጽ 6 ዞሯል

ዋና ዳይሬክተሩ ከአርብቶ አደሮችና ከጎሳ መሪዎች ጋር ሲወያዩ

Page 6: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 3. ቁጥር 4 | ሰኔ 2007 | 6

በሚገኝበት አካባቢ የሚኖሩ አርብቶ አደሮች ለዘመናት ከአገሪቱ ልማት ተጠቃሚ ሳይሆኑ የቆዩ መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ ሽፈራው ፕሮጀክቱ በአካባቢው መተግበሩ ልማትን ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ከማዳረስ አንጻርም የጎላ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል፡፡

በተያያዘ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ከአካባቢው አርብቶ አደሮችና የጎሳ መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የኦሞ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ በቅርቡ ምርት የሚጀምር መሆኑን ጠቁመው “ከመሬታችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ስኳር ሊመረት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋቸዋል አርብቶ አደሮቹን፡፡በውይይቱ “ልጆቻችሁም ትምህርት ቤት

ገብተዋል፣ ሰልጥነውም በተለያዩ የስራ መስኮች በፕሮጀክቱ ተቀጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኛ በኩል ያቀድነውን እየሰራን ነው” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የአካባቢውን ሠላም በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ አርብቶ አደሮቹ የሚጠበቅባችውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ከነበሩት አርብቶ አደሮች መካከል የተወሰኑት በሰጡት አስተያየት ፕሮጀክቱን በአካባቢው ተግባራዊ ማድረግ ሲጀመር የተገባው ቃል በተግባር እየተለወጠ በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አዘጋጅቶ በሰጣቸው መሬት ላይ በቆሎ በማልማት ከራሳቸው አልፎ ሌሎችን መርዳት መጀመራቸውን ገልጸው፣ ፋብሪካው ስራ ሲጀምር ሸንኮራ አገዳ በማልማትና ለፋብሪካው በመሸጥ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን የፋብሪካውን ስራ መጀመር እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን ዋና ዳይሬክተሩ ከክልሉ፣ ከዞንና ከወረዳ የአርብቶ አደር ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱም በካፋ ዞን በዴቻ፣ በቤንች ማጂ ዞን ደግሞ መኢኒት ሻሻ፣ በማጂና ሱርማ ወረዳዎች በቀጣይ በመንደር የሚሰባሰቡ አርብቶ አደሮችን በተመለከተ ከፕሮጀክቱ የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ጋር በጋራ ዝርዝር እቅድ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በኦሞ ኩራዝ ስካር ልማት ፕሮጀክት ከሚገነቡት አምስት ፋብሪከዎች የሦስቱ ግንባታ የተካሄደ ሲሆን፣ የሁለቱ ግንባታ ደግሞ በሁለተኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡

በኮርፖሬሽን ደረጃ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ተመሠረተ* ማህበሩ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካትና ሠራተኛውን ተጠቃሚ ለማድረግ ይረዳል

በስኳር ኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶችን እንዲሁም ዋናውን መስሪያ ቤት በአንድነት ያካተተ በኮርፖሬሽን ደረጃ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሰኔ 12 ቀን 2007ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤት ተመሰረተ፡፡ ማህበሩ ለአገራዊ ራዕይ ስኬት፣ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካትና ሠራተኛውን በየደረጃው

ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

በማህበሩ ምስረታ ላይ የስኳር ፋብሪካዎችን፣ ፕሮጀክቶችንና ዋና መስሪያ ቤትን የወከሉ 156 የዘርፍ ሠራተኛ ማህበር ስራ አስፈጻሚዎችና የጉባኤ አባላት እንዲሁም የኦዲት ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል፡፡ በእለቱም የማህበሩ

ምክር ቤት አባላት፣ የስራ አፍጻሚዎችና የኦዲት ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል፡፡

በዚሁ መሠረት አቶ ተመስገን ወልደመስቀል ሊቀመንበር (ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ)፣ አቶ ድሪብሳ ለገሰ ምክትል ሊቀመንበር (ከፊንጫአ

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት አካባቢ...

» ወደ ገጽ 7 ዞሯል

» ከገጽ 5 የዞረ

የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር መስራች ጉባሄ በተካሄደበት ወቅት

Page 7: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

| 7

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ስኳር ፋብሪካ)፣ አቶ አበራ አወኖ ዋና ጸሐፊ (ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ) ሆነዋል፡፡

አቶ ጌታሁን አርፊጮና አቶ ተሾመ ያሚ በቅደም ተከተል ማህበሩን በሂሳብ ሹምነትና በገንዘብ ያዥነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል፡፡ እንዲሁም አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ የማህበራዊ ጉዳይ እና የኢንዱስትሪ ግንኙነት ተጠሪ እንዲሆኑ ጉባኤው ሲመርጣቸው ወይዘሮ የትምወርቅ ደረሰ ደግሞ የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ሆነዋል፡፡ በማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነትም አቶ ፅጋበይ ወንድምዓለም፣ አቶ እያሱ ንጉስ፣ አቶ አለነ ካሳሁን እና አቶ ድንበሩ ታደሰ ተመርጠዋል፡፡

በኦዲት ኮሚቴነት የተመረጡት ደግሞ አቶ ተሰማ ሔራሞ ሰብሳቢ፣ ወይዘሮ ሠላማዊት አብርደው ፀሐፊ እንዲሁም አቶ ተካልኝ መገርሳ አባል በመሆን ነው፡፡

በማህበሩ ምስረታ ጉባኤ ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ባደረጉት ንግግር የማህበሩ መመስረት ሠራተኛው ለአገራዊ ራዕይና ኮርፖሬሽኑ ለተቋቋመበት ዓላማ ስኬት በጋራ ተሰልፎ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግበትን እና በአገራዊ የልማት አጀንዳ ዙሪያ ተሳታፊና በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበትን እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

በህብረት ስምምነት ድርድር ወቅትም ድርድሩ ኃላፊነት በተሞላውና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ መካሄድ እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት በፕሮጀክቶችና ፋብሪካዎች እንዲሁም በዋና መስሪያ ቤት የዘርፍ ሠራተኛ ማህበራት ሲመሰረቱ ተገቢውን ድጋፍ መስጠቱን አስታውሰው፣ በቀጣይም አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትብብርና ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሌ በበኩላቸው ስኳር ኮርፖሬሽን የሠራተኞችን በነጻ የመደራጀት መብት በማክበር የፕሮጀክት ሠራተኞች ከነባር ፋብሪካዎች ጋር በአንድነት እንዲደራጁና መብትና ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ላደረገው ከፍተኛ እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የስኳር ኢንዱስትሪው የአገሪቱን የስኳር ምርት ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የውጭ ምንዛሪ የማስገኘት ኃላፊነት የተሰጠው በመሆኑ መንግሥትና ሕዝብ ከኮርፖሬሽኑ ውጤት እንደሚጠብቁ ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ማህበሩ ኮርፖሬሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ እንዲያሳካ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በእለቱ በማህበሩ መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ የተሰጡ አስተያየቶች እና ማሻሻዎች ተካተው እንዲቀርቡ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በኮርፖሬሽን ደረጃ መሠረታዊ የሠራተኛ...

የስኳር ልማቱ እያስገኘ ባለው ጠቀሜታ ላይ ከአፋር አርብቶ አደሮችና ጎሳ መሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ ከሚገኙ 11 ቀበሌዎች ከተውጣጡ ከ400 በላይ አርብቶ አደሮች፣ ጎሳ መሪዎች እና አስተባባሪዎች ጋር የስኳር ልማቱ እያስገኘ ባለው ጠቀሜታ ላይ ግንቦት 2007ዓ.ም ዱብቲ ከተማ በሚገኘው የፋብሪካው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውይይት ተካሄደ፡፡

ውይይቱ በዋነኛነት ያተኮረው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ለአካባቢው ሕዝብ እያበረከተ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በሚያስቀጥልበት ሁኔታና

ይበልጥ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በሚያስቸሉ ጉዳዮች ላይ ነበር፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ እስማኤል አሊሴሮ እንደተናገሩት መንግሥት አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በመንደር ተሰባስቦ የተረጋጋ ኑሮ በመምራት የማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኝና የኑሮ ዘይቤው የተሻለ እንዲሆን እየሰራ ነው፡፡

በተለይም በክልሉ እየተካሄደ ያለው

የስኳር ልማት ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ከሚፈጥረው የስራ ዕድል ባሻገር አርብቶ አደሩ በሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ማኅበራት ተደራጅቶ ሸንኮራ በማምረትና ለፋብሪካው በማቅረብ ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ የሚሆንበት ጥሩ አጋጣሚ ተመቻችቷል ነው ያሉት፡፡ አያይዘውም ጠቀሜታው ቀጣይነት እንዲኖረው እና የስኳር ልማቱ ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ የአርብቶ አደሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ለልማቱ ስኬት የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡ » ወደ ገጽ 8 ዞሯል

» ከገጽ 6 የዞረ

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ውይይቱ ሲካሄድ

Page 8: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 3. ቁጥር 4 | ሰኔ 2007 | 8

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሙከራ ምርት ወቅት የነበሩበት ችግሮች ተፈተው ወደ መደበኛ የማምረት ስራ እየገባ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የፋብሪካው ጊዚያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አትክልቲ ተስፋዬ እንደገለጹት የስኳር ኮርፖሬሽን አመራር ባካሄደው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ፋብሪካው ጥቅምት 2007ዓ.ም የሙከራ ምርት መጀመሩን አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው ሙከራ ሲጀምር በቀን ይፈጭ የነበረውን 2 ሺህ ቶን አገዳ በሂደት ችግሮችን በመለየትና የማስተካከያ ርምጃ በመውሰድ በቀን ወደ 3 ሺህ ቶን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል፡፡ በተከናወኑ በርካታ ሥራዎችም ፋብሪካው ከሙከራ ምርት ወደ መደበኛ ሥራ እየገባ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የሁለተኛው ምዕራፍ የፋብሪካ ግንባታ ወደፊት የሚጀመር በመሆኑ ፋብሪካው ከሚኖረው ሰፊ የሸንኮራ አገዳ መሬት አንፃር አሁን ያለውን 20 ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ሽፋን ለማስፋት የአካባቢው ሕዝብ በልማቱ አምኖ ከፋብሪካው ጎን እንዲሰለፍ ሰፊ የሕዝብ ንቅናቄ መካሄዱንም አቶ አትክልቲ ገልጸዋል፡፡

ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የጎሳ መሪዎችን እና የአካባቢው አርብቶ አደሮችን በማወያየት የተጀመረው የሕዝብ ንቅናቄ የፌዴራል እና የአፋር ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የክልሉ የጎሳ መሪዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የማጠቃለያ መድረክ ተዘጋጅቶ በስኬት መጠናቀቁንና ይህም ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አትክልቲ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም አጠቃላይ መግባባት ላይ መድረስ በመቻሉና የአካባቢውን አርብቶ አደር ከልማቱ የመጀመሪያ ደረጃ ተጠቃሚ የማድረግ ሰፊ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው በመቀጠላቸው የፋብሪካው የስራ እንቅስቃሴ በሁሉም የስራ መስክ በኩል እየተቀላጠፈ ይገኛል ብለዋል፡፡

ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ወደ መደበኛ የማምረት ስራ እየገባ ነው

በተመሳሳይ በውይይቱ ወቅት የተገኙት የሱልጣን አሊሚራህ ልጅ አቶ ሀቢብ አሊሚራህ ባደረጉት ንግግር የኢፌዲሪ መንግሥት አገሪቱን ከድህነት ለማውጣት በሁሉም ክልሎች በርካታ ሥራዎችን እያካሄደ መሆኑን ገልጸው፣ በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ የሚገኙ አርብቶ አደሮችም በስኳር ልማቱ በስፋት በመሳተፍ እና ጠንክረው በመስራት ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን ዘመቻ ከዳር ማድረስ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የስኳር ልማቱ በመንደር እንዲሰባሰቡና የማህበራዊ አገልግሎቶች እና የመሰረተ ልማት አውታሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዳስቻላቸው አስረድተው፣ አሁን ደግሞ በማኅበር ለተደራጁ አርብቶ አደሮች ከ2,740 ሄክታር በላይ የለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ በልማቱ ያላቸው ተሳትፎም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ ሆነናል ብለዋል፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከሚያለማው 50 ሺህ ሄክታር ሸንኮራ አገዳ መሬት ውስጥ 25 ሺህ ሄክታሩ የሚለማው በአካባቢው አርብቶ አደሮች በተደራጁ የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢ ኅብረት ሥራ ማህበራት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም አስቦዳ እና ቦይና በተባሉ ቦታዎች በመንደር የተሰባሰቡ አርብቶ አደሮች በስድስት ማኅበራት ተደራጅተው በ1 ሺህ 119 ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ በማልማት ላይ ይገኛሉ፡፡

የሙከራ ምርት የጀመረው የተንዳሆ 1 ስኳር ፋብሪካ እስካሁን ከ14 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ፣ ኮንትራትና ጊዚያዊ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 5 ሺህ 571 የሚሆኑት የአፋር ብሔረሰብ እና የክልሉ ተወላጆች ናቸው፡፡

ግንባታው በሁለት ምዕራፍ የሚከናወነው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የአንደኛው ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ተንዳሆ አንድ ወደ መደበኛ የማምረት ሥራ እየገባ ሲሆን ሲሆን፣ የተንዳሆ ሁለት ሥራም ይቀጥላል፡፡

የቁጥር 1 እና 2 አጠቃላይ ሥራ ተጠናቆ በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ በጋራ በቀን 26ሺህ ኩንታል ስኳር ያመርታሉ፡፡ አመታዊ የስኳር ምርት መጠናቸውም ደረጃ በደረጃ እያደገ በአመት ከ6ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በላይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የስኳር ልማቱ እያስገኘ ባለው ጠቀሜታ...

» ወደ ገጽ 9 ዞሯል

» ከገጽ 7 የዞረ

Page 9: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

| 9

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

ለኩራዝ ስኳር ፋብሪካ አንድና ሁለት ሸንኮራ በወቅቱ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግንባታቸው በመካሄድ ለሚገኙት ፋብሪካ አንድና ሁለት የሚያስፈልገውን የሸንኮራ አገዳ በወቅቱ ማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄደ፡፡

በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ በግንቦት ወር መጨረሻ በተካሄደው ውይይት በቅርቡ ወደ ምርት እንደሚገባ ለሚጠበቀው ፋብሪካ ቁጥር አንድ ከሚያስፈልገው 15 ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ውስጥ 10 ሺህ ሄክታሩ መተከሉንና ቀሪውን 5 ሺህ ሄክታር እስከ ነሐሴ 30/2007 ዓ.ም ለማልማት ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ለዚህም እንዲረዳ የመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታን በማከናወን ላይ የሚገኙት የፌዴራልና የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ውሃ

ሥራዎች ለግንባታው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን በማሟላት ቀሪ ሥራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

ለፋብሪካ ሁለት ደግሞ 15 ሺህ ሄክታር (ከኦሞ ወንዝ በስተግራ 13ሺህ ሄክታርና በስተቀኝ 2ሺህ ሄክታር) እስከ ነሐሴ 30/2008 ዓ.ም ድረስ ለመትከል በመስኖ አውታሮች ግንባታ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ተቋማት ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡

የሸንኮራ አገዳ ልማቱን ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ ለማድረግ በፋብሪካ ቁጥር

ሦስት አካባቢ የጠቅላይ መንደር ቤቶች ግንባታም ከወዲሁ እንዲጀመር አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ለዚህም የደቡብ ብ/ብ/ሕ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ቢሮ ስራውን በአስቸኳይ ለመጀመር የሚያስችሉ ቅድም ዝግጅቶች እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ከጠቅላይ መንደሩ ቤቶች ግንባታ ጎን ለጎንም የእርሻ ባለሙያዎች መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በቅድሚያ መዘጋጀት

እንዳለበት ተገልጿል፡፡

በውይይቱ ላይ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌዴራል ውሃ ስራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት፣ የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ውሃ ስራዎች፣ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር እና የቤቶች ልማት ቢሮ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የመስኖ አውታር ግንባታ በመካሄድ ላይ የሚገኙባቸውንና በቀጣይ ግንባታ የሚካሄድባቸውን የተለያዩ ቦታዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ፋብሪካው አጠቃላይ ከሚኖረው 50 ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማሳ ውስጥ ግማሹ በአካባቢው አርብቶ አደር እንዲለማ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ፋብሪካው ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ለጊዜው ለመስጠት ካቀደው 10ሺህ 29 ሄክታር መስኖ-ገብ ማሳ ውስጥ 4ሺህ 22 ሄክታሩ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው አርብቶ አደር እየለማ እንደሚገኝ የገለጹት ደግሞ ሐጂ አብዱ ሐሰን የፋብሪካው የሕዝብ አደረጃጀት፣ የሕዝብ ግንኙነትና ማኅበራዊ ጉዳይ አገልግሎት ኃላፊ ናቸው፡፡

የአፋር ክልል አርብቶ አደር በመንደር ተሰባስቦ የልማቱ ተጠቃሚ መሆን ይችል ዘንድ በዱብቲ ወረዳ ብቻ መንግስት ለማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ለመሰረተ ልማት አውታሮች ግንባታ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉንም ሐጂ አብዱ አብራርተዋል፡፡

በሁለት ምዕራፍ እየተገነባ ያለው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 26 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡

አቶ አትክልቲ ተስፋይ

ዋና ዳይሬክተሩ ውይይቱን ሲመሩ

Page 10: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 3. ቁጥር 4 | ሰኔ 2007 | 10

በፕሮጀክቱ የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለፀ

በወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የአካባቢውን ሕዝብ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ፡፡

በስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ ኤካል ነትር በፕሮጀክቱ ቆራሪትና ማይ ዝህልቶ የተባሉ የሰፈራ መንደሮችን ከጎበኙ በኋላ በሰፈራ መንደሮች፣ በማህበራዊና በመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ እንዲሁም አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራትን በማደራጀት ረገድ አበረታች ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በማይ ዝህልቶ ሕዝቡ የሚሰፍርበት ቦታ መረጣና ሽንሸና መጠናቀቁ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው እንዲሁም

ጤና ጣቢያና ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ሥራ መጀመሩ የሚበረታታ ነው ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ቀደም ብሎ በተቋቋመው ቆራሪት ሰፈራ መንደርም የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት ሕዝቡ እየተገለገለባቸው መሆኑን እና በመንደሩ በመፈጠር ላይ በሚገኘው የስራ እድልም ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን አክለው ተናግረዋል፡፡

በመንደሩ የተመሠረቱ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በልዩ ልዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊው፣ ማህበራቱ አባሎቻቸውን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች የሚያስፈልጋቸውን ሸቀጦች በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን አብራርተዋል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሴት ሠራተኞች ከአመራሩጋር ውይይት አደረጉ

• ለሴት ሠራተኞች በኃላፊነት ደረጃ ዕድገት መሠጠቱ ተገለፀየመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሴት ሠራተኞች ከአመራሩ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡ የሴቶችን ተሣትፎ ለማሣደግ ሴት ሠራተኞችን በኃላፊነት ደረጃ ዕድገት መሰጠቱም ተገልጿል፡፡

በውይይት መርሐ ግብሩ ላይ ሴት ሠራተኞች በስራ ላይ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በተለይም በዕድገት አሠጣጥ እና በተለያዩ ፆታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከፋብሪካው አመራር ጋር ተወያይተዋል፡፡

የፋብሪካው አመራር ከሥርዓተ ፆታ ጽህፈት ቤት ጋር በመሆን የሴቶችን ተሣትፎ ለማሣደግ በአፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ በርካታ ሴት ሠራተኞችን ያለውድድር በኃላፊነት ቦታ መመደቡን ዋና ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

የፋብሪካው የሥርዓተ ፆታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አለሚቱ ጉልቴ በበኩላቸው በተቋሙ ተምረው ዕድል ያላገኙ ሴቶች በተማሩት የትምህርት ዓይነት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የክህሎት ማዳበሪያ የሙያ ሥልጠና እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ 300 አካባቢ የነበረውን የሴት ሠራተኞች ቁጥር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ800 በላይ ማድረስ መቻሉም ተገልጿል፡፡

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ይማም ሴቶች የሀገሪቱ ልማት ግማሽ አካል መሆናቸውን እና ከወንዶች እኩል ብቻ ሣይሆን ከወንዶችም በበለጠ አቅም ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው ይሁንና ባለፉት ሥርዓቶች የደረሱባቸው ተፅዕኖዎች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ተሣትፎ ወደኋላ እንዲቀሩ አድርገዋቸዋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም በአሁኑ ወቅት የሴቶችን ተሣትፎ ለማሣደግ በሁሉም መድረኮች ለሴቶች ድጋፍ እንደሚደረግና ሴቶች ከወንዶች እኩል ነጥብ ቢያመጡ እንኳ ቅድሚያ ለሴቶች እንደሚሠጥ አውስተዋል፡፡

Page 11: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

| 11

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

የፌዴራል የስኳር ኢንዱስትሪ ምርምር ካውንስል ተመሠረተ

የፌዴራል የስኳር ኢንዱስትሪ ምርምር ካውንስል በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ሚያዚያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም በተካሄደ አውደ ጥናት ተመሠረተ፡፡

የምርምር ካውንስሉ የአገሪቱ የስኳር ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የምርምር ስራዎችን የመምራትና የማማከር ተግባራትን እንደሚያከናውን ይጠበቃል፡፡

በካውንስሉ ምስረታ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽፈራው ጃርሶ ካውንስሉ በምርምር የተገኙ ቴክኖሎጂዎች በሚጠበቀው ደረጃ እና መጠን በኢንዱስትሪው ኢንዲሰርጹ በማድረግ የስኳር ኢንዱስትሪውን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ነው የገለጹት፡፡

በስኳር ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እና የመሪነት ሚና ያላቸው አገራትን ልምድ በመቀመር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሌሎች ሙያዎች በተጨማሪ በሸንኮራ አገዳ አመራረት እና በስኳር ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት እንዲችሉ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት ተቀርጾ ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡

የትምህርት ተቋማቱ የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት በተጨማሪ በአካባቢያቸው የሚገኙትን የስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች ተወዳዳሪነትና ምርታማነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ቴክሎጂዎችን በማላመድ፣ በማሻሻል እና በማፍለቅ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ነው የጠቆሙት፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚያከናውኗቸው ምርምሮች በኢንዱስትሪው ችግሮች ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ እና የምርምር ድግግሞሽን በማስቀረት ውጤታማ እንዲሆኑ የምርምር ካውንስሉ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስረድተዋል፡፡

የካውንስሉን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በስኳር ኮርፖሬሽን የምርምርና ስልጠና ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ መኳንንት ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በምርምር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን በጽሁፍ አቅርባዋል

የምርምር ካውንስሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርን፣ የትምህርት ሚኒስትርን እና ሌሎች የባለድርሻ አካላትን በአባልነት ያካተተ ነው፡፡

የፌደራል ስኳር ኢንዱስትሪ ምርምር ካውንስል ምስረታ ጉባዔ

Page 12: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 3. ቁጥር 4 | ሰኔ 2007 | 12

“ከሬድ ታግ” ነጻ የወጣ አውቶቡስ

በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ከተጣለ ከአምስት ዓመት በላይ ያስቆጠረ አውቶቡስ በመስክ መሳሪያ ጥገና ክፍል የተሽከርካሪዎች ጥገና የካይዘን ልማት ቡድን ሠራተኞች ተጠግኖ ለዳግም አገልግሎት በቃ፡፡

አውቶቡሱ አስፈላጊው ጥገና ተደርጎለትና የሞዲፍኬሽን ሥራዎች ከተሰሩለት በኋላ በሚገባ ተፈትሾ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ በሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ዙሪያ የነበረውን እጥረት ከመቀነሱም ባሻገር አዲስ አውቶቡስ ለመግዛት ይወጣ የነበረውን ወጪ ማስቀረት ችሏል፡፡

በከሰም እና ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካዎች ዙሪያ የሚኖሩ የአፋር ተወላጅ አርብቶ አደሮች ስኳር ፋብሪካዎቹ በየአካባቢያቸው በመገንባታቸው የበርካታ ዕድሎች ተጠቃሚ መሆን እንዳስቻሏቸው ገለጹ፡፡

ሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ያሉ የአፋር ክልል አርብቶ አደሮች እንደገለጹት፣ ፋብሪካዎቹ በየአካባቢዎቻቸው በመገንባታቸው በሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢነት፣ በፋብሪካዎቹ የተለያዩ የስራ ክፍሎች፣ በሸንኮራ አገዳ ማሳ እንክብካቤ ስራ እና በተለያዩ የስራ መስኮች

መሰማራት እንዲችሉ በርካታ ዕድሎችን ፈጥረውላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በስኳር ልማቱ ሳቢያ የተለያዩ ማኅበራዊ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች በአካባቢያቸው በመገንባታቸው በአንድ ቦታ ተረጋግተው የተሻለ ኑሮ እንዲመሩ አስችሏቸዋል፡፡

በከሰም ስኳር ፋብሪካ ቅጥር ግቢ “በአረንጓዴ ልማት” በቋሚ ሰራተኛነት ከተቀጠሩ 60 ሴቶች መካከል አንዷ የሆነችው አስና መሐመድ የአፋር ብሔረሰብ ተወላጅ ስትሆን የፋብሪካው በአካባቢዋ መገንባት ያመጣላትን ትሩፋት ስትገልጽ “ቀደም ሲል በአካባቢያችን

ምንም ዓይነት የልማት እንቅስቃሴ ያልነበረ በመሆኑ በተለይ እኛ ሴቶች የስራ ዕድል አግኝተን አናውቅም፤ አሁን ግን በፋብሪካው ተጠቃሚ መሆን ችያለሁ፤ ቋሚ የፋብሪካው ተቀጣሪ በመሆኔ እና የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና መሰረተ ልማቶች በአካባቢዬ በመገንባታቸው ቤት መስራት እንዲሁም ከቦታ በታ ሳልዘዋወር ተረጋግቼ መኖር ጀምሬያለሁ” ብላለች፡፡ አስና አያይዛም ተረጋግታ በመኖሯ እና በአካባቢዋ ትምህርት ቤት በመቋቋሙ ልጆቿን ማስተማር እንደምትችል ገልጻለች፡፡

“በአካባቢያችን የተገነቡት ስኳር ፋብሪካዎች በርካታ ዕድሎችን አምጥተውልናል”

የአፋር አርብቶ አደሮች

ቆይታ

Page 13: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

| 13

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

መቅደስ ወልዴ የከምባታ ብሔረሰብ ተወላጅ ናት፡፡ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ እና በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የተሰጣትን የተግባርና የንድፈ ሐሳብ ስልጠና ተከታትላ በማጠናቀቅ በከሰም ስኳር ፋብሪካ በትራክተር ኦፕሬተርነት እያገለገለች ትገኛለች፡፡ እንደ እርሷ በትራክተር ኦፕሬተርነት ሙያ እያገለገለች የምትገኝ ሴት ባለሙያ እንዳለች የገለጸችው መቅደስ፣ ስራዋን ከወንዶቹ ባልደረቦቿ እኩል ማከናወን እንደምትችል ትናገራለች፡፡ አክላም ሌሎች ሴቶች የእርሷን ፈለግ እንዲከተሉ ትመክራለች፡፡

የከሰም ስኳር ፋብሪካን ደህንነት ለመጠበቅ በፋብሪካው በጥበቃ ስራ የተሰማሩ አምስት የአፋር ተወላጆች እንዳሉ የምትናገረው አርባኢ ዓሊ ናት፡፡ ወታደራዊ ስልጠና ወስዳ የፋብሪካውን ደህንነት በማስጠበቅ ስራ ላይ የምትገኘው አርባኢ ፋብሪካው በአካባቢዋ በመገንባቱ እርሷን ጨምሮ በርካታ ሴት እና ወንድ ወጣቶች በርካታ የስራ ዕድሎች እንደተፈጠሩላቸው ትገልጻለች፡፡ ከብዙ የስራ ዕድሎች ባሻገር በርካታ የማኅበራዊ ተቋማት እና የመሰረተ ልማቶችን ለአካባቢዋ ይዞ የመጣውን የከሰም ስኳር ፋብሪካ ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ የተሰጣትን ኃላፊነት በአግባቡ የምትወጣው ይዞላት የመጣውን ትሩፋት እና የአካባቢውን የወደፊት ብሩህ ተስፋ በመገንዘብ እንደሆነ አርባኢ

ትናገራለች፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በአካባቢዋ በመገንባቱ በአስቦዳ መንደር ማሰባሰቢያ ጣቢያ ቀደም ሲል በተሰጣት በመስኖ የሚለማ መሬት አማካይነት በቆሎ በመዝራት ተጠቃሚ ሆና እንደቆየች እና በአሁኑ ወቅት ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርገኛል ብላ ባመነችበት ጋብላይቱ አገዳ አብቃይ የኅብረት ስራ ማኅበር አባል በመሆን የሸንኮራ አገዳ አብቃይና አቅራቢነት ስራ የተሰማራችው ሞሚና ሁመድ አሊ የአፋር ብሔረሰብ ተወላጅ ናት፡፡

ወደ ሸንኮራ አገዳ ልማት ስራው የገባችው ከፋብሪካውና ከክልሉ የሚመለከታቸው መስተዳድር አካላት ጋር ከተወያየችና ካመነችበት በኋላ መሆኑን የምትናገረው ሞሚና በተሰጣት መሬት ላይ ለምታፈሰው ጉልበት እንደሚከፈላትና አገዳው ሲደርስም ለፋብሪካው አቅርባ ለመሸጥ የሸንኮራ አገዳ ልማት ስራዋን እያከናወነች እንደምትገኝ ገልጻለች፡፡

“ቀደም ሲል ብዙ ርቀት ተጉዤ ነበር ትምህርቴን የምከታተለው፤ አሁን ላይ ግን በርካታ የማኅበራዊ ተቋማት በመገንባታቸው በአካባቢዬ መማር ችያለሁ” ስትል ስኳር ፋብሪካው የፈጠረላትን መልካም ዕድል የምትገልጸው ሞሚና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ

ስትሆን ወደፊት በትምህርቷ ገፍታ በመቀጠል በፋብሪካው የተለያየ የስራ ክፍል መስራት ትፈልጋለች፡፡

ሌላው በጋብላይቱ አገዳ አብቃይ የኅብረት ስራ ማኅበር ታቅፎ በተሰጠው አንድ ሄክታር መስኖ ገብ መሬት ሁለት ዙር በቆሎ አምርቶ ተጠቃሚ መሆን እንደቻለ የሚናገረው ወጣት አሊ ሚኢ ማሂ ነው፡፡ ወጣቱ በአገዳ አብቃይና አቅራቢነት ከፋብሪካው ጋር ቢሰራ ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል አምኖ በማሕበሩ ታቅፎ እየሰራ ይገኛል፡፡ የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን አጠናቆ በማታው መርሃ ግብር በአዳዳሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በሂሳብ አያያዝ ትምህርት የአንደኛ ዓመት ተማሪ ነው፡፡ በትምህርቱ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ለመድረስም በሸንኮራ አገዳ ማሳው ለሚያፈሰው ጉልበት የሚከፈለው ደምወዝ ብቻ የትምህርት ወጪውን በመሸፈን ኑሮውን በተሻለ ሁኔታ ለመምራት እንዳስቻለውም ይናገራል፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ማሳ በስፋት በለማበት ዱብቲ ወረዳ ብቻ አርብቶ አደሩን በመንደር ከማሰባሰብ ጋር በተያያዘ ለተገነቡ በርካታ የማኅበራዊ ተቋማት እና የመሰረተ ልማት አውታሮች መንግሥት ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡

አርባኢ አሊ -የከሰም ስኳር ፋብሪካ የጥበቃ ሰራተኛ ሞሚና ሁመድ - በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ አገዳ አብቃይና አቅራቢነት ስራ ላይ የተሰማራች

Page 14: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

ቅፅ 3. ቁጥር 4 | ሰኔ 2007 | 14

በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ

Page 15: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

| 15

ጣ ፋ ጭ ዜ ና መ ፅ ሄ ት

በስኳር ኮርፖሬሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ 3 ወሩ የሚዘጋጅ

በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ

Page 16: ጣፋጭ ዜና መጽሄት ቁጥር 3 ቅፅ 4. ቁጥር 2 ሰኔ 2007

:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A [email protected] || www.facebook.com/etsugar

የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተመረቀበት ወቅት