Top Banner
የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት ዋና አዘጋጅ አቶ ብርሀኑ ስርጃቦ አዘጋጆች ብሩክ ዋጋዬ ወንደሰን አሊ ብሩክ ጥላሁን ሰላማዊት ራያ ገነት ደምሴ Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow አድራሻ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት Tel: +251-11-4-39-17 00 +251-11-4-39–16 82 +251-11-4-39-66 4 +251-11-4-39-22 59 Fax:+251-11-4-39-22 59 P.O.Box: 24692 code 1000 A/A E-mail: [email protected] Web www.lidi.gov.et Facebook FDRE:-Leather industry development inis- titute
14

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

Nov 05, 2020

Download

Documents

dariahiddleston
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

ዋና አዘጋጅ

አቶ ብርሀኑ ስርጃቦ

አዘጋጆች

ብሩክ ዋጋዬ

ወንደሰን አሊ

ብሩክ ጥላሁን

ሰላማዊት ራያ

ገነት ደምሴ

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow

አድራሻ

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት

ኢንስቲትዩት

Tel: +251-11-4-39-17 00

+251-11-4-39–16 82

+251-11-4-39-66 4

+251-11-4-39-22 59

Fax:+251-11-4-39-22 59

P.O.Box: 24692 code 1000

A/A

E-mail: [email protected]

Web www.lidi.gov.et

Facebook FDRE:-Leather

industry development inis-

titute

Page 2: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 11

‹‹መጪው ዘመናችንን በዛሬዎቹ ህጻናት እንመልከት››

ህዳር 18 ቀን 2012 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችና አመራሮች በአለም አቀፍ ለ 30ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ለ 14ኛ ጊዜ

የሚከበረውን የህጻናት ቀን መጪው ዘመናችንን በዛሬዎቹ ህጻናት

እንመልከት በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡

አለም አቀፍ የህጻናት ቀን በህጻናት ላይ የሚደርሱ ማህበራዊ

፣ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል እና አቅጣጫ ለመስጠት

ያግዝ ዘንድ በአለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡ ይህንንም ቀን ታሳቢ

በማድረግ የኢንስቲትዩቱ ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ

ዳይሬክቶሬት 14ኛው አለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/የነጭ ሪባን /

ቀን ሴቶችንና ህጻናትን ከጥቃት በመጠበቅ ሁላችንም ሀላፊነታችንን

እንወጣ በሚል ተከብሯል፡፡

በእለቱም ከህጻናት አድን/save the children/ ድርጅት በመጣ ባለሙያ የህጻናት ፖሊሲ አላማና ራዕይ የኢትዮጵያ ህጻናት

መብቶቻቸው ተከብሮና ደህንነታቸው ተጠብቆ ማየት እንዲሁም ህጻናት የተሟላ ስብዕና ተላብሰው እንዲያድጉ፣መብታቸው እንዲከበርና

ደህንነታቸው እንዲረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር መልካም ስነ-ምግባር የተላበሰ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ማፍራት ፣ስለ ብሄራዊ

የህጻናት ፖሊሲ አስፈላጊነት፣የፖሊሲ መርሆች እና የፖሊሲው ማስፈጸሚያ ስልቶች በሚል የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው ሽፈራው እንደዚህ አይነት መድረክ መዘጋጀቱ አስፈላጊና መሰረታዊ መሆኑን በመግለጽ የህጻናት

ጉዳይ የቤተሰብ ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን የማህበረሰብ፣የመንግስት፣የበጎ አድራጎት ተቋማት ሃላፊነት በአጠቃላይ የሀገር ሀላፊነት በመሆኑ

በቀጣይ ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶት ስልጠና መሰጠት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

Page 3: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 12

የፈረንሳይ ልኡካን ቡድን በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንሲቲትዩት ጉብኝት አደረገ

የፈረንሳይ ልኡካን ቡድን ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንሲቲትዩት ጉብኝት አደረገ የኢንስቲትዩቱ የጫማና

የቆዳ ውጤቶች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይለኪሮስ ደበሳይ ስለ ኢትዮጵያ የቀንድ ከብት፣ስለ ውጭ ንግድ አፈጻጸም፣ስለ

ኢንስቲትዩቱ ፋሲሊቲዎች እና የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚገኝበት አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

አቶ ሀይለ ኪሮስ በገለጻቸው ኢትዮጵያ 123 ሚሊየን የቀንድ ከብት እንዳላትና በአለም 6ተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ እንዲሁም

የኢትዮጵያ የበግ ቆዳ ከሌሎች አገራት በተለየ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ለጓንት፣ለጫማ፣አፐር፣ለአልባሳትና እቃዎች ተስማሚና ምቹ እንደሆነ

በዚህም ከጃፓን የጥራት ደረጃ መለያ(ብራንድ) ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የልኡካን ቡድኑ ባቀረቡት ሰነድ የፈረንሳይ የቆዳ ማህበር የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ከ 90% በላይ

አንደሚሸፍን እንዲሁም በቆዳው ዘርፍ የሚሰሩ 40 ኩባንያዎች እንዳሉት ተገልጿል፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ልኡካኑ በኢትዮጵያ በቆዳ

ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩም ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት የታደለች ሀገር ከመሆኗ በሻገር ለኢንቨስትመንት ምቹ ከሚያደርጓት ነገሮች

መካከል በመንግስት የሚሰጡ ማበረታቻዎች፣ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል መኖር፣ለሀይል አቅርቦት የሚከፈል ክፍያ ከሌሎች ሀገራት

አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ፣የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መስፋፋት፣የጫማ እና የቆዳ ፋብሪካዎች የግል መሆናቸው በአሜሪካና በአውሮፓ

አገሮች ያለ ቀረጥ ምርቶችን የመሸጥ እድል መኖሩ በዋነኛነት እንደሚጠቀሱና ከቻይና፣ከህንድ፣ከጃፓን እና ከሌሎች ሀገራት ጋር ያለው

ትስስር አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለቆዳ ዘርፍ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው በቆዳው ዘርፍ በጋራ ለመስራት

ቃል ገብተዋል፡፡ በመጨረሻም ልዑካን ቡድኑ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የተለያዩ ፋሲሊቲዎችና አገልግሎቶት መስጫ

ክፍሎችን ጎብኝተዋል፡፡

Page 4: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 13

ሰባት አባላት የሚገኙበትና በዶክተር ሉጋኖ ዊልሰን የሚመራ ከተለያዩ ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች የተውጣጡ

ልዩ ልዩ ባለሙያዎች የሚገኙበት የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ኢኒስቲትዩትን ጎብኝቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት

የተቀበሉት የኢኒስቲትዩቱ የቆዳ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሃላፊ

ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ሁሴን ናቸው፡፡

የልዑካን ቡድኑ ህዳር 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00

ሠዓት ጀምሮ በኢኒስቲትዩቱ ማኔጂመንት መሰብሰብያ

አዳራሽ ውስጥ በመገኘት ስለኢኒስቲትዩቱ አመሰራረት፣

ዓላማና አሁን የሚገኝበት ደረጃና ሥለአጋጠሙት

ተግዳሮቶችና የመፍትሄ እርምጃዎች ገለጻ ተደርጎለታል፡፡

ገለጻውን ያደረጉት አቶ ዴኔቦ መኩርያ የኢኒስቲትዩቱ

የትምህርት ሥልጠናና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክተር ሲሆኑ የጥሬ ቆዳ መንከርያና ማለስለሻ፣ የቆዳ አልባሳት፣ እቃዎች ማምረቻና ማስተማሪያ ሞዴል

ፋብሪካዎችን፣ የአካባቢ ጥበቃ ሞዴል ግንባታን፣ የፊዚካል፣ ኬሚካልና የምርምር ላብራቶሪና የዲዛይን

ማውጫ ክፍሎችን ጎብኝቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት ሥለነበራቸው ቆይታ

ምስጋና በማቅረብ የተደረገላቸው ገለጻ

ትምህርታዊና ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ

ተሞክሮዎችን በሚሰሩባቸው የምርምር

ተቋማት ውስጥ እንደሚጠቀሙባቸውና

አንዳንድ ተጨማሪ ተሞክሮዎችን ለመተግበር

በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ቆዳ

ኢንዱስትሪ ኢኒስቲትዩት ጋር በትብብር

እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የታንዛኒያ ልዑካን ቡድን ኢኒስቲትዩቱን ጎበኙ

Page 5: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 14

ከቆዳ ፋብሪካዎች የሚለቀቅ ደረቅ ቆሻሻን ጥቅም

ላይ ለማዋል የተለያዩ የምርምር ስራዎች እየተሰሩ

እንደሚገኝ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22 ፣ 2012 (ኢ.ሊ.ዲ ኮ.ጉ.ዳ) የቆዳ

ፋብሪካዎች በምርት ማምረት ሂደት ወቅት ወደ ዎንዞች

የሚለቀቅ ፈሳሽ ቆሻሻን፣ ወደ አዬር የሚለቀቅ በካይ ጋዝን

እና ከፋብሪካዎች የሚወጣ ተረፈ ምርት ደረቅ ቆሻሻን

ያመነጫሉ፡፡ ከፋብሪካዎች የሚለቀቁት ዉጋጆች

(ቆሻሻዎች) በሀገራችን አካባቢን በመበከል እና

የፋብሪካዉን ስራ በማስተጓጎል አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደሩ

ይገኛል፡፡ ብዙ ጥናቶችም እንደ ሚያመለክቱትም ከተነከረ

1000 ኪ.ግ (1 ቶን) ጥሬ ቆዳና ሌጦ ባለቀለት ደረጃ

ጥቅም ላይ የሚዉለዉ 270 ኪ.ግ ብቻ ነዉ፡፡ ስለሆነም

730 ኪ.ግ በቆሻሻ መልክ የሚወገድ መሆኑን ያሳያሉ፡፡

ይህም ደግሞ የቆዳ ፋብሪካዎች በምርት ሂደት ዉስጥ

በርካታ ተረፈ ምርት እንዲያወጡ ያደርጋቸዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ ቆዳ ፋብሪካዎች የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ

አካባቢ (ወንዞች) ሲለቁ የአካባቢ ደንና አየር ንብረት

ለዉጥ ኮሚሽን ባወጣዉ የልቀት ደረጃ መስፈርት

መሰረት መሆን እንዳለበት ያስገድዳል፡፡ ስለሆነም

አብዝሀኞቹ የቆዳ ፋብሪካዎቹ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ፋሳሽ

ማጣሪያ በመገንባት ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ የደረቅ ቆሻሻን

በተመለከተ ደግሞ በማዘጋጃ ቤት ቆሻሻ መጣያ

እያጓጓዙ ሲጥሉ ቆይተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ርጥብ ቆሻሻን (ፍለሽንግ

ዌስት) እንደማይቀበል ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰረት

ፋብሪካዎቹ እርጥብ ቆሻሻ መጣያ ቦታ አጥተዉ

እየተቸገሩ ይገኛሉ፡፡

ሆኖም ግን ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ (ኤሊኮ) ካጋጠመዉ

ችግር ተነስቶ ከአዋሽ ቆዳ ፋብሪካና ከአቢሲኒያ ቆዳ

ፋብሪካ የሚወጣዉን የደረቅ ቆሻሻ ወደ ጠቃሚ ነገር

ለመቀየር የምርምር ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በኢንዱስትሪዉ የዲዛይን፣ የምርምርና ስርፀት፣ የጥራት

ማረጋገጫና የአካባቢ ጥበቃ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ጌቱ ከቆዳ

ፋብሪካዎቹ የሚለቀቀዉ የፍሳሽ ቆሻሻ በአሁኑ ጊዜ ላይ

በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም በአካባቢዉ

በሚገኙ ማህበረሰብ በኩል አካባቢን ከመጠበቅና

የተጣራ የፍሳሽ ቆሻሻዎችን ወንዞች በመልቀቁ ጥሩ

ተቀባይነት እያገኙ መሆናቸዉን ይናገራሉ፡፡ የደረቅ ቆሻሻን

በተመለከተ ግን ፋብሪካዎቹ ላይ እንዲሁም አካባቢ ላይ

ተፅእኖ እያደረገ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

አቶ ሰለሞን ጌቱ ከፋብሪካዉ ስለሚወጡ ደረቅ ቆሻሻ

በተመለከተ ከጥሬ ቆዳ ጀምሮ እስካለቀለት ቆዳ ድረስ

መኖሩን ይናገራሉ፡፡ የጠጣር ቆሻሻ መፈጠር የሚጀምረዉ

ጥሬ ቆዳ ከመከርከም እና ቆዳዉን ሳይበላሽ ለማቆየት

ከምንጠቀመዉ ጨዉ ነዉ፡፡ ቀጥሎም የጥሬ ቆዳዉ ፀጉር

ከሚነሳበት ክፍል እና ከሚላጭበት ክፍል ብዙ ርጥብ

ቆሻሻ ከመዉጣቱም በላይ ለማጓጓዝም ምቹ አይደለም፡፡

ከዛም ቀጥሎ ባለዉ ሂደት ዉስጥ ከላይም ስፕሊቲንግ፣

ከፍሌሽንግና ከፔልት ትሪሚንግ የሚወጣዉ ደረቅ ቆሻሻ

በርካታ ነዉ፡፡ ቀጥሎም ከክሮም ሼቪንግ፣ ክሮም

ስፕሊቲንግ፣ ባፊንግ ደስት፣ ድራይ ሼቪንግ ደስት

እንዲሁም በምርት ሂደት በሚፈጠሩ ችግሮች ከክረስት

ቆዳና ካለቀለት ቆዳ የሚወገዱ ደረቅ ቆሻሻ መኖራቸዉን

ይናገራሉ፡፡

ከቆዳ ፋብሪካዎቹ የሚወጣዉን ደረቅ ቆሻሻ ወደ ጥቅም

ለመቀየር ስላነሳሱዋቸዉ ምክንያቶች አቶ ሰለሞን ሲያነሱ

የአለም አቀፍ ገበያ አካባቢ ጥበቃን መሰረት ባደረገ መልኩ

የተመረተ ምርትን ተመራጭ በማድረጉና ኢንዱስትሪዉ

ከተቋቋመበት አላማ አንፃር አካባቢን በማይበክል መልኩ

ስራዎችን መስራት የስለሚገባ በመሆኑን (Conversation

of Tanneries Solid West to Commercialized Prod-

uct) የሚል ፕሮጀችት በመቅረፅ ከአራት ወራት በፊት

Page 6: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 15 Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow

ኢንዱስትሪዉ በምርምር ስራዉ ካካተታቸዉ ስራዎች መካከል ከፍለሽንግ ዌስት ኦርጋኒክ ፈርቲላይዘር ኮምፖስት

(ማዳበሪያ) ማዘጋጀት፣ ከባፊንግ ደስትን ከድራይ ሼቪንግ ደስትንና ከክሮም ሼቪንግ ሌዘር ቦርድ ማዘጋጀት፣ ዉሀን

ከእንደገና መጠቀም ማስቻል፣ ክሮም ፓዉደር ከእንደገና ለመጠቀም የሚያስችል እንዲሆንና ፕሮቲን ፊለሩን ለፋብሪካዉ

ግብአት እንዲሆን እየተሰራ ነዉ፣ ከፔልት ትሪሚንግ ማጣበቂያ (glue) ማዘጋጀት፣ ከክሮም ሼቪንግ ደግሞ ፈሳሽ ፕሮቲን

ክሮም ፕሮቲን ፊለር ማምረት፣ ከጸጉሩ ደግሞ ኬራቲን ወደሚባል ፈሳሽ በመቀየር ለመዋቢያ እንዲሆኑ ለማድረግና

ለተለያዩ የታኒንግ ኬሜካል እንዲሆን ማምረት፣ የፍሳሽ ቆሻሻዉ ከተጣራ በኋላ የሚቀረዉን ዝቃጭ (sludge) ለግንባታ

እንዲዉሉ ብሎኬትን ለመተካት የሚያስችል ጡብ (Brick) እነዲሆኑ ማዘጋጀትና በፋብሪካዉ ዉስጥ ከሚገኙ ቅጠላ

ቅጠሎች ከፋብሪካዉ የሚወጣዉን መጥፎ ጠረን ለማጥፋት እየተሰራ መሆኑን እንዲሁም ስራዎቹ ዉጤት እያሳዩ መሆኑን

አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

በኢንዱስትሪዉ የተጀመሩት የምርምር ስራዎችን ከግብ ለማድረስ ኢንዱስትሪዉ ከቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር

በመሆን ፕሮጀክቱን የጋራ በማድረግ ከሁለቱም ኢንዱስትሪዎች የተለያዩ ባለሙያዎችን ያቀፈ ቡድኖችን በማዋቀር ከላይ

እንደተገለፀዉ ከፍለሽንግ ዌስት ኦርጋኒክ ፈርቲላይዘር ኮምፖስት (ማዳበሪያ) ማዘጋጀት፣ ከባፊንግ ደስትን ከድራይ ሼቪንግ

ደስትንና ከክሮም ሼቪንግ ሌዘር ቦርድ ማዘጋጀት፣ ዉሀን ከንደገና መጠቀም ማስቻል፣ ጨዉንም ከእንደገና መጠቀም

ማስቻል፣ ከሌዘር ስፕሊት ኳስ ማዘጋጀት እንዲሁም ክሮም ፓዉደር ከእንደገና ለመጠቀም የሚያስችል እንዲሆንና ፕሮቲን

ፊለሩን ለፋብሪካዉ ግብአት እንዲሆን ለማስቻል በስድስት ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ

ተፈራርመዋል፡፡ የምርምር ስራዎቹን ስራ በጋራ መስራት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በስድስት ወር ዉስጥ እንደሚጠናቀቅና

ፕሮጀክቶቹ የአዋጭነት ጥናት እንደሚዘጋጅላቸዉም ተጠቁሞዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ሰለሞን ፕሮጀክቶቹ ዉጤት አምጥተዉ ተግባራዊ ሲደረጉ በማህበረሰቡ ዘንድ ቆዳ ፋብሪካዎች አካባቢን

በካይ ናቸዉ የሚለዉን አመለካከት ሊቀይር የሚችል መሆኑንና ለፋብሪካዎች ከፍተኛ የሆነ ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ ሊሆኑ

እንደሚችል እንዲሁም ለሀገሪቱ ደግሞ ተጨማሪ የስራ እድል መፍጠር የሚችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Page 7: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 16

የሞጆ ከተማ ከንቲባና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች

የኢንስቲትዩቱን አገልግሎትና የአነስተኛና መካከለኛ

ኢንዱስትሪዎችን ያላቸውን ተሞክሮ ጎበኙ፡፡

በሞጆ

ከተማ

ከንቲባ

የተከበሩ ወ/

ሮ መሠረት

አሰፋ እና

በምክትል

ከንቲባቸው

የተከበሩ አቶ

ተሾመ ጁፋር

የኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ፅ/ቤት ኃላፊ፣ የቴክኒክኒ ሙያ ፅ/

ቤት ሀላፊዎች፣ዲኖች እና የስልጠና ባለሙያዎች፤ የቆዳና ቆዳ

ውጤቶች ኢንተርፕራይዝ ተወካዮች፣ የቆዳና ቆዳ ወጤቶች

ኢንተርፕራይዝ ማህበር አባላት፣የቢሮ ሀላፊዎች እና የተለያዩ

ባለሙያዎችን ያካተተ ቡድን ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም በቆዳ

ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና በኢትዮ-ኢንተርናሽናል

ፉትዌር ክላስተር ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማ (ኢፍኮስ) የአንድ ቀን

የግንዛቤ ማስጨበጫ በመውሰድ እና እየተሰራ ያለውን

ተሞክሮ ለመቅሰም ጉብኝት አደረጉ፡፡

የጉብኝቱ አላማ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ወጣቶች አነስተኛና

መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች በሀገር ውስጥ

ያላቸውን ድርሻ እንዲያውቁና ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ፣

በገበያ፣በግብዓት ትስስር በማምረቻ ችግር ያለባቸውን

ኢንዱስትሪዎችን ለመለየት፣ ለአነስተኛና መካከለኛ

ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች የኢንስቲትዩቱን የድጋፍ ማዕቀፍ

ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ፣ ኢንስቲትዩቱ ያመረታቸውን

የቴክኖሎጂ ምርቶችና የምርምር ውጤቶችን የሚጠቀሙበትን

ሁኔታዎች ለማመቻቸት እና በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ

ኢንዱስትሪዎችና የህብረተሰብ ክፈሎች በዘርፉ ልማት ላይ

ሁሉም የራሱን ድርሻ በመወጣት ወደ ስራ መግባት እንዲችሉ

አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የተመቻቸ ፕሮግራም መሆኑን

የኢንስቲትዩቱ የገበያ ጥናት ዳይሬክተር አቶ አንቲገኝ ከበደ

ገልፀዋል፡፡

እንደ ኢፍኮስ ፋይናንስ ማናጀር አቶ አበበ ከፍያለው ገለፃ እስካሁን

በሀገራችን ብዙም ባልተለመደው የክላስተር አደረጃጀት ስርዓት

በጫማው ኢንዱስትሪ እሴት ሰንሰለት ከዲዛይን እስከ ችርቻሮ

ሽያጭ ድረስ ያሉትን ተግባራት በአንድ ክላስተር ላይ በማደራጀት

የተቀናጀ የዕሴት ሰንሰለት በስራ ላይ በማዋል ሁሉም ሰራተኞች

የየራሳቸውን ስራ ስፔሻላይዝድ በማድረግ እንዲሰሩ በሚያስችል

መልኩ የተደራጀ ክላስተር ነው፡፡

በመቀጠልም በኢንስቲትዩቱ የሚገኙ የተለያዩ ፋሲሊቲዎችን

ከጎበኙ በኋላ በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ በተደረገ ውይይት ስልጠናን

በተመለከተ፣ የስራ ማስጀመሪያ ካፒታልና የስራ ቦታን እና

የመሳሰሉ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰቷቸዋል፡፡

የሞጆ ከንቲባ የተከበሩ ወ/ሮ መሰረት አሰፋ ጣልያን ሳንታ ክሮች

በሚባል ከተማ ወደ 400 የሚጠጉ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ያሉባት

የሞጆ አይነት ከተማ መሆኗን በማስታወስ በከተማዋ

የሚመረቱትን ቆዳ ውጤቶች ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች

በርካታ በመሆናቸው ከተማዋ ተጠቃሚ መሆነኗን ተናግረዋል፡፡

ክብር ከንቲባዋ ከተማዋ በቆዳ የምትሸትና የምትጠላ ሳትሆን

ኢኮኖሚዋን በሚያሳድግ እንደ እነ ጉቺ አይነት አለማቀፍ

ተቀባይነት ያላቸውን ብራንዶች በመፍጠር ነው፡፡ እዚ ደረጃ

የደረሱትም ከእኛ ሀገር የተሻለ የቆዳ ሀብት ኖሮአቸው ሳይሆን

የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ስለቻሉ መሆኑን የተናገሩት ክቡር

ከንቲባዋ፤ የሞጆ ከተማ መስተዳድር በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና

ጥቃቅንና አነስተኛ አደረጃጀቶች በቆዳው ዘርፍ ትኩረት

እንዲያደርጉ በማድረግ ቢሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል

ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል የሞጆ ከተማ ምክትል ከንቲባ የሆኑት የተከበሩ አቶ

ተሾመ ጁፋር በበኩላቸው በውይይትና በጉብኝት የቀሰሙትን

ልምድ በመጠቀም በአካባቢያቸው ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የቆዳ

ተረፈ ምርቶችና ያለቀለት ቆዳ በመውሰድ ወደ ምርት በመቀየር

ምርቶቹን እንዲያመርቱና በቆዳው ዘርፍ ላይ ሰፊ ግንዛቤ

በመፍጠር የከተማ አስተዳደሩ እና ህብረተሰቡ በሞጆ ከተማ

ውስጥ ካሉ ኢንዱስትሪዎች ጋራ የተሻለ የስራ እና ዘላቂ የልማት

ግንኙነት ለመፍጠር የሚያሰስችል ልምድ እንዳገኙ ገልፀዋል ::

የኢንስቲትዩቱ ጫማና ቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አቶ ኃይለኪሮስ ደበሳይ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ እና

የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት በትንሽ ኢንቨስትመንት እና

በቀላል ግብአት ውጤታማ መሆን የሚቻልበት ዘርፍ መሆኑን

አለም አቀፍ ተሞክሮን በማጣቀስ አብራርተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም ገበያን መሰረት ያደረገ ክላስተር ለመመስረት

በኢንስቲትዩቱ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ አስፈላጊውን

ግብአት አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ኢንፍራስትራክቸር

መስራት መጀመር እንደሚጠበቅ ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ

ለማድረግ የኢንስቲትዩቱን ዝግጁነት ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው በሞጆ

ከተማ ያለውን የTVET ኮሌጆችን ማጠናከር፣ በቆዳው ዘርፍ

የሚሰሩ አነስተኛና ጥቃቅንም ሆነ የህብረት ስራ ማህበራትን

ለማቋቋም እንዲቻል የሚመለከታቸው የኢንስቲትዩቱ የስራ

ክፍሎች ሞጆ በመሄድ ምን እየተሰራ እንደሆነ፣ እንዴት እየተሰሩ

እንደሆነ፣ ምን የተሟላ ነገር እንዳላቸው፣ ምን እንደሚጎላቸውና

እንዴት መደገፍ እንደሚቻል በማጥናት ወደ ስራ እንዲገባ የስራ

መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

Page 8: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 7

ለሃገሬ የጠፈር ምርምር

የድርሻዬን እየተወጣሁ ነው…

ይህን ያለችው በሃገረ አሜሪካ

በታዋቂው የጠፈር ምርምር

ተቋም ናሳ በጽዳት ሥራ

ተቀጥራ በማገልገል ላይ

የምትገኝ አንዲት ሴት

ከጋዜጠኞች ለቀረበላት ጥያቄ

የመለሰችው መልስ መሆኑን

የነገረን ለቃለ ምልልስ

ወደቢሮው ሥናመራ

ያገኘነው ወጣት ነው ፡፡

በዛሬው ርዕሰ ጉዳያችን

በህንድ አገር ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የብር ሜዳልያ

አግኝተው ከተመለሱት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ

ከሆነው ወጣት ታረቀኝ በቀለ ጋር ያደረግነውን ቆይታ

ልናወጋችሁ አንድ ብለናል፡፡

በኢኒስቲትዩቱ የቆዳ አልባሳትና እቃዎች ዳይሬክቶሬት ውስጥ

በተመራማሪነት ለአምስት ዓመት አገልግያለሁ ከዚህ ውስጥ

ሁለቱን ዓመት በ /CREATIVE DESIGN & CAD COM/

የሙያ መስክ የሁለተኛ ዲግሪየን ከትምህርት ክፍሉ ከፍተኛ

ነጥብ በማምጣት ከላይ የተጠቀሰውን ሽልማት መቀበል

ችያለሁ በማለት ገልጾልናል፡፡

የመጀመርያ ዲግሪውን በኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ

ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተቀበለው ወጣት ታረቀኝ በቡድን ሥራ

ውጤታማና ጠንካራ፣ የሚሰማውን ማንኛውንም ጉዳይ ፊት

ለፊት ከመናገር ወደኋላ የማይል፣ ተግባቢና ሰው አክባሪ

መሆኑን በቃለ ምልልሱ ወቅት ከሚያቀርባቸው ጠንካራ

ሃሳቦችና ሌሎች የስራ ባልደረቦቹ ስለርሱ ከሚናገሩት መረዳት

ችለናል፡፡

ወጣቱ ትዳር ያልመሰረተ ቢሆንም የወደፊት የትዳር ህይወቱን

የምታደምቅለት ጓደኛ እንዳለችውና በሥራ ህይወቱም

ድክመቴ ነው የሚለው ጉዳይም ሥራን ከሃላፊው

እስኪሰጠው መጠበቁ እንደሆነም አልሸሸገም፡፡

ከኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ኢኒስቲትዩት ለትምህርት ወደ

ህንድ አገር ከተላኩት ሰምንት ተማሪዎች አንዱ እንደነበርና

በርሱ የትምህርት ዘርፍ የተመደቡት ደግሞ ሦስት እንደነበሩ

የሚያወሳው ወጣት ታረቀኝ ለተቋሙ ሁሉም የስራ ዘርፎች

ቀጣይነት ያለው የትምህርት ሥልጠና እንደሚያስፈልግ፣

በስልጠና ወቅት ቤተሰቡን የሚያስተዳድር አንድ ሰው

ትምህርቱን አጠናቆ እስኪመለስ የሚሰጠው ወርሃዊ የምግብ

ወጪና የደሞዙ ግማሽ ብቻ በቂ አለመሆኑን አብራርቷል፡፡

ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመለሱ ሠራተኞች በተለይም

በከፍተኛ ውጤት የሚመረቁ ሠልጣኞች መላ አቅማቸውን

ተጠቅመው ኢኒስቲቲዩቱን በብቃት እንዲያገለግሉና ለውጥ

እንዲያመጡ ለማድረግ ለተመራቂዎች እውቅና መስጠትና

ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ ታረቀኝ ያምናል፡፡

የናሳ የጠፈር ምርምር ማዕከል የጽዳት ሠራተኛ ለተቋሙ ምን

ያህል እንደምታስብ የሚታወቀው በምታደርገው አስተዋጽኦ

ይለካል፣ የተቋሙ ለሰራተኞች ምቹ መሆን የሥራ ባህሪን

ይለውጣል፣ የእያንዳንዱ ሰው አስተዋጽኦም ለእድገቱና

ለተቋሙ መለወጥ ምክንያት ይሆናል ሲል ያለውን ሃሳብ

አካፍሎናል፡፡

Page 9: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 8

በቆዳዉ ዘርፍ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ካሳዩ የህንድ

ሀገር ባላሀብቶች ጋር ዉይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2012 (ኢ.ሊ.ዲ ኮ.ጉ.ዳ) የቆዳ

ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከህንድ ሀገር ከመጡ በቆዳዉ

ዘርፍ በተለይ በበሬ ቆዳ ማልፋትና ማለስለስ ስራ ላይ ወደ

ኢንቨስትመንት ለመግባት ፍላጎት ካሳዩ ባለሀብቶች ጋር ሀገሪቱ

በዘርፉ ስላሉዋት ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ እንዲሁም ችግሮች ላይ

ዉይይት አድርጎዋል፡፡

በወቅቱ በሀገሪቱ ስላለዉ የቆዳ ዘርፍ ነባራዊ ሁኔታ

በኢንስቲትዩቱ የጫማና የቆዳ ዉጤቶች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይለኪሮስ ደበሳይ ገለፃ አድርገዋል፡፡ በገለፃቸዉም

ሀገሪቱ ስላላት የቀንድ ከብት ሀብት፣ የቆዳዉ ጥራት ደረጃ፣ የኤክስፖርት አፈፃፀም ደረጃ፣ እንዲሁም በዘርፉ ለሚሰማሩ

ኢንቨስተሮች ሀገሪቱ ስላላት ምቹ ሁኔታዎች ተናግረዋል፡፡

በዉይይቱም ከባለሀብቱ በተለዬ ከበሬ ቆዳ ጥራት ጋር በተያያዘ ያለዉ ችግር እንዲሁም የአለቀለት ቆዳ ኤክስፖርት መቀነስ

ዙሪያ እና አጠቃላይ ስለ ዘርፉ ሁኔታ ጥያቄ አንስተዋል፡፡ በምላሹም የቆዳ ጥራት ጉዳይ በተሻለ ቴክኖሎጅ ማሻሻል የሚቻል

መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኤክስፖርት አፈፃፀም መቀነሱ ከአለም አቀፍ የቆዳ ፍላጎት ማነስ የገበያዉ አለመረጋጋት ምክንያት

እንደሆነ ተነስቶዋል፡፡በመጨረሻም ባለሀብቶቹ በኢንስቲትዩቱ የሚገኘዉን ለዘርፍ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ፍሲሊቲዎችን

ጎብኝተዋል፡፡

Page 10: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 9

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በንግድና

ኢንዱስትሪ ዘርፍ የአስር አመት መሪ እቅድ ዙሪያ ውይይት

አካሄደ

ህዳር 2 ቀን 2012 ዓ.ም የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ

የአስር አመት መሪ እቅድን መነሻ በማድረግ ተቋማዊ እቅድ

ለማዘጋጀት የተቋቋመው ኮሚቴ ባካሄደው ውይይት የእቅዱ

መነሻዎች፣የትኩረት አቅጣጫዎች፣የትኩረት

መስኮች፣አላማዎችና ጥቅል ግቦች እንዲሁም ማስፈጸሚያ

ስትራቴጂዎች ተካተዋል፡፡

ሀገራዊና የዘርፉ ራእይ የእቅዱ መነሻ እንደሆነና በ2022

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግና በአለም

አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የንግድና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ

ዘርፍ መፍጠር መሆኑን በቀረበው ሰነድ

ተገልጿል፡፡በተጨማሪም ፖሊሲና ስትራቴጂዎች፣አለም አቀፍና

አህጉራዊ ስምምነቶች ፣ካለፉት አመታት አፈጻጸሞች የተለዩ

ክፍተቶችና ተግዳሮቶች መኖራቸውም ተገልጿል፡፡

እቅዱ የትኩረት አቅጣጫውን የንግድ ፋሲሊቴሽንና ሬጉሌሽን

አቅም መገንባት፣ቀጣይነት ያለው የኤክስፖርት

እድገት፣የኢንዱስትሪ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት

ማሳደግ፣የማኑፋክቸሪንግ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት ላይ

ያደረገ ሲሆን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም፣የኤክስፖርትን

ገቢን መጨመር፣ቀልጣፋና ተደራሽ የንግድ አሰራር፣የኢንዱስትሪ

ኢንቨስትመንት ልማት፣የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ

ኢንዱስትሪዎች ልማት፣የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ

ምርታማነትና ተወዳደሪነት የትኩረት መስኩ መዳረሻዎች

ናቸው፡፡

ኮሚቴውን በዋናነት የሚመራው የኢንስቲትዩቱ የእቅድ ዝግጅት

ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ሲሆን የእቅዱም ግቦች

ኢትዮጵያ በንግድ ስራ አመቺነት አሁን ካለችበት 159ኛ ደረጃ በ

2022 ዓ.ም ከ70-80 ካሉ አገሮች ተርታ ማሰለፍ ፣

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አሁን ካለው 6.8 በመቶ የኢኮኖሚ

ድርሻ በ 2022 17 በመቶ ማሳደግ፣የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ

ከ 2008-2012 ዓ.ም ከነበረበት አማካይ 16.6 በመቶ እድገት ከ

2013-2022 ወደ 20.6 በመቶ ማሳደግ፣አሁን ያለው 50%

አማካይ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም በእቅድ ዘመኑ

መጨረሻ ላይ 85% ማድረስ፣የአለም የንግድ ድርጅት አባል

መሆንና ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ሙሉ ተጠቃሚ መሆን እና

በ 2022 በአገር አቀፍ ደረጃ የ 25 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር

የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማድረስ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የተቋማት ቁርኝት ትግበራ

ፕሮጀክት፣የምርታማነትና ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም፣የአዳዲስ

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ልማት፣የንግድ ስራ ለመጀመር ያለ

ምቹነት ሪፎርም ስራዎች ማጠናከር፣የኢንዱስትሪ ልማት

ፖሊሲና ስትራቴጂን መከለስና የንግድ ፖሊሲ

ማዘጋጀት፣አስተማማኝና ዘመናዊ የንግድና ኢንዱስትሪ መረጃ

ስርአት ማደራጀት እና ዘመናዊ የምርት ግብይት ስርአት

ማጎልበት እቅዱን ለማስፈጸም የተዘጋጁ ስተራቴጂዎች ናቸው፡፡

ኮሚቴው የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ እቅድ ወደ ቆዳው ዘርፍ

ለማውረድ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን (GTP2) ፖሊሲዎችና

ስትራቴጅዎችን እንደገመገመ እና እቅዱንም ለማዘጋጀት

የድርጊት መርሀ-ግብር(Action plan)እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡

የበላይ አመራሩም እቅዱ ሰፊ ጊዜ ከመውሰዱ አንጻር ኮሚቴው

ትኩረት ሰጥቶ መስራት እነደሚገባው እንዲሁም ምርትና

ምርታማነትን ከማስፋፋት ባሻገር የኢንዱስትሪውን መሰረት

ማስፋት እና ቴክኖሎጂ ላይ የትኩረት አቅጣጫውን ማድረግ

እንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል::

Page 11: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 10

እርሱ በፈቀደው ይሆናል ‘By the will of God' እንደማለት…

ሀሳቡን በየትኛውም ሥፍራ ከመግለጽ ወደኋላ ብሎ

አያውቅም ፤ ወጣትነቱም ተጨምሮ ከማንኛውም ሰው ጋር

መግባባት የሚችል፣ ደስተኛና ፍልቅልቅ ነው፡፡ በጠይም ፊቱ

ላይ ብርሀናዊ አስተሳሰቡ ሲታከልበት ሌሎችን የማበርታት

ሃይል አለው፡፡

እስከአሁን በነበረው የዕድሜ ዘመኑ ጊዜውን ሁሉ በመማር፣

በማንበብና መንፈሳዊ ህይወቱን በማጠንከር ላይ እንዳተኮረ

ይናገራል፡፡

በቅርብ ጊዚ የጀመረው የትዳር ህይወቱም አዲስ ብስራት

ይዞለት በመምጣት ላይ በመሆኑ ደስታውን እጥፍ

እንደሚያደርገው ይገምታል፡፡

ወጣት እርሱባለው መለሰ ይባላል በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ

ልማት ኢኒስቲትዩት በቆዳ አልባሳትና እቃዎች ዳይሬክቶሬት

በምርምርና ምርት ልማት ቡድን መሪ ሆኖ በማገልገል ላይ

ይገኛል፡፡

በኢኒስቲትዩቱ ውስጥ ከነበረው ስድስት ዓመት የቆይታ ጊዜ

ሁለቱን ዓመት በህንድ አገር ኖይዳ በምትባል ከተማ

በትምህርት አሳልፏል፡፡

ሠብዕናው ለበርካቶች ምሳሌ ይሆናል ተብሎ ሥለታመነበት

እርሱባለው ማን ነው? ብለን ጠየቅን እርሱም ታሪኩን

አልሸሸገንም፡፡

ግጥሞችን መጻፍና ማንበብ እወዳለሁ፣በተለይ ደግሞ በዕድሜ

ዘመኔ መማርን የመሰለ ነገር ያለ አይመስለኝም፤ ይህን

የማደርገው አንድም እራሴን የተሻለ ቦታ ለማድረስ ሌላም

ቤተሰቤን የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማድረግ ነው ይላል፡፡

በአዲስ አበባ ውስጥ ተወልዶ ያደገው እርሱ ባለው የመጀመርያ

ዲግሪውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ የትምህርት

ክፍል በኬሚካል ኢንጅነሪንግ የማዕረግ ተመራቂ እንደነበር

የሚያስታውሰው ወጣቱ በቅርብ ጊዜ ውስጥም የማኔጅመንት

ዲግሪውን እንደሚያጠናቅቅ አጫውቶኛል፡፡

ለዛሬው ዘገባ ምክንያት የሆነው ደግሞ በህንድ አገር በኖይዳ

የጫማና የዲዛይን ልማት ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪውን በ

‘Retail Fashion Merchandize' የትምህርት ዓይነት

ከዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛውን

ነጥብ በማምጣት ‘Over all Toper in MSC' የወርቅ

ሜዳልያና ከትምህርት ክፍሉ ደግሞ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ

በመሆን የብር ሜዳልያና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ በመሆን

ኢትዮጵያውያንን ጉሮ ወሸባ አሰኝቷል፡፡

ይህ ሁሉ የሆነው ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም እንደነበረ

የታወቀ ሲሆን በኢኒስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬትና

በተቋሙ ሥም እንኳን ደስ ያለህ እንላለን፡፡

የትምህርት ዘርፉ ለቆዳ ቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን በመላ ሃገሪቱ

የገበያ አቅምን ማሳደግና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን

ማቅረብ እንደሚቻል የሚያስገነዝብ በመሆኑ እስከአሁን

ያላስተዋወቅነውን የቆዳ ምርት ገበያ ሰንጥቆ ለመግባትና ለዓለም

ማስተዋወቅ የሚቻልበትን መንገድ ይመራናል ብዬ አስባለሁ

የሚለው እርሱ ባለው ወደፊት የቆዳ ዘርፉን ወጭ ለመቀነስ

የሚያስችል የምርምር ሥራ ውስጥ ለመግባት በዝግጅት ላይ

መሆኑን አብራርቷል፡፡

ኢኒስቲትዩቱ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ በቀደምት ዓመታት

በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ውጪ ተምረው በሚመጡ ተማሪዎች

ዘንድ ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም በሰው ሃብት አቅም ግንባታ

ዘርፍ የሚደረገው ጥረት ፍሬ እያፈራ መሆኑንና ሌሎች

ወጣቶችንም በዚህ መልኩ እያሰመረቀ መሆኑን ወደፊት

የምንዘግብ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

Page 12: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 11

የሀገሪቱ ቱባ ባህል በቆዳ ጥበብም ይገለፃል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2012 (ኢ.ሊ.ዲ ኮ.ጉ.ዳ) የቆዳ ኢንዱስትሪ

ልማት ኢንስቲትዩት በጫማና የቆዳ እቃዎችና አልባሳት የምርት

ማልማት ማዕከሉ የተለያዩ አዳዲስ ወቅቱ የሚፈልገዉንና የሀገሪቱን

ባህል የሚያንፀባርቁ ምርቶችን በማምረት ለኢንዱስትሪዉ

ያስተላልፋል፡፡ ኢንዱስትሪዎችም በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ አዳዲስ

ምርቶችን ሙሉ ንድፋቸዉን በመዉሰድ በስፋት እንዲያመርቱ

በማድረግ ለዘርፉ ድጋፉን ያበረክታል፡፡

በ2012 ዓ.ም በሚካሄደዉ የመላ አፍሪካ የቆዳ ዘርፍና የፋሽን አዉደ

ርዕይ ላይ አዳዲስ ምርቶችን የሀገራችንን ባህል የሚያንፀባርቁ ወይም

የሚገልፁ ይዞ ቀርቦዋል፡፡ ይህም የሀገራችንን ባህል ለመላዉ አለም

ከማስተዋወቁ በተጨማሪ ለኢንዱስትሪዉ የሀገሪቱን መልክ የያዘ ምርት

ለገበያ በማቅረብ በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

ዘንድሮ በተካሄደዉ የመላ አፍሪካ የቆዳ ዘርፍና የፋሽን አዉደ ርዕይ ላይ

ለዕይታ የሚቀርቡ ምርቶች የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ወደ ምስራቂቱ

ኢትዬጵያ (ሐረር) በመሔድ የአካባቢዉን ባህል የሚገልፅ የጀጎል ግንብን

ጨምሮ የአደሬን ባህል የሚገልፁ ሀሳቦችን በመውሰድ የተለያዩ በቆዳ የተሰሩ

ምርቶችን ለዕይታ አቅርበዋል፡፡

Page 13: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 12

የፀረ ሙስና ቀን እና የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኢንስቲትዩቱ ተከበረ

በሀገራችን ለ15ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የፀረ ሙስና ቀን

“መልካም ስነምግባርን በመገንባት ሙስናን

ለመታገል ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጥ” በሚል

መሪ ቃል እንዲሁም ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረዉ

የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን "ህገ መንግስታዊ

ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም" በሚል መሪ ቃል የቆዳ

ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩቱ አመራሮችና

ሰራተኞች የኢንስቲትዩቱን ቅጥር ግቢ በማፅዳትና

ዉይይት በማድረግ ህዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም

አክብረዋል፡፡

በወቅቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሁፍ ስለ ብሄሮች፣

ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አስመልክቶ የቀረበ ሲሆን

ስለ ሀገራችን ፌደራል ስርዓት ምን ይመስላል፣ የፌደራል ስርዓት የስገኛቸዉ ጥቅሞች እንዱሁም በስርዐቱ የታዩ

ክፍተቶች እንዲሁም ስለ ቀጣይ ምክረ ሀሳቦች በኢንስቲትዩቱ የቆዳ ቴክኖሎጅ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ

መሀመድ ሁሴን ገለጻ ተደርጓል፡፡ የፀረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሁፍ በኢንስቲትዩቱ የስነምግባር

መኮንን አቶ ደግሴ ጫኔ ገለፃ ተደርጓል፡፡ በገለፃዉም ስለ ሙስና ምንነት፣ የሙስና አይነቶችና ሙስና በሀገር ላይ

ስለሚያስከትላቸዉ ቀዉሶች ተብራርቷል፡፡

በቀረቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የጥያቄና መልስ ዉድድር በኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች መካከል የተካሄደ ሲሆን በዉድድሩ ከአንድ

እስከ ሶስት ለወጡት ሽልማት ተበርክቷል፡፡ በዉድድሩ አንደኛ የወጣዉ ወጣት መላኩ ሽልማቱን በሀምሊን ፌስቱላ ሆስፒታል

ለሚገኙ ህሙማን እናቶች ያበረከቱ ሲሆን ሽልማቱንም ለሰራተኛዉ መልሶ ለጨረታ በማቅረብ 1100 ብር ገቢ አስገኝቷል፡፡

ገንዘቡም በሆስፒታሉ ለሚገኙ በሥነ ልቦናና ሥነ ተዋልዶ ጤና ለተጎዱ እናቶች የሚበረከት መሆኑ ታዉቋል፡፡

Page 14: የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም ...lidi.gov.et/images/Publication2 - Copy.pdfየቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2012 ዓ.ም የህዳር ወር ዜና መጽሄት

Web www.lidi.gov.et LIDI Engineering Tomorrow 13

የኢኒስቲትዩቱ የሴቶች ፎረም ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የሴቶች ፎረም አባላት የ2012 የመጀመርያ ሩብ ዓመት ጠቅላላ ጉባዔ

ተካሄደ፡፡

በኢኒስቲትዩቱ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ጉባዔ ከግማሽ በላይ አባላት የተገኙ ሲሆን የውይይት መድረኩን በንግግር

የከፈቱት የኢኒስቲትዩቱ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሪት ለምለም ደቦጭ ሲሆኑ፣

የፎረሙን አስፈላጊነት፣ የስራ እንቅስቃሴና የበጀት ሪፖርቱን ያቀረቡት ደግሞ ወ/ሮ ሸዋ ይርገድ ዲበኩሉ የፎረሙ ሥራ

አስፈጻሚ ናቸው፡፡

በውይይቱ ወቅት ሁሉም አባላት ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ የፎረሙን የገቢ ምንጭ በማሳደግ፣ አዳዲስ አባላትን

በማሳተፍና የተጓደሉ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ማሟላት በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ሁለት ሠዓት የፈጀ ሰፊ ውይይት

የተደረገ ሲሆን የተለያዩ ውሳኔዎችም ተላልፈውበታል፡፡

እንደጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ተሳትፎ ያልነበራቸው ሴቶችና አዳዲስ የመጡ ሰራተኞች

የፎረሙን የመተዳደርያ ደንብ መሰረት በማድረግና ፍቅር በተሞላበት ሁኔታ ችግሮችን በሚፈታ መልኩ ግንዛቤ በማስጨበጥ

እንደገና እንዲካተቱ ማድረግ እንደሚገባ፣ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ አዲስ የሚመዘገቡ አባላትን ጨምሮ

እንዲከናወንና በርካታ የገቢ ማሳደጊያ ሃሳቦች በውይይቱ ላይ ከተነሱ ሃሳቦች ጥቂቶቹ ሲሆኑ ፎረሙም የኢኒስቲትዩቱን ሴት

ሠራተኞች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንደሚሰራ ታውቋል፡፡

በመጨረሻም ሌላ ጉባዔ በአጭር ጊዜ በማካሄድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን የማጠናከርና የቡና ጠጡ ፕሮግራምም ለመጀመር

የተወሰነ ሲሆን ሌሎች የገቢ ምንጮችንም ለመጀመር ዝግጅት እንደሚደረግ ወ/ሪት ለምለም ደቦጭና ወ/ሮ ሸዋ ይርገድ ዲበኩሉ

በየተራ ለጉባኤው አባላት አብራርተዋል