Top Banner
{ ባላፉት ትንሽ አመታት በኦንቴሪዮ እና ሌሎች ክፍለ ሃገራት እና ቴሪቶሪዎች ስለቱሃን የሚፃፈው ዘገባ በቁጥር ጨምሯል። ማንም ሰው በየትም ቦታ በቱሃን ሊጠቃ ይችላል። ቱሃኖች ትንንሽ የሚናከሱ ፣ በቀላሉ የሚራቡ እና ከቦታ ወደ ቦታ የሚተላለፉ ተባዮች ናቸው። ቱሃኖችን መከላከልም መቆጣ ጠርም ይቻላል። በፍጥነት እርምጃ መውሰድ ይህንን ተባይ በተሳካ ሁኔታ ለመቆጣጠር ይረዳል። መከላከል ቤቴ ውስጥ ቱሃን እንዳይገባ የምከላከለው እንዴት ነው ? ምንም እንኳን በጣም ንፁህ ቤቶች እና ሆቴሎች ቱሃን ሊኖራቸው ቢችልም ቀጣይ የሆነ ፍተሻ ፣ ፅዳት እና ፍራሽ ቫኪዩም ማድረግ ቱሃኖቹ ሳይ ሰራጩ በጊዜ እንዲገኙ በማድረግ ይጠቅማል። ትርምስ ቤታችሁ ውስጥ ካለ ማፅዳት ቱሃኖች ሊደበቁበት የሚችሉበትን ቦታ ይቀንሳል ፍተሻንም ያቀላል። ቱሃን ባይኖራችሁም ግድግዳ ውስጥ ያለ ቀዳዳን እና ስንጥቅን መድፈን ጥሩ ሃሳብ ነው። ይህም ቱሃንን እና ሌሎች ተባዮች ለመከላከል እና ቤታችሁ ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ ይረዳል። ከዚህ በፊት ሰው የተጠቀመበት እቃ ወይንም ልብስ ስትገዙ በጥንቃቄ መርምሩ። እናንተ ከመፈተሻችሁም በተጨማሪ ቱሃን እንዳይኖረው ተመር ምሮ እንደሆነ ጠይቁ። ተጥሎ ያገኛችሁት አልጋ፣ ፍራሽ፣ የአልጋ ቦክስ እስፕሪንግ፣ የቤት ቁሳቁስ ወይንም ኤሌክትሮኒክስ ቤታችሁ ውስጥ አታስ ገቡ። እነዚህ ነገሮች በቱሃን ተወረው ሊሆን ይችላል። ከጉዞ ስመለስ ይዤያቸው እንዳልመጣ ምን ማድረግ እችላለሁ? በምትጓዙበት ጊዜ ክፍላችሁን እና ቁሳቁሶቹን የደም ምልክት፣ የቱሃን ሰገራ ወይንም ቱሃኖች እንዳይኖሩ መርምሩ።የቱሃን ምልክት ካያችሁ ሌላ ክፍል እንዲሰጣችሁ ጠይቁ። ቤታችሁ ስትመለሱ ሻንጣችሁን በደንብ መርምሩ፣ ቢቻል ቤት ውስጥ ከመግባታችሁ ቢሆን ይመረጣል። በተጨማ ሪም ከመንገድ እንደተመለሳችሁ ልብሳችሁን በትኩስ ውኋ አጥባችሁ በማድረቂያ ውስጥ በከፍተኛ ሙቀት በትንሹ ለ30 ደቂቃዎች አድርቁ። ለይቶ ማወቅ ቱሃኖች ምንድናቸው? ቱሃኖች ሞላላ ሰውነት ያላቸው እና ክንፍ የሌላቸው ነፍሳት ናቸው። ቱሃኖች አብዛ ኛውን ጊዜ የሚናከሱት በሌሊት ነው። የሚናከሱትም ሰውነት ሙሉ በተለይም ፊት፣ አንገት፣ ከወገብ በላይ፣ ክንዶች እና እጆች ላይ ነው። በአሁኑ ጊዜ የሚታወቅ ቱሃኖች በሽታን ከሰው ወደ ሰው ያስተላለፉበት ጊዜ የለም። እንዴት ላገኛቸው እችላለሁ? ብሩህ የሆነ ባትሪ ተጠቅማችሁ ቱሃኖችን ወይንም ሰገራቸውን መኝታ ቤት ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶች፣ መስኮቶች እና የበር ጠርዞች ላይ ፈልጉ። ወይንም የፀጉር ማድረ ቂያ፣ ቀጭን ቢላ ወይንም አሮጌ መጫወቻ ካርታ ተጠቅማችሁ ከመደበቂያቸው ቦታ አስወጧቸው።
2

መከላከል - National Capital FreeNet

May 19, 2022

Download

Documents

dariahiddleston
Welcome message from author
This document is posted to help you gain knowledge. Please leave a comment to let me know what you think about it! Share it to your friends and learn new things together.
Transcript
Page 1: መከላከል - National Capital FreeNet

{ባላፉት ትንሽ አመታት በኦንቴሪዮ እና ሌሎች ክፍለ ሃገራት እና ቴሪቶሪዎች ስለቱሃን የሚፃፈው ዘገባ በቁጥር ጨምሯል። ማንም ሰው በየትም ቦታ በቱሃን ሊጠቃ ይችላል። ቱሃኖች ትንንሽ የሚናከሱ ፣ በቀላሉ የሚራቡ እና ከቦታ ወደ ቦታ የሚተላለፉ ተባዮች ናቸው። ቱሃኖችን መከላከልም መቆጣጠርም ይቻላል። በፍጥነት እርምጃ መውሰድ ይህንን ተባይ በተሳካ ሁኔታ ለመቆጣጠር ይረዳል።

መከላከል ቤቴ ውስጥ ቱሃን እንዳይገባ የምከላከለው እንዴት ነው ? ምንም እንኳን በጣም ንፁህ ቤቶች እና ሆቴሎች ቱሃን ሊኖራቸው ቢችልም ቀጣይ የሆነ ፍተሻ ፣ ፅዳት እና ፍራሽ ቫኪዩም ማድረግ ቱሃኖቹ ሳይሰራጩ በጊዜ እንዲገኙ በማድረግ ይጠቅማል። ትርምስ ቤታችሁ ውስጥ ካለ ማፅዳት ቱሃኖች ሊደበቁበት የሚችሉበትን ቦታ ይቀንሳል ፍተሻንም ያቀላል። ቱሃን ባይኖራችሁም ግድግዳ ውስጥ ያለ ቀዳዳን እና ስንጥቅን መድፈን ጥሩ ሃሳብ ነው። ይህም ቱሃንን እና ሌሎች ተባዮች ለመከላከል እና ቤታችሁ ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ ይረዳል።

ከዚህ በፊት ሰው የተጠቀመበት እቃ ወይንም ልብስ ስትገዙ በጥንቃቄ መርምሩ። እናንተ ከመፈተሻችሁም በተጨማሪ ቱሃን እንዳይኖረው ተመርምሮ እንደሆነ ጠይቁ። ተጥሎ ያገኛችሁት አልጋ፣ ፍራሽ፣ የአልጋ ቦክስ እስፕሪንግ፣ የቤት ቁሳቁስ ወይንም ኤሌክትሮኒክስ ቤታችሁ ውስጥ አታስገቡ። እነዚህ ነገሮች በቱሃን ተወረው ሊሆን ይችላል።

ከጉዞ ስመለስ ይዤያቸው እንዳልመጣ ምን ማድረግ እችላለሁ?በምትጓዙበት ጊዜ ክፍላችሁን እና ቁሳቁሶቹን የደም ምልክት፣ የቱሃን ሰገራ ወይንም ቱሃኖች እንዳይኖሩ መርምሩ።የቱሃን ምልክት ካያችሁ ሌላ ክፍል እንዲሰጣችሁ ጠይቁ። ቤታችሁ ስትመለሱ ሻንጣችሁን በደንብ መርምሩ፣ ቢቻል ቤት ውስጥ ከመግባታችሁ ቢሆን ይመረጣል። በተጨማሪም ከመንገድ እንደተመለሳችሁ ልብሳችሁን በትኩስ ውኋ አጥባችሁ በማድረቂያ ውስጥ በከፍተኛ ሙቀት በትንሹ ለ30 ደቂቃዎች አድርቁ።

ለይቶ ማወቅ ቱሃኖች ምንድናቸው? ቱሃኖች ሞላላ ሰውነት ያላቸው እና ክንፍ የሌላቸው ነፍሳት ናቸው። ቱሃኖች አብዛኛውን ጊዜ የሚናከሱት በሌሊት ነው። የሚናከሱትም ሰውነት ሙሉ በተለይም ፊት፣ አንገት፣ ከወገብ በላይ፣ ክንዶች እና እጆች ላይ ነው። በአሁኑ ጊዜ የሚታወቅ ቱሃኖች በሽታን ከሰው ወደ ሰው ያስተላለፉበት ጊዜ የለም።

እንዴት ላገኛቸው እችላለሁ?ብሩህ የሆነ ባትሪ ተጠቅማችሁ ቱሃኖችን ወይንም ሰገራቸውን መኝታ ቤት ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶች፣ መስኮቶች እና የበር ጠርዞች ላይ ፈልጉ። ወይንም የፀጉር ማድረቂያ፣ ቀጭን ቢላ ወይንም አሮጌ መጫወቻ ካርታ ተጠቅማችሁ ከመደበቂያቸው ቦታ አስወጧቸው።

Page 2: መከላከል - National Capital FreeNet

መርምሩ:

• ከአልጋ ኋላ እና አልጋ ላይ ወይንም አካባቢ የሚገኙ ስንጥቆች ውስጥ።

• የፍራሽ ስፌቶች እና እጥፋቶች ውስጥ።

• ቦክስ እስፕሪንግ ውስጥ እና በአልጋው ዙሪያ ፡፡

• ከአልጋ ጀርባ የሚገኙ ስንጥቆች።

• አልጋ አጠገብ የሚቀመጡ ጠረጴዛዎች ውስጥ እና አካባቢ።

• ሌሎች የመኝታ ቤት ቁሳቁሶች፣ መስኮት፣ የበር ዙሪያዎች፣ ፎቶግራፎች፣ በአልጋ አካባቢ የሚገኙ ቁሳቁሶች፣ የላላ የግድግዳ ወረቀት፣ ቤት ማከፋፈያዎች እና ትርምስ።

ቱሃን ሲነክስ ምን ይመስላል፣ ምንስ ይሰማል?አብዛኛውን ጊዜ በቱሃን መነከስ መጀመሪያ ላይ አያምም በኋላ ግን ትልቅ የሚያሳክክ ቁስል ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ምንም አይሰማቸውም። አብዛኛዎቹ እብጠቶች በትንሽ ቀኖች ውስጥ ያለምንም ህክምና ይጠፋሉ።

እርምጃ ውሰዱ ቤቴ ውስጥ ቱሃን ካለ ምን ማድረግ እችላለሁ? ለአከራያችሁ፣ የህንፃው አስተዳዳሪ፣ የአካባቢው የህዝብ ጤና ጥበቃ ወይንም ተባይ ቁጥጥር ባለሙያ አስታውቃችሁ ቱሃን እንዳለ እንዲያረጋግጡላችሁ ጠይቁ።

ቫኪዩም ላይ ያለውን ቱቦ በመጠቀም ቱሃኖችን፣ ገና ያላደጉ እንጭጭ ቱሃኖችን እና እንቁላሎችን አስወግዱ። ትራሳችሁ ላይ፣ አልጋችሁ፣ የአልጋው ዙሪያ በሙሉ ቫኪዩም አድርጉ። በየቀኑ ቫኪዩም እያደረጋችሁ ወዲያውኑ የቫኪዩም ክሊነሩን ከረጢት አውጥታችሁ አሽጋችሁ ማቀዝቀዣችሁ (ፍሪዘራችሁ) ውስጥ ለብዙ ቀናት አስቀምጡ። ልብሶቻችሁን፣ የአልጋ ልብሶችን፣ ብርድ ልብሶችን፣ የፍራሽ ሽፋኖችን፣ ትራሶችን እና የትራስ ልብሶችን በትኩስ ውኋ አጥባችሁ በከፍተኛ ሙቀት በትንሹ ለ30 ደቆቃዎች ማድረቂያ ውስጥ ክተቱ።

አላስፈላጊ ትርምስን ሁሉ አስወግዱ። እንጨት፣ አልጋ ራስጌ ወይንም ሌላ ቦታ ያሉ ሰባራዎች እና ስንጥቆችን በሙሉ ድፈኑ። መላጥ የጀመረ የግድግዳ ወረቀት ካለ አድሱት ወይንም ላጡት። በቱቦዎች ዙሪያ፣ በሽቦዎች ወይንም ቤታችሁ ውስጥ የሚገቡ ምንም አይነት ነገሮችን በደንብ መርምሩ (በሁለት አፓርትመንቶች መሃል ላሉ ግድግዳዎችን ትኩረት ስጡ)። መፀዳት የማይችሉ በቱሃን የተጠቁ እቃዎችን አውጥታችሁ ጣሉ። ሁሉንም ነገር በላስቲክ ከረጢት አሽጋችሁ በደንቡ እንደሚታይ አድርጋችሁ ፅፋችሁበት ጣሉት።

የተባይ መከላከያ ድርጅት ለምን እጠቀማለሁ ?ቱሃንን ለመቆጣጠር የተዋሃደ የተባይ አመራር (ኢንተግሬትድ ፔስት ማኔጅመንት አይ ፒ ኤም) ያስፈልጋል። ይህም ተገቢ ዝግጅት፣ ፍተሻ፣ ለይቶ ማወቅን እና ቤት ፅዳትን ያጠቃልላል። ይህም የተባይ መከላከያን በአግባቡ ለመጠቀም ፣ ከባቢ አየርን ለመጠበቅ እና የመድሃኒቱን ስኬታማነት ለመጨመር ይረዳል።

ቱሃኖችን ለማስወገድ አብዛኛውን ጊዜ የተባይ መከላከያን መጠቀም ያስፈልጋል። የተባይ መከላከያ ባለሙያዎች ብቻ ናቸው ለቱሃን የሚሆን ተባይ መከላከያ መርጨት የሚችሉት። ፎገርስ(በጭስ የሚያፍኑ) እና ባግ ቦምብስ ለቱሃን መከላከያነት አያገለግሉም። በኦንቴሪዮ ውስጥ ቱሃን ለመከላከል ትክክለኛ ስልጠና እና ልምድ ያላቸው በቁጥር ብዙ የሆኑ ፍቃድ ያላቸው የተባይ መቆጣጠሪያ ድርጅቶች ይገኛሉ፡ ፈቃድ ያለው ድርጅት ለማግኘት ወደሚከተሉት ድረገፆች መሄድ ይችላላችሁ:

www.spmao.ca www.pestworld.org

Amha

ric C

atalo

gue

No. 0

1630

0 Ma

rch

2011

© 2

011

Quee

n’s P

rinte

r of O

ntar

io